24
Dr. Sirak Hailu Chiropractic Physician በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ Saint Paul 1821 university Ave. w. Suit106 St. Paul, MN 55104 (651) 647 9100 Minneapolis 615 Cedar Ave. South Minneapolis, MN 55454 (612) 990-5314 የረዥም ዓመታት የጋራ የሥራ ልምድ አለን የረዥም ዓመታት የጋራ የሥራ ልምድ አለን የረዥም ዓመታት የጋራ የሥራ ልምድ አለን የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ጥር 2005 ቅጽ IV ቁጥር. 47 ዘወትር ሰኞ የተማሪዎች ብፌ ሐሙስ እና እሁድ የተለመደው ብፌ ይጠብቃችኋል (651)-646 6900 or 1-877-302-3347 1821 university Ave. w. Suit 143 St. Paul, MN 55104 ዕውነትን እንጽፋለን፤ ዕውነት ያሸንፋል!! 2812 university Ave, Mpls, MN 55414 Tel: (612)770-3270 www.aklogasfawinsurancemn.com $10 Home sell- ing and buying is easy when you list with Demssie AMERICAN REALTY GROUP. Call the guy that knows how to make It happen! በመተባበር፣ በመመካከር አብረን እንክበር OFF. (763) 951 2931 Cell (612) 644 7665 Fax (763) 432 5069 [email protected] 47ኛው ሱፐር ቦውል 21 6 የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃውና ጉልበቱ በ20$ ብቻ። - Engine - Brakes - Suspension - Transmission - Electrical - Body - Interior More... Ze-Habesha Newspaper Jan. 2013 No.47 ኬክ በትዕዛዝ ማቅረብ ጀምረናል 651-214-2584 ወይም 651-489-9220 አሁን ጊዜው የኢስት አፍሪካ የጤፍ እንጀራ ነው የሃገራችንና የውጭ ሃገር ቁርስ፣ ምሣና ራቶችን አድራሻችን የቀድሞው የሕንድ ሬስቶራንት የነበረው ራጃ መሐል ፍራንክሊን አቬንዩ ላይ ሚኒያፖሊስ 3025 E Franklin AveMpls, MN 55406 ( 612-344-5829) Lucy Ethiopian Restaurant ኬተሪንግ እንሠራለን ኬተሪንግ እንሠራለን ኬተሪንግ እንሠራለን በደቡብ አፍሪካ ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፎ እየተሳተፈ ከሚገኘው የብሄራዊ ቡድናችን አጨዋወት ሌላ ከፍተኛ የሚዲያዎችን ትኩረት ያገኘው የደጋፊዎቻችን ሁኔታም ጭምር ሆኗል። ከትናንትሽ እስከ ትላልቅ ሚዲያዎች ትናንት ጃንዋሪ 20 ቀን 2012 ብሄራዊ ቡድናችን ከአምናው የውድድሩ ሻምፕዮን ዛምቢያ ጋር 1 ለ1 በተለያየበት ጨዋታ በስታዲየሙ የተገኙት የብሔራዊ ቡድናችን ደጋፊዎች ሰፊ የሚድያ ሽፋን አግኝተዋል። በዓለማችን ከፍተኛ ተነባቢነት ያላቸው የስፖርት ድረገጾችም “የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ደጋፊው ለዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውበትን ሰጥተውታል” በማለት ጽፈዋል። በውስጥ ገዶቻችን በአፍሪካ ዋንጫ ዙሪያ የተለያዩ ዘገባዎችን ይዘናል ገላልጠው ያንብቡት። ያመፁ የኤርትራ ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ለአንድ ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለቅቀው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡ ወደ አንድ መቶ እንደሚሆኑ የተነገረው ወታደሮች ወደ ደቡብ የጦር ሠፈራቸው የተመለሱት ከፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ዛሬ አብዛኛውን ቀን ዝግ ሆኖ የዋለው የሃገሪቱ ቴሌቪዥን ጠፍቶ የዋለበትን ምክንያት ሣይናገር ምሽት ላይ መደበኛ ፕሮግራሙን ቀጥሏል፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያው ድንገት ከመቋረጡ በፊት (ዘገባውን በገጽ 6 ላይ ይመልከቱ) “ከሁሉ ያስደነቀኝ ደግሞ የብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ቆራጥ አቋም ነው። የማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን ጥመኞችንም አላገለግልም ! ለዚህ የማመስገኛ ቃላት ያጥረኛል። ቤተክርስቲያን ውለታዎንና ተጋድሎዎን መቼም አትረሳውም። ምናለበት፥ እንደርስዎ ሌሎቹም አባቶች ተከ ትለዎት ቢወጡ ኖሮ ፥ አሰኝቶኛል። አንዳንዴ እንዲህ ያለ አቋም ቁጭ ብሎ ትርጉም የሌለው ንትርክ ከመነታረክ፥ አስር እጥፍ ይሻላል።”(ትንታኔውን በገጽ 4 ላይ ይመልከቱት ) ‹‹በአባቴ የሐሞት ከረጢት ውስጥ ከ100 በላይ ጠጠር ተገኘ መባሉ እኔንም አሳስቦኛል፤ ለመሆኑ የሐሞት ጠጠር በዘር ይተላለፍ ይሆን?›› አለምሰገድ ‹‹የሐሞት ከረጢቴ በቀዶ ህክምና ተቆርጦ ከወጣ በኋላ የጨጓራ በሽታ አስቸግሮኛል፤ የሐሞት ጠጠርና ጨጓራ ግንኙነት ይኖራቸው ይሆን?›› ሰለሞን (በገጽ 17 ላይ የሌሎችም ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል) የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአንድ ሳምንት ወዲህ በካምፓሳቸው ውስጥ ሰላት እንዳይሰግዱ መከልከላቸው ለሬድዮ ቢላል ገለፁ ፡፡ ከዚህ በፊት የጀምዓ(አርብ ጸሎት) ሰላት በመከልከላቸው አንዳንዱ ተማሪ በግሉ መስገድ ይችል እንደነበር ከዚህ በፊት የወጣው መመሪያ የሚያመለክት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን እስከነጭራሹ መስገድ ተከልክለናል ሲሉ ተማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ ሰላት በመከልከላችን ካፌ ገብተን መብላት አቁመን ሣለ አንድ እንኳን የትምህርት (ወደ ገጽ 18 የዞረ) “ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን እንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ነዉ። ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ ነዉ።” ይላል የግንቦት 7 የሃገር ውስጥ ኢንተለጀንስ ግሩፕም ጥናት። ግንቢት ሰባት ይህን ተከትሎ የትግራይ ሕዝብ በቃ ሊለው የሚገባውን ዘረኝነት በማስረጃ ዘርዝሯል። ይህ ጥናት በገጽ 5 ላይ ተስተናግዷል። - ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል በአሁኑ ወቅት በምድር ዙሪያ ስለምናየውና ስለምንሰማው አለመረጋጋት ከመጨነቅና ሰላም ከማጣት ይልቅ ሁሉን ወደሚችለው ፈጣሪያችን ፊት በምልጃና በጸሎት እንቅረብ (ገጽ 6 ላይ ይመልከቱ) ኢሳያስ አፈወርቂ አልተፈነቀሉም 21

Chiropractic Physician Call the guy that knows how to · PDF fileDr. Sirak Hailu Chiropractic Physician በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት

Embed Size (px)

Citation preview

Dr. Sirak Hailu

Chiropractic Physician

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

Saint Paul 1821 university Ave. w.

Suit106 St. Paul, MN 55104

(651) 647 –9100

Minneapolis 615 Cedar Ave. South

Minneapolis, MN 55454

(612) 990-5314

የረዥም ዓመታት የጋራ የሥራ ልምድ አለንየረዥም ዓመታት የጋራ የሥራ ልምድ አለንየረዥም ዓመታት የጋራ የሥራ ልምድ አለን

የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47

ዘወትር ሰኞ የተማሪዎች ብፌ ሐሙስ እና እሁድ የተለመደው ብፌ ይጠብቃችኋል

(651)-646 6900 or 1-877-302-3347 1821 university Ave. w. Suit 143

St. Paul, MN 55104

ዕውነትን እንጽፋለን፤ ዕውነት ያሸንፋል!!

2812 university Ave, Mpls, MN 55414

Tel: (612)770-3270

www.aklogasfawinsurancemn.com

$10

Home sell-

ing and buying is

easy when you list

with Demssie

AMERICAN REALTY GROUP.

Call the guy that

knows how to

make

It happen!

በመተባበር፣ በመመካከር አብረን እንክበር OFF. (763) 951 2931 Cell (612) 644 7665 Fax

(763) 432 5069 [email protected]

47ኛው ሱፐር ቦውል 21 6

የመኪናዎን ዘይት

ካለቀጠሮ እንቀይራለን

የዝናብ መጥረጊያዎን

ለማስቀየር እቃውና ጉልበቱ በ20$ ብቻ።

- Engine - Brakes - Suspension - Transmission

- Electrical - Body - Interior

More...

Ze-Habesha Newspaper Jan. 2013 ᴥ No.47

ኬክ በትዕዛዝ ማቅረብ ጀምረናል

651-214-2584 ወይም 651-489-9220

አሁን ጊዜው የኢስት አፍሪካ

የጤፍ እንጀራ ነው

የሃገራችንና የውጭ ሃገር ቁርስ፣ ምሣና ራቶችን አድራሻችን የቀድሞው የሕንድ ሬስቶራንት የነበረው ራጃ መሐል ፍራንክሊን

አቬንዩ ላይ ሚኒያፖሊስ

3025 E Franklin Ave፣ Mpls, MN 55406

( 612-344-5829)

Lucy Ethiopian Restaurant ኬተሪንግ እንሠራለንኬተሪንግ እንሠራለንኬተሪንግ እንሠራለን

በደቡብ አፍሪካ ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፎ እየተሳተፈ ከሚገኘው የብሄራዊ ቡድናችን አጨዋወት ሌላ ከፍተኛ የሚዲያዎችን ትኩረት ያገኘው የደጋፊዎቻችን ሁኔታም ጭምር ሆኗል። ከትናንትሽ እስከ ትላልቅ ሚዲያዎች ትናንት ጃንዋሪ 20 ቀን 2012 ብሄራዊ ቡድናችን ከአምናው የውድድሩ ሻምፕዮን ዛምቢያ ጋር 1 ለ1 በተለያየበት ጨዋታ

በስታዲየሙ የተገኙት የብሔራዊ ቡድናችን ደጋፊዎች ሰፊ የሚድያ ሽፋን አግኝተዋል። በዓለማችን ከፍተኛ ተነባቢነት ያላቸው የስፖርት ድረገጾችም “የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ደጋፊው ለዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውበትን ሰጥተውታል” በማለት ጽፈዋል። በውስጥ ገዶቻችን በአፍሪካ ዋንጫ ዙሪያ የተለያዩ ዘገባዎችን ይዘናል ገላልጠው ያንብቡት።

ያመፁ የኤርትራ ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ለአንድ ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለቅቀው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡ ወደ አንድ መቶ እንደሚሆኑ የተነገረው ወታደሮች ወደ ደቡብ የጦር ሠፈራቸው የተመለሱት ከፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ዛሬ አብዛኛውን ቀን ዝግ ሆኖ የዋለው የሃገሪቱ ቴሌቪዥን ጠፍቶ የዋለበትን ምክንያት ሣይናገር ምሽት ላይ መደበኛ ፕሮግራሙን ቀጥሏል፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያው ድንገት ከመቋረጡ በፊት (ዘገባውን በገጽ 6 ላይ ይመልከቱ)

“ከሁሉ ያስደነቀኝ ደግሞ የብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ቆራጥ አቋም ነው። የማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን ጥመኞችንም አላገለግልም ! ለዚህ የማመስገኛ ቃላት ያጥረኛል። ቤተክርስቲያን ውለታዎንና ተጋድሎዎን መቼም አትረሳውም። ምናለበት፥ እንደርስዎ ሌሎቹም አባቶች ተከ ትለዎት ቢወጡ ኖሮ ፥ አሰኝቶኛል። አንዳንዴ እንዲህ ያለ አቋም ቁጭ ብሎ ትርጉም የሌለው ንትርክ ከመነታረክ፥ አስር እጥፍ ይሻላል።”(ትንታኔውን በገጽ 4 ላይ ይመልከቱት )

‹‹በአባቴ የሐሞት ከረጢት ውስጥ ከ100 በላይ ጠጠር ተገኘ መባሉ እኔንም አሳስቦኛል፤ ለመሆኑ የሐሞት ጠጠር በዘር ይተላለፍ ይሆን?›› አለምሰገድ ‹‹የሐሞት ከረጢቴ በቀዶ ህክምና ተቆርጦ ከወጣ በኋላ የጨጓራ በሽታ አስቸግሮኛል፤ የሐሞት ጠጠርና ጨጓራ ግንኙነት ይኖራቸው ይሆን?›› ሰለሞን (በገጽ 17 ላይ የሌሎችም ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል)

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአንድ ሳምንት ወዲህ በካምፓሳቸው ውስጥ ሰላት እንዳይሰግዱ መከልከላቸው ለሬድዮ ቢላል ገለፁ ፡፡ ከዚህ በፊት የጀምዓ(አርብ ጸሎት) ሰላት በመከልከላቸው አንዳንዱ ተማሪ በግሉ መስገድ ይችል እንደነበር ከዚህ በፊት የወጣው መመሪያ የሚያመለክት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን እስከነጭራሹ መስገድ ተከልክለናል ሲሉ ተማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

ሰላት በመከልከላችን ካፌ ገብተን መብላት አቁመን ሣለ አንድ እንኳን የትምህርት (ወደ ገጽ 18 የዞረ)

“ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን እንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ነዉ። ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ ነዉ።” ይላል የግንቦት 7 የሃገር ውስጥ ኢንተለጀንስ ግሩፕም ጥናት። ግንቢት ሰባት ይህን ተከትሎ የትግራይ ሕዝብ በቃ ሊለው የሚገባውን ዘረኝነት በማስረጃ ዘርዝሯል። ይህ ጥናት በገጽ 5 ላይ ተስተናግዷል።

- ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል

በአሁኑ ወቅት በምድር ዙሪያ ስለምናየውና

ስለምንሰማው አለመረጋጋት ከመጨነቅና

ሰላም ከማጣት ይልቅ ሁሉን ወደሚችለው

ፈጣሪያችን ፊት በምልጃና በጸሎት

እንቅረብ (ገጽ 6 ላይ ይመልከቱ)

ኢሳያስ አፈወርቂ አልተፈነቀሉም 21

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

መልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ እንዴት እንደሰነበትን፥ ሁላችንም እናውቀዋለንና። ለመላው

የቤተክርስቲያን ልጆች እያሳለፍነው ያለው ሳምንት የሐዘንና፥ ተስፋችንን አጨላሚ፥ ሆኖ ነው የሰነበተው። ይህ ሳምንት፥ ለሃያ አንድ ዓመታት ፥ መከፋፈል በተባለ በሽታ ፥ ታማ የነበረችው እናት ቤተክርስቲያን ፥ ስትሰቃይ ኖራ ፥ ያረፈችበት ሳምንት ነው። ነገር ግን አጥብቀን ከቀድሞው አብዝተን ከጮህን፥ ልክ በወንጌሉ እንደተጻፈው የሞተውን የሚያስነሳው ትንሣኤና ሕይወት የሆነ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ እስትንፋሷን ሊመልሰው ይቻለዋል። በእምነታችንም ጸንተን እያንዳንዳችን ማድረግ ያለብንን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አንበል፤ በማለት ሰሞኑን አእምሮዬን ሲሞግቱኝ ወደ ከረሙት ጉዳዮች ተራ በተራ ልግባ።

መጀመሪያ በአሁኑ ወቅት ከበሽታቸው ጋር እየታገሉ የሚገኙት ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፣ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብጹዕ አቡነ ቄርሎስና ሌሎችም በአጠቃላይ፥ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የሰጣችሁን፥ ከባድ አደራ በመወጣት ላይ ለምትገኙ አባቶቻችን፥ ለእናንተ ያለን ፍቅርና አክብሮት እጅግ የላቀ መሆኑን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን። ባሳያችሁት ጽኑዕ አቋም ምክንያት ብዙዎቻችን ጨርሰን ተስፋ እንዳንቆርጥ ረድቶናል። እያደረጋችሁት ያለውን ጥረትና ተጋድሎም፥ በእኛ ልጆቻችሁ ልቡና ለዘላለሙተቀርጾ በሃይማኖት ጸንተን እንድንኖር ይረዳናል። ዋጋችሁም በማይጠፋው መዝገብ ተመዝግቦ ከእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ እንደምትቀበሉም ሙሉ እምነታችን ነው። ይህ ስሜት የብቻዬ ስላልሆነ ጉዳይ በሚመለከተን የቤተክርስቲያን ልጆች ስምም፥ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።

ከሁሉ ያስደነቀኝ ደግሞ የብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ቆራጥ አቋም ነው። የማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን ጥመኞችንም አላገለግልም ! ለዚህ የማመስገኛ ቃላት ያጥረኛል። ቤተክርስቲያን ውለታዎንና ተጋድሎዎን መቼም አትረሳውም። ምናለበት፥ እንደርስዎ ሌሎቹም አባቶች ተከትለዎት ቢወጡ ኖሮ ፥ አሰኝቶኛል። አንዳንዴ እንዲህ ያለ አቋም ቁጭ ብሎ ትርጉም የሌለው ንትርክ ከመነታረክ፥ አስር እጥፍ ይሻላል። ብጹአን አባቶቼ፥ መቼም መሣሪያ ደቅነው ከያዙ ጨካኞች ጋር እንደምትጋፈጡ ይገባኛል፥ ነገርግን ቢያንስ የታሪክ ተወቃሽ እንዳትሆኑ፥ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሲወጡ፥ ሌሎቻችሁም ብትከተሉና ፤በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አባቶቻችን በዕርቁ ጉዳይ ሳይስማሙ ተለያዩ ፤ ተብሎ ቢነገረን፥ ይሻል ነበር ብዬ አስባለሁ።

ለነገሩ አሁንም ቢሆን፥ ያለቀ የደቀቀ ነገር ስላልሆነ፥ ከዚህም በኋላ እነሱ በሚያደርጉት ማንኛውም የመሿሿሚያ ስብሰባዎች

ራሳችሁን ብትለዩ ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ። አባቶቼ ዝምታም እኮ ተቃውሞ ነው፤ እነ አባ አብርሃምና አባ ሳሙኤል እርስስ በርሳቸው ይሿሿሙ፥ ይሰብሰቡ፥ ነገ እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣል። ብጹአን አባቶቻችን ፥ ከቻላችሁ በአቋማችሁ የምትስማሙት አንድ ላይ በመሆን ተቃውሞአችሁን ቀጥሉ፥ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማወቅ ባለበት መጠን አሳውቁ። በመንግስት አይዞአችሁ ባይነት እየተንቀሳቀሱ

ያሉት አባቶች፥ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኝ እረኞች ስለሆኑ እና በሥልጣን ጥመኝነትና በጥላቻ ስለሰከሩ፤ ከዚህ በፊት ለመጠቆም እንደሞከርኩት የተሰጣቸውን ተተልዕኮ ከማስፈጸም ፥ ወደ ኋላ

አይመለሱም። ብጹአን አባቶች፤ ውሃ ሽቅብ እንደማይፈስ አውቃለሁ። ነገር ግን ሁላችሁም ከእግዚአብሔር ያገኛችሁት ትልቅ መንፈሳዊ ሀብት በእጃችሁ አለ። አስፈላጊውን ማሳሰቢያ ከሰጣችሁ በኋላ፥ በእንቢታቸው ጸንተው ፥ የእነ አባይ ጸሐዬን ጠብ መንጃ ተመክተው፥ እንመርጣለን ብለው ከተነሱም፥ በመጨረሻውን ውሳኔ ስጡ! ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ በእጃችሁ ትገኛለችና!

ሁለተኛ፦ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ እባካችሁን ስለቤተክርስቱያናችን የወደፊት

ሕልውናና ስለእኛ ስለተበተነው ልጆቻችሁ ስትሉ በተደጋጋሚ ያሳያችሁትን ትዕግስት አሁንም ቀጥሉ። ቢያንስ ቢያንስ እነ አባ ሳሙኤል እና መሰሎቻቸው በስልጣን ጥመኝነት አእዕምሮአቸውን አጥተው እስኪለይላቸው ድረስ ሕዝቡን የሚያጽናና፣ የሚያረጋጋና አንድነቱን የሚያጠናክርበትን መንገድ በማሳየት በጎቻችሁን በመልካምና በለምለም ሣር ላይ አሰማሩ። እንዲህ ከሆነ ይህን፥ ወይም ያንን፥ እናደርጋለን ከማለት ከእልኸኝነት የሚመነጭ ውሳኔ ተቆጠቡ።

ሦስተኛ፦ የሰላምና አንድነት ኮሚቴም እስከ አሁን ድረስ የደከማችሁትን ድካም ልጆቻችሁ የሆንን ሁሉ እንረዳለን። እግዚአብሔር በሰማያት ዋጋችሁን እንዲከፍላችሁ ጸሎቴ ነው። ከዚህ በኋላ ፥ ያጋጠማችሁን ፈተናና ሰላም እና አንድነቱን ለማምጣት ስትሉ ከመናገር የተቆጠባችሁትን ሁሉ የመግለጽ ኃላፊነት ይጠበቅባችኋል። በአንድነት ምዕመናኑን በመምራት ፥ ለሰላም ይበጃል የምትሉትን ሁሉ ሃሳብ ከመስጠት አትቆጠቡ። አቅማችሁ በቻለ መጠን ከሁለቱም ወገን ይህ መከፋፈል ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ሞክሩ።

አራተኛ፦ለማህበረ ቅዱሳን አንድ ግልጽ መልዕክት አለኝ። ማህበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጀምሮ ትኩረቱን በቤተክርስቲያን ብቻ ላይ በማድረግ፤ ከፖለቲካ ነጻ በሆነ መንገድ፥ ስብከተ ወንጌል በማስፋፋት፣ ቤተክርስቲያንን ከመናፍቃንና ከተሐድሶያዊያን በመታደግ፣ አዲሱን ትውልድ ለቤተክርስቲያን የሚገደውና የሚቆረቆር አድርጎ በመቅረጽ ጊዜ የማይሽረው ትልቅ አሻራ ጥሏል። ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን በምትፈልገው ቦታ ሁሉ ስድብን፣መታሰርን፣መጉላላትንና ሌሎች በዚህች ጹሑፍ ዘርዝሬ ልገልጸው የማልችላቸውን ፈተናዎች ታግሶ፥በአዲሱ ትውልድ ላይ፥ በእግዚአብሔር ቸርነት፥ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ፥ ለመሆንም

በቅቷል። ይህን ሁሉ መከራና ዋጋ የተከፈለላት ቤተክርስቲያንና ልጆቿ ያለ መሪ ሲቅበዘበዙ፥ ብጹአን አባቶቻችን በህቡዕ ሣይሆን በግልጽ ድጋፍ ሲያስፈልጋቸው፥ ምንም እንዳልተፈጸመ ዝምታችሁ ሊገባኝ አልቻለም። ይልቁንም አንዳንድ የማህበሩ አባላት በዕርቁ ዙሪያ

ያላቸውን ሃሳብ ሲሰጡ፤ የማህበሩ ሃሳብ አይደለም! ብሎ እራሱን ከመንግስት ቁጣ ለማዳን የሚያደርገው ድርጊት ትዝብት ላይ ከጣለው ሰነበተ። ቤተክርስቲያን ስትከፈል ደጆቿ ሲዘጉ የማህበሩ ጽሕፈት ቤት እንዳይዘጋ የምታደርጓቸው ጥንቃቄዎችም አሳዝኖኛል!! ለቤተክርስቲያን የመከራ ቀን ድምጹን አሰምቶ እኛ አለንልሽ ቤተክርስቲያን ካላለ፥ የዚህ ማህበር ፋይዳው ምንድን ነው? እኔ በበኩሌ ይህ ማህበር ፥በሰላሙ ሰዓት ብቻ ለስብከተ ወንጌል የሚሯሯጡ ሰባኪያንን ብቻ ሳይሆን፥ በዓላውያን መንግስታት ፊት አንገታቸውን

ለሰይፍ የሰጡትን ሰማዕታትን እነቅዱስ ጊዮርጊስን የሚተካ ትውድም የሚያፈራ አድርጌ እቆጥረው ነበረ። ከዚህ በላይ ምን እስኪሆን ነው የሚጠበቀው? ከአፍቃሬ ማህበርነት የሚፈለግ ቢሆንም ከሁሉም በላይ አፍቃሬ ቤተክርስቲያን መሆኑን የሚያሳይበት ወቅት አሁን መሆኑን ልገልጽ እወዳለሁ። ለዚህ ወቅታዊ ጥያቄ ምላሽ በአስቸኳይ ያስፈልገዋል!

በመጨረሻም፦ በውጭው ዓለም የምትገኙ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች በየቤተክርስቲያናችሁ በዚህ ጉዳይ ተሰባስባችሁ አቋማችሁን ዛሬም ለመግለጽ ዛሬም ጊዜ አላችሁ። ከሕሊና ባርነት የአንድ ቀን ነጻነት ይሻላል። ብዙ አደር ባዮች በበዙበት ዘመን እውነትን ለመናገር ዳተኛ መሆን ከክርስቲያን አይጠበቅም። የፈለገው ይሾም ስም ለመጥራት ዝግጁ ነን፥ ቅዱስ ሲኖዶስ አይሳሳትም ፤ወለም ዘለም አንልም የሚባል ዜማ እያዜሙ የመንግስትን ሹመኞች እንድንቀበል መድረኩን የሚያዘጋጁ ካህናትና ምዕመናን እየተስተዋሉ ነው። በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ነው የሚባለው ሲኖዶስ ይኼ ነው ወይ? ብጹዕዓን አባቶቻችንን በገዛ ጽሕፈት ቤታችው እያስፈራራቸው ያለው ግለሰብ፥ አባይ ጸሐዬ፥ መቼ ነው የሲኖዶሱ አባል የሆነው? የሚገርመው እነአባ አብርሃም ፓትርያርኩ ያለ መንግስት ተጽዕኖ ነው መንበር ጥለው የተሰደዱት ይበሉን? እንደው በእመ አምላክ የመንግስትን ተጽዕኖ መኖር የሚጠራጠር ሰው ይኖር ይሆንን? እንኳን የዛሬ ሃያ አንድ ዓመት፥ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ሲያሳድዱ ይቅርና ፤ዛሬ ሰላም ነው ተብሎ በሚለፈፍበት ጊዜ እንኳን አዳር ውሎአቸው ቤተክህነት አይደለምን? እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል። የሚቀብረን ነው ያጣነው።

ይቅርታ ይደረግልኝና በታሪክ የምናውቃቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የድሮዎቹ፤ ወኔ የነበራቸው፥ እንኳን ለቤተክርስቲያናቸው ቀርቶ ለሃገራችው ለእናት ኢትዮጵያ ሥጋቸውን ለአሞራ የሚሰጡ ነበሩ። ለዚህ መቼም ጥቅስ ፍለጋ አልደክምም። በአጭሩ ግን፥ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በር ተዘግቶ የካቶሊክ እምነት በር አይከፈትም በማለት፤ በአጼ ሱስንዮስ ዘመን፥ በአንድ ቀን ብቻ፥ ከመላው ኢትዮጵያ ሰማዕትነት አያምልጥህ እየተባባሉ፤ አስር ሺህ ምዕመናን ጎንደር ላይ ሰማዕትነትን የተቀበሉበትንና የቅዱሱን ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስን ሰማዕትነት ለአንባቢ ማስታወስ ግድ ይለኛል።

እንደው ለመሆኑ ሳናውቀው ጥሩ ጥሩ ነገሮች ላይ ብቻ የሚሳተፍ፥ ሀገር ጎብኚ፥ መረር ያለ ነገር ሲመጣ እነእገሌ ይህን ያድርጉ፤ እኔ የለሁበትም የሚል ትውልድ ሆነን እንቅር? እንዲህ እንዲህ ይሸቱ የነበሩት እንኳን መናፍቃኑ ነበሩ። እረ ጎበዝ ምን ነካን? እዚህ ላይ ይብቃኝ።

አምላከ ቤተክርስቲያን እባክህ ተመልከተን! እኛ ደክመናል። ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

በፖስታ፤ ኢሜይል፤ በሶሻል ኔትወርኮች፣ በስልክ እና በአካል እናንተ አንባቢያን ያቀረባችሁት አስተያየት የሚስተናገድበት ነጻ አምድ ነው። ይጻፉልን፤ ይደውሉልን። (e-mail:- [email protected])

Ze-Habesha Newspaper is Legally

Registered in state of Minnesota -

USA

Founded in December 2008 Publisher :-

ZeHabesha LLC

ዋና አዘጋጅ:- ሔኖክ

ዓለማየሁ ደገፉ

Editor in

Chief:-

Henok A.

Degfu e-mail:- [email protected]

[email protected]

አዘጋጆች:- ሊሊ ሞገስ፣

[email protected] ሮቤል ሔኖክ፣

[email protected] ቅድስት አባተ ዘላለም ገብሬ (ቺካጎ) [email protected]

አማካሪ፡- ዶር ዓብይ ዓይናለም

Ze-Habesha newspaper Address:-

6938 Portland Ave,

Richfield MN 55423

612-226-8326

www.zehabesha.com

www.facebook.com/zehabesha

www.twitter.com/zehabesha “Journalism can never be silent: that is its greatest virtue and its greatest fault. It must speak, and speak immediately, while the echoes of wonder, the claims of triumph and the signs of horror are still in the air.”

Henry Anatole Grunwald

በሚኔሶታ - አሜሪካ የተቋቋመ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው

ዓላማው የማህበረሰባችን የወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ መገኛ መሆን ነው።

ዘ-ሐበሻ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ድርጅት፣ ጎሳ፣ ያልወገነ፣ ነጻ ጋዜጣ ነው፡፡

ዓብይ መልዕክት

ከዓለማየሁ ገበየሁ 16 ብሄራዊ ቡድኖች ደቡብ አፍሪካ ላይ በሰላማዊ የስፖርት

ትግል መፋጠጥ ጀምረዋል፡፡ ቡድኖቹ ለማፍጠጥ ብቻ ሳይሆን ተቀናቃኛቸውን በአሳማኝ መልኩ ለማንበርከክ ይችሉ ዘንድ በቅድመ ዝግጅት ስራ ተወጣጥረዋል ፡፡

ከ16ቱ ቡድኖች 12ት ያህሉ መጠሪያቸው መሰረት ያደረገው የዱር እንስሳት ላይ ነው ፡፡ ዝሆኖቹ ፣ ነብር ፣ ሰማያዊ ሻርክ ፣ አንበሳ ፣ ንስር አሞራ ፣ ዋሊያዎቹ እያለ የሚቀጥል ነው ፡፡ በዱር እንስሳት የጫካ ህግ መሰረት አንበሳ ‹ አለቃ ነኝ ! › ማለቱ አይቀርም ፡፡ ይሁን እንጂ ዝሆንና ነብሮችን እንዲሁ በቀላሉ ማንበርከክ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ትግሉና ፉክክሩ በዚህኛውም ጠርዝ ከባድ መሆኑን ማንበብ ይቻላል ፡፡

ኮትዲቭዋር በወቅታዊ የአንደኛ ደረጃነታችን ዋንጫው ከእኛ እጅ አይወጣም ብለው 39 ነኛ ደረጃ የሚደርሰውን የኢትዮጽያ ዋሊያ ማጣጣል ይከብዳቸዋል ፡፡ ምክንያቱም በቅድመ ዝግጅታቸው ጥናት ወቅት ተቀላቅሎ የገባው ‹ የተናቀ ያስረግዛል › የሚለው ስነ ቃል ትኩረታቸውን ስቦታልና ፡፡ ከሰሞኑ ይህን መሰሉ የቅድሚያ ግምት ለማምከን ይመስላል የስልጠናውና የወዳጅነት ግጥሚያዋች ተጠናክረው የቀጠሉት ፡፡

ከ31 ዓመታት ቆይታ በኃላ ወደ ትግሉ ሜዳ የወረዱት ዋሊያዋች የቅድመ ዝግጅታቸውን ምዕራፍ የከፈቱት የኢትዮጽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ በማፍጠጥ ነበር ፡፡ ‹ ቃል የገባህልን ገንዘብ ካልከፈልከን ስልጠናችንን እናቆማለን ! › የሚል መድፍ ተኮሱ ፡፡ ይህን የመሰለ ጥያቄ በማንሳት አቧራ የሚያስነሱት እንኳ የናይጄሪያዋቹ ንስር አሞራዋች ነበሩ ፡፡ ፕሮፌሽናሊዝምን ብቻ ሳይሆን የመብት ጥያቄን በተሞክሮነት እየወሰዱ መቀመር ምን ያህል ጠቃሚ መሆኑን ዋሊያዎቹ ዛሬ የተረዱ ይመስላል ፡፡ ከ50 እስከ 130ሺህ ብር በፈጠነ መልኩ ኪሳቸው ውስጥ ሲወረወር አይተዋልና፡፡ ከዚህ በኃላ ሁለት ስር ነቀል ጥቅሶች መለማመጃ ሜዳ ላይ ተሰቅለው ነበር አሉ ፡፡

1 . ከእንግዲህ ዱቤ አናስተናግድም ! 2 . እጅ በእጅ ፍቅር እንዲደረጅ ! ይህ በእንዲህ እንዳለ ብሄራዊ ቡድኑ ማጣሪያውን ካለፈ 5

ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ሽልማት እሰጣለሁ ያሉትን ሼክ አላሙዲ ቃል ዱቤ ይሁን ንግግር የሚያጠና በዛውም መፍትሄ የሚያፈላልግ የተጫዋቾች ኮሚቴ ለማቋቋም እያሰቡ መሆኑ በስታዲየም ዙሪያ በሚገኙት ድራፍት ቤቶች እየተወራ ነው ፡፡

ዋሊያዎቹ 36 ተኛ ደረጃ ከሚገኘው ኒጀር ጋር ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ በብቸኛ ጎል ማሸነፋቸው ሌላው የቅድመ ዝግጅት ውጤት ሆኗል ፡፡ መሪውን የጨበጡት አቶ ሰውነት ቢሻው ተጠቅጥቆ ሲጓዝ ከነበረው ተሳፋሪ 23 ያህሉን ብቻ በማስቀረታቸው አሁን አንድ ወንበር ለአንድ ሰው የሚል መርህ የተያዘ ይመስላል ፡፡ ይሁን እንጂ አውቶብሱን እንዲለቁ ከተነገራቸው ተጫዋቾች መካከል የቀድሞው የኦርላንዶ ፒሬት ፕሮፌሽናል ተጫዋች የነበረው ፍቅሩ ተፈራ ሹፌሩ ያለ መንጃ ፍቃድ እያሽከረከሩ መሆኑን የሚያሳይ የመሰለ ትችት አቅርቧል ፡፡ ‹‹ እውቀት የሌለው አቶ ሰውነት በህይወቱ ፕሮፌሽናል ጨዋታ አድርጎ አያውቅም ፤ ግን በኔ ዝና ታዋቂነትን ማግኘት ይፈልጋል ›› ብሏል - ለሶደሬ ፡፡ እናም ይሄም የቅድመ ዝግጅትም የመፋጠጥም አካል ሆኖ የሚታይ ነው ፡፡

ዋሊያዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያቀኑት ለተሳትፎ ሳይሆን ተዓምር ለመስራት ነው እያለ የሚገኘው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ 80 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ በማቀዱ በሞባይል ሳይቀር ቢንጎና ገባ - ወጣ እያጫወተ ነው ፡፡ የብሄራዊ ቡድኑን ሎጎም ይፋ አድርጓል ፡፡ በሎጎ ውስጥ ዕድሜ የጠገበ ዋሊያ የፊት እግሮቹን ወደ ላይ አንስቶ ኳሷ ላይ አፍጥጧል ፡፡

ምልከታው ብዙ ጥያቄዋችን ያነገበ አስመስሎታል ፡፡ ዋሊያና እግር ኳስ ምንና ምን ናቸው ? እውነት ጠላቶቼ የሆኑት ነብርና አንበሳን እንዴት ነው ማሸነፍ የሚቻለው ? ስምና ተግባርስ አንድ ናቸው ? ለምሳሌ አንበሳ የሚል መጠሪያ ያላቸው ቡድኖች ዋንጫውን ያሸነፉት ስንት ግዜ ነው ?

እኛም አስፈላጊ ከሆነ ዋሊያውን መሰረት አድርገን መሰረታዊ

ጥያቄዋችን ማንሳት እንችላለን ፡፡ ለብሄራዊ ቡድናችን ‹‹ ዋሊያዎች ›› የሚል መጠሪያ ስም የወጣው ከምን መነሻ ነው ? ከዋሊያ ባህሪ አንጻር ውክልናው ተስማሚ ነው ወዘተ እያልን ፡፡

የእግር ኳስ መጠሪያ በአፍሪካ ሁሉም የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች ልዩ መጠሪያ አላቸው ፡፡

ሀገሮች የቡድናቸውን መጠሪያ ከባንዲራ ፣ ከጥንካሬ ፣ ከማሊያ ፣ ሀገራቸው ጎልታ ከምትታወቅበት ጉዳይ ፣ ቡድኑ እንዲሆን ከሚፈለገው አንጻርና ከመሳሰሉ ጉዳዮች ተነስተው ይሰይማሉ፡፡

ይህ ማለት ግን ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ስም የለጠፉ የሉም ማለት አይደለም ፡፡ ለምሳሌ የኮንጎ ብሄራዊ ቡድን Red Devils ነው የሚባለው ፡፡ ይህን ስያሜ የቤልጂየም ብሄራዊ ቡድንና ማንችስተር ዩናይትድ ይጋሩታል ፡፡ ሰይጣን ጥቁር ነው በሚባልበት ዓለም ቀያዮቹ ማንቸስተሮች ተምሳሌቱን የተጠቀሙበት ለምን እንደሆነ ይገባናል ፡፡ በመልክ ከሆነ ለሰይጣን የቀረቡት ኮንጎዎች ራሳቸውን ቀይ ሰይጣን የሚሉበት አግባብ አለ ቢባል እንኳን በአሳማኝነቱ ዙሪያ ዕድሜ ልክ ሊያከራክር የሚችል ነው ፡፡

የስያሜ እጥረት ያለ ይመስል የሌላውን ሀገር የደገሙም አሉ ፡፡ የኮትዲቭዋር ‹ the elephant › በጊኒ < the national elephant > ሆኖ ይገኛል ፡፡ ለአብዛኛው አፍሪካዊያን ቡድን መጠሪያ የሆኑት ግን የዱር እንስሳት ናቸው ፡፡ ርግጥ ነው አፍሪካ በዱር እንስሳት ሃብት አትታማም ፡፡ ይህ በራሱ መነሻ ሆኖ ሊሆን ይችላል ፡፡ በሌላ በኩል የአፍሪካዊያንና የዱር እንስሳት ትስስር ስናጤን ግን መነሻው ተግባር ላይ መዋል እንዳቃተው ህግ ሽባ ሆኖ ይታየናል ፡፡ አፍሪካዊያን የዱር እንስሳትን ቢወዱም ለስጋቸው ፣ ለጀብዱ ፍለጋ ፣ ኪሳቸውን ለማደለብ ሲሉ ያለ ርህራሄ ይገድሏቸዋል ፡፡ አፍሪካዊያንና የዱር እንስሳት እንደ ኦቴሎና ዴዝዲሞና የሚመሳሰሉ ናቸው ፡፡ እየወደዱ የሚገድሉ ፡፡

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ከሀገራችን ዋሊያ ጋር የሚደረገውን ግብግብ እናንሳ ፡፡ ዋሊያ ለመጀመሪያ ግዜ የታየው በ1835 ነበር ፡፡ በ1960ዋቹ ለስሊ ብራውን በተባለ ሰው በተደረገው ጥናት ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ ጣሊያን ሀገራችንን ሲወር እጅ አንሰጥም ያሉ አርበኞች ተራራው ላይ መሽገው ይዋጉ ነበር ፡፡ በአካባቢው የታየው ዋሊያም ‹‹ ምን እንበላለን ? ›› ለሚለው ወቅታዊ ጥያቄያቸው ሁነኛ አማራጭ ሆነ ቀረበ ፡፡ በዚህም ሳቢያ ቁጥሩ አሽቆለቆለ ፡፡

ጣሊያን ሀገሪቱን ለቆ ከወጣ በኃላም ዋሊያ በአካባቢው

ነዋሪዋች ለስጋውና ለቀንዱ ይታደን ነበር ፡፡ ደገኛው ስጋውን እያጣጣመ በቀንዱ ኩባያ ሰርቶ ጠላ ይጠጣበታል ፡፡ ይህ ገደላ ጋብ ያለው በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚሰራው The International union for conservation of nature / IUCN / ቀጭን ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኃላ የኢትዮጽያ መንግስት ብሄራዊ ፓርኩን በ1966 በማቋቋሙ ነው ፡፡ ዋሊያ ዛሬም ድረስ በመጥፋት ላይ የሚገኝ እንስሳት ዝርዝር ውስጥ ቢገኝም ቁጥሩ ከ 500 በላይ መድረስ ችሏል ፡፡

አንበሳ አፍቃሪዎች እውነቱን ለመናገር እንደ ኢትዮጽያዊያን አንበሳን የብዙ ነገር

መጠሪያና መወኪያ ያደረገ አገር የለም ፡፡ ዘፈኑ ፣ ሙገሳና ቀረርቶው አንበሳን ያማከለ ነው ፡፡ አንበሳ ጫማና አንበሳ ጫማ ብቻ ሳይሆን አቶ አንበሴንም ከጎፈራሙ እንስሳ ጋር ያዛምዳቸዋል ፡፡ አያሌ የግልና የመንግስት መ/ቤቶች ሎጎ ቢፈተሸ አንበሳ ይገኝበታል ፡፡ እረ ገንዘባችን ላይ ሁሉ አለ ፡፡ የዚህን ድንቅ እንስሳ ለብሄራዊ ቡድናቸው መጠሪያ ያደረጉት ግን ካሜሮን ፣ ሞሮኮና ሴኔጋል ናቸው ፡፡

ዘንድሮ ማጣሪያውን ማለፍ ያቃታቸው ካሜሮን Indomitable lions ይባላሉ ፡፡ የማይሸነፉ አንበሶች እንደማለት ፡፡ ርግጥ ነው የኛ ሀገር የስፖርት ጋዜጠኞች የማይበገሩ አንበሶች እያሉ ነው የሚጠሯቸው ፡፡ ካሜሮን በ1972 ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማለፍ አለመቻሉ የሀገሪቱን ፖለቲከኞች አነጋግሮ ነበር ፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አህመዱ አሂዶ የሀገሪቱ የስፖርት መዋቅር በአዲስ መልክ እንዲገነባ ትዕዛዝ አስተላለፉ ፡፡ የስፖርት ሚኒስትሩ በጉዳዩ ዙሪያ ሲሰሩ ከተነሱት አጀንዳዋች መካከል የቡድኑ ስያሜ ነገር ይገኝበታል ፡፡ ቡድኑ ጥንካሬን እንዲላበስ ‹ አንበሳ › ማለት እንደሚገባ ቢያስቡም ይህ አንበሳ ከሌሎቹ ሀገሮች በምን ይለያል የሚለውን ጥያቄ መመለስ አስፈልጎ ነበር ፡፡ እናም ‹ Indomita-ble › የሚል ቃል ከፊቱ እንዲገባ ስምምነት ተደረገ ፡፡ ዘንድሮ ግን አንበሶቹ የሉም ፡፡ ይህ ያስቆጫቸው የቀድሞዎቹ እነ ሮጀር ሚላ ባለጌ ወንበር ላይ ተሰይመው ‹‹ አንበሳ ሲያረጅ የዝምብ መጫዎቻ ይሆናል ! ›› እያሉ ነው አሉ ፡፡

የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ስያሜ ‹ The lion of Terenga › የሚል ነው ፡፡ በሀገሪቱ ቋንቋ ‹ Terenga › እንግዳ ተቀባይ ማለት ነው ፡፡ ጥሬ ትርጉሙ እንግዳ ተቀባዩ አንበሳ ሊሆን ነው ፡፡ ስምን አንበሳ ብሎ ተግባሩን (ዋልያ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

(በግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ የተጠናና የተዘጋጀ)

ዘረኛዉ የወያኔ ስርአት የኢትዮጵያን ህዝብ ለጥቂት አመታት ኢትዮጵያዊያንን ባሰረና በገደለ ቁጥር ገንዘብ የሚሰጡትን አለም አቀፍ ድርጅቶችና አርዳታ ሰጪ አገሮች ደግሞ 21 አመት ሙሉ ካታለለበት መንገድ አንዱ የፌዴራል ስርአት መስርቼ ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር አደረኳት የሚለዉ ባዶ አባባሉ ነዉ። ይህንን ተጋልጦ እርቃኑን የቀረ አባባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተገንዝቦ ወያኔን መታገል ከጀመረ ቆይቷል፤

