View
12
Download
1
Category
Preview:
Citation preview
1
ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLL
mNGST db#B nU¶T Uz@È DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTH
NATIONS, NATIONALITIES AND PEOPLES’ REGION STATE
አዋጅ ቁጥር-------/2011 ዓ.ም
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች
ክልልመንግስት ጠቅላይ ዓቃቤን ሕግ ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ
ሕገ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን
እንዲሁም የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር፤ ወጥነት
ያለው ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ፤
የሕዝብንና የመንግስትን ጥቅም በተሟላ ሁኔታ
የሚያስጠብቅ አንድ ጠንካራ ሕግ አስከባሪ የዓቃቤ
ሕግ ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሕዝብ ተአማኒነት ያለው፣ በተሟላ ተቋማዊና
ሙያዊ ነፃነት የሚያገለግል እንዲሁም ለሙያዊ፣
ተቋማዊና ሕዝባዊ ተጠያቂነት የሚገዛ፣ በግልጽነትና
በአሳታፊነት የሚሰራ የዓቃቤ ሕግ ተቋም ማቋቋም
በማስፈለጉ፤
በተለያዩ ተቋማት ተበታትኖ የሚሰራው የዓቃቢያነ ህግ
ስራ በአንድ ተቋም ስር ተደራጅቶ መሰራት እንዳለበት
PROCLAMATION No. ------/2018
A DRAFT PROCLAMATION TO PROVIDE FOR
THE ESTABLISHMENT OF THE ATTORNEY
GENERAL OF THE THE SOUTH NATIONS,
NATIONALITIESAND PEOPLES’ REGION STATE
WHEREAS, it has been found necessary to
establish one strong law enforcement public
prosecution institution which can comprehensively
protect public and government interest and deliver
uniform, effective and efficient service as well as
enforcing the constitution and constitutional
systems and the supremacy of law;
WHEREAS, it has been found necessary to re-
organize institution which enforces rule of law and
ensures that laws are properly organized and
government works are conducted in accordance
with the law;
WHEREAS, it has been believed that the public
prosecution activity to be performed at various
organizations shall be performed by organizing
under sole institution;
bdb#B B/@éC½B/@rsïC ?ZïC KL§êE
mNGST Mክር b@T ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ›mT q$_R (((((¼2011
hêú qN 2011 ›.M
Year No Hawassa /2018
2
በመታመኑ;
በ1994 ዓ ም በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕገ-መንግስት አንቀፅ
51 ንዑስ አንቀፅ 3 (ሀ) መሰረት የሚከተለው
ታውጇል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር --------/2011” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
በዚህ አዋጅ ውስጥ የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም
የሚያሰጥ ካልሆነ በስተቀር፤
1. “ክልል” ማለት “የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና
ህዝቦች ክልል ነው፤
2. “ምክር ቤት” ማለት በደቡብ
ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት በየእርከኑ የሚገኙ የህግ አዉጭ
አካል ነው፡፡
3. “መስተዳድር ምክር ቤት” ማለት በተሻሻለው
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 65 መሠረት
የተገለጸው ሆኖ የክልሉ ከፍተኛ የአስፈፃሚ
አካል ወይም ካቢኔ ነው፡፡
4. “አስተዳደር ምክር ቤት” ማለት በደቡብ
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት በየእርከኑ የሚገኙ አስፈፃሚ
መስሪያ ቤት ሀላፊዎች በአባልነት የሚገኙበት
NOW, THEREFORE, in accordance with the sub
article 3 (a) of Article 55 (1) of the 2002 revised
Constitution of the Southern Nations,Nationalities
and Peoples’ Region State, it is hereby Proclaimed
as follow;
PART ONE
GENERAL
1. Short Title
This Proclamation may be cited as the “South
Nations, Nationalities and Peoples’ Region
State Attorney General Establishment
Proclamation No. ---- ------- /2018”.
2. Definition
In this Proclamation unless the context
otherwise requires:
1. “region” means the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Region;
2. “council” means a legislative organ in
each administration of the South Nations,
Nationalities and Peoples’ Region;
3. “executive council” means a Supreme
Executive Organ or cabinet us defined
under urticle 65 of the revised
Constitution of the South Nations,
Nationalities and Peoples’Region;
4. “administration council” means an
executive organ, which heads of each
level executive organization are
members, in the Southern Nations,
3
አስፈፃሚ አካል ነዉ፡፡
5. “የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች” ማለት
ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ሙሉ በሙሉ ወይም
በከፊል በክልሉ መንግስት በጀት የሚተዳደሩ
አካላት ሆነው የክልሉ መንግስት የልማት
ድርጅቶችንም ይጨምራል፡፡
6. ““ሕግ” ማለት በፌደራል መንግስቱ ህግ
አውጪ ወጥተው በክልሉ ውስጥ ተፈጻሚነት
ያላቸው የሕግ ማእቀፎችን፣ በክልሉ ሕግ
አውጪ አካላት የወጡ አዋጆችን፣ ደንቦችን
እና ስልጣን በተሰጣቸው የክልሉ መንግስት
አካላት የወጡ መመሪያዎችን ያጠቃልላል፡፡
7. “ሕገ-መንግስት” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ
ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ እና የተሻሻለው
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
ሕገ-መንግስትን ያጠቃልላል፡፡
8. “የወንጀል ሕግ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ
ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት የተደነገገ የወንጀል ሕግ ነው፡፡
9. “ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” ማለት “የደቡብ ብሄሮች
ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ነው፤
10. “ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” ማለት “በደቡብ
ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት
በርዕሰ መስተዳድር አቅራቢነት በክልል ምክር
ቤት የተሾመ የክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ ነው፤
11. “ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” ማለት
Nationalities and Peoples’ Region;
5. “offices of the regional state” means
organs with legal personality relay
wholly or partly on the Regional State
budget to be administered, encluding the
developmental organizations of the
Regional State;
6. “law” means legal packages that are
applicable in the Region, issued by the
Federal Government’s legislative organ;
Proclamations and Regulations issued by
the Regional Legislative organ and
encludes Directives issued by the
empowered Regional State’ organs;
7. “constitution” means the Constitution of
the Federal Democratic Republic of
Ethiopia and encludes the revised
Constitution of the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Region;
8. “criminal law” means the criminal law
provided by the House of Peoples’
Representatives of the Federal
Democratic Republic of Ethiopia;
9. “Attorney General” means Attorney
General office of the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Regional
State;
10. “chief Attorney General” means a chief
head of the Regional Attorney General
office submitted by excutive council and
appointed by the South Nations,
Nationalities and Peoples’ Regional
Council;
11. “deputy Attorney General” means a
4
“በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት ርዕሰ መስተዳድር የተሾመ የክልል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ምክትል
ኃላፊ ነው፤
12. “ዓቃቤ ሕግ” ማለት በመስተዳድር ምክር ቤት
በሚወጣ ደንብ መሰረት የሚቀጠር ወይም
የሚመደብ እና የሚተዳደር የሕግ ባለሙያ
ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7 መሠረት
የተሾሙ ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉን፣ ምክትል
ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግን እና በየእርከኑ ያሉት
የዓቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችንም
ይጨምራል፤
13. “ፖሊስ” ማለት ስልጣን ያለው የክልል ወይም
የፌደራል ፖሊስ ነው፡፡
14. “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤
15. የፆታ አገላለፅ፤ በዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ
ፆታ የተገለፀው ሴትንም ይጨምራል፡፡
ክፍል ሁለት
መቋቋም፣ተጠሪነት፣ሥልጣን እና ተግባር
3. መቋቋም
“የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ከዚህ
በኋላ “ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” እየተባለ የሚጠራ
ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው የመንግስት
መስሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፡፡
4. ዋና መስሪያ ቤት
የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዋና መስሪያ ቤት በሀዋሳ
deputy head of the Regional Attorney
General office appointed by the Chief
Executive of the South Nations,
Nationalities and Peoples’ Region State;
12. “public prosecutor” means a lawyer
employed or assigned and administered
under Regulation that is issued by the
Executive Council and includes the Chief
Attorney General, the deputy Attorney
General and heads of Attorney General
office in each level which are appointed
in accordance with Article 7 of this
Proclamation;
13. “police” means federal or regional police
with legal Power;
14. “person” means a natural person or a
body with legal personality;
15. Gender expression; for the purpose of
this Proclamation, expression in the
masculine gender includes the feminine.
