12

የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006

  • Upload
    meresaf

  • View
    969

  • Download
    15

Embed Size (px)

DESCRIPTION

የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006

Citation preview

Page 1: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
Page 2: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በግል የውጭ ባለሃብቶችና በመንግስት ሽርክና በኩባንያ መልክ የተጀመረው በ1946 ዓ.ም ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ወንጂ ላይ ሲሆን በሽርክና ወደ ስራ የገባው የውጭ ኩባንያም ኤች.ቪ.ኤ. የተሰኘ የደች ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው አምስት ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ስራ የጀመረው ሰኔ 18 ቀን 1943 ዓ.ም ነበር፡፡ ኩባንያው የፋብሪካ ግንባታውን መጋቢት 11 ቀን 1946 ዓ.ም አጠናቆ ስኳር ማምረት ሲጀምር የነበረው የመፍጨት አቅም በዓመት እስከ 70 ሺህ ቶን የሚደርስ ሲሆን ምዕዙን ስኳር እና ባለ አስር ሳንቲም እሽግ ስኳር ለገበያ ያቀርብ ነበር፡፡ በወቅቱ የወንጂ አካባቢ በዓለማችን ከፍተኛ ምርት ከሚያስመዘግቡና ለስኳር ምቹ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ የነበረ ሲሆን ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ ምስረታ ጋር ተያይዞም በሰኔ ወር 1953 ዓ.ም የወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ ተቋቁሞ ደስታ ከረሜላ አምርቶ ለገበያ

ማቅረብ ጀመረ፡፡ እዛው ወንጂ ላይ የተገነባው የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ በ1955 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ፋብሪካው በወቅቱ በዓመት የነበረው የመፍጨት አቅም ከ70 እስከ 80 ሺህ ቶን ድረስ ነበር ፡፡

ሌላውና ለአገራችን ሁለተኛው የሆነው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በአክሲዮን መልክ ሰኔ 26 ቀን 1957 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግስትና የደች ኩባንያ በሆነው ኤች.ቪ.ኤ. መካከል ተመስርቶ በ1962 ዓ.ም ልዩ ስሟ መርቲ ተብላ በምትታወቀው ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ ቦታ ተከፈተ፡፡ መጀመሪያ ላይ ፋብሪካው ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚያውለው 11,000 ሄክታር መሬት ተሰጥቶት ወደ ምርት ሲገባ የማምረት አቅሙ በቀን 1,700 ኩንታል ስኳር ብቻ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው ያለው አማካይ ዓመታዊ ስኳር የማምረት አቅም 1,300,000 ኩንታል ገደማ ነው::

በ1967 ዓ.ም በተደረገው የመንግስት ለውጥ ምክንያት ፋብሪካዎቹ በመንግስት ይዞታ ስር ሆኑ:: በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ህግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 58/1970 የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቁሞ ወንጂ ሸዋ እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ አዲስ ከተማ እና አስመራ ከረሜላ ፋብሪካን እንዲያስተዳድር ተደረገ፡፡

ለአገሪቱ ሶስተኛ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለመገንባት በ1967 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት ተካሄዶ የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ምርት አዋጭ ሆኖ ተገኘ ፡፡ ጠለቅ ያለ ጥናት እንዲካሄድበትም ቡከርስ አግሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ ኩባንያ አማካይነት ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ ስለፕሮጀክቱ ዝርዝር ጥናት ተካሄደ፡፡ በፋይናንስ ዕጥረት ሳቢያ ለተወሰነ ጊዜ የተጓተተው የፋብሪካው ግንባታም የአፍሪካ ልማት ባንክና የልማት ፈንድ ፣ የአውስትራሊያና የስፔን መንግስታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች የፋይናንስ ምንጮች መሆናቸው ተረጋግጦ የፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ጥር ወር 1981 ዓ.ም እንዲሁም የሸንኮራ አገዳ ተከላ ስራው በ1984 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡

የወንጂ ሸዋን እና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የአዲስ ከተማንና የአስመራ ከረሜላን ያስተዳድር የነበረው ኮርፖሬሽን በ1984 ዓ.ም

በህግ ሲፈርስ በምትኩ በደንብ ቁጥር 88/85 መተሐራ ስኳር ፋብሪካ፣ በደንብ ቁጥር 88/85 ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና በደንብ ቁጥር 199/86 ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ (በወቅቱ አዲስ የተጀመረ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ነበር) እራሣቸውን የቻሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሆነው እንዲቋቋሙ ተደረገ፡፡

ከቀደምቶቹ ስኳር ፋብሪካዎች በተሻለ ዘመናዊ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካና ኤታኖል ግንባታ ያከናወኑት ኤፍ.ሲ.ሼፈርና አሶሽየትስ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ እና በእርሱ ስር የፋብሪካውን ተከላ ያካሄደው ድዌቶ ኢንተርናሽናል የተባለ የደች ኩባንያ ሲሆኑ በርካታ አገር በቀል ድርጅቶችም በግንባታው ተሳትፈዋል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ የተጠናቀቀውም የደርግ ሥርዓት ተወግዶ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በወሰደው እርምጃ ነው፡፡

ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ምርት የጀመረው የካቲት ወር 1990 ዓ.ም ቢሆንም መደበኛ ስራውን የጀመረው በ1991 ዓ.ም ነው፡፡ በዚሁ ዓመት ያስመዘገበው ዓመታዊ ምርት 500,000 ኩንታል ስኳር ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለስኳር ፋብሪካዎቹ

የጋራ አገልግሎት እንዲሰጥ “የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል አክስዮን ማህበር” በሶስቱ ስኳር ፋብሪካዎች፣ በልማት ባንክ እና በመድን ድርጅት በአክስዮን መልክ ህዳር 1990 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ በመቀጠልም አራተኛውና በአፋር ብሔራዊ ክልል እየተገነባ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር 122/98 የተመሰረተ ሲሆን ፋብሪካው በሃምሳ ሺህ ሄክታር ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት እንዲኖረው እና ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑ 619,000 ቶን እንዲሁም ዓመታዊ ኤታኖል ምርቱ 55.4 ሚሊዮን ሊትር እንዲሆን ታቅዶ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው፡፡ በኋላም ድጋፍ ሰጪ ማእከሉን በማፍረስ “የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ” በአዋጅ ቁጥር 504/98 ተቋቁሞ የስኳር ፋብሪካዎቹን በመቆጣጠር፣ በፕሮጀክት ልማት፣ በምርምር፣ በስልጠናና በግብይት ረገድ ድጋፍ ሲሰጥ ቆየ፡፡

