12
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) www.montgomeryschoolsmd.org የሃይማኖት ብዝሃነት/RELIGIOUS DIVERSITY 2019–2020 ስለማክበር መመሪያ አማርኛ/Amharic Rockville, Maryland

2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

  • Upload
    others

  • View
    7

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)

www.montgomeryschoolsmd.org

የሃይማኖት ብዝሃነት/RELIGIOUS DIVERSITY

2019–2020ስለማክበር መመሪያ

አማርኛ/Amharic

Rockville, Maryland

Page 2: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

ራእይ

ለእያንዳንዱና ለማንኛውም

ተማሪ እጅግ የላቀውን ህዝባዊ

ትምህርት በማቅረብ መማርን

እናበረታታለን።

ተልእኮ

እያንዳንዱ ተማሪ በኮሌጅ

እና በሥራ መስክ ውጤታማ

እንዲሆን/እንድትሆን፣

በአካደሚክስ፣ ችግር

የመፍታት ዘዴ/ ብልሃት

ፈጠራ፣ እና የማህበራዊ

ስሜት ክህሎቶች ይኖሩታል/

ይኖሯታል።

ዋና ዓላማ

ሁሉንም ተማሪዎች የወደፊት

ህይወታቸው እንዲዳብር/

እንዲበለጽግ ማዘጋጀት፡፡

ዋነኛ እሴቶች

መማር/እውቀት

ግንኙነቶች

አክብሮት

ልቀት

ፍትኃዊነት/ሚዛናዊነት

Board of Education የትምህርት ቦርድ

Mrs. Shebra L. Evans ወ/ሮ ሸብራ ኤል. ኢቫንስ President ፕሬዚደንት

Mrs Patricia B. O’Neill ወ/ሮ ፓትሪሻ ቢ ኦኔይል Vice President ም/ፕሬዚደንት

Ms. Jeanette E. Dixon ሚስ ጃኔት ኢ. ዲክሰን Dr. Judith R. Docca ዶ/ር ጁዲት አር. ዶካ Ms. Karla Silvestre ሚ/ስ ካርላ ሲልቨስትሪ

Mrs. Rebecca K. Smondrowski ወ/ሮ ርብቃ ኬ. ስሞንድሮውስኪ Ms. Brenda Wolff ሚስ ብረንዳ ዎልፍ Mr. Nathaniel Tinbite አቶ ናትናኤል ትንቢተ Student Member የተማሪ አባል

Montgomery County Public Schools (MCPS) Administration የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አስተዳደር

Jack R. Smith, Ph.D. ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር) Superintendent of Schools የት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ

Monifa B. McKnight, Ed.D. ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. መክናይትም/ሱፐርኢንተንደንት

Maria V. Navarro, Ed.D. ማሪያ ቪ. ናቫሮ የትም/ዶክተር Chief Academic Officer የአካደሚ ዋና ኃላፊ

Kimberly A. Statham, Ph.D. ኪምበርሊ ኤ. ስታተም (ዶ/ር) Chief of School Support and Improvement የትምህርት ቤት ድጋፍ እና መሻሻል ዋና ኃላፊ

Andrew M. Zuckerman, Ed.D. አንድሪው ኤም. ዙከርማን (ዶ/ር) Chief Operating Officer ዋና የሥራ ኃላፊ

850 Hungerford DriveRockville, Maryland 20850www.montgomeryschoolsmd.org

Page 3: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

MARYLAND ሜሪላንድ

ውድ ወዳጆች፡-

የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የማህበረሰባችንን ብዙሃነት የሚያቅፍ እና እያንዳንዱ ተማሪ ለስኬትና ለብልፅግና እድል እንዲኖረው ለሚያረጋግጥ የመከባበርና ለርተአዊነት ባህል ቁርጠኝነት ቃል ገብቷል። ይህ ቁርጠኝነት በሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ ACA ላይ ተካቷል፣አድሎ የሌለበት፣ እኩልነት/ፍትህ፣ እና የዳበረ ባህላዊ ብቃት፣ ፍትሐዊነትን ለመፍጠር፣ ለመንከባከብ፣ እና ለማሳደግ፣ ሁሉን የሚያካትት እና ሁሉን መቀበል/በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው የማህበረሰባችንን የረዥም ጊዜ ጥረት የሚያረጋግጥ ነዉ። የዚያ ግዴታ በከፊል ተማሪዎቻችን የሃይማኖትና ሃይማኖት-የለሽ እምነቶች እና ልምምዶች፣ ከኣድልዎ፣ ማሸማቀቅ፣ ወይም ወከባ ነፃ በሆነ መንገድ የመግለፅ መብታቸውን ማረጋገጥ ነው። እንደ ት/ቤት ዲስትሪክት፤ ለእነዚህ እምነቶች እና ልምምዶች ሊተገበር የሚችል እና ተቀባይነት ያለው ማመቻቸት ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል።

ለዚህም ነው ይህን መመርያ ያዘጋጀነዉ። በዚህ ኣስፈላጊ ኣርእስት ትኩረት የሚያደርጉ በርካታ የቦርድ መመርያዎችና የMCPS ደንቦችና ሂደቶች ኣሉ። የሚጠበቁብን ለሰራተኞቻችን፣ ለተማሪዎቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ እና ለማህበረሰባችን ግልፅ እንዲሆኑ ይህን ሁሉ መረጃ ኣንድላይ በኣንድ ቦታ ላይ ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኖ ስለተሰማን ነው።

ይህን መመርያ ለመፍጠር ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የስራ ኣስፈፃሚ የእምነት ማህበረሰብ የስራ ቡድኖች እና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በቅርበት አብረን ሰርተናል፣ አጋርነታቸውንና ትብብራቸውንም እናደንቃለን። እነዚህ አጋርነቶች ስለትምህርት፣ ስለግንኙነቶች፣ ስለመከባበር፣ ስለልቀት፣ እና ስለፍትህ ያለንን ዋነኛ እሴቶቻችንና የገባነውን ኣደራ ጥልቀት ይሰጡታል።

ይህን መመርያ ትምህርታዊ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ ኣለን። ለሁሉም ተማሪዎቻችን ሰላማዊ፣ አወንታዊ፣ እና መከባበር የሰፈነባቸው የመማርያ አካባቢዎችን ለመፍጠር በምናደርጋቸው ጥረቶች በቀጣይነት ስለምታደርጉልን ድጋፎቻችሁ እናመሰግናችኋለን።

ከአክብሮት ጋር፣

Shebra L. Evans ሼራ ኤል. ኤቫንስPresident, Montgomery County Board of Education የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕረዚደንት

Jack R. Smith, Ph.D. ዶር. ጃክ ኣር. ስሚዝ Superintendent, Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክስኩልስ ዋና ተቆጣጣሪ

Page 4: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል
Page 5: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

1

መግቢያ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የኃይማኖት ብዙህነትን ማክበር

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎቻችንን ሃይማኖቶች፣ እምነቶች፣ እና ልምዶች ብዙሃነት መከባበርና አድናቆትን ለማስፈን በቁርጠኝነት ይሠራል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ብዙ ዓይነት ባህል አጅጉን ከላቁት ጥንካሬዎቻችን ኣንዱ እንደሆነና በት/ቤቶቻችን አብረን ስንማር ማኅበረሰባችንን ማበልፀግ አለበት ብሎ ያምናል። መከባበር የ MCPS ዋነኛ እሴት ነው፣ ስለሆነም፣ ሁሉም ቤተሰቦች አክብሮት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ባህል መኮትኮት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

አገራችንና የሜሪላንድ ስቴት ለሃይማኖት ነፃነት ጥበቃ እና በቤተክርስቲያን እና በመንግስት መለያየት ለሁለቱም ጥልቅና የቆየ ግዴታ ኣላቸው። የመጀመርያው የዩ.ኤስ. የህገ መንግስት ማሻሻያ አንቀጽ እንደሚለው፡- "ኮንግሬስ የሀይማኖት መቋቋምን የሚያከብር ምንም ኣይነት ህግ ኣያወጣም፣ ወይም የዚያኑ ነፃ ትግባሬ የሚከለክል..." ይህም ማለት መንግስት ኣንደኛውን ሃይማኖት ከሌላው በላይ ማራመድ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት-የለሽ ለይቶ መምረጥ፣ ወይም ጥላቻ መግለፅ ወይም ሃይማኖትን መቃወሞ ኣይችልም።

የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል የሃማኖትን ህዝባዊ ድጋፍ መስጠት ውድቅ እያደረጉ በሌላ በኩል የሁሉንም ተማሪዎች የሃማኖት ነፃነትን መብቶች መጠበቅ ኣለባቸው። ት/ቤቶች ሃይማኖትን ማራመድ ወይም ማደናቀፍ የለባቸውም፣ ተማሪዎችም በኮርሶች ወይም በት/ቤት ስፖንሰር በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ እንደ ምረቃ ወይም ስብሰባዎች በመሳሰሉ፣ የሃይማኖት እምነቶች ጥብቅና የማይደረግበት ኣካዴሚያዊ ኣካባቢ መብት ኣላቸው። በተመሳሳይ መልኩ፣ ተማሪዎች ለሃይምኖታዊነታቸው ወይም ሃይማኖት-የለሽነት እምነቶችና ልምዶቻቸዉ፣ ከኣድልዎ፣ ማሸማቀቅ፣ ወይም ወከባ ነፃ የሆነ መብት ኣላቸው፣ እናም MCPS ለነዚያ እምነቶችና ልምዶች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉና ተቀባይነት ያላቸው መገልገያዎች ለማድረግ ግዴታ ገብቷል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የስራ ኣስፈፃሚ የእምነት ማህበረሰብ የስራ ቡድን ጋር በመተባበር እነዚህን መመርያዎች የፈጠረው፣ ተማሪዎች በት/ቤት ውስጥ እና በት/ቤት ስፖንሰር በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ባሉበት ወቅት ስለ ሃይማኖት መመርያዎች ኣዘውትረው ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ነው። ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኛችሁት ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ መመርያ ውስጥ ስላለ ማንኛውም ነገር ጥያቄ ካላችሁ፣ እባካችሁ በቅድሚያ ከት/ቤታችሁ ኣስተዳዳሪዎች ጋር ተነጋገሩ። ሌላ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉዎት፣ የ MCPS Office of the Chief of Staff, Student Welfare and Compliance በስልክ ቁጥር፦ 240-740-3215፣ ወይም [email protected] ያግኙ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩል (MCPS) የሥራ ባልደረቦች ጥያቄዎን ለመመለስ ካልቻሉ የትምህርት ቦርድ የሠራተኞች ኃላፊን/Board of Education Chief of Staff/Ombudsman በስልክ ቁጥር፦ 240-740-3030፣ ወይም [email protected] ለማግኘት ይችላሉ።

እነዚህ መመርያዎች የተተለሙት፣ በነዚህ ርእሶች ዲስትሪክቱን የሚመሩትን በርካታ የሞንትጎመሪ ካውንቲ (Montgomery County) የትምህርት ቦርድ መመርያዎች እና የMCPS ደንቦች፣ እንዲሁም የስቴትና የፌደራል ህጎችን በሚመለከት፣ ፈጣን ማጣቀሻ ለመስጠት ነው። እነዚህ ህጋዊ ግዴታዎች ሊለውጡ የሚችሉ ናቸው እናም በዚህ ህትመት ከተጠቀሱት መግለጫዎችና ማጠቀሻዎች ይልቅ የበላይነት እንዳላቸው እባክዎ ይገንዘቡ። ተጨማሪ መረጃ በእኛ ድረገጽ፣ www.montgomeryschoolsmd.org ይገኛል።

ፈጣን የማጣቀሻ መመርያ

ዘወትር የሚቀርቡ ጥያቄዎችየኃይማኖት በአላትን ለማክበር ተማሪዎች ሲቀሩ ይቅርታ ይደረግላቸዋል ወይ? አዎ ቤተሰቦች ቀሪዎችን ለማሳወቅና ለመሰነድ ሁሉንም መደበኛ ሂደቶች መከተል አለባቸው። ለተጨማሪ መረጃ በኃይማኖት በዓላት ምክንያት መቅረት የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 2) እባክዎ ይመልከቱ።

ተማሪዎች በበአላት ምክንያት ሲቀሩ ለተጓደለ ስራ መተካት ይችላሉ ወይ? አዎ ቤተሰቦች ለተጓደለ ስራ ማካካሻ ለማሳካት ከልጃቸው ት/ቤት ጋር አብረው መስራት አለባቸው። ይበልጥ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባካችሁ ለሃይማኖት በዓላት መቅረት የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 2) ተመልከቱ።

ተማሪዎች በትምህርት ቀን ፀሎት ማድረግ ይችላሉ ወይ? እዎን፣ በተወሰኑ ሁኔታዎች። ለልዩ ተጨማሪ መረጃ እባካችሁ ፀሎትና ሃይማኖታዊ ኣለባበስ የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 3) ተመልከቱ።

ተማሪዎች ከሃይማኖታቸው ጋር የተዛመደ ልብስ መልበስ ይችላሉ ወይ? አዎ በቦርድ መመርያና በ MCPS ደንቦች መሰረት፣ ተማሪዎች ስካርቮች፣ ሂጃቦች፣ ያርሙልኮች፣ ፓትካዎች፣ ወይም ሌላ ከሃይማኖታቸው ጋር የተያያዘ ልብስ መልበስ ይችላሉ። ስለልዩ ተጨማሪ መረጃ እባካችሁ ፀሎትና ኃይማኖታዊ ኣለባበስ የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 3) ተመልከቱ።

በት/ቤት ስራዎች የሀይማኖት ርእሶች መወያያ ሊሆኑ ይችላሉ ወይ? አዎ ተማሪዎች የስራ ግዴታዎችን እስካሟሉ ድረስ፣የሃይማኖት እምነታቸውን ወይም ሃይምኖት-

Page 6: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

2

የለሽነታቸውን በት/ቤት ስራዎች መግለፅ ይችላሉ ለርእሱ ተፈላጊ እስከሆነና አግባብነት እስካለዉ ድረስ፣ እናም በዚህ መመርያ ላይ የተገለጹትን ሌሎች መመርያዎች እስከተከተሉ ድረስ። በተጨማሪ፣ በስነፅሁፍ፣ ታሪክ፣ እና በኪነጥበባት ውስጥ ስለ ሀይማኖት ያልተዛቡና ሀቀኛ ትምህርቶች የስርአተትምህርት አካል ሊሆኑ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ ሃይማኖት በትምህርት ፕሮግራም ውስጥ የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 3) እባክዎ ይመልከቱ።

ት/ቤቶች የተማሪዎችን ሀይማኖት-ነክ የአመጋገብ ማእቀቦችን ያስተናግዳሉ ወይ? አዎ ት/ቤቶች ከሀይማኖት ጋር የተያያዙ የአመጋገብ ገደብ ካለቸው ተማሪዎች ጋር ያለማቋረጥ ይሰራሉ። ለተጨማሪ መረጃ ምግብና የሃይማኖት ስነ ስርኣትየሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 5) እባካችሁ ተመልከቱ።

ተማሪዎች የሀይማኖት የመረጃ ቁሳቁሶችን ማሰራጨት ይችላሉ ወይ? አዎ ተማሪዎች የሃይማኖት የመረጃ ቁሳቁሶችን ልክ እንደሌሎች ከት/ቤት እንቅስቃሴዎች ጋር ያልተያያዙ የመረጃ ቁሳቁሶች ደንቦች መሰረት ማሰራጨት ይችላሉ ። ተማሪዎች ቁሳቁሶች የት፣ መቸ፣ እና እንዴት እንደሚሰራጩ የት/ቤት ህጎችን ማክበር ኣለባቸው። ለተጨማሪ መረጃ እባካችሁ የሃይማኖት መረጃ ቁሳቁሶች ስርጭትየሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 5) ተመልከቱ።

ሀይማኖታዊ ከትምህርት ውጭ ክበቦች በት/ቤት ይፈቀዳሉ ወይ? አዎ አንደ ሌሎች በት/ቤት ከሚቀርበው ኣርእስት ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው የተማሪ ከትምህርት-ጊዜ-ውጭ ቡድኖች፣ ተማሪዎች ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ ክበቦች የማደራጀት ወይም ተሰብስቦ የሃይማኖት ስብሰባዎች፣ የፀሎት ቡድኖች፣ ወይም ሌሎች ሃይማኖታዊ ልምዶችን ከትምህርት-ጊዜ-ውጭ የማክበር መብት ኣላቸው። እነዚህ ሃይማኖት-ነክ ከትምህርት-ጊዜ-ውጭ ስብሰባዎች ወይም ክበቦች በተማሪዎች የሚመሩ መሆን ኣለባቸው። ለተጨማሪ መረጃ እና ልዩ መመርያ፣ እባካችሁ ከስርእተትምህርት ውጭ የተማሪ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች የሚለውን የነዚህን መመርያዎች ክፍል (ገፅ 6) ተመልከቱ።

በሃይማኖት በኣላት ምክንያት ቀሪዎች

ክትትል እና የሃይማኖት በዓላትን ለማክበር መቅረትበየእለቱ በት/ቤት ተገኝቶ ክትትል ማድረግ ለተማሪ ስኬት ወሳኝ ነው። ቢሆንም፣ ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች፣ የሃይማኖት በዓላትን ለማክበር ጨምሮ፣ ኣልፎ ኣልፎ ከት/ቤት እንደሚቀሩ MCPS ይገነዘባል። አነዚህ የተፈቀዱ መቅረቶች ናቸው፣ ተማሪዎችም ለጎደሉ ስራዎች መተኪያ አንዲያደርጉ ይፈቀድላቸዋል። ተማሪዎች ከት/ቤት ከቀሩ፣ ትቤት ከተመለሱበት በሶስት ቀኖች ውስጥ የፅሁፍ ማብራርያ የሚሰጥ ማስታወሻ ከወላጅ/ኣሳዳጊ ማምጣት ኣለባቸው።