ዋና ዋናዎቹ እርዳታ ለጋሾችም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ግድ የሌለዉ ወያኔ ወጣቶቻችንን እየገበረ ጥቅማቸዉን ስለሚያስከብርላቸዉ ነዉ እንጂ ወያኔ እንኳን እየደገፉ እርዳታ የሚሰጡት በአንድ ተርታም አብረዉ ለመቀመጥ የማይመች የእኩዮች ስብስብ እንደሆነ ካወቁ ቆይቷል።

ህወሀት በፌዴራል ስርአቱ ዉስጥ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ በሚጠራዉ ፓርላማ ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ 8 ብቻ ነዉ። እዚህ ፓርላማ ዉስጥ የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ የሚለዉ ህወሀት ነዉ፤ ትግራይ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ክልል ናት። የተቀሩት 8 ክልሎች በዚህ የእኩልነት ምልክት በሆነዉ ፓርላማ ዉስጥ ያላቸዉ የመቀመጫ ብዛት 569 ነዉ። ሆኖም በወያኔ መንደር የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ህዝብ ሳይሆን ጠመንጃ ነዉና ወያኔ ፓርላማዉ ዉስጥ 8 ወንበር ብቻ ይዞ 569 ወንበር ያላቸዉን የኦሮሚያን፤ የአማራን፤ የደቡብ ክልልንና የተቀሩትን አምስት ክልሎች እንደ መኪና ይነዳቸዋል። የየክልሉን መሪ ይሾማል፤ ይሽራል ወይም የማይስማማዉን የክልል ባለስልጣን ያስራል። ፓርላማዉ ዉስጥ አንድ መቶ ሰባ ስምንት፤ አንድ መቶ ሰላሳ ስምንትና አንድ መቶ ሀያ ሦስት መቀመጫ ያላቸዉ የኦሮሚያ፤ የአማራና የደቡብ ክልል ፓርቲዎች በራሳቸዉ ጉልበትም ሆነ ህልዉና ስለሌላቸዉ አንዱ ከሌላዉ የበለጠ ስልጣን ወይም ሹመት ለማግኘት አንጋጥጠዉ ወደ ላይ የሚመለከቱት ህወሀትን ነዉ።

ለመሆኑ ወያኔ የፌዴራል ስርዐት መስርቼ የኢትዮጵያን

ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት አረጋገጥኩ ሲል ምን ማለቱ ነዉ? እኩልነቱ የፖለቲካ ነዉ የኤኮኖሚ? ወይስ በየአመቱ ህዳር ወር ላይ የፌዴራልዝም ቀን ሲከበር እንደምናየዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠዉ በዘፈን ብቻ ነዉ? የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዐት ከላይና ከታች የሚቆጣጠረዉና ይህንኑ የፖለቲካ ስርአት የሚደግፍ የኤኮኖሚ መዋቅር ዘርግቶ የአገራችንን ኃብት የሚቦጠብጠዉ ህወሀት ብቻ ነዉና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ተረጋገጠ የሚባለዉ አባባል ከተራ የቃላት ድርደራ ዉጭ ሌላ ምንም ትርጉም

የለዉም። አፄ ቴዎድሮስን እንደ ልጅነት ሞዴሉ የሚመለከተዉ ኮሎኔል መ ን ግ ስ ቱ ኃ / ማ ሪ ያ ም የመጀመሪያዉን የኢትዮጰያ ዘመናዊ ወታደራዊ እንጂኔሪንግ ተቋም ሲመሰርት ስሙን “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ ነበር የሰየመዉ። ስያሜዉ የአፄ ቴዎድሮስ ስራና ስም ህያዉ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ የተደረገ ሙከራ እንደነበር ግልጽ ነዉ። የኢትዮጵያን የቀድሞ መሪዎች በጅምላ የሚዘልፈዉ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ከአንዲት የአገር ዉስጥ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገዉ ቃለ ምልልስ አፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ ያሰሩትን መድፍና መንግስቱ ኃ/ማሪያም “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የሰየመዉን ወታራዊ ተቋም አስመልክቶ ሁለቱንም መሪዎች

ሲያንቋሽሽ ተደምጧል። የሚገርመዉ ዛሬ ወያኔ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺን ብሎ የሚጠራዉ ግዙፍ የሲቪልና ወታደራዊ እንዱስትሪ ተቋምና በዚህ ተቋም ዉስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ፋብሪካዎች ደርግ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የጀመራቸዉ የከባድ እንዱስትሪ ጅምሮች ናቸዉ። በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ስራዉን ሲጀምር የፋብሪካዉ ሀላፊዎች፤ እንጂኔሮች፤ የመምሪያ ሀላፊዎችና ቴክኒሺያኖች የስራ ዕድል የሚያኙት የትምህርት ደረጃቸዉ፤ ችሎታቸዉና የሰራ ልምዳቸዉ ብቻ እየታየ ነበር፤ ወይም ትግርኛ ስለተናገረ ስራ የሚከለከል አማርኛ፤ ኦሮምኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ስለተናገረ አድሎ የሚደረግለት ዜጋ አልነበረም። ዛሬ ወያኔ ከደርግ ስርአት ተረክቦ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ብሎ በሰየመዉ እንዱስትሪ ዉስጥ አብዛኛዉን የሀላፊነት ቦታ የያዙ ሰዎች ለቦታዉ የበቁት በስራ ልምዳቸዉና ችሎታቸዉ ሳይሆን የተወለዱበት ዘርና የሚናገሩት ቋንቋ እየታየ ነዉ። ወታራዊዉ አምባገነን ደርግም ሆነ ወያኔ ይህንን እንዱስትሪ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ዘርፍ መሰረት ይሆናል የሚል ራዕይ ነበራቸዉ። ልዩነታቸዉ የእንዱስትሪዉ አስፈላጊነት ላይ ሳይሆን እንዱስትሪዉን ማን ይቆጣጠረዋል የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ። ደርግ በሱ መሪነት ለማንም ችሎታ ላለዉ ኢትዮጵያዊ የእንዱስትሪዉን በር የከፈተ ሲሆን ወያኔ ግን እንዱስትሪዉ እንዳለ በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እንዲገባ አድርጓል። ደርግም ወያኔም አምባገነኖች ስለሆኑ አንዱስትሪዉን ከህዝብ ቁጥጥር

ዉጭ አድርገዉታል፤ ወያኔ ግን ከአምባገነንም የጎሳ አምባገነን ስለሆነ ይህንን ትልቅ እንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር አድርጎታል።

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባለለፉት ሦስት አመታት ይህንን ወያኔ ገነባሁ የሚለዉን የፌዴራል ስርአትና በስርአቱ ዉስጥ የተለያዪ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚጫወቱትን ሚና በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አቅርቧል። የዛሬ ሁለት አመት ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ መላከያ ሰራዊት ዉስጥ የተዘረጋዉን የወያኔ የዘረኝነት መረብ ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮቴሌኮምን የዘረኝነት አደረጃጀት በመረጃ በማስደገፍ ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺንን የዘረኝነት አደረጃጀትና በዚህ አደረጃጀት ዉስጥ ማን ምን እንደሆነ ያጣናዉን የጥናት ዉጤት በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል። ግንቦት ሰባት ሃያ አራት ሰአት ሙሉ የሚከታተሉትን የወያኔ የደህንነት ሰራተኞች ከበባ ጥሶ የወያኔን ዘረኝነት የሚያጋልጡ መረጃዎችን ከራሱ ከወያኔ ጓዳ እየጎተተ አዉጥቶ ለህዝብ የሚያቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኝነት አያውቀዉም በሚል አስተሳሰብ አይደለም። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ የፈጠረዉ ከፍተኛ የመረጃ ጉድለት አለ ብሎ ያምናል፤ስለሆነም ህዝቡ የወያኔን ዘረኝነት ቢረዳም መጠኑን፤ስፋቱንና ጥልቀቱን በሚገባ ላያዉቅ ይችላል ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቀኑ ደሙን እንደ መዥገር የሚመጠዉን ወያኔን የመሰለ የጀርባ ላይ አጥንት ተሸክሞ መኖር የለበትም ብለን ስለምናምን ህዝብን ለትግል ከምናዘጋጅበትና ከምናነሳሳባቸዉ መንዶች ዉስጥ አንዱ እንደዚህ ህዝብ በገዛ አገሩ “እኩል አደረግንህ” ብለዉ በሚነግሩት ከሀዲዎች ቅኝ አገዛዝ እየተገዛ መሆኑን በማሳወቅ ነዉ።

ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዋና ዳይረክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ ፓርላማ ዉስጥ ተገኝቶ የኮርፓሬሺኑን የሁለት አመት የስራ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ኮርፓሬሺኑ የግል ባለኃብቶችን አያሳትፍም እንዳዉም እያቀጨጫቸዉ ነዉ፤ ለሙስና የተጋለጠ ነዉ፤ ደግሞም አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባል ነዉና ይህ አሰራር ሠራተኞችን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አይሆንም ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዉለት ነበር። የግሉን ዘርፍ መቅጨጭ በተመለከተ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀድሞዉንም ቢሆን “የወያኔ ዘርፍ” እንጂ የግል ዘርፍ የሚባል ነገር የለምና ጥያቄዉ መቅረብም አልነበረበትም። ሙስናም ቢሆን የወያኔ ስርዐት ዋናዉ መገለጫ ባህሪይ ስለሆነ ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ሙስና “ሙስናን እናጠፋለን” ስለተባለ ብቻ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ግንቦት ሰባትን እጅግ በጣም

ያሳዘነዉና ያስገረመዉ ነገር ያንን ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ የሚናገርለትን ፓርላማ ያስጨነቀዉ (ተጨንቆ ከሆነ) የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ሳይሆን አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸዉ ነዉ። በእርግጥ የአንድ ትልቅ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ የጦር ሠራዊት አባላት ሲሆኑ የአሰራርና የአስተዳደር ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ ሆኖም የሠራዊቱ ታማኝነት ለህዝብ ታዛዥነቱ ደግሞ ለህገ መንግሰስቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህ ችግር በቀላሉ የሚወገድ ችግር ይሆን ነበር።

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአምሰት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሺን ፕላን ዉስጥ የሚጫወተዉን ቁልፍ ሚና ፓርላማዉ በሚገባ የሚገነዘበዉ ይመስለናል፤ ታዲያ ይህ በአገር እድገት ዉስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወተዉ ኮርፖሬሺን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ሲወድቅ ምነዉ የብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት

የሆነዉ ፓርላማ አፉን ዘግቶ ተመለከተ? ፓርላማዉን ይበልጥ የሚገድደዉ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር ሆኖ ሌሎቹ ብሔረሰቦች ተመልካች ሲሆኑ ነዉ ወይስ የአንድ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሲሆኑ ነዉ? ለመሆኑ የወያኔ ዘረኝነት በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዉስጥ ምን ያህል ዘልቆ ገብቷል? የኦሮሞ፤ የአማራ፤ የሶማሌ፤ የሲዳማና ሌሎቹም ብሔር ብሔረሰቦች በዚህ ለአገር እድገት ቁልፍ በሆነ ኮርፖሬሺን ዉስጥ የሚጫወትቱት ሚና ምን ይመስላል?

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በአስራ አንድ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን ያስተዳድራል፤ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀቀበት ቀን ድረስ ቁጥራቸዉ በዉል ተለይቶ ባይታወቅም አስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎችም እያንዳንዳቸዉ በስራቸዉ ብዙ ፋብሪካዎችንና የማምረቻ ተቋሞችን ያቀፉ ናቸዉ። የኮርፖሬሺኑን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና

ሀላፊነት፤ በዳይረክተርነተና በምክት ል ዳይረክትርነት የሚመሩ 29 የከፍተኛ አመራር አባላት አሉ። ከእነ ዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉ ስጥ 69 በመቶዉ ወይም ሃያዉ ህወ ሀት ሆን ብሎ ያስቀመጣቸዉ ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸዉ።በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያላቸዉ ቦታ 31 በመቶ ወይም ከእያን ዳንዳቸዉ በቅደም ተከተል ሦስትና ስድስት ሰዎች ብቻ ሲሆን ከተቀሩት አምስት ክልሎች በዚህ ከፍተኛ የአመ ራር ቦታ ላይ የተመደበ አንድም ሰዉ የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ እንዱስትሪ ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ከፍተኛዉን ሚና ይጫ ወታል የሚባለዉ የብረታ ብረት እን ጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በሲቪልና ወታራዊ መምሪያዎች ተከፋፍሎ የተዳራጀ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎች ይገኛሉ። እነዚ ህን እንዱስትሪዎች በማስተዳደሩ በኩ ል የብሔር ብሔረሰቦችን ድርሻ ወይ ም ኮታ ስንመለከት ከአስራ ሦስቱ ኢንዱስትሪዎች ዘጠኙን የሚያስተ ዳድሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በኮርፖሬሺኑ ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን ከተሰጣቸዉ የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ እነ ብረጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን ዋና ዳይረክተር ፤ ኮ/ል ተከስተ ኃ/ማሪያም በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮ ዳክሺን ግንባታ ሀላፊ ፤ ኮ/ል ፀጋሉ ኪሮስ በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕ ረግ የኮርፖሬት ወታደራዊ ምርቶች ሀላፊ ፤ ኮ/ል ሙሉ ወ/ሰንበት በምክ ትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖ ሬት ፕሮጀክቶች አስተደዳደር ሀላፊ፤ ሻምበል ካህሳይ ክሽን የምርመራና ል ማት ዳይረክተርና ሻምበል ገ/ስላሴ ገ/ጊዮርጊስ የአቅም ግንባታና ስልጠና ማዕከል ዳይረክተርን የመሳሰሉ የህወ ሀት ታጋይ መኮንኖች ይገኙበታል።

ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረ ታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ (የትግራይ... ወደ ገጽ 18 የዞረ)

መኳንንት ታዬ ከሚኒሶታ የግዜው መጨመር የሁኔታዎች መለወጥ በተነሳ እና በታሰበ ግዜ ቅር ሳይለን ልናነሳ የምንወደው ዘመኖች እራሳቸው እንደ አለት ድንጋይ ተነባብረው ከማስፈራታቸውም በላይ ሥለ ተፈጠሩበት ሁነት እንደምን ብሎ ጥያቄ የሚያጭር ነገር እንዳለ ውልብ ሊለን የሚገባ መሆኑን ማስተዋል ሁለቴ ማሰብ አይጠይቅም። እርግጥ አንድም ለማሰብ ማስተዋል ገንዘብ ማድረግ ከሚያመጣው ቁጣ በቶሎ እንደ መዳን ይቁጥረው። የእኔ የፀሃፊውም እስቲ ይህችን ለመግቢያ ካልኩ መንደርደሩን በዚህ ልግታና ገንዘብ ይሆነኝ ብዬ ወደ አነሳሁት ርዕስ ልጓዝ። ነገሩ ከዚህ ይጀምር ባይባልም ከተጀመረበት ጀምሮ

መስማት ደግ ነውና፤ አንድ ሁለት ወር ይሆነዋል በትምርት አጋጣሚ የሰማሁት አንድ ጥያቄ አጫረበኝና ከአንባቢ ጋር ልጋራትና ድንጋይ ኪሱ ለከተተ ትውልድ መፍትሄ አፈላላጊ ብትሆን ።

ጥንት ግዜ ነው አሉ መርጌታው ሲያስተምሩ(የደብረሰላም መድሃኒዓለም ቤ/ክ) ጥንት ግዜ ዝንጀሮ ልጆቿን ስትመክር “እናንተ ወደሰው ማሳ ስትሄዱ ባለቤቱ ወዳእናንተ እየመጣ እያለ ጎንበስ ያለ እንደሆን ድንጋይ ሊያነሳ ነውና ግር ብላችሁ ሽሹ አደራ ስትል፤ በዚህን ግዜ አንዲት አናሳ ዝንጀሮ ከልጆቹ ምሃል ጥያቄ ጠየቀች’

እንዲህ ስትል” እማዬ ድንጋይ ኪሱ የጨመረ ቢመጣስ? ጥያቄ እንዳስከተለች እና እናቷን እንዳሳሰበች ተናገሪው ትውልድን ያማከለ ትምህርት አዘል ምክር ሠጥተው ነበርና፤ በዚህን ግዜ እኔም ጥያቄው ስለተመቸኝ መርጌታን እያመሰገንኩ አማርኛ የተናገረችውን ዝንጀሮ እያደነቅኩ ለዛሬ የምትሆን ቋጠሮ እንዳዘጋጅ ሆኖኛል።

ከየት እንነሳ ? እኛስ ምን ብለን እንጠየቅ እኛ ነን ድንጋይ ኪሳችን ጨምረን የመጣናው ወይስ ድንጋይ ኪሱ የጨመረ መጥቶብን ነው? ብቻ ብዙ ብዙ። ዛሬ ሃገራችን እጅግ መጠነ ሰፊ ችግሮች አንዱ አንዱን እየጋበዘ ከየት ጋር እንደጀመረ፤ ማን እንደጀመረው ግራ እስከሚያጋባና መፍትሄ የለሽ መራሹ ትውልድ እንደ ጥሩ ስም ሲያንከባልለው ሲያንከባልለው እዚ ደርሶ ፈተናው ልንወጣው ከምንችለው በላይ እየሆነ ነው። እንደምሳሌ የወሰድን እንደው ከሃገሩ ወጥቶ ካሰበበት ሳይደርስ የባሕር አሳ ሲሳይ የሆነ ፤ቤተሰቤን እረዳ ብለው በየ አረቡ ቤት ለሰራተኝነት ሄደው ባደባባይ ሲቀጠቀጡና ሲሞቱ የሰማናቸው፤ የእነሱ ከዚ ጋር እንኳን ቢያበቃ በሃገር ቤት የሚሰማው ከቤተመንግስተ እስከ ቤተ መቅደስ ብሎም እስከ ቤተ መስጊድ ብቻ ምኑ ቅጡ ምዕራፍ እና ቁጥሩ በማይታወቅ መልኩ አንባቢ ሳያስተውለው ተፅፎ ያለ የትላንትና ውሎ ለዛሬው ተጥሎ የነገ ሰንኮፍ ለመሆን ዝግጅት ላይ ነው። ከዛ በፊት ግን ለምን እንዴት እስከ መቼ የሚሉ እጅግ ጥቂት ጥያቄዬዎቸ ተንሰተው ለመልስ ሲዘጋጁ አየታይም። ለዚህም እንደምሳሌ የምናነሳው በዘር በጎሳ ተከፋፍለን የመኖራችንን ሁኔታ ብዙዎች ኑሮአቸው አድርገውት ዛሬም እንደትላንቱ ኪሳቸው ያለውን ድንጋይ እንደጨመሩ ናቸው ።

በሃይማኖት እና በሃይማኖተኞች ምሃከል የሚታየው ውጥንቅጥ እንዲሁ ሌላው ለነገ እንኳን ከኪሳችን ልናወጣው ያልቻልነው ዘመን የወለደው ትልቅ ድንጋይ ነው ። ግን ለምን? ዛሬ ያልጣልነው ድንጋይ መቼ ለእነማን? በእነማን ?

እርግጥ ነው አንድ እውነት አለ፤ ይኸውም ችግሮችን መፍጠር የኛ ተቀዳሚ ስራ የችግሩ መፍትሄ እንዲመጣ መፈለጋችን ከሌሎች፤ ይኸውም አንድ ከኛ ጋር የኖረ ድንጋይ ነው ።ህብረትና አንድነትን እርም ብሎ መርሳት አንዱ ልንጥለው ወይም እያንከባለልን አምጥተን ዛሬ ላይ ያደረስነው ለነገም ያዘጋጀነው ትልቅ ድንጋያችን ነው ።እውነት ነው ለዚህ ሁሉ ጉዳይ መፍትሄ ሳይኖር ቀርቶ አደለም፤ ነገርግን በመደማመጥና በመከባበር ዜግነትን እንደ አንድ ግዙፍ ስጦታ አለማየት ብሎም ሃለፊነትን ቦታ ሰጥቶ ከአለማየት የመነጨ ነው።

አስቲ ለ አንድ ደቂቃ ህሊናችንን አሰባስበን ከየት ተነስተን ወዴት እንደደረስን ልብ ብለን እናስብ ከየት ተነስተን የት እንደደረስን የችግር ምጣዳችን ሰምቶ አለም መሳሳቂያ ያደረገንስ? አዎ ሁሉም ሊታሰብበት የሚገባ ና ዘመናችን ያለ ፍሬ ያበቀለልን ሰብላችን ቦታውን በማናውቀው ኪሳችን የጨመርነው ድንጋያችን ነው። ለዚህ ትልቅ ችግር ነው ለምንለው ክፍተት በዘመናዊነትና በአድርባይነት በሌለበት የብቃት ህይወት ተረክበን ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ በሁሉም መስመር ትውልድን የሚፈነክት ድንጋይ በኪሱ ጭምር ይዞ እየተጓዘ የመጣውን ማንነት መሥመሩን ማቋረጥ ከእኛ የሚጠበቅ ነው።

በጥቅሉ አለም አንድ ናት። አንድ ሠው የሚኖረውን የተፈቀደለት በአንድ ምድር ከመሆኑም በላይ ፀሃይ የሚሞቃትም አንድ ግዜ ነው። ህሊና ግን ማመዛዘን የሚችል ባህሪዋ ገንዘቧ ነው፤ ለምንም ስህተት የሚስጥር ቁልፍ የለውምና።

ቸር እንሰብት

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

“ኩዴታ ሲደረግ በቅድሚያ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚገባው የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያ ነው። በአስመራ ይህ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም። ታዲያ እንዴት ነው ኩዴታ ተከናውኗል ሊባል የሚችለው? በርግጥ ገለልተኛና ነጻ የውጪ ሚዲያዎች አለመኖራቸው የመረጃውን መጠንና ጥራት ቢገድበውም እስካሁን የሚወጡት መረጃዎች እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ እንጂ የማስገደድ አይመስልም። በዚህ መነሻ ኢሳያስ ሙሉ በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው ማለት አይቻልም። ግን የመደራደር ነገር ሊኖር ይችላል” አውሮፓ የሚኖር ኤርትራዊ ለጎልጉል የተናገው ነው።

አስር ሺህ የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሏት የሚነገርላት ኤርትራ ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ ዜና አሰምታለች። የተቀየሙ የጦር ሃይሎች የማስታወቂያ ሚኒስቴርን ከበው የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ በማስገደድ ላይ እንደሆኑ የተለያዩ የዓለም መገናኛዎች እየዘገቡ ነው። የመፈንቅለ መንግሥት መደረጉንና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንዳበቃላቸው የገለጹም አሉ። ተቃዋሚዎችን ጨምሮ፡፡

የጎልጉል ዝግጅት ክፍል በቀጥታ አስመራ በመደወል ባገኘው መረጃ መሰረት ዋናውን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቁጥራቸው ከፍተኛ የተባለ ወታደሮች ተቆጣጥረውታል። ወታደሮቹ አፍቃሪ ኢሳያስ የሚባሉት ይሁኑ፣ አፈነገጡ የተባሉት ለማጣራት ግን አልቻለም። “ከተለመደው ውጪ በርካታ ወታደሮች ይመላለሳሉ። አውሮፕላን ጣቢያው ጤነኛ እንቅስቃሴ አይታይበትም” በማለት የተመለከተውንና የታዘበውን ይገልጻል። አያይዞም በከተማዋ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከወትሮው የተለየ እንደሆነ ተናግሯል።

የቴሌቪዥን ጣቢያ የአገር ውስጥ ስርጭቱ እንደተቋረጠ የነገረን የአስመራ ነዋሪ፣ ህዝቡ ሁኔታውን የተረዳና አንድ ነገር እንደሚፈጠር የተረዳ በሚመስል መልኩ ተረጋግቶ ሁኔታዎችን እየተከታተለ እንደሆነ አስታውቋል። በኤርትራ ሁለተኛ ታላቅ ከተማ የምትባለው ባጽዕ (ምጽዋ) ኩዴታ ባከናወኑት ሃይሎች እጅ እንደሆነች መስማቱንም ይናገራል።

አዲስ አበባ መቀመጫቸውን ያደረጉት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ተቃዋሚዎች ለአልጃዚራ እንደተናገሩት የጦር ሃይሉ በኑሮ ውድነት ተማሯል። እለት እለት እየተባባሰ በመጣው የኑሮ ቀውስ መንግስትና ወታደሩ አለመተማመን ደረጃ መድረሳቸውን ከመጠቆም ውጪ በትክክል ምን እየተደረገ እንደሆነ አልገለጹም።

አስመራ የውጪ አገር መገናኛዎችና ገለልተኛ የዜና ወኪሎች ባለመኖራቸው እስካሁን ትክክለኛና ሁሉንም ወገኖች ያካተተ መረጃ አልተሰማም። ይሁን እንጂ በተባበሩት መንግስታት የኤርትራ አምባሳደር አርአያ ደስታ “ምንም ችግር የለም፣ ሁሉም ነገር መፍትሄ ተበጅቶለታል። ሁሉም ነገር መልካም ነው” ሲሉ ለአልጃዚራ አስታውቀዋል።

ታዛቢዎች እንደሚሉት የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ከሚጠይቁት ውጪ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት እንደማይታይ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ግን ኢሳያስ አስመራ እንደማይገኙና ምን አልባትም ምጽዋ እንደሚገኙ የሚጠቁሙት ክፍሎች የኤርትራ መንግስት ኮማ ውስጥ ስለመሆኑ ከበቂ በላይ ምልክቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ከአስመራ በስልክ ያነጋገርነው የከተማዋ ነዋሪ እንዳለው ባጽዕ (ምጽዋ) ያለው ሃይል ከከዳ በርግጥም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ችግር ውስጥ ናቸው ማለት እንደሆነ ገልጾዋል።

በመጨረሻ ባገኘነው መረጃ ኤርትራ ውስጥ መንግስት እንዳልተገለበጠና መንግስትን ለመገልበጥ የሚያስችል እንቅስቃሴ አለመስተዋሉን ነው። ፕሬዚዳንቱ በትክክል ያሉበት ባይገለጽም በቅርብ በመከታተል መመሪያ በመስጠት ላይ እንደሆኑ ከአስመራ በስልክ ሰምተናል። አፈንጋጮቹን ለሚመሩት የጦር መኮንኖች የፖለቲካ እስረኞች የሚፈቱበት አግባብ እንደሚመቻች ቃል መግባታቸውም ተነግሯል።

የአሜሪካ ሬዲዮ አላዝቦ ያቀረበው ዜና አማጺ ያላቸው ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴርን በመቆጣጠር የታሰሩ እንዲፈቱ፣ እኤአ በ1997 የተዘጋጀው ህገመንግስት ይከበር የሚል መግለጫ በማስገደድ ማስነበባቸውን አስደምጧል።ዘግይቶ የደረሰን ዜና በማለት አሜሪካ ዜጎቿ ወደ አስመራ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲገድቡ ትዕዛዝ መስጠቷን ተናግሯል። አፈንጋጮቹ በግዳጅ ላይ ካለው የጦር ሃይል ዘንድ ስላላቸው የጠበቀ ግንኙነት እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ የማስታወቂያ ሚኒስቴርን በመቆጣጠር አስገድደው ያስነበቡትን መግለጫና የፖለቲካ አስረኞች ይፈቱ ጥያቄ ተከትሎ ከዋናው ስቱዲዮው በመቀበል ዜናውን የሚያሰራጨውን መስመር (ዋናውን አንቴና) እንዲቋረጥ በታዘዘው መሰረት ዜናው የጦር ሃይሉና ህዝብ ጆሮ በሚፈለገው ደረጃ እንዳልተዳረሰ ለማወቅ ተችሏል። አስመራ ያልተለመደ የወታደሮች እንቅስቃሴ ከመታየቱ በቀር ሁሉም ነገር የተረጋጋና የመንግስት ማስወገድ እንቅስቃሴ አለ

የሚያስብል አይስተዋልም።

It's a Great Time to BUY a

Home in Minnesota!

"There hasn't been a better

time to BUY in Years..."

Mortgage rates are at an all

time low! Sellers are motivated = Affordble Prices!

Mulugeta Mikael Big Real Estate 1561 Selby Ave

St.Paul, MN

www.bigrealtymn.com

[email protected]

Cell (612) 600-4823

Fax( 651) 967-0484

Real Estate Is Still One of the Best Investments You Can Make

If you are buying or selling a home in the in the Twin city Metro and need agent to help you make the experi-

ence less stressful and more exciting then, Mulugeta Mikael is the right agent for you.

Owning a home is a great investment in your fu-

ture and can lead to many, many years of

happiness.

So why wait? It's a Great Time to BUY!

Call Mulugeta today! @

612-600-4823

የቪኦኤ ዘገባ፡ - ያመፁ የኤርትራ ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ለአንድ ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለቅቀው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡ ወደ አንድ መቶ እንደሚሆኑ የተነገረው ወታደሮች ወደ ደቡብ የጦር ሠፈራቸው የተመለሱት ከፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ዛሬ አብዛኛውን ቀን ዝግ ሆኖ የዋለው የሃገሪቱ ቴሌቪዥን ጠፍቶ የዋለበትን ምክንያት ሣይናገር ምሽት ላይ መደበኛ ፕሮግራሙን ቀጥሏል፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያው ድንገት ከመቋረጡ በፊት አንባቢው ሕገመንግሥቱ እንዲከበር እና የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ መግለጫ ያነብብ እንደነበረ ታውቋል፡፡

ስድስት ሚሊየን ሕዝብ ባላት ኤርትራ ከአምስት ሺህ እስከ አሥር ሺህ የፖለቲካ እሥረኞች ወህኒ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ቢሮ ገልጿል፡፡ እሥረኞቹ (ሰኞ ጃንዋሪ 21) ረፋዱ ላይ በብረት ለበስ መኪና መምጣታቸውንና ቅሬታዎቻችን ናቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች ዝርዝር ይዘው እንደነበረ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ብዙ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሠራተኞች አመልክተዋል፡፡ የወታደሮቹ ጥያቄ ምን እንደነበረ እና አመፁ በምን እንደተፈታ ለጊዜው የተገኘ ዝርዝር መረጃ የለም፡፡ አሥመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ አሥመራ ከተማ ውስጥ ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ አውጥቷል፡፡ የኤምባሲው መግለጫ የሚናገረው በአንዳንድ የዋና ከተማይቱ አካባቢዎች ወታደሮች በብዛት እየታዩ መምጣታቸውን ዲፕሎማቶች መናገራቸውን ነው፡፡ በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከተገነጠለችበት ጊዜ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ መንበሩን እንደተቆናጠጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ኤርትራ ለውጭው ዓለም በአመዛኙ ዝግ የሆነችና በጠንካራ እፍኞች ተጨብጣ የሆነች ሃገር እንደሆነች ይነገራል፡፡ ዛሬ ስለተፈጠረው አጋጣሚ የመንግሥቱን አስተያየት ለመጠየቅ ስልክ በተደጋጋሚ ቢደወልም ባለሥልጣናቱ ስልኮቹን ሳያነሱ ቀርተዋል፡፡ ኤርትራ ሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ አማፂያንን ታስታጥቀለች፤ ትረዳለች በሚል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ - እአአ በ2009 ዓ.ም ማዕቀብ እንደጣለባት ይታወሣል፡፡

በአሁኑ ወቅት በምድር ዙሪያ ስለምናየውና ስለምንሰማው

አለመረጋጋት ከመጨነቅና

ሰላም ከማጣት ይልቅ ሁሉን ወደሚችለው

ፈጣሪያችን ፊት በምልጃና በጸሎት እንቅረብ

“ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና

ስለመኳንንትም ሁሉ እንዲደረግ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ”

1ኛ ጢሞቴዎስ 2:1

ከዳንኤል ክብረት Danielkibret.com

በዘመናዊው የስፖርት ታሪካችን ውስጥ በእግር ኳስ ዓለም እንደ ትናንቱ አንገታችንን ቀና አድርገን በኩራት የሄድን አይመስለኝም፡፡ ለካስ እንችላለን፤ ለካስ ከሠራን የማንሆነው የለም፣ ለካስ ጥረት ካለ ለእኛ ያልተፈቀደ ነገር የለም፤ ለካስ ትብብር ካለ እንዳንወጣው የተከለከለ ተራራ፣ እንዳንሻገረም የታጠረ ገደል የለም፤ ለካስ ‹እችላለሁ› ብሎ ማሰብ ከተቻለ የማይቻል ነገር የለም፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ብራዚል ስትጫወት፣ እንደ ጣልያን ስትከላከል፣ እንደ ስፔን ስታጠቃ ከማየት በላይ ምን መታደል አለ፡፡ ልጆቹ ከባርሴሎና ማሠልጠኛ የወጡ ናቸው እንዴ? የአፍሪካ ዋንጫ የተጀመረው ዛሬ ነው እንዴ? እያሉ እነ ቢቢሲና ሲኤንኤን፣ አልጄዚራና ሱፐር ስፖርት ውዳሴ ሲያዘንቡ መስማት መታደል ነው፡፡

ምርጥ ደራሲ ደርሶት፣ ምርጥ ዳይሬክተር አዘጋጅቶት፣ ምርጥ ተዋንያን እንደተወኑት ምርጥ ድራማ፤ የተጠና፣ የተቀናበረ፣ ምት ያለው፣ የተሠናሰለ፣ ምርጥ ጨዋታ ነበር ልጆቻችን ያሳዩን፡፡ በዚህኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያውን ቀይ ካርድ አይተን፣ በዐሥር ተጨዋች ተጫውተን፣ አስቀድሞ ግብ ገብቶብን በሙሉ መተማመንና፣ በኢትዮጵያዊ ወኔ መጨዋት፣ መረበሽን ተቋቁሞ ከመከላከል ወደ ማጥቃት መዞር፣ በራስ የግብ ክልል እንኳን ተረጋግቶ ኳስ መቀባበል፣ ይህ ነው መጀመርያ የተሸነፈው ቡድን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሀገሩ ወጥቶ ሲጫወት ብዙዎቻችን የምንፈራው ብዙ ግብ አስተናግዶ እንዳይመጣ ነበር፡፡ ሽንፈቱ ቀለል ያለና አጥንት የሚሰብር እንዳይሆን ነበር፡፡ ዛሬ ይህ አስተሳሰብ ተሸንፏል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ መጀመርያ ያሸነፈው ዛምቢያን አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያንን ነው፡፡‹ድብልቅልቃቸው ወጥቶ፣ ደርዘን ግብ አስተናግደው፣ የሌሎች የነጥብ መሰብሰቢያ ሆነው፣ አንገታችንን አስደፍተው ይመጣሉ፤ እኛ ሩጫ እንጂ እግር ኳስ አይሆነንም፤ እንዲያውም ሳናልፍ በቀረብን› የሚሉ የሀገር ቤት ቡድኖችን ነው ያሸነፉት፡፡ ሳላህዲን በዛምቢያ ላይ የተሰጠውን ፍጹም ቅጣት ምት ስቶታል፡፡ በደካማ አስተሳሰቦች ላይ፣ አይሆንም፣ አይሳካም፣ አይቻልም፣ የትም አንደርስም በሚሉ ቀድመው የሚሸነፉ ስሜቶች ላይ የመታውን ፍጹም ቅጣት ምት ግን በሚገባ አስቆጥሮታል፡፡

በጨዋታው አጋማሽና በጨዋታው መጨረሻ በዲኤስ ቲቪ ሱፐር ስፖርት ጨዋታውን ይተነትኑ የነበሩት ባለሞያዎች በኢትዮጵያውያኑ አጨዋወት፣ በራስ መተማመን፣ መናበብ፣ ታክቲክና ጥንካሬ ላይ አስደናቂ የሆኑ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር፡፡ ያውም ከብራዚል ጋር እያነጣጠሩ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ይተላለፉ ከነበሩ የሬዲዮ ፕሮግራሞች በአንዱ የተገኙ አንድ የእግር ኳስ አሠልጣኝም ‹የእኔም ሥጋት ዛሬ ተቀርፏል›› ብለው ነበር የተናገሩት፡፡ ከዚህ በላይ ምን ድል አለ?

አስቀድሞ ሳላህዲን ሰኢዲ ፍጹም ቅጣት ምት ሲስት፣ በኋላም ኢትዮጵያዊው ግብ ጠባቂ በቀይ ሲወጣ የተከፈተው የተስፋ መስኮት ገርበብ ያለ መስሎ ነበር፡፡ በወቅቱ በፌስ ቡክ አስተያየታቸውን ይሰጡ የነበሩ ኢትዮጵያውያንም ‹‹አይይይ›› ‹‹ኡፍፍፍ›› ‹‹ውይይይ›› የሚሉ የንዴት፣ የተስፋ መቁረጥና የቁጭት ድምጾችን ያሰሙ ነበር፡፡ ልጆቹ ግን የነበረውን እንዳልነበረ፣ የተደረገውን እንዳልተደረገ ቆጥረው ግብ እንዳገባ ተጨዋች ነበር የሚጫወቱት፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ያስመዘገበው አዲስ ድል ይህ ነው፡፡ ዳኛው በግብ ጠባቂው ላይ ቀይ ካርድ ቢመዙም፣ ተጨዋቾቹ ግን በመደናገጥና በመረበሽ፣ ተስፋ በመቁረጥና ከንግዲህ አለቀልን በሚለው ስሜት ላይ፣ ከፊሽካ በፊት በመሸነፍና ከፍጻሜው በፊት በመጨረስ ድክመት ላይ ነበር ቀይ ካርዳቸውን

የመዘዙት፡፡ ትናንት ግብ ጠባቂያችን ጀማል ጣሰው አይደለም ከሜዳ

የወጣው፡፡ ‹‹አንችልም አይሆንልንም፣ ዛምቢያኮ ያምናው ሻምፒዮና ነው፤ በጎዶሎ ተጨዋች መጨዋት ከባድ ነው፤ ከእንግዲህ ሌላ ግብ እንዳይገባ መጠበቅ ብቻ ነው፤ በቃ አለቀልን ማለት ነው፤ የኛ ነገር እንዲህ ሊሆን ነው›› የሚለው ቀድሞ አብሮን ይጫወት የነበረ አሥራ ሁለተኛው ክፉ ተጨዋች ነበር በቀይ ካርድ የወጣው፡፡ እንዲያማ ባይሆን እንዲህ ያለ መረጋጋት፣ እንዲህ ያለ በራስ መተማመን፣ እንዲህ ያለ ወኔ፣ እንዲህ ያለ በጎደሎ ተጨዋች ተጫውቶ ማጥቃት፣ እንዲህ ያለ ከቅጣት በኋላ ውብ ጨዋታ ማሳየት፣ እንዲህ ያለ በፈተና ውስጥ እያለፉ ታሪክን መቀየር ከየት ይመጣ ነበር? ጀማል አንተ አይደለህም ከሜዳ በቀይ ካርድ የወጣኸው፣ ይሄ አሥራ ሁለተኛው ክፉ ተጨዋች ነው ከሜዳ የተባረረው፡፡

ቀዩ ካርድ ተመዘዘ፡፡ አንድ ተጨዋች ተቀነሰ፡፡ ተመርተን በመጀመርያው አጋማሽ ከሜዳ ወጣን፡፡ መልበሻ ክፍል ውስጥ ምን ተመከረ? እንዲህ ነበር ያሉት ‹‹እኛ ሙሉ ነን፤ ፈጽሞ ጎደሎ እንደሆንን አናስብ››፡፡ እውነትም ከዕረፍት መልስ የወጣው ቡድን ጎደሎ አልነበረም፡፡ ሙሉ ነበር፡፡ አንድ ብሔራዊ ቡድን

የሚያስፈልገውን ሁሉ የታጠቀ፤ ወኔና ክሂሎት የሰነቀ ቡድን ነበር፡፡ ትናንትና ከዛምቢያ ጋር ነጥብ ተጋርተን ነበር

የወጣነው፡፡ ‹‹ጎዶሎ ነን›› በሚለው ስሜት ላይ ግን ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዘን ነው የወጣነው፡፡

እውነታቸውን ነው ዓለም እንደሆነ ምንጊዜም አትሞላም፡፡ ‹‹ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ›› የሚሆነው ለማስታወቂያ ብቻ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ጉዞ ሲሞላ ሲጎድል ነው፡፡ ታድያ ለምን ያለንን እንጂ የጎደለንን እናስባለን፡፡ ዓይን ላይኖረን ይችላል፤ ግን አእምሮ አለን፤ እጅ ላይኖረን ይችላል፤ ግን ዓይን አለን፤ ሥራ ላይኖረን ይችላል፤ መሥራት የሚችል ሙሉ ጤና ግን አለን፤ እናት ላይኖረን ይችላል፤ ከእናት የሚመረጥ አባት ግን አለን፤ አባት ላይኖረን ይችላል፤ እንደ አባት የሚከባከቡ ብዙ አጎቶች ግን አሉን፤ ውጤት ማምጣት ያለብን ስንሟላ ብቻ ነው እንዴ?

የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ‹ጎደሎ እንደሆንን አናስብ፡፡ በቤታችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በቢሯችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በትዳራችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በንግዳችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በሀገራችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በትምህርታችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በጤናችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በአካላችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ በፍላጎታችን ያልተሟላ ነገር አለ፡፡ ግን ለምን ጉድለታችንን ብቻ እናስበዋለን፡፡ ለምንስ መጉደላችንን ብቻ እየሰብን እንብሰከሰካለን፡፡ ለምንስ የወደፊቱን ላለፈው ነገር ስንል እንሠዋለን፡፡ ለምንስ ነገን በትናንት ምክንያት እናበላሸዋለን፡፡

ተጨዋቾቹ ምንድን ነው ያደረጉት? አንድ ተጨዋች

ጎድሎብናል፡፡ አዎ፡፡ ልንተካው እንችላለንን? አንችልም፡፡ ታድያ ምን እናድርግ? ጎደሎውን በሌላ ነገር እናሟላው፤ በምን? ባለን ነገር ጎደሎውን እንሙላ፡፡ ምን አለን? ተናብቦ፣ ተገናዝቦ፣ ተሳስቦና ተረባርቦ የመጨዋት ችሎታ አለን፡፡ ሀገራዊ ወኔና፣ ኢትዮጵያዊ የማሸነፍ መንፈስ አለን፤ ስለዚህም ይህ ችሎታችን አሥራ አንደኛ ተጨዋች ሆኖ ይጫወታል፡፡ የጎደለን ነገር የለም፡፡ እኛ ሙሉ ነን፡፡ ጎደሎ አይደለንም፡፡ ይህ ነበር ውሳኔው፡፡ ይህ ነበር መርሑ፡፡

ጎደሎውን ባልጎደለው ነገር መሙላት እንጂ ጎደሎውን እኝኝ እያሉ ማሰብ ጉድለትን አያስቀረውም፡፡ የአንዳንዱ ጉድለት የሚታይ ነው፡፡ የሌላው ጉድለት ግን የማይታይ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሙሉ ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን አንድ ተጨዋች ቢጎድለውም የዛምቢያ ቡድን ደግሞ ብዙ ነገር ይጎድለው ነበር፡፡ በአንድ ተጨዋች የማይሟላ ብዙ ጉድለት ነበረበት፡፡ እንዲያውም ትናንት ፍጹም ቅጣት ምቱ ባይሳት ኖሮ የዛምቢያ ቡድን ተሸናፊ ነበር፡፡ ለምን? ቢባል ከአንድ ተጨዋች የሚበልጥ ብዙ ጉድለት ነበረበት፡፡ የእነርሱ ጉድለት እንደኛ ስላልታየ፤ ስላልተቆጠረና በዳኛ ውሳኔ የተፈጸመ ስላልሆነ ነበር ልዩነቱ፡፡

በትናንትናው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ያመጣንበት ትልቅ ድል ቢኖር ‹‹ጎደሎ ነን ብሎ በማሰብና በመጨነቅ›› ላይ የተቆጠረው

ሦስት ነጥብ ነው፡፡ እንደዚያ የምንወዳቸውና የምንንሰፈሰፍላቸው ወላጆቻችን እንኳን ስንት ጉድለት አለባቸው፡፡ እንዲያ ነፍሳችንን የምንሰጥላቸው የአብራካችን ክፋይ፣ የማኅፀናችን ፍሬ የሆኑ ልጆቻችን እንኳን ስንት ጉድለት አለባቸው፡፡ እኛ ራሳችን ስንት ፈልገን ያላገኘነው፤ ጥረን ያልደረስንበት፣ አስበን ያልሆንነው፤ ታግለን ያልጨበጥነው ስንት ጉድለት አለብን፡፡ ግን ጎደሎነታችንን አናስብ፡፡ ያጣነውን ትተን ያገኘነውን እናስብ፤ የሌለንን ትተን ባለን እንጠቀም፤ ያልሆንነውን ትተን በሆንነው እንሥራበት፤ ያልደረስንበትን ትተን በደረስንበት እናፍራበት፡፡ የማይጎድል የለምና፡፡ የዚህ ዓለም ጉዞ አንዱን ጎደሎ እየሞሉ ሌላ ጎደሎ መፍጠር ነው፡፡

ደረጃችን የሚመጥን ጨዋታ ተጫውታችኋል፡፡ አንገታችን ቀና አድርገን እንድንሄድ አድርጋችኋል፡፡ ብዙ ነጥብ አስቆጥራችኋል፡፡ ስለ እናንተ በኩራት እንዲወራ አድርጋችኋል፡፡ ሌሎች ቡድኖች በአውሮፓ ታላላቅ ቡድኖች የሚጫወቱ ተጨዋቾች ይዘዋል፤ እናንተ የላችሁም፡፡ ግን ጎደሎአችሁን አታስቡ፡፡ ሌሎች ቡድኖች ብዙ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፈዋል፤ እናንተ ከሠላሳ ዓመት በኋላ መጥታችኋል፤ ይህንን እንደ ጉድለት አታስቡት፤ ስለ ሌሎቹ ብዙ ይነገር ይሆናል፤ ይህንን እንደ ጉድለት አታስቡ፡፡ ሌሎች የሌላቸው፣ እናንተ ብቻ ያላችሁ ብዙ ነገር አለና ያንን አስቡት፡፡ ለጎደላችሁ ሳይሆን ላላችሁ ነገር ቦታ ስጡት፡፡ ደግሞም ይህ የአድዋ ጦርነት አይደለም፡፡ እግር ኳስ መሆኑንም አትርሱት፡፡ አንችልም፣ አይታሰብም የሚለውን ቡድን አሸንፋችሁ ‹‹የይቻላል ዋንጫ›› ካመጣችሁ እኛ በኩራት ጉሮ ወሸባዬ እያልን እንቀበላችኋለን፡፡ ‹ካፍ› ያልሰጣችሁን ዋንጫም እንሰጣችኋለን፡፡

መልካም ዕድል፡፡

17.7243 18.0788

27.6871 28.2408

1843.4000 1880.2680

250.5100 255.5202

294.3200 300.2064

297.9100 303.8682

98.5000 100.4700

31.0028 31.6229

21.0500 21.4710

22.2555 22.7006

17.2920 17.6378

17.8696 18.2270

4.7260 4.8205

4.8254 4.9219

22.1447 22.5876

2.1151 2.1574 ዋጋ እናወዳድራለን፤ ሌላ ቦታ ውሰዱ በተባሉበት ዋጋ እንሸጥልዎታለን

617 Cedar Ave S Minneapolis, MN 55454

612-332-7020

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ከሰሞኑ ግብይት የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ

24ቱ የሃገር ቤት

ኦርጋኒክ ቢራ በማይታመን

ዋጋ

አክሱሚት እና ጉደር ሁለቱ 15$ ብቻ የሃገር ቤት ጠጦችን ይዘዙን በተመጣጣኝ ዋጋ እናደርሳለን።

ምንዛሪ ግዢ ሽያጭ

የአሜሪካን ዶላር 18.2377 18.6025

ፓውንድ 28.9396 29.5184

ስዊዝ ፍራንክ (100) 1955.1600 1994.2632

የስዊድን ክሮነር(100) 278.6300 284.2026

የኖርዌይ ክሮነር(100) 324.9800 331.4796

የዳኒሽ ክሮነር (100) 324.9700 331.4694

የጅቡቲፍራንክ(1000) 101.3000 103.3260

የህንድ ሩፒ (100) 33.9369 34.6156

የኬንያ ሽልንግ (100) 20.9500 21.3690

የጃፓን የን (100) 20.3750 20.7825

የካናዳ ዶላር 18.3589 18.7261

የአውስትራሊያ ዶላር 19.1824 19.5660

የሳዑዲ ሪያል 4.8630 4.9603

የኤመሬትስ ድርሃም 4.9652 5.0645

ዩሮ 24.2598 24.7450

የደቡብ አፍሪካ ራንድ 2.0529 2.0940

0

ከአፍሪካ ዋንጫ ምን እንጠብቅ?