ከጥቅምት 19 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ እንዲፈርስ ተደርጎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 የአሁኑ “ስኳር ኮርፖሬሽን” ተቋቁሞ የስኳር ልማትን በአገራችን በስፋት ለማካሄድ በሚያስችለው መልኩ ተደራጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar

1 2

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

አንጋፋው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ

Page 3: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ ስትራተጂያዊ ማዕቀፍ

የአገራችን ኢኮኖሚ ባለፉት አሥር ተከታታይ አመታት በየአመቱ በአማካይ 11 በመቶ ዕድገት የተመዘገበበት ነው፡፡ ይህንን ፈጣን እና መሰረተ ሰፊ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስቀጠል መንግስት የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች ከማሳካት ባሻገር እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2012-2015 ባሉት አመታት አገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ አገራዊ ራዕይ አስቀምጦ ለስኬቱ በጽናት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ተልዕኮ ስኬት ባለፉት አመታት በተካሄዱ የልማት ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ መልካም ተሞክሮዎችንና የአገሪቱን ራዕይ መሰረት በማድረግ ህዝቡ በየደረጃው በስፋት የተሳተፈበት የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

የአምስት አመቱ እቅድ አላማዎች አጠቃላይ ኢኮኖሚው በየአመቱ ቢያንስ በአማካይ 11 በመቶ እድገትን በማስመዝገብ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ መታየት የጀመሩትን የዋጋ ግሽበትን የመሣሰሉ ችግሮችን በማስወገድና በማቃለል የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ለማሳካት የሚያስችል ርብርብ እየተካሄደ ነው፡፡ የትምህርትና ጤና አገልግሎት ሽፋንን በመጨመርና ጥራቱን በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተ ማህበራዊ ልማት በማካሄድ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ማሳካት፣ የተረጋጋ ዲሞክራሲያዊና ልማታዊ መንግሥት መፍጠርና ማጠናከር፣ ለቀጣይ የአገር ግንባታ ስራ ምቹ መደላድል መፍጠርና እነዚህን አላማዎች በተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ውስጥ መፈጸም የልማቱን ቀጣይነት የማረጋገጥ ጉዳይ በመሆናቸው በዚህ ረገድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

የኢንዱስትሪው ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ቁልፍ ሚና እንዲጫወት በተነደፈው ስትራተጂ መሰረት በአጠቃላይ የአገሪቱን የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በተመለከተ የተነደፉትን አላማዎችና የአፈጻጸም አቅጣጫዎች መሰረት በማድረግ በኢንዱስትሪው ዘርፍም ተያያዥ ዝርዝር አላማዎች የተቀረጹ ሲሆን ከዘርፉ በአመት እስከ 18 በመቶ እድገት ይጠበቃል፡፡

መንግሥት በነደፈው የአምስት አመት እቅድ መሰረት የገቢ ምርቶችን የሚተኩ ኢንዱስትሪዎች ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የላቀ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲስፋፉ እየተደረገ ነው፡፡ የአገራችን ነባር የስኳር ፋብሪካዎች የሚያመርቱት የስኳር ምርት እያደገ የመጣውን የአገር ውስጥ ፍላጎት ማርካት ባለመቻሉ ይህንኑ ዕጥረት ለመቅረፍ መንግስት ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ ስኳር ከውጪ አገር አስገብቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ

ለመለወጥም መንግስት በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን ከማካሄድ ባሻገር የነባር ስኳር ፋብሪካዎችን ለማስፋፋቱ ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተንቀሳቅሷል፤ በመንቀሳቀስ ላይም ይገኛል፡፡

በኢንዱስትሪ ልማት ስትራተጂው መሰረት ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በተለይ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች ስር ለሚመደበው የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ ትኩረት የተሰጠው በብዙዎቹ ቆላማ የአገራችን አካባቢዎች ምርቱን ማምረት የሚቻል በመሆኑና በተለይም በእነዚህ አካባቢዎች ለመስኖ ልማት የተመቸና ሊለማ የሚችል ሰፊ መሬት ያለ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከህዝቡ የኑሮ እድገት ጋር ተያይዞ የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎት እየጨመረ በመሄዱና የስኳር ምርት ሰፊ የውጭ ገበያ ያለው በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የመንግስት ስኳር ፋብሪካዎች በዘርፉ ልማት ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በሌላ በኩል የስኳር ፋብሪካዎቹን በአለም ገበያ በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪ ለማድረግ በአውሮፓ ገበያ ለስኳር አምራች የአፍሪካ አገሮች የተሰጠውን ልዩ እድል ለመጠቀም እንዲሁም ከዘርፉ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ነባራዊ ሁኔታዎች እና የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግም የዘርፉን የልማት እንቅስቃሴ ለመምራትና ለማስፈጸም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 ስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቁሞ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

3 4

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar

Page 4: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

በማቋቋሚያ አዋጁ የተቀመጡ የስኳር ኮርፖሬሽን ዓላማዎችff የሸንኮራfአገዳናfስኳርfየሚያስገኙfሰብሎችfማልማት፣ff ስኳር፣f የስኳርfውጤቶችን፣f የስኳርf ተረፈfምርቶችንf እናf የስኳርfተረፈfምርትfውጤቶችንfበፋብሪካfማዘጋጀትናfማምረት፣ff ምርቶቹንናf ተረፈf ምርቶቹንf ለአገርf ውስጥf እናf ለውጭf ገበያfማቅረብ፣ff አዳዲስናf የማስፋፊያf የስኳርf ልማትf ፕሮጀክቶችf የአዋጭነትfጥናት፣fየዲዛይንfዝግጅት፣fየቴክኖሎጂfመረጣናfድርድር፣fየተከላናfኮሚሽኒንግfስራዎችfእንዲካሄዱfማድረግ፣ff ከሚመለከታቸውf አካላትf ጋርf በመተባበርf በሸንኮራf አገዳናfበስኳርfአመራረትfቴክኖሎጂfጥናትናfምርምርfማካሄድናfጠቃሚfውጤቶችንfበስራfላይfማዋል፣ff አቅሙf ካላቸውf የአገርf ውስጥf ድርጅቶችf ጋርf በመተባበርfለመንግስትf የስኳርf ፋብሪካዎችf የሚያስፈልጉf የማምረቻfመሳሪያዎችናfመለዋወጫዎችfዲዛይንናfፋብሪኬሽንfስራዎችfበሀገርf