ሃይማኖታዊ በዓል ከማክበር ጋር በተያያዘ ምክንያት ዘግይቶ መምጣት ወይም አስቀድሞ ለመለቀቅ ተቀባይነት ያላቸውን ጥያቄዎች MCPS ያስተናግዳል፣ ነገር ግን በወላጅ/አሳዳጊ መፈቀድ አለባቸው።

ምንም እንኳን ማንኛውም የኣትሌቲክ ክውነት ወይም ልምምድ ተሳትፎ በኣብዛኛው በክውነቱ ወይም በልምምዱ እለት ኣትሊቶቹ የተመደበላቸውን የትምህርት ፕሮግራም እንዲከታተሉ ተፈላጊ ቢያደርገውም፣ እንደ የሃይማኖት በኣል ኣከባበር የመሰሉ ኣስቀድመው የተመደቡ እንቅስቃሴዎች ያሏቸው ተማሪዎች አስቀድመው ከት/ቤታቸው ፈቃድ እስካገኙ ድረስ፣ በኣትሌቲክ ክውነቶች ወይም ልምምዶች በቀሪው ቀን እንዲሳተፉ ይፈቀድላቸዋል።

ነፃ የሃይማኖት ኣምልኮ የህገ መንግስት መብት ስለሆነ፣ ፍፁምነት ላለው የትምህርት ክትትል ሽልማት ያላቸው የMCPS ት/ቤቶች መቅረቶቻቸው ለተፈቀዱላቸው ለሃይማኖት በኣላት ብቻ ለሆኑ ተማሪዎች ሽለማቶቹን ላይከለክሉ ይችላሉ።

• ለተጨማሪ ዝርዝሮች፣ የMCPS ደንብ JEA-RA፣ የተማሪ ክትትል፣ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy/pdf/jeara.pdfን ተመልከቱ።

ከሃይማኖት በኣላት ማክበር መቅረት በኋላ የመተኪያ ስራተማሪዎች ከት/ቤት በመቅረታቸው ላልሰሩት ስራ ሃላፊነት ኣለባቸው ባጠቃላይም እንዲተኩ ይጠበቅባቸዋል። የሃይማኖት በኣላት ሲያከብሩ የሚያመልጣቸውን ለመተካት መራዘሚያዎች ወይም ሌላ መገልገያዎች ለማሳካት ኣስቀድመው ፕላን ማድረግ ለተማሪዎችና ለወላጆች/ኣሳዳጊዎች የተሻለው ኣማራጭ ነው። ቢሆንም፣ MCPS ይህ ሁልጊዜ ተግባራዊ ነው ወይም ሊሆን ይችላል ማለት እንዳልሆነ ይገነዘባል። ቀሪነቱ ፈቃድ ካለው፣ የተማሪው/ዋ መምህር ያመለጠውን ጊዜ ለመተካት ተማሪው(ዋ)ን ያግዘዋል/ታግዘዋለች/ያግዛታል/ታግዛታለች፣ ዳግመ-ፈተና ያቀርባል/ታቀርባለች፣ ወይም በተማሪው/ዋ የሃይማኖት በኣል ሲከበር መፈፀም ለነበረበት የክፍል ስራ ወይም የቤት ስራ ማራዘሚያ ጊዜ መስጠት። እያንዳንዱ ሁኔታ አንድ ባንድ መታየት እንዳለበት የተጠበቀ ሆኖ፣ ከተፈቀደ የሀይማኖት በአል ለማክበር መቅረት በኋላ ተማሪዎች እስከ ሶስት የትምህርት ቀኖች ለመተኪያ የማራዘም ብቃት ይኖራቸዋል።

በተጨማሪ፣ የቤት ስራ ሲሰጡ፣ ት/ቤቶች ለማህበረሰባችን አባላት ኣስፈላጊ የሆኑትን ባህላዊ፣ የዘር፣ የሃይማኖት፣ እና ሌሎች በዓላት ወይም ክውነቶች ግንዛቤ ውስጥ እንዲያስገቧቸው ያስፈልጋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ በድረገጽ ላይ፦ www.montgomerycountymd.gov/mcg/commemorations.html. የሚገኙ፣ የሃይማኖታዊ፣ የዘር፣ እና ከካውንቲ ነዋሪዎች ባህላዊ ቅርስ ጋር የተዛመዱ የተወሰኑ በዓላትን የሚያካትቱ፣ የሚከበሩ እለቶችን ዝርዝር አዳብሯል።

Page 7: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

3

በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ የሚገኘው የቀን መቁጠርያ Days of Commemoration/የክብረ በዓላት ቀኖችን የ MCPS የት/ቤት መዘጋት በመረጃነት በተጨማሪ፣ ለሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና የማህበረሰብ አባላት ማጣቀሻ እንዲሆኑ እንዲታዩ ያደርጋል። የቀን መቁጠርያው በ www.montgomeryschoolsmd.org/info/calendars/ ይገኛል።

ፀሎት እና ሃይማኖታዊ ልብስ

ፀሎት በት/ቤትእንቅስቃሴዎቹ በፍላጎት የሚካሄዱ፣ በተማሪ የተነሳሱ፣ እና የመማርያ ክፍል ትምህርትን፣ ሌሎች የት/ቤት አንቅስቃሴዎችን፣ ወይም የሌሎችን መብቶች በጣም ካልረበሹ ወይም ካላደናቀፉ በስተቀር፣ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን ለመፀለይና በሃይማኖታቸው ኣመለካከት ለመወያየት ነፃ ናቸው። ለምሳሌ፣ እንድ ተማሪ ከምግብ በፊት ወይም ከፈተና በፊት ኦፊሲየል ባልሆኑ ቦታዎች፣ እንደ ካፊቴርያዎች ወይም መተላለፍያዎች፣ ተማሪዎች ሃይማኖታዊ ባልሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ በተፈቀደላቸው መጠን፣ መፀለይ ወይም የሃይማኖት ፅሁፎችን ማንበብ ይችላል/ትችላለች፤ ወይም አንድ የተማሪ ኣትሊት ከውድድር በፊት ወይም የተችዳውን ወይም የጎል ግብ ካገኘ(ች) በኋላ ውድድሩን ከመጠን በላይ እስካላዘገየው ወይም እስካልረበሸ ወይም በሌሎች ኣትሊቶች ወይም ተመልካቾች መብቶች ጣልቃ እስካልገባ ድረስ መፀለይ ይችላል/ትችላለች። ምንም እንኳን ተማሪዎች የመፀለይ መብታቸውን በትምህርት ቀን ወይም ከት/ቤት በተያያዙ እንቅስቅሴዎች ማስከበር ቢችሉም፣ ሌሎችን በፀሎት፣ ስብከት፣ ወይም በሌላ የሀይማኖት እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ወይም እንዲያዳምጡ ማስገደድ፣ ማዋከብ፣ ወይም መገፋፋት አይችሉም። ለምሳሌ፦ በተማሪ-የተመሩ ፀሎቶች በት/ቤቱ የህዝብ ማስታወቂያ ስርኣት ለሁሉም ክፍሎች ማሰራጨት ኣይፈቀድም።

ኣንድ ተማሪ ለፀሎት የሚሆን ፀጥተኛ ቦታ ከጠየቀ/ች፣ ቦታ እስካለ ድረስ፣ የተማሪ ደህንነት ለማረጋገጥ የሚቆጣጠር ኣግባብ ያለው ሰራተኛ እስካለ ድረስ፣ እና የትምህርት ሂደት እስካልረበሸ ድረስ፣ ት/ቤቶች ጥያቄውን ለማስተናገድ ተገቢ ጥረት ያደርጋሉ። ይህም በሚድያ ማእከል፣ ባዶ የመማርያ ክፍል፣ ወይም በሌላ ክፍል ውስጥ ኣንድ የፀጥታ የተሞላበት ስፍራ ማለት ሊሆን ይችላል።

ተማሪዎች እና ወላጆች/ኣሳዳጊዎች መገንዘብ የሚኖርባቸው የ MCPS መምህራን፣ ኣስተዳዳሪዎች፣ እና ሌሎች ሰራተኞች የተማሪ ፀሎቶች ወይም ሌሎች የተማሪ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች በትምህርት ሰኣቶች ወይም በት/ቤት ስፖንሶርድ በሆኑ ክውነቶች ኣያደራጁም፣ ኣይመሩም፣ ኣያነሳሱም፣ ኣይደግፉም፣ ወይም በተግባር ኣይሳተፉም። በተማሪ ፀሎቶች ወይም ሌሎች በተማሪ የሚመሩ የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች የ MCPS ሰራተኞች ሊገኙ ይችላሉ ኣላማዎቹ ግን የተማሪንና የት/ቤት ደህንነት ለማረጋገጥ ለመከታተልና ቁጥጥር ለማድረግ ብቻ ነው።