PART TWO
Establishment, Accountability,
Powers And Duties
3. Establishment
The South Nations, Nationalities and Peoples’
Region State Attorney General (hereafter
called the “Attorney General”) is hereby
established as an autonomous government
office, which has its own legal personality.
4. Head Office
5
ከተማ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በክልሉ በተለያዩ
ቦታዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ወይም
ምድብ ጽህፈት ቤቶች ሊኖሩት ይችላል፡፡
5. ተጠሪነት
1. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ለርዕሰ
መስተዳድሩ እና ለመስተዳድር ምክር ቤት
ይሆናል፡፡
2. በዞን እና በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ያሉ የዓቃቤ
ህግ መምሪያ እና በልዩ ወረዳ ያሉ የዓቃቤ ህግ
ፅ/ቤቶች ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ እና
በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ዋና አስተዳዳሪ
ወይም ካንቲባ እና አስተዳደር ምክር ቤት
ይሆናል፡፡
3. በወረዳ፣በከተማ አስተዳደር እና በሀዋሳ ከተማ
ክፍለ ከተማ ያሉ የዓቃቤ ህግ ፅ/ቤቶች
ተጠሪነታቸው ለዞን፣ለልዩ ወረዳ ወይም
ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ህግ መምሪያ
ሀላፊ እና በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ዋና
አስተዳዳሪ ወይም ካንቲባ ወይም ስራ አስፈፃሚ
እና አስተዳደር ምክር ቤት ይሆናል፡፡
4. በክልሉ በየትኛውም ደረጃ ለሚገኝ ዓቃቤያነ ሕግ
የበላይ ኃላፊ ጠቅላይ ዓቃቤ-ህግ ነው፡፡
5. በዚሁ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 4 የተጠቀሰው
እንደተጠበቀ ሆኖ በየትኛውም ደረጃ ያለ ዓቃቤ
ህግ ለበላይ ኃላፊያቸውና ለተመደቡበት የስራ
ዘርፍ ኃላፊዎቻቸው ተጠሪ ይሆናሉ፡፡
6. ሥልጣንና ተግባራት
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሚከተሉት ሥልጣንና
The head office of the Regional Attorney
General shall be in Hawassa and may have
branch or allocate offices in different area of
the region, as may be necessary.
5. Accountability
1. The Regional Attorney General shall be
accountable to the Chief Executive and
Executive Council;
2. The departments of public prosecutors in
zone and Hawassa City administration and
public prosecutor offices in especial woreda
shall be accountable to the Regional
Attorney General and to the chief
administrater or Mayor found at each
administration level;
3. The public prosecutor offices in woreda and
sub city of Hawasssa city shall be
accountable to the public prosecutor
departments of Zone, especial woreda or
Hawassa city administration and to the chief
administrater or Mayor or Executive found
at each administration level and
administration council;
4. Chief Attorney General shall be a head of
public prosecutors found at every level in
the Region;
5. Subject to Sub Article 4 of this Article,
public prosecutor at every level shall be
accountable to their principal heads and to
the division heads they are assigned;
6. Power and duties
6
ተግባራት ይኖሩታል፤
1. በሕግ ጉዳዮች የክልል መንግስት ዋና አማካሪ
እና ተወካይ ሆኖ ይሰራል፤
2. በፌደራል መንግስት ተዘጋጅቶ የጸደቀውን
የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ በክልሉ ውስጥ
ተግባራዊ እንዲሆን ያስተባብራል፣
ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
3. የወንጀል ፍትሕ መረጃዎችን መሰብሰብ፣
ማደራጀት፣ መተንተንና ማሰራጨት
የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስፈፅማል፡፡
4. በፌዴራልና በክልሉ ሕገ-መንግስታት እና
በሌሎች ሕጎች የተደነገጉ የግልና የቡድን
መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች
መከበራቸውን ያረጋግጣል፣
5. የወንጀል ጉዳይን በተመለከተ፤
ሀ) በክልሉ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር በሚወድቁ
በማናቸዉም የፀረ-ሙስና እና የታክስ ህጎችን
በመጣስ በሚፈፀሙ የወንጀል ጉዳዮች
እንዲሁም ከባድና ውስብስብ በሆኑ ሌሎች
የወንጀል ድርጊቶች የወንጀል ምርመራ
ከፖሊስ ጋር አብሮ ያጣራል፣ምርመራውን
በበላይነት ይመራል፡፡
ለ) በሕዝብ ጥቅም መነሻ ወይም በወንጀል
የማያስጠይቅ ሁኔታ መኖሩ በግልፅ ሲታወቅ
የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ ወይም
የተቋረጠው የወንጀል ምርመራ እንዲቀጥል
ያደርጋል፤ ማናቸውም የወንጀል
ምርመራዎች በሕግ መሰረት መከናወናቸውን
ያረጋግጣል፤ አስፈላጊውን ህጋዊ ትእዛዝ
ለሚመለከተዉ አካል ይሰጣል፤
The Regional Attorney General shall have the
following power and duties:
1. works as principal advisor and
representative of the Regional government
regarding law;
2. coordinates, follows up and ensures the
implementation of the criminal justice
policy, prepared and ratified by Federal
government, in the Region;
3. Develop the system enables to collect,
organize, analyze and distribute the
informations of criminal justice; execute the
same;
4. Ensure if basic right and liberties of the
individual and group stated in federal and
Regional Conistitutions and in other
laws,are respected;
5. regarding criminal matters:
a) Investigates tough and complex criminal
cases as well as every criminal cases
committed by violating the anti-
corruption and tax laws, with police,
which are falling under the jurisdiction
of Regional courts,direct investigation
principally.