ከቦጋለ አበበ የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር

ባለፉት አስር ዓመታት ከተካሄዱ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች በብዙ መልኩ ይለያል። በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ለሃያ ዘጠነኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ዋንጫ በአንድ ዓመት ልዩነት የተካሄደ ልዩ የዋንጫ ውድድር ነው። ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ ወደ መሰረተችው የአፍሪካ ዋንጫ ከሰላሳ አንድ ዓመት በኋላ ባልተጠበቀ ሁኔታ በድንቅ ብቃት የተመለሰችበት ነው። ኬፕቨርዴ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊ ውድድሩን ተካፋይ የሆነችበት መሆኑም ለልዩነቱ ሌላው ምክንያት ነው።

ኢትዮጵያ ከበርታ ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ስትመለስ፤ኬፕቨርዴ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ የመሆን እድል ታግኝ እንጂ ሁለቱ ሀገሮች ሻምፒዮናውን ለመቀላቀል ያሳዩት ብቃት ዓለምን እያስደመመ ይገኛል። ኢትዮጵያ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ያላቸው ቤኒንና ሱዳንን የመሳሰሉ ሀገሮችን በአስደናቂ ሁኔታ አሸንፋ በአፍሪካ ዋንጫው የመሳተፍ እድል ማግኘቷ በሀገራችን እግር ኳስ ላይ ታላቅ መነቃቃት ፈጥሯል። ዋልያዎቹ በመባል የሚታወቁት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቻችን በሻምፒዮናው የተለየ ደረጃ ይደርሱ ዘንድ ፌዴ ሬሽኑ ከህዝብ ጋር ተባብሮ የተወሰኑ የወዳ ጅነት ጨዋታዎች ለማካሄድ ችለዋል። የወዳጅነት ጨዋ ታዎቹ ላይ ዋልያዎቹ ያሳዩት አስደናቂ ብቃትም ሀገራችን ከተሳትፎ ባለፈ በአፍሪካ ዋንጫ ጠንካራ ተፎካካሪና አዲስ ክስተት ትሆናለች የሚል ግምት ከዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ተሠጥቷል።

(ከአፍሪካደ ገጽ 13 የዞረ)

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Two Location

5103 University Ave, NE,

5104Columbia Heights, MN 55421 2929 university Ave. SE

Minneapolis, MN 55414

የኢሳያስ ከበደ ምላሽ፡- የአራስነት ጊዜ እስከመቼ እንደሆነ ለብዙዎቻችን ግልጽ ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንዶች የተወለደው ልጅ ዓመት እስኪሞላው ተራክቦ የማይፈጽሙ አሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ መንፈቅ ዓመት ይጠብቃሉ፡፡ ፈጠን ያሉት ደግሞ በ3ኛው ቀን ግንኙነት እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ ይሄ ሁሉ ታዲያ ስህተት ቢሆንም ላለማሳሳት ግን ማወቅ የግድ ነውና ለተራክቦ ቁርጥ ያለው ቀን መለየት ይኖርበታል፡፡ በህክምናው ዓለም አንድ ነፍሰ ጡር ሴት በወለደች እስከ 42ኛው ቀን ከወሲባዊ ግንኙነት እንድትርቅ ትመከራለች፡፡ ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋናዎቹ ግን የመራቢያ አካላቶችና ስነ ልቦናዊ ዝግጅቶች ከ42ኛው ቀን በፊት ስለማይኖሩ ነው፡፡ በወሊድ የተነሳ ከማህፀን ጀምሮ እስከ ውጪው የብልት ክፍል ድረስ ቁስለቶች ከመኖራቸውም አንፃር

ህመም ማስከተላቸውና ለኢንፌክሽንም በቀላሉ የተጋለጡ ስለሚሆኑ የ6 ሳምንታት ማገገሚያ ቀናት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚያም ላይ የተራክቦአዊ ሆርሞኖች አመራረት የተዛባ በመሆኑ በቂ የስነ ልቦናዊ ዝግጁነት በሴቲቱ ዘንድ ሊኖር ስለማይችል ወንዱ ተፅዕኖ ማድረግም አይጠበቅበትም፡፡

ወደ ጥያቄው ስንመለስ በ2ኛው ወሲባዊ ግንኙነታችሁ ወቅት ደም ከብልትሽ ሊፈስ ችሏል፡፡ እንግዲህ የብልት ደም ምንጭ ከውጪኛው ፍትወት አካል እስከ ውስጠኛው ማህፀን ክፍል ድረስ ካሉት የመራቢያ አካላት ሊነሳ እንደሚችል ይታወቃል፡፡ ከአንቺ የደም አፈሳስ መገመት የሚቻለው ግን ከማህፀንሽ ውስጥ ሳይመነጭ አልቀረም፡፡ ብዙውን ጊዜ የረጋ ደም የሚፈሰው ከዚህ ክፍል ነው፡፡ ማህፀን ልጅሽን ለዘጠኝ ወር ሲመግብ የቆየውን የእንግዴ ልጅ አስጠግቶና ላዩ ላይ

አጣብቆ ደም ሲለግስ ከርሟል፡፡ ልጁም ሲወለድ ከእንግዲህ ምንም የማይሰራው የእንግዴ

ልጅ እምቦቀቅላውን ተከትሎ አብሮ ከማህፀን ይወገዳል፡፡ እንግዴ ልጅ የተጣበቀበት የማህፀን ክፍል ወደ እንግዴው ይሄዱ የነበሩ ደም ስሮች እስኪዘጉና ይህም ቦታ በደንብ እስኪያገግም ድረስ ለተወሰኑ ጥቂት ቀናት በብልት ደም መምጣቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አፈሳሰሱ በየቀኑ እየቀነሰ መምጣት ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ሙሉ በሙሉ መቆም አለበት፡፡

ወሲብ ከላይኛው የአንጎል ክፍል እስከ ታችኛው የእግር ጫፍ ድረስ ያሉ አካላዊ ክፍሎችን በሞላ የሚያስተባብር ክዋኔ ነው፡፡ በተለይ ማህፀን ደግሞ በእርካታ ወቅት ዋነኛው ተርገብጋቢ አካል ነውና እያገገመ ካለው የማህፀን ቁስለት ደም

አገርሽቶ ሊፈስ ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ወዲያው ስለሚያቆም ጉዳት ላያስከትል ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ የወለዱ ሴቶች የወር አበባ ማየት የሚጀምሩት ከ6ኛው ሳምንት በኋላ እንደሆነ ቢታወቅም አንዳንዴ ግን በወለዱ በወራቸው ሊያዩ የሚችሉ ይኖራሉ፡፡ ወሲብ ደግሞ ይህን መሰል የደም ፍሰት አባባሽ ነውና ብዙም የሚያስደነግጥ አይሆንም፡፡ ለማንኛውም ደም ፍሰቱ ያልተጠበቀ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሊያሳስባችሁ ቢችልም የሐኪም እርዳታን ለመሻት የሚያነሳሳው ግን ደሙ በየቀኑ መፍሰሱን ካላቆመ ወይም ብዙ ደም ከፈሰሰ ነውና ድንገት ፈሶ የቆመ ደም ተመልሶ እንደገና በራሱ ካልፈሰሰ በቀር አስጊ አይደለም፡፡ እናም ዳግም እንዲህ መሰል መሳሳት ግን ከ3 ሳምንታት በፊት እንዳይፈፀም ያስፈልጋል፡፡

መልካም ዕድል።

የአጋጣሚ ነገር ሆኖ 31ኛ ዓመት የልደት በዓሌን ካከበርኩ ከሶስት ቀን በኋላ የምታምር ሴት ልጅ በሰላም ተገላግያለሁ፡፡ ከባለቤቴ ጋር ለአራት ዓመት በፍቅርና በመተሳሰብ ቆይተን በያዝነው እቅድ መሰረት ልጅ የማግኛ ጊዜያችን ነው ባልንበት ወቅት ነው እግዚአብሔር ተጨምሮበት ልጃችንን ለመሳም የበቃነው፡፡ በእርግዝናዬ ወቅት የህክምና ክትትል በማደርግበት ሆስፒታል ትንከባከበኝ የነበረችውን ባለሙያ በማማከር ከባለቤቴ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ይህም የፈጠረብኝ ምንም አይነት ችግር የለም፡፡ ልጅ ከወለድኩ አንድ ወር ከሞላኝ በኋላ ከባለቤቴ ጋር ግንኙነት ጀምረናል፡፡ ችግሩም ከዚህ በኋላ የተከተለ ነው፡፡ ከባለቤቴ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ግንኙነት ካደረግኩ በኋላ ከብልቴ ደም መውረድ ጀመረ፡፡ ከዚያም በኋላ አንድ ሁለቴ ተመሳሳይ ሁኔታ አስተዋልኩ፡፡ ጉዳዩ ቢያሳስበኝ ለጓደኛዬ አማከርኳት፡፡ እሷም ቢያንስ መንፈቅ (6 ወር) ሳይሞላሽ ግንኙነት ማድረግ አልነበረብሽም አለችኝ፡፡ ለመሆኑ የደም መፍሰሱ የተከተለብኝ በትክክል ግንኙነት በመጀመሬ ነው? ልጅ ከተወለደ በኋላ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ የሚፈቀደው ከስንት ጊዜ በኋላ ነው? በአራስነቴ ወሲብ መፈፀሜ የሚያስከትልብኝ የጤና ችግር ይኖራል? የችግሬን አሳሳቢነት ተረድታችሁ ከሌሎች ጥያቄዎቻችሁ አስቀድማችሁ ምላሽ እንደምትሰጡኝ እተማመናለሁ፡፡ ሰላም ነኝ

ምላሽ፡- በቅድሚያ ለረጅም ዘመን ወሲብ ሳትፈፅም መቆየትህን ገልፀሃል፡፡ ከዚህ ጀርባ ደግሞ የህይወት ህልምህን ከግብ ሳታደርስ መቀመጡን አለመምረጥህን ጠቁመሃል፡፡ በእውነት ይሄ በአርአያነት ሊጠቀስ የሚችል ታላቅ ራስን የመ ጠበቅ ተግባር ነውና በራስህ መሸማቀቅና ማፈር ሳይሆን እንዲያውም ልትኮራ ይገባሃል፡፡ አስታውስ፣ ከድሃ ቤተሰብ ተወልዶ ህይወቱን ለማሳመር ደፋ ቀና ማለት ሲገባው የወጣትነት እሳታዊ ጥሪውን ተቀብሎ ከእሳት ጋር ለመጫወት የመረጠና እንደ ድርጊቱ የእሳት ራት ሆኖ፣ ሰርቶ ራሱንና ሀገሩን ሊጠቅም በሚችልበት ዕድሜ የአልጋ ቁራኛ ለመሆን የሚበቃው እንኳ ጥቂት አይደለም፡፡ ዘመኑ የአደጋ ነው፡፡ እግሩን ሊሰበስብ የመረጠው ረጅምና ጤናማ ህይወት ይጠብቀዋል፡፡ መዝለልን የመረጠው ደግሞ ዕድሜውንና ጤናውን ይሰብራል፡፡ ታዲያ በዚህ ዘመን ከወሲብ ተቆጥቦ አላማው እስኪሳካ ድረስ መጠበቅ ሌላ የጤና ችግር የሚያመጣ ቢሆን እንኳ ‹‹ይሁን›› የሚባል ነው፡፡ አስደሳቹ ነገር ደግሞ ከወሲብ ታቅቦ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚያስከትለው አንዳችም አካላዊና አዕምሯዊ የጤና መዘዝ አለማስከተሉ ነው፡፡ ወንዶችን በተመለከተ ይህንን እውነታ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ በእርግጥ ሴቶችን በተመለከተ ድንግልና በመኖሩ ምክንያት የመበራከት አዝማሚያ ያላቸው ጥቂት የጤና ችግሮችን (ለምሳሌ የኦቫሪ ካንሰርን) እየጠቃቀሱ ይህንን እውነት መፈታተን ይቻላል፡፡ ሆኖም በተቃራኒው ወሲብ አዘውታሪዎች ዘንድ የሚከሰቱት በቁጥርና በስፋት የትየለሌ የሆኑ ችግሮችን በማውሳት በእርግጠኝነት ተቆጥቦ መኖር የተሻለው አማራጭ መሆኑን ልንጠቁም እንወዳለን፡፡ የሰውነታችን የወሲብ ጥሪ እንደ ሌሎች አስፈላጊ ድርጊቶች (ለምሳሌ መፀዳዳት) ለረጅም ጊዜ ሳይደረግ ቢቆይ ችግር የሚያመጣ አይደለም፡፡ ወንዱ ላይ ያለውን ሁኔታ ለአብነት እንመልከት፡፡ የወንድ የዘር ፍሬ ወሲብ ተደረገ አልተደረገም የዘር ፈሳሽ (Semen) ማመንጨቱን ይቀጥላል፡፡ የወሲብ ግፊት ይመጣል፡፡ ይህ ግፊት ተጭኖ ከታለፈ አካላችን የራሱን እርምጃ ይወስዳል፡፡ በእንቅልፍ ሰዓት የዘር ፍሬን ማፍሰስ (natural emission) የዚህ የአካላችን ምላሽ መግለጫ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ራስን በራስ የማርካት ድርጊት (masturbation) ይጨምርና የአካል ጥሪ ምላሹ

ይሟላለታል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በአዘቦቱ እንደ ኃጢአት የሚታዩና ለድርጊቱ ፈፃሚ ደግሞ ራስን የመጥላት ስሜት የሚያሳድሩ ቢሆኑም ተፈጥሯዊውን የአካል ጫና በማለዘብ በኩል ካላቸው ድርሻ አንፃር በአንፃራዊነት የተሻሉ ሊባሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ በዚህ መሀል ከወሲብ የተቆጠበ ሰው ለህይወቱ አጋር የምትሆነዋን ሴት መርጦ ወደ ጋብቻ ሲያመራ ‹‹ቀና መንገድ›› ተብሎ ይመሰከርለታል፡፡ ሆኖም በቂ የወሲብ ልምድ አለመኖርና በአንተ ላይ የተስተዋለው ‹‹መቆየቴ ችግር ያመጣብኝ ይሆን?›› የሚለው ጭንቀት ወሲባዊ ክህሎት (Performance) ላይ ጣጣ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ወሲባዊ ብቃትና ክህሎት በአዕምሮ ወለድ ረብሻዎች በቀላሉ ሊታወክ የሚችል ስሱ (sensitive) ነው፡፡ የስነ ወሲብ ተመራማሪዎች በተደጋጋሚ እንደገለፁት የወሲብ እንከኖች ምንጫቸው አብዛኛውን ጊዜ የባለቤቱ አዕምሮ ነው፡፡ አንዳችም አይነት አካላዊና ስር ነቀል የአዕምሮ ህመም ሳይኖራቸው ‹‹ብቃት የለኝም›› በሚል ጭንቀትና በራስ የመተማመን መንፈስ በማጣት የተነሳ ብቃታቸው በማሽቆልቆሉ ምክንያት በቀላሉ የስንፈተ ወሲብ ሰለባ የሚሆኑ ጥቂት አይደሉም፡፡ ይህ ችግር በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ በሚያደርጉ ላይ ይስተዋላል፡፡ በሚደረገው ነገር እርግጠኝነት አለመኖር፣ ባይሳካልኝስ የሚል ጭንቀትና ጉጉት ተደራርበው የወሲብ አካልመነቃቃት (erection) እንዳይኖር፣ ወይም ወሲብ ሳይጀመርና እንደተጀመረ ወዲያው የዘር ፈሳሽ ማፍሰስ... የመሳሰሉት ሁኔታዎች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ፡፡ ጊዜ ሲቆይና በራስ መተማመኑ ሲዳብር እንዲሁም ከወሲብ ተጋሪ ጋር መላመድ ሲፈጠር እኚህ ሁኔታዎች የመክሰም አዝማሚያ አላቸው፡፡ ሀሳቡን ጠቅለል አድርገን ስናስቀምጠው የሚከተሉት ምክሮች እንዲህ ይሉናል፡፡ 1. ያለ ወሲብ ለረጅም ጊዜ መቆየትህ የሚያስከትለው ጣጣ እንደሌለ ለራስህ ደጋግመህ ንገረው፡፡ ይህ ጭንቀት ለብቃትህ አለመኖር ተጠያቂ እንደሆነ አትዘንጋ፡፡ 2. ወሲብ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈፀም አጥጋቢ ስኬት አለማግኘቱ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ጊዜ ሲቆይ ይህ ችግር ቀስ እያለ ይለዝባል፡፡ 3. ከወሲብ ተጋሪህ (ጓደኛህ) ስለነገሩ በግልፅ መወያየት ከሁሉም የሚጎላው መፍትሄ ነው፡፡ በግልፅ ተነጋገሩ፤ (ያለ ወሲብ... ወደ ገጽ 11 የዞረ)፟

የ27 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ በዕቅድና በቁጠባ በመኖር ወደ ፊት የራሴን ተቋም የመመስረት አላማ አለኝ፡፡ በአጭር ጊዜም ይህን እንደማሳካም እተማመናለሁ፡፡ ራዕዬ ብዙ ነው፡፡ ይህን ማሳካት የምፈልገው በቤተሰቦቼ ሀብት፣ በብድር አሊያም ተገቢ ባልሆነ መንገድ ሳይሆን በራሴ እውቀትና በማጠራቅመው የቁጠባ ሂሳብ አማካኝነት እንደሚሆንም እርግጠኛ ነኝ፡፡ አሁን መንገዴን አጋምሼዋለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህም ሆኖ ግን በፍቅር ህይወት የሚረብሸኝ ነገር አላጣሁም፡፡ የወደፊት ራዕዬን ለማሳካት በማሰብ ከሴቶች ጋር አንዳችም ወሲባዊ ግንኙነት ላለማድረግ በመወሰን ታቅቤ እኖራለሁ፡፡ ይህን ያደረግኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ወደ ዝርዝሩ ባልገባም ከዚህ ቀደም ከሁለት ሴቶች ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደነበረኝ መሸሸግ አልፈልግም፡፡ የመጀመሪያዋ በምስጢር የእንግሊዝ ሀገር ጉዞዋን ስታመቻች ቆይታ ሳትነግረኝ መሄዷ ብዙ ጎድቶኝ ነበር፡፡ ራሴን ካረጋጋሁ በኋላ ግን ሃይስኩል አብራኝ ትማር ከነበረች ልጅ ጋር በአጋጣሚ ተገናኝተን በፍቅረኝነት ቆይተን ነበር፡፡ ሆኖም እየዋሸችኝ ተቸገርኩና በሰላም ለመለያየት ወሰንን፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ወሲብን እርግፍ አድርጌ የተውኩት፡፡ አሁን እያሳሰበኝ የሚገኘው ያሳለፍኩት ታሪክ አይደለም፡፡ አላማዬን ለማሳካት ስል ከሴት ጋር ግንኙነት ሳላደርግ ረዥም ጊዜ መቆየቴ ወደ ፊት ከማገኛት ፍቅረኛዬ አሊያም የትዳር አጋሬ ጋር የወሲብ አለመጣጣም ችግር ሊያመጣብኝ ይችል ይሆን ወይ? እያልኩ ከራሴ ጋር እሟገታለሁ፡፡ ያለ ወሲብ ረዥም ጊዜ መቆየቴ ወደ ፊት ችግር ያስከተልብኝ ይሆን?... ችግሩ የሚፈጠር ከሆነስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል? ሰለሞን

መልስ፡- በመጀመሪያ የታዘዘልህን መድሃኒት ከባለሙያ ጋር ሳትመካከር የታዘዘልህን መድሃኒት ማቋረጥህ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከባለሙያ ትዕዛዝ መድሃኒት መውሰድም ሆነ የታዘዘ መድሃኒትን ማቋረጥ ለበርካታ ውስብስብ ችግሮች ያጋልጣል፡፡ በመቀጠል ደግሞ ‹‹ጭንቅላቴ ውስጥ የሚጮህና በሰው ተመስሎ በሄድኩበት የሚከታተለኝ ነገር አለ›› ብለሃል፡፡ የጠቀስከው ነገር ምን አልባት ከሌላ የስነ አዕምሮ ቀውስ ጋር የተገናኘ ሊሆን ስለሚችል ባለሞያ ማማከር አለብህ፡፡

ውድ ጠያቂያችን እንቅልፍ መተኛት አለመቻለህ በራሱም ሌላ አሳሳቢ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም እንቅልፍ ለሰው ልጅ አስፈላጊ ከሆኑ የተፈጥሮ ግዴታዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ አንድ ሰው ጤናማና አምራች የሚሆነው እንዲሁም የተስተካከለ የአካልና አዕምሮ ጤና የሚኖረው ‹‹ንቁ›› የስራ መንፈስ ኖሮት ከሌሎች ሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖር የሚችለው በቂ እንቅልፍ ማግኘት ሲችል ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም የአዕምሮ ሰላምና እንቅልፍ ማጣት አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማህበራዊ ጤናን ያናጋል፡፡ አንድ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ጎልማሳ የተስተካከለ ጤና እንዲኖረው በቀን ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ለሚሆን ጊዜ እንቅልፍ መተኛት አለበት፡፡

ውድ ጠያቂያችን ክፍሌ የእንቅልፍ ችግር ለተለያዩ የጤና ቀውሶች ያጋልጣል፡፡ ድንገተኛ የሆነ ክብደት መጨመር፣ ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት፣ አደገኛ ለሆነ የልብ ህመም የመጋለጥ አደጋ፣ ስኳርን ለመሳሰሉ ተላላፊ ላልሆኑ የጤና ችግር የመጋለጥ አደጋ፣ የሰውነት የበሽታ መከላከል ብቃትን መቀነስ፣ ለድብርት ህመም መጋለጥ እንዲሁም በስራም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ዘገምተኛ መሆን ዋነኛዎች ናቸው፡፡

ውድ ጠያቂያችን ክፍሌ የእንቅልፍ ችግር የአንተ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እስከ 58% የሚሆኑ አሜሪካዊያን የተለያየ መጠን ባለው የእንቅልፍ ማጣት ችግር ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜም የእንቅልፍ የማጣት ችግር ዕድሜያቸው ከ20 እስከ 45 ዓመት በሆኑ ሰዎች ላይ በስፋት ይታያል፡፡

እንደ አንተ አይነቱ የእንቅልፍ ችግርን የስነ ልቦና ባለሞያዎች ኢንሶሚኒያ በማለት ይጠሩታል፡፡ የእንቅልፍ ማጣት ችግር ሁለት አይነት መገለጫዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚታይ እንቅልፍ ችግር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይና እንቅልፍ ማግኘት ያለመቻል ወይንም በእንቅልፍ ወቅት በተደጋጋሚ መንቃትን ተከትሎ በቂ እንቅልፍ ማግኘት አለመቻል ነው፡፡

በአጠቃላይ እንደ የስነ ልቦና ባለሞያዎች ገለፃ እንቅልፍ የማጣት ችግር የተከሰተበትን ጊዜ መነሻ በማድረግ እንቅልፍ የማጣት ችግርን በሶስት ዋና ዋና አይነቶች ይከፍሉታል፡፡ የመጀመሪያው ቀላል የሆነ እንቅልፍ የማጣት ችግር (ትራንሲነንት ኢንሶሚኒያ) ነው፡፡ ቀላል እንቅልፍ የማጣት ችግር ከአንድ ሳምንት ላልበለጠ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ሲሆን መንስኤውም በተለያዩ ጊዜያዊ ህመሞች መጠቃት፣ ድብርት ለተባለው ህመም በመጋለጥና ከፍተኛ መጠን ላለው ለጭንቀት በመጋለጥ የተነሳ ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህ አይነቱ የእንቅልፍ ማጣት ችግር የተጠቁ ሰዎች መፍዘዝና የሰውነት መዳከምን የመሳሰሉ አካላዊ ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡

ውድ ጠያቂያችን ክፍሌ ሁለተኛው የእንቅልፍ ማጣት ችግር ደግሞ ከባድ እንቅልፍ የማጣት ችግር (አኪውት ኢንሶሚኒያ) ነው፡፡ ይህ አይነቱ እንቅልፍ የማጣት ችግር ከአንድ ወር ላላነሰ ጊዜ በተከታታይ የሚከሰት ሲሆን መንስኤውም መፍታት ያልቻልነው ጊዜያዊ ችግሮችን ተከትሎ በሚከሰት ጭንቀትና መረበሽ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡

ውድ ጠያቂያችን በሶስተኛ ደረጃ የሚቀመጠው የእንቅልፍ የማጣት ችግር ደግሞ ዘላቂ እንቅልፍ የማጣት ችግር (ክሮኒክ ኢንሶሚኒያ) በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ አይነቱ የእንቅልፍ ማጣት ችግር ለወራት ብሎም ለዓመታት የሚዘልቅ ነው፡፡ ዋነኛ መንስኤውም በተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች መጠቃትን፣ ከባድ በሚባል ችግርና ጭንቀት ውስጥ መግባትን፣ የሆርሞኖች ለውጥ መከሰትና በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ሳይኮቲንስ የሚባለው ኬሚካል መጠን መዛባትን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል፡፡

በአደገኛ እንቅልፍ የማጣት ችግር መጠቃት በተጠቃው ሰው ላይ በርካታ ችግሮችን ያስከትላል፡፡ የአካልና የአዕምሮ መድከም፣ የሌሉ ድምፆችን መስማትንና በአካባቢው ላይ የሌሉ ምስሎችንና እንቅስቃሴዎችን መመልከት የመሳሰሉ ችግሮችን ያስከትላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አደገኛ እንቅልፍ የማጣት ችግር ያለባቸው ሰዎች ነገሮችን ሲመለከቱ የተደበላለቀና ብዥ ያለ ምስል ይሰጣቸዋል፡፡ ነገሮችን በቶሎ የመገንዘብ አቅማቸውም እጅግ አነስተኛ ነው፡፡

ውድ ክፍሌ በደብዳቤህ ላይ የጠቀስካቸውን ነገሮች መነሻ በማድረግ የአንተ ችግር አደገኛ ወይንም ዘላቂ የሚባለው እንቅልፍ የማጣት ችግር እንደሆነ እንገምታን፡፡ ከባድ የሚባለው እንቅልፍ የማጣት ችግር በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ቢችልም ስኪዞፍሬኒያን ጨምሮ ለተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች መጋለጥ ዋነኛ መንስኤው ነው፡፡ ጭንቀትም ሌላኛው የእንቅልፍ ማጣት ችግር መንስኤ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ አነቃቂ እፆችን ማለትም ቡና፣ ጫት፣ ኒኮቲንና ኮኬይንን በጭስ ወይንም በፈሳሽ መልኩ መውሰድ እንዲሁም አልኮል አብዝቶ መጠጣት የእንቅልፍ ማጣት ችግርን ያባብሳል፡፡ ለተለያዩ ህመሞች ተብለው የሚወሰዱ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳትም የእንቅልፍ ችግርን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከባድ የእንቅልፍ ማጣት ችግር ሪህን በመሳሰሉ የእግር ህመሞች የተነሳ በሚፈጠር የማቃጠልና የመጠዝጠዝ ስሜት የተነሳም ሊከሰት ይችላል፡፡ ስራ ማጣትና የገንዘብ አቅም መሳሳትን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አዕምሮ በመረበሽ የተነሳም ሊከሰት ይችላል፡፡ አንጎል ላይ የሚደርስ ጉዳት፣ የመኝታ ክፍላችን ምቹ አለመሆን በተደጋጋሚ አስደንጋጭና አስፈሪ ህልሞችን መመልከት፣ ከመኝታ በፊት ከባድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እና በራስ ወይንም በቤተሰብ ላይ የሚደርስ ድንገተኛ ጉዳት ወይንም አደጋ ዘላቂ የሆነ እንቅልፍ የማጣት ችግርን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ውድ ጠያቂያችን ወደ መፍትሄው ከማምራታችን በፊት በቅድሚያ ለዚህ ችግር የተዳረከው ምን አልባት ከላይ ከተዘረዘሩት የእንቅልፍ ማጣት መንስኤዎች በአንዱ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ‹‹ለዚህ ችግር ሊያጋልጠኝ ይችላል›› የምትለውን ምክንያት ለይተህ ለማወቅ ሞክር፡፡ በመቀጠል ደግሞ ባለሞያዎችን ቀርበህ ለማማከር ሞክር፡፡

ውድ ክፍሌ በህክምና ባለሞያ የሚታዘዘው የእንቅልፍ መድሃኒትም ጭምር ከሰውነታችን ጋር እየተላመደ ሲመጣ መድሃኒቱን ካላገኘ ለመተኛት ስለሚቸገር ግድ ካልሆነብን በስተቀር ባንወስደው ይመረጣል፡፡ ከመድሃኒቱ ይልቅ የምንተኛበትን የመኝታ ክፍልና የምንተኛበትን የመኝታ ቦታ ምቹ ማድረግ፣ አነቃቂ አደንዛዥ እፆችን ከመውሰድ መቆጠብ፣ እንቅልፍ የማጣት ችግርን የሚያስከትሉ አላስፈላጊ ባህሪዎችን ማስወገድ፣ ራስን ዘና ማድረግንና በሰውነት ውስጥ የሚኖር የደም ዝውውር ጤናማ ማድረግ ማንኛውንም አይነት የእንቅልፍ ችግርን ያቃልላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቋሚ የሆነ የመኝታ ሰዓት መኖር፣ ወደ መኝታ ከመሄዳችን በፊት አብዝቶ ውሃ አለመጠጣት፣ ከመተኛታችን በፊት በተለይ ሃይማኖታዊ መጽሐፍትን የማንበብ ልማድን ማዳበር፣ ወደ መኝታ ከመሄዳችን በፊት ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ፣ ቀለል ያሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይመከራል፡፡

ክፍሌ እባላለሁ፡፡ የ28 ዓመት ወጣትና በንግድ ስራ የምተዳደር ነኝ፡፡ ከፍተኛ የእንቅልፍ ችግር አለብኝ፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት መተኛት አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱን ባላውቅም በፍፁም እንቅልፍ አይወስደኝም፡፡ ለደንቡ አልጋዬ ላይ እወጣለሁ እንጂ ምንም አይነት እንቅል በአይኔ ሳይዞር እንዲሁ ስገላበጥ ነግቶ ወደ ስራ እሄዳለሁ፡፡ ችግሩ የጀመረኝ ከሁለት ዓመት በፊት ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን በጣም እየተባባሰብኝ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አልፎ አልፎ ጭንቅላቴ ይጮህብኛል፡፡ በሰው ተመስሎ በሄድኩበት ቦታ የሚከታተለኝ ነገርም አለ፡፡ ይሄ ነገር ብዙ ችግር እያስከተለብኝ ሰውነቴን ጎድቶታል፡፡ መስራት እንዳልችል አድርጎኛል፡፡ ከሰው ጋር እንድጋጭና ነጭናጫ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ በአካባቢያችን ወደሚገኝ ሆስፒታል ሄጄ ለእንቅልፍ ችግር ብለው የሰጡኝ መድሃኒት ችግሬን በተወሰነ መልኩ ቢያቃልለውም ጥሩ የማይባል ስሜትን ስለሚፈጥርብኝ አቁሜዋለሁ፡፡ መድሃኒቱን መውሰድ ካቆምኩ በኋላ ችግሬ እንደገና አገርሽቶብኛል፡፡ በዚህም የተነሳ እኔም ሆንኩ ቤተሰቦቼ ተረብሸናል፡፡ ስለዚህ እናንተ መፍትሄ የሚሆን ምክር አታጡምና በፍጥነት አንድ ነገር በሉኝ፡፡

ከሊሊ ሞገስ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ችግሮችን የሚያሸንፉበት ኃይልን

የሚሰጣቸው ምንድነው? የዛሬው ርዕሰ ጉዳያችን የሆነው ‹‹ጽናት›› የምንለው ነገር አንድ ሰውን ወደ አምላካዊ ኃይል መጠጊያ መንፈሳዊ ጉልበት ይሰጣል፡፡ አንዴ በጦርነቱ ከተሸነፉና ዓለም ሁሉ በተቃወማቸው ጊዜ በጽናት ውጊያቸውን ለሚቀጥሉ ሰዎች ጥበብ እራሷን አሳልፋ ትሰጣለች፡፡ ለዚህም እንደ ሄነሪ ፎርድ አይነት ሰዎች ከትቢያ ተነስተው ጸንተው በመታገላቸው ብቻ በአለማችን ታላቁን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የበቁ ሰዎችን፣ እንዲሁም እንደ ቶማስ ኤዲሰን ከሶስት ወር ባነሰ ትምህርት የዓለም ምርጥ ፈላስፋ የሆኑትን፣ ጽናትን ወደ ተናጋሪ ማሽንነት፣ ተንቀሳቃሽ ማሽንነት የለወጡ ሰዎችን ተመልከቱ፡፡ ታዲያ የነዚያን ሰዎች የቅርብ ታሪክ ብታጠኑ ሁሉም ለታላቅ ስኬት ያበቃቸው ጽናት እንደሆነ ትረዳላችሁ፡፡

በእርግጥም አንድ ሰው የአለማችንን ነብዮች፣ ፈላስፎች፣ የተአምር ሰዎችንና የሐይማኖት ሰዎችን ታሪክ ቢያጠና ኃይልን ለማስተባበር ጽናትና የተወሰነ አላማ የስኬታቸው መሰረቶች

እንደሆኑ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል፡፡ የመንፈስ ጠንካራነት መሰረቱ አንድን ነገር የመሻት ኃይል ነው፡፡ የመሻት ኃይልና ፍላጎት በሚገባ ሲጣመሩ ደግሞ ሊለያዩ የማይችሉ ጥንዶች ይሆናሉ፡፡

ብዙ ሰዎች የመጀመሪያ እክል ምልክት ሲያጋጥማቸው ያቀዷቸውን አላማዎችና ግቦችን ለመተው ጊዜ አይፈጅባቸውም፡፡ ጥቂቶቹ ግን ምንም እንኳ ብዙ እክሎች ቢያጋጥሟቸውም አላማቸውን እስኪያሳኩ ድረስ በቁርጠኝነት ይቀጥሉበታል፡፡ የመንፈስ ጽናት የሚለው ቃል ጀግንነት የሚል አንድምታ ላይኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን የብረት መገለጫ ጥራቱ ካርቦን እንደሆነ ሁሉ የሰውም መገለጫ ጠባዩ መንፈሰ ጠንካራነቱ ነው፡፡

ለውድቀት ዋነኛው ምክንያት መንፈስ ልል መሆን ነው፡፡ ከዚህም በላይ መንፈስ ልልነት በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ በተግባር እንደታየው የብዙ ሰዎች ድክመት ነው፡፡ ይህ ግን በጥረት ሊወገድ የሚችል ነው፡፡ ሆኖም ይህ የሚወሰነው በአጠቃላይ በእያንዳንዱ ሰው የፍላጎት ጽናት ነው፡፡ የሁሉም ስኬት መጀመሪያ ነጥብ ያለው ፍላጎት ላይ ነው፡፡ ሁልጊዜ

ይህን በአዕምሮህ አስተውል፤ ደካማ ፍላጎቶች የሚያስገኙት ደካማ ውጤት ነው፡፡ ጥቂት እሳት ጥቂት ሙቀት እንደሚሰጠው ሁሉ መንፈሰ ልልነት ካጋጠመህ ይህን ድክመት ማስወገድ የምትችለው ባለህ ፍላጎቶች ላይ ጠንካራ እሳቶች ስታነድ ነው፡፡

መንፈሰ ጠንካራነት ፍላጎትን ወደ ገንዘባዊ ተመጣጣኙ ለመለወጥ በሚደረገው ጉዞ መነገድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ሀብትን ለመገንባት የፍልስፍናውን ሁሉንም መርሆች መጠቀም ይሻል፡፡ እነዚህ መርሆች ግንዛቤ ያሻቸዋል፡፡ ገንዘብን በሚፈልጉ ሁሉ ቀጣይነት ባለው መልኩም ሊተገበሩ ይገባል፡፡ ፍላጎትን ወደ ተመጣጣኝ ገንዘብ የሚቀየርበት ዘዴ ስድስት እርግጠኛ የሆኑ ተግባራዊ እርምጃዎችን ያካትታል፡፡

1. ምን ያህል ገንዘብ እንደምትፈልግ በአዕምሮህ ውስጥ ወስን ‹‹ገንዘብ እፈልጋለሁ›› ማለት ብቻውን አይበቃም፡፡

2. ገንዘብ ለማግኘት የምትከፍለውን ነገር በትክክል ወስን፡፡ ‹‹በነፃ ማግኘት›› የምትለው እውነታ በፍፁም የለም፡፡

3. መቼ ማግኘት እንዳለብህ ትክክለኛውን ቀን ወስን፡፡ 4. ፍላጎትህን ማሟያ እርግጠኛ፣ ቁርጥ ያለ እቅድ

አውጣ፡፡ እናም ተዘጋጀህም አልተዘጋጀህም እቅድህን ወደ ተግባር ለመቀየር ወዲያው ጀምር፡፡

5. ግልጽና አጭር በሆነ መንገድ ምን ያህል ገንዘብ እንደምትፈልግ፣ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ምን ማግኘት እንዳለብህ፣ ገንዘቡን ለማግኘት አንተ የምትከፍለውን እናም የገንዘቡን ማግኛ እቅድህን ጻፈው፡፡

6. የፃፍከውን ድምጽህን ከፍ አድርገህ አንብበው፡፡ ይህንን በቀን ሁለት ጊዜ ጠዋትና ማታ እያነበብክ ልክ ገንዘቡ እጅህ እንደገባ ይሰማህ፤ ይታይህ፡፡

እነዚህን ስድስቱን ትዕዛዞች መከተል አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ስድስተኛውን መከተል በጣም አስላጊ ነው፡፡ ‹‹እንዳገኘህ›› አድርጎ ማሰቡ ሊከብድህና የማይቻል ነው ልትል ትችላለህ፡፡ እዚህ ጋ ነው እንግዲህ የሚንበለበል ፍላጎት አገልግሎቱ፡፡

የእውነት ገንዘብ የማግኘት ፍላጎት ካለህና ያ ፍላጎትህ እንደ ልክፍት ከሆነ ራስህን እንዳገኘህ ዋናው ነገር መፈለግህ፤ ለማግኘት መወሰንህና ማግኘት መቻልህን ማመንህ ነው፡፡

ትእዛዞችን ብትከተል ያለህ ጉጉነት በምን ያህል መጠን ለማደግ ወይም ምን ያህል ያነሰ ገንዘብ ለማከማቸት እንደምትፈልግ በግልጽ ያሳያል፡፡ ራስህን ግድ የለሽ ሆነህ ካገኘኸው በእርግጠኝነት ሀብት ከማከማቸትህ በፊት ሊኖርህ የሚገባው ‹‹በገንዘብ ላይ አመለካከትህን መቀየር ነው›› ገንዘብ ለማግኘት ከመነሳትህ በፊት ይህን ለማድረግህ እርግጠኛ መሆን ይገባል፡፡ ውሃ ወደ ውቅያኖስ እንደሚሳብ ሁሉ ሀብትም በአዕምሯቸው ሊስቡት በተዘጋጁ ሰዎች እንደተሳበ ነው፡፡

ይሁንና እነዚህን ህጎችና መመሪያዎች አልፎ አልፎ ለመጠቀም የሚደረግ ጥረት ጥቅም የለውም፡፡ ውጤት ለማግኘት ደንቦች ከአንተ ጋር ቋሚ ልምድ ሆነው እስኪቀሩ መጠቀም አለብህ፡፡ ከዚህ ውጪ ‹‹የገንዘብ ፍላጎትህን›› በሌላ መንገድ ልታዳብረው አትችልም፡፡ ገንዘብ ለማግኘት አቅዶ ለተንቀሳቀሰ ሰው ገንዘብ እንደምትሳብለት ሁሉ ድህነት የምትሳበውም ለድህነት ለተመቻቸ ሰው ነው፡፡ የሚከናወኑትም በአንድ አይነት ህጎች ነው፡፡ ገንዘብን አጥብቆ የማይሻ ሰው አዕምሮው ድህነት በመሻት የተያያዘ ነው፡፡ ድህነት የሚሻ አዕምሮ እንዲኖርህ ማሰብ አያስፈልግም፡፡ ገንዘብን መሻት ግን አብሮ ካልተወለደ በስተቀር ሊፈጠር ይገባል፡፡

ሀብትን ለማከማቸት የመንፈስ ጽናትን አስላጊነት ማወቅ አለብህ፡፡ መንፈሰ ጠንካራነት ከሌለህ ትሸነፋለህ፤ መንፈሰ ጠንካራ ከሆንክ ታሸንፋለህ፡፡ አቃዥቶህ የምታውቅ ከሆነ የመንፈስ ጽናትን ዋጋ ትረዳለህ፡፡ ባልጋህ ላይ ተጋድመሃል፣ በመጠኑም ነቅተሃል፤ የመታፈን ስሜት ይሰማሃል፤ ለመገልበጥ ወይንም ለመንቀሳቀስ አትችልም፡፡ ጡንቻዎችህን ማንቀሳቀስ አቅቶሃል፣ ጡንቻዎችህን መልሰህ መቆጣጠር መጀመር እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡ ከጽኑ የማድረግ ፍላጎት በኋላ የአንድ እጅህን ጣቶች ታንቀሳቅሳለህ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሌላኛው እጅህን መቆጣጠር ትችላለህ፡፡ ከዚያም ወደ ሌላኛው እግር ይዘልቃል፡፡ ከዚያም ከፍተኛ በሆነ ፍላጎትና ጥረት አጠቃላይ ሰውነትህን ጡንቻዎች ስርዓት የመቆጣጠር አቅሙን ታገኛለህ፡፡ እናም ከፍተኛ ድምጽ አሰምተህ ከቅዠት ትወጣለህ፡፡ ደረጃ በደረጃም ጨዋታው ተለወጠ ማለት ነው፡፡