ውስጥfእንዲከናወኑfማድረግ፣ff በህግfመሰረትfለስራውfየሚያስፈልገውfመሬትfባለይዞታfመሆንናfማልማት፣ff የአገዳf ምርታቸውንf ለመንግስትf የስኳርf ፋብሪካዎችf የሚያቀርቡfአገዳfአብቃዮችንfማበረታታትናfመደገፍ፣ff ለስኳርfኢንዱስትሪfየሚፈለገውንfየሰለጠነfየሰውfሃይልfበሚፈለገውfአይነት፣fመጠንናf ጥራትf ለማፍራትf እንዲቻልf ከሚመለከታቸውfየትምህርትfተቋማትfጋርfመተባበር፣ff የገንዘብናf ኢኮኖሚf ልማትf ሚኒስቴርf የሚያወጣውንf መመሪያናfየፖሊሲf አቅጣጫf መሰረትf በማድረግf ቦንድf መሸጥናf በዋስትናfማስያዝfእናfከአገርfውስጥናfከውጭfየገንዘብfምንጮችfጋርfየብድርfውልfመደራደርናfመፈራረም፣ff አላማውንf ከግብf ለማድረስf የሚረዱf ሌሎችf ተዛማጅf ስራዎችንfመስራትfናቸው፡፡

fÒ በቀጣይfዕድገትfላይfየተመሰረተናfበዓለምfተወዳዳሪfየሆነfየስኳርfኢንዱስትሪfመፍጠር፣

የስኳር ኮርፖሬሽን ራዕይ፣ተልዕኮ እና እሴቶች

ራዕይ፡-f� በሀገርfደረጃfለሚደረገውfየፖለቲካልfኢኮኖሚfለውጥfማለትምfፈጣን፣ቀጣይfእናfፍትሀዊfእድገትfለማምጣትfየጎላfድርሻfየሚያበረክትfተቋምfመፍጠር፣f� ልማታዊfአመለካከትናfስነምግባርfያለውfለለውጥfየሚሰራ፣fለስራውfተፈላጊfክህሎትfያለውfለውጤትናfለስኬትfየሚተጋfአመራርናfሰራተኛfመፍጠር፣f

ተልዕኮ፡-

f� የአገሪቱንfየስኳርfፍላጎትfማርካት፣ff� በዓለምfገበያfከፍተኛfየኤክስፖርትfድርሻfመያዝ፣ff� የስኳርfተረፈfምርቶችንfበመጠቀምfየአገሪቱንfየኢነርጂfአቅርቦትfመደገፍ፣f� ለዜጎችfሰፊfየሥራfዕድልfመፍጠር፣ff� ስኳርfልማቱfበሚካሄድበትfአካባቢfየባህልናfማህበራዊfእድገትንfማፋጠን/ማገዝ፣

f� በስኳርfልማትfየቴክኖሎጂfሽግግርfማምጣት፣f� ተጓዳኝf ሰብሎችንf በማልማትf የኢንዱስትሪውንf ተወዳዳሪነትfማጎልበት፤f� የስኳርf ኢንዱስትሪውንf ስትራቴጂካዊf አላማዎችf ለመፈፀምfየሚያስችልfተቋማዊfብቃትfመፍጠር፣ff� ማህበራዊናfኢኮኖሚያዊfትስስርfመፍጠር፡፡

ቁልፍ ዕሴቶችኮርፖሬሽኑfየእለትfከዕለትfስራውንfየሚያከናውነውfየሚከተሉትንfቁልፍfእሴቶችfመሰረትfበማድረግfነው፡፡እነርሱም፡-

fh ውጤትf ተኮርf እናf ወጪf ቆጣቢf የአመለካከትናf የአሰራርfስርአትfማስፈን፣fh የማያቋርጥfለውጥናfቀጣይfተወዳዳሪነት፣fffh መልካምfአስተዳደርfማስፈን፣

fh መልካምfስነfምግባር፣ffh ከአካባቢውf ህዝብf ጋርf አጋርነትf መፍጠርናfተጠቃሚነታቸውንfማረጋገጥ፡፡f

የስኳር ኮርፖሬሽን የአምስት ዓመት ዓላማዎችና ግቦችአጠቃላይfዓላማዎች

ft የአገሪቱንfየስኳርfፍላጎትfአቅርቦትfማረጋገጥ፣ft በአገሪቱfየስኳርfተጓዳኝfምርቶችንfበማሳደግfየኃይልfአቅርቦትንfመደገፍናfቁልፍfየኢኮኖሚfአገልግሎትfላላቸውfተግባራትfማዋል፣ft የስኳርfንዑስfዘርፍfለብሔራዊfኢኮኖሚfዕድገትfየሚኖረውንfአስተዋጽኦfማሣደግfእናfለዜጎችfየሥራfዕድልfመፍጠር፣ft በዓለምfገበያfከፍተኛfየኤክስፖርትfድርሻfመያዝ፣ft የስኳርfልማትfኢንዱስትሪfንዑስfዘርፍንfስትራቴጂካዊfዓላማዎችfለመፈጸምfየሚያስችልfየሰውfኃይልfልማትf፣fየምርምርናfየቴክኖሎጂfድጋፍfየሚያደርግfተቋማዊfብቃትfመፍጠርfናቸው፡፡

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar

65

Page 5: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

tt የስኳርtምርትንt 2.25tሚሊዮንt ቶን፣t የኤታኖልtምርትንt 181,604t tሜትርtኪዩብtማድረስ፣tt በልማትtዘመኑtመጨረሻtዘመንtላይt 101tሜጋtዋትt t የኤሌክትሪክtኃይልtለብሔራዊtየኤሌክትሪክtኃይልtቋትtማበርከት፣tt በወንጂtሸዋt፣በመተሐራ፣በፊንጫአtእናtበተንዳሆtስኳርtፋብሪካዎችtየተጀመሩትንt የነባርt ስኳርt ፋብሪካዎችtማስፋፊያናt የአዲስt ስኳርtፋብሪካtግንባታtማጠናቀቅ፣tt ተጨማሪtአስርtአዳዲስtስኳርtፋብሪካዎችንtመትከል፣tt በዕቅድtዘመኑtውስጥtደረጃtበደረጃtበማሳደግtበ2007tበጀትtዓመትtመጨረሻtእስከt623,000tቶንtጥሬtስኳርtእናt623,000tቶንtነጭtስኳርtበድምሩt1,246,000tቶንtስኳርtኤክስፖርትtማድረግ፣tt በዕቅድt ዘመኑt ውስጥt ደረጃt በደረጃt በማሣደግt በ2007t በጀትtዓመትt መጨረሻt እስከt 137,464t ሜትርt ኪዩብt ኬሮሲንt (Kero-sene)tበማምረትtለምግብtማብሰያናtለሌሎችtግብዓቶችtአገልግሎትtማዋልናtከውጭtበዚሁtመጠንtይገባtየነበረውንtምርትtመተካት፣tt በዕቅድtዘመኑtውስጥtደረጃtበደረጃtበማሣደግtበ2007tበጀትtዓመትt