b) Effects the discontinuation or restart of
discontinued investigation on the basis of
public interest or when it is clearly
known that there could be no criminal
liability, ensures that investigation is
conducted in accordance with the law,
gives the necessary instruction to the
7
ሐ) ምርመራቸው በፖሊስ በተጀመረባቸው
መካከለኛ፣ ቀላል እና በግል አቤቱታ
በሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ
በአግባቡ ስለመከናወኑ በቅርበት ክትትል
ያደርጋል፤ በተጀመረ የወንጀል ምርመራ
አስመልክቶ ፖሊስ ለዓቃቤ ህግ ማሳወቁን
ያረጋግጣል፤
መ) በወንጀል መዝገብ ላይ የተሰጠ የዓቃቤ
ሕግና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን
ለሚመለከተው ፖሊስ ያሳውቃል፣ የወንጀል
ምርመራ መዝገቦችን አስመልክቶ በየደረጃው
ባሉ ዓቃቤያነ ሕግ በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ
በፖሊስ የሚቀርቡ አቤቱታ ተቀብሎ ውሳኔ
ይሰጣል፤
ሠ) የተጠናቀቁ የምርመራ መዝገቦችን ከሕግና
ከማስረጃ አንፃር መርምሮ በሥነ-ሥርዓት
ሕግ መሰረት የተቀመጡ መመዘኛዎች
ሲሟሉ የ’አያስከስስም’ ወይም የ’ተዘግቷል’
ውሳኔ ይሰጣል፤
ረ) የጥፋተኝነት ድርድር ይወስናል፣ ድርድር
ያደርጋል፣ አማራጭ የመፍትሄ እርምጃ
እንዲወሰድ ይወስናል፣ ተግባራዊነቱን
ይከታተላል፤
ሰ) መንግስትን በመወከል የወንጀል ጉዳዩች ክስ
ይመሰረታል፣ ይከራከራል፣ ለህዝብ ጥቅም
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ክስ ያነሳል፣
የተነሳ ክስ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡
ሸ) የወንጀል ድርጊት ጠቋሚዎችና ምስክሮች
በህግ መሰረት ጥበቃና ከለላ እንዲያገኙ
concern body;
c) effects immediate follow up if a
criminal investigation of medium, simple
and perivatly presented petition issues
which has been started by the police are
conducted appropriately; ensures if the
police notify regarding criminal
investigation to the public prosecutor.
[
d) informs the relevant police about
decisions given on criminal case files by
the public prosecutor and court; receives
and gives decision on appeals presented
by the police against decisions given at
different level of the public prosecution;
e) provides appropriate legal decision on
completed investigation files based on
evidence and law in accordance with
procedure law;
f) determines guilty plea, conducts plea
bargaining, decides alternative actions to
be taken, follows the implementation;
g) institutes criminal case charges by
representing the federal government,
litigates, withdraws charge when found
necessary in the interest of the public,
resumes withdrew charge.
8
ያደርጋል፡፡
ቀ) በማረፊያ ቤትና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር
ሥር ያሉ ተጠሪጣሪዎችንና ታራሚዎችን
ይጎበኛል፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ
መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፣ ሕገ ወጥ
ተግባር ተፈፅሞ እንደሆነ እንዲታረም
ያደርጋል፡፡ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች
ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ ይወስዳል ወይም
እንዲወሰድ ያደርጋል፤
በ) በዕርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶች
በእርቅ የሚጠናቀቁበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
ተ) ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጡዋቸው
ውሳኔዎችና ትእዛዞች መፈፀማቸውንና
መከበራቸውን ይከታተላል፣ ሳይፈፀሙ ከቀሩ
ወይም አፈፃፀማማቸው ሕግን ያልተከተለ
ከሆነ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት
በማመልከት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ
ያደርጋል፤
ቸ) በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የወንጀል ቅጣቶች
በአግባቡ እንዲፈፀሙ ለማድረግ የሚያስችሉ
ሥርዓቶችን ያደራጃል ወይም መደራጀታቸውን
ያረጋግጣል፤
ኀ) የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ
በኩል እንዲቀርብ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን
ይከታተላል፡፡
6. የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በተመለከተ፤
h) Enacts the criminal act informant and
evidences to have protection and secure
under law;
i) pays visit to suspected and inmates under
custody at police stations and prisons,
ensure their handling and reside is
carried out in accordance with the law,
cause unlawful act to be corrected; take
measures or cause measures to be taken
based on the law against people who are
found to have transgressed the law;
j) facilitates the condition in which
criminal acts that are completed with
settlement to be considered with
settlement;
k) follows the implementation and
enforcement of judgments and orders
given by courts under criminal case,
applies to the court that gave judgments
and orders and makes corrective action
to be taken where they have not been
implemented or their implementation is
contrary to law;
l) organizes or ensures the establishment of
systems for the proper execution of
criminal punishments imposed by the
court of law;
m) causes death penalty decisions to be
submitted to the President of the
Federal Democratic Republic of
Ethiopia through Federal Attorney
General; follow up the execution.
9
ሀ) በክልል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የሕዝብ
እና የክልል መንግስት መብትና ጥቅም ወኪል
ሆኖ ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ እንዲከበሩ
ያደርጋል፣ የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፤
ለ) ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶችን የውል
ዝግጅት እና ድርድር ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር በመሆን ያደርጋል፣ የሕዝብና የክልል
መንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ይጎዳል ብሎ
ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች ውል እና የመግባቢያ
ሰነዶች ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል ወይም
የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤
ሐ) የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶችን በመወከል
የፍትሐብሔር ክስ ይመሰርታል፤ በከሰሱበት
ወይም በተከሰሱበት የፍትሐብሔር ጉዳዮች
ላይ ክርክር ያደርጋል፤ በተጀመረ ክርክር
ተቋማትን ተክቶ በተናጠል ወይም በጋራ
ይከራከራል፣ ወይም በክርክር አመራር ላይ
ለመሥሪያ ቤቶች አቅጣጫ ይሰጣል፣ በሕግ
መሠረት ለተሰጡ ዉሳኔዎች ፍርድን
ያስፈፅማል፤
መ) በክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና በግል
ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች መካከል የሚከሰቱ
የፍትሐብሔር ክርክሮች በድርድር እንዲያልቁ
ጥረት ያደርጋል፤ድርድሩ ካልተሳካ ጉዳዩን
ስልጣኑ ለሚፈቅድለት ፍርድ ቤት አቅርቦ
ይከራከራል፣
ሠ) የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ
በርሳቸው ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር
6. regarding civil matters:
a) litigates, enforces, causes enforcement,
follows and controls the process of
enforcement within the regional
government offices by acting as an agent
of rights and interest of the public and
regional government;
b) advises and participates with concerned
bodies in contract preparation and
negotiation of large government projects;
participates or advises concerned bodies
in other contract and consensuse
document preparation and negotiation
when it believes that public and
government interest could be affected;
c) institute civil suits on behalf of the federal
government office; represent them in civil
litigation where they sue or sued,
represent them in an ongoing civil
litigation by its own or together with
them; gives direction to government
offices on the management of the
litigation; cause execution of judgment on
decision imposed in accordance with law;
d) cause effort on the civil despute arising
among the regional government offices
and non-governmental organizations or
individuals to be completed in
negotiation; litigates presenting the issue
10
ጉዳዩች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት
ውጭ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ
እንዲወሰን ውሳኔ ሀሳብ ይሰጣል፤ በውሳኔው
መሰረት መፈፀሙን ያረጋግጣል፤
ረ) የተመዘበረ የመንግስት ገንዘብ ስልጣን ባለዉ
ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ያስመልሳል፡፡
የሙስና ወንጀል ዉጤት የሆኑት እና በፍርድ
ሂደት ላይ ያሉ ንብረቶችን ያስተዳድራል፤
እንዲወረስ ዉሳኔ የተሰጠባቸዉን ንብረቶች
ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል
ያስተላልፋል፡፡
ሰ) የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም
የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣
ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን
ወክሎ ይከራከራል፤
ሸ) የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ
ተበዳዩች እንዲካሱ መልሰው እንዲቋቋሙ