ካጋጠመህ የድንዛዜ መንፈስ በፍጥነት ለመላቀቅ በተመሳሳይ መንገድ መጀመሪያ በቀስታ ከዚያም ፍጥነት እየጨመርክ በመሄድ መላቀቅ አስፈላጊ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፡፡ ምንም እንኳን መጀመሪያ ብትንቀረፈፍም ያልተቆጠበ ጥረት አድርግ፡፡ ስኬት የሚመጣው ካልተቆጠበ ጥረት ነው፡፡

የመንፈስ ጽናት የዳበሩ ሰዎች ለድል ዋስትና አላቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ቢሸነፉ እንኳን በመጨረሻ የመሰላሏ ጫፍ ላይ ይደርሳሉ፡፡ አንዳንዴ በውስጣችን የተደበቀ፣ ሰዎችን በተስፋ አስቆራጭ መንገዶች የሚወስድ ድብቅ መሪ ያለ ይመስላል፡፡ ከተሸነፉ በኋላ እራሳቸውን አንስተው ሙከራቸውን የሚቀጥሉ ከግባቸው ይደርሳሉ፡፡ ዓለምም (ጽናት... ወደ ገጽ 10 የዞረ፟)

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

(ኤፍሬም እሸቴ www.adebabay.com)

በዚህ ሰሞን መቼም ከእግር ኳስ ውጪ ማውራት በሕማማት ስለ ቁርጥና ጥብስ እንደማውራት ሳይቆጠር አይቀርም። እኔም ብሆን ስለ እግር ኳሱ ማውራቱን መች ጠልቼው። በርግጥ ይኼ ሁሉ ወፈ ሰማይ የስፖርት ተንታኝ በየኤፍ.ኤሙ ሲተችበት በሚውለው የተጫዋቾቻችን ብቃት፣ ጥራት፣ የኳስ ጥበብ፣ የሽልማት ዓይነት፤ የተጋጣሚዎቻችን ሁኔታ፣ የተጫዋቾቻቸው ዝና፣ ማን ከየትና ከየትኛው ክለብ እንደመጣ፣ አሰላለፋቸው እና ከኢትዮጵያ ጋር ሲገጥሙ ሊኖራቸው ስለሚችለው አያያዝ ለመተንተን ሙያውም መረጃውም የለኝም። (“ችሎታ የለኝም” አለማለቴ ይሰመርበት። ማን ይሞታል። መቸም “አልችልም” ማለት ጎጂ ባህል ሆኗል።) ቢያንስ የእንጀራ አገሮቻችን አሜሪካ እና ስዊዲን ስላፈሯቸው እና ለእናት አገራችን ኢትዮጵያ ስላበረከቷቸው ተጫዋቾቻችን መወያየት ይቻላል።

ኢትዮጵያውያን እንደ ጨው በመላው ዓለም ተበትነዋል። በብዙ ቦታዎች አንድ ትውልድ አልፎ ሁለተኛ ትውልድ ላይ ደርሷል። በቅርብ ከሚገኙት ኬንያና ሱዳን እስከ አረብ አገሮች፣ ከምዕራብ አውሮፓና ስካንዲኔቪያን አገሮች እስከ አሜሪካና አውስትራሊያ ድረስ ብዙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ከእነርሱ መካከል የአሜሪካ ሜኔሶታው ፉአድ ኢብራሒም እና የስዊዲኑ ዩሱፍ ሳላህ ተገኝተዋል። ፉአድ ኢትዮጵያ ተወልዶ አሜሪካ ያደገ፤ ዩሱፍ ደግሞ እዛው ስዊዲን ተወልዶ እዛው ያደገ እግር ኳስ ተጫዋች ነው። የብዙ ኢትዮጵያውያን የኋላ ማንነት ማሳይ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆች ናቸው። አድገውና ለቁም ነገር ደርሰው አገራቸውን ለመወከል መብቃታቸው ደስ ይላል። “አለ ገና፣ ገና፣ አለ ገና” እንላለን።

ጣዕመ-ኢትዮጵያ፣ ባህለ-ኢትዮጵያ በቀዘቀዘባቸው ባህሎች መካከል አድገው በመጨረሻ አገራቸውን ለመወከል መቻላቸው ትልቅ ነገር ነው። ስለ ፉአድ ያነበብኩት አንድ ጽሑፍ ይህ ወጣት ለአሜሪካ እግር ኳስ ቡድን (ከ17 ዓመት በታች እንዲሁም ከ21 ዓመት ላሉት) ቢጫወትም የማታ ማታ ግን አገሩን ለመወከልና የአገሩን ማሊያ ለመልበስ መወሰኑን ያትታል። ስዊዲን እነ ኢብራሒሞቪችን (በአባቱ ቦስንያዊ) እና ታዋቂው ሔንሪክ ላርሰንን (አባቱ ከኬፕቬርዴ ናቸው) የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በማሰለፏ እናውቃታለን። ዩሱፍም ተመሳሳይ በሆነ መልክ ተመሳሳይ ዕድል ሊያገኝ እንደሚችል እገምታለኹ። ነገር ግን ያንን ትቶ የአገሩን መለያ ለብሷል።

ዳያስጶራው ለረዥም ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወደ አገሩ በመላክ አገሩን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲደግፍ ቆይቷል። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ

ከዳያስጶራው የሚገኘው ገቢ አገሪቱ ከወጪ ንግድ ከምታገኘው በእጅጉ እንደሚበልጥ የዓለም ባንክ ጥናቶች በተደጋጋሚ አሳይተውናል። ከዚህ የቀጥታ ገንዘብ ርዳታ ባሻገር ትውልደ-ኢትዮጵያዊው በአገሪቱ አጠቃላይ ሕይወት ላይ በጎ ሱታፌ ማሳየቱ አገሩን ለሚወድ ወገን ሁሉ ትልቅ ተስፋ ነው። ዩሱፍና ፉአድ ለዚህ መልካም አብነቶች ይሆናሉ።

ፉአድ ዩሱፍና ፉአድ ወደ አገራቸው ሲመለሱ በዚያው መጠን

ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ ዳያስጶራነት ጎራ እየተቀላቀሉ ነው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በዋሺንግተን ዲሲ የተደረገ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ሐኪሞች ማኅበር ስብሰባ ተገልጿል እንደተባለው በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዶክተሮች ይልቅ በውጪ የሚገኙት ቁጥር ይበልጣል። አዝማሚያውን ስንመለከተው ይኸው የዕውቀትና የአዕምሮ ስደት እንደሚቀጥል እርግጥ ነው። ለዚህ ምክንያቱ

ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ማጣት እና ፖለቲካዊ ነጻነት አለመኖር ነው። ከኢኮኖሚው በበለጠ ፖለቲካዊ ጫናው ለብዙው ወገናችን መሰደድ ምክንያት ነው የሚለው የብዙዎች እምነት ነው። በፖለቲካዊ ምክንያቶች የተሰደዱት ደግሞ በየወጡበት አገር ባላቸው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን መንግሥት ዘወትር መክሰስ ቀጥለዋል። በቅርቡም ይቆማል ተብሎ አይጠበቅም። ይህም ፉአድንና ዩሱፍን የመሳሰሉ ትልውደ ኢትዮጵያውያን በየሙያቸው ትውልድ አገራቸውን እንዳያገለግሉ እንቅፋት ይሆናል። በአገሪቱ ያለው የሰብዓዊ መብት ገፈፋ ሲሻሻል ዳያስጶራውም ተጠቃሚ ይሆናል።

ዳያስጶራውን በጥቅማጥቅም ማባበል መጠነኛ ደጋፊ ያስገኛል፤ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት መጠበቅና ሕገ መንግሥቱን ማክበር ግን ሙሉ ድጋፍ ያስገኛል።

ዳያስጶራው በየሚኖርበት አገር የሚተነፍሰው ፖለቲካዊ፣ ኅሊናዊ፣ አካላዊ እና ሰብዓዊ ነጻነት ይኸው ነጻነት በአገሩ እንዲኖር በጎ ምኞት ይቀሰቅስበታል። ስለዚህ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በአገሩ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይኮንናል፤ ተጽዕኖ ለመፍጠርም የማይወጣው ዳገት የማይወርደው ቁልቁለት የለም። ይህም የተለያየ አመለካከት መፍጠሩ አይቀርም። ዳጳስጶራው “አክራሪ ነው” ከሚለው ጀምሮ “የአገሩን ነባራዊ ሁኔታ የማያውቅ” እንዲሁም “50 ዶላር ልኮ አገር ውስጥ ያለው ወጣት እንዲማገድ ይፈልጋል” ወዘተ ተብሎ ይቀርባል።

ሐሳቡ ቀደም ብሎ በመንግሥት ብቻ ተደጋግሞ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ተርታ ዜጎችም

በማኅበራዊ ድረ ገጾቻቸው ሲያስተጋቡት ይስተዋላል። በአጭር አባባል ለማቅረብ “ዳያስጶራ ዝም በል” ወይም “ዝም እንዲል አድርጉት” የሚል አዋጅ የተነገረ ይመስላል።

በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ዜጋ ከአገሩ ርቆ በመኖሩ ስለ አገሩ ያለውን ሐሳብ፣ በመንግሥቱ ላይ የሚኖረውን ቅዋሜ እና ለችግሮች የሚኖረውን መፍትሔ ከማቅረብ ሊከለክለው የሚችል ሕግ የለም። ስለ አገርህ ለመናገር በአገርህ መሬት መኖር አለብህ የሚል “የቀበሌ ትእዛዝ” የመሰለ ሐሳብ ውኃ አያነሣም። ነቢዩ ዳዊት ስለ ኢየሩሳሌም ሲናገር “ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እንዳለው “እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ ለትርስዐኒ

የማንየ፣ ኢትዮጵያ ሆይ ብረሳኝ ቀኜ ትርሳኝ” የሚሉ ኢትዮጵያውያንን ‘እኮ ምን አግብቷችሁ’ ማለት ከስድብ ይልቅ ያማል።

ዛሬ ባንኖርባት ተወልደንባት አድገንባታል፤ ዘር ማንዘሮቻችን ኖረው አልፈውባታል። ክቡር አጥንታቸው ረግፎባታል። በየወቅቱ በሚመጣና በሚሄድ ሥልጣን የአንድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱ አይገመገምም። ኢትዮጵያዊነትን ማንም ባለሥልጣን አልሰጠንም፣ ማንምም አይነፍገንም። ከደርቡሽና ቱርክ፣ ጣሊያንና ግብጽ፣ ከሌሎችም ድንበር ገፊዎች ሲታገሉ በወደቁ ወገኖቻችን የቆመ ዜግነት እንጂ እንጀራ ፍለጋ፣ ነጻነት ፍለጋ እንደምንኖርባቸው አገሮች በወረቀት ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከወረቀት እና ከፖለቲካ ወገንተኝነት እንዲሁም ከየብሔረሰባዊ ማንነታችን በላይ ነው።

በሌላም በኩል ካየነው ስለ ሰብዓዊ መብት ለመናገር የግድ የዚያ አገር ዜጋ መሆን፣ በዚያ አገር መኖርም አይጠይቅም። ሰብዓዊ መብቱ እንዲጠበቅለት የሚፈልግ ማንም ሰው የሌላው ሰው መብት ሲጣስ አይደሰትም። ሌላው ሁሉ ታሪካዊ ሐተታ እንኳን ቢቀር በቅርቡ ዘመን የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ከኛ ሚሊሻ ጋር አብረው የተዋደቁልንን ኩባውያንን መስዋዕትነት እንደምናከብረው፣ ዕድሜ ዘመናቸውን በሴቶች (ፊስቱላ) ሕክምና ረገድ አገራችንን የጠቀሙትን ሐኪሞች እንደምናመሰግነው ሁሉ ለዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት የሚከራከሩትንም በዚሁ መነጽር ልንመለከታቸው ይገባል።

በተጨማሪም የመንግሥትን አሠራር ማሔስ አገርን መተቸት አይደለም። መንግሥት የአገር መሪ እንጂ አገር አይደለም። ፓርቲና መንግሥትነት ከዘር ጋር በመቆራኘታቸው ፓርቲውን መተቸት የመጣበትን ዘር እንደመውቀስ ተደርጎ መቆጠሩም ትልቅ ስሕተት ነው። ፓርቲዎች በዓላማቸውና በአሠራራቸው መነቀስና መተቸት ግዴታቸው ስለሆነና በዘር ላይ የተመሠረተ የፓርቲ አወቃቀር እስካለ ድረስ ከፓርቲው ጀርባ ያለው ዘር ወቀሳው ለርሱ የተወረወረ አለመሆኑን ለመረዳት ብዙ ጥበብ አያስፈልገውም።

እንኳን የኢትዮጵያ መንግሥት በዲሞክራሲያዊነታቸው ወደር የማይገኝላቸው አገሮች የየጊዜው መንግሥታት ሳይቀሩ ከትችት አያመልጡም። ትችት መንግሥታቱን ከዓምባገነንነት የሚያተርፋቸው ፍቱን መድኃኒት ነው። ተቃዋሚዎችን፣ ፕሬሶችን፣ ጥቃቅን ስብስቦችን ሁሉ በመዋጥና በዓይነ ቁራኛ በመመልከት፣ ትችትን ሳይሆን ተቺውን በማፈን ጥሩ መንግሥት መሆን አይቻልም። “ልማት ላይ ነን አትንኩን” የሚል ፈሊጥ ወንዝ አያሻግርም። ጥያቄው ግድቡና ሕንጻው ላይ አይደለም። የዜጎችን ሰብዓዊ ሕንጻ እያፈረሱ የድንጋይ ሕንጻ እንሠራለን ማለት አይቻልም። ከግዑዝ ሕንጻ ሰብዓዊ ዜጋ ይቀድማል፤ከግድብ ግንባታም መብት ይቀድማል።

በውጪ የሚገኘው ዜጋ የአገሩን ሁኔታ በትኩረት ለመከታተል ቴክኖሎጂው ትልቅ ዕድል ይሰጠዋል። አራት ኪሎ የተፈጠረው አቃቂ፣ አንዱ ክፍለ ሀገር የተሠራው ሌላው ሳይረዳው ሳይሰማ፤ እረኛና አዝማሪ እንኳን ለዘፈኑና እንጉርጉሮው በራሱ ላይ ግላዊ-ሴንሰርሺፕ በጣለበት ዘመን፣ ከአንድ አፍ በሚወጣ (ዝም በል... ወደ ገጽ 11 የዞረ)

ከሚኒሶታ የሄደውና ለብሔራዊ ቡድናችን የሚጫወተው ፉአድ

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

መብት የተሰኘው አምዳችን በአሜሪካን ሃገር እየኖርን ሕግን ሳናውቅ ብዙ ነገሮችን ለምናጣ ወገኖቻችን ትልቅ ትምህርት ሰጪ አምድ ነው። በአምዱ ላይ በአሜሪካ ሕጎች ዙሪያ ጥያቄዎቻችሁን ተቀብለን እዚሁ ከሚገኙ

የሕግ ባለሙያዎች መልስ እናሰጣችኋለን። ጥያቄዎቻችሁን ላኩልን።

ይህ አምድ በአሜሪካ የኢትዮጵያውያንን ኑሮ በትዝብት መልክ አቅርቦ እንደንማማርበት ታስቦ የተከፈተ ነው። ሁሉም የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አንባቢ በዚህ አምድ ላይ ትዝብቱን ማስፈር ይችላል። ታዲያ ትዝብቱ መስተማርን አንግቦ ቢቀርብ ለኮምዩኒቲያችን ትልቅ ትምህርትን ይሰጣል ብለን እናምናለን። ተሳተፉበት።

ናዖድ ቤተሥላሴ

www.naodlive.com ‹‹በእናንተ ጊዜ›› አለኝ ዲያቆኑ ወንድሜ፡፡ ‹‹በእናንተ ጊዜ፤ በጥምቀት በዓል ላይ ፤ አርሞኒካ እየነፉ፤

ክብ ሰርተው፤ ዳንስ የሚደንሱት ጎረምሶች...›› አለኝ

‹‹በደንብ እንጂ››…አልኩት በትዝታ ወደ እኛ ዘመን ሄጄ፡፡ በእኔ ጊዜ፤ ጥምቀት፤ ሃይማኖታዊ በዓልና የታቦት ንግስ ብቻ ሳይሆን አሜሪካኖቹ ካርኒቫል እንደሚሉት አይነት የፈንጠዝያ በዓልም ነው፡፡ ብስክሌት መንዳት ከመለማመድ ጀምሮ ልጃገረዶችን በሙሉ ዓይን እስከማየት የምንደፍረው፤ ዳንስ ከመለማመድ ጀምሮ የቡድን ድብድብ ውስጥ መመዝገብ የምንጀምረው፤ በጥምቀት በዓል ነው፡፡ማሳሰቢያ፡በእኔ ዘመን አልኩ እንጂ እኔ አላልኩም፡)

‹‹ያ ሁሉ አሁን የለም›› አለና ከትዝታ እንቅልፌ አባነነኝ፡፡

‹‹የየሰፈሩ ወጣቶች፤ ዓመቱን ሙሉ፤ በየቤቱ እየዞሩ ሳንቲም ሰብስበው›› አለኝ ‹‹ለታቦታቱ ቀይ ምንጣፍ ገዝተው፤ ሳር

ጎዝጉዘው፤ አንድ አይነት ቀለም ያለው ቲሸርት ገዝተው፤ ታቦት እያጀቡ ነው፡፡›› አለኝ፡፡ ከዚያ ሕዝቡ ታቦት ሳይጋፋ እንዴት እንደሚሄድ፤ ሁለት ታቦታት ሲገናኙ እንዴት ሞቅ ያለ የፈንጠዝያ ሰላምታ እንደሚደረግ፤ ሞቅ ያለ ዜማ፤ ማዕጠንት፤መዝሙር እና መተቃቀፍ እንደሚደረግ ወዘተ ነገረኝ፡፡ እኔም ሰማሁ፡፡ ሃይማኖታዊ በዓል፤ ታቦት ማንገስ፤ ስለ ጽድቅ ብቻ የሚደረግ ነገር አይደለም፡፡ ጽድቅማ፤ ከሞት በኋላ ያለ፤ ማን እንደሚያገኘው የማይታወቅ፤ የእግዚአብሔር ምስጢር ነው፡፡ አረ እዚሁ ምድር ላይ ያለ ጥቅም አለው፡፡ ጥምቀት፤ ታቦት

ማክበር፤ ወዘተ….ከማንነታችን ጋር የተቆራኘ፤ ትልቅ ማህበራዊም ዕሴት፤ ሀገራዊም ቅርስ ነው፡፡ ሌላ አማኝም፤ ኢ-አማኝም፤ ጸረ

-አማኝም- ጸረ-ጸረ-አማኝም….ሁሉም በበጎ ሊያው የሚገባ ነገር ነው፡፡

ፈረንጆች (አሜሪካኖች ማለቴ ነው፤ የእኔ ፈረንጆች እነርሱ ናቸውና)፤ እንደ ጥምቀት ያለ በዓል ቢኖራቸው፤ ምን እንደሚያደርጉ ታውቃላችሁ፡፡ በውድም፤ በግድም፤ በስብከትም በሎጂክም፤ በሳይንስም በፊልምም አድርገው፤ አለም ሁሉ ታቦት እንዲኖረው፤ የጥምቀት በዓል እንዲኖረው ያደርጉ ነበር፡፡

ወንድሜን ታዲያ ‹‹አሁን የት ነው ያለኸው›› አልኩት፡፡

‹‹የካ ሚካኤልን፤ በዓታን፤ ገብርዔልን፤… የሰፈራችንን ታባታት በሙሉ አጅቤ፤ ወደ ጃንሜዳ እየሸኘሁ ነው፤ አለኝ፡፡

‹‹ድሮ…›› ብዬ ስጀምር ገና መሳቅ ጀመረ፡፡ ብዙ ነገር ብዙ ከመቀያየሩ የተነሳ፤ እኔ የማወራው ነገር ሁሉ፤ ከ100 ዓመት በፊት የተደረገ እየመሰው መሰለኝ፡፡

‹‹ድሮ፤ የየካ ሚካኤልን የምንሸኘው፤ እንግሊዝ ኤምባሲ አጥር ላይ ሆነን ነበር…›› ስለው መሳቅ ጀመረ፡፡ ‹‹የእንግሊዝ ኤምባሲ

አጥር፤ የጦር ሜዳ ምሽግ ነው የሚመስለው እኮ፤ እንኳን ልትንጠለጠልበት፤ ልትጠጋውም አትችል›› አለኝ፡፡ እናንተ ጋስ እንዴት ነው በዓል አለኝ፡፡ እኛጋም ታቦት ይወጣል፤ ይከብራልም፤ እኛም እንወጣለን፤ እናከብራለንም፡፡ ልዩነቱ

አካሄዳችን ላይ ነው፡፡ እኛ ጋር ‹‹ታቦቱ ወደ ጥምቀተ ባሕር የሚሄደው፤ በሊመዚን መኪና ነው፤ እኛም የምናጅበው በመኪናችን

ነው›› አልኩት፡፡ በዓይነ ህሊናው የታየው ምን እንደሆነ ባላውቅም፤ በነገርኩት እውነት ተገርሞ ሳቀ፡፡ በአሜሪካ ታቦት ይዞ

በእግር መሄድ ሊታሰብ የማይችል መሆኑ አልታየውም፡፡ መጥቶ ካላየው እንዴት ይገባዋል?፡፡ በእግርም ሆነ በሊመዚን፤ ኢትዬጵያም ሆነ አሜሪካ፤ የጥምቀት በዓል መንፈስ ግን አንድ ነው፡፡ ለእኔ እና ለባለቤቴ፡፡ ትልቁ ስጋቴ

ለልጆቼ ነው፡፡ ከጥምቀት በዓል፤ ባሕል እና እሴት፤ ስንት ፐርሰንት ይገባቸው ይሆን?

ጽናት... ከገጽ 9 የዞረ

ለነሱ ‹‹ብራቮ! እንደምትሰሩት እርግጠኛ ነበርን›› እያለ ይጮሃል፡፡ ድብቁ መሪም ማንም የመንፈስ ጥንካሬን ፈተናን ሳያልፍ የትልቅ ስኬት ባለቤት አያደርግም፡፡ ጥረታቸውን ፊት ለፊት የማይቀጥሉ ውጤት አይኖራቸውም፡፡

ፈተናውን የሚጋፈጡት በመንፈስ ጽናታቸውን በብዙ ይሸለማሉ፡፡ ምንም አይነት ግብ ያለው ስኬትን እንደ ካሳ ይቀበላሉ፡፡ ከቁሳዊ ካሳ ይልቅ የማያልቅ እውቀት ያገኛሉ፡፡ ይህም እያንዳንዱ ውድቀት ተመጣጣኝ የሆነ ጥቅም እንደሚያስከትል ማወቃቸው ነው፡፡ ከዚህ ህግ የተለዩ ህጎች አሉ፡፡ ጥቂቶች ብቻ ናቸው ከልምድ የመንፈሰ ጠንካራነትን ጠቃሚነት የተረዱት፡፡ እነሱም ሽንፈትን ያልተቀበሉና ጊዜያዊ መሆኑን የተረዱ፣ ፍላጎታቸውን ያለማቋረጥ በመተግበር ሽንፈትን ወደ ድል እንደሚቀይሩ የሚያምኑ ናቸው፡፡

ከዳር ቆመን ለምናየው ብዙ ሰዎች ሲሸነፉ የማይነሱ ይመስላል፡፡ የሽንፈትን ጽዋ የሚቀምሱትን ስናይ የበለጠ ጥረት እንደሚያስነሳሳቸው እናያለን፡፡ እነዚህ እንዳጋጣሚ ሆኖ የህይወትን የኋላ ማርሽ አይቀበሉም፡፡ ነገር ግን ልናየውና ለመኖሩ ልንጠረጥረው የምንችለው በተስፋ አስቆራጭ ጊዜ

ጥረት የሚያደርጉት አዳኛቸው ጽኑነት ነው፡፡ ‹‹መንፈሰ ጠንካራነት›› የምንለው ኃይል ነው፡፡ አንድ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ነገር መንፈሰ ጠንካራነት የሌለው ምንም አይነት ተጨባጭ ውጤት አያመጣም፡፡

መንፈሰ ጠንካራነት የአዕምሮ ብቃት ነው፤ ስለዚህ ማዳበር ይቻላል፡፡ ልክ እንደሌሎቹ የአዕምሮ ብቃቶች ሁሉ መንፈሰ ጠንካራነት የተመሰረተው ቁርጥ ባሉ ምክንያቶች ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. የዓላማ እርግጠኝነት /Definiteness of Purpose/ ለመንፈሰ ጠንካራነት እድገት የመጀመሪያው ምናልባትም

ትልቁ ጠቃሚ እርምጃ አንድ ሰው ምን እንደሚፈልግ ማወቁ ነው፡፡ ከፍተኛ ፍላጎት አንድ ሰው ብዙ ችግሮችን እንዲያልፍ ይረዳዋል፡፡

2. ፍላጎት /Desire/ ከፍተኛ የሆነ ፍላጎትን በመከተል በአንፃራዊ መልኩ

በቀላሉ መንፈሰ ጠንካራነትን ለማግኘት፣ ለመጠበቅ ይችላል፡፡ 3. በራስ መተማመን /Self - reliance/ አንድ ሰው ያቀደውን አላማ ለመፈፀም ችሎታው

እንዳለው ማመኑ ያቀደውን ተግባር ከዳር ለማድረስ ያበረታታል፡፡ (ጽናት.... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

8th Immigrant and Minority Farmers

Conference - Saturday and Sunday,

February 2 & 3, 2013 in St. Paul, MN. St. Paul— Minority and immigrant farmers are invited to participate in the 8th Annual Immigrant and

Minority Farmers Conference. Hosted by the Association for

the Advancement of Hmong Women in Minnesota, Minne-

sota Food Association, USDA-Farm Service Agency and

USDA- Natural Resource Conservation Services, the two-day

conference provides education and resources to small farm

operators and fosters relationships between farmers and com-

munity partners. Major sponsors of the conference include:

AgriBank, AgStar, Minnesota Department of Agriculture,

National Immigrant Farmers Initiative, USDA – National

Agriculture Statistic Service and the University of Minnesota.

The theme of the 2013 Conference is “Planting Seeds for

Success on your Farm.” Keynote presenters at the conference

will be Senator Fong Hawg from St. Paul on Saturday, Febru-

ary 2 and Maria Moreira, Project Director at Flats Mentor

Farm in Lancaster, Massachusetts on Sunday, February 3.

Also on Saturday, Senator Amy Klobuchar will welcome

farmers to the conference with a short video. Each day over

the lunch hour Bo Thao-Urabe, from Asian Americans/

Pacific Islanders in Philanthropy will use visual facilitation

to assist a lunch time panel of farmers in telling their stories

about immigrating to the United States and their love for farming.

Women and immigrants are among the fastest growing sector of farmers. The conference supports

these new and aspiring farmers and their contribution to building an adequate supply of local foods,

local economic development and healthy communities.

The 8th Immigrant and Minority Farmers Conference will be held on Saturday and Sunday (please

note change of days from previous years), February 2 & 3, 2013 at the North Central States Re-

gional Council of Carpenters Event Hall, 710 Olive Street, St. Paul, MN.

Registration is on-line at www.mnfoodassociation.org/content/12915, or by calling MFA at 651-433-

3676, or Panukoochi Yang at the Association for the Advancement of Hmong Women in Minnesota

at 952-388-3275. The conference is free to farmers. Language interpretation is available. The cost

for other interested parties is $50 per day.

Interested farmers and CBOs who have questions should contact:

Ly Vang, at 651-222-0475, e-mail: [email protected];

Joci Tilsen at 651-433-3676 ext. 14 or e-mail: [email protected]

Nigatu Tadesse at 651-602-7705 or email [email protected]

በሰሜን ጐንደር ልዩ ቦታው ድጐማ በሚባል ስፍራ ባለ በለስ ምንጭ ላይ በመንግስት ባለስልጣናት እና በህዝቡ መካከል ከፍተኛ ግጭት ተፈጠረ፡፡

በተጠቀሰው በለስ ምንጭ ላይ ለመስኖ በሚል መንግስት 1.3 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ ለነዋሪው እየሰራ እንዳለ ከዞኑና ከወረዳው ባለስልጣናት ቢነገርም አሁን ግን ምንጩን ውሃ አሽገው ለሚሸጡ የግል ባለሃብት መሸጡ ተጠቁሟል፡፡ በዚህም የተነሳ በህዝቡና በፖሊስ መካከል ታህሣሥ 4 እና 5 ቀን 2005 ዓ.ም የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ታውቋል፡፡

ከነዋሪው ህዝብ መካከል ያነጋገርናቸው ስማቸው እንዲገነፅ ያልእንደገለፁልን ከሆነ ቦታው ከ500 በላይ አባወራዎች የሚጠቀሙበት ምንጭና የሰይፍ አጥራ ማርያም ቤ/ክርስቲያን እኛን ሳያማክሩን ሳይነግሩን ለባለሃብት ሸጠዋል፤ ሌላው ከ1982 ዓ.ም ጀምሮ የችግኝ ጣቢያ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ነው ሲሉ የግጭቱን ምክንያት አስረድተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት 15 ያህል ሰዎች መታሰራቸውና ሌሎችንም ለማሰር እንደታሰበ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የወረዳው አስተዳደር አቶ ግዛት

አንተነህ በበኩላቸው የበለስ ወንዝ ምንጭን ለባለሃብቱ ፈቃድ የክልሉ ማዕድንና ኤነርጂ ቢሮ ነው፣ የተሰጠውም የመንግስት መሬት ነው እንጂ እኛ ህዝብ የሚጠቀምበትን አልነካንም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዕለቱ ግጭት የቀሰቀሱትም ህገወጥ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች በመሆናቸው ታስረዋል፤ ገና ሌሎችም በቁጥጥር ስር የሚውሉ አሉ ሲሉ ነግረውናል፡፡

በተያያዘ ዜና በጐንደር ዙሪያ ወረዳ በምትገኘው ማክሰኚት ከተማ የኢህአዴ ግን “አዲስ ራዕይ” የተሰኘ መፅሔት የአቶ መለስ ታሪክ የያዘ ነው በሚል አንዱን በ100 ብር ዋጋ በአካባቢው ቢሰራጭም ገዥ እንዳልተገኘ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ምክንያት ታህሣሥ 27 ቀን 2005 ዓ.ም የወረዳው ርዕሳነ መምህራን ተሰባስበው ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት በአካባቢው ገዥ ያጡት የመለስ ታሪክ ያለበት “አዲስ ራዕይ” በት/ቤቶች በጀት እንዲገዛ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡ ይህንንም ለማጣራት ወደ ወረዳው ትምህርት ቢሮ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ ከአዘጋጁ፡ (በኢትዮጵያ እንዳይታተም የታገደው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በዘ-ሐበሻ ላይ እንዲታተም የላከው ነው።)

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Low cost tax preparation!! በቅናሽ ዋጋ SINGLE, MARRIED, SELF EMPLOYED INCLUDES: electronic filing

Get your 2012 federal and state income tax prepared

Bisrat (Bis) Alemayehu & Assoc.

1821 University Avenue #301

St. Paul MN 55104 Fax: (651) 649-0620

Other services provided : ተጨማሪ አገልግሎቶቻችን

Auto , Home & Business insurance 2)Residential &Investment Real Estate sales

3) Mortgages –for purchase and /or refinance 4) Buying and selling of businesses

YOUR TRUSTED FINANCIAL ADVISORS

በወንድማችን ምስጋናው የተከፈተው አዲሱ አልፋ ጋራዥ መኪናዎ በማንኛውም ሰዓት ብትጋጭ ወይም ቀለም ሲፈልጉ ቀጠሮ አክብሮ በፍጥነት ያድሳል፤ ለማንኛውም ጥገናም ወደ ጋራዣችን ይምጡ፤ በቂ የሰው ኃይል አለን!

Interest Interest Free Free

FinancingFinancing

Alpha Auto SalesAlpha Auto Sales Lowest Price Guaranteed!

213 West 29th Street, Minneapolis, MN 55408 651-239-6540

የኛ ትርፍ የደንበኞቻችን ደስታ ነው

We Guarantee Customer SatisfactionWe Guarantee Customer Satisfaction

ያለ ወሲብ... ከገጽ 8 የዞረ

በሀፍረት ተሸብበህ በዝምታ ብትቀመጥ እርሷም የራሷ የተሳሳተ መደምደሚያ ላይ ትደርሳለች፡፡ በግልፅ መወያየቱ ብቻ ጭንቀትህን ከማቅለሉ ባሻገር ከግምትህ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ እሷም በጣም ትረዳሀለች፤ ልትረዳህም ዝግጁ ትሆናለች፡፡ 4. ከወሲብ በፊት የሚደረጉ መነቃቂያዎች (foreplay) ማነስም መብዛትም የለባቸውም፡፡ ከዚህ ባሻገር ወሲብ አካል አልቆም ብሎ ሲለግም በእጅ (አንተ ወይም እርሷ) ለማነቃቃት መሞከር ሊረዳህ ይችላል፡፡ 5. እንደ ጫትና መጠጥ አይነቶቹ ዕፆች ፍላጎትን አሻቅበው ብቃትን የሚነጥቁ ሁነኛ የወሲብ ጠላቶች ናቸው፡፡ እነርሱን በተመለከተ ጥንቃቄ አድርግ፡፡

ዝም በል... ወደ ገጽ 9 የዞረ

ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚና ቁጥጥር የተደረገበት ወሬ አገር በሚተዳደርበት ጊዜ፣ አለመስማትን እና አለማወቅን (መንግሥታዊ የመረጃ ግርዶሽን) መታገል ሲገባ የሰማውንና ያወቀውን “እኮ ማን ስማ አለህ” ማለት አያዋጣም። ይህንን የሚለው አካል ነገሩ እንዳይሰማበት የፈለገው እንጂ ተጎጂው አለመሆኑም በቅጡ ይታወቃል።

ዳያስጶራውን አምርሮ የመጥላት እና በጅምላ ክፉ ስም የመስጠት ተደጋጋሚ ሙከራ ፍሬ ማፍራቱን ለማወቅ ተርታ ግለሰቦች እና ቤተ እምነቶች ሳይቀር ማንጸባረቅ የጀመሩትን ተመሳሳይ አመለካከት መመልከት ይገባል። የግለሰቦቹን እንኳን

ለጊዜው ብናቆየው የአንዳንድ ቤተ እምነት አስተዳደሮችና መሪዎች ከውጪ የሚመጣላቸውን የአማኛቸውን ሐሳብ፣ ልክ እንደ መንግሥት፣ “አፍራሽ፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጥያቄ” አድርገው ሲመለከቱት ማየት እየተለመደ መጥቷል። ‘አጋጣሚ ነው ወይስ የተላለፈ አዋጅ አለ?’ የሚያሰኝ ነው። የቤተ እምነት መሪዎች ሰማያዊውን መንግሥት መጠበቅ ትተው ምድራዊውን መንግሥት ለመጠበቅ ደፋ ቀና ሲሉ እነርሱን የሚከተላቸው ምእመን እንደሚመለከታቸው እንኳን ይዘነጉታል። እነርሱም ከምድራዊው ባለ ጉልበት ጋር ተደርበው “ውጪ ያላችሁት ዝም በሉልን፣ እንደፈቀድን እንሁን” ሲሉ አዋጃቸውንም በደህና ጊዜ የሚናገሩትንም ሰማያዊ ቃል የሚሰማቸው ጆሮ ያጣሉ። በርግጠኝነት ግን ማንም ዝም አይልም።

መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን!!!! ይቆየን - ያቆየን

ጽናት... ከገጽ 11 የዞረ

ያለበት አንድ ሳያስተውሉ የዘለሉት ነገር አለ፡፡ ይህም ነገር ‹‹ውድቀትን›› ወደ ‹‹ስኬት›› ለመቀየር የሚያስፈልግ ዕውቀት ነው፡፡

ጽናትን እንዴት ማጎልበት ይቻላል፤ አራት ቀላል የጽናት ባህል ማጎልበቻ መንገዶች አሉ፡፡ ትልቅ እውቀት ወይም ከፍተኛ ትምህርት አይጠይቅም፤ ግን ትንሽ ሰዓት ወይም ጥረት ነው የሚጠይቁት፡፡

አስፈላጊዎቹ እርምጃዎች 1. በጽኑ ፍላጎት የተደገፈ ቁርጠኛ አላማ፤

2. ቀጣይነት ባለው ጥረት የሚገለጽ የተወሰነ አላማ፤ 3. ለእኩይ እና አሰናካይ ተጽዕኖዎች የተዘጋ አዕምሮ፤

ከዘመድ ከወዳጅና ከቅርብ ሰዎች ሁሉ የሚመጣ ተጽኖ፤ 4. በአላማህና እቅድህ የሚያበረታቱህ እና የሚደግፉህ

ሰዎች ትብብር፤ እነዚህ አራት እርምጃዎች በማንኛውም ህይወት ውስጥ

ለሚደረግ ስኬት አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ በነዚህ እርምጃዎች ነው አንድ ሰው የኢኮኖሚ ህይወቱን መጨረሻ የሚወስነው፡፡ ራስ ወደ መቻል የሚደርሱት ይብዛም ይነስም ለብልጽግና የሚያደርሱ እርምጃዎች ናቸው፡፡ ወደ ኃይል፣ ዝናና እውቀት የሚመሩ መንገዶች ናቸው፡፡ ከውድቀት በኋላ የተደላደለ ህይወትን ይሰጣሉ፤ ህልምን ወደ እውኑ ዓለም ይቀይራሉ፡፡ ፍርሃትንና ተስፋ መቁረጥን የምናስቀርባቸው መንገዶችም ናቸው፡፡ እነዚህን እርምጃዎች ለማወቅ የሚጥር ሰው ታላቅ ሽልማት አለው፡፡ እነዚህ የራስን እድል፣ ስኬት የምትቆጣጠርባቸውና ከህይወት የምንጠይቀውን ሁሉ የምናገኝባቸው መንገዶች ናቸው፡፡

‹‹ኤዲ ካንደር በ1929 በደረሰው ቀውስ ምክንያት ገንዘቡን ሁሉ አጣ፡፡ ግን ድፍረቱን እና ጽናቱን አላጣም ነበር፡፡ በነዚህ ምክንያቶች በኋላ በጥረቱ ገቢው በሳምንት 10,000 ዶላር መድረስ ችሎ ነበር፡፡ በእውነት ጽናት ያለው ሰው ሌላ ምንም ነገር ባይኖው የመከራ ጊዜን ማለፍ ይችላል›› ይላል የናፖሊዮን ሂል፡፡

ክብደት... ከገጽ 16 የዞረ

እንቅስቃሴና ለጤናማ አመጋገብ ቅድሚያ መሰጠቱ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አሳስበዋል፡፡

ውፍረት ከተስተካከለ በኋላ ያገረሻል? በአካላዊ እንቅስቃሴ፣ በአመጋገብ መስተካከልም ሆነ በጠቀስናቸው መድሃኒቶች የተስተካከለ ውፍረት የሚያገረሽበት አጋጣሚ ሰፊ መሆኑን ዶክተሯ ይናገራሉ፡፡ ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ሲያስረዱም ከተስተካከሉ በኋላ በቸልተኝነት ወደቀድሞው ያልተስተካከለ አመጋገብ፣ አካላዊ እንቅስቃሴን ማቆምና የመሳሰሉት ነገሮች ወደቀደመ ውፍረታቸው ስለሚመልሳቸው ሳይሰለቹና ሳይዘነጉ ጤናውን አመጋገብ፣ አካላዊ እንቅስቃሴውንም ሆነ የሐኪም ምክርን መከተልን ባህል ማድረግ እንዳለባቸው፣ በተለይ መድሃኒቱ ውፍረትን ለመቀነስ ማስጀመሪያ እንጂ እንደ ዘላቂ መፍትሄ መወሰድ እንደሌለበት በመምከር ሀሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡

Zehabesha.com ከሚኒሶታ አልፎ በዓለም አቀፍ

ደረጃ በፍጥነት እያደገ ያለ ድረገጽ፤ ፈጣን መረጃ

ሲፈልጉ ድረገጻችንን ይጎብኙልን።

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ትልቁን የMoroccan Oil ሻምፖና

ኮንዲሽነር ከገዙ

Moroccan Oil ለሚገዙ

Bouncy

Cream Large

Nairobi Products

በደቡብ ክልል ጋሞ ጐፋ ዞን በሚገኘው ምዕራብ አባያ ወረዳ ልዩ ስሙ አልገሌ ቀበሌ ሺለሸኮ አካባቢ ሰፊ የፍርፍሬ እርሻ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን መደረጉ ተጠቆመ፡፡ በተለይ የአቶ መሐመድ መጠሎ እና የአቶ ተቀባ መጠሎ የሙዝ እርሻ አላግባብ መመንጠሩ ተገልጿል፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመው ሐሙስ ጥር 3 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 4 ሰዓት አካባቢ የወረዳው መስተዳደር ተወካይ አቶ ከፍያለው ቦጋለ እና የወረዳው ሲብልሰርቪስ ኃላፊ

አቶ አርባ ጐጃ በተገኙበት በመሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ማድረጉን ምንጮቻችን ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በዕለቱ የማሳው ባለቤቶች በሥፍራው የነበሩ ሲሆን የአካባቢው ሞሌ የተባለ አጐራባች ቀበሌ ነዋሪዎች በድርጊቱ ላይ የተሳተፉም እንዳሉ ተገልፆል፡፡

የጉዳዩን አሳሳቢነት አስመልክተው ጉዳት የደረሰባቸው የአካባቢው ገበሬዎች ለዞኑ መስተዳደር አካል ለሆኑት ለአቶ እሸቱ ቅሬታቸውን በአካል ሄደው ማምልከታቸው ታውቋል፡፡ የመስተዳደሩ አካልም የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ አርባን ቅሬታ አቅራቢዎች በተገኙበት ስለጉዳዩ ሲጠይቋቸው “የፍራፍሬ ማሣው የተጨፈጨፈባቸው አላግባብ ነው፤ ድርጊቱን የፈፀሙት ላይም እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ገበሬዎች ግን “እንኳን የፍራፍሬ ማሳችሁ ቀርቶ ገና ራሳችሁንም እናጠፋችኋለን የሚል ገና ማስፈራሪያ የወረዳው አስተዳዳሪዎች ባሉበት ተሰጥቶናል፤ ስለዚህ አሁንም ጉዳዩ ግልፅ ስላልሆነ ስጋት አለን” ብለዋል፡፡

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣም ስለጉዳዩ ለማጣራት የወረዳው ዋና አስተዳደር የሆኑትን አቶ አዲሱ አርባ ጋር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ ከአዘጋጁ፡ (በኢትዮጵያ እንዳይታተም የታገደው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በዘ-ሐበሻ ላይ እንዲታተም የላከው ነው።)

አባባሎች - አንዲት እናት ሴት ልጇ ከቀጠሮ ቦታ ዘግይታ ወይም ፈጥና ስትመለስ ትጨነቃለች፡፡ - ትክክል የመሆኛው እጅግ በጣም አደገኛው ጊዜ ሁሉም ሰው ስህተት በሚሆንበት ጊዜ ነው፡፡ - ለማያምን ሰው ሞት መጨረሻው ነው፤ ለሚያምኑት ግን መጀመሪያ ነው፡፡ - አንድን ወንድ በጓደኞቹ ማወቅ ትችላለህ፡፡ አንዲትን ሴት ግን ገና በቅርቡ በተወችው ጓደኛዋ ነው ልታውቃት የምትችለው፡፡ - አንዲት ቀኑን ሙሉ ስታወራ የምትውል ሴት ሌሊቱን ሙሉ ሲያነጥስ የሚያድር ባል ያስፈልጋታል፡፡

ከ8 ወደ 10 እንጀራ አደገ

ዌብሳይት ለማሰራት

ቢዝነስ ካርድ ሲፈልጉ ለፍላየር ህትመት ለሠርግ ካርድ የጠርሙስና የቲሸርት ህትመቶች ለሁሉም እኛ ጋር ይደውሉ።

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Phone:- 651-641-0931 2147 university avenue west suite 117 . St. Paul, MN 55114

www.gobena-law.com

Law Practice with Passion!