የሃይማኖት ልብስ በሚከተሉት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር ተማሪዎች በኣለባበሳቸው ምክንያት ብቻ የዲሲፕሊን እርምጃ ኣይወሰድባቸዋም፡- • በት/ቤት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ረብሻ የሚያስከትል መስሎ ከታየ፣

• ለጤና ወይም ለደህንነት ኣስጊ ከሆነ፣ • የኮርስ ወይም የእንቅስቃሴ ተገቢ ግዴታ ማሟላት የሚሳነው ከሆነ፣

• ከወንበዴዎች ጋር ግንኙነት ካለው፣ • ሴሰኛ፣ ስድ፣ ፀያፍ፣ ወይም የሚያጋልጥ ወይም ፆታዊ ባህርይ ካለው፣ ወይም

• የትምባሆ፣ የኣልኮል፣ ወይም ሌሎች እፆች መጠቀምን የሚገፋፋ/የሚያደፋፍር ከሆነ።

አለባበሳቸው ከነዚህ መመርያዎች ጋር የሚስማማ እስከሆነ ድረስ፣ ተማሪዎች ከሀይማኖታቸው ጋር የተያያዙ ወይም የሀይማኖት መልእክት የያዙ ያንገት ሻሾች፣ ሂጃቦች፣ ያርሙልክስ፣ ፓትካስ፣ ወይም ሌላ ልብስ ወይም ጌጣጌጥ መልበስ እንዲፈቀድላቸው ይገባል።

በሚቻል ወቅት፣ በኣካል ማጠንከርያ ትምህርት ወቅት ወይም በት/ቤት ስፖንሰር በሚሆኑ እንቅስቃሴዎች የተወሰኑ ልብሶችን፣ ከሃይማኖት እምነታቸው ኣንፃር ኣስነዋሪ ሆኖ ከታያቸው፣ ለመልበስ ወይም ላለመልበስ ተማሪዎች (ወይም ለወላጅ/ኣሳዳጊ በነሱ ፈንታ) ፈቃድ ከጠየቁ ት/ቤቶች ተገቢ መስተንገዶ መስጠት ኣለባቸው። የዚህ አይነቶቹ መስተንግዶዎች/ማመቻቸቶች የተማሪን በአንድ እንቅስቃሴ መሳተፍ አይከለክሉም/አያግዱም። ለምሳሌ፣ የሜሪላንድ ህዝባዊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ኣቴሊቲኮች ማህበር በት/ቤቶች መካከል በሚካሄዱ ውድድሮች የሚሳተፉ ኣትሌቶችን "የራስ መሸፈኛ፣ ጥምጣም፣ ወይም ሌላ አስፈላጊ የሆኑ ሀይማኖታዊ ልብስ ለተጫዋች ወይም ለሌሎች ሻካራ፣ ጠንካራ፣ ወይም ኣደገኛ ያልሆነ፣ እናም በጨዋታ ጊዜ ተመንጥቆ እንደማይሄድ ሆኖ የተለበሰ እንዲለብሱ" ይፈቅዳል። የአትሌቲኮች መስተንግዶዎችን የሚመለከቱ ስለሌሎች ጥያቄዎች፣ እባካችሁ የት/ቤት አትሌቲክ ዳይሬክተር ወይም የ MCPS አትሌቲክ ክፍልን ያማክሩ።

ሃይማኖት በትምህርት ኣሰጣጥ ፕሮግራም ውስጥ

ሃይማኖት በት/ቤት ስራዎች ውስጥ መግለጫዎቻቸው ለኣርእስቱ ኣስፈላጊ እስከሆኑና የስራ ግዴታዎችን እስካሟሉ ድረስ ተማሪዎች የሃይማኖት እምነቶቻቸውን ወይም ኣለማመናቸውን በት/ቤት ስራዎች ለመግለፅ ነፃ ናቸው። በት/ቤት ስራዎች ግምገማ ላይ፣ መምህራን በተማሪዎች ስራ ውጤቶች ላይ ከሃይማኖት ይዘት በመነሳት ኣድልዎ ኣይፈፅሙም። የት/ቤት ስራ የሚመዘነው በመደበኛ ኣካዴሚያዊ መመዘኛዎችና በሌሎች ህጋዊ የትምህርት ጥቅሞች ነው። ለምሳሌ፣ ኣንድ ስራ ግጥም መፃፍን የሚያካትት ከሆነ፣ ተማሪ ያቀረበ/ችው

Page 8: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

4

በፀሎት መልክ የተፃፈ ግጥም ስራ (እንደ መዝሙረ ዳዊት ወይም ፒዩት/piyyut) በኣካዴሚያዊ መመዘኛዎች (እንደ የስነፅሁፍ ልቀት) ይገመገማል እንጂ በግጥሙ የሃይማኖት ይዘት በመነሳት ኣይ(ት)ቀጣም ወይም ኣይ(ት)ሸለምም።

በሃይማኖት ምክንያት ከትምህርት ፕሮግራም የመቅረት ፈቃድ ጥያቄዎችበተቻለ መጠን፣ በሃይምኖታዊ እምነቶቻቸው ላይ ትርጉም ያለው ጫና ይፈጥርብናል ብለው ከሚያምኗቸው ከተወሰኑ የመማርያ ክፍል ውይይቶች ወይም እንቅስቃሴዎች ይቅርታ እንዲደረግላቸው ከተማሪዎች፣ ወይም ከወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው ተማሪዎቻቸውን በመወከል፣ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ት/ቤቶች የትምህርት ፕሮግራሞችን ተቀባይነት ያላቸውና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚያስችሉ የማስተካከል ስራዎች ለመተግበር ሙከራ ማድረግ አለባቸው። ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው፣ እንቅስቃሴው የተማሪው(ዋ)ን ሃይማኖት በማመልከት የተማሪው(ዋ)ን ብቸኝነት የሚደፍር መሆኑን ካመኑበት፣ ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው ተማሪዎቻቸውን በመወከል፣ ከመማርያ ክፍሉ ለመቅረት እንዲፈቀድላቸው የመጠየቅ መብት ኣላቸው። አንድ/ዲት ተማሪ ከት/ቤት እንቅስቃሴዎች እንዲቀር/እንድትቀር ሲፈቀድለት/ላት፣ ተማሪዉ/ዋ ለት/ቤት እንቅስቃሴው ወይም ስራ ተለዋጭ ኣማራጭ ይሰጠዋል/ይሰጣታል።

እነዚህን መርሆች በመተግበር፣ተመሳሳይ የትምህርት ዓላማዎችን የሚያሟላ አማራጭ በመስጠት በሀይማኖታዊ መስኮች/ስፍራዎች አንድ የተለየ የጽሑፍ- ምንባብ ሥራ ላይ ተመርኩዞ ከተማሪዎች ወይም ከወላጆቻቸው/ሞግዚቶቻቸው የሚቀርብን ተቃውሞ ማስተናገድ ተገቢ ሊሆን ይችላል። ቢሆንም፣ ተነጥሎ የመቅረት ጥያቄዎች ከመጠን በላይ እየበዙ ወይም ከመጠን በላይ እየከበዱ ከመጡ፣ ት/ቤቱ ጥያቄዎቹን ማስተናገድ ሊቃወሙ ይችላል። ት/ቤቶች የተማሪን የሃይማኖት ልምድ ወይም እምነት ለማስተናገድ ብለው የትምህርት ፕሮግራም መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ፣ ወይም የተለየ የትምህርት ፕሮግራም ወይም ልዩ የትምህርት ኮርስ መፍጠር ኣይፈለግባቸውም። ለምሣሌ፦ ሙዚቃ የሜሪላንድ ስነጥበብ ሥርዓተትምህርት መሠረታዊ አካል ስለሆነ ኃይማኖትን መሠረት በማድረግ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ከየሙዚቃ ትምህርት እንዲታቀቡ ማድረግ አይጠበቅባቸውም፣ ነገር ግን በተቻለ መጠን በኃይማኖታዊ ተቃውሞ ምክንያት ትምህርቱን እንዲጫወቱ ወይም እንዲያዜሙ የሚጠበቅባቸውን ትምህርት ቤቶች ለማስወገድ ይችላሉ።

በት/ቤት ስለ ሃይማኖት ወይም ስለ ሃይማኖት በዓላት ማስተማር ት/ቤቶች ልጆች ከራሳቸው የተለዩ ባህሎችንና ቅርሶችን እንዲማሩና እንዲያደንቁ የሚችሉበት ኣካባቢ ማዳበር እንዳለባቸው MCPS ያምናል። በዚህ ኣላማም፣ የ MCPS ስርኣተትምህርት በስነፅሁፍ፣ በታሪክ፣ በሰብኣዊ ጥናቶች፣