እንዲሁም ከጉዳቱ የተያያዙ የፍትሐብሔር
ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እነሱን በመወከል
የፍትሐብሔር ክስ ያቀርባል ወይም
ይደራደራል፤
7. የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅ እና ማስረፅ ሥራን
በተመለከተ፤
ሀ). በክልል መንግሥት የሚወጡ ሕጎች የሕግ
ረቂቅ ዝግጅት ስራ ይሰራል፤ የመንግስት
አካላት የሚያዘጋጁት ረቂቅ ህግ ከፌዴራልና
ከክልሉ ሕገ መንግስትና ከሌሎች ሕጎች ጋር
የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፣
to the court eligible if the negotiation fails
e) give decision for settlement of disputes
arising between regional government
offices through judicial means or out of
court alternative dispute settlement
mechanisms, and ensures the execution
of the decision;
f) administers properties that are on the
process of the court verdict and result
from corruption; pass the properties
which are decided to be successes to the
concerned government body; causes the
corrupted government money to be
returned by presenting charge to the court
havig power;
g) conducts litigation by representing
citizens who do not have financial
capacity to institute civil action; specially
women, children, disabled and the elderly;
h) represent victims of crime who do not
have financial means in litigations or
negotiations for their compensation,
reinstitution and protection of their civil
interests emanated from the damage
sustained;
7. regarding legal study, drafting and
decimination activity;
a) perform preparation of draft laws to be
promulgated by the regional
11
ለሚመለከታቸው ክፍሎችም አስተያየት
ያቀርባል፤
ለ) በክልሉ በስራ ላይ ባሉ ህጎች ጥናት በማድረግ
ሕጎች እንዲሻሻሉ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣
ሲደገፍም ለተባሉት ማሻሻያዎች ረቂቆችን
በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት
ያቀርባል፣
ሐ) ሕጐችን የማሰባሰብ፣የማጠቃለልና የኮዲፊኬሽን
ሥራ ይሰራል፤ የክልሉን ህጎች በባለአደራነት
ይይዛል፣ ያሰራጫል፤
መ) ዓቃቤያነ ሕግ ስለ ስራቸው ያላቸውን
አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት በተከታታይ
እና በየደረጃው ለማሳደግ ትምህርት እና
ሥልጠና ይሰጣል፤እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤
ሠ) የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ለማዳበር ለክልሉ
ህብረተሰብ በተለያዩ ዜደዎች የንቃተ ህግ
ትምህርት ይሰጣል፤
8. የጠበቆች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ሲቪክ
ማህበራት እና የሰነድ ማረጋገጥን በተመለከተ፤
ሀ. በክልሉ ፍርድ ቤቶች ለሚከራከሩ ጠበቆች
ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ስራቸውን
ይቆጣጠራል፣ የጠበቆችን ዲሲፕሊን
ጉዳዮች አይቶ ይወስናል፤ በህግ መሰረት
ይሰርዛል፣
ለ) በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያውያን የበጎ
አድራጎት ድርጅቶችንና ማህበራትን
ይመዘግባል፣ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ
ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ስራቸውን
government; ensure that draft laws
prepared by government organs are
consistent with the federal and regional
Constitutions and others laws; provide
legal opinion to concerned bodies;
b) conducts legal studies on the functional
laws in the region and present decision
idea to be reformed; submits to the
concerned bodies by preparing draft for
raised amendement when supported;
c) carry out codification, compilation and
consolidation of laws; hold and dispense
regional laws as atitle holder;
d) provide training or cause provision of
training and education at every level for
continuous development of the attitude,
knowledge and skill of public
prosecutors;
e) Provide legal awareness education in
different methods to the regional society
for the development of their legal
awareness.
8. regarding advocates, charity organizations,
civic societies and ;document certification;
a) supervise advocates practicing at
regional courts and services provided by
them; license, renew, revoke the license
in accordance with the law; determines
by overtaking disciplinary issues of
advocates;
b) recored the Ethiopian charity
12
ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፣ በሕግ መሰረት
ይሰርዛል፣
ሐ) አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ሰነዶችን
ይመዘግባል፣ ያረጋግጣል፣ ይሽራል፣
ይሰርዛል፣
መ) ነፃ የሕግ ድጋፍ አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን
ይቀርፃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ በመስኩ
የሚሰማሩ አካላትን ያስተባብራል፤
9. ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀግብር
መነሻ በማድረግ ክልላዊ ሰብአዊ መብት የድርጊት
መርሀ ግብርን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በመሆን ያዘጋጃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
በክልል ደረጃ የሚመለከታቸውን አካላት
ያስተባብራል፣ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት
ያቀርባል፤
10. የዓቃቤ ሕግ የውሳኔ አሰጣጥ እና የፍቅደ ሥልጣን
አጠቃቀም ወጥነትን ለማረጋገጥ በጠቅላይ ዓቃቤ
ሕግ የፀደቀ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን
ያረጋግጣል፤
11. በዓቃቤያነ ሕግ የሚሰጡ ውሳኔዎች በሕግ
መሰረት መከናወናቸውን የሚያረጋግጥ
የኢንስፔክሽን ክፍል ያደራጃል፣ ጉድለቶችን በጥናት
አስደግፎ ይለያል፤ በግኝቱ መሠረትም እንዲታረሙ
ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ ይወስዳል
ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፣ መልካም
ተሞክሮዎችን ይቀምራል፤ ያስፋፋል፤
12. የክልሉን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
organizations and companies working in
the Region; issue legal personality
assurance certificate; supervise their
work; ensure; revoke by law;
c) record, ensure, repeal, and revoke
document under pertinent law;
d) design strategy for provision of free legal
aid, follow up implementation of same,
coordinate bodies engaged in the sector;
9. prepare regional human right action plan
together with the concerned bodies based
on national human rights action plan,
follow up implementation of same,
coordinate the concerned bodies at national
level; submit report to the relevant bodies;
[
10. ensure that the directive issued by the
Attorney General with the view to ensure
consistent application of discretion and
provision of decision of the public
persecutors is enforced;
11. organize inspection department and
investigate that decisions passed by public
prosecutors are in accordance with the law,
identify defects based on studies and take
corrective measures on the bases of findings
to rectify the problems; when necessary, take
measure or cause measures to be taken;
compute, scale up good practices;
13
ያስተባብራል፤የህግ ታራሚዎች ይቅርታ
የሚያገኙበትን ስርዓት ይዘረጋል፡፡
13. የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር
በሚወስነው አዋጅ የመስተዳድር ምክር ቤት አባል
ለሆኑ አስፈፃሚ አካል መስሪያ ቤቶች የተሠጡ
የወል ሥልጣንና ተግባርን ሥራ ላይ ያውላል፤
14. የንብረት ባለቤትና የይዞታ ባለመብት ይሆናል፣
ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
15. በሕግ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ወይም
ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን
ያከናውናል፡፡
7. ሹመት
1. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ በርዕሰ መስተዳድሩ
አቅራቢነት በክልል ምክር ቤት ይሾማል፡፡
2. ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በክልሉ ርዕሰ
መስተዳድር ይሾማል፡፡
3. በዞን፣በልዩ ወረዳ እና በሀዋሳ ከተማ
አስተዳደር ያሉ የዓቃቤ ህግ መምሪያ ኃላፊዎች
በየአስተደደር እርከኑ ዋና አስተዳዳሪ/ካንቲባ
አቅራቢነት በየእርከኑ ባሉ ምክር ቤቶች
ይሾማሉ፡፡
4. በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደር እና በክፍለ ከተማ
በየእርከኑ ያሉ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በየአስተደደር
እርከኑ ዋና አስተዳዳሪ/ካንቲባ/ ወይም ስራ
አስፈፃሚ አቅራቢነት በየእርከኑ ባሉ ምክር
ቤቶች ይሾማሉ፡፡
12. lead, follow up, coordinate principally the
activities of Regional prisonss administration
commission, develop the system in which
legal inmates acquire pardon;
13. exercise the common powers and duties
provided for, the offices of executive organ
and member of the Executive Council, under
the Definition of Powers and Duties of the
Executive Organs of the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Regional State
Proclamation;
14. own and possess property, enter into
contracts, sue or be sued in its own name;
15. perform other activities that help to achieve its
objectives or carry out its power and duties
given by law.