መጨረሻt እስከt 44,340t ሜትርt ኪዩብt ኤታኖልt ለብሌንዲንግt(Blending)tአገልግሎትtማዋል፣tt ከፍተኛtምርትtየሚሰጡtስድስትtበምርምርtየተገኙtየሸንኮራtአገዳtዝርያዎችtመልቀቅ፣tt አንድtየተሟላtየሸንኮራtአገዳtማዳቀያtጣቢያt(BreedingtStation)tማቋቋም፣tt የተጀመሩtአራትtየቲሹtካልቸርtላቦራቶሪtእናtግሪንtሀውስtማጠናቀቅ፣tt ምርታማነትንtበማሻሻልናtከሄክታርtየሚገኘውንtምርትtአሁንtካለበትtአማካይt145tቶንtወደt155tቶንtማሳደግ፣tt ለ21,500t ሠራተኞችt በተለያየt ደረጃt የዕውቀትናt ሙያt ማሻሻያtትምህርት/ሥልጠናtመስጠት፣tt በስኳርtልማትtዘርፉtበሚካሄድt የእርሻ፣tፋብሪካ፣tቤቶችናtመስኖtልማትtሥራtከt200tሺህtበላይtለሚሆኑtዜጎችtተጨማሪtየሥራtዕድልtመፍጠር፣tt የንዑስt ዘርፉንt ዋናt መስሪያt ቤትt የጋራt የቢሮt ህንፃt እንዲሁምtየምርምርናtሥልጠናtተቋማትንtመገንባትtናቸው፡፡

ዋና ዋና ግቦች

ኮርፖሬሽኑ እነዚህን ያስቀመጣቸውን ዓላማዎችና ግቦች ከዳር ለማድረስ በነባር ስኳር ፋብሪካዎች ላይ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ያከናወነ ሲሆን፣ አንድ ጅምር የስኳር ልማት ፕሮጀክትን የማጠናቀቅ እንዲሁም አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን የመገንባት ስራም እያከናወነ ይገኛል፡፡

የነባር ስኳር ፋብሪካዎች የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች

1. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካበአገራችንt የስኳርt ፋብሪካt ታሪክt ፋናt ወጊtየሆነውtየወንጂtስኳርtፋብሪካtበ1946tዓ.ምtግንባታውtተጠናቆtማምረትt የጀመረtሲሆንtየሸዋt ስኳርt ፋብሪካt ደግሞt እዛውt ወንጂtላይt በ1955t ዓ.ምt ተመርቆt ስራt የጀመረtሌላውt ስኳርt ፋብሪካt ነው፡፡t ሁለቱt አንጋፋtፋብሪካዎችt በአንድt አስተዳደርt እየተዳደሩtያመርቱt የነበረtሲሆንtወንጂt እናt ሸዋt ስኳርtፋብሪካዎችt ስራቸውንt እስካቆሙበትtማለትምtወንጂtእስከt2004tእንዲሁምtሸዋtእስከt 2005t በጀትt ዓመትt መጨረሻt ድረስtየነበራቸውt የማምረትt አቅምt በአማካይtበአመትt75,000tቶንtስኳርtነው፡፡tሁለቱምtስኳርt ፋብሪካዎችt ኤች.ቪ.ኤt በተባለt የደችtኩባንያt የተገነቡናt በኩባንያውናt በመንግስትtየጋራt ባለቤትነትt በሽርክናt የተቋቋሙtነበሩ፡፡t የወንጂt ሸዋt ስኳርt ፋብሪካt ነባርt

አጠቃላይt የሸንኮራt አገዳtመሬትt ሰባትtሺህtሄክታርt የነበረt ሲሆንt ከዚህt መካከልt አንድtሺህt ሄክታሩt ይለማt t የነበረውt በአካባቢውtበሚገኙt አገዳt አብቃይናt አቅራቢt አርሶtአደሮችt አማካይነትt ነበር፡፡t ነባሩንt የወንጂtሸዋtስኳርtፋብሪካtበአዲስናtዘመናዊtፋብሪካtለመተካትtየማስፋፊያtፕሮጀክትtበፋብሪካtእናtበእርሻtዘርፍtተከናውኖtየፋብሪካtማስፋፊያtስራውtበ2005tበጀትtዓመትtመጨረሻtላይtተጠናቋል፡፡

በፋብሪካt ማስፋፊያt በኩልt በተከናወነውtየማስፋፊያt ስራt አማካይነትt ፋብሪካውtመጀመሪያtወደtስራtሲገባtበቀንt6,250tቶንtአገዳt በመፍጨትt በዓመትt 174,946t ቶንtስኳርt የማምረትt አቅምt የሚኖረውt ሲሆንtደረጃtበደረጃtየማምረትtአቅሙንtበማሳደግ

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar •

ተወዳዳሪtየስኳርtኢንዱስትሪtመገንባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

7 8

አዲስtየተገነባውtየወንጂ/ሸዋtስኳርtፋብሪካt

Page 6: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar •

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለአገራችን ሁለተኛው የስኳር ፋብሪካና ከአዲስ አበባ 200 ኪ.ሜ ርቀት የሚገኝ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ ስኳር ማምረት የጀመረው በ1962 ዓ.ም ነበር፡፡ ፋብሪካው በአክስዮን መልክ በኢትዮጵያ መንግስትና ወንጂ

ሸዋ ስኳር ፋብሪካን በገነባው የደቹ ኤች.ቪ.ኤ ኩባንያ አማካይነት የተቋቋመና በአሁኑ ወቅት 10,235 ሄክታር በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ነው፡፡ የፋብሪካው አማካይ የማምረት አቅም በዓመት 136,692 ቶን ስኳር ሲሆን በአገራችን ካሉት ነባር ስኳር ፋብሪካዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የተሻለ የማምረት አቅም የነበረው ፋብሪካ ነው፡፡ ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት የኤታኖል ማምረቻ ፕላንት ገንብቶ ከ2003 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው በዓመት እስከ 12.5 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል የማምረት አቅም አለው፡፡

2. የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ

3. የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካየፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምዕራብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ውስጥ ይገኛል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ በ1990 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ቢሆንም ወደ ምርት የገባው ግን በ1991 ዓ.ም ነው፡፡ ፋብሪካው የማስፋፊያ ስራ ከማከናወኑ በፊት በዓመት 110,000 ቶን ስኳር እና እስከ 8 ሚሊዮን ሊትር የሚደርስ ኤታኖል ያመርት ነበር፡፡ እስከ 2003 ዓ.ም አጋማሽ ድረስም ብቸኛው ኤታኖል የሚያመርት ፋብሪካ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለማከናወን ካቀደው የፋብሪካ እና የእርሻ ማስፋፊያ ስራ መካከል የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራውን በ2005 በጀት ዓመት አጠናቋል፡፡ የእርሻ ማስፋፊያ ስራው ከፊንጫአ ወንዝ በስተምሥራቅ ኢስት ባንክ እና ነሼ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች እንዲሁም በፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ በለማው የአገዳ መሬት አጠገብ በሚገኙ ክፍት ቦታዎች ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው እያካሄደ ባለው የእርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አማካይነት የሸንኮራ አገዳ መሬቱን 21,000 ሄክታር ለማድረስ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስከ 2006 ዓ.ም መጀመሪያ ወራት ድረስ ብቻ በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬቱን ከ17,000 ሄክታር በላይ አድርሷል፡፡