እና በኪነጥበባት የሃማኖቶችን ሚና እውቅና ይሰጣል። እንዲያውም፣ የሃይማኖታዊ ተፅእኖዎችን ግንዛቤ ሳይሰጡ እነዚህን ርእሶች ማስተማር በጣም ኣስቸጋሪ ያደርገዋል። የ MCPS ስርኣተትምህርት በባለበርካታ ባህል ኣገር ውስጥ ሙሉ ዜግነትን ለማዘጋጀት በመንግስትና በሃይማኖት ነፃነት መካከል ስላለው ግንኙነት የተማሪዎችን ግንዛቤ በተጨማሪ ይገነባል። በተገኘ ቁጥር፣ የሃይማኖት ገፅታዎች ውይይት የሚደረግባቸው ስለ የሃማኖቶች ታሪክና ኣመዛዛኝ/comparative ጥናት የሚመረጡ/elective የክፍል ትምህርቶች ተማሪዎች መከታተል ይችላሉ።

ተማሪዎች ስለሃይማኖት ሲማሩ፣ መጠበቅ ያለባቸው የትምህርት እንቅስቃሴዎች ርተአዊ፣ ያልተዛቡ፣ እና ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ሆነ ኢሀይማኖታዊ እምነቶች የማያንቋሽሹ ናቸው። የህብረ-ብዙ ህብረተሰብ ኣይነተኛ ባህርይ የተማሪዎችን የተለያዩ እምነቶች ማክበር ነው። በመምህራን፣ ተማሪዎች፣ እና በእንግዳ ተናጋሪዎች የሚሰጡ ንግግሮች የተለዩ ሃይማኖታዊ ርእዮቶችን ከሌሎች ሃይማኖትዊ ወይም ኢሃይማኖታዊ ርእዮቶች ይሻላሉ ብሎ መስበክ ወይም ማቀንቀን የለባቸውም። ተማሪዎች ስለ ሃይማኖት ባህሎች ኣስተያየታቸውን ለማካፈል መምረጥ ወይም ላለመምረጥ ይችላሉ። ተማሪዎችም በበኩላቸው ለሃይማኖታዊ ልምዶች ቃል ኣቀባዮች ወይም ወካዮች እንዲሆኑ ኣንጠየቅም ብለው መጠበቅ ኣለባቸው። ለእንደዚህ ኣይነቱ ሁኔታ ተማሪዎችን ለይቶ ማውጣት ምቾት እንዳይሰማቸው ሊያደርግ ይችላል፣ እናም የአንድን ተማሪ የሃይማኖት ተሞክሮ የጠቅላላ ቡድን ወካይ ፈፅሞ መደረግ የለበትም።

እንደ የማስተማርያ መሳርያ ወይም መገልገያ፣ ት/ቤቶች የሃይማኖት ምስሎች/symbols ን እንደ የሃይማኖት ወይም ባህላዊ ናሙናዎች ኣድረገው ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህ የትምህርት መሳርያዎች ወይም መገልገያዎች መታየት ያለባቸው ኣግባብ ያለው የመማርያ ክፍል ትምህርት ለማጀብ ለጊዜያዊ ወቅት ብቻ መሆን ኣለበት።

የትምህርት ኣካል በማድረግ፣ ት/ቤቶች ስለሃይማኖታዊ በኣላት እንደ እለታዊ ሃቅ/factual manner ማስተማር ይችላሉ። የት/ቤት እንቅስቃሴዎች የበኣልን ኣለማዊ/መንፈሳዊ ያልሆኑ ገፅታዎችን ማንፀባረቅ ይችላሉ፣ ነገር ግን የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች በሃይማኖታዊ ልምድ ወይም ክውነት መሳተፍን ላያካትት ይችላል። የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው፣ ተማሪዎች ከተወሰኑ የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች ከመሳተፍ ይቅርታ እንዲደረግላቸው መጠየቅ ይችላሉ። መምህራን ጥያቄ ላቀረቡ ተማሪዎች ኣማራጭ እንቅስቃሴ በማዘጋጀት እነዚህን ጥያቄዎች ለማክበር መስራት ኣለባቸው። የልደት ቀኖች ወይም ብዙዎች ኣለማዊ ናቸው ብለው የሚገነዘቧቸው ሌሎች ወቅቶች፣ እንደ ሃሎዊን እና ቫሌንቲንስ ዴይ፣ በሌሎች እይታ የሃይማኖት ኣዝማሚያነታቸዉ ያመዝናል ተብለው ሊታዩ ይችላሉ። ት/ቤቶች በነዚህ ኣካባቢ እንቅስቃሴዎች ሊኖራቸው ይፈቀድላቸዋል—ኣለማዊ ጠባይ እስከያዙ

Page 9: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

5

ድረስ—መሳተፍ ለማይፈልጉ ተማሪዎችም ይቅርታ ሊያደርጉላቸው ይችላሉ።

ሃይማኖት በት/ቤት ስብሰባዎች እና በሙዚቃ በአላትልዩ የት/ቤት ክውነቶች፣ ስብሰባዎች፣ የሙዚቃ በአሎች፣ እና ፕሮግራሞች ኣለማዊና ያልተዛባ የትምህርት ፕሮግራም ለማራመድ መተለም ኣለባቸው እናም በኣንድ ሃይማኖት ወይም የሃይማኖት በኣል ማተኮር የለባቸውም። ለምሳሌ፣ የፕሮግራሙ ኣጠቃላይ መልእክት/effect ኢሀይማኖታዊ እስከሆነ ድረስ የሃይማኖት ሙዚቃ በዊንተር የሙዚቃ በኣል መቅረብ ይችላል፣ እናም ኢሃይማኖታዊ ሙዚቃ ሚዛናዊና ሁሉን የሚያካትት አካሄድ ኣካል ሆኖ በተጨማሪ ይካተታል።

ስብሰባዎች ወይም ፕሮግራሞች የተማሪ የሙዚቃ ጓዶች ወይም ሌሎች የሙዚቃ ቡድኖችን ሲያካትቱ፣ ተሳታፊ ተማሪዎች የሃይማኖት ሙዚቃ ማከናወን ከሃይማኖታቸው ኣንፃር ተገቢ ሆኖ ካልተሰማቸው ተቀባይነት ያለውና ሊከናወን የሚችል መስተንግዶ መጠየቅ ይችላሉ። የመስተንግዶ ጥያቄዎችን ሲያስተናግዱ፣ የት/ቤት ሰራተኞች ተማሪዎችን ከሚያሳፍር ሁኔታ፣ ወይም ከመጋጨት ለማዳን ከተማሪዎችና ከወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻችው ጋር መመካከር አለባቸው።

በስብሰባዎች የተማሪ ወይም የእንግዳ ተናጋሪዎች መመረጥ ያለባቸው ሃይማኖትን በማይደግፉ ወይም በማይቃወሙ በርትአዊ መስፈርቶች ተመስርቶ መሆን ኣለበት። የተማሪን ወይም የእንግዳ ተናጋሪን ኣስተያየቶች (ሃይማኖታዊ ይሁኑ ኣይሁኑ) ት/ቤቱ ይደግፋል በማለት ወደ ሌሎች ተማሪዎች፣ ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው፣ ወይም እንግዶች የሚተላለፈውን ኣስተያየት ለማስወገድ ት/ቤቶች ተገቢ፣ ነፃ የሆኑ ማስተባበያዎች ማድረግ ኣለባቸው። በተጨማሪ፣ ሃይማኖት-ነክ ርእሶች ወይም በኣላት የሚያካትቱ ስብሰባዎችና ሌሎች የት/ቤት ክውነቶች በት/ቤቶች ፕሮግራም እድሜ ታሳቢ እንደሚሆን ወላጆች/ኣሳዳጊዎች መገንዘብ ኣለባቸው። ምንም እንኳን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በርትአዊ መንገድ እንዲናገሩ የተመረጡ ተማሪዎች ወይም እንግዶች ኣስተያየቶችን ት/ቤት የማይደግፍ መሆኑን ሊገነዘቡ ቢችሉም፣ የመካከለኛና የኤሌሜንተሪ ተማሪዎች፣ የት/ቤት ሰራተኞች በኣግባቡ ማስተባበያ ቢሰጡም፣ ይህን ለመለየት መቻላቸው ኣጠራጣሪ ነው።

ምግብና የሃይማኖት በኣል

ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የምግብ አይነት ገደቦችና ፆም ተማሪዎች፣ ወይም ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው፣ አይማኖት-ነክ የኣመጋገብ ገደብና ፆምን ይሚያካትቱ ተቀባይነት ያላቸውና ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ መስተንግዶዎች እንዲያደርጉ ት/ቤቶችን መጠየቅ ይችላሉ። የMCPS የምግብና የኣመጋገብ ኣገልግሎቶች