GOBENA & ASSOCIATES Attorney At Law

ከአፍሪካ... ከገጽ 7 የዞረ

ከሀገር ውስጥ ሊጎችና በውጭ ከሚገኙ ጥቂት ተጫዋቾች የተዋቀረው የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ስብስብ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በፊት ይህ ነው የሚባል ግምት ባያገኝም ከስዊድን ሀገር የመጣው የክንፍ ተጫዋች ዩሱፍ ሳላ፤ከአሜሪካ ሜኒሶታ የመጣው ፉአድ ኢብራሂም፤በግብፅ ዋዲ ዳግላ ክለብ የሚጫወተው ሳላዲን ሰኢድ፤አዳነ ግርማና ሌሎች የአገር ውስጥ ሊጎች ተጫዋቾች እያሳዩት ያለው ብቃት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የተለየ ግምት እንዲሰጣት አድርጓል።

በዋልያዎቹ ስብስብ ሳላዲን ሰኢድ አፍሪካ ዋንጫ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር ከሚችሉ ተጫዋቾች ዋነኛው ሊሆን እንደሚችል ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በመዘገብ ላይ ይገኛሉ። ሳላዲን ከእነ ዩሱፍ ሳላና ፉአድ ኢብራሂም ጋር የፊት መስመሩን በመምራት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ከሰላሳ አንድ ዓመት በኋላ ያልተጠበቀ ውጤት እንድታስመዘግብ የማድረግ አቅም እንዳለው እየተነገረለት ነው።

በሌላ በኩል የኮትዲቯር ወርቃማው የእግር ኳስ ትውልድ የተባለለት የእነ ዲዲየር ድሮግባ፤ኮሎ ቱሬና ያያ ቱሬ ስብስብ የአፍሪካ ዋንጫን የማንሳት የመጨረሻ እድላቸው የዘንድሮው ውድድር ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው። በተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር የቻሉ

በርካታ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን ያሰባሰበው የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ የፊፋን የደረጃ ሰንጠረዥ በቀዳሚነት መምራት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። ይሁን እንጂ ወርቃማው የእግር ኳስ ትውልድ በተደጋጋሚ ለፍፃሜ ቢደርስም ዋንጫውን ለማንሳት በለስ አልቀናውም። ባለፉት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች እንኳን ለፍፃሜ ደርሶ በግብፅና በዛምቢያ በመለያ ምት ተሸንፎ ዋንጫ ሳያነሳ ቀርቷል። የኮትዲቯር ኮከቦች እድሜያቸው እየገፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን የመሆን የመጨረሻ እድላቸው በመሆኑ የስብስቡን ወርቃማነት የሚያስመሰክር ዋንጫ የሚያነሱበት አጋጣሚ አሁን ነው። በእዚህም የተነሳ ዝሆኖቹ በመባል የሚታወቁት የኮትዲቯር ተጫዋቾች የሚታወሱበትን ዋንጫ ለማንሳት ከመቼውም በላይ የተለዩ ሆነው እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

በእንግሊዙ ቼልሲ ክለብ አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ባለፈው የውድድር ዓመት መጨረሻ ወደ ቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሽኑዋ ያመራው ዲዲየር ድሮግባ በሀገሩ ታላቅ ክብር ቢሰጠውም የአፍሪካ ዋንጫን አንስቶ ለሚያከብረው የሀገሩ ህዝብ ደስታን መፍጠር አልቻለም።ይሁን እንጂ ምናልባትም የመጨረሻው በሆነው የአፍሪካ ዋንጫ የተለየ ችሎታውን ተጠቅሞ ታሪክ የሚሰራበትን እድል ሊፈጥር የማይከፍለው መስዋዕትነት አይኖርም።

ጥቋቁር ከዋክብት በመባል የሚታወቁት የጋና ብሔራዊ

ቡድን ተጫዋቾች የአፍሪካ ዋንጫን ለማግኘት ጉጉት ያደረበትን ህዝባቸውን ለማስደሰት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ናቸው። ጋናውያን ተጫዋቾችም ዋንጫ ለማንሳት የዘንድሮው ስብስብ ትልቅ እድል እንዳለው አምነው ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

ጋናውያን በተለያዩ የአፍሪካ ዋንጫዎች ቢያንስ ግማሽ ፍፃሜ የመድረስ እድል ነበራቸው።ነገር ግን በተለያዩ ስህተቶች ዋንጫ ለማንሳት ሳይታደሉ ቀርተዋል።እ.ኤ.አ በ2010 የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ያኮራ ብቃት ካሳዩ ጋናውያን ተጫዋቾች መካከል በርካቶቹ በዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የጥቋቁር ከዋክብቱ አባላት ናቸው። ከእነዚህም መካከል ዋነኛው አሳሞአ ጂያን ተአምር ይፈጥራል የሚል ግምት አግኝቷል።

ባለፈው የኢኳቶሪያል ጊኒና ጋቦን የአፍሪካ ዋንጫ ያልታሰበ ታሪክ የሰሩት ዛምቢያዎች ለዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ሲያደርጉ ባካሄዷቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በበርካቶቹ መሸነፋቸው በዋንጫው የተሰጣቸው ግምት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮባቸዋል። የአምናው ስብስብ አሁንም አንድ ላይ በመኖሩ ያለፈውን ብቃታቸውን የመድገም እድል

እንዲኖራቸው ያደርጋል። «በክርስቶፈር ካቶንጎ የሚመራው የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞው ጥንካሬውንና የቡድን

መንፈሱን አሁንም ከደገመ ታሪክ ይሰራል» የሚሉ አስተያየቶች በዝተዋል። አንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ግን

ዛምቢያዎች የምድብ ጨዋታቸውን እንኳን ለማለፍ ይቸገራሉ እያሉ ይገኛሉ። ከአስራ ስድስት ዓመት በፊት ባስተናገደችው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን መሆን የቻለችው አስተናጋጇ ደቡብ አፍሪካ ዘንድሮም ተመሳሳይ ታሪክ የመስራት እድል ይኖራታል ተብሎ ይጠበቃል።

ዮሐንስ... ከገጽ 15 የዞረ

አስባለሁ፡፡ በዙሪያዬ ያሉት ጓደኞቼም ስላገቡ እኔም አስባለሁ፡፡ በተለይ በጣም ረጅም ጊዜ የኖርኩት ከይገረም ደጀኔ ጋር ነው፡፡ ይገረም ወንድሜም ጓደኛዬም አባቴም ብዙ ነገሬ ነው፡፡ ከስድስት ዓመት በላይ አብረን ኖረናል፡፡ እሱ ለእኔ ሮል ሞዴሌም ነው፡፡ የሱን ጥሩ የትዳር ህይወት ሳይ እየተገፋፋሁ ነው፡፡ ሌላ አብዮት የሚባል ጓደኛችን አግብቷል፡፡ ሚዜ ነበርኩ፡፡ በሱ በሱ ሁኔታ እኔም እየጓጓሁ ነው አሁን፡፡

ብዙ ችግሮችን አልፈህ ነው አሁን ያለህበት የደረስከው፡፡ ያንተ ጥንካሬ ምን ነበር? ለሌሎችስ ምን ትመክራለህ?

ዮሐንስ፡- እንዳልኩት ምንም ነገር አልነበረኝም፡፡ ብዙ ችግር አይቻለሁ፡፡ ብዙ ነገር የሚሸፍንልኝ ይገረም ነበር፡፡ እኔም አልሰንፍም፡፡ ያገኘሁትን ስራ እሰራለሁ፡፡ ቴአትር እየሰራሁ ቀለም መቀባት ሳገኝ ሰፈር ውስጥ ቀለም እቀባ ነበር፡፡ እና ለሌላውም የምለው ነገር ስራን ያለመናቅ ሰው ለመሆንና ካለንበት ችግር የማምለጫው ብቸኛ አማራጭ ትዕግስት እያደረጉ ያገኙትን መስራት ነው፡፡ ይሄን ነው የምለው፡፡

“let our family fight for your family”

የኮዲ ቤተሰብ ጠበቃዎች ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር አብረው በመሥራትና ጥብቅና በመቆም የረዥም ልምድ አላቸው!!

የኮዲ ሕግ ጠበቃዎች ቡድን በሥራ ቦታ አደጋ፣ በመኪና አደጋ፣ በራስ ላይ

በሚደርስ ማንኛውም አደጋ የሰዎችን መብት በማስከበር ማግኘት የሚገባቸውን

ጥቅም በማስገኘት የታወቀ ነው። እርስዎም ምርጫችሁ እኛ እንሁን።

Phone: 651.294.0994 Fax: 651.292.4955 Email: [email protected] Our Location: 359

Commerce Court Vadnais Heights, MN 55127 www.codylawgroup.com

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

520 Snelling Avenue North Saint Paul, MN 55104

(651) 644-3500 ወይም (952) 688 3099 ከፋሲካ ምግብ ቤት ጎን

ጆን አመሰግናለሁ ለፈቃደኝነትህ፡፡ ዮሐንስ፡- እኔም በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ይሄን እድል

ስለሰጣችሁኝና እንግዳ ስላደረጋችሁኝ፡፡ ከገመና ድራማ እንጀምር ስካርን እንዴት አገኘኸው? ዮሐንስ፡- /እየሳቀ/ በአካባቢዬም በሰፈሬም ብዙ

ካራክተሩን የሚመስሉ ስላሉ ብዙም አላስቸገረኝም፡፡ አንተስ ሰክረህ ታውቃለህ? ዮሐንስ፡- አይ እንደዚህ ራሴን ስቼ ሰክሬ አላውቅም፡፡

አንዳንዴ ከጓደኞቼ ጋር እዝናናለሁ፡፡ ሲጀመር ከልክ በላይ መሄዱን አልወደውም፡፡ እና ሰክሬ አላውቅም፡፡

ቅዱስ መጽሐፍ አትስከር ይላል፤ የመጠጥ ጥሩና መጥፎ ጎኑ ምንድን ነው ትላለህ?

ዮሐንስ፡- ጥሩ ጎን አለው፡፡ መጥፎ ጎን አለው ልንለው የምንችለው ነገር አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ራሱን ለማኖር የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት ይሰራል ይለፋል፡፡ ያንን የድካሙን ጊዜ ደግሞ ራሱን ዘና ለማድረግ ለቀጣይ ስራ ፍሪ ለመሆን ሲል ይዝናናል፡፡ ሰው ደግሞ የተለያየ ፍላጎት ይኖረዋል፡፡ እንደ መልካችን ባህሪያችንና ፍላጎታችንም ይለያያል፡፡ የሚያዝናናንም ነገር ይለያያል፡፡ እና እንደ መዝናኛ ከጓደኞችህ ጋር ልክህን ሳታሳልፍ ከተዝናናህበት ጎጂ ነገር የለውም፡፡ ያው ሰውነታችንም የተወሰነ ፐርሰንት አልኮል ይፈልጋል ይባላል፡፡ እሷንም ለማሟላት አይከፋም /ሳቅ/ ግን ከዛ ሲያልፍ ደስ አይልም፡፡ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች ታያለህ እና ለምንድን ነው የሚጠጣው እንዲህ ለመሆን ከሆነ ትላለህ፡፡

የገመና ስራህ ምን አይነት አስተያየቶችን አመጣልህ? ዮሐንስ፡- ገመና እንግዲህ ሲጀምር አካባቢ ሰው ትንሽ ግራ

የመጋባት ነገር ነበረው፡፡ ከመጀመሪያው ገመና ጋር የሚቀጥል ታሪክ ጠብቀው ስለነበር ያ ሳይሆን ሲቀር ግራ ተጋብተው ነበር፡፡ አሁን ግን ከአምስት ክፍል በኋላ እየጠራ የመጣ ነገር ስላለ አሁን በፍላጎት የማየት ነገር ይታያል፡፡ ከተለያዩ ሰዎች የምሰማው አስተያየት አሪፍ ነው፡፡ ተከታታይ ድራማዎች ደግሞ እየቀጠሉ ሲሄዱ ነው የበለጠ እየተወደዱ የሚሄዱት፡፡ አሁን እንዲህ ነው ለማለት ያዳግታል፡፡ ግን ቢሆንም አሁንም ያለው ነገር ጥሩ ነው የነገውን ያመላክታል፡፡ ብዙ የማገኛቸው ምላሾች ጥሩ ናቸው፡፡ በተለይ የእኔ ካራክተር በየቤቱ ያለ ችግር ወይም ጉዳይ ስለሆነ ወጣቱም እናቶችም የኛ ቤት ነው ይላሉ፡፡ አንዱ እንደውም የእኔን ታሪክ የነገራችሁ ሰው አለ እንዴ? የእኔ ታሪክ ነው አባቴ የህግ ባለሙያ ነው እናቴ ቤት ውስጥ ካሉት ልጆች እኔን ነው የምትወደው አለማያ ዩኒቨርሲቲ ሄጄ አቋርጬ ነው የመጣሁት ብሎ የሆነ ቀን ነግሮኝ አስገርሞኝ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገሮች አሉ፡፡ ጥሩ ምላሽ ነው ያገኘሁት፡፡

እሱን ካራክተር እንድትሰራ ስትመረጥ ትንሽ ውዝግብ ነበር ይባላል ምን ያክል እውነት ነው?

ዮሐንስ፡- ገመና ላይ ሲጀመር እንግዲህ ተከራክረው ነበር መሰለኝ እኔን ለማድረግና ላለማድረግ፡፡ እና አቶ እቁባይና አዲስ ተስፋ ሁለቱ ናቸው ትልቁን ሚና የተጫወቱት፡፡ ከዛ ሌሎቹም ተስማምተውበት ነው እኔን ካስት ያደረጉኝ፡፡ ሌሎች ተዋናዮችም ታስበው የታጩ ነበሩ የኔን ቦታ ለመስራት፡፡

ትወናህን ስታየው በብቃት ተወጥቼዋለሁ ትላለህ? ዮሐንስ፡- እንደዛ ለማለት እንኳን ገና ነኝ፡፡ እንደዛ ለማለት

አልደፍርም፡፡ ይሄን ማለት ያለበት ተመልካቹ ይመስለኛል፡፡ ድራማውም ገና ነው፡፡ እኔ ግን የቻልኩትን ሁሉ ከማድረግ አልቦዘንኩም፡፡ የአቅሜን ያህል እየሰራሁ ነው፡፡

የውሸት መስከር የቱ ጋር ነው ክብደቱ? ምናልባት መሃል ላይ ኖርማል የመምሰል ችግርም ሊደጋገም አይችልም?

ዮሐንስ፡- አዎን፡፡ አንዳንዴ ይከብዳል፡፡ ከስካሩ የምትወጣበትና ኖርማል የምትሆንበት ሰከንድ ይኖራል፡፡ በነገራችን ላይ ግን ሰካራሞችን አይተህ ከሆነ በእነሱም ላይ እንዲህ ያለው ነገር አለ፡፡ ብዙ ጊዜ ድብን ያለ ሰካራም ይመስሉና በመሀል ደግሞ ኖርማል አነጋገር ኖርማል አረማምድ ሲጠቀሙ ታያለህ፡፡ እና ከዚህ አንግል ከተመለከትነው ምንም አይደለም፡፡ ግን እንደ ትወና ፍፁም ልትሆንና ያለምንም መንገጫገጭ ልትሰራው ይገባሃል፡፡ እዚህ ጋር ትንሽ ይከብዳል ልንለው እንችላለን፡፡ በተረፈ ግን እንደ ተዋናይ ግዴታ ነው፡፡ የሚያንሸራትቱ ዲያሎጎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡

አንተ በቲቪ ስታየው እንዲህ ሰርቼዋለሁ በማለት የተገረምክበት ክፍል አለ?

ዮሐንስ፡- የራስህን ስራ ስታይ እንደዛ አትልም፡፡ ምናልባት ለየት ሊልብህ ይችላል አንዳንድ ቦታ ላይ፡፡ ምክንያቱም ስትሰራው እና ስታየው አንተ የተለያየ ሰው ነህ፡፡ ስትሰራው ካራክተሩ ውስጥ ሆነህ ስለሆነ በዛ በስካር ሙድ ውስጥ ነው የምትሆነው፡፡ ስታየው ግን አንተነትህን ራስህን ሆነህ ስለሆነ ስህተቱ ሊታይህ ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ ገምጋሚ ነው የምትሆነው፡፡ እና ወይኔ እዚህ ቦታ ላይ እንዲህ ባደረኩት ኖሮ የምትለው ነገር ነው የሚበዛው እንጂ ፐ የምትልበት ነገር አይኖርም፡፡

የሰራኸው ከአንጋፋዎች ጋር ነው ከነሱ ጋር በመስራት ምን አይነት ልምድ አገኘህበት?

ዮሐንስ፡- እኔ ስራውን ከመስራቱም ከዝናውም ከተወዳጅነቱም ሁሉ በላይ በእውነት ነው የምልህ ከእነሱ ጋር መስራቱ ያስደስተኛል፡፡ ከጀማነሽ ጋርም ከተፈሪ ጋርም ከሌሎቹም ጋር መስራት መቻሌ በጣም እድለኛ ነኝ ብዬ እንዳስብ ነው ያደረገኝ፡፡ በተለይ ጀማነሽ ተፅዕኖ ፈጥራብኛለች፡፡ ችሎታዋ ይገርምሃል፡፡ እና ደስ ብሎኛል፡፡ በተለይ ጀማነሽና ተፈሪ ከጅነቴ ጊዜ ጀምሮ የገዘፈ ስምና ስራ ነው ያላቸው፡፡ በእኔ ውስጥ አብሬያቸው መስራቱን አስቤውም አላውቅም ነበርና ሲሆን ደስ ነው ያለኝ፡፡ እድለኛ ነኝ ነው የምለው፡፡

አሁን ደግሞ ወደ ፊልሞችህ እንምጣ የመጀመሪያ ፊልምህ የቱ ነው?

ዮሐንስ፡- በሲኒማ ቤት ደረጃ ሙሉ ካራክተር ይዤ የተጫወትኩት ‹‹ስስት›› የተሰኘውን ፊልም ነው፡፡ ገና ‹‹ስስት›› ነው የመጀመሪያ ስራዬ እላለሁ፡፡ ግን በቪሲዲ የወጡ ፊልሞች አሉ፡፡ ለገበያ የቀረቡ ማለት ነው፡፡

እስኪ የተወሰኑትን ርዕሳቸውን ንገረን? ዮሐንስ፡- ለምሳሌ በቪሲዲ ለገበያ ቀርበው ከታዩትና ጥሩ

ምላሽ ከነበራቸው ልጥቀስልህ፤ ፈንጂ ወረዳ፣ ጩኸት፣ ሾተል፣ አልወድሽም የተሰኘው ፊልም ላይም ትንሽ ካራክተር ነበረኝ፡፡ ብዙም ረዥም ጊዜ ያለው ካራክተር ባልወክልም እነዚህ ፊልሞች ላይ ሰርቻለሁ፡፡ በሲኒማ ቤት ደረጃ ሙሉ ካራክተር የተጫወትኩት ‹‹ስስት›› ላይ ነው፡፡

ከረዳት ገፀ ባህሪያት ወደ አቀንቃኝ /ዋና/ ገፀ ባህሪያት ‹‹ስስት›› ላይ ስትመጣ አልከበደህም?

ዮሐንስ፡- ፍፁም በጣም ጥሩ ልጅና የሚገርም አቅም ያለው ነው፡፡ ከተገናኘንበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ኃላፊነቶችን ወስዶ ነው ከእኔ ጋር የሰራው፡፡ እኔ በፊት መጀመሪያ ላይ የሰራሁት ፊልሞች ላይ የኮሜዲ ካራክተሮችን ነበር የተጫወትኩት፡፡ እና ብዙ ሰዎችም ካራክተሩ ትራጄዲ ስለሆነ ይሄ ልጅ ኮሜዲ ያደረግብሃል በማለት ስጋታቸውን ነግረውት ነበር፡፡ እናም እኛ ሀገር ደግሞ እንዲህ ሃላፊነትን የሚወስድና ይስራው የሚል ዳይሬክተሮች በዛው በተወደድህበት ገፀ ባህሪ ነው የሚያሰሩህ እንጂ ሌላ ስራ ሊያሰሩህ ሃላፊነቱን አይወስዱም፡፡ እና ፍፁም ግን ይሄን ሃላፊነት ወስዶ ነበር ያሰራኝ፡፡ ከዛ በፊት ብዙም አያውቁኝም፡፡ እና ስሰራ ከልቤ ነበር ታሪኩም ውስጥህን ይይዝሃል፡፡ ታሪኩ ደግሞ ከሱ ጋር አብሮት ብዙ ጊዜ የኖረ ስለሆነ እያንዳንዷን ነገር የካራክተሩን ምንነት ያውቀዋል፡፡ እና እየሰራ በጣም ነፃነት እንዲሰማኝ ነው ያደረገው፡፡ እየሰራሁ እንዲመስለኝ አላደረገም፡፡ ሁላችንም እንደ ፊልም ቡድን ሳይሆን እንደጓደኛ ሆነን ስለሰራን የእንግድነት ስሜት እንዳይሰማኝ ስላደረጉኝ በነፃነት ነው የሰራሁት፡፡ እና ከብዶኝ አይደለም የሰራሁት፡፡ በዚህ አጋጣሚ ፍፁምን አመሰግናለሁ፡፡ ከዛ በኋላም ነው የተለያየ ፊልም ላይ ለመስራትና ገመና ላይም ለመጠራት የበቃሁት፡፡

‹‹ስስት›› ላይ ያለው የወከልከው ካራክተር ምን አይነት እንደነበር ለአንባቢዎቻችን ትንሽ ታካፍልልን?

ዮሐንስ፡- ‹‹ስስት›› ላይ ያለውና የተጫወትኩት ገፀ ባህሪ አሸናፊ የሚባል ወጣት ነው፡፡ በቤተሰብ ችግር ያደገ ሲሆን ካደገ በኋላ ራሱን ለማኖር ይታገል የነበረ ልጅ ነው፡፡ ፀጉር ቤትም እየሰራ በዚህ የኑሮ የትግል ጉዞ ውስጥ እንዳለ የኑሮው መንገድ ከዛች ልጅ ጋር ያገናኘዋል፡፡ እሷን ያፈቅራል፤ የሱን ጥሩነት አይታ እሷም የበለጠ ጥሩ ሰው ሆና ነው የምትቀርበው ቤተሰቧን ሁሉ ጥላ፡፡ እና በወጣትነት ጊዜ ደግሞ ገደሉን ሳይሆን ሳሩን ስለምታይ እዛ ፍቅር ውስጥ ከገባ በኋላ በቤተሰብም ችግር ተፈጥሮ የህይወት ምስቅልቅል ውስጥ የሚገባና የሚያሳዝን ካራክተር ነው፡፡ መሰናክሎችን ለማለፍ ሲጥር ከየአቅጣጫው የሚመጡበት ሰው ነው፡፡

በፊልም ታሪክ መማር ነው ያለብን ወይስ መዝናናት ብቻ? ዮሐንስ፡- ሁለቱንም በአጥጋቢ ሁኔታ የምናገኝበት ቢሆን

ይመረጣል፡፡ መዝናናት ብቻ የሆነው ግን ብዙም መብዛት የለበትም፡፡ አያዝናና እያልኩ አይደለም፡፡ ምክያቱም የጥበባዊ እሴቶች አንዱ አላማ ማዝናናት ነው፡፡ ሰውም ብዙ ጊዜ ዘና ለማለት ሲል ነው ፊልም ቤት ልግባ የሚለው፡፡ ግን የበለጠ ጥሩ የሚሆነው ተዝናንተህበትም ለህይወትህ አንድ ትምህርትን ገብይተህበት መውጣት ስትችል ነው እላለሁ በራሴ እምነት፡፡ የምትማርበት ሲሆንም ነው የፊልም ትልቁ ጥቅሙና የሀገር እድገትንም መፍጠር የሚችለው፡፡ አለበለዚያም ማዝናናት ብቻ ሲሆን አንዴ ብቻ አይተኸው የምትረሳው ይሆናል፡፡ ግን በአንዴ መረሳት የለበትም፡፡ መታወስና ለውጥ አምጪ መሆን መቻል ይኖርበታል፡፡ የትውልድን መስመር ማቅናት አለበትና፡፡

አሁን የወጡ ፊልሞችም አሉህ አይደል? ዮሐንስ፡- አዎን አንድ ሁለት ፊልሞች ወጥተዋል፡፡ አንዱ

አሁን ሊመረቅ ነው፡፡ ከፍፁም ጋርም የሰራነው እያለቀም ያለ አለ የወጡት ፊልሞች ያለ ሴት እና ተስፈኞቹ ናቸው፡፡ አንደኛው ፊልም በጣም ጥሩ ፊልም መሆን የሚችል ነበር፡፡ ግን ዳይሬክተሩና ፕሮዲውሰሩ ጋር አለመስማማት ስለነበር ፊልሙ መታየት ባለበት ደረጃ እንዳይታይ ሆኗል፡፡ ያው

መቼም ሁሉም ነገር የሚስተካከለው በእግዚአብሔር ፈቃድ ጭምር አይደል እየታየ ነው፡፡ ግን ሰው ትንሽ ቅር የተሰኘበት ስህተት ተፈጥሯል፡፡ ያው መስማማት ከሌለ ደግሞ ስኬት የለም፡፡

የፊልም ስራ ህብረትና መስማማትን ይጠይቃል አሁን እንደገለፅከው፡፡ እንደዛ ሳይሆን ሲቀር ደግሞ ውጤታማ ያለ መሆኑም እንዳለ ሆኖ በአርቱም ላይ ሆነ በአርቲስቱ ላይስ የሚፈጥረው ችግር የለም?

ዮሐንስ፡- በትክክል አለ፤ ይሄ ስራ የሚገርምህ ነገር በፍቅር ሆነህ ተቻችለህና አቻችለህ ስትሰራው ነው የሚሳካው፡፡ ምን ያህል ምርጥ ታሪክ ምርጥ ስብስብ ብትይዝ ስምምነትና ቀናነት ከሌለበት አይሳካም፡፡ በቅንነት ሲሰራ ነው የሚሳካው፡፡ ይሄንንም በተመኩሮ አይቼዋለሁ፡፡ ከተለያዩ ሰዎች ጋር በምሰራበት ወቅት፡፡ ቀና ሆነው የሚሰሩት ጋር ያለውን ውጤት አየዋለሁ፡፡ የሆነ ነገር አስበው ደግሞ የሚሰሩት ሰዎች ጋር ያለውን ብልሽት አየዋለሁ፡፡ ስለዚህ ሙያው መጀመሪያ ቀናነትን በአርቱ መቆምን ይጠይቃል፡፡ እንደዛ ካልሆነ ትርፉ ድካም ነው፡፡ አርቱንም መግደል አርቲስቱንም ማድከምና እጀ ሰባራ ማድረግ ነው፡፡

የተዋናይ ህይወት ፈተናው ወይም ትግሉ ምንድን ነው ትላለህ?

ዮሐንስ፡- ትግሉ ሲጀመር ከውሳኔው ይጀምራል፡፡ ተዋናይ ልሁን ብለህ ስትወስን ቻሌንጁ ከውሳኔው ይጀምራል፡፡

አኗኗራችን ላይ በቤተሰብም በኩል ያለው ሆነ በራስህም በኩል ወደዚህ ሙያ ስትመጣ ምንም የለም ሲጀመር፡፡ ተስፋ አድርገህና ስሜትህን አዳምጠህ ነው የምትመጣው፡፡ እና ከምንም ነገር በላይ ከገንዘብም ከኑሮም በላይ የምታስበው መድረኩን አግኝተህ መስራት የምትችልበት እድል ማግኘትህን ነው የምታስበው፡፡ የሆነች ቦታ ላይ ሰርተህ ከሰው የምታገኛትን ምላሽ ነው ላንተ ትልቁ ነገርና የምታስበው፡፡ እና ያንን ነገር እስክታገኝ ብዙ ቻሌጅ አለው፡፡ መራብ መጠማትን ጨምሮ ብዙ ውጣ ውረዶችን ታሳልፋለህ፡፡ ከቤተሰብ ጋር ሁሉ ተጣልተህ ልትወጣ ትችላለህ፡፡ ደግና መጥፎ ነገሩን እርግፍ አድርገህ አልሆን ሲልህ ትተኸው ሌላ ነገር መስራት የምችልበት ነገር አይደለም፡፡ ከገባህበት ልትወጣ አትችልም፡፡ ምናልባት እንኳን ለትንሽ ጊዜ ብትወጣ ትንሽ እንደቆየህ ይመልስሃል፡፡ ወይ ጓደኛህን ስታይ ወይ የሆነ ነገር ስታይ እንደገና ጎትቶ ይወስድሃል፡፡ እና ግን አሪፍ ነገር ነው ከገባህበትና መድረኩን ካገኘህ በኋላ ያለው ነገር፡፡

አንተ ይሄን ዕድል ለማግኘት ምን አይነት ችግሮችን አሳልፈሃል? ከገባህበት በኋላ ምን ተጠቅመህበታል?

ዮሐንስ፡- በትወናው እኔ አገኘሁት ወይም ተጠቀምኩት የምለው ከገንዘቡ በላይ ወይም ከእውቅናው በላይ የባህሪ ለውጥ እንዳመጣ አድርጎኛል፡፡ በልጅነቴ ትንሽ አስቸጋሪ ልጅ ነበርኩ፡፡ እዚህ ሙያ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ግን በችግር ነው ያለፍኩት፡፡ ራሴን እያስተማርኩ ነው የመጣሁት፡፡ የቤተሰብ አንዳችም እርዳታ አልነበረኝም፡፡ ምክንያቱም እናትና አባቴ በልጅነቴ ነው የሞቱት፡፡ ከችግር ጋር ነበርና የምታገለው እዚህ ሙያ ውስጥ ወስኜ ስገባ ቻሌንጆች ነበሩ፡፡ ብዙ ገንዘብ የምታገኝባቸው ነገሮች ሁሉ ጥለህ ነውና የምትገባው ያስቸግራል፡፡ ከወር እስከ ወር ገንዘብ ምንም የማታገኝበት ብዙ ጊዜ ይኖራል፡፡ ስራ አለ የተባለበት ቦታ ሁሉ የማንገባበት የለም፡፡ ፋዘር /ጋሽ ተስፋዬ አበበ/ ጋር ብዙ ቆይቻለሁ፡፡ እና ስትፈልግ ብዙ ነገሮች ውስጥ እንድትገባ ትሆናለህ፡፡ እንድታነብ ትሆናለህ፡፡ ሌላውና ትልቁ ነገር ትዕግስተኛ ያደርግሃል ይሄ ሙያ፡፡ እኔ በጣም ትግስተኛ ሆኛለሁ፡፡ አሁን ላይ እኔ ማንኛውም ነገር በትዕግስት ማለፍና እነዛን የሚገጥሙኝን ነገሮች መቋቋም የምችልበትን አቅም ሰጥቶኛል፡፡ ይሄን ጠቅሞኛል፡፡

በገንዘቡስ በኩል? ዮሐንስ፡- አሁን ላይ ሆነህ ስታስበው ትናንት ከነበሩት

ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበሩት ጊዜያት አሁን ያለው የተሻለ ነው እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ግን ሙያው የምትለፋውን ያህል የምታገኘው ነገር ተመጣጣኝ አይደለም፡፡ ግን ትናንት በዜሮ የሰሩ ስለነበሩ ዛሬ ይብዛም ይነስም እያገኘህ ምቾት ተሰምቶህ ተደላድዬ እኖራለሁ ባትልም እየተንገዳገድክም ቢሆን ትኖርበታለህ፡፡ አንተ ከጣርክ ደግሞ የራስህንም ነገር እየሰራህ ከጠነከርክ ገንዘብ የምታገኝበት ሙያ ነው፡፡

ከትወና ውጪ ድርሰት ትሞክራለህ? ዮሐንስ፡- አዎን፡፡ እንደውም ስጀምር አካባቢ ፋዘር ቤት

እያለሁ በጣም እደፍር ነበር፡፡ እያነበብኩ ነገሮችን እየተረዳሁ ትምህርቶችን እየወሰድኩ ስመጣ ግን አሁን አሁን ፈሪ ሆንኩ፡፡ እና በተለይ ፊልምን ለብቻ መስራትን አልመርጥም፡፡ በህብረት ሆነህ ቡድን መስርተህ መስራት እንዳለብህ ማመን ጀምሬያለሁ፡፡ እና መጻፍ ጀምሬ ብቻዬን መስራት የለብኝም ስል እተወዋለሁ፡፡

የምትፅፈው ነገር አያረካህም? ዮሐንስ፡- እንደዛ ሳይሆን በእኔ እምነት ፊልም የአንድ ሰው

እይታ ብቻ መሆን የለበትም በማለት አምናለሁ፡፡ የብዙ ሰው እይታ ቢሆን የበለጠ አጥጋቢ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ የውጪ ፊልሞችንም ስታይ የፊልም ታሪክ ተብሎ ሶስት አራት ሰው ልታይ ትችላለህ፡፡ ስክሪን ፕሌይ ተብሎ ሁለት ሶስት ሰው ልታይ ትችላለህ፡፡ እና ለምን ሆነ ብለህ ስታስብ ፊልሞቻቸው ፐርፌክት የሚሆኑት የብዙ ሰው ጉልበት ሙሉ ነገር ስለሚፈጥር ነው የሚለውን ምላሽ እንድታገኝ ያደርግሃል፡፡

ያንን ስለማስብ ነው እንጂ የሆነ ወቅት ላይ እጽፍ ነበር፡፡ ታዲያ በህብረተስ ወደፊት ስትል ምን የመጠንከው ነገር አለ? ዮሐንስ፡- የጀመርናቸውም ነገሮች አሉ፡፡ ወደፊትም በሰፊው የምንሰራው ነገር አለ፡፡ አንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ‹‹ፍቅር የትናየት›› የተሰኘውን የመጀመሪያ ቴአትራችንን ስንሰራ አብረን የሰራነው፡፡ የሱ ደራሲ መኮንን ታጠቅ ይባላል፡፡ ከሱ ጋርና ሌሎችም ልጆች አሉ፡፡ ለምሳሌ መፈንቅለ ሴቶችን የጻፈ ጎበዝ ልጆች አሉ፡፡ ከነሱ ጋር ሀሳብ በመስጠት መፈንቅለ ሴቶች ላይም አስተዋፅኦ አድርገናል፡፡ እና እኛ ያንን መንገድ ከነሱ ጋር አብረን ቀጣይ ስራ ለመስራት ጀምረናል፡፡ እንግዲህ የሚያሳካው እግዚአብሔር ነው፡፡ ከፍቅር የትናየት ቴአትር ሌላ ሰርተሃል? ዮሐንስ፡- አዎን፡፡ የሸዋፈራው ቴአትር መስተፋቅር ላይ ሰርቻለሁ፡፡ ፋዘር ቤትም ሰርቻለሁ፡፡ አሁንም አንድ ሁለት ቴአትሮችን በማጥናት ላይ ነኝ፡፡ በቅርቡ ይወጣሉ፡፡ የወደፊት ራዕይህ? ዮሐንስ፡- እንዲህ እንዲህ ልል አልችልም፡፡ ምክንያቱም በብዙ ችግር ውስጥ ነው ያለፍኩት፡፡ ብዙ ነገሮች አንተ እንዳሰብከው ላይሆኑ የሚችሉበት ጊዜ ስላለው ‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው›› የምትለዋ የሰለሞን ጥቅስ በውስጤ ትልቅ ስፍራ አላት፡፡ እግዜር ሲፈቅድ ግን የምሰራቸው ብዙ ነገሮች ውስጤ አሉ፡፡ ከትወና ውጪ የዮሐንስ የግል ህይወቱ ምን ይመስላል? አግብቷል? ዮሐንስ፡- የሚገርምህ ነገር በፍቅር ውስጥ ጠለቅ ብዬ የገባሁት ጊዜ የለም፡፡ ትንሽ እፈራለሁ፡፡ ያሳለፍኩትም ጊዜ ችግር ውስጥ የነበረ ስለሆነ ጠንከር ብዬ አልሄድኩም በፍቅር፡፡ እና አላገባሁም፡፡ እኔ ገና አልቆምኩም፡፡ መጀመሪያ በራሴ ጠንክሬ መቆም አለብኝ ስለምል ነው፡፡ አሁን ጥሩ ጅምር ላይ ስለሆንኩ ወደ ፊት (ዮሐንስ... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

አግልግሎትዎን

መዲናመዲናመዲና ጋዜጣ ላይ ለማስተዋወቅ 612-226-8326

በርከት ያሉ ስራዎችን ለፊልም ተመልካቹ አቅርቦ ተወዳጅነትን ያተረፈ ወጣት አክተር ነው፡፡ ፈንጂ ወረዳ፣ ጩኸት፣ ሾተል፣ አልወድሽም፣ ስስት የተሰኙትን ፊልሞችን ብንጠቅስ በእነዚህ ፊልሞች ላይ ያሳያቸው የትወና ብቃቶቹ ይህን ወጣት አርቲስት የነገረውን የተዋጣና ብሩህ የትወና ጉዞ የሚያመለክቱ እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ አሁንም ከነዚህ ከጠቃቀስናቸው ፊልሞች ሌላ ተሰርቶ አልቀው ለተመልካቹ ሊቀርቡ በዝግጅት ላይ ያሉና የምረቃ ዕለታቸውን የሚጠባበቁም በርከት ያሉ ፊልሞች መኖራቸውንም ልንገልፅ እንወዳለን፡፡ ለምሳሌ መፈንቅለ ሴቶች፣ 3000 እና ሌሎችም፡፡ ዮሐንስ ተፈራ በዚህም ሳያበቃ ገመና 2 በተሰኘውን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈ ድራማም መተወኑ ይታወቃል፡፡

በገመና 2 ድራማ ቀለል ያለና ነገር ግን ተወዳጅ የሆነውን የሰካራሙን ልጅ ካራክተር የወከለ ሲሆን እሱም ጥሩ አድርጎ እንደተወነው የድራማው ተከታታዮች የሚስማሙበት እውነት ነው፡፡ ‹‹በህይወት ዘመኔ ብዙ ችግሮችን አሳልፌ ነው እዚህ አሁን ያለሁበት ደረጃ የደረስኩት›› ከሚለን ወጣት አርቲስት ጋር ስለ ሙያውም ስለ አሳለፋቸው አስቸጋሪ የህይወት ገጠመኞች አውግተናል፡፡

ታክስዎን ኤክስፕረስ በመምጣት ያሰሩታክስዎን ኤክስፕረስ በመምጣት ያሰሩታክስዎን ኤክስፕረስ በመምጣት ያሰሩ

በቅርቡ አንድ የመዳብ ሐውልት ተመርቆ ለተመልካች እይታ ክፍት መሆኑ የዓለም የመገናኛ ብዙሃንን እያነጋገረ ነው ያለው፡፡ ይህ የመዳብ ሐውልት የቆመው ጀርመን ውስጥ ሲሆን መታሰቢያነቱም ከእናታቸው ማህፀን ሲወጡ አካለ ጎደሎ ሆነው ለተወሰዱት 10,000 ህፃናት ማስታወሻነት ለማድረግ ነበር፡፡ እነዚህ 10,000 ህፃናት ደግሞ የተወለዱት ጀርመን ውስጥ ብቻ አልነበረም፣ ከመላው ዓለም የተገኙ ናቸው፡፡ ህፃናቱ ተወለዱበት ዘመን በፈረንጆች አቆጣጠር በ1950ዎቹና በ1960ዎቹ ዓመታት ስለነበረም በአሁኑ ወቅት እድሜያቸው በአዋቂነት የእድሜ ክልል ውስጥ ስለሚሆን አሁንም እየተሰቃዩ ነው ማለት ነው፡፡

በእርግጥ በዘመናዊው የህክምናው ዓለም ውስጥ ይህን የመሰለውን ከባድ ቀውስ ያስከተለው ሌላ መድኃኒት አልነበረም ለማለት ይቻላል፡፡ መድሃኒቱ ታሊዶማይድ ይባላል፣ ታሊዶማይድ ከሌሎች መድሃኒቶች ይልቅ በጣም ጎልቶ እንዲታይ ያደረገውም ችግር በፈጠረባቸው ጉዳቶች ቁጥር በዝቶ መገኘት ብቻ ሳይሆን፣ መድኃኒቱ ባስከተለው የጎንዮሽ ጉዳት ነበር፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ታሊዶማይድ ከ10,000 ያላነሱ ህፃናት በአካለ ጎደሎነት እንዲወሰዱ አድርጓል፡፡ አካለ ጎደሎነት ሲባልም ያለ እጅ ወይም እግር እንዲሁም የተጣመመ ወይም በጣም ያጠረ እጅ ወይም እግር ይዘው ይወለድ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አንዳንዶቹ ደንቆሮና አይነ ስውር ሆነው የተለወዱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ጠማማ የጀርባ አጥንት ወይም ደግሞ ጉድለት ያለበት ልብ ወይም አንጎል ይዘው ነበር የተወለዱት፡፡

ይህ የተረገመ መድኃኒት ተፈብሮኮ ለገበያ የቀረበው በ1950ዎቹ ውስጥ ሲሆን መድኃኒቱ ለገበያ በቀረበበት ወቅትም እፁብ ድንቅ የተባለለት መድኃኒት ነበር፡፡ በእርግጥ መድሃኒቱ ከመድሃኒት ቤት የሚሸመተው ያለሐኪም የማዘዣ ወረቀት መሆኑም የተፈጠረውን ችግር የበለጠ እንዲባባስ አድርጎት ነበር፡፡ በእርግጥ መድሃኒቱ ከመድሃኒት ቤት የሚሸመተው ያለ ሐኪም የማዘዣ ወረቀት መሆኑም የተፈጠረውን ችግር የበለጠ እንዲባባስ አድርጎት ነበር፡፡ በጊዜው መድሃኒቱን ይወስዱ የነበሩትም ልክ እንደማስታገሻ ሆኖ ራሳቸውን ለማረጋጋት ነበር የሚጠቀሙበት፡፡ የመድሃኒቱ አምራች ደግሞ ካማ ግሩነንታል የተባለ አነስተኛ የጀርመን ኩባንያ ሲሆን ኩባንያውም ለመድሃኒት አምራችነቱ አዲስ መሆኑ፣ እንዲሁም ‹‹ነፍሰጡር ሴቶች ቢጠቀሙበት በእነሱም ሆነ በፅንሱ ላይ የሚያስከትለው ችግር አይኖርም›› ከሚለው ማስታወቂያ ጋራ መድሃኒቱ መሸጡ፣ እንዲሁም መድሃኒቱንም በ46 አገሮች ውስጥ መሸጡ የተከሰተውን ችግር ይበልጥ አስከፊና ውስብስብ አድርጎታል፡፡ መድሃኒቱ ገበያ ላይ የቆየበት ጊዜ ደግሞ ለ4 ወራት ብቻ ሲሆን ሀኪሞችም መድሃኒቱን ያዙት የነበረው በነፍሰጡር ሴቶች ላይ ለሚከሰተው የማቅለሽለሽና የማስመለስ ችግር እና የእንቅልፍ ማጣት ሕመም ነበር፡፡ ታዲያ በጊዜውም መድሃኒቱ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ተሽጦ ነበር፡፡

መድሃኒቱ ተፈብርኮ ለገበያ ከቀረበ 50 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ታዲያ ኩባንያው መድሃኒቱን አምርቶ ለገበያ አቅርቦ ያን ሁሉ ትርፍ ባጋበሰበት ወቅት ያስከተለውን አሰቃቂ ክስተት በተመለከተ ለተቀረው ዓለም ምንም ትንፍሽ ያለው ነገር አልነበረም፡፡ እንደሚባለው ከሆነ ከኩባንያው ሰራተኞች ውስጥ የአንድ ሰው ሚስት ጆሮ የሌለው ህፃን ልጅ የወለደች ቢሆንም ኩባንያው ግን ለዚህ ክስተት ምንም ቦታ አልሰጠውም ነበር፡፡ እናም ይህ በሆነ በ2 ዓመት ውስጥ ምስራቅ ጀርመን ውስጥ አንድ ሚሊዮን ሰዎች መድሃኒቱን በየዕለቱ ወስደውታል ተብሎ ይገመታል፡፡

ይሁን እንጂ እስከ 1959 ዓ.ም ድረስ የወጡ ሪፖርቶች እንዳመለከቱትም መድሃኒቱ መርዛማ ባህሪይ ነበረው፡፡ የበርካታ አዋቂዎችን የነርቭ ስርዓትን በመጉዳት ‹‹ፕሪፌራል ኒዩራይቲስ›› የሚባል ህመም እንዳስከተለባቸው ለማወቅ

አስችሎ ነበር፡፡ ታዲያ በዚያ ወቅት ግን ኩባንያው በመድሃኒቱ አማካኝነት

በበርካታ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያጋበሰ ነበር፡፡ ምንም እንኳ መድኃኒቱ እያስከተለ ያለው የጎን ጠንቅ ያላቆመ ቢሆንም ግን ዶክተሮችን በጉቦ እያባበለ ጉዳዩን በሚስጢር ለመጠበቅ ችሎ ነበር፡፡ ታዋቂ የህክምና መጽሔትም ጉዳዩን አስመልክቶ እውነቱን እንዳይዘግቡ የተለያዩ የአፈና ስራዎችን ይሰራ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1961 ላይ አንድ አውስትራሊያዊ ዶክተር ነበር

ታሊዶማይድ አካለ ጎደሎ ሆነው ከሚወለዱ ህፃናት ጋር ተያያዥነት እንዳለው ይፋ ያደረገው፡፡ በዚህ ወቅት እውነታው እየታወቀ እንኳን ኩባንያው መድሃኒቱን ከገበያ ለማውጣት አራት ወራት ያህል ፈጅቶበት ነበር፡፡ ታዲያ መድሃኒቱ በመጀመሪያ ለገበያ ቀርቦ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ከገበያ እስከወጣበት ድረስ 100 ሺህ ነፍሰጡር ሴቶች ይውጡት እንደነበር የታወቀ ሲሆን በዚህም ቢያንስ 90 ሺህ ያህል ሴቶች እንዲያስወርዱና