በፋብሪካ ማስፋፊያ ረገድ ደግሞ እስከ 2005 በጀት ዓመት በቀን 5,000 ቶን አገዳ ይፈጭ የነበረውን ፋብሪካ ወደ 12,000 ቶን የማሳደግ እንዲሁም ኤታኖል ፋብሪካውን የማስፋፋት ስራ ለማጠናቀቅ ተይዞ የነበረውን ግብ ለማሣካት ተችሏል፡፡ በዚህ የማስፋፊያ ስራ አማካይነትም በእቅዱ አመታት መጨረሻ ፋብሪካው በአመት 270,000 ቶን ስኳር እና 20,000 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ማምረት ወደሚችልበት ሙሉ አቅም ይሸጋገራል፡፡

9 10

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

በቀን 12,500 ቶን አገዳ ወደ መፍጨት ከፍ የሚል እና ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑም ወደ 222,700 ቶን የሚያድግ ይሆናል፡፡ የዚህ አዲስና ዘመናዊ ፋብሪካ ኤታኖል የማምረት አቅምም በመጀመሪያ ምዕራፍ 10,000 ሜትር ኪዩብ ወደ ማምረት አቅም ቀጥሎም በሁለተኛው ምዕራፍ በሚኖረው አቅም 12,800 ሜትር ኪዩብ እንዲደርስ የታቀደ ሲሆን ፋብሪካው በእቅዱ አመታት መጨረሻ ለብሔራዊ የኃይል ቋት የሚያበረክተው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠንም 22 ሜጋ ዋት ይደርሳል፡፡በሌላ በኩል ነባሩ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ እርሻ መሬትን

የማስፋፋት ስራ ዋቄ ጢዮ፣ ሰሜን ዶዶታ እና ወለንጪቲ ተብለው በሚታወቁ አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ይሄው የእርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ አዲሱ ፋብሪካ በአጠቃላይ 16,000 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት የሚኖረው ሲሆን እስከ 2005 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ 4000 ሄክታር ተጨማሪ መሬት በሸንኮራ አገዳ እንዲሸፈን ተደርጓል፡፡ የፋብሪካው አጠቃላይ የሸንኮራ አገዳ እርሻ ማስፋፊያ ስራ በአገዳ አብቃይ ገበሬዎች ይዞታ ስር ያለና በእነርሱ አማካኝነት የሚለማ ነው፡፡

ኤታኖል ማምረቻ ፋብሪካ የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ

Page 7: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

የ • w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar •

ስኳር ኮርፖሬሽን በስኳር ልማት ዘርፍ በአምስት አመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመንና ከዚያ ቀጥሎ ባሉት ጥቂት ዓመታት በነባሮቹና አዲስ በሚገነቡ የስኳር ፋብሪካዎች አማካይነት አሁን ባሉት ሦስት ነባር ፋብሪካዎች በአመት በአማካይ እየተመረተ ያለውን 300 ሺህ ቶን ገደማ የሚሆን ስኳር ወደ 2.25 ሚሊዮን ቶን፣ እንዲሁም በዓመት ይመረት

የነበረውን 8 ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ኤታኖል ወደ 181,604,000 ሊትር ለማሳደግ ታቅዷል፡፡በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ ፋብሪካዎቹ ከስኳር ተረፈ ምርት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨትና የራሳቸውን የኃይል ፍላጎት በማሟላት 101 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት ማበርከት እንዲችሉ በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ በነባሮቹና አዲስ በሚገነቡ የስኳር ፋብሪካዎች 137,464 ሜትር ኪዩብ ኬሮሲን በማምረትና በዚሁ መጠን ከውጭ የሚገባውን ኬሮሲን በመተካት ለምግብ ማብሰያና ለሌሎች ግብዓቶች አገልግሎት ለማዋል እንዲሁም 44,340 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ለብሌንዲንግ እንዲውልና አገራችን ለዚህ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለመቀነስ አቅዶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ከአንድ ሚሊዮን ሔክታር መሬት በላይ ከሚሸፍኑ እና ለዘርፉ ምቹ ከሆኑ የውኃ እና የመስኖ ልማት ቦታዎች መካከል ከ500,000 ሺህ ሔክታር የሚበልጥ የአገሪቷን መሬት ለሸንኮራ አገዳ ልማት ማዋል እንደሚቻል በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ ጥናት ታውቋል፡፡ በዚሁ መሰረትም በግንባር ቀደምትነት ለስኳር ልማት እንደሚሆኑ የተፈተሹት ቦታዎች የላይኛውና ታችኛው በለስ አካባቢዎች፣ከጣና ሐይቅ በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኘው የላይኛው ዲንደር ፣ የተከዜን ወንዝና ገባሮችን ተከትሎ በወልቃይትና ሁመራ፣ በአንገር ወንዝ ሸለቆ በነጌሶ፣በመካከለኛው ገናሌ ወንዝ እና በጋምቤላ አካባቢ የባሮና ጊሎ ወንዞችን ተከትለው የሚገኙት አካባቢዎች ናቸው፡፡

በዚህ መሠረት በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ጥናት ከተካሄደባቸው ከላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች መካከል በጣና በለስ በ75,000 ሄክታር ላይ የሚለማን የሸንኮራ አገዳ መሬት የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸው በቀን አስራ ሁለት ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሦስት የስኳር ፋብሪካዎች ይገነባሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ኦሞ፣ቤንች ማጂ እና ካፋ ዞኖች (ኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት) በ175,000 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ላይ የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት

የሚጠቀሙ ሁለት እያንዳንዳቸው በቀን 24 ሺህ እንዲሁም ሶስት በቀን እያንዳንዳቸው 12 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ አምስት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት ታቅዶ በትግበራ ላይ ይገኛል፡፡ በወልቃይት (ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት) በ50,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ የሚጠቀም በቀን 24 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲሁም በአፋር ክልል በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት በ20,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ ተጠቅሞ በቀን 10 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል አንድ ስኳር ፋብሪካ በአጠቃላይ አስር ስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት የሚያስችል ሰፊ ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በአፋር ክልል በ50,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን የሸንኮራ አገዳ