7. Position
1. A chief Attorney General shall be appointed
by Council of the region up on the
recommendation of the Executive Council.
2. A Deputy Attorney General shall be
appointed by the Executive Council.
3. The heads of public prosecutor offices in
Zone, especial woreda and Hawassa City
administration shall be appointed at Council
of their level by approval of their
administrative level administrater/mayor.
4. The heads of public prosecutor offices in
woreda, urban center administration and sub
city levels shall be appointed at council of
their level by approval of their administrative
14
5. በየትኛውም ደረጃ የሚሾም የዓቃቤ ህግ
መስሪያ ቤት ሀላፊ በህግ ትምህርት እውቅና
ካለው ተቋም የተመረቀ መሆን አለበት፡፡
8. የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቋም
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣
1. አንድ ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና ምክትል
ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግ፤
2. የሥራ ዘርፎች፤
3. የማኔጅመንት ኮሚቴ፤
4. የክልል ዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ፤
5. በዓቃቤ ሕግ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት
የተቀጠሩ/የተመደቡ ዓቃቢያነ ሕግ፤ እና አስፈላጊ
ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡
9. የዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥልጣንና ተግባር
1. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የጠቅላይ ዓቃቤ
ሕግ የበላይ ኃላፊና የካቢኔ አባል በመሆን
በሙያውና በሕግ መሠረት ጠቅላይ ዓቃቤ
ሕግን ይመራል፣ ያስተዳድራል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፤
ሀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 የተመለከቱትን
ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ
ያውላል፤
ለ) በክልል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና
ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ 142/2004፣
እንዲሁም በተሻሻለው የገቢዎች
level administrater/mayor or executive.
5. The head of public prosecutor to be
appointed at every level shall be a graduate in
legal education from recognized institution.
8. Organization of the Attorney General
The Attorney General shall have:
1. a chief Attorney General and Deputy
Attorney Generals;
2. line divisions;
3. Management Committee;
4. Regional Public Prosecutors
Administration head Council;
5. Public prosecutors employed/assigned in
accordance with the public prosecutor
administrative Regulation; and necessary
staffs.
9. Powers and Duties of the ChiefAttorney
General
1. The Chief Attorney General shall be the
head of the Attorney General and a
member of cabinet; and lead and
administer the Attorney General
professionally and in accordance with the
law.
2. Without prejudice to sub-article of this
Article, the Chief Attorney General shall
have the powers and duties to:
a) exercise the powers and duties
stipulated under Article 6 of this
Proclamation;
b) exercise the prosecution powers and
duties given to the organizations in the
15
ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
143/2004 ለተቋማት ተሰጥተው የነበሩ
የዓቃቤ ህግነትን የተመለከቱ ሥልጣንና
ተግባራትን ሥራ ላይ ያውላል፤
ሐ) በምክትል ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግ
እንዲሁም በየእርከኑ ባሉ የዓቃቤ ህግ
መስሪያ ቤት ኃላፊዎች የዓቃቤ ህግ ስራ
አስመልክቶ የተሰጡ ውሳኔዎችን
ያፀድቃል፣ያሻሽላል፣ይለውጣል፣ይሽራል
ወይም ጉዳዩ እንዲጣራ ወይም እንደገና
እንዲታይ ያደርጋል፤
መ) ዓቃቢያነ ህግን በኣቃቢያነ ህግ መተዳደሪያ
ደንብ መሰረት እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ
ሠራተኞችን በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ
ህጎች መሰረት ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፣
በህግ መሰረት ያሰናብታል፤
ሠ) የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን ስትራቴጂክ
ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም በስራ
ላይ ያውላል፤
ረ) ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተፈቀደለት በጀት
እና የሥራ ፕሮግራም መሰረት ገንዘብ
ወጪ ያደርጋል፤
ሰ) ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደርጉት
ግንኙነቶች ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን
ይወክላል፤
ሸ) የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን የሥራ አፈጻጸም
እና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ
ለመንግስት ያቀርባል፤
ቀ) ለሥራ ቅልጥፍናና ውጤታማነት
Regional Ethics and Anti- corruption
Commission under its establishment
Proclamation No 142/2012 and in the
revised Revenues Authority under its
establishment Proclamation No.
143/2012;
c) revoke, change, modify, suspend,
approve the decision given by deputy
Attorney Generals and heads of public
prosecutors office concerning public
prosecutor activity, or refer the case
for re-examination or revision by the
one that has given the decision;
d) hire, administer public prosecutors in
the by laws of public prosecutors and
the supporting staff of the Attorney
General in accordance with the
Regional civil service laws; and
dismiss in accordance with law;
e) prepare strategic plan and budget of
the Attorney General, and implements
same upon approval;
f) effect payment in accordance with the
budget approved and work program of
the Attorney General;
g) represent the Attorney General in
its dealings with third parties;
h) prepare and submit the performance
and financial report of the Attorney
General to the Government;
i) delegate part of his powers and
16
በሚያስፈልግ መጠን ከሥልጣንና
ተግባሩ በከፊል ለምክትል ዋና ጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ፣ ዓቃቤያነ ሕግና ሠራተኞች
በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡
በ) በሕግ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት
ያከናውናል፡፡
10. የምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥልጣንና ተግባር
ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ለዋና
ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ሆኖ፣
1. ለዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የተሰጡትን
ሥልጣንና ተግባራት በማቀድ፣ በማደራጀት፣
በመምራትና በማስተባበር ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ
ሕጉን ያግዛል፤
2. የሚመደብባቸውን ዘርፎች ይመራል፣
ያስተዳድራል፤
3. በዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ተለይተው
የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
4. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ በማይኖርበት ጊዜ
ውክልና ያልተሰጠ እንደሆነ በሹመት
ቅድሚያ ያለው ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
የዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግነት ሥራን ተክቶ
ይሰራል፤
11. ከሹመት ስለመነሳት
1. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ እና ምክትል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንደዚሁም በየእርከኑ
የሚገኙ የዐቃቤ ሕግ ሀላፊዎች
ከሹመታቸዉ ሊነሱ ይችላሉ፡፡
duties to deputy chief attorney
general, public prosecutors and
employees to the extent necessary
for effective and efficient
performance of the activities of the
Attorney General;
j) perform other activities given to him
by law.