ክፍል የኣመጋገብ ገደቦች ያሏቸው ተማሪዎች በምግቦች ተለጣፊ ማስታወቂያ በማድረግ/labeling food እና/ወይም ለቁርስ፣ ለምሳ፣ እና ለቅምሻዎች/snacks እንደ የኣሳማ ስጋ-ነፃ፣ የተለያዩ ኣማራጮች በማቅረብ ማገዝ ይችላሉ፤ ነገር ግን ት/ቤቶች የኣንድን ተማሪ ልዩ ሃይማኖታዊ ፍላጎቶችን ለማርካት ልዩ ምግቦች እንዲያዘጋጁ ኣይጠበቅባቸውም። ለተጨማሪ መረጃ፣ www.montgomeryschoolsmd.org ን ጎብኙ፤ ምግብንና የስነምግብ ኣገልግሎቶች መፈተሽ።

በተመሳሳዩ፣ በሃይማኖት ምክንያት የሚፆሙ ተማሪዎች፣ ተገቢ የሰራተኛ ቁጥጥር እስካለ ድረስ፣ በምሳ ሰኣት ከካፊቴርያ ይልቅ ወደ ሚድያ ማእከል ወይም ወደ ሌላ የተለየ ቦታ እንዲሄዱ ሊፈቀድላቸው ይችላል። በተጨማሪ፣ በሃይማኖት ምክንያት የሚፆሙና በኣካል ማሰልጠኛ ትምህርት ከከባድ እንስቃሴዎች ክመሳተፍ ይቅርታ እንዲደረግላቸው የሚጠይቁ ተማሪዎች መጠነኛ መስተንግዶ እንዲደረግላቸው ይገባል። ተማሪዎች የተጠየቀውን ከፆም ጋር የተያያዘ መስተንግዶ የሚለይ የፅሁፍ ማብራርያ የሚያቀርብ ማስታወሻ ከወላጅ/ኣሳዳጊ ወደ ት/ቤት ማምጣት ኣለባቸው።

የሀይማኖታዊ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ስርጭት

ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የመረጃ ቁሳቁሶች ለማሰራጨት የተማሪ ጥያቄዎችተማሪዎች ከት/ቤት ስርኣተትምህርት ወይም እንቅስቃሴዎች ጋራ ያልተያያዘ ሌላ መረጂያዊ ቁሳቁስ ለማሰራጭት በተፈቀደላቸው ተመሳሳይ ሁኔታዎች መሰረት ሃይማኖት-ነክ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ለት/ቤት ጓዶቻቸው ሊያሰራጩ ይችላሉ። ይህም ማለት ስርጭቱ በስንት ሰኣት ሊከናወን እንደሚችል፣ የት ቦታ እንደሚቻል፣ እና እንዴት ሊደረግ እንደሚችል ት/ቤቶች መደንገግ ይችላሉ፣ እነዚህ ጊዜ፣ ቦታ፣ እና የስነምግባር ገደቦች በሁሉም ከት/ቤት-ጋር-ባልተያያዙ የተማሪ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ፀንተው ተግባራዊ እስከሆኑ ድረስ ማለት ነው።

እነዚህ የጊዜ፣ ቦታ፣ እና የስርጭት ዘዴ ግዴታዎች በ MCPS ደንብና ህጎች ውስጥ ተንፀባርቀዋል -የተማሪዎች የሃይማኖታዊ መረጂያዊ ቁሳቁሶች ስርጭት፣ ልክ እንደ ፖለቲካዊ ቁሳቁሶች ወይም ሌላ ከት/ቤት-ጋር-ያልተያያዘ መረጂያዊ ቁሳቁስ፣ መከናወን ያለበት ከትምህርት ጊዜ ውጭ እና ረብሻ በማያካትት ሁኔታ ነው። ለምሳሌ፣ በእግር መንገዶችና በካፊቴሪያ፣ የተፈቀዱ ኮሪደሮች፣ ወይም የተማሪ አስተዳደር ክፍሎች ወይም መስኮች መረጂያዊ ቁሳቁሶች ለማሰራጨት ት/ቤቶች ለተማሪዎች ሊፈቅዱላቸው ይችላሉ። የሆነ ሆኖ፣ ተማሪዎች ከት/ቤት-ጋር ያልተያያዙ መረጂያዊ ቁሳቁሶች በመማርያ ክፍሎች፣ የሚድያ ማእከል፣ ወይም በሌሎች ት/ቤት ክፍሎች በትምህርት ቀን ማሰራጨት የለባቸውም፣ (ሀ) ክፍሉ እንደ የበጎ-ፈቃደኛ መሰብሰብያ ቦታ ተብሎ ጥቅም ላይ እስከዋለ ድረስ ወይም (ለ) መረጂያዊ ቁሳቁሱ መመርያ ክፍል ውስጥ እንደ መደበኛ ትምህርት

Page 10: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

6

ፕሮግራም አካል ወይም የበጎ-ፈቃደኛ መድረክ ወይም በተማሪዎች የተካሄደ ሴሚናር ካልሆነ በስተቀር። በተጨማሪ፣ ተማሪዎች ሀይማኖታዊም ሆነ ፀያፍ፣ ስም-አጥፊ፣ የትምህርት አካባቢ ረባሽ፣ ወይም በት/ቤት አካባቢ የሚገኙ የሌሎችን መብቶች የሚደፍሩ መረጂያዊ ቁሳቁሶችን በት/ቤት መቼት ማሰራጨት አይችሉም።

• ለተጨማሪ መረጃዎች፣ የ MCPS ደንብ JFA-RA፣ የተማሪ ሃላፊነቶችና ግዴታዎችን ይመልከቱ። www.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy/pdf/jfara.pdf

• ስለ ተማሪዎች ባልሆኑ የቁሳቁሶች ስርጭት መመርያዎች፣ የ MCPS ደንብ CNA-RA፣ የመረጂያዊ ቁሳቁሶች ማስታወቂያዎች ትርእይትና ስርጭት ተመልከቱ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy/pdf/cnara.pdf

• በተጨማሪ የሚመለከቱት፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ደንብ/MCPS Regulation KEA-RA፣ በፖለቲካ ዘመቻ መሣተፍ እና የዘመቻ ቁሳቁሶችን/ማቴሪያሎችን ማሠራጨት፦ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy/detail.aspx?recID=322&policyID=KEA-RA&sectionID=11

ከስርኣተትምህርት ውጭ የተማሪ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች

ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ ከስርኣተትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎችና ክበቦች ተማሪዎች ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት ውጭ ክበቦች ለማደራጀት ወይም ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች፣ የፀሎት ቡድኖች፣ ወይም ሌሎች የሃይማኖት ልምዶች ማክበር ትምህርት ከሚሰጥበት ጊዜ ውጭ የማካሄድ መብት ኣላቸው። እነዚህ ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት ውጭ ስብሰባዎች ወይም ክበቦች በተማሪዎች የሚመሩ መሆን ኣለባቸው። የ MCPS ሰራተኞች የተማሪና የት/ቤት ደህንነት ለማረጋገጥ ቁጥጥርና ክትትል ሊያቀርቡ ይችላሉ፣ ነገር ግን በነዚህ ከስርኣተትምህርት ውጭ ስብሰባዎች ወይም ክበቦች በሚካሄዱ ፀሎቶች ወይም ሌሎች ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ማደራጀት፣ መምራት፣ ማነሳሳት፣ መደገፍ፣ ወይም በተግባር መሳተፍ ኣይገባቸውም።

በተማሪዎች-መሪነት የሚካሄዱ ማናቸውም ኃይማኖታዊ የሆኑ፣ ተጨማሪ ሥርዓተ ትምህርት ክለቦች ወይም እንቅስቃሴዎችን በት/ቤት ክልል ውስጥ በቂ ቦታ ለማግኘት በቅድሚያ የ MCPS አስተዳደርን ማነጋገርና ማሳወቅ አለባቸው። ልክ እንደ ሌሎች ከስርኣተትምህርት ውጭ በት/ቤት ውስጥ ትምህርት ከሚሰጥበት ርእስ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሌላቸው የተማሪ ቡድኖች፣ የተማሪ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ለት/ቤት መገልገያዎች፣ መሳርያ፣ እና አገልግሎቶች እኩል መዳረሻ ኣላቸው። ይህም የማስታወቂያ ሰሌዳዎችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ እና የት/

ቤት ጋዜጣ ማስታወቂያዎችን ያካትታል፣ እንደዚህ አይነቱ መዳረሻ በት/ቤት ውስጥ ትምህርት ከሚሰጥበት ርእስ ጋር ግንኙነት ለሌላቸው የተማሪ ቡድኖች ተደርጎላቸው ከሆነ። እነዚህ ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት ውጭ ቡድኖች በት/ቤት የኣመት መፅሄት ትምህርት ከሚሰጥበት ርእስ ጋር ግንኙነት ለሌላቸው ለስርኣተትምህርት ውጭ ቡድኖች በተወሰነው ክፍል መዘርዘርም ይችላሉ።