በግብዓትነት ተጠቅሞ በአመት 619,000 ቶን ስኳር ማምረት የሚችል ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ እና በኢሉ አባቦራ ዞኖች አልሀበሻ በሚል መጠሪያ በአንድ የፓኪስታን የግል ኩባንያ የተቋቋመውንና ግንባታው ከዘጠና በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ስኳር ፋብሪካን ኩባንያው ስራውን መቀጠል ባለመፈለጉ ወደ ኮርፖሬሽኑ ንብረትነት በ2005 ዓ.ም እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ የፋብሪካ ግንባታውን የማጠናቀቅ እና በኩባንያው ብዙም ያልተገፋበት የሸንኮራ አገዳ ልማት ስራ በስፋት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ይህ በኮርፖሬሽኑ ይዞታ ስር የሆነው የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የስኳር ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 12,000 ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ ዲዛይን የተደረገ ነው፡፡

የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች

11 12

Page 8: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

የ • w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar •

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 677 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአፋር ብሔራዊ ክልል በሚሌ፣ ዱብቲ፣ አሳኢታ እና አፋምቦ ወረዳዎች ውስጥ

ይገኛል፡፡ የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ1998 ዓ.ም የተጀመረና በ50,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ ተክል ልማት የሚካሄድበት ፕሮጀክት ነው፡፡ ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከሚኖረው 50,000 ሄክታር መሬት ውስጥ 25,000 ሄክታር የሚሆነው በሸንኮራ አገዳ አብቃይ የአካባቢው አርሶ አደሮች የሚለማ ሲሆን ቀሪው 25,000 ሄክታር ደግሞ በፋብሪካው የሚለማ ነው፡፡ ለዚሁ ስኳር ልማት የሚውለው ውኃ ከተንዳሆ ግድብ የሚገኝ ሲሆን ግድቡ 1.8 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ የመያዝ አቅም አለው፡፡ ፋብሪካው

ከ10,000 ሄክታር በላይ በመስኖ የሚለማ መሬት ለአካባቢው ተወላጆች በማመቻቸቱም የአካባቢው አርብቶ አደር ወደ ከፊል አርሶ አደርነት መሸጋገር የቻለበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ተወላጁ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡

የፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በ2006 በጀት ዓመት ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 13000 ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን ከሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ጋር ተዳምሮ ፋብሪካው በአጠቃላይ በቀን 26,000 ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ በሁለት ምዕራፍ ግንባታው የሚካሄደው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ሲጠናቀቅና በሙሉ አቅሙ ማምረት ወደሚችልበት ደረጃ ሲሸጋገር በአፍሪካ ግዙፉ

የስኳር ፋብሪካ ይሆናል፡፡

የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የስኳር ምርት መጠኑ ደረጃ በደረጃ አድጎ በዓመት 619,000 ቶን ስኳር እና 55.4 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል እንዲያመርት የሚጠበቅ የአገራችን የስኳር ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በእቅዱ ዘመን በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ ለ42,000 ያህል ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥርና አገራችን ወደፊት ለውጭ ገበያ ከምታቀርበው ስኳር ውስጥ ጉልህ ድርሻ የሚይዝ ነው፡፡ በእቅዱ አመታት መጨረሻ በአጠቃላይ ከሚያመነጨው 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ለብሔራዊ የኃይል ቋት የሚያበረክተው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠንም 91 ሜጋ ዋት ይደርሳል፡፡

1. የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

13 14

2.የከሰም ስኳር ልማትፕሮጀክት

ከሰም ስኳር ልማት በአፋር ብሔራዊ ክልል በዞን አምስት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በ50 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ በ20,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ ተክል የሚካሄድበት ነው፡፡ የሸንኮራ አገዳ እርሻ ልማቱ ከሰም ከተባለው አካባቢ በተጨማሪ ቦልሀሞን በተሰኘ አካባቢም የሚከናወን ነው፡፡ የከሰም ሰኳር ልማት ፕሮጀክት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ የተጀመረ ቢሆንም ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ወዲህ ቦታው ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀት አንፃር ተመዝኖና ተጠንቶ እራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል፡፡

ፋብሪካው በመጀመሪያ 6,000 ቶን ከዚያም ደረጃ በደረጃ ወደ 10,000 ቶን ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚፈጭበት ደረጃ እያደገ የሚሄድ ሲሆን የኤታኖል ፋብሪካና የኮጀነሬሽን ፋሲሊቲም የሚኖረው ይሆናል፡፡ ስኳር ፋብሪካው በመጀመሪያ ወደ ምርት ሲገባ እስከ 153,000 ቶን ስኳር እና እስከ 12,500 ሜትር ኪዩብ የሚደርስ ኤታኖል በዓመት የማምረት አቅም የሚኖረው ሲሆን ሙሉ አቅሙ ላይ ሲደርስ ደግሞ በዓመት 260,000 ቶን ስኳር እና 30,000 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡ ፋብሪካው ከዚህ ባሻገር 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን ከዚህም ውስጥ 15 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡ የተንዳሆ ግድብ

Page 9: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar •

15 16

3.ኩራዝ ስኳር ልማትፕሮጀክት ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የሰላማጎ እና የኛንጋቶም ወረዳዎች፣ በቤንች ማጂ ዞን የሱርማ እና የሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች እንዲሁም በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ የተመረጡ አካባቢዎች የሚካሄድ ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት የሚገነቡት አምስት ስኳር ፋብሪካዎች ሲሆኑ ሶስቱ በቀን እያንዳንዳቸው 12 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት እና በዓመት 278 ሺህ ቶን ስኳር እንዲሁም 26,162 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ማምረት የሚችሉ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ሁለቱ ፋብሪካዎች በቀን እያንዳንዳቸው 24 ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት እያንዳንዳቸው በዓመት 556,000ቶን ስኳር እንዲሁም 52,324 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ማምረት የሚችሉ ናቸው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ በ175,000 ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ

አገዳ ልማት ይከናወናል፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገው ውኃ ኦሞ ወንዝ ላይ በሚገነባና 381 ሜትር ስፋት እና 22.4 ሜትር ከፍታ ባለው የውኃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት የሚገኝ ነው፡፡

በኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሚገነቡት አምስት ስኳር ፋብሪካዎች ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ በአጠቃላይ በዓመት እስከ 1,946,000 ቶን ስኳር እና 183,134 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ማምረት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ፋብሪካዎቹ 415 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመርቱ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 275 ሜጋ ዋት ለብሔራዊ ኤሌክትሪክ ቋት ያበረክታሉ፡፡

ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ በ1,200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በትግራይ ብሔራዊ ክልል ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት አንድ የስኳር ፋብሪካ ይገነባል፡፡ ፋብሪካው ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት 484 ሺህ ቶን ስኳር እና 41,654 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል ማምረት የሚችል ነው፡፡ ፋብሪካው 50,000 ሄክታር ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት ይኖረዋል፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገው የውኃ አቅርቦት የሚገኘው ዛሬማ ወንዝ ላይ ከሚገነባው የሜይ-ደይ ግድብ ሲሆን ግድቡ 840 ሜትር ስፋት እና 135.5 ሜትር ቁመት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ ነው፡፡ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ 3,497,000,000 ሜትር ኪዩብ ውኃ የመያዝ አቅም ይኖረዋል፡፡ የግድቡ ግንባታ እየተከናወነ ያለው አገር በቀል በሆነው ሱር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ነው፡፡

4.ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት

በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዋናነት የሚገኘው በአማራ ብሔራዊ ክልል ሲሆን የተወሰነ የአገዳ እርሻ ልማቱ ሥራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ውስጥ ይካሄዳል፡፡ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ 576 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት የሚገነቡት ሦስት ስኳር ፋብሪካዎች ሲሆኑ በአጠቃላይ በ75,000 ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ልማት የሚከናወንበት ፕሮጀክት ነው፡፡ ፋብሪካዎቹ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለውን ውኃ የሚያገኙት በበለስ ወንዝ ላይ በተገነባ የውኃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት ነው፡፡ ሦስቱም ስኳር ፋብሪካዎች ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ እያንዳንዳቸው በዓመት 242,000 ቶን ስኳር እና 20,827 ሜትር ኪዩብ ኤታኖል የማምረት አቅም ይኖራቸዋል፡፡ በፕሮጀክቱ የዘር እና የኮሜርሻል አገዳ ተከላ፣የፋብሪካ ግንባታ፣ የመኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

5. በለስ ስኳር ልማትፕሮጀክት

Page 10: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

6.አርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክትአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋ ዞን እና በኢሉ አባቦራ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ - ጅማ - በደሌ - ነቀምቴ መስመር በ540 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እ.አ.አ በ2009 አል-ሐበሻ ስኳር ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሚል መጠሪያ ተቋቁሞ የነበረ ሲሆን ኩባንያው ፕሮጀክቱን ማስቀጠል ባለመቻሉ ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር የሽያጭ ውል በመፈጸም እ.አ.አ ከ2012 ነሐሴ ወር ጀምሮ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን

ንብረትነት ተዘዋውሯል፡፡ ፕሮጀክቱ ወደ ኮርፖሬሽኑ በተዘዋወረበት ወቅት የፋብሪካው ግንባታ ስራ ከዘጠና በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ2005 በጀት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ የሥራ አመራር አባላት ተመድቦለትና በየደረጃው የሰው ኃይል ተሟልቶለት ተልዕኮውን ለማሣካት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ፋብሪካው በመጀመሪያ ምዕራፍ አቅሙ በቀን 8 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን የፋብሪካው ዲዛይን ወደፊት በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar •

1817

ስኳር ኮርፖሬሽን በአዳዲስ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የስኳር ልማቱን የሚደግፉ የውኃ ግድብ፣ የመስኖ አውታር፣ የመሬት ዝግጅት፣ የመንገድ፣ የመብራት፣ የውኃና የስልክ አገልግሎት እንዲሁም መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ቤቶች ግንባታን ደረጃ በደረጃ ማከናወን ይኖርበታል፡፡ ተልዕኮውን ለማሣካት ኮርፖሬሽኑ በራሱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ ልማቱ ከሚካሄድባቸው ክልሎች ጋር በቅንጅት በመስራት ውጤት አስመዝግቧል፡፡ እንዲሁም ከተለያዩ የግል፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር የስራ ውል በመግባት ልዩ ልዩ ሥራዎችን እንዲሰሩ እያደረገ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚገነባቸው በሁሉም አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች የሚሰሩ መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ከአግሮስቶን ምርት የሚገነቡና ወጪ እና ጊዜን በመቆጠብ ረገድ እጅግ አዋጭ የሆኑ ናቸው፡፡ ይህም ኮርፖሬሽኑ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርና ከሚኒስቴር መ/ቤቱ አማካሪ ድርጅት ጋር በጋራ በመስራት ከአካባቢዎቹ ሁኔታ ጋር

ተስማሚ ዲዛይን ያላቸው ቤቶች ግንባታ ለማከናወን የቻለበት ውጤታማ ተግባር ነው፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ለመሰል ግንባታዎች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ እና ይባክን የነበረውን የግንባታ ጊዜ በእጅጉ መቀነስ ተችሏል፡፡

ኮርፖሬሸኑ የሚያስገነባቸው እነዚህ አስር አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በእርሻ፣ በፋብሪካ፣ በቤቶችና መስኖ ልማት ስራ ለሚሰማሩ ቁጥራቸው ከ500,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ተጨማሪ የስራ ዕድል ይፈጥራሉ፡፡

በአገሪቱ በሚገነቡ አስር አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች፣አንድ ጅምር ስኳር ፋብሪካ እና ንብረትነቱ ወደ ኮርፖሬሽኑ የተዛወረውን የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ እንዲሁም በነባር ስኳር ፋብሪካዎች ላይ በተከናወኑ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት በእቅድ አመቱ መጨረሻና ከዚያ በኋላ ባሉ ጥቂት ዓመታት ላይ የአገሪቱን የስኳር ምርት መጠን ከ300,000 ቶን ወደ 2,252,013 ቶን ለማሳደግ ታቅዶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው፡፡

Page 11: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

19 20

ወቅታዊ የስኳር ስርጭት ስልት

በመላ አገሪቱ የስኳር ስርጭት የሚከናወነው ንግድ ሚኒስቴርና ስኳር ኮርፖሬሽን በሚመድቡት ኮታ አማካይነት ሲሆን ስርጭቱ የሚከናወነው በሦስት መንገዶች ነው፡፡ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡-

በአሁኑ ወቅት ስኳር ለአዲስ አበባ ተጠቃሚዎች የሚሰራጨው የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኮታ በመደበላቸው የሸማቾች የሕብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት በራሳቸው ሱቅና ለቸርቻሪ ነጋዴዎች በማሰራጨት ነው፡፡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስኳር የሚያገኙት በኢትፍሩት አማካይነት ነው፡፡

የስኳር ስርጭት ስልት በአዲስ አበባ

በክልሎች ስኳር ለተጠቃሚዎች የሚሰራጨው በጅንአድ አማካይነት ወደተመረጡት ማሰራጫ ከተሞች ከተጓጓዘ በኋላ የየክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮዎች መርጠው በሚያቀርቧቸው ጅምላ ነጋዴዎች በኩል ለቸርቻሪ ነጋዴዎች በማሰራጨት ነው፣