በህይወት ካልተወለዱት መካከል በሺዎች የሚቆጠሩት በተለያየ መልኩ አካል ጉዳተኛ ሆነው እንደተወለዱ ታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ በ1970 ኩባንያው ለጉዳተኞች 28 ሚሊዮን ዶላር በካሳ መልክ ለመክፈል ለመጀመሪያ ጊዜ ተስማማ፡፡ በገንዘብ አማካይነት ከተሰጠው ማካካሻ በዘለቀ ግን ጉዳተኞቹና ቤተሰቦቻቸው የሚገባቸውን ካሳ እና ይቅርታ ከኩባንያው ለማግኘት አምስት አስርት ዓመታትን መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ ምንም እንኳን ታሊዶማይድ በሺዎች በሚቆጠሩት ላይ ውርጃንና አካል ጉዳተኝነትን ያስከተለ መሆኑን የሚያመላክቱ ማስረጃዎች የነበሩ ቢሆንም እነዚህ አካል ጉዳተኞች ህይወታቸውን ሙሉ ለመንከባከብ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ግን የኪማ ግሩናንታል ኩባንያ አጥብቆ ሲያቅማማ ቆይቷል፡፡ ኩባንያው አሁንም ቢሆን በዚህ አቋሙ እንደገፋበት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ባልፈው ዓመት በፈረንጆች ነሐሴ ወር ላይ 31 የኩባንያው አዲሱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሔሮልጅ እስቶክ ከኩባንያው ዋና መስሪያ ቤቶች ፊት ለፊት የቆመውን የመዳብ ሐውልት በይፋ በከፈቱበት ወቅት የጉዳተኞቹን ቤተሰቦችና ጉዳተኞቹን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በወቅቱም ‹‹ባለፉት 50 ዓመታት ወቅት ሰብአዊነት ከሚሰማው ሰው ሊደረግ በሚገባው መልኩ ልንደርስላችሁ ባለመቻላችን ከልባችን ይቅርታ እንጠይቃለን›› የኩባንያውን የይቅርታ ድምጽ አሰምተዋል፡፡

ኩባንያው በጉያው ውስጥ ከታቀፈው ጥቁር ታሪክ ጎን ለጎንም ሌሎች አሳዛኝ ታሪኮችም ነበሩ፡፡ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንዳለቀ ወዲያውኑ በወንጀለኛነት ተጠርጥረው የሚፈለጉና ጅምላ ጨራሽ ምርመራቸውን በአስከፊዎቹ የሞት ካምፖች ውስጥ ያከናወኑ የናዚ ጀርመን ተመራማሪዎች በብዛት በኩባንያው ውስጥ መቀጠራቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ሳይንቲስቶች ውስጥ የተወሰኑት በታሊዶማይድ ምርመራና ዝግጅት ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ እነዚህ ሳይንቲስቶች በኩባንያው የተፈለጉበት ምክንያት ደግሞ በናዚ ጀርመን ዘመን ያከናወኑትን ኢሰብአዊ የምርምር ውጤት ለኩባንያው በምክር መልክ ለመስጠት ነበር፡፡ እነዚህ ተመራማሪዎች ምርመራቸውን ያካሄዱባቸው የሰዎች ማጎሪያ ካምፖች ደግሞ የሰው ልጅ ህይወት አለቅጥ የረከሰበትና ይህም ሳይንቲስቶችን ለሰው ልጅ ስቃይ ደንታ ቢስ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ጊዜ ነበር፡፡ ታዲያ ታሊዶማይድ የተባለው አሰቃቂ መድሃኒትም ተሰራ ተብሎ የሚታሰበው በነዚህ የማጎሪያ ጣቢያዎችና በነዚህ አስገራሚ ሳይንቲስቶች አማካይነት ነበር፡፡

ስፍራው ሰቶልዘርግ ይባላል፡፡ በከተማው ውስጥ አጀብ ብለው የተገነቡ የሚያማምሩ ህንፃዎች አሉ፡፡ የከተማው ሐብት በአብዛኛው የተገኘውም የቨርትዝ ቤተሰብ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ያፈራው ሐብት ነው፡፡ የቨርትዝ ቤተሰብ አክራሪ

የሚባል የካቶሊክ እምነት ተከታይ ሲሆን ለበርካታ አስርት ዓመታት ያህልም የከተማዋ ማህበረሰብ ማገርና ምሰሶ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህ ባለፀጋ ቤተሰብ በእርግጥ በዛ ባሉ የምግባረ ሰናይ ስራዎች ላይ ተሳትፎ የሚያደርግ ሲሆን ከነዚህም መካከል በከተማዋ ማዕከል ላይ ቆመውና በቻርልማን አማካይነት የተገነባው የኢምፔሪያል ካቴድራል ያሰራው አዲስ ጣሪያ ይገኝበታል፡፡ ቻርልማን በ8ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓን ቅኝ ለመግዛት የቻለ ጀግና ነበር፡፡

ይህ ኩባንያ በአሁኑ ወቅት የመድሃኒት ምርቱ አለማቀፍ ስጭት ያለው ሲሆን በ26 አገራት ውስጥም ቅርንጫፎች አሉት፡፡ በመላው ዓለምና 4,200 ያህል ሰዎችን ቀጥሮ የሚያሰራ ሲሆን ዓመታዊ ሽያጩም እስከ 1.3 ቢሊዮን ይደርሳል፣ ገቢውን በአብዛኛው የሚያገኘው ደግሞ ከህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ነው፡፡ በከተማዋ ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ መካከል አብዛኛው ህይወቱ ከኩባንያው ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የተወሰኑት ሠራተኞችም ለበርካታ ዓመታት ያህል በኩባንያው ውስጥ የሰሩ ናቸው፡፡ ታዲያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በባርያነት በኩባንያው ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ ህፃናት ወንዶችና ሴቶች ስለኩባንያው ያለፈ ታሪክ ምንም ነገር

ትንፍሽ ሳይሉ ለመቆየት ነበር የፈለጉት፡፡ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በተቀሰቀሰበት በ1939 ላይ

ኩባንያ በኸርማን ዊርዝ አማካይነት መተዳደር ጀመረ፡፡ አልፍሬድ የሚባለው መንትያ ወንድሙም መሃንዲስ ሲሆን የናዚ ፓርቲ አባል ነበር፡፡ ሒትለር አይሁድን ከንግዱ ዓለም ሲያባርርም ሁለት የአይሁድ ኩባንያዎችን በእጁ ውስጥ ለማስገባት ችሎ ነበር፡፡ ከእነዚህ ሁለት ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ደግሞ እስካሁን ድረስ ለገበያ እየቀረበ ያለው ታባክ የሚባለውን መድሃኒት ይጨምራል፡፡

እንደ ብዙዎቹ እምነት ከሆነ ከታሊዶማይድ በስተጀርባ ያለው የስነ ኬሚካል ባለሙያ ፕሮፌሰር ቨርነት ቩልማን ሳይሆን አይቀርም ይባላል፡፡ ይህ ሳይንቲስት የመጀመሪያውን ሰው ሰራሽ ፀረ ወባ መድሃኒትን ያዘጋጀና መድሃኒቱንም በሰዎች ላይ የሞከረ ሳይንቲስት ነበር፡፡ ሙከራውንም በሆስፒታሎችና በካምፖች ውስጥ አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ ታሊዶማይድ ያለውን ተያያዥነት በተመለከተ በርካታ መረጃዎች በየጊዜው እየወጡ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን የኩባንያው ስራ አስኪያጅ በቅርቡ የሰጡት ይቅርታ በቂ እንዳልሆነ ነው፡፡

ከመጠን ያለፈ ውፍረት በአካል እንቅስቃሴና በምግብ መስተካከል አልመለስ ሲል መድሃኒት ከመጠቀም ይልቅ በአካል እንቅስቃሴውና በምግብ መመጠኑ ሳይሰለቹ መቀጠሉ ጠቃሚ መሆኑ ተነገረ፡፡

በረጅም የጊዜ ሂደትም ሆነ በተለያዩ የጤና እክሎች ከመጠን በላይ ወፍረው በስፖርታዊ እንቅስቃሴና በምግብ መመጣጠን ብቻ በቀላሉ የማይመለሱ ውፍረቶች እንዳሉና የእነዚህም አይነት ውፍረቶች መንስኤ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል የባላንስ ሄልዝ፣ የኒውተሪሽን እና ዳይቴቲክስ አማካሪዋና የስነ ምግብ ባለሙያዋ ዶ/ር መአዛ ደበበ ገልፀዋል፡፡

እንዲህ አይነት ከመስመር ያለፉ ውፍረቶች በአካላዊ እንቅስቃሴና ምግብን በማስተካል መመለስ ካልቻሉ ቀድሞ ምክንያታቸው መፈለግ እንዳለበት የጠቀሱት ባለሙያዋ ውፍረት ከልክ ሲያልፍ ሰውየው አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግም ሆነ ምግብን ለማመጣጠን ስለሚቸገር በሁለቱ መንገዶች ላይስተካከል እንደሚችል አብራርተዋል፡፡ ውፍረት ከልክ አልፎ አልመለስ ከሚልባቸው ምክንያቶች መካከል የሰውነታችን አንዳንድ ክፍሎች በተለያዩ ምክንያቶች መታወክ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚኖሩ ሆርሞኖች በትክክል አለመሰራጨት፣ ከአዕምሯችን የሚመነጩ ሆርሞኖች በትክክልና በትክክለኛው መጠን አለመስራት፣ በካንሰርና በተለያዩ ህመሞች ምክንያት ሰውነታችን ውስጥ ያሉ እጢዎች ሲታወኩ የሚሰራው ንጥረ ነገር ሊያንስም ሊበዛም በሚችልበት ጊዜ እነርሱ የሰውነታችንን ሂደት የሚቆጣጠሩ ስለሆኑ በሚታወኩበት ወቅት የሰውነታችንን ስብ የማቃጠል ኃይል፣ የማደግና የመጠገን ሃይሉ፣ የጮማ መጠራቀምን የሚቆጣጠሩ ሆርሞኖች ሊታወኩ እንደሚችሉ የሚያብራሩት ዶክተሯ በእነዚህ የሚመጣውን ከፍተኛ የውፍረት መጠን የምግብ መስተካከልና አካላዊ እንቅስቃሴ ሊያስተካክለው እንደሚችል ያብራራሉ፡፡

የችግሩ መፍትሄ ምን ይሆን? ዶ/ር መአዛ እንደሚሉት በዋናነት የችግሩን መንስኤ ፈልጎ

ማግኘት ለሚወሰደው የህክምና እርምጃ ወሳኝ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ ‹‹የችግሩ ምክንያት ከተለየ በኋላ እንደየችግሩ ደረጃ ቀዶ ህክምናም ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ ከውጭ በሚተኩ ሆርሞኖችም ችግሩ ሊፈታ ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግ መንስኤው ይወስነዋል›› ብለዋል ባለሙያዋ፡፡

ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንደ ስኳር፣ ደም ግፊትና የልብ ህመምን ሊያስከትል በመቻሉ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለማይችሉ ሰዎች የመድሃኒት እገዛ እንደሚደረግላቸው ያብራሩት የስነ ምግብ አማካሪዋ ይህን መድሃኒት ሁለት አይነት መልክ እንዳለውም አብራርተዋል፡፡ ‹‹በእርግጥ መድሃኒቶቹ በሐኪም ለተፈቀደላቸውና ውፍረታቸው ከልክ አልፎ መመለስ ስላልተቻለ እና በአስጊ ሁኔታ ላይ ላሉ እንጂ ገና ለገና ውፍረት

አለና ይታዘዝልኝ ማለት አይቻልም›› ይላሉ ዶ/ር መአዛ፡፡

የመድሃኒቶቹ አይነት ከላይ እንደተገለፀው የውፍረታቸው መጠን አስጊ የሆኑ

ሰዎች ውፍረታቸው መቀነስ እንዲጀምር ሁለት አይነት መድሃኒቶች ይወስዳሉ፡፡ አንደኛው ከምግብ ጋር ተወስዶ በአንጀታችን ውስጥ ስራውን የሚያከናውን ሲሆን የዚህ መድሃኒት ዋነኛ ስራ ከምግብ የሚገኘውን ቅባት ሰውነታችን እንዳይጠቀመው ማድረግ ነው፡፡ ይህም ቅባት ሰውነታችን ሳይጠቀመው ተመልሶ ይወጣል፤ እንደባለሙያዋ ገለፃ፡፡ ይህ መድሃኒት ‹‹ኦርሌስታት›› ወይም ‹‹ዘንካል›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህ መድሃኒት በሐኪም ክትትል፤ ምግብን እያስተካከለ አካላዊ እንቅስቃሴን እየሞከረ የሚወስደው ከሆነ በዓመት ውስጥ እስከ 12 ኪሎ ግራም ክብደት ሊቀንስ ይችላል፡፡

ይሁን እንጂ ከሐኪም ክትትል ውጭ በዘፈቀደ የሚወሰድ ከሆነ፣ የምግብ መስተካከልና አካላዊ እንቅስቃሴ የማይታከልበት ከሆነ መድሃኒቱ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለውም ባለሙያዋ በአፅንኦት ይናገራሉ፡፡ ‹‹ከጎንዮሽ ጉዳቶቹ ውስጥ ከቅባቱ ጋር አብረው በሚወጡ ንጥረ ነገሮች እጥረት መጎዳት፣ የሆድ መታወክ፣ ተቅማጥ፣ የጋዝ (ፈስ) መብዛት እና ባስ ሲልም ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል ሊያስከትል ይችላል›› ይላሉ ዶ/ር መአዛ፡፡

ሁለተኛው የመድሃኒት አይነት የምግብ ፍላጎታቸውን ለመቀነስ የሚያግዝ እንደሆነ ዶክተሯ ገልፀው ይህ መድሃኒት በአንጎላችን ውስጥ የሚፈጠሩ ፈሳሾችና ሆርሞኖች የምግብ ፍላጎታችን የሚፈጠረውን ሆርሞን በማስተካከልና በመቀነስ ስራውን ያከናውናል፡፡ ይህ መድሃኒት አብዛኛውን ጊዜ የመንፈስ ጭንቀት ላላቸው ሰዎች የሚሰጥ ነው፡፡ መድሃኒቱ የምግብ ፍላጎትን በመቀነስ ሰውነት ያለውን ሃይል እንዲጠቀም ጉልበት ይሆነዋል፡፡

‹‹ይህም መድሃኒት ‹ፌንትራሚን› የሚባል ሲሆን

ኢፌድሪን የሚባል በጉንፋን መድሃኒት የሚገኝ አይነት ኬሚካል ይዘት ያለውም ነው፡፡ መድሃኒቱ እንደ ኦርሌስታት ሁሉ በሐኪም ክብደታቸው አስጊ ነው ለተባሉ ሰዎች የሚሰጥ ሲሆን ጥቅም ላይ የሚውለውም በሐኪሞች ክትትል እንደሆነ ዶ/ር መአዛ አስታውሰው አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ የራሱ የሆነ

የጎን ጉዳት እንዳለው ያሳስባሉ፡፡ ከሚያስከትላቸው የጎን ጉዳቶች የልብ ህመም፣ የደም ብዛትን ከፍ ማድረግና የሰውነት መንቀጥቀጥን ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡

ሁለቱንም አይነት መድሃኒቶች ምንም አስጊ ውፍረት ቢኖርባቸው እርጉዝ ሴትና ከ16 ዓመት

በታች ያሉ ልጆች በፍፁም እንዳይጠቀሙት ማስጠንቀቂያ

ይሰጣል የሚሉት ባለሙያዋ ሁሉም በሐኪም ክትትል

ስለሚወሰድ ከላይ ለተጠቀሱት የህብረተሰብ ክፍሎች አስጊ አይደለም

ብለዋል፡፡ ይህ አይነት ውፍረት

አሳሳቢ በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የተለያዩ ምርምሮች እየተደረጉ እንደሆኑ

የጠቆሙት ባለሙያዋ እስከዛሬም ተመርተው

ከጥቅማቸው ጉዳታቸው በማየሉ ከጥቅም ውጭ ሆነው ከገበያ እንዲጠፉ የሆኑ መድሃኒቶች

እንዳሉም ገልፀው ለጊዜው ግን ከላይ የተገለፁት ብቻ በጥቅም ላይ

እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

ከመጠን ላለፈ ውፍረት ማስተካከያ የሚሆኑ

ምግቦች ይኖሩ ይሆን? ከመጠን ላለፈ ውፍረት ማስተካከያ ተብለው በመድሃኒት መልክ የሚዘጋጁ ምግቦች ይኖሩ እንደሆነ ለባለሞያዋ ጥያቄ አቅርበንላቸው ሲመልሱ ‹‹እርግጥ

ገበያ ውስጥ አይጠፉም በተለይ ያከሳል ያስተካክላል እየተባለ በየሱፐር ማርኬቱ የሚሸጥ ምግብ ይኖራል፡፡ ይህ ግን በሳይንስ የተደገፈ አይደለም›› የሚሉት ባለሙያዋ ውፍረት በምግብ መስተካከል ካለበት በትክክለኛው መንገድ ከቫይታሚኑም፣

ከሚኒራሉም፣ ከፕሮቲኑም ሆነ ከካርቦሃድሬቱ ተመጣጥኖ መወሰድ መቻል አለበት ይላሉ፡፡ ‹‹እርግጥ ምግብ ውፍረትን ለመቀነስ ብቻ በሚለው መልኩ መታየት የለበትም ምግብ የሚያጠግበን፣ ሰላም እንዲሰማን የሚያደርግና ማህበራዊ ትስስርንም የሚያጠብቅ ነው፡፡ ስለዚህ በመድሃኒት መልክ የተሰራ አለ ለማለት እቸገራለሁ›› ያሉት ዶክተሯ በእርግጥ የምግብ ምትክ የሚባል ሁሉም አይነት ንጥረ ነገር ያለውና ‹ስሊም ፋስት› ተብሎ የሚጠራ ተበጥብጦ የሚጠጣ ነገር አለ፡፡ ይህ የምግብ ምትክ ለቸኮለ፣ በስራ ለሚወጠር ሰው ጥሩ ነው፡፡ ውፍረታቸው ከፍተኛ ለሆነም መቀነስ ያስጀምራቸዋል›› የሚሉት ባለሙያዋ ሁሉንም ይዘት ከያዘ መጠኑን ቀንሶ ትክክለኛውን ምግብ መመገብ የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ፡፡

ከላይ የተገለፁት መድሃኒቶች በሀገራችን ጥቅም ላይ ውለዋል?

‹‹እነዚህ መድሃኒቶች በአገራችን ጥቅም ላይ ውለዋል ለማለት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስመጣቸው ይኑር አይኑር መረጃ የለኝም፡፡ እርግጥ በውጭው ዓለም የማይቀንስ ውፍረት አሳሳቢ ስለሆነ የቅባት መቀነሻው መድሃኒት በተወሰነ መጠን በየመድሃኒት ቤቱ ይሸጣል፡፡ ግን መጠኑ ዝቅተኛ እንደሆነ ዶ/ር መአዛ ይናገራሉ፡፡ በዋናነት አፅንኦት የሰጡት ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት መድሃኒቶች ውፍረትን መቀነስ እንዲያስጀምሩ ከጥቂት ሳምንታት ግፋቢል እስከ ሶስት ወራት ብቻ የሚወሰዱ እንጂ በዘላቂነት የሚጠቅሙ በመሆናቸው አዋጪ አለመሆናቸውን ገልፀው ሁሉም ሰው አመጋገቡን ማስተካከሉንና አካላዊ እንቅስቃሴውን ጠበቅ ማድረግ እንዳለበት ያሰምሩበታል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ውፍረት መቀነስ ካላሳየ አሁንም ምክንያቱን መፈለግ አለበት ይላሉ ባለሙያዋ፡፡

በሀገራችን ችግሩ ምን ያህሉ አሳሳቢ ነው ‹‹እርግጥ ሁሉንም አግኝቻለሁ ባልልም ከልክ አልፎ

አልቀንስ ያለ ውፍረት እስካሁን አላጋጠመኝም›› ያሉት ባለሙያዋ እስካሁን ከውፍረት ጋር በተገናኘ ያማከሯቸው ሰዎች ምክሩን መሰረት በማድረግ በወሰዷቸው እርምጃዎች መሻሻልን እያመጡ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ በሀገራችን ያለው ውፍረት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር ቢያሳይም ከመጠን ያለፈና አልመለስ ያለ ውፍረት ችግር በሀገራችን በምን ደረጃ ላይ እንደሚኝ ለመናገር ጥናት ያስፈልጋል ባይ ናቸው ዶክተሯ፡፡ በመጨረሻም ‹‹ውፍረት ያስጨነቃቸው ሰዎች ይህን ጉዳይ ሲያነቡ ከውጭ ይምጣልን ሊሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ማተኮር ያለብን ‹ውፍረት ይቀንሳሉ› የሚለው ላይ ብቻ ሳይሆን ምን ያስከትላሉ ጥቅም ላይ የዋሉት በየትኛው አገርና ጊዜ ነው የሚለውም መጤን አለበት›› ሲሉ ያሳስባሉ፡፡ ከዚያ ይልቅ ማንኛውም ሰው ከአካላዊ (ክብደት... ወደ ገጽ 11 የዞረ)

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

በቋንቋ የተነሳ የኮምፒውተር ፈተናውን ማለፍ ተስኖዎታል? በዚህ የተነሳ መኪና መንዳት አልቻሉም? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር

አለ፤ አስተምረን ወስደን እናስፈትንዎታለን።

ልብ ይበሉ የእርስዎን ቋንቋ እንናገራለን

2400 Minnehaha Avenue #204 Minneapolis, MN 55404 (612) 275-0970

በተጨማሪም የትርጉም ድርጅታችን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲኖርብዎ ወይም በማንኛውም ሰዓት የትርጉም ሥራ

ሲያስፈልግዎ ክፍት ነው።

አዘጋጅ፦

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

‹‹በአባቴ የሐሞት ከረጢት ውስጥ ከ100 በላይ ጠጠር ተገኘ መባሉ እኔንም አሳስቦኛል፤ ለመሆኑ የሐሞት ጠጠር በዘር ይተላለፍ ይሆን?››

አለምሰገድ ‹‹የሐሞት ከረጢቴ በቀዶ ህክምና ተቆርጦ ከወጣ በኋላ የጨጓራ

በሽታ አስቸግሮኛል፤ የሐሞት ጠጠርና ጨጓራ ግንኙነት ይኖራቸው ይሆን?››

ሰለሞን ‹‹የሐሞት ጠጠር አለብህ ተብያለሁ፡፡ እኔ የእህል ዘር እንጂ

ጠጠር ተመጋቢ አይደለሁም፡፡ መቼ የዋጥኩትን ጠጠር ነው አለብህ የተባልኩት?››

አቶ አላምረው በሐሞት ጠጠር ችግር ምንነት፣ መንስኤና መፍትሄዎች

እንዲሁም ከጨጓራ በሽታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ በደብዳቤና በስልክ ከተለያዩ አንባቢዎች እነዚህን መሰል ጥያቄዎች ደርሰውናል፡፡ ጥያቄዎቻችሁን በመያዝ አንድ የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአንጀት፣ የጨጓራና የጉበት ስፔሻሊስት ሐኪም አነጋግረንላችኋል፡፡

የእህል ውጤቶች ተመጋቢ ነኝ፡፡ ነገር ግን የሐሞት ጠጠር አለብህ ተብያለሁ፡፡ ለመሆኑ መቼ የዋጥኩት ጠጠር ነው? እንዴት ነው የሐሞት ጠጠር የሚከሰተው? ብሎ ለጠየቀን አንባቢያችን ምላሽ ቢሰጡልን?

ዶ/ር ፡- የሐሞት ጠጠር ሲባል በሐሞት ውስጥ የሚፈጠር ጠጠር ማለት ነው፡፡ በሰውነታችን የአሰራር (ሜታቦሊዝም) ሂደት ውስጥ ከሚከሰቱ ጉዳዮች አንዱ የሐሞት ጠጠር (ክሪስታልስ) ነው፡፡ የሚፈጠሩት ጠጠሮች ኮሌስትሮልና ፒግመንትድ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ አፈጣጠሩ መጀመሪያ በሐሞት ከረጢት ውስጥ ከጭቃ መሰልነት ጀምሮ ቀስ በቀስ ወደ ጠጠርነት የሚለወጥ ነገር ይፈጠራል፡፡ የሐሞት ከረጢት በጉበት ተመርቶ የሚመጣውን ሐሞት ከማከማቸት ባሻገር የሐሞት ፈሳሽ ለመደበኛ ተግባሩ ዝግጁ እንዲሆን የማድረግ ስራንም ያከናውናል፡፡

በሐሞት ከረጢት ውስጥ የሚፈጠረው ጠጠር በአንድ በኩል ዝም ብሎ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አልያም ደግሞ ቅባታማ ምግቦችን በምንምገበብበት ጊዜ የተመገብነውን ምግብ ለመፍጨት ሲል ሐሞት ይረጫል፡፡ በዚህ ሒደት ጠጠር ካለ የህመም ስሜት ሊሰማን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ ጠጠር በሐሞት መፍሰሻ ቀጭን ቱቦ ውስጥ በመግባት ቱቦውን ሊዘጋው ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት ይሰማናል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ጠጠሩ ቢኖርም ህመም ሳይፈጠር ዝም ብሎ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ የተፈጠረው ጠጠር ከቀላል እስከ ሐሞት መፍሰሻ ቱቦ መዘጋት የሚደርስ ህመም ሊያስከትል ይችላል፡፡

ለሐሞት ጠጠር አጋላጭ ተብለው የሚጠቀሱ ሁኔታዎችስ ይኖሩ ይሆን?

ዶ/ር ፡- እስካሁን የጤና ሳይንሱ በደረሰበት የእድገት ደረጃ የሐሞት ጠጠር በዚህና በዚህ ብቻ ይከሰታል የሚል መደምደሚያ ላይ አልደረሰም፡፡ ነገር ግን ጠጠሩ እንዲፈጠር አልያም እንዲባባስ የሚያደርጉ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከነዚህ ምክንያቶች ውስጥ የሐሞት የምርት መጠን ከሚፈለገው በላይ መሆን፣ በደም ውስጥ የቅባት መጠን መጨመር፣ የሐሞት ከረጢት የሚያመርተው ልፋጭ መብዛት፣ ኢንፌክሽን፣ ሴት መሆን፣ ውፍረትና ቅባታማ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ለሐሞት ጠጠር ችግር ከሚያጋልጡ ጉዳዮች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ የተፈጠረው ጠጠር አደገኛ የሚሆነው የህመም ስሜት ሲፈጥር፣ የሐሞት መፍሰሻ ቱቦን ሲዘጋ፣ በቱቦው መዝጋት ሳቢያ ሐሞቱ ወደ ኋላ በመመለስ የጉበት ሴሎችን ሲመርዝና የጉበት መድከም (ስራ ማቆምን) ሲያስከትል ነው፡፡

አቶ አለምሰገድ ይባላሉ፡፡ ሰሞኑን በፃፉልን ደብዳቤ

እንደገለፁት አባታቸው በጠና ይታመማሉ፡፡ ህክምና ሲያደርጉ የሐሞት ጠጠር እንዳለባቸው ይነገራቸዋል፡፡ በተደረገላቸው ቀዶ ህክምና ከ100 በላይ የሐሞት ጠጠር ይወጣላቸዋል፡፡ በአባታቸው የጤና ጉዳይ ሳቢያ አቶ አለምሰገድ ምናልባት የሐሞት ጠጠር በዘር የመተላለፍ አጋጣሚ ካለው የእኔስ እጣፈንታ ምን ይሆናል? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ለመሆኑ የሐሞት ጠጠር በዘር የመተላለፍ እድል አለው?

ዶ/ር ፡- በእርግጥ ጠያቂው እንዳሉት የሚፈጠረው የጠጠር መጠን ከሰው ሰው የተለያየ ነው፡፡ አንድ ብቻ ትልቅ ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላም በኩል ጭቃ መሰል ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ 100 እና 200 የሚደርሱ ከፍ ከፍ ያሉ ክርስቲያል ጠጠሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለመቆጠር የሚያዳገቱ አሸዋማ መሰል ጠጠሮችም የሚፈጠሩበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ ጠጠሩ ትልቅ ስለሆነ ይጎዳል፤ ትንሽ ስለሆነች ደግሞ አትጎዳም ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ይሆናል፡፡

የሐሞት ጠጠር ችግር ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ እድል የለውም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጥናቶች ከዘር ጋር የመያያዝ ሁኔታ እንዳለው ይገልፃሉ፡፡ በዘር ሲባል

ከአባት (ከእናት) ወደ ልጅ በቀጥታ ማለት ሳይሆን በተጥሮ ወፍራም ሐሞት ባላቸው ቤተሰቦች ውስጥ የሐሞት ጠጠር በተደጋጋሚ የሚታይበት አጋጣሚ አለ፡፡ ስለዚህ የሐሞት ጠጠርን በዘር የመውረስ ሁኔታ ዜሮ ሳይሆን በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን

አጋጣሚው ይኖራል፡፡ ሰሞኑን በሐሞት ጠጠር ዙሪያ አንዳንድ ፅሑፎችን ሳነብ

ያገኘሁት መረጃ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በሐሞት ጠጠር ችግር የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው ይላል፡፡ መረጃው እውነትነት አለው ይሆን?

ዶ/ር ፡- ትክክለኛ መረጃ ነው፡፡ ለሐሞት ጠጠር ተጋላጭነት ይጨምረዋል፡፡ በተለይም ወፍራም የሆኑ፣ አዘውትሮ የሆድ ህመም ያለበቸው፣ የሆድ መነፋት በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸው፣ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ እና የወለዱ ሴቶች በተለየ ሁኔታ ለሐሞት ጠጠር ችጥ የተጋለጡ ናቸው፡፡

ወ/ሮ አለምፀሐይ ይባላሉ፡፡ ባለትዳርና የ3 ልጆች እናት ናቸው፡፡ የ42 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ናቸው፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት በሐሞት ጠጠር ሳቢያ የሆስፒታል አልጋ ይዞ እስከ መተኛት የደረሰ የጤና ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡ እሳቸው እንደሚሉት የሐሞት ጠጠሩን ሳያውቁት ለብዙ ጊዜ በመቆየቱ የሐሞት ጠጠሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰ ኢንፌክሽን ተጠቅቷል ተብለው በቀዶ ህክምና ተቆርጦ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ የጠጠሩ ችግር ቢወገድም የሀሞት ቀረጢቱ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ በጨጓራ በሽታ ተቸግረዋል፡፡ ምግብ ሲመገቡ ስለሚያቃጥላቸው አለመብላትን ይመርጣሉ፡፡ በቂ ምግብ ባለመመገባቸው ደግሞ ከዕለት ወደ ዕለት የሰውነታቸው ክብደት

እየቀነሰ ነው፡፡ በጨጓራ ህመሙ የተነሳ እሳቸውም ሆነ ቤተሰባቸው በስጋትና በጭንቀት ውስጥ ናቸው፡፡ ለመሆኑ የሐሞት ጠጠር እና የጨጓራ በሽታ ያላቸው ግንኙነት ምንድን ነው? የትኛው በሽታ ለየትኛው መንስኤ የመሆን ዕድል አለው? ዶ/ር ፡- የወ/ሮ አለምፀሐይ የጤና ሁኔታም ሆነ የቤተሰባቸው ችግር እንደሰው ማንንም ያስጨንቃል፡፡ ያሳዝናልም፡፡ ግን ደግሞ ጠያቂዋም ሆነ በተመሳሳይ የጤና ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች የሐሞት ቀረጢት በቀዶ ህክምና ከወጣ በኋላ ከሚከሰቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች (ችግሮች) አንዱና ዋነኛው የጨጓራ ህመም መሆኑን መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄን ልናስቀረው አንችልም፡፡ የሐሞት ቀረጢትና ጨጓራ በተጥሮአዊ አፈጣጠር የሚጋሩት የነርቭ ስርዓት አላቸው፡፡ ይሄም ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ሰዎች የቀኝ ትከሻ (የጀርባ) ህመም ተሰምቷቸው መጥተው የሐሞት ጠጠር የሚገኝባቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህ የሚሆነው የነርቭ ስርዓታችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የስሜት መወራረስን የሚያስከትሉ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የሐሞት

ቀረጢትና ጨጓራ የሚጋሩት የነርቭ ስርዓት ሰለባ አንዳንድ ጊዜ የሐሞት ጠጠር የጨጓራን የህመም ስሜት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ከህመም ስሜት በዘለለ የሐሞት ጠጠር የጨጓራን፣ ጨጓራም የሐሞት ጠጠር በሽታን የማምጣት ዕድል የላቸውም፡፡ የጨጓራ በሽታ ያለበት ሰው የሐሞት ጠጠር ይኖርብኝ ይሆን ብሎ ቢጠረጥር ተገቢነት አይኖረውም? ዶ/ር ፡- ቀደም ብሎ እንደገለፅኩት የሀሞት ቀረጢትና ጨጓራ በአፈጣጠር ምክንያት የሚጋሩት ነርቭ አለ፡፡ በዚህም ሳቢያ የሐሞት ጠጠር በሚፈጠርበት ወቅት ጨጓራ አካባቢ ህመም ስሜቶች መፈጠራቸው አይቀርም፡፡ ከዚህ በመነሳትም ማንኛውም የጨጓራ ህመም ያለበት ሰው የሐሞት ጠጠርን በመጠርጠር ምርመራ ቢያደርግ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ የሐሞት ጠጠር ሲከሰት ከሚስተዋሉ ህመም ነክ ምልክቶች በቀዳሚነት የሚጠቀሱት የትኞቹ ናቸው? ዶ/ር ፡- በቀኝ ሳንባ መጨረሻና ጉበት ያለበት

አካባቢ የህመምና የማሳከክ ስሜት ይኖራል - የመደንዘዝ ስሜት ይኖራል፤ - የአይን ቢጫ መሆን - የሰገራ መንጣት እና ተቅማጥ ይከሰታል፡፡ እነዚህን ዝም ብዬ ጠቀስኩ (ሐሞት... ወደ ገጽ 18 የዞረ)

ምንቀረሽ ኢትዮጵያ አካልሽ፡ ተቆረሠ፣ ወርድ ቁመትሽ አነሠ፣ በውስጥሽ እራብ እርዛት ነገሠ። እንዳትገቢ ወጥተሽ፣ እንዳይዘረጋ እጅ እግርሽ፣ ዙሪያውን በር ዘጉብሽ። ልጆችሽ ከምር ተገፍተው ቢሰደዱ፣ አልቀናቸውም መንገዱ፣ በእየሄዱበት ተዋረዱ።

መጠጊያ አጡና መድረሻ፣ ማጠብ ቢሄዱ ያረብ ቅርሻ፣ ከፎቅ ተወረወሩ እንደመናምንቴ ቆሻሻ። አድባራትና ገዳማትሽ ተደፈሩ፣ መሰጅዶችሽ ተወረሩ፣ ልጆችሽ በማንነታቸው አፈሩ። የጀግኖችሽ መታሰቢያዎች ፈረሱ፣ ኒሻን መዳሊያዎችሽ ተወረሱ፣ ታሪካዊ እሴትችሽ ለተተኪው እነዳይደረሱ።

ምንቀረሽ እንግዴህ ሃገሪ፣ የሚተላለፍ ለነገ ከዛሪ፣ ለነበር እንኳ ለወሪ። ቆመን እያየን ሁሉም ጠፋ፣ ጭላንጭል ሳይተው ለተሰፋ፣ አለ የሚባል የታሪክ አንጋፋ። ልጆችሽ አብረው እንዳይውሉ፣ ያገኙትን ተካፍለው እንዳይበሉ፣ በዘር በሀይማኖት ተከፋፈሉ። እየው ቆመዋል ለእየ ብቻቸው፣ አንድነት ጠፍቷል በመካከላቸው፣ ኢትዮጵያ እስኪቢሰሙሽ ተማጸኛቸው።

ተስፋ አንድ ሰው ቢጐድለን..

...አሥር እንቀራለን ኢትዮዽያውያን ነን

...መች ተስፋ እንቆርጣለን?!? የፈለገው ይምጣ.. እጅ እኮ አንሰጥም አረንጉዋዴ ቢጫ..

ቀዩ ሰንደቃችን ከቶ አይለወጥም እናሸንፋለን...

መቼም ተስፋ አንቆርጥም!!! ከፋሲል ተካልኝ አደሬ

ልባም ሲሉ እየሰማሁ በጣም ይገርመኛል በደል ተንተርሶ ህዝባችን ተኝቷል

ልሂቃን ነን ያሉም መርጠዋል ዝምታን አይነሳም ብለው ምድር ሰማይ ቢሆን። ተዉ እባካችሁ! ዝም አይነቅዝም ይቅር

መማር ያስፈልጋል ከተፈጥሮ ኩነት አምሳያ ቁምነገር

ስታነቃንቀው የረጋውን ኩሬ ከመሃል እስከዳር ተስፈንጥራ ገብታ አንዲት ትንሽ ጠጠር።

ዋለልኝ እግዜር ኅዳር 28 ቀን 2005 ዓ.ም. - ዋሺንግቶን ዲ.ሲ.

የማለዳዋ ልጃገረድ ኃያል ነው ጸዳልሽ

በላዬ ስትፈሺ ጋረደኝ ብርሃንሽ ላፍታ እንዳላይሽ ዝናብ አለምኩልሽ ታጥቦ ቢወገድልሽ የቀናተኞች ቅናት በረዶ አለምኩልሽ ንዳድሽ ቀዝቅዞ ቢወገድ ህማምሽ

እንዳልሆን አጠገብሽ ትፈጂኝ አንድደሽ ደሞ እንዳርቅሽ

ይወርሰኝ ፅልመትሽ ይጠዝጥዘኝ በረዶሽ

የማለዳ ጮራዬ ሁሌ ምሽት አንቺን መጠበቅ ማሰቡ

እንደ ማራኪ ስዕል ምንኛ ደስ ይላል ልቤ ተንጠልጥሎ ጨረቃ ጣራ ላይ ሰው ጠይቃለሁ ፀሐዬን ያያችሁ ንገሩኝ እላለሁ ተስፋ አረጋለሁ ይነግሩኛል ብዬ

አላቸው እነሱም የራሳቸው ጸሐዬ በጥቅጥቁ ደመና ላይ መራመድ ብችል

ጽልመት በወረሰው ዙሪያውን ፀሐዬን አያታለሁ

ምንም እንደማይጋርዳት አውቃለሁ፡፡ ከዳዊት ወርቁ

እንጀራ አለ ይላሉ ተስፋ በሰለጠኑት ሀገር

ርቆ የተሰቀለ ዳቦ ይሉት ነገር ደሀው ካገር ወጣ ሊያገኛት ተሰዶ

አልገባውም እንጂ እሱ ነው የዳቦው ማብሰያው ማገዶው

ከካስስንድ (ከካሳሁን ተሾመ ቦጋለ)

የከንፈርሽ ፊርማ (Signature of Your Lips)

የከንፈርሽ ፊርማ ከንፈሬ ላይ አርፎ ገላሽ ከገላዬ ሲደንስ ተቃቅፎ

ልብሽ ከልቤ ጋር ገነት ገባ ከንፎ ሲቃሽ ጆሮዬ ውስጥ እንደ ዜማ ጦፎ

*** Singnature of your lips

lands on mine As our bodies dance

Our hearts fly to heaven Your ‘aah’ melody in my ears

ከኤልያስ ሙሉኪሮስ

በፒያሳ ገበያ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል አንዳንዶቹን እናስታውሳችሁ

ታዋቂው የኢንሹራንስ ባለሙያ ኤፍሬም በጥሩ ዋጋ ጥሩ የኢንሹራንስ ከለላ ለመኪናዎ፣ ለቤትዎና ከፈለጉም ለጤናዎ ያስገኝልዎታል

በቦሌ ሃዋላ እና በመኒ ግራም በመጠቀም ወደ ሃገር ቤት

ገንዘብዎን በፍጥነት እናደርሳለን

የበግ፣ የበሬና የዶሮ ሥጋ አለን፤ ለቁርጥ የሚሆነውን ጊርጊሮ ሥጋችንንም

ይጠይቁን

በፒያሳ ገበያ፡ ቅመማ ቅመማ ቅመሞች፣ ጤፍ፣ ጀበና፣ ሲኒ፣ የሃገር ባህል

አልባሳት፣ ወርቅ፣ ሻንጣዎች፣ የስልክ ካርዶች፣ አዳዲስ ሙዚቃዎችና ቪዲዮዎች

ሁሉም አሉን።

ኬተሪንግ ጀምረናል

የሐሞት ጠጠርን ለመከላከል መደረግ የሚገባቸውና የማይገባቸው ጉዳዮች

- ለሐሞት ጠጠር ችግር የመጋለጥ እድልና የሚያፋጥነው የደም የቅባት መጠን (ኮሌስትሮል) መቆጣጠር

- የሰውነት ክብደትና ከዕድሜና ከቁመት ጋር ማመጣጠን - ቅባታማ ምግቦችን ቢቻል ከምግብ ስርዓት ውስጥ ማስወገድ ካልተቻለ ደግሞ መቀነስ - ሰውነታችን እለታዊ ተግባሩን በብቃት ማከናወን እንዲችል በየቀኑ ቢያንስ ሁለት ሌትር ውሃ

የመጠጣት ባህልን ማሳደግ፡፡ ምክንያቱም በሰውነት ውስጥ በቂ ውሃ መኖር ደም በተገቢው መጠን እንዲቀጥን፣ የልብ ምት ስርዓታችን የተስተካከለ፣ የደም ዝውውራችን ጤናማ እንዲሆንና ሌሎችንም ጤና ነክ ጥቅሞች ያስገኛል፡፡

- አትክልትና ፍራፍሬውን ጨምሮ አሰር ያላቸውን ምግቦች መመገብ ማዘውተር - በሰውነታችን ውስጥ አላግባብ የሚከማቹ ስቦችን በማሶገድም ሆነ ለተሟላ የጤና ሁኔታ መሻሻል

አካላዊ እንቅስቃሴን አዘውትሮ መስራት፡፡ በአጠቃላይ የየዕለት ህይወታችን በእንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሆን መጣር ተገቢ ይሆናል፡፡

- ምንም አይነት የህመም ስሜት ሲኖር ሐኪምን ፈጥኖ ማማከር ተገቢ ይሆናል፡፡ - የጨጓራ ህመም ስሜት ሲኖር የሐሞት ጠጠር ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ከሮቤል ሔኖክ ሚኒሶታ አዲስ ሰው ሲመጣ፤ ከተማው ውስጥ

ረዥም ጊዜ የቆዩ ሰዎች አዲስ መጤውን ይዘውት የሚሄዱት ዩኒቨርሲቲ አቬንዩ ነው ይባላል። ብዙ ሰዎችንም ብትጠይቁ ምናልባትም “መጀምሪያ ሚኒሶታ ስመጣ የሄድኩበት መንገድ ወይም ያየሁት ቦታ ዩኒቨርሲቲ አቬንዩን ነው” ሊሏችሁ ይችላሉ። ዳውንታውን ሚኒያፖሊስን ከዳውንታውን ሴንትፖል ጋር የሚያገናኘው ትልቁ የባቡር ሃዲድ እየተገነባበት የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ አቬንዩ እነሆ አዲስ የኢትዮጵያውያን ማርኬት ተከፈተበት። ባላገሩ ማርኬት።

የሱቁ ባከቤቶች ወጣት ሴቶች ናቸው። ፍጥነታቸው፣ ለሥራ ያላቸው ተነሳሽነትና ኢነርጂያቸው የሚያስገርም ነው። “ሱቁ ውስጥ እቃ ሊገዛ የመጣ ሰው እኩርፎ እንኳ ቢመጣ ስቆ ይሄዳል” ሲል ነበር መስተንግዷቸውን በአድናቆት የሚገልጸው የሱቁ ደንበኛ ማርቆስ በላይ።

811 university Avenue W St. Paul MN

55104 ላይ የሚገኘው ባላገሩ ማርኬት ባለቤቶች ሰናይት ሞገስና ሰላም ሞገስ ይባላሉ። ማርኬቱን እንዴት “ባላገሩ” ሲሉ ሊሰይሙት እንደቻሉ ጠየኳቸው።

ሰላም ፈጠን ብላ “ሃገር ቤት በአሁኑ ወቅት የንግድ ቤት ተከፍቶ የሚሰየመው በውጭ ሃገራት ከተሞች ስም ነው። ለንደን ካፌ፣ አምስተርዳም ሬስቶራንት፣ ስቶክሆልም ሬስቶራንት፣ ዋሽንግተን ካፌ፣... ምን አለፋህ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሳይቀር በስማቸው ጸጉር ቤትና ሥጋ ቤት ተከድቶላቸዋል። እኛ እዚህ ያለነው ደግሞ በተገላቢጦሽ ነን። አብዛኞቻችን ንግድ ከፍተን ስያሜውን ሃገርኛ ነው የምናደርገው። ይህም ለሃገራችን ያለንን ናፍቆትና ሃገራችንን ለማስተዋወቅ ያለንን ፍላጎት ያሳያል። እኛም መደብራችንን ባላገሩ ያልነው ሕብረተሰባችን እኛ ጋር ሲመጣ ሃገር ቤት ያለ እንዲመስለው በማሰብ ነው” በማለት መለሰችልኝ።

በሱቁ ውስጥ አዳዲስ የሃበሻ ቀሚሶች፣ በተለይም በቅርብ ጊዜ ውስጥ እየተወደዱ የመጡት ድምጻውያን እየለበሱት ያለው ባህላዊ ቁምጣዎች እና ቲቨርቶች (ጎሳዬ ተስፋዬና ጃኪ ጎሲ የለበሷቸው) በብዛት አሉ። ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ ጃንጥላዎች፣ ቅብአ ቅዱስ፣ እጣን እና ጧፎች አሉ። ባህላዊ ጌጣጌጦች፣ እንጀራዎች፣ የኢትዮጵያ ቅመማ ቅመሞች፣ ሰፌድ፣ የክትፎ ማቅረቢያ ጣባ የቡና ማንከሽከሻ፣ የቡና ብረት ምጣድን ጨምሮ አብዛኛው የሃገራችን ባህላዊ እቃዎች

ከግሮሰሪዎች ጋር ሞልቶበታል። ሰናይት ቀጠለች “የኛን ማርኬት ለየት የሚያደርገው ሰዎች

ካሁን በኋላ የሃበሻ ልብስ ሲፈልጉ ሃገር ቤት መሄድ የለባቸውም። ፋሽን የሆኑ አልባሳትን እዚህ ተለክተው ኢትዮጵያ አሰርተን እናመጣላቸዋለን። በ እጃችን ያሉ ልብሶችም አሉ እነርሱን መውሰድም ይችላሉ”።

በምግብ ሥራ ጥሩ ሙያ እንዳላት የሚነገርላት ሰናይት ሌላም የምስራች ከባላገሩ ማርኬት አለ ትላለች። አካፍይን አልናት፤ እሷም “እንደሚታወቀው በአሁኑ ወቅት ሁሉም በሥራ በጣም ስለሚወጠርና ስራም ስለሚበዛበት ሽንኩት ከፍቶ አቁላልቶ ምግብ መሥራትን አይፈልግም። ለዚህም ነው በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ የቁሌት ገበያ እየጨመረ የመጣው። ባላገሩ ማርኬት ቁሌት አቅርቧል። ከዚህ ውጭ

ያለን ትልቅ የምሥራች ደግሞ ለዓመት በዓልም ሆነ የታመመ ሰው ለመጠየቅ ሲፈልጉ እኛን ቢያዙን ዶሮ ከነ12 ብልቶቹ ሠርተን እናቀርባለን።” ብላናለች።

“ሃገር ቤት በባላገሩ ማርኬት” በሚል መርሆ የተነሳው አዲሱ የገበያ ማዕከል የሚኒሶታ ማህበረሰብን ተቀላቅሏል። እነሆ እነዚህን ወጣት ልጆች ደውለንም ሆነ፤ ሱቃቸው ድረስ በመሄድ እንኳን ደስ ያላችሁ ልንላቸው ይገባል። ከሱቃቸውም በመገበያየት ኮምዩኒቲያችንን በገንዘብ እናጠራቅም።

የባላገሩ ማርኬት ስልክ ቁጥር 651-209-1399 ነው።

አድራሻቸውም ከላይ እንደተጠቀሰው 811 university Ave-

nue W St. Paul MN 55104። ዘ-ሐበሻ በዚህ አጋጣሚ እነዚህን ወጣቶች እንኳን ወደ

ኮምዩኒቲ አገልግሎት በሠላም መጣችሁ ትላለች፡፡

ሐሞት... ከገጽ 17 የዞረ

እንጂ ከሐሞት መፍሰሻ ቱቦ መዘጋት፣ ከጉበት መድከም (ስራ ማቆም) ጋር በተያያዘ ደረጃ በደረጃ የሚታዩ የህመም ምልክቶች ይኖራሉ፡፡

ከሰውነት ውፍረት፣ ከደም ብዛት፣ ከስኳርና ከኮሌስትሮል ጋር የሐሞት ጠጠር የሚያገናኘው ነገር ይኖር ይሆን?

ዶ/ር ፡- ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት መኖርና በደም ውስጥ ቅባት መጨመር የሐሞት ጠጠርን በማምጣትም ሆነ በማባባስ በኩል የቀጥታ ግንኙነት አላቸው፡፡ የደም ግፊቱና ስኳሩ ግን ግንኙነት ቢኖራቸውም ቀጥታ ነው ማለት አይቻልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የኮሌስትሮል መጠናቸው ከፍ ይላል፡፡ የኮሌስትሮል ከፍ ማለት ደግሞ የሀሞት ጠጠርን ያስከትላል፡፡

ደም ግፊትን በተመለከተ ሁለት አይነት ነው፡፡ በተፈጥሮ የሚመጣና በኮሌስትሮል መጠን መብዛት ሳቢያ የሚመጣ ደም ግፊት አለ፡፡ በተጥሮ የሚመጣው ደም ግፊት ከሐሞት ጠጠር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም፡፡ በኮሌስትሮል የሚመጣው ደም ግፊት ግን የሐሞት ጠጠርን የማምጣት እድል አለው፡፡

የሐሞት ጠጠር የጤና ችግር በአገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

ዶ/ር ፡- የጤና ችግሩ በአገራችን ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ የተጠና ነገር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ መረጃውም የለኝም፡፡ ነገር ግን በአገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሐሞት ጠጠር ከጊዜ ወደ ጊዜ ስርጭቱ እየሰፋ እንደመጣ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ለአብነት የአሜሪካንን ሁኔታ ብንመለከት እንኳ ችግሩ አለማቀፋዊ ገፅታ ያለው መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአሜሪካ ከአጠቃላይ ህዝቡ ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆኑት የሀሞት ጠጠር ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የህመም ምልክት አያሳዩም፡፡ በአጠቃላይ የሐሞት ጠጠር የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ሳይሆን የሁሉም ሰው ችግር ነው፡፡ ይሄን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ተመራጭ ነው፡፡

የጤና ችግሩን ለማስወገድ ያለው አማራጭ መፍትሄ ምንድን ነው?

ዶ/ር ፡- የህክምናው ሳይንስ አሁን በደረሰበት ሁኔታ ያለው የመፍትሄ አማራጭ ቀዶ ህክምና ብቻ ነው፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ ሙሉ በሙሉ በመክፈት ጠጠሩን የማውጣት ሂደት ይከናወን ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት የህክምናው ሳይንስ በተፈጠረው ቴክኖሎጂ ማለትም ሙሉ በሙሉ ሰውነት ሳይቀደድ በአፍ በኩል በኢንዶስኮፒ በመጠቀም ቀዶ ህክምና ሳይካሄድ ጠጠሩን እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ በሌላም በኩል የተወሰኑ ቀዳዳዎችን በምፍጠር በላፖራስኮፒ አማካኝነት ጠጠሩን ማውጣት ይቻላል፡፡ ከአጠቃላይ የሀሞት ጠጠርን ችግር ሙሉ በሙሉ ቀዶ ህክምና ሳይደረግ መፍትሄ መስጠት የሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ይህ አይነት የህክምና አቅም በአገራችንም እየተሰራበት ይገኛል፡፡

የሐሞት ጠጠርን በተመለከተ እስካሁን ከቀዶ ህክምና ውጭ በመድሃኒት መፍትሄ የሚሰጥበት እድል የለም፡፡

ቶሎ ህክምና ያልተደረገበት የሀሞት ጠጠር የሚያስከትላቸው ጉዳቶች ምንድን ናቸው?

ዶ/ር ፡- - የሐሞት መፍሻ ቱቦን ሙሉ በሙሉ ይዘጋል፡፡ - የተመረተው ሐሞት ተግባሩን ሳያከናውን ወደ ጉበት

በመመለስ የጉበት ሴሎችን ይመርዛል - የምንመገበው ምግብ በተለይም ቅባት ነክ ምግቦች ሐሞትን

አግኝተው ስለማይፈጩ ጥቅም ሳይሰጡ በሰገራ መልክ ይወጣሉ፡፡

- የጉበት መድከም (ስራ ማቆም) ይከሰታል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሰውነት ማበጥ፣ መድከም፣ የሆርሞኖች መዛባት እና ከጉበት ጋር የተያያዙ በሽታዎች ሁሉ ይከሰታሉ፡፡

የእንስሳት ሐሞት ይሸጣል ሲባል ይሰማል፡፡ እውነት ነው? የሰው ሐሞትስ ይሸጥ ይሆን?

ዶ/ር ፡- የእንስሳት ሐሞት አይሸጥም፡፡ የሚሸጠው ከእንስሳቱ ሐሞት ውስጥ የሚሰራ ጠጠር ነው፡፡ ይህን ጠጠር በውጭው ዓለም ለጌጥ ለመጠቀም ሲሉ በከፍተኛ ዋጋ እንደሚገዙት ይታወቃል፡፡ ከጌጥነት በዘለለ ግን ሐሞት ለህክምናዊ አገልግሎት ጥቅም ላይ አይውልም፡፡ የሰውን በተመለከተ እስካሁን ምንም አይነት መረጃ የለኝም፡፡ በመሆኑም ይሸጣልም (አይሸጥምም) ልልህ አልችልም፡፡

የትግራይ... ወደ ገጽ 5 የዞረ

የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ነዉ። ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ ነዉ። በ2004 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ 90 ሚሊዮን አንደሚሆን የተገመተ ሲሆን ከዚህ ቁጥር ዉስጥ በትግራይ ክልል 5.4 ሚሊዮን ህዝብ በተቀሩት ስምንት ክልሎች ደጎሞ 84.6 ሚሊዮን ሀዝብ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ይህ ጥናት በዋናነት የሚያመለክተዉ በዋና ዋና የሀላፊነት ቦታ የተቀመጡትን ግለሰቦችና ግለሰቦቹ የመጡበትን ብሔር ስለሆነ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺንን የሰዉ ኃይል ምደባና የደረጃ እድገትን ጠለቅ ብለን ስንመለከት አብዛኛዎቹ እንጂኔሮችና ቴክኒሻኖች የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ፤ የደረጃ እድገትን በተመለከተም

ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ሲነፃፃር በፍጥነት የደረጃ እድገት የሚያገኙት እነዚሁ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። ይህ ደግሞ በአጋጣሚ የሆነ ነገር ሳይሆን ወያኔ በረሀ ዉስጥ እያለ አቅዶት ባለፉት ሃያ አመታት በስራ ላይ ያዋለዉ የረጂም ግዜ እቅድና ዝግጅት ዉጤት ነዉ። ለምሳሌ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ ኤም አይ ቲ ወይም የመቀሌ ቴክኖሎጂ እንስቲቲዩት ብሎ የሚጠራዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ተቀብሎ የሚያስተምረዉ የትግራይ ተወላጆችን ሲሆን ከዚህ ተቋም የሚመረቁ እንጂኔሮችና ተክኒሺያኖች ናቸዉ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን የሚሊታሪ ክንፍና በኢትዮቴሌኮም የስለላ ተቋሞች ዉስጥ ተመድበዉ ከፍተኛ የስለላ ስራ የሚሰሩት።

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝና አገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ቡችሎቹ የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ድርጅቶች በተለይ በዳያስፖራ ዉስጥ የሚገኘዉን ለእናት አገሩ ተቆርቋሪ የሆነ

ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጅምላ “የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች” እያሉ ለአመታት ሲዘልፉን ኖረዋል። የፖለተካ ትግላችን አላማና ግብ ከጥላቻ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለዉ ቢሆንም – ለመሆኑ ይህንን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተና አንዱን አለቃ ሌላዉን ተላላኪ፤ አንዱን የሚሾም ሌላዉን የሚሽር፤ አንዱን አብልቶ የሚያጠግብ ሌላዉን የበይ ተመልካች የሚያደርግ፤ አንዱን የአገር መሪነት ቦታ ተረካቢ ሌላዉን ኮብልስቶን ድንጋይ ጠራቢ የሚያደርግ ስርዐት የሚወድ ማን አለ? ይህንን በንጹህ ዜጎች ደም እጁ የቆሸሰና ያደፈ ዘረኛ ስርአት ዉደዱ የሚለንስ ማነዉ? በምድርም በሰማይም የከሰሩ እነ ሚሚ ስብሀቱን የመሳሰሉ የፖለቲካ ሴሰኞች ሊነግሩን እንደሚፈልጉት ትግላችን የትግራይ ወንድሞቻችንንና እቶቻችንን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የትግላችን ብቸኛ አላማ ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር ሊያጋጩን የሚሞክሩትን የህወሀት ወንጀለኞች አስወግደን

ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር ማድረግ ነዉ።

ቻምፕዮንስ... ከገጽ 21 የዞረ

ተሰጥኦ እና ጥራት የታየበት ጨዋታ ነበር፡፡ ዚነዲን ዚዳን፣ ልዊስ ፊጎ፣ ሮቤርቶ ካርሎ እና ፈርናንዶ ሄዬሮ የነበሩበት ቡድን ለማየት የሚያስደንቅ ነበር፡፡ ግጥሚያው ድንቅ በመሆኑም ሮማን አብራሞቪች የእግርኳስ ክለብ ለመግዛት ወሰኑ፡፡

ከዚያ በኋላ ማድሪድ በቻምፒየንስ ሊግ የዋንጫ ድርቅ ተመትቷል፡፡ የቅርብ ተቀናቃኙ ባርሴሎና ለሶስት ጊዜያት ባለትልልቅ ጆሮዎቹን ዋንጫ ሲያነሳ ሪያል ማድሪድ በታሪኩ 10ኛ ዋንጫውን ለማንሳት ዳገት የመውጣት ያህል ከብዶታል፡፡ ስለዚህ ፕሬዝዳንቱ ፊዮሬንቲኖ ፒሬዝ ከባርሴሎና ጋር ለመፎካከር ከፍተኛ ገንዘብ አወጡ፡፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ካካ፣ ካሪም ቤንዜማ፣ አንሄል ዲ ማሪያ፣ ፋቢዮ ኮኤንትራኦ እና ሉካ ሞድሪችን (ቻምፒዮንስ... ወደ ገጽ 22 የዞረ)

ገጽ page January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ይህ አምድ እያዝናኑ የሚያስተምሩ፤ ቁምነገሮች የሚስተናገዱበት ነው። በአምዱ ላይ የአንባቢያን ተሳትፎ ይበረታታል። ምንጭ ጠቅሰው ያስገረመዎትን እውነታ ያካፍሉን

ለፈገግታ የስፐርሙ ናሙና

ሰውየው የመካንነት ችግር ስላጋጠማቸው የዘር ፍሬ ህዋሳት ቆጠራ (spermcount) ለማሰራት ወደ አንድ እውቅ ዶክተር ዘንድ ያመራሉ፡፡ ‹‹እባክህ ዶክተር አሁን የመጣሁበት ጉዳይ ይህ ነው፡፡ ለዚህ ምን ትመክረኛለህ?›› በማለት ጥያቄአቸውን ያቀርባሉ፡፡ ዶክተር፡- ምንም ችግር የለ ሁሉንም ማሰራት ይቻላል፡፡ ለማንኛውም ይህንን ዕቃ ይዘው ይመለሱና ለናሙና የሚሆን የዘር ፈሳሽዎን ለነገ ይዘው ይምጡ፡፡ በሁለተኛው ቀን ዕቃውን ይዘው ወደ ዶክተሩ ይመለሳሉ፡፡ ዶክተሩ ዕቃውን ከተቀበሉ በኋላ ሲከፍቱት ውስጡ አንዳችም ነገር አልነበረውም፡፡ ዶክተሩ በጣም ተገርመው በለስላሳ አንደበት ‹‹ምነው አባት ምንም ናሙና አላመጡም'ኮ›› ይላቸዋል፡፡ ‹‹አይ ዶክተር በጣም ተቸገርኩ፡፡ በመጀመሪያ በግራ እጄ ሞከርኩ፣ ግራዬን ሲደክመኝ በቀኝ እጄ ተያያዝኩት፡፡ ነገር ግን በሁለት እጄም ብሞክር ሊሆንልኝ አልቻለም፡፡ ሚስቴ የምሰራው ነገር ገርሟት በኔ ያምራል በማለት በሁለት እጇ ልታግዘኝ አሰበች፡፡ በአፏም ብዙ ደከመች ግን ሊሳካ አልቻለም፡፡ በመጨረሻ ግራ ቢገባን የጎረቤታችንን ወጣት ኮረዳ ጠራናት፡፡ የበኩሏን ሁሉ ሞከረች ነገር ግን የሶስታችንም ድካም ከንቱ ሆነና ናሙናውን ማምጣት አልቻልኩም፡፡ ዶክተሩ በጣም ይገረማሉ፤ ‹‹ጭራሽ የሚስትዎ ሲገርመኝ ከጎረቤትም አስጠርተው ሞከሩ?›› ‹‹አዎ ዶክተር ቢጨንቀኝ›› ዶክተር፡- እና ምን ይሻላል፡፡ ‹‹እናማ የሰጡኝን ዕቃ መክፈት አልቻልንም››

የህፃናት ጥያቄና የአባታቸው መልስ

‹‹ገንዘብ ዛፍ ላይ ካልበቀለ፤ ለምንድን ነው ባንክ ቤቶች ቅርንጫፍ የሚኖራቸው?›› - ገንዘብ እንደውሃ ሳር ቅርንጫፍ እንጂ ስር ስለሌለው ‹‹ውሃ ውስጥ ሆኖ ማልቀስ ይቻል ይሆን?›› - ‹‹ይቻላል፤ ከአንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም ይባል የለ?›› ‹‹ሞተህ ገነት ብትገባ፤ የምትለብሳቸው ልብሶች ሞተህ ስትቀበር የነበሩትን ነው?›› - ሰማይ ቤትም በተቀበርንበት ጉድጓድ ውስጥ ከኖርን! ‹‹አይነስውር የሆነ ሰው የወደፊት ህይወቱን ማየት ይችላል?›› - ልብ እንጂ አይን አያይም፤ የማይታያቸው ልበ ቢሶች ናቸው! ‹‹ለምንድን ነው የሴትና የወንድ ጫማ ቁጥሮች የተለያዩ የሆኑት?›› - ቁጥሮች ሁሉ አንድ ስላልሆኑ! ‹‹የመጀመሪያ ሴት ፕሬዝዳንት ብትኖረን፤ ባሏም የመጀመሪያ ይሆናል ማለት ነው?›› - ትክክል፤ ‹‹ቀዳማዊ ጌታ›› ተብሎ ስለሚጠራ... ‹‹በአንድ ጊዜ ወደ ቀኝና ወደ ግራ እንሄዳለን?›› - ይህን እንኳን የሚችለው ወታደር ነው!

ምንጭ አልባ አንደበቶች - ዓሳ መሽተት የሚጀምረው ከጭንቅላቱ ነው፡፡

- ቅንነት ምርጥ ፖሊሲ ነው፡፡ ምክንያቱም ውድድሩ እጅግ በጣም አነስተኛ ስለሆነ ነው፡፡

- ጋብቻ ጥቂት ሴቶችን ወደ ሽርክና ሌሎችን ደግሞ ወደ ተወዳዳሪነት ይቀይራቸዋል፡፡

- ማንም በራበው ሰዓት የመሳም ፍላጎት የለውም፡፡ - የጠላትህ መከራ ላንተ ጣፋጭ ነው፡፡

- ባል በበር ሲገባ ውሽማ በመስኮት ይወጣል፡፡ - የሴትን ኃይል ዝቅ አድርገህ አትገምተው፤ ዕድሜዋንና

ክብደቷንም ከመጠን አብልጠህ አትገምተው፡፡ - ጥቂት ሰዎች በጣም ብዙ ያነባሉ፤ ጥቂት ሰዎች ደግሞ በጣም

ብዙ ይጽፋሉ፡፡ ግን ሁሉም ሰው ብዙ ያወራል፡፡ - ተፈጥሮን ልታሸንፋት አትችልም፡፡ የምታበጥረው ፀጉር ባነሰ

ቁጥር ብዙ የምትታጠበው ፊት ይኖርሃል፡፡ - ሲራቡ የሚያገኙት ቁራሽ ሲጠግቡ ከሚያገኙት ክምር

ይሻላል፡፡

ከመጻህፍት ዓለም - ሰው ሁሉ በህግ ፊት እኩል ነው የሚለው የህጋችሁ አንቀጽ፤ በሐሰት የተለበጠና በግብር የማይገለጽ የማስመሰያ እምነታችሁ ዝቃጭ ማስረጃ ነው፡፡ እስኪ የት ነው? ማን ነው? ትክክለኛ የፍትህ ሸንጎ በምትሉት የአድልዎ አደባባያችሁ ላይ እውነተኛ ፍርድን ያገኘ?

/የወዲያነሽ/ - መማር ከፈለክ አድማጭ ሁን፡፡

/አመድ አፋሽ/ - የትንሣኤ መጀመሪያ ሞት እንደሆነ ሁሉ የስኬትም መጀመሪያ ውድቀት ነው፡፡ ያልወደቀ አይነሳም፡፡ በንቅፋት አልባ መንገድ ላይ የሚራመድ ከወደቀ መነሳት ያዳግተዋል፡፡ መውደቅ መነሳትን የለመደ፤ ቢወድቅ እንኳ ተኝቶ አይቀርም አቧራውን እያራገፈ ይነሳል፡፡ የዚህ ሁሉ ስር መሰረት የመነሳት ደወል ሲደወል ማዳመጥ ነው፡፡

/ራማቶሓራ/ - ህሊና ያለራሱ የሚፈራው ዳኛ የለም፡፡

/ጎሚ/ - ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም፡፡ ህይወት እንደ ቡና ወተቱ ነው፤ ወተት እውነት ቡናው ውሸት ይሁን፡፡ ግን ይሄ ልዩነት በአንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው፡፡ ብትቀምሰው ቡናው አይደለም ወተቱም አይደለም ቡና በወተት ነው፡፡ ህይወት ውስጥም በቀኝ በኩል እውነት፣ በግራ በኩል ውሸት አይገኝም፡፡ ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነትና የውሸት ቅልቅል ነው፡፡

/ሌቱም አይነጋልኝ/ - የሚዋደዱ ሰዎች አይን ለአይን ተያይተው አይጠጋገቡም፡፡ አብረው ውለው ቢያድሩ እንኳ አይሰለቻቹም፡፡ መረሳሳትና መጠጋገብ፣ መኩራራትና የተለየ ፀባይ ማሳየት የሚመነጨው ግን ሌላ ሶስተኛ ሰው መሀል ሲገባ ነው፡፡

/የመከራ ቋት/ - ህይወት የግዴታዎች ሰንሰለት ናት፡፡

/ኦሮማይ/

ያውቁ ኖሯል?! - ተንጠልጣይ የጆሮ አካላቸው ቀይ የሆነ ሴት ዶሮዎች ቡናማ እንቁላሎችን ይጥላሉ፤ ባንፃሩ ይሄ አካሏ ነጭ የሆነ ዶሮ ነጭ እንቁላሎችን ትጥላለች፡፡ - የመጀመሪያውን የንቅሳት ማሽን የፈለሰፈው ግለሰብ ሳሙኤል ኦ ሬይሊ ይባላል፡፡ ይህ ሰው ቀደም ብሎ ቶማስ ኤዲሰን ጠንካራ አካላትን ለመቅረፅ ይጠቀምበት የነበረን መሳሪያ ለዚህ ፈጠራው ተጠቅሞበታል፡፡ - አንድ ሰው በየቀኑ ለተጨማሪ 20 ደቂቃ ያህል የእግር ጉዞ በማድረግ በዓመት ውስጥ 7 ፓውንድ የሚሆን የሰውነት ስብን ያቃጥላል፡፡ - አንድ በአማካይ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሰው 42 ሚሊዮን የሚገመቱ የፋት ሴሎች አሉት፡፡ - ታላቁ የፈጠራ ሰው ቶማስ ኤዲሰን በጥይት ባሩድ (gunpowder) የሚሰራ ሔሊኮፕተር ዲዛይን አድርጎ እንደነበር ያውቃሉ? ይሁን እንጂ ሔሊኮፕተሩ ፈንድቶ ፋብሪካውንም አጋይቶበታል፡፡ - ከግራኝ ሴቶች ጋር ሲነፃፀር የግራኝ ወንዶች ቁጥር በግማሽ እጥፍ የላቀ ነው፡፡ - እሳተ ገሞራ 50 ኪሎ ሜትር ያህል ከፍታ ወደ ከባቢ አየር አመድ የማስነሳት በቂ ኃይል እንዳለው ያውቃሉ? - ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ የዋለችው ‹‹German Focke-wulf FW 61›› የተባለችው ሔሊኮፕተር የተፈለሰፈችው እ.ኤ.አ በ1936 ዓ.ም ነው፡፡ - ‹‹ሥለግ›› የተባለው የቅጠል ትል አራት አፍንጫዎች አሉት፡፡ - የመጀመሪያው የሮናልድ ማክዶናልድ ‹‹weatherman Willard Scott›› ይባላል፡፡ - እውነተኛ ስፓይደሮች ድር የሚፈትሉበት ‹‹Spinnerets›› የተባሉ የመፍተያ አካላት አላቸው፡፡ - በሶላር ሲስተማችን ውስጥ መንኮራኩር ያመጠቀባት ብቸኛዋ ፕላኔት ናት-ፕሉቶ፡፡ - ቀዳማዊት ንግስት ኤልሳቤጥ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ትንሽ የሽቶ ብልቃጥ የተንጠለጠለበት የአንገት ሐብል ያደርጉ ነበር፡፡ - እ.ኤ.አ በ1963 ዓ.ም ‹‹ክሊዮፓትራ›› የተሰኘውን ፊልም ለመስራት 44 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፊልሙ 300 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያወጣል፡፡ - የአርካ ዓሣ ነባሪ ትንፋሹን ለ15 ደቂቃዎች ያህል መያዝ ይችላል፡፡

ዘወትር ሐሙስ የክትፎ

በቆጮ ቀን

Mursi tribe woman Ethiopia By Eric Lafforgue Mursi woman, the most agressive tribe i met. Agressive in the way that when you come to see them (after hours of 4x4 on a very bad track), they only think about the money they can get from you! The craziest thing is that they ask for a fee to park the car (20 euros!) at the entrance of the village!! They use those wild pigs tusks as a decoration. The main problem is that they tend to use more and more things to attract photographers! You may have seen or read books about this area by great photographers those last years, and many of the people inside are just "disguised"... But at the end, those tribes really live like in the primitives times, whithout anything around apart their cattle, and still fighting with other tribes to catch cows and women... This is a daily reality in this area of the world! 7 000 tourists visit the mursis every year. It makes an average of 20 by day in a very big area, so it's very few.But as 70% are from Spain and pay a low fee to the tour operator, some tribes start to settle close to "hotels" or campings to get money from the photographers. I had the chance to go in Omo valley with a guide who avoid those touristic spots. The Mursi (also called Murzu) is the most popular tribe in the southwestern Ethiopia lower Omo Valley, 100 km north of Kenyan. They are estimated to 10 000 people and live in the Mago National Park, estab-lished in 1979. Due to the climate, they move twice a year between the winter and summer months. They herd cattle and grow crops along the banks of the Omo River. The Mursi are sedentary rather than nomadic. Their language belongs to the Nilo-Saharan linguistic family.Very few Mursi people speak Amharic, the official Ethiopian language. Although a small percentage of the Mursi tribe are Christians, most still practice animism. Mursi women wear giant lip plate, a sign of beauty, like in Suri tribe, and also a prime attraction for tourists which help to sustain a view of them, in guidebooks and travel arti-cles, as an untouched people, living in one of the last wildernesses of Africa. When they are ready to marry, teenagers start to make a hole in the lower lip with a wood stick. It will be kept for one night, and is removed to put a bigger one. This is very painful at this time. Few months after, the lip plate has its full size, and the girl is seen as beautiful by the men. The lip plate is made of wood or terracotta. They have to remove the lower incisors to let some space for the disc. Sometimes the lip is broken by the pressure of the plate. This is a big problem for the girl because men will consider her as ugly, she won't be able to marry anyone in the tribe apart the old men or the sick people. Women and men are shaved because they hate hairiness. Both like to make scarifications on their bodies. Women as a beauty sign, men after killing animals or ennemies as competition for grazing land has led to tribal conflicts. The Mursi men have a reputation for being aggressive and are famous for their stick fighting ceremony called donga. The winner of the donga will be able to select the girl of his choice to have relations with if she agrees. Similar to the Surma tribe, the Mursi tribe commonly drink a mixture of blood and milk. Over the past few decades they and their neighbours have faced growing threats to their livelihoods cause the Ethiopian government officials have been actively evicting Mursi people from the Omo Na-tional Park, without any compensation to rent their land to foreign investors. Drought has made it diffi-cult for many families to feed themselves by means of their traditional mix of subsistence activities. The establishment of hunting concessions has added to the pressure on scarce ressources. © Eric Lafforgue www.ericlafforgue.com

ገጽ page January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ዋሊያ.... ከገጽ 4 የዞረ

ለማዳና የዋህ ማድረግ ሊጋጭ ይችላል ፡፡ ግን ደግሞ ሴኔጋሎች ስፖርት ዝምድናን ማጠናከሪያ መሆኑን በመረዳት ከአስፈሪ ይልቅ ሰላማዊ ስያሜ የመስጠታቸው ሀሳብ ከዚህ የመነጨ ሊሆን ይችላል ፡፡

የሞሮኮዎቹ ‹ The lion of the Atlas › የሚለው ስያሜ ደግሞ ከሴኔጋሉ በተቃራኒ የሚተነተን ነው ፡፡ ሞሮኮዎቹ የሚያምኑት አንበሳ በጫካ ውስጥ ሃይለኛና ጠንካራ መሆኑን ነው ፡፡ ይህ አንበሳ ደግሞ በሀገራቸው ጎልቶና ደምቆ በሚገኘው የአትላስ ተራራ ውስጥ እንደ ድምጻዊው አሸብር በላይ ‹ ይሰለፍና ፈረስ ከእግረኛ

እኔ ነኝ ያለ ይሞክረኛ ! › እያለ የሚፈነጭ ነው ፡፡ እናም ቡድናቸውም የማይደፈር እንዲሆን ከመፈለግ አንጻር የተነሱ ይመስላል ፡፡ ከአፍሪካ ዉጪም ቡልጋሪያ ‹ the lions › ፣ ኢራ ቅ ‹ the Babylon lions › ፣ ሉክሰምበርግም ‹ the lions › የ ሚል መጠሪያ ያላቸው መሆኑን ስንረዳ ልንገረም እንችላለን ፡፡

አዳኝ አእዋፋት ማሊ / The eagles / ፣ ናይጄሪያ / The super eagles / ፣

ሱዳን / Desert Hawks / ፣ እና ቱኒዚያ / The eagles of Carthage / ንስር አሞራና ፋልኮን ከረጅም ርቀት መሬት ላይ ያለ እንቅስቃሴን አጥርተው ይመለከታሉ ፡፡ አይናቸው ለአጉሊ መነጽር መፈብረክ መንስኤ ሆኖ ቢገኝ እንኳ አይበዛበትም ፡፡ በሚገርም ፍጥነት ወደ ታች ተምዘግዝገው የሚበሉትን ነገር ገቢ ማድረጋቸው ሲታይ ለሚሳይል መፈጠር ለምን መነሻ አልሆኑም ብሎ እስከ መከራከር ያደርሳል ፡፡

ንስር አሞራ ረጅም እድሜ ከሚኖሩ አእዋፋት መካከል አንደኛው ነው ፡፡ 70 ዓመት ይኖራል ፡፡ እዚህ እድሜ ላይ የሚደርሰው ግን ጠንካራ ውሳኔዋችን በማሳለፍ ነው ፡፡ በተለይም 40 ዓመት ሲሞላው እንስሳትን ሰቅስቆ የሚይዝበት ረጅም ጥፍሩ መያዝ ያቅተዋል ፡፡ ስጋን ቦጭቆ የሚያነሳው የአፉ መንቆር ይጣመማል ፡፡ ትልቁ ክንፉ ለመብረር ያስቸግረዋል ፡፡ ስለዚህ መሞት ወይም በአስቸጋሪ ፈተና ውስጥ ማለፍ ከተባሉ አማራጮች ጋር ይፋጠጣል ፡፡ ቀጣይ ዕድሜ ያስፈልገኛል ካለ የአፉን መንቆር ከድንጋይ ጋር እያጋጨ ማስወገድ ይኖርበታል ፡፡ ክንፎቹንም ነቅሎ መጣል ፡፡ ይህንን ተግባር በከባድ ስቃይ ውስጥ አልፎ ከከወነ ከአምስት ወራት አስቸጋሪ ጉዞ በኃላ አዲስ ክንፍና መንቆር ያወጣል ፡፡ እናም ቀጣዩን ሰላሳ ዓመታት በአስተማማኝ ሁኔታ ይኖራል ፡፡

ይህን አስቸጋሪ የህይወት ጉዞና ጥንካሬ በማሰብ ለቡድና ቸው ስያሜ የሰጡ ሀገሮች መነሻቸው ለክፉ አይሰጥም ፡፡ ችግሩ ዉጤት ላይ ነው፡፡ ቱኒዝያ አንድ ግዜ ፣ ናይጄሪያ ደግሞ ሁለት ግዜ ብቻ ነው የአፍሪካን ዋንጫን ያነሱት ፡፡ ከዚህ አንጻር ባለ ስያሜዋቹ ሀገሮች ዛሬም መንቁራቸውንና ጥፍራቸውን ከድንጋይ ጋር በመጋጨት ላይ የሚገኙ ይመስላል ፡፡

የተለየ ስያሜ ማላዊ የሚለው ቃል ‹ Flame › የሚል ትርጉም አለው ፡፡

የማላዊ ብሄራዊ ቡድንም ስያሜ ‹ Flames › ነው ፡፡ ሊቢያ ደረቅና በረሃማ ብትሆንም ማሊያውን መሰረት በማድረግ ቡድኑ ‹ Green › ተብሏል ፡፡ ልጆቹ ወይም ባፋና ባፋና የደቡብ አፍሪካ መለያ ነው ፡፡ ግብጽ የጥንት ጠንካራ ገዢ መደብን ለማስታወስ ‹ The Pharaohs › ነው የምትባለው ፡፡ ጎበዝ ተዋጊዎች / Brave warriers / ናምቢያን ሲወክል ፣ የመዳብ ጥይቶች / The copper bullets / የሚባሉት ዛምቢያዋቹ ናቸው ፡፡

ኮኮብን አራት ሀገሮች ተጋርተዋል ፡፡ ጥቁር ኮኮብ የጋና ፣ የሃራምቤ ኮኮብ የኬንያ ፣ የውቅያኖስ ኮኮብ የሶማሊያ ፣ የኪሎማንጀሮ ኮኮብ ደግሞ የታንዛንያ መጠሪያ ነው ፡፡ የጋና ጥቁር ኮኮብ የመነጨው ከሀገሪቱ ባንዲራ ነው ፡፡ ይህ ባንዲራ የኢትዮጽያ ግልባጭ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ ቀይ ፣ ቢጫና አረንጓዴ ፡፡ ቢጫው መሃል ጥቁር ኮኮብ አለ ፡፡ ይህ ኮኮብ ጥቁር ቢሆንም የሚያንጸባርቅና ማንነታቸውን የሚያመላክት ነው ፡፡ ጋና የአፍሪካ ዋንጫን አራት ግዜ በማንሳትም ትልቅ ስም ገንብታለች ፡፡

የሀገራችን ‹‹ ዋሊያዋች ›› የስያሜ መነሻ የኢትዮጽያ ብሄራዊ ቡድን ‹‹ ዋሊያዋቹ ›› የሚል ስያሜ

የተሰጣቸው ከምን አንጻርና መመዘኛ እንደሆነ የሚያብራራ መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ፡፡ ይሁን እንጂ ለእውነት በጣም የቀረበ ግምት መሰንዘር ይቻላል ፡፡ ስም አውጪዎቹ ለመረጣ መነሻ የሆናቸው ሀገራችንን የሚያስጠራ ነገር የመፈለጋቸው

ጉዳይ ነው ፡፡ ከዚህ አንጻር ኢትዮጽያ ሲባል ምንድነው ገዝፎ ሊነሳ ወይም ሊታይ የሚችለው መገለጫ የሚለው ሀሳብ - ሀሳባቸውን እንዳፋፋመው አይጠረጠርም ፡፡

በወቅቱ ባንኖርም የወደቁና የተወሰኑ ነገሮችን እንገምት ፡፡ . ኢትዮጽያ ነጻነቷን ጠብቃ የቆየች ብቸኛ አፍሪካዊ ሀገር

ናት . ኢትዮጽያ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎችን በጦርነት በማሸነፍ

የምትታወቅ ብቸኛ ሀገር ናት . ኢትዮጽያ የሰው ልጅ መገኛ ሀገር ናት . ኢትዮጽያ የቡና መገኛ ሀገር ናት . ኢትዮጽያ 13 ወራት ጸሃይ የምታበራ ሀገር ናት . ኢትዮጽያ የራሷ የሆነ ፊደል ያላት ብቸኛ አፍሪካዊ ሀገር

ናት . ኢትዮጽያ በሌላው ዓለም የማይገኙ ብርቅዬ እንስሳት

ባለቤት ናት እናም አንዱን ካንዱ የግድ አበላለጡና ብርቅዬ የዱር

እንስሳቱ ነገር ቀልባቸውን አሸነፈው ፡፡ በሀገራችን ብርቅዬ የሚባሉት አጥቢ እንስሳት ደግሞ ዋሊያ ፣ ቀይ ቀበሮ ፣ የስዋይን ቆርኬ ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ ፣ የሚኒሊክ ድኩላ እና የደጋ አጋዘን ናቸው ፡፡ እነዚህን ሲያወዳድሩ ደግሞ ምርጫቸው ዋሊያ አይቤክስ ላይ አረፈ ፡፡ እናም የብሄራዊ ቡድኑን መጠሪያ ‹‹ ዋሊያዎቹ ! ›› አሉት ፡፡

ዋሊያ ምኑ ይስባል ? ወንዱ ዋሊያ ክብደቱ በአማካኝ 120 ኪሎግራም ነው ፡፡

በጣም ከሚስበው ሰውነቱ አንደኛው ጠመዝማዛውና ጉጣሙ ቀንዱ ነው ፡፡ የቀንዱ ርዝመት 110 ሴ.ሜ ያህል ሲሆን በቀንዱ ላይ ያሉ ጉጦች የእድሜ ክቦች ናቸው ፡፡ ዋሊያ ትልቁ ዕድሜው ከ 12- 15 ነው ፡፡ ቀንዱ ላይ አስር ጉጦች ከታዩ አስር አመት አካባቢ እንደሆነ ይገመታል ፡፡ ይህ ስሌት የፈረንጆቹ እንጂ በሀገራችን የተደገፈ ማስረጃ አላየሁም ፡፡ ቸኮሌት የመሰለው መልኩና ጺሙም አይን ወጣሪዋች ናቸው ፡፡ የሚኖረው ከ2500 እስከ 4000 ሜትር በሚደርስ ተራራ ላይ ነው ፡፡ ብዙ ውሃ ባያገኝ ግድየለውም ፡፡ ሳሩ ላይ የማይጠፋውን ጤዛ ከላሰ ‹‹ ተመስገን ! ›› ለማለት ይበቃል ፡፡ አካባቢው በብርድ ወራት በረዶ የሚሰራ መሆኑ ለዋሊያ አይስክሬም እንደ መላስ ሳይጠቅመው አይቀርም ፡፡ ዋሊያ ልክ እንደ ጭላዳ ዝንጀሮ ገደል ለገደል ሲሮጥ እወድቃለሁ ብሉ አይሰጋም ፡፡ ይህም ጠላቶቹ እንዳይደርሱበት ሁነኛ ምሽግ ሆኖታል ፡፡

የዋሊያ ውክልና ነገር ? ዋሊያ በስሪያ ወቅት ካልሆነ በስተቀር ብቸኛ ነው ፡፡ ሲበላና

ሲንቀሳቀስ የሚታየው በማለዳና ሲመሻሽ ነው ፡፡ ከዚህ ውጪ ያሉ ግዜያትን የሚያሳልፈው ጥሻና ገደላ ገደሉ ውስጥ በመደበቅ ነው ፡፡ ማህበራዊ ህይወቱ እጅግ የተቆጠበ ፣ በጥርጣሬ ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ከሰሜን ትላልቅ ተራራዋች ወደ ታች ወርዶ ለመኖር ፣ አካባቢውን ለመጎብኘትና የሌሎችን ህይወት በአንክሮ ለማጤን ፍቃደኛ አይደለም ፡፡ ‹‹ አትድረሱብኝ- አልደርስባችሁም ! ›› የሚል ሎጎ አሰርቶ ዘወትር የሚያውለበልባት ይመስላል ፡፡ የዚህ ብሂል መነሻን ለመፈተሸ ስብሰባ ቢጤ ቢዘጋጅ የዋሊያ ምላሽ የአካባቢዋቹን ሰዋች መሰረት ያደረገ ሊሆን ይችላል ‹‹ የራሷን የማትሰጥ የሰው የማትነካ ኢትዮጽያ መሆኗን አልተረዱም ለካ ! ›› ስለሚሉ ፡፡ መሬትም ዳገትም ላይ የሚኖረው ጭላዳ ዝንጀሮ ግን ለዚህ የዋሊያ መፈክር ‹‹ አይሰማም ! ›› የሚል ምላሽ ሰጥቶ ተጎራብቶታል ፡፡ ዋሊያ ማህበራዊ መስተጋብሩ ቁጥብና ገለልተኛ ከሆነ እንዴት ለምሳሌነት ሊበቃ ቻለ የሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት ይኖርበታል ፡፡ በኢትዮጽያ ብቻ የሚገኙትን ሌሎች ብርቅዬ እንስሳት ትተን ከቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮ አንጻር ልናነጻጽረውና ልናወዳድረው እንችላለን ፡፡

እንደሚታወቀው ቀይ ቀበሮ አይጥ እየተመገበ የሚኖር እንስሳ ነው ፡፡ ማህበራዊ ህይወታቸው ጠንካራ ነው ፡፡ ለማህበራዊ ሰላምታና ድንበራቸውን ለመቃኘት ማለዳ ፣ ከሰዓትና ሊመሻሽ ሲል ይሰባሰባሉ ፡፡ ሌሊቱንም አብረው ያሳልፋሉ ፡፡ የጋራ ምግባራቸውም የሚገርም ነው ፡፡ ምግብ መካፈል ፣ ወዳጅነትን የሚያሳይ መተሻሸትና በጥርስ መነካካት ፣ መባረርና የቀልድ ጸብ በዝቶ ይታይባቸዋል ፡፡ ድንበራቸውን የሚከልሉት በሽንታቸው ፣ በዓይነምድራቸውና መሬቱን በመቧጨር ነው ፡፡ የበሉትንም በማስመለስ ቡችሎቻቸውን ይቀልባሉ ፡፡

የቀይ ቀበሮ ልዩ ባህሪ በእጅጉ አዳኝ መሆኑ ነው ፡፡ አይጥ ለማደን በትዕግስት ያደፍጣል ፡፡ ታዳኙ ቀለበት ውስጥ ገብቷል ብሎ ሲያስብ ሁለት እግሮቹን ወደ ላይ አንስቶ ወደ መሬት

በመወርወር በአፍንጫው ሰርስሮ በመግባት አይጡን አንጠልጥሎ ያወጣል ፡፡ ይህን ተግባር 90 ዲግሪ ላይ ያረፈ ምርጥ የቅጣት ምት ፣ ከማዕዘን የተሻማ ኳስን ነቅንቆ በጭንቅላት እንደማስገባት አሊያም ወደ ጎል የተመታች አደገኛ ኳስን ተወርውሮ እንደመያዝ ሊመሰል ወይም ሊቆጠር ይችላል ፡፡ ታዲያ ቀይ ቀበሮ በጥሩ ምሳሌነቱ ለምን ቀዳሚ የብሄራዊ ቡድናችን ስያሜ አልሆነም ብንል እንደመሳሳት አያስቆጥርም ፡፡

ጭላዳ ዝንጀሮም ለቡድናችን ስያሜ ተመራጭ የሚሆንበት አግባብ አለ ፡፡ አንደኛው ልክ እንደ ዋሊያ የመልኩና የአቋሙ ጉዳይ ነው ፡፡ ጸጉር የሌለው ቀይ ደረቱ በእጅጉ ይስባል ፡፡ ወንዱ አንበሳን ያስታውሳል ፡፡ በጎፈሬው ማለት ነው ፡፡ የጅራቱ ጫፍም ልክ እንደ አንበሳ ጎፈሬያም ነው ፡፡ አፉን እየከፈተ ሲራመድ ያስደነግጣል ፡፡ የጭላዳ ልዩ ባህሪ በጋራና በመንጋ መኖራቸው ነው ፡፡ ቀኑን የሚያሳልፉት እንደ ዋሊያ በመተኛት ሳይሆን በእጃቸው ሳር በመጫር ነው ፡፡ በጣም ‹ ቢዚ › ናቸው ፡፡ አንዳንዴ ርስ በርስ ለመፈታተሸና ሚስት ለመጥለፍ የሚያደርጉት ሩጫና ትግል ምን ያህል ጠንካራ አትሌትና ቡጠኛ መሆናቸውን ያስረዳል ፡፡ ነገረ ስራቸው ሁሉ ስፖርታዊ ነው ፡፡ ታዲያ ለምን ከስፖርቱ ጋር አልተያያዙም ቢባል ከላይ የቀረበው ማስረጃ ያዋጣል ፡፡

በርግጥ ጭምቱ ዋሊያ ፣ ሜዳ ሳይሆን ተራራ ይመቸኛል የሚለው ዋሊያ ፣ ከሌሎች እንስሳት ጋር በሰንበቴና ዕቁብ መገናኘት ያልፈለገው ዋሊያ እንዴት ከኳስ ጋር ተያያዘ ? ከብርቅዬዋቹ እንስሳት ጋርስ በአግባቡ ተወዳድሮ ነው ያሸነፈው ? ይህ ውክልናስ ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት አንጻር ሲታይ ምን ያህል የሰመረ ነው ? ምክንያቱም አዳኝ አይደለም ! ራሱንና ጓደኞቹን አስተባብሮ የሆነ ተዓምር ወይም ለውጥ ለማምጣት ተነሳሽነት የሚታይበት አይደለም ! እንቅልፋም እንጂ ሰራተኛ አይደለም ! ግልጸኝነት ይጎድለዋል ! በቡድን ለመኖርም ሆነ ለመተጋገል የፈጠነ አይደለም ፡፡ ውድ የኢትዮጽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹ ፈሪ ለእናቱ › ብሎ የተደበቀን እንስሳ ፣ በዘመኑ ሂስና ግለ ሂስ ግምገማ ሂሳብ ቢታይ C- ሊያገኝ የሚችልን እንስሳ እንዴት ለብሄራዊ ቡድን መጠሪያነት አበቃችሁት ? በቀለሙ ? በቀንዱ ? በጺሙ ? በተራራ አፍቃሪነቱ ? ነው ዋሊያም በእውቀት ሳይሆን በእምነት የመስራት ሳይንስ ልዩ ዋጋ እንዳላት ተረድቷል ፡፡

የተዘነጉ አማራጮች ‹‹ ዋሊያዋቹ ›› የተባለው ብሄራዊ ቡድናችን ልክ እንደ ዋሊያ

ለ 31 ዓመታት ወደ አፍሪካ ውድድር አልወጣም በማለት ተደብቆ ነበር ፡፡ የእንስሳው ተግባር ተጋብቶባቸው ይሆን ; ደቡብ አፍሪካ ላይስ በ ‹ ዋሊያ › ተግባር ነው ፍልሚያውን እንዲያካሂዱ የሚጠበቀው ? ህብረትና ወረራ ፈጥረው ዝሆን ፣ ነብር ፣ ንስር አሞራ ፣ የበረሃ ተኩላንና የመሳሰሉትን ለማጥቃት የተለየ ስነ ልቦና ሰንቀው ይሆን ? አይታወቅም ፡፡

ኢትዮጽያ ለብሄራዊ ቡድንዋ ልዩ ስያሜ ለማውጣት እንደ ባህር የሰፋ አማራጭ ውስጥ የተቀመጠች ሀገር መሆኗም መጠቀስ ይኖርበታል ፡፡ ብቸኛ ባለ ቋንቋ ሀገር በመሆኗ ‹‹ ፊደል ›› ፣ የቡና መፈጠሪያ በመሆኗ ‹‹ ቡና ›› ፣ ተራራማ ሀገር በመሆኗ ‹‹ ራስ ዳሽን ›› ፣ ጀግና የበቀለባት በመሆኗ ‹‹ አድዋ ›› የሚል ስያሜ ለማውጣት ማን ይከለክላታል ፡፡

ቀደምት የስልጣኔ ባለሟል በመሆኗ ‹‹ አክሱም ›› ፣ የትልቅ ወንዝ ባለሃብት በመሆኗ ‹‹ አባይ ›› ፣ በተአምረኛ ሃውልቷ ‹‹ ላሊበላ ›› ፣ ብሎ ለመጥራትም አማራጭ አለ ፡፡

ተአምር ከሚያሳዩና በቱሪስት በብዛት ከሚጎበኙ ብሄር ብሄረሰቦች ተግባር ውስጥ የጎላውን ማውጣትም ይቻላል ፡፡ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ዘጠኝ ቅርሶቻችንም እኛን ለማስተዋወቅ ዓለማቀፍ መታወቂያ ያላቸው መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል ፡፡

ኢትዮጽያ በተፈጥሮ ድሃ ሳትሆን ድሃ ሆና ቆይታለች ፡፡ በርካታ ወንዞች እያሏት በውሃ ጥም ፣ በኤሌትሪክ ሃይልና በድርቅ ቅጥል ብላለች ፡፡ በዚህ የተለመደ አባባል መሰረት ቆይታችንን ብንገመግመው ከሚከተለው አባባል ጋር ያላትመናል ‹‹ በርካታ ድንቅና ውብ መወኪያ ስም ቢኖራትም ስም ማውጣት አልቻለችም ! ››

ስምን መልዓክ ያወጣዋል የሚባለው አባባላችንና ‹‹ ዋሊያዋቹ ›› ምንና ምን ናቸው ?

ለማንኛውም መልካም ጥቅስ ሳይሆን መልካም ዕድል - ለዋሊያዋች !!!

ጽናት... ከገጽ 10 የዞረ

4. ቁርጥ ያለ እቅድ (Definiteness of plan) ደካማና በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስቸግር ቢሆንም

እንኳን የተቀናጀ እቅድ መንፈሰ ጠንካራነትን ያበለፅጋል፡፡

5. ትክክለኛ እውቀት (Accurate knowledge) የታቀዱት እቅዶች ጥሩ መሆናቸውን ብሎም በልምድና

በእይታ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ማወቅ ለመንፈሰ ጠንካራነት እድገት ጠቃሚ ነው፡፡ ‹‹በእውቀት ሳይሆን በግምት የሚሰራ መንፈሰ ጠንካራነት›› ያጠፋል፡፡

6. ትብብር (Co-operation) ከሌሎች ጋር ሀሳቦችን መለዋወጥ፣ የሌሎችን መረዳትና

የተቀናጀ ትብብር ጠንካራነትን ያዳብራል፡፡ 7. የመሻት ኃይል (Will - Power) በእቅድና አላማ ላይ ትኩረት የመስጠት ልምድ

ወደመንፈሰ ጠንካራነት ያመራል፡፡ 8. ልምድ /Habit/ መንፈሰ ጠንካራነት በቀጥታ የልምድ ውጤት ነው፡፡

አዕምሮአችን ልምዱን እየቀሰመ ከዚያም የዕለት ልምድ እየሆነ ይመጣል፡፡ የጠላቶች ሁሉ ጠላት የሆነው ፍርሃትም ድፍረት በተሞላባቸው ተደጋጋሚ ድርጊቶች ሊወገድ ይችላል፡፡ በጦርነት ላይ ንቁ ተሳታፊ የሆነ ሁሉ ይህን ያውቀዋል፡፡

ከዚህ የጽናት ጉዳይ ሳንወጣ እስኪ እራስህን መርምርና ከነዚህ አስፈላጊ ብቃቶች ያጣኸውን አግኝ፤ ራስህን ነጥብ በነጥብ በድፍረት መዝንና በጽናት ከሚያስፈልጉት ስምንት ነገሮች ስንቱን እንደሌለህ ለማየት ሞክር፡፡ ጥናቱ ስለ ራስህ አዲስ ፍንጭ ሊሰጥህ ይችላል፡፡ ባነተና በስኬት መካከል የቆመውን ጠላት እዛ ጋር ታገኘዋለህ፡፡ እዛ ጋ የመንፈሰ ልልነትህ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በልቡስ ጥላህ ውስጥ ያለውን ምክንያት ታውቀዋለህ፡፡ ዝርዝሩን በደንብ አጥናው፡፡ እራስህን በነዚህ እይና ልታደርግ የምትችለውን እወቅ፡፡ ገንዘብ ያካበቱ ሰዎች ያፈራረሷቸው ድክመቶች እነዚህ ናቸው፡፡

- የምትፈልገውን መወሰን እና ማወቅ አለመቻል፤ - በምክንያት ወይም ያለምክንያት ለውሳኔ መድረስ

መቸገር፤ - ልዩ እውቀትን ለማግኘት ፍላጎት ማጣት፤ - ነገሮችን ከመጋፈጥ ይልቅ ለማምለጥ መወሰን፤ - ለችግሮች መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ምክንያት

መደርደር፤ - በራስ መርካት፡፡ ለዚህ ጉዳይ ምንም ፈውስ የለውም፤

ተጠቃሚውም ተስፋ የለውም፤ - ቸልተኝነት፡፡ ይህ ተቃኒን ከመጋፈጥ ይልቅ ሁልጊዜ

እያቻቻሉ መኖር ነው፤ - በራስህ ስህተት ሌሎችን የመቀወስ ልምድ፤ ችግሮችና

ሁኔታዎቸ ፈጽሞ እንደማይወገዱ አድርጎ መቀበል፤ - የፍላጎት ድክመት፡- ይህ የሚመጣው ሊያስገድደን

የሚችል ነገር በውስጣችን ካለመፍጠር ነው፡፡ - በመጀመሪያው ሽንፈት ለማቆም መዘጋጀት፤ መጓጓት፤ - የተቀናጀ እቅድ እጦት፤ ተጽፎ የተቀመጠ ነገር

ያለመኖር፤ - ሀሳብን ለማንቀሳቀስ ወኔ ማጣት ወይም እድል በሩን

ሲከፍት ለመጠቀም ያለመቻል፤ - ከመፈለግ ይልቅ መመኘት፤ - ከብልጽግናና ከማቀድ ይልቅ ከድህነት ጋር ተቻችሎ

የመኖር ልምድ፤ በጥቅሉ ለመሆን፣ ለመስራት አሊያም ለማግኘት ፍላጎት ማጣት፤

- በአቋራጭ ለመክበር መሞከር፡፡ ለምሳሌ በቁማር፣ በማጭበርበር... ያለምንም ተመጣጣኝ መስዋዕትነት በአቋራጭ ለመክብ መሞከር፤

- ትችትን መፍራት፡፡ እቅድ ማውጣት ያለመቻል እና ወደ ተግባር ለመቀየር ያለመቻል፤ ሌሎች ምን ይላሉ ወይንም ምን ያደርጋሉ፤ የሚለው ምክንያት ማለት ነው፡፡

እስኪ ጥቂት የትችት ፍርሃት ምልክቶችን እንምርምር፡፡ አብዛኛውን ሰው ዘመዶቹ፣ ጓደኞቹ፣ ህብረተሰቡ የራሱን ህይወት እንዳይኖር ተጽዕኖ እንዲያደርጉበት ይፈቅዳል፡፡ ምክንያቱም ትችትን ስለሚፈራ ነው፡፡ ሰዎች አንድ ስራ ለመጀመር እድላቸውን መሞከር ይፈራሉ፤ ምክንያቱም ባይሳካላቸው መተቸትን ስለሚፈሩ ነው፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች የትችት ፍርሃት ከስኬት ጥማት ይጠነክራል፡፡

ትልቅ ግብን ለራሳቸው ማቀድን ብዙ ሰዎች አይደፍሩም ወይም እድገትን መመኘት ቸል ይላሉ፡፡ ምክንያቱም ‹‹ትልቅ ነገር አትመኝ ሰዎች እብድ ነው ሊሉህ ይችላሉ›› የሚለውን የዘመዶች እና የጓደኞች ትችትን ይፈራሉ፡፡ ብዙ ሰዎች የገንዘብ ስኬት ‹‹የውድቀት›› ውጤት ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ለዚህ እምነት ጥቂት መሰረት አለው፡፡ ነገር ግን በዕድል ላይ የተመሰረተ ከሆነ ውጤቱ በአብዛኛው ያስከፋል፡፡ ምክንያቱም ስኬት ከመምጣቱ በፊት መኖር (ጽናት... ወደ ገጽ 11 የዞረ)

Nuru Dedefo, ESQNuru Dedefo, ESQNuru Dedefo, ESQ... Attorney at Law & CounselorAttorney at Law & CounselorAttorney at Law & Counselor

If you have legal issues, If you have legal issues, If you have legal issues,

you need a lawyer who you need a lawyer who you need a lawyer who

fights for your rights. fights for your rights. fights for your rights.

Nuru Dedefo fights for Nuru Dedefo fights for Nuru Dedefo fights for

your rights.your rights.your rights.

--- Car AccidentsCar AccidentsCar Accidents

--- Work place injuriesWork place injuriesWork place injuries

--- ImmigrationsImmigrationsImmigrations

--- Family LawFamily LawFamily Law

--- Criminal LawCriminal LawCriminal Law

If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:

3989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 554213989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 554213989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 55421

(763)(763)(763)---781781781---5254 (office), (6125254 (office), (6125254 (office), (612---559559559---0489) Cell0489) Cell0489) Cell

(763)(763)(763)---781781781---5279 Fax5279 Fax5279 Fax

ነጻ ፓርኪንግ ከሬስቶራንታችን ፊት

ለፊት ዩኤስ ባንክ ፓርኪንግ

ባርሴሎና በአሁኑ ወቅት ብዙ ተጨዋቾችን ከአካዳሚው በማፍራት በአውሮፓ በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡ የካታላኑ ክለብ 38 ተጨዋቾችን ከላ ማሲያ ማፍራት ችሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ አሁንም በባርሳ ሲገኙ 24ቱ ደግሞ በተለያዩ ክለቦች እየተጫወቱ ናቸው፡፡ አንድ ክለብ ተጫዋች አወጣ የሚባለው ተጫዋቹ በአካዳሚው ሶስት ዓመታት እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ በማጎልበት ፕሮግራም ሲያልፍ ነው፡፡ በተለይ ይህ የሚሆነው በእግርኳስ እጅግ ወሳኝ

የማደጊያ የዕድሜ ክልል በሚባሉት ከ15-21 ባሉት ጊዜያት ነው፡፡ ባርሳ ካፈራቸው 38 ተጨዋቾች መካከል 36ቱ ሙሉ ለሙሉ በክለቡ ሂደት ውስጥ ያለፉ ወይም በሌላ አገላለፅ በባርሳ ከ15-21 ዓመታቸው ውስጥ ከሶስትና በላይ ዓመታት ያሳለፉበት የመጀመሪያ ክለባቸው

የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ የተለያዩ ክስተቶችን አሳይቶናል፡፡ ከመሪው ማንቸስተር ዩናይትድ መ ጨረሻ ደረጃ ላይ እስከሚገኘው ኪው.ፒ.አር ምርጥ ብቃታቸውን ያሳዩ ተጫዋቾችም አሉ፡፡ እነማ ናቸው?

አርሰናል፡- ሳንቲ ካዞርላ በትዕግስት ለሚጠብቁ መልካ ም

ነገሮች መድረሳቸው አይቀርም፡፡ በ2011 አርሰን ቬንገር ሳንቲ ካዞር ላን ለማስፈረም ሞክረው ነበር፡፡ ከ12 ወራት በኋላ የማላጋ የገንዘብ ጡንቻ በመዳከሙ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ፕሌይሜከሩን ከቀድሞው ባነሰ ዋጋ አግኝተውታል፡፡ ‹‹ትንሹ›› ስፔናዊ አርሰናል ምርጥ ተጫዋቾች ን አያስፈርምም የሚለውን እሳቤ የሚያፈርስ ብቸኛው ተጫዋች ነው ፡፡ ፈረንሳዊው ሲያስፈርሙት ካሰ ቡት በላይም ጎል አስቆጣሪ ነው፡፡ ቬንገር ላይ ጫናው በበረታባቸው ወቅት ካዞርላ ሬዲንግ ላይ የሰራው ሀት-ትሪክ ጊዜውን የጠበቀ ነበር፡፡ በውድድር ዘመኑ የአርሰናል ምርጥ ድሎች በሆኑት የሊቨርፑል እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ግጥሚያዎች ላይ ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡

ቼልሲ፡- ሁዋን ማታ የቼልሲ የቅድመ ውድድር ዘመን እቅድ አንድ

ስፔናዊን ውጤታማ ማድረግ ከሆነ ተሳክቷል፡፡ አይኖች ሁሉ ያረፉት ፈርናንዶ ቶሬስ ላይ ቢሆንም ሁዋን ማታ ያገሩን ልጅ አልፎት ሄዷል፡፡ እንደ እርሱ ተመሳሳይ ተሰጥኦ ያላቸው ኦስካር እና ኤዴን ሀዛርድ ስታምፎርድ ብሪጅ መድረስ ቢመቸውም ማታ ፈጣሪ ከሆኑት ተጫዋቾች ምርጡ ሆኗል፡፡ በሴፕቴምበር እና ኦክቶበር ምርጥ ጊዜን አሳልፏል፡፡ በሁለቱ ወራት ስድስት ጎሎችን አስቆጥሮ በአምስት ጨዋታዎች አምስት ጎል የሆኑ ኳሶችን አቀብሏል፡፡ በውድድር ዘመኑ ምርጥ መሆኑም አስመስክሯል፡፡

ፉልሃም፡- ዲሚታር ቤርባቶቭ እግርኳስን በራሱ መንገድ ብቻ ይጫወታል፡፡

የሚገዛውም በራሱ ህጎች ብቻ ነው፡፡ ፉልሃም እና ማርቲን ዮል የዲሚታር ቤርባቶቭን ወጣ ያለ ባህሪይ

የሚያከብሩ ብቻ ሳይሆኑ የፈለገውን እንዲያደርግ የሚፈቅዱለት ክለብ እና አሰልጣኝ ሆነውለታል፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ በኳስ ቁጥጥሩ ምርጡ ሊሆን ይችላል፡፡ በ10 ቁጥር ሚና የሚጫወተው ቡልጋሪያዊ በፕሪሚየር ሊጉ በእያንዳንዱ ጨዋታ ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል፡፡

ሊቨርፑል፡- ልዊስ ሱአሬዝ ብዙ ቡድኖች በብቸኛ አጥቂ ቢጫወቱም አንድ

አጥቂ ብቻ ያላቸው ክለቦች ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ የሊቨርፑል ባለፈው ክረምት ተጨማሪ አጥቂ የማስፈረም ሩጫ በዝውውር ቀኑ መጨረሻ ላይ ያለስኬት ሲጠናቀቅ እና ፋቢዮ ቦሪኒ ሲጎዳ በልዊስ ሱአሬዝ ትከሻ ላይ የነበረው ጫና ይበልጥ ገዘፈ፡፡ እርሱም በሚገባ ተቋቁሞታል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን የበዙ የጎል ዕድሎችን በማምከን የተተቸው አጥቂ ዘንድሮ ከከፍተኛ ጎል አግቢዎች ዝርዝር ስሙ አልጠፋም፡፡ ከጎሎቹም በላይ ሱአሬዝ ለፕሪሚየር ሊጉ ሌሎች ነገሮችንም አበርክቷል፡፡

ማንቸስተር ሲቲ፡-ፓብሎ ዛባሌታ

ግራ በሚያጋባው የዘንድሮው ማንቸስተር ሲቲ ከምርጦቹ ተጫዋቾች ጥቂቶቹ ብቻ የማ ይዋዥቅ ብቃት አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን ፓብሎ ዛባሌታ 100% ለቡድኑ ራሱን ሰጥቷል፡፡ አርጀንቲናዊው ሲቲ ከቼልሲ ጋር ያለ ጎል ባጠናቀቀው ግጥ ሚያ የጨዋታው ኮከብ ነበር፡፡ በትልልቅ ግጥሚያዎች ምርጥ መሆኑን እና በውድድር ዘመኑ ሚካህ ሪቻርድስ አለመኖሩ ችግር እንደማ ይፈጥር በብቃቱ አስመስ ክሯል፡፡ በማንቸስተር ደርቢ ደግሞ ሲቲን ከተመሪነት ወደ አቻነት ያሸጋገረች ጎል አስቆጥሯል፡፡ አምበል ሲሆን ከወትሮ በተለየ እንደሚ ጫወትም ታይቷል፡፡ የአቻነት ጎሏ ግን ሲቲን ነጥብ እንዲያገኝ በቂ አልነበረኝም፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ በመጨረሻው ደቂቃ ጎል ሲያስቆጥር ዛባሌታ የግብ ቋሚውን ተደግፎ ያዘነበት መንገድም

ለቡድኑ ራሱን ምን ያህል እንደሰጠ ያሳየ ነበር፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ፡-ሮቢን ቫን ፔርሲ ያለፈው የውድድር ዘመን የሮቢን ቫን ፔርሲ

ጥራት እና የማይዋዥቅ ብቃት ብዙዎችን አስደንቆ ሊሆን ቢችልም የዘንድሮው አቋሙ ደግሞ የተለመደ ይመስላል፡፡ ይህ ምናልባትም ዘንድሮ በምርጥ ተጨዋቾች ስለተከበበ ወይም ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ በ24 ሚሊዮን ፓውንድ ሲዘዋወር የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል አግቢ ስለነበር የተፈጠረ ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ቫን ፔርሲ ጎሎችን ማዝነቡን ቀጥሏል፡፡ ጎሎቹ ከብዛት እና ጥራታቸውም በላይ ወሳኞች ናቸው፡፡ ቡድኑ በሳውዛምፕተን 2-0 ሲመራ ሃት-ትሪክ በመስራት እንዲያሸንፍ አድርጎታል፡፡ ሊቨርፑል ላይ የፍፁም ቅጣት ምት አግብቷል፡፡ አርሰናል ላይ የመክፈቻዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሲቲ ላይ በመጨረሻው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎል አግብቷል፡፡

ሙሉውን የፕሪምየርሊጉን ስታሮች ለማየት ወደ ድረ ገጻችን www.zehabesha.com ይግቡ።

ዳኒ ከሚኒያፖሊስ ባለፈው ዕትም በአሜሪካን እግር ኩዋስ ዓለም

ሲከናወን የነበረውን በተለይም ከ 12-15ኛው ሳምንት ውስጥ የነበረውን ክንዋኔ አብረን ተከታትለናል። በዚህ እትም ከ 16ኛው ሳምንት ጀምሮ እስከ ዋንጫ ድረስ የተከናወኑትን ዜናዎች ላካፍላችሁ ተዘጋጅቻለሁ። አብራችሁኝም እንደምትከታተሉ ተስፋ አለኝ።

በ 16ኛው ሳምንት ታዋቂው የቫይኪንግስ(vikings) ሯጭ ኤድሪያን ፒተርሰን(AP) 86 ያርድ በመሮጥ ቫይኪንግስ(vikings) 23 ለ 6 ሂዩስተን ቴክሳንስን(Houston Texans) እንዲያሸንፉ ምክንያት ከመሆንም ባሻገር ለጥሎ ማለፍ እንዲቃረቡ ረድቶዋቸዋል። የ vikings ወርዋሪ (አከፋፋይ) ክ ር ስ ቲ ያ ን ፖን ደር ለ ቶ ቢ ጌ ር ሃ ር ት በማቀበልየመጀመሪያውን ግብ እንዲያስቆጥር አድርጎታል። ሚኒሶታ ቴክሳንስን(Texans) ማሸነፋቸው የሞራል ብርታትን እንዲጎናፀፉ ብቻም ሳይንሆን የረዳቸው ለ17ኛው ሳምንት ከምድባቸው አንዱ የሆነውን ግሪን ቤይ ፓከርስን(Green Bay Packers) ለማሸነፍ ብቃት እንደሚኖራቸው አረጋግጦላቸዋል።

17ኛው ሳምንት በብዙ ሚኒሶታም(Minnesota) ሆነ የ ጎረቤታችን ዊስካንሰን(Wisconsin) ደጋፊዎች በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ግጥሚያ ነበር። ጨዋታው የተካሄደው በሚኒያፖሊስ ከተማ ነበር። ይህ ቀን ለvikings ማሸነፍ ያለባቸው ቀን ብቻም ሳይሆን ነገር ግን በብዙ NLF አፍቃሪዎች ሲጠበቅ የነበርው ታዋቂው vikings ሯጭ በ Eric Dickerson ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ሲሰብር ማየት ነበር። ነገር ግን ፒተርሰን ሪከርዱን

ለመስበር 9 ያርድ ብቻ ቀርቶት ጨዋታው ተገባዱዋል። ለ ፒተርሰን ⶸዋታውን ማሸነፍ የመጀመሪያ አላማው ስለነበረ ምንም ሪከርዱን ባይሰብርም ⶸታውን 37 ለ 34 አሸንፎ ለጥሎ ማለፍ በማለፉ ደስ ተሰኝቷል። vikings ይህን ቀን በማሽነፋቸው ግሪን ቤይ ፓከርስን(Green Bay Packers) ለመቸረሻ ግዜ በሜዳቸው በመሄድ በሳምንቱ(18ኛው) ሳምንት ግጥሚያ እንደሚያደርጉ በማሰብ ቀኑን አገባደዋል።

Vikings እና Packers ሳስብ ማኑ(Manu) እና ቸልሲ(Chelsea) ትዝ ይሉኛል። Packers ከሳምንት በፊት በvikings መሸነፋቸው እልህ ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው ይመስል ነበር።

በተለይም የ Packers ወርዋሪ ራጀርስ(Rogers) ቂም ለመበቀል ቆርጦ የተነሳ ይመስልም ነበር። እንደ ምድብ ያሉ ሁለት ጠንካራ ቡድኖች ሲታገሉ ማየት የማንኛውም ስፖርት

አፍቃሪ ምኞት ነው። Packers እንደፎከሩ እልሃቸውን በሜዳቸው ለመወጣት ዝግጅት ያደረጉ መሆናቸውን በመጀመሪያዎቹ 30ደቂቃ ውስጥ ውጤት በማምጣት አሳይተዋል። ለሚኒሶታ መሸነፍ ወሳኙ ምክንያት ይሆናል ብዬ የማስበው ባልተጠበቀ ሰዓት የ vikings ወርዋሪ(አከፋፋይ) ፖንደር(Poder) በጉዳት ምክንያት ባለመሰለፉ ብዙ ውጤትን እንዳናመጣ አድርጎናል። ተተኪው ወርዋሪ ጆ ዌብ(Webb) ከልምድ ማነስ የተነሳ የ Packersን ጎበዝ ተከላካዮች በችሎታ መብለጥ ባለመቻሉ ሚኒሶታ እንዲሸነፉ እና ከጨዋታ ውጭ እንዲሆኑ ምክንያት ሆኑዋል።

ይህ 2012 የጨዋታ ወቅት ለ vikingsም ሆነ ለ ፒተርሰን ያልተጠበቀ እና የሚያስመሰግን ወቅት ነበር ብዬ እገምታለሁ።

ግሪን ቤይ ፓከርስን(Green Bay Packers) ሚኒሶታን

ቢያሸንፉም ነገር ግን በተከታዩ ሳምንት ሳን ፍራንሲስኮ ሄደው በ49ers ሊሸነፉ ችለዋል። ባለፈው ቅዳሜ(January 12) ባልትሞር(Baltimore Ravens) ዴንቨር (Denver Broncos) ን ሲያሸንፍ ሳን ፍራንሲስኮ(San Francisco) 49ers ደግሞ Packersን አሸንፏል። እዲሁም በ እንዲህ እንዳለ ባለፈው እሁድ አትላንታ(Atlanta) ሲያትልን አሸንፎ New England ቴክሳንስን(Texans) በማሸነፍ 4 ቡድኖች ቀርተዋል። አሁን ባሳለፍነው እሁድ(January 20th) ፍራንሲስኮ ሄደው በ49ers አትላንታን 28 ለ 24 በማሸነፍ NFCን ዋንⶻ ሲደርስ ባልትሞር(Baltimore) New Englandን 28-13 በማሸነፍ AFCን ወክሎ ለዋንⶻ ደርሱዋል። የዋንጫ ጨዋታው የሚደረገው February 3rd 5:30PM በ ኒው ኦርልያንስ ሉዊዚያና(New Orleans, Lou-isiana) ከተማ ሲሆን ይህን ቀን ልዩ የሚያደርገው የሁለቱም

ቡድን አሰልጣኞች ወንድማማቾች መሆናቸው ነው። ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ ችሎታ ስላላቸው የትኛው

ቡድን ያሸንፋል የሚለውን ጥያቄ መመለስ ቢያዳግትም ነገር ግን እንተንብይ ከተባለ ባልትሞር ሬቨንስ(Ravens) በጥቂት ነጥብ ያሸንፋል ብዬ እተነብያለሁ።

ባለፉት 2ወራት የአሜሪካን እግር ኩዋስ ዓለምን አብረን ስንከታተል ቆይተናል።

በዚህ አጋጣሚም ይህንንም ሆነ ከዚህ በፊት የፃፍኩትን በማንበብም ሆነ አስተያየት በመስጠት አብራችሁኝ በመሆናችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። February 3rd ለዋንጫ የሚደረገውን Super Bowl 47ን ለማየት እንዳትረሱ በማለት ጽሁፌን አገባድዳለሁ።

ዳኒ ከሚኒያፖሊስ። [email protected]

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

በቻምፒየንስ ሊጉ የእንግሊዝ ክለቦች

ወደ ሩብ ፍፃሜው መግባት ይችሉ ይሆን?

የቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ለእንግሊዛዊያን ክለቦች አስጨናቂ ይመስላል፡፡ ከ1995/96 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድም የእንግሊዝ ክለብ በሩብ ፍፃሜው ላይታይ ይችላል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲ፣ ሊቨርፑል እና አርሰናል በግማሽ ፍፃሜ ደርሰው ተሸንፈዋል፡፡ ቼልሲ ዋንጫውን በ2012 ቢያነሳም የቦሩሲያ ዶርሙትድ፣ ጁቬንቱስ እና ሻክታር ዶኔትስክ ዋነኛ ተፎካካሪ መሆን እና የባርሴሎና፣ ሪያል ማድሪድ እና ባየርን ሙኒክ አንሸራትቷቸዋል፡፡ ዘንድሮ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ ከምድባቸው እንኳን ማለፍ አልቻሉም፡፡ ማድሪድ እና ባየርን ከአውሮፓ ሶስት ምርጥ ክለቦች መካከል ከተመደቡ የዩናይትድ እና አርሰናል እጣ ፈንታ ከወዲሁ የተወሰነ ይመስላል፡፡ እስኪ የእንግሊዝ ክለቦች ወደ ሩብ ፍፃሜው መግባት ይችሉ እንደሆነ እንመልከት፡፡

ማን.ዩናይትድ- ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ለመጨረሻ ጊዜ ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ

የተገናኙት በ2003 ነበር፡፡ በግጥሚያው በሳንቲያጎ ቤርናቢዩ ራኡል ጎንዛሌዝ በኦልድትራፎርድ ደግሞ ሮናልዶ ድንቅ ሆነው አመሹ፡፡ የጋላክቲኮዎቹ (ቻምፒዮንስ... ወደ ገጽ 18)

ሮናልዶ የቀድሞ ክለቡን ማን.ዩናይትድን ሲገጥም ለማየት ብዙዎች በጉጉት እየጠበቁ ነው።

ደረጃ

ክለብ ሀገር በክለቡ ሙሉ ለሙሉ ያደጉ

ሁለተኛ ክለባቸው

ድምር በክለቡ የሚገኙ

በሌላ ክለብ

የሚገኙ

1 ባርሴሎና ስፔን 36 2 38 14 24 2 ሊዮን ፈረንሳይ 29 2 31 10 21 3 ሪ.ማድሪድ ስፔን 27 2 29 8 21 4 ሬን ፈረንሳይ 21 3 24 7 17 5 ማን.ዩናይትድ እንግሊዝ 20 4 24 9 15 6 ባ.ሙኒክ ጀርመን 21 2 23 7 16 13 አርሰናል እንግሊዝ 14 6 20 6 14 46 ማ.ሲቲ እንግሊዝ 12 0 12 3 9 51 ቼልሲ እንግሊዝ 11 1 12 2 10 60 ሊቨርፑል እንግሊዝ 10 0 10 7 3

ደረ

ክለብ በክለቡ ሙሉ

ለሙሉ ያደጉ

ሁለተኛ

ክለባቸው

ድምር አሁንም

በክለቡ

የሚገኙት

1 ማን.ዩናይትድ 20 4 24 9

2 አርሰናል 14 6 20 6

3 አስቶንቪላ 15 0 15 8

4 ቶተንሃም 13 2 15 8

5 ዌስትሃም 13 0 13 5

6 ኒውካስል 11 2 13 8

7 ማን.ሲቲ 12 0 12 3

8 ሳውዛምተን 11 1 12 5

9 ቼልሲ 11 1 12 2

10 ሊቨርፑል 10 0 10 7

ነው፡፡ ሊዮኔል ሜሲ፣ አንድሬስ ኢኒዬሽታና ካርሎስ ፑዮል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በባርሳ አድገው አሁን በሌላ ክለብ ውስጥ ከሚገኙት 24 ተጨዋቾች ኦሪዮል ሮሚዮ በቼልሲ፣ የሊቨርፑሉ ፔፔ ሬይና እንዲሁም የአርሰናሉ ሚኬል አርቴታ ከላማሲያ ምሩቆች መካከል ይመደባሉ፡፡ ከ38ቱ ሁለቱ ተጨዋቾች አይሳክ ኩኤንካና ክሪስቲያን ቲዮ የመጀመሪያ ክለባቸው በተከታታይ ሲኤፍ ሪዮስና ኤስፓኞል በመሆኑ ባርሳ እንደ ሁለተኛ አሳዳጊ ክለባቸው ይቆጠራል፡፡ በአውሮፓ ምርጥ አምስት ታላላቅ ሊጎች ባርሳን ተከትለው ሊዮን (31) ሪያል ማድሪድ (29)፣ ሬን (24) እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትድ (24) በተከታታይ ተቀምጠዋል፡፡ በአውሮፓ ብዙ ተጫዋቾችን ያፈሩ ክለቦች (ከላይ የቀረቡትን ሁለት ሰንጠረዦች ይመልከቱ) ሁለተኛ ክለባቸው የሚለው ተጨዋቾቹ ከ15-21 ዕድሜያቸው ወደ ክለቡ መጥተው ያደጉ ናቸው፡፡ በእንግሊዝ ከፍተኛ አምስት ዲቪዚዮኖች ከሚወዳደሩ 98 ክለቦች መካከል ዩናይትድ 24 ተጨዋቾችን ከአካዳሚው በማውጣት ቀዳሚው ሆኗል፡፡ ከእነዚህ ተጨዋቾች ውስጥ ዘጠኙ አሁንም በዩናይትድ ይገኛሉ፡፡ ጆኒ ኢቫንስ፣ ሪያን ጊግስ፣ ፖል ስኮልስ፣ ቶም ክሌቨርሊና ዳኒ ዌልቤክ የሰር አሌክስ ፈርጉሰኑን ቡድን እያገለገሉ ናቸው፡፡ በዩናይትድ አካዳሚ ውስጥ አልፈው አሁን በሌሎች ክለቦች ከሚገኙት መካከል ፊል ኔቭል በኤቨርተን፣ ኪዮራን ሪቻርድሰን በፉልሃም፣ ሮን-ሮበርት ዚለር በሀኖቨር፣ ፖል ፖግባ በጁቬንቱስ እንዲሁም ሪያን ሾውክሮስ በስቶክ ሲቲ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ዩናይትድ ከአካዳሚው ካወጣቸው 24 ተጨዋቾች ውስጥ አራቱ ከ15-21 ዕድሜ መካከል በሚገኙበት ወቅት አካዳሚውን የተቀላቀሉ ናቸው፡፡ እነዚህን ተጨዋቾች ዩናይትድ ከሌላ ክለብ በማምጣት እንዲጎለብቱ ወሳኝ ሚናን ተወጥቷል፡፡ ራፋኤልና ፋቢዮ ዳ ሲልቫ፣ ዌይን ሩኒና ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚህ ጎራ የሚካተቱት አራቱ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ ዩናይትድን ተከትለው አርሰናል (20)፣ አስቶንቪላ (15)፣ ቶተንሃም (15)፣ ዌስትሃምና ኒውካስል እያንዳንዳቸው (13) እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ፣ ሳውዛምፕተንና ቼልሲ (12) ተቀምጠዋል፡፡

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ከኢሳያስ ከበደ ደስተኛ ለመሆን የነደፍኩት ፕሮጀክት

ከሚመለከታቸው አበይት ጉዳዮች መካከል አንዱ የትዳር ህይወቴ ነው፡፡ እንደ በርካታ ሰዎች ትዳር ለእኔም የሕይወቴ፣ የቤተሰቤና የደስታዬ ዋነኛ አላባዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

ደስተኛ ህይወት ለመኖር የወጠንኩትን ፕሮጀክት ስጀምርና በህይወቴ መለወጥ ስለምፈልጋቸው ነገሮች ሳሰላስል በትዳሬ አምስት የተለያዩ ችግሮች እንዳሉብኝ ልገነዘብ ችያለሁ፡፡ ምንም እንኳን ፈታኝ ቢሆኑም፣ ችግሮቹና ልቋቋማቸው የነደፍኳቸው ስትራቴጂዎች ቀጣዮቹ ናቸው፡፡

1. ምስጋናና ሙገሳ መፈለግ መቼስ፣ ምስጋናንና ሙገሳን የማይፈልግ

ሰው በዚህች ምድር ማግኘቱ አስቸጋሪ ነው፡፡ እኔ ደግሞ የቤት ውስጥ ስራዬን በሰራሁ ቁጥር ከባለቤቴ ምስጋናንና ሙገሳን እጠብቃለሁ፡፡ በዚህ ረገድ ግን ባለቤቴ ደካማ መሆኑ ያናድደኛል፣ የሰራሁት ስራም ተቀባይነት ያላገኘ ይመስለኛል፡፡

ለዚህም ምላሽ እንዲሆን በአሁኑ ወቅት ይበልጡኑ ነገሮችን ለራሴ ብዬ ለመስራት እያሰብኩ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም፣ ‹‹መጻህፍቱን በየቦታው ማስቀመጤን ሲያይ ደስ ይለዋል››፣ እንዲሁም ‹‹መኪናዋን ለጉዟችን በሚያስፈልጉት እቃዎች በመሙላቴ ይደሰታል››፣ ወዘተ... በማለት ለባለቤቴ ጥሩ ነገሮችን እያደረግሁ እንደሆነ ለራሴ እነግረው ነበር፡፡ ሳያመሰግነኝ ሲቀር ግን በንዴት እጦፋለሁ፡፡ አሁን ግን እነኚህን ነገሮች የማደርገው እኔ ስለፈለግሁ እንደሆነ ለራሴ እየነገርኩት ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ ‹‹እንዴ፣ የማእድ ቤቱ መሳቢያዎች በሙሉ ጽዱ ሆነዋል!››፣ ‹‹አስቤዛችንን ሳያልቅ መግዛቴ ጠንቃቃ እንደሆንኩ ያሳያል!›› የሚሉትን የመሰሉ አስተያየቶች ለራሴ መናገር ጀምሬያለሁ፡፡ ነገሮችን ለራሴ ስል ስለማደርግ ባለቤቴ በማንኛውም መልኩ ምላሽ ይሰጠኛል ብዬ አልጠብቅም፡፡

2. ቆጣ ብሎ መናገር በተፈጥሮዬ ግልፍተኛ በመሆኔ በቀላሉ

ቱግ እላለሁ፤ ይሁንና ባለቤቴ በቁጣ አንደበት ስናገር ደስ አይለውም፡፡ ይህን ጻባዬን ለመቆጣጠር ብዙ ነገሮችን ሞክሬያለሁ፡፡ በጣም እሰኪርበኝና እስኪበርደኝ ድረስ አልጠብቅም (ከነኚህ ሁኔታዎች ላይ የምደርሰው በቀላሉ ነው) ምስቅልቅል ወይም ዝርክርክ ያለ ነገር ስለሚጨንቀኝ

የምንኖርበትን አፓርታማ በተቻለኝ አቅም ሁሉ ስርዓት ያለው እንዲሆን እጥራለሁ፡፡ ባለቤቴ ቁጣዬን በተመለከተ ቀልድ ቢጤ ጣል ለማድረግ ሲሞክር አብሬው ለመሳቅ እሞክራለሁ፡፡ ድምፄ ትዕግስት የለሽ ወይም ወቃሽ እንዳይመስል ቀለል ያለና አስደሳች ላደርገው እሞክራለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ለዓመታት በጽናት ብታገልም፣ አሁንም ድረስ ያስቸግረኛል፡፡

3. በቂ ግምት አለመስጠት የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣

ባለትዳሮች አንዳቸው ለሌላኛው ካላቸው የበለጠ ትህትና ለሌሎች ሰዎች ያሳያሉ፡፡ እኔም ብሆን ለባለቤቴ ብዙም ትህትና አላሳየውም፡፡

ያም ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ መሰረታዊ ለውጦችን እያደረግሁ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ እቤት ሲገባና ሲወጣ ሞቅ ያለ ሰላምታ እሰጠዋለሁ፣ ከሱ ጋር በስልክ እያወራሁ እያለ ሌላ ነገር አልሰራም፡፡

4. ነጥብ ያዥነት

እኔ በበኩሌ አንዳችን የሰራነውን ነገር በተመለከተ ሁሌ ነጥብ እንደያዝኩ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ ባለቤቴን ‹‹ወጥ ቤቱን ስላፀዳሁ፣ ‹‹አስቤዛ የምትገዛው አንተ ነህ›› እለዋለሁ፡፡ ይህን ዝንባሌ ለመታገል ሁለት ዘዴዎችን አግኝቻለሁ፡፡

በቀዳሚነት፣ ለምናበረክተው አስተዋፅኦ ሳናውቀው ከሌሎች ሰዎች አንፃር የተጋነነ ግምት እንደምንሰጠው ራሴን አስታውሰዋለሁ፡፡ በእርግጥ፣ ሌሎች ሰዎች ከሚሰሩት ነገር ይልቅ እኛ ስለምናከናውነው ነገር የበለጠ ግንዛቤ ስለሚኖረን ይህ አባባል ትክክል ነው ማለት ይቻላል፡፡ The Happi-ness Hypothesis መጽሐፍ ደራሲ ጆታናን

ሄይድን እንደሚሉት፣ ‹‹ባሎችና ሚስቶች እያንዳንዳቸው ስለሚሰሩት የቤት ውስጥ ስራ መቶኛ ሲያሰሉ ግምታቸው ከ120 በመቶ በላይ ይመጣል›› የመብራት፣ የጋዝና የውሃ የመሰሉ ሂሳቦችን ለመክፈል ስለማቃጥለው ጊዜ ቅሬታዬን ብገልፅም፣ ባለቤቴ መኪናችንን ለማሳደስ የሚያቃጥለውን ጊዜ ከግምት ውስጥ አላስገባውም፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ በባለትዳሮች መካከል ቅሬታንና የተጋነነ የይገባኛል ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ስለዚህም፣ ‹‹እንዲህ ለማድረግ የምቸገረው እኔ ብቻ ነኝ›› ወይም ‹‹ለምንድን ነው እኔ ሁሌ...›› ከማለት ይልቅ ስለማላደርጋቸው ሰዎች ራሴን አስታውሰዋለሁ፡፡

በሁለተኛው ደረጃ የመንፈሳዊ መሪዬን የሊሲዬዋ ቅድስት ቴሬስን፣ ‹‹አንድን ሰው ስናፈቅር ስሌት ማድግ የለብንም›› የሚለውን አባባል ራሴን አስታውሰዋለሁ፡፡ ስለዚህም፣ ትዳሬን በተመለከተ በስሌት መመራት የለብኝም፡፡

5. ባለቤቴን ችላ ማለት ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ሁሉ፣

ባለቤቴ የሚያከናውናቸውን የቤት ውስጥ ስራዎች በተመለከተ በርካታ በጎ ጎኖቹን በመተው ለህፀፆቹ ትኩረት እሰጣለሁ፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ በቁጣ ቃል አለመናገሩ ቢከብደኝም፣ ባለቤቴ አንድም ጊዜ በዚህ መልኩ አናግሮኝ አለማወቁ አንድ የሚያስመሰግነው ነገር ነው፡፡ ባለቤቴን የምወድባቸውን ነገሮች በንቃት ለመከታተልና በትንሽ ትልቁ መበሳጨቱን ለመተው እየሞከርኩ ነው፡፡ ይሁንና፣ ይህን መተግበሩ ቀላል አልሆነልኝም፡፡

ከባለቤቴና ከልጆቼ ጋር ፍቅር አዘል በሆነ መልኩ የትዳር ህይወቴን ለመግፋት ከበፊቱ ይበልጥ መሳሳም፣ መተቃቀፍና መደባበስ ውጤታማ እንደሆነ ደርሼበታለሁ፡፡ የትዳሬን ሳንካዎች ለማስወገድ ተግባራዊ ከማደርጋቸው መፍትሄዎች መካከል አንዱ ይኸው ይበልጥ