ሃይማኖት-ነክ ከስርኣተትምህርት ውጭ ቡድኖች ኣልፎ ኣልፎ የውጭ ኣዋቂዎች ወይም የሃይማኖት መሪዎችን መጋበዝ ይችላሉ። ቢሆንም፣ በት/ቤቱ ተማሪዎች ያልሆኑ ግለሰቦች በተማሪ በተመሩ ከስርኣተትምህርት ውጭ ቡድኖች ፀሎቶች ወይም ሌሎች ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን ዘወትር መምራት፣ መከታተል፣ ወይም መቆጣጠር ኣይችሉም።

በተማሪ-የሚመሩ ቡድኖች፣ ሃይማኖታዊም ይሁኑ ኢሃይማኖታዊ፣ ኣካላዊ ጥቃት ወይም ጥላቻ የሚያራምዱ፣ በህገ-ወጥ እንቅስቃሴ የሚሳተፉ፣ ትርጉም ያለው ረብሻ በት/ቤት የሚቀሰቅሱ፣ የ MCPSን ፀረ-አድልዎ መመርያዎችን የሚጥሱ፣ ወይም በት/ቤት ኣካባቢ የሌሎችን መብቶች የሚደፍሩ ከሆነ በ MCPS ት/ቤቶች እንዲሰበሰቡ ኣይፈቀድላቸውም። የሆነ ሆኖ፣ የኣወዛጋቢና ውስብስብ ማህበራዊና ህጋዊ ጉዳዮችን ውይይት በማካተታቸው ምክንያት ብቻ ት/ቤቶች ተማሪዎችን ቡድኖች ከመመስረት መከልከል የለባቸውም።

ተማሪዎች በቅድመ- ወይም ድህረ-ትምህርት ክውነቶች ሃይማኖታዊ ይዘት ባላቸው ክውነቶች ልክ በሌሎች ከስርአተትምህርት ጋር ባልተያያዙ በት/ቤት ግቢ እንቅስቃሴዎች አንደሚደረገው መሳተፍ ይችላሉ።

የ MCPS ኣጠቃቀም በሃይማኖታዊ ድርጅቶች ንብረት በሆኑ መገልገያዎችሃይማኖታዊ ያልሆነ ኣማራጭ ቦታ የሚቻልና ለእንቅስቃሴ ወይም ተግባር ተቀባይነት ባለው ደረጃ ተስማሚ መድረክ ሆኖ እያለ በሃይማኖታዊ ድርጅቶች ንብረት በሆኑ ወይም በነሱ በሚንቀሳቀሱ መገልገያዎች ለት/ቤት-ነክ እንቅስቃሴዎች ወይም ተግባሮች ት/ቤቶች እንደማይጠቀሙበት ተማሪዎችና ወላጆቻቸው/ኣስዳጊዎቻቸው ማወቅ ኣለባቸው። ት/ቤቶች ማንኛውንም የግል ሃይማኖታዊ መገልገያን የዚህ ኣይነቱ መገልገያ ከማንም የሃይማኖት ኣስተምህሮዎች ገፅታ ጋር በመያያዙ በመመስረት ብቻ ኣይመርጡም ወይም ውድቅ ኣያደርጉም፤ እንዲያውም፣ እነዚህን ኣገልግሎቶች ለመምረጥ ለMCPS ቅርበት፣ የመገልገያው ተስማሚነት ለሚፈለገው ኣገልግሎት፣ ጤናና ደህንነት፣ ተመጣጣኝ ወጪ፣ እና መዳረሻን የመሳሰሉ ከሃይማኖት ነፃ የሆኑ መስፈርቶች ኣገልግሎት ላይ ይውላሉ።

ት/ቤት-ነክ የሆነ መገልገያ ወይም ተግባር በኣንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት ንብረት በሆነ ወይም በሚንቀሳቀስ መገልገያ ውስጥ ከተካሄደ፣ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው ት/ቤቱ መገልገያውን ከሃይማኖት ነፃ

Page 11: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

7

ለሆነ ኣላማ እንደሚጠቀምበት ይለያል፣ በተቻለ መጠን ደግሞ፣ ት/ቤት-ነክ እንቅስቃሴዎች በሚካሄዱበት ወቅት የሃይማኖት ምስሎች፣ መልእክቶች፣ ወይም የኪነጥበብ ስራዎች በክፍሎቹ እንደማይታዩ ያረጋግጣል። በተጨማሪ፣ የት/ቤት-ነክ እንቅስቃሴ ወይም ተግባር ተሳታፊዎች በሚያልፉባቸው ኣካባቢዎች የጎሉ ሃይማኖታዊ ምስሎች፣ መልእክቶች ወይም ኪነጥበባት መጋለጥን ለማስወገድ ወይም ለማሳነስ የተቻለ እርምጃ ሁሉ ይወሰዳል።

ህብረት በት/ቤቶችና በእምነት ማህበረሰቦች መካከል ልክ ከቢዝነሶችና ሌሎች የማህበረሰብና የሲቪል ቡድኖች ጋር እንደሚያደርገው፣ MCPS ከእምነት ህብረተሰብ ጋር ሽርክናዎችን ለመንከባከብና ለማዳበር ይሰራል። እያንዳንዱ የህብረተሰብ ኣካል ትምህርትን ለመደገፍ ሲሰባሰብ ተማሪዎችና ት/ቤቶች እጅግ በጣም ያተርፋሉ።

ማንኛውም የእምነት ማህበረሰብ ሽርክና ፕሮግራም የጠራ ኣለማዊ/መንፈሳዊ ያልሆነ ኣላማ እንዲኖረው ያስፈልጋል እናም ሃይማኖትን ማራመድ ወይም ማገድ የለበትም። ተማሪዎች እንዲሳተፉ የሚመረጡት፣ በማናቸውም ኃይማኖታዊ ቡድን አባልነት፣ወይም ማናቸውንም ኃይማኖታዊ እምነትን ስለተቀበሉ ወይም ስላልተቀበሉ፣ ወይም በማናቸውንም ዓይነት የኃይማኖት እምነት እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኞች መሆናቸውና ያለመሆናቸዉን መሠረት በማድረግ አይደለምም።

የእምነት ማህበረሰቦች በጎ-ፈቃደኞች የማንኛውም አጋርነት ዓላማ በተፈጥሮ ትምህርታዊና ኢሀይማኖታዊ/ዓለማዊ መሆኑን፣ እናም በጎ-ፈቃደኞች በኣንደኛ ማሻሻያ አዋጅ/First Amendment የተማሪዎችን መብቶች ማክበር እንዳለባቸው ማወቅ ኣለባቸው። በት/ቤት ስፖንሰር በሚደረግ እንቅስቃሴ በመምራት ወይም በመሳተፍ ላይ በሚገኙበት ወቅት በጎ-ፈቃደኞች ወይም ተሳታፊዎች በማንኛውም የእምነት ማህበረሰብ የጋራ ፕሮግራም ስለ ሃይማኖታቸው ለተማሪዎች መስበክ ወይም በሃይማኖታዊ አምልኮ መሳተፍ አይችሉም። የእምነት ማህበረሰብ ሽርክና ፕሮግራም በጎ-ፈቃደኞች እና ተሳታፊዎች በሌሎች የማህበረሰብ ድርጅቶች እንደሚደረገው ሁሉ በMCPS የመረጂያዊ ቁሳቁሶች ስርጭት ህጎችን መከተል ኣለባቸው።

ለሁሉም የመከባበር ባህልን ማዳበር/ማሳደግ

በሁሉም የ MCPS ማህበረሰብ መካከል የመከባበር ባህል እንዲዳብር ለመርዳት እነዚህ መመርያዎች ተዘጋጅተዋል። በማህበረሰቦች ውስጥ ካለው ከፍተኛ ብዙሃነት/diversity ጋር፣ የመከባበር፣ መቀባበልና የመቻቻል ባህል ሲኖር እርስ-በርሳችን የምንማረው በጣም ብዙ ይኖራል። ት/ቤቶቻችን ደጋፊና ምቹ የመማር ኣካባቢ ለመፍጠር ይሰራሉ፣ እናም ወላጆች/ኣሳዳጊዎች ከመምህራንና ከኣስተዳዳሪዎች ጋር የቤተሰቦቻቸውን ፍላጎቶች ሃይማኖታዊ እምነቶቻቸውንና ልምዶቻችውን ደጋፊ እንደመሆናቸው ለመገንዘብ በቅርብ እንዲሰሩ ይበረታታሉ።