የስኳር ስርጭት ስልት በክልሎች

ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች ስኳር የሚያገኙት ደግሞ ንግድ ሚኒስቴርና ኮርፖሬሽኑ በኮሚቴ በጥናት የመደቡላቸውን የስኳር መጠን (ኮታ) ነው፡፡ ሁሉም በስርጭቱ የሚሳተፉ አካላት ስኳር የሚያከፋፍሉት ከኮርፖሬሽኑ የስኳር መጋዝኖች በመረከብ ነው፡፡

የስኳር ስርጭት ለልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች

Page 12: የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006

• w

ww

.ets

ugar

.gov

.et |

| ww

w.fa

cebo

ok.c

om/e

tsug

ar •

ተወ

ዳዳ

ሪ የስ

ኳር

ኢንዱ

ስትሪ

መገን

ባት! |

| Bui

ldin

g Co

mpe

titi

ve S

ugar

indu

stry

!

21 22

የስኳር ኮርፖሬሽን ወቅታዊ አደረጃጀት

ስኳር ኮርፖሬሽን በአንድ ዋና ዳይሬክተር የሚመራ በርካታ የሥራ ዘርፎች ያሉት ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም ነባር ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም ጅምር እና አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን የሚመራ ተቋም ነው፡፡ የዋና መስሪያ ቤቱን አደረጃጀት በተመለከተ በ2004 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ ተጠናቆ ተግባራዊ በተደረገው የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) መሠረት በምክትል ዋና ዳይሬክተሮች የሚመሩ አስራ አንድ ዘርፎች አሉት፡፡ ከ2005 ዓ.ም መጨረሻ ወራት ጀምሮም የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ተቋቁሞና ኃላፊም ተሾሞለት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ የጽሕፈት ቤቱና የዘርፎቹ ተግባርና ኃላፊነትም የሚከተለው ነው፡-

1.የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤትበዋና ዳይሬክተሩ ተለይተው የሚሰጡ ልዩ ክትትል የሚያስፈልጋቸውን ስራዎች (ስፔሻል አሳይመንትስ) መከታተልና ማስፈጸም፣ የሥራ አመራር ስብሰባዎችን ማቀድ፣ ማስተባበርና ማስፈጸም፣ ለዘርፎች በጋራ የተሰጡና ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ሥራዎች መከታተል፣ ማስተባበርና ስለአፈጻጸማቸው ሪፖርት ማቅረብ፣

2.የመስኖና ቤቶች ግንባታ ዘርፍ በነባርና አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ኮርፖሬሽኑ የሚያካሄደውን የመስኖ እና የቤቶች ግንባታ ማከናወን፣ የጥገና አገልግሎት መስጠትና የአካባቢ ጥበቃ ስራ ማከናወን እና መምራት፣

3.የኦፕሬሽን ዘርፍበነባርና አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የእርሻ እና የፋብሪካ ኦፕሬሽን ስራዎች ላይ ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር ማድረግና መምራት፣

4.የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍበነባር እና አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የሚገኙ የሸንኮራ አገዳ አብቃዮችና አነስተኛ ተቋማትን ማደራጀት፣ ማስተባበርና መከታተል፤ ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሕዝብ ግንኙነት፣ የካሳ ክፍያ፣ የመልሶ ማቋቋም እና የመሬት ርክክብ ስራዎችን መምራትና ማስፈጸም፣

5.የግብይት ዘርፍበስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ላይ የገበያ ጥናትና የፕሮሞሽን ስራ ማከናወን፣ የአገር ውስጥ ስርጭትን መምራትና ማከናወን፣ የውጭ ግብይትና የሎጅስቲክ ማኔጅመንት ስራ ማከናወን፣

6.የምርምርና ስልጠና ዘርፍበሸንኮራ አገዳ አመራረት እና ተያያዥ ስራዎች ላይ ምርምር

የማካሄድ፣ ለሸንኮራ አገዳ ዝርያ ዴቨሎፕመንት የምርምር ስራዎችን ማከናወንና መምራት፣ በስኳር ቴክኖሎጂ ዙሪያ የምርምር ስራዎችን መምራትና ማከናወን፣ የስልጠና እና ስርጸት ስራዎችን መምራትና ማስፈጸም፣

7.የዕቅድና ፕሮጀክት ዘርፍየኮርፖሬት ፖሊሲዎችን እና ስትራተጂክ ዕቅዶችን ማዘጋጀት፣ የኦፕሬሽን ዕቅድ፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን መምራትና ማስፈጸም፣ የጥናትና ፕሮጀክት ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ማከናወን፣

8.የሰው ሀብት ልማትና አመራር ዘርፍየሰው ሀብት አመራርና አስተዳደር ስራዎችን መምራትና መፈጸም፣ የሰራተኛና ኢንዱስትሪ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ተግባራትን መምራትና ማከናወን፣ የሰው ሀብት ልማትና አሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ መምራትና ማስፈጸም፣

9.የፋይናንስ ዘርፍ

የፋይናንስ እና ተያያዥ ስራዎችን ማከናወን፣ የፋይናንስ ቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን እና የፈንድ አስተዳደር ስራዎችን መምራትና መፈጸም፣ የትሬዠሪ ማኔጅመንት ስራዎችን መምራትና መፈጸም፣

10.የአገዳ ተክል ልማት እና ፋብሪካ

ግንባታ ዘርፍበነባር እና አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች የሚካሄዱ የአገዳ ተክል ልማት እና የፋብሪካ ግንባታ ስራዎችን መምራት እና ማስፈጸም፣

11.የኮርፖሬት ካይዘንና የለውጥ ሥራ አመራር ዘርፍ

የትራንስፎርሜሽን ሥራ አመራር ለውጥ ሥርዓት በመዘርጋት መምራትና ማስፈጸም፣ የካይዘን ትግበራን በመከታተል፣ በመቆጣጠርና ማስፈጸም፣ የለውጥ ፕሮግራም ዲዛይን ማድረግና ማስተዋወቅ፣ የለውጥ ፕሮግራም ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀትና እንዲተገበር ማድረግ እና በለውጥ ፕሮግራም የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ማስፈጸም፣

12.የግዢና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ የግዢ፣ የንብረትና የፋሲሊቲ አስተዳደር ስራዎችን መምራትና ማከናወን፣

የስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ፡- ዳይሬክተር - መድኩን ተክሌ ሞባይል- +251-913539694 ቢሮ- +251-11 552 74 75 የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ስልክ ፡ +251 11 552 66 53/67 ፖስታ - 20034 የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

[email protected] || www.facebook.com/etsugar

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