10. Power and Duties of the Deputy Attorney
Generals
Deputy attorney general shall be accountable
to a chief attorney general, and;
1/ shall assist the Chief Attorney General
in planning, organizing, leading and
coordinating powers and duties given
to a chief Attorney General;
2/ shall lead and administer the line
divisions to which he is assigned;
3/ shall perform specific duties given to
them by the Chief Attorney General;
4/ in the absence of the Chief Attorney
General, without giving delegation, the
senior Deputy Attorney General shall
represent and perform the duties of the
Chtef Attorney General;
11. Removal from position
1. The Chief Attorney General and the
Deputy Attorney General as well as the
public prosecutors at various levels may
be removed from their position.
17
12. የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር
የዓቃቤያነ ሕግ አስተደደር በመስተዳድር ምክር
ቤት በሚወጣ የዓቃቢያነ ህግ መተዳደሪያ ደንብ
ይወሰናል፡፡
13. የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ
1. የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ በዚህ
አዋጅ ተቋቁሟል፤ የጉባኤው ሰብሳቢ ዋና
ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ይሆናል፡፡ የጉባኤውን
አባላት፣ የአሠራር ሥነ-ሥርዓትና ሌሎች
ዝርዝር ጉዳዮች የመስተዳድር ምክር ቤት
በሚያወጣው የዓቃቢያነ ህግ አስተዳደር ደንብ
ይወሰናል፡፡
2. የራሱ ጽህፈት ቤት፣ለስራዉ የሚያስፈልጉ
ዓቃቢያነ ህግ እና በዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ
የሚሰየም የጽህፈት ቤት ኃላፊ ይኖረዋል፡፡
ክፍል ሶስት
ሙያዊ ነፃነትና ተጠያቂነት
14. የዓቃቤያነ ሕግ የሙያ ነፃነት
ዓቃቤ ሕግ ሥልጣኑንና ተግባሩን ሲያከናውን
ከማንኛውም ሰው ወይም አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ
ሆኖ በሕግ መሠረት ብቻ ይፈፅማል፡፡
15. . ተጠያቂነት
በየትኛውም ደረጃ ያለ ዓቃቤ ሕግ በሥራ
አፈፃፀማቸውና በሥነ-ምግባራቸው ለሚታየው
ጉድለት የዲስፕሊን ተጠያቂነቱ በመስተዳድር ምክር
ቤት በሚወጣው የዓቃቢያነ ህግ መተዳደሪያ ደንብ
` 12. Administration of Public Prosecutors
The administration of public prosecutors
shall be determined by by-laws of public
prosecutors which is issued by the Executive
Council.
13. public prosecutors’ administration head
council
1. The Public Prosecutors Administration head
Council is hereby established with this
Proclamation; the chair person of the council
shall be a chief Attorney General. The
members, working procedures and the details
of which shall be determined by public
prosecutors administration regulation to be
issued by the Executive Council.
2. The assembly shall have its own office,
public prosecutors necessary for work, and
head of the office who is assigned by a Chief
Attorney General.
PART THREE
Proffetional Independence And
Accountablity
14. Public Prosecutors’ Professional
Independence
The Attorney General shall discharge its
powers and duties based on law independently
free from any person or body’s interference.
15. Accountability
Public prosecutors in every level shall be
accountable, in accordance with the public
prosecutors’ working Regulation issued by
Executive Council, for defects in their work
18
መሰረት ይሆናል፡፡
16. አቤቱታ የማቅረብ መብት
1. ዓቃቤ ሕግ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ
ያለው ማንኛውም ሰው በየደረጃው ለሚገኙ
የዓቃቤ ሕግ ኃላፊዎች አቤቱታ የማቅረብ
መብት ይኖረዋል፤ አቤቱታ የቀረበለት ኃላፊ
ጉዳዩን በአፋጣኝ አጣርቶ ውሳኔ መስጠት
አለበት፡፡
2. አቤቱታ የቀረበለት ኃላፊ ጉዳዩን ለማጣራት
አግባብ ያላቸውን ባለሙያዎች የሚያካትት
ኮሚቴ ሊያቋቁም ይችላል፡፡
3. አቤቱታውን የመረመረው ኃላፊ የሕግና
የማስረጃ ምክንያቱን በመጥቀስ በበታች ዓቃቤ
ሕግ የተሰጠውን ውሳኔ ለማጽደቅ፣
ለማሻሻል፣ለመለወጥ፣ለመሻር፣ለማገድ ወይም
ጉዳዩን አስቀድሞ አይቶ ወደ ወሰነው ክፍል
ለመመለስ ይችላል፡፡
4. ከላይ በአንቀፅ 3 መሰረት በተሰጠዉ ዉሳኔ
ቅሬታ ያለዉ አካል ቅሬታዉን ደረጃዉን
ጠብቆ እስከ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ድረስ
በየእርከኑ ላሉት የበላይ ሀላፊዎች ማቅረብ
ይችላል፡፡ሆኖም የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ዉሳኔ
የመጨረሻ ይሆናል፡፡
17. ጥቆማ ወይም አስተያየት የማቅረብ መብት
1. ማንኛውም ሰው በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
ሥልጣንና ተግባር ውስጥ የሚወድቅ
ማንኛውም መታረምና መስተካከል አለበት
የሚለውን ጉዳይ ወይም ተፈጽሟል የሚለውን
የሥነ-ምግባርና የሕግ ጥሰት በማናቸውም
መንገድ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲሁም
performance and ethics.
16. Right to Lodge Complaint
1. Any person who has grievance against the
decision of public prosecutor has the right
to lodge complaint to the public
prosecutor’s heads at different levels. A
head received complaint shall urgently
investigate and give decision.
2. A head received complaint may form a
committee containing relevant professionals
to investigate the case.
3. A superior considering the complaint may
suspend, change, modify, revoke or approve
the decision of the subordinate public
prosecutor or return the case to the section
that saw the case previously by stating his
legal and factual reasons.
4. A body that has an appeal on decision set in
accordance with Article three may submit
its appeal to the heads of Attorney General
at each level; whereas the decision by
Attorney General shall be the end,
17. Right to Inform or Present Suggestion
1. Any person may inform or present
suggestion to the Attorney General or to
the public prosecutor’s heads at different
levels in any way on any matter which
falls under the power and duty of the
Attorney General which he believes
19
በየአስተዳደር እርከኑ ላሉት የዓቃቤ ህግ
መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ጥቆማ ወይም
አስተያየት ለማቅረብ ይችላል፡፡
2. በዚህ አንቀፅ በንዑስ ቁጥር አንድ መሰረት
ጥቆማ ወይም አስተያየት የሚቀበሉ አካላት
ጥቆማ፣ አስተያየትና ቅሬታዎችን
የሚቀበሉበትን፣ የሚያጣራበትና የመፍትሄ
እርምጃ የሚወሰድበት እና ለሕብረተሰቡ
የሚገለጽበትን የአሠራር ሥርዓቶች ይዘረጋል፡፡
ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
18. መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ
1. በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት አስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር
ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 161/2008
እና በሌሎች ሕጎች ለፍትሕ ቢሮ ተሰጥተው
የነበሩ ሥልጣንና ተግባራት በዚህ አዋጅ
መሠረት ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተላልፈዋል፡፡
2. በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና
ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 142/2004
እና በሌሎች ሕጎች ለክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-
ሙስና ኮሚሽኑ ተሰጥቶ የነበረ የዓቃቤ
ሕግነት ሥልጣን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
ተላልፏል፡፡
3. በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ
ቁጥር 143/2004 እና በሌሎች ሕጎች ለባለስልጣኑ
ተሰጥቶ የነበረው የዓቃቤ ሕግነት ሥልጣን ለጠቅላ
ይጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተላልፏል፡፡
should be corrected and rectified or his
claim of ethical and legal violation which
has been committed.
2. In accordance with sub article 1 of this
Article, bodies that collect inform and
suggestion shall lay down working system
whereby suggestion and complaints are
received, investigated and corrective
measures are taken and notified to the
public.
PART FOUR
Miscelaneous Provisions
18. Transfer of Rights and Duties
1. The powers and duties given to the Bureau of
Justice under the Definition of Powers and
Duties of the Executive Organs of the
Southern Nations, Nationalities and
Peoples’Regional State Proclamation No.
161/2016 and other laws are hereby
transferred to Attorney General pursuant to
this Proclamation.
2. The public prosecution power given to the
Southern Nations, Nationalities and Peoples’
Regional State Ethical and Anti-corruption
Commission under its establishment
Proclamation No142/2012 and other laws are
hereby transferred to Attorney General.
3. The public prosecution power given to the
Southern Nations, Nationalities and Peoples’
Regional State Revenues Authority under its
establishment Proclamation No. 143/2012 and
other laws are hereby transferred to Attorney
General.
20
4. የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር
እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
161/2008 አንቀፅ 30 ንዑስ አንቀፅ 13 እና
በማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ማቋቋሚያ
ደንብ ቁጥር 137/2008 አንቀፅ 6 ንፁስ አንቀጽ 1
መሰረት የክልሉን ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
አስመልክቶ ለጸጥታና አስተዳደር ቢሮ የተሰጠዉ
ስልጣን በዚህ አዋጅ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ
ተላልፉል፡፡
5. በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር
813/2ዐዐ6 እንዲሁም በሌሎችሕጎች ለንግድ
ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ተሰጥቶ
የነበረው የዓቃቤ ሕግነት ሥልጣን ለክልል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተላልፏ፡፡
6. በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ
ቁጥር 813/2ዐዐ6 እንዲሁም በሌሎች ሕጎች
ለንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን
ተሰጥቶ የነበረው የወንጀል ምርመራ የማድረግ
ሥልጣን ለክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተላልፏል፡፡
7. የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
የፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማዕክል
ተጠሪነት በዚህ አዋጅ ለጠቅላይ ዓቃቤ-ህግ
ተላልፏል፡፡
19. የመተባበር እና የመፈጸም ግዴታ
1. የክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ዓቃቤያነ ሕግ በሕግ
የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር ለመወጣት
4. The power given to the security and
administration bureau, regarding the regional
prisons commission, according to Article 30,
sub Article 13 of the Proclamation
No.161/2016 which is issued to redetermine
the Powers and duties of the executive organs
of the Southern Nations, Nationalities and
Peoples’ Region State and the prisons
administration commission of the region is
accountable to the security and administration
bureau of the region in Article 6, sub Article 1
of Regulation No.137/2016 , is transferred to
Attorney General hereby this Proclamation.
5. The prosecution power given to the Trade
competition and consumers protection
Authority under the proclamation. No
813/2013 and other laws are hereby
transterred to the region state Attorney
General.
6. The crime investigation power to the Trade
competition and consumers’ protection
Authority under proclamation No.813/2013
and other laws are hereby transferred to the
region police commission.
7. The accountability of the Suthern Nations,
Nationalities and Peoples’ Reogion Justs
Organs profesionals traiming center
transferred to Attorney General hereby this
Proclamation.
19. Duty to Cooperate
1. Any person who is requested to cooperate
with the Regional Attorney General and
public prosecutors in the execution of their
21
ትብብር የተጠየቀ ማንኛውም ሰው ከአቅም በላይ
ያልሆነ እና ጉዳት የማያስከትልበት ከሆነ
የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
2. ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በሥራ ላይ የነበሩ
የክልል ፍትህ ቢሮ እና የስር መዋቅር አመራር እና
ሠራተኞች፣የገቢዎች ባለሥልጣን አመራር እና
ሰራተኞች በዚህ አዋጅ መሠረት የሚደረገውን
ሽግግር የመተባበርና የመደገፍ ግዴታ አለባቸው፡፡
3. ማንኛውም የፖሊስ አባል የዓቃቤ ሕግን የመጨረሻ
እና ሕጋዊ ውሳኔ የማክበር እና የመፈጸም ግዴታ
አለበት፡፡
20. የወንጀል ተጠያቂነት
1. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና ዓቃቤያነ ሕግ
ሥራቸውን በነፃነት እንዳያከናውኑ ጣልቃ
የሚገባ ወይም የሚሰጡትን ህጋዊ ውሳኔ
የማያከብርና የማያስፈጽም እንዲሁም
የመተባበር ግዴታውን የማይወጣ ማንኛውም
ሰው አግባብ ባለዉ የወንጀል ህግ ይጠየቃል፡፡
2. ማንኛውም የፖሊስ አባል የዓቃቤ ሕግን
የመጨረሻ እና ሕጋዊ ውሳኔ በመቃወም
ያልታዘዘ እንደሆነ አግባብ ባለው ሕግ
በወንጀል ይጠየቃል፡፡
21. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች
1. በመስተዳድር ምክር ቤት የወጡ ደንቦች፣ በፍትሕ
ቢሮ፣ በክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን እና በክልል
የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የወጡ የጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ ሥልጣንና ተግባር ለማስፈፀም
አግባብነት ያላቸው መመሪዎች እና ማኑዋሎች
በሌሎች ደንቦች፣ መመሪያዎች ወይም ማኑዋሎች
powers and duties has a duty to cooperate if it
is not beyond his capacity and does not cause
danger.
2. Leaders and employees of the Regional
Justice Bureau and the subordinate structure,
leaders and employees of the revenue
authority who have been in charge before the
coming into force of this Proclamation have
duty to cooperate with and assist the transition
based on this Proclamation.
3. Any member of the police shall have duty to
respect and execute final and legal decision of
the public prosecutor.
20. Criminal Liability
1. Any person, who does not respect and
execute the authorized decision provided as
well as does not exercise; or interferes
against the Attorney General and public
prosecutors inorder not perform their work
independently, shall be liable by pertinent
criminal law.
2. Any member of the police who resists and
fails to execute the final and legal decision
of the public prosecutor shall be punished in
accordance with relevant law.
21. Transitory Provisions
1. The regulations issued by the Executive
Council, directives and manuals issued by the
Bureau of Justice, Regional Revenues
Authority, Regional Ethics and Anti-
corruption Commission which are relevant
for the enforcement of the powers and duties
of the public prosecution shall be applicable
22
እስካልተተኩ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል፡፡
2. አግባብነት ያላቸው የተሻሻለው የፌደራል የፀረ-
ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ አዋጅ
434/97 (በአዋጅ ቁጥር 882/2007
እንደተሻሻለ)፣የተሻሻለው የፌደራል ስነ ምግባርና
ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
433/2007 (በአዋጅ ቁጥር 883/2007
እንደተሻሻለ)፣የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ
አዋጅ ቁጥር 881/2007 በክልሉ በሚፈፀሙ
የሙስና ወንጀሎች እንደየአግባብነቱ ተፈፃሚ
ይሆናሉ፡፡
3. በክልሉ ፍትህ ቢሮ፣በገቢዎች ባለስልጣን እና
በክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ተቀጥረው ወይም ተመድበዉ በሥራ ላይ የሚገኙና
በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የሚወጡ መሥፈርቶቹን
አሟልተው ወደ ክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ
ቤት የሚዛወሩ ዓቃቤያነ ሕግ በዚህ አዋጅ መሠረት
በዓቃቤ ሕግነት ሥራቸውን ይቀጥላሉ፡፡፡
4. በክልሉ ፍትህ ቢሮ፣በገቢዎች ገቢዎች ባለስልጣን
እና በክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ለዓቃቤ ሕግ የሥራ ክፍሎች በድጋፍ ሰጪነት
ሥራ ላይ የሚገኙና በክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
ውሳኔ ወደ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሚዛወሩ
የመንግስት ሰራተኞች በዚህ አዋጅ መሠረት የክልል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሠራተኞች ሆነው ሥራቸውን
ይቀጥላሉ፡፡
5. በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ
ሆነው ነገር ግን በክልሉ ፍትህ ቢሮ፣የሥነ-
ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ በገቢዎች
ባለሥልጣን ተይዘው በመታየት ላይ የሚገኙ
unless replaced by other regulations,
directives or manuals.
2. The Federal Ethics and Anti-corruption
Commission under its establishment
Proclamation No 433/2005 (as amended by
Proclamation No. 883/2015) and the Revised
Anti-corruption Special Procedure and
Evidence Proclamation No. 434/2005 (as
amended by Proclamation No. 882/2015 and
Proclamation No.881/2015 issued to
determine the Corruption crimes shall be
executed as may be necessary.
3. The Public prosecutors, who are employed or
assigned to worke for Regional Ethics and
Anti-corruption Commission, Revenues
Authority, and Justice Bureau, and
transferred to the Attorney General upon
satisfying the criteria issued by Attorney
General, shall continue their work as public
prosecutors pursuant to this Proclamation.
4. Public servants, working as supporting staff
for prosecution departments, in the Regional
Justice Bureau, Ethics and Anti-corruption
Commission, and Regional Revenues
Authority, and transferred to the Attorney
General by decision of the Regional Attorney
General, shall continue their work as
employees of the Regional Attorney General
pursuant to this Proclamation.
5. The criminal and civil cases, which are
pending under the power of the regional
Justice Bureau, Ethics and Anti-Corruption
Commission, and Revenues Authority but
23
የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች የክልሉ ጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ በአራት ወር ውስጥ እስኪረከባቸው
ድረስ በተጀመሩበት አኳኋን መታየት ይቀጥላሉ፣
እንዲሁም በነዚህ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ዓቃብያነ-
ሕግ እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች አስተዳደር
በነበረበት ሁኔታ ይቀጥላል፡፡
6. በዲሲፕሊን ኮሚቴዎች ወይም በሌሎች የዓቃቤ
ሕግ አስተዳደር ጉባኤዎች በመታየት ላይ ያሉ
የዓቃቤ ሕግ የዲስፕሊን ክስ ጉዳዮች በዚህ አዋጅ
መሠረት ለተቋቋመው የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር
ጉባኤ ተላልፈዋል፡፡
7. በክልል ፍትህ ቢሮ፣ የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና
ኮሚሽን እና በክልል ገቢዎች ባለሥልጣን እጅ
የሚገኙ ጥቆማዎች፣ የምርመራ እና የዓቃቤ ሕግ
መዛግብትና ሰነዶች እንዲሁም
ኤግዚብቶች፣የተያዙና በክርክር ላይ ያሉ ንብረቶች
ወደ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይዛወራሉ፡፡
8. በክልሉ ስነ ምገባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና
በክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የተጀመሩ
የወንጀል ምርመራዎች ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን
ተላልፏል፡፡
22. በጀት
የክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከመንግስት
በሚመደብለት በጀት ይተዳደራል፡፡
droped under the jurisdiction of the Attorney
General, shall be continued in the manner
they were started until the Regional Attorney
General accepts them within four months; the
public prosecutors and supporting staff
administration shall continue as they are.
6. Discipline charge Cases of the public
prosecutors pending under the discipline
committee or other public prosecutors
administration councils shall be transferred to
the public prosecutors administration council
established in accordance with this
Proclamation;
7. The uncovering, investigation found under
the Regional Justice Bureau, Regional Ethics
and Anti- corruption Commission, and
Regional Revenues Authority, and files and
documents of public prosecutors, as well as
showings, seized properties and properties on
dispute shall be transferred to Attorney
General.
8. Criminal investigations that are strated in the
Region Anti corruption Commision and
Revenue Authority are transmitted to the
Region Police Commission
22. Budget
The Regional Attorney General shall be
administered by budget allocated by the
Government.
24
23. የሂሳብ መዛግብት
1. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተሟላና ትክክለኛ የሂሳብ
መዛግብት ይይዛል፡፡
2. የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ
ሰነዶች በክልል ዋና ኦዲተር ወይም በዋና ኦዲተር
በሚሰየም ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡
24. ደንብና መመሪያ የማውጣት ስልጣን
1. የመስተዳድር ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም
የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
2. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይህን አዋጅ እና በዚህ
አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የወጡ
ደንቦችን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን
ሊያወጣ ይችላል፡፡
3. በህግ መሰረት ለህዝብ ይፋ እንዳይደረጉ
ከተከለከሉ ሚስጥራዊ ሰነዶች በስተቀር
የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በማናቸውም
መንገድ እንዲታተሙ እና እንዲሰራጩ
ይደረጋል፡፡
25. ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች
ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ሕጎች
በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዳዩች ላይ
ተፈፃሚት አይኖራቸውም፡፡
26. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ በክልል ምክር ቤት ከፀደቀበት ቀን
ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
ሀዋሳ …….. ቀን 2011 ዓ.ም ሚሊዮን ማቲዎስ
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር
23. Books of Accounts
1. The Attorney General shall keep complete
and accurate books of account.
2. The books of accounts and financial
documents of the Attorney General shall be
audited annually by the Regional Auditor
General or by an auditor designated by him.
24. Power to Issue Regulation and Directive
1. The Executive Council may issue
regulations necessary to enforce this
Proclamation.
2. The Attorney General may issue directives
necessary for the enforcement of this
Proclamation and regulations issued
pursuant to sub-article (1) of this Article.
3. Except the secret documents banned to
public by law, directives issued shall be
published and disseminated by any means.
25. Inapplicable Laws
No laws, in so far that they are inconsistent
with this Proclamation, shall be applicable
with respect to matters covered under this
Proclamation.
26. Effective Date
This Proclamation shall enter into force on the
date of its approval by regional council.
Hawassa this -------day of 2018
Milion Mathewos
Chief executive of the South Nations,
Nationalities and Peoples Region state
25
Recommended