ኣወንታዊና ክቡር የሆኑ ት/ቤቶችን ለመፍጠር ከምናደርገው ጥረት ኣካል፣ ተማሪዎች ሰላማዊ የመማርያ ኣካባቢ የማግኘት መብት ኣላቸው፣ ከማንኛውም ኣይነት ማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ እና ከማስፈራራት ነፃ የሆነ የተማሪው/ዋ ሃቀኛ ወይም የሚገመቱ የግል ባህሪዮች ላይ የተመሰረተ ማስፈራራት፣ ሃይማኖትን ጨምሮ። ኣመፅ የደረሰባቸው ተማሪዎች፣ ኣመፅ የሚፈፅሙ ተማሪዎች፣ እና ኣመፅ ቆመው የሚመለከቱ ተማሪዎች ለጤና፣ ደህንነት እና ለትምህርት ኣሉታዊ ውጤቶች ኣደጋዎች የተጋለጡ ናቸው። ማሸማቀቅን፣ ወከባን፣ ወይም ማስፈራራትን ለመከላከል እና ሲፈፀም በውጤታማነት ጣልቃ ለመግባት፣ እንዲሁም ማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት ዘገባ በሚያቀርቡ ላይ የበቀል እርምጃ የሚፈፅሙትን ለመከላከል MCPS ስርኣት-አቀፍ ኣቅርቦት ተልሞ ተግባራዊ ኣድርጓል። ማንኛውንም የዚህ ኣይነት ተግባሮች ለማስታወቅ፣ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው/ኣሳዳጊዎቻቸው ከት/ቤት ኣስተዳዳሪዎች ጋር ማናቸውንም ጉዳዮች ለመፍታት የ MCPS ን ቅጽ 230-35፣ Bullying, Harassment, or Intimidation Reporting Form/ማሸማቀቅ፣ ወከባ፣ ወይም ማስፈራራት ማሳወቂያ ቅጽ፣ በዚህ የሚገኘውን መሙላት፡- በ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/forms/pdf/230-35.pdf.

Page 12: 2019–2020...የዩ.ኤስ የበላይ ፍ/ቤት ት/ቤቶች ለሃይማኖት ገለልተኝነት እንዲኖራቸው ኣስምሮበታል። ት/ቤቶች ባንድ በኩል

ROCKVILLE, MARYLAND

ህትመት፦ Department of Materials Management for the Office of Student and Family Support and Engagementትርጉም፦ የቋንቋዎች ትርጉም አገልግሎት ክፍል

Language Assistance Services Unit • Department of CommunicationsCopyright © 2019 Montgomery County Public Schools, Rockville, Maryland

1360.19 • Editorial, Graphics & Publishing Services • 7/19 • NP

የሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የፀረ-መድሎ መግለጫ MCPS Nondiscrimination Statement

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ዘርን፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ የዘር ሃረግ፣ የብሔር ማንነት፣ ኃይማኖት፣ የስደተኝነት ሁኔታ፣

ጾታ፣ ስነ-ጾታ፣ የጾታ ማንነት (gender identity)፣ የጾታ አገላለጽ (gender expression)፣ የጾታዊ ግንኙነት ዝንባሌ/ምርጫ (sexual

orientation)፣ የቤተሰብ/የወላጆች የኑሮ ደረጃ/አቋም/ሁኔታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ እድሜ፣ ድህነት፣ እና የማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ አቋም፣

ቋንቋ፣ የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳተኝነት፣ በህገመንግስት ጥበቃ የተደረገላቸው ሁኔታዎችን ባህሪያትን ወይም ተዛማጅነት ያላቸውን

(affiliations) መሠረት ያደረገ ሕገ-ወጥ አድሎ/መድሎ ይከለክላል። መድሎ ወይም አድሎአዊነት፤ በሕብረተሰባችን ለረዥም ጊዜ

እኩልነትን፣ ፍትሕ፣ አብሮነት፣ሁሉን አቀፍነትን፣ ለመፍጠርና ለማሳደግ/ለመንከባከብ፣ ሲደረግ የቆየ ትጋትን ይሸረሽራል/ያበላሻል።

አድልዎ የሚከተሉትን የተወሰኑ ምሳሌዎችን ያካትታል፦ጥላቻ፣ ሁከት፣ ደንታቢስነት፣ ወከባ፣ ማስፈራራት፣ ማሸማቀቅ፣ ንቀት፣ ወይም

ማጥቃት። የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ደምብ/Policy ACA ስለ ጸረ-መድሎ፣ ፍትህ፣ የዳበረ

ባህል ይመርምሩ። ይህ መመርያ እያንዳንዱ ተማሪ አስፈላጊ/ተፈላጊ መሆኑ(ኗ)ን፣ በተለይም የትምህርት ውጤቶች የሚረጋገጡት በምንም

ዓይነት ግለሰብ ባለበት(ባለባት) ምክንያት ወይም ይሆናል ተብሎ የሚገመት ግላዊ ጠባዮች የሚተነበዩ አለመሆናቸውን የቦርዱን እምነት

ያረጋግጣል። ፖሊሲው በቅድሚያ መወሰድ ስላለባቸው የፍትህ እርምጃዎች የተዛባ አመለካከትን፣ ማረጋገጫ የሌላቸው የማዳላት/ልዩነት

አፈጻጸሞችን የሚያስከትሉትን አሉታዊነት፣ የትምህርት እና የሥራ መቀጠር እኩልነትን የሚያሰናክሉ መዋቅራዊ እና ድርጅታዊ አሠራር

ደንቃራዎችን በተለይ ያስገነዝባል።

በMCPS ሰራተኛ* ላይ ስለደረሰ መድሎዎ ጥያቄዎች ወይም ቅሬታዎች ለማቅረብ

በMCPS ተማሪዎች ላይ የአድልዎ ጥያቄዎች ወይም ቅሬታዎች ካላችሁ*

የሰራተኛ ተሳትፎ እና የሥራ ግንኙነት ጽ/ቤትየአፈጻጸም እና የክትትል/የምርመራ መምሪያ Department of Compliance and Investigations 850 Hungerford Drive, Room 55Rockville, MD [email protected]

Office of the Chief of StaffStudent Welfare and Compliance850 Hungerford Drive, Room 162Rockville, MD 20850240-740-3215COS–[email protected]

* ክትትል፣ ቅሬታ/ስሞታ፣ ወይም ስንክልና ላለባቸው ተማሪዎች አመቺ ስፍራ ለመጠየቅ፤ ወደ ልዩ ትምህርት ተቆጣጣሪ ጽ/ቤት፣ የቅሬታ ሰሚና መፍትሔ ሰጪ ን/ክፍል በ ስልክ ቁጥር 240-740-3230 ሊቀርብ/ሊመራ ይችላል። ለሰራተኞች መገልገያዎች ወይም ማሻሻያዎች በሚመለከት የሚቀርቡ ጥያቄዎች ወደ Office of Employee Engagement and Labor Relations, Department of Compliance and Investigations/ የሰራተኛ ተሳትፎ እና የስራ ግንኙነት የአፈጻጸም እና የክትትል (የምርመራዎች) መምርያ፣ ስልክ፦ 240-740-2888 ሊመሩ ይችላሉ። በተጨማሪ፣ አድሎአዊነት ቅሬታዎች ለሌሎች ኤጀንሲዎችም ፋይል ሊደረጉ ይቻላል። እነርሱም፦ the U.S. Equal Employment Opportunity Commission, Baltimore Field Office, City Crescent Bldg, 10 S. Howard Street, Third Floor, Baltimore, MD 21201, 1-800-669-4000, 1-800-669-6820 (TTY); ወይም U.S. Department of Education, Office for Civil Rights, Lyndon Baines Johnson Dept of Education Bldg., 400 Maryland Avenue, SW, Washington, DC 20202-1100, 1-800-421-3481, 1-800-877-8339 (TDD), [email protected], ወይም www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/complaintintro.html.

ይህ ሠነድ ካስፈለገ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ከእንግሊዝኛ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አማራጭ ቅርፀት ሊገኝ ይችላል። በአካል

ጉዳተኝነት ስለሚኖሩ አሜሪካውያን ደንብ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት/MCPS Department

of Communications በስልክ ቁጥር፦ 240-740-2837፣ 1-800-735-2258 (ሜሪላንድ ማዞሪያ)፣ ወይም [email protected].

የምልክት ቋንቋ ትርጉም የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም የንግግር ትርጉም/ምልክት አገልግሎት ለማግኘት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/

ቤቶች የትርጉም አገልግሎት ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር፦ 240-740-1800, 301-637-2958 (VP) ወይም MCPSInterpretingServices@

mcpsmd.org መገናኘት ይችላሉ። የሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS)፤ ወጣት ስካውቶችን (ወንድ/ሴት) እና ሌሎችም

የሚመለከታቸውን ወጣት ቡድኖችን በእኩል ያስተናግዳቸዋል።

ጁላይ 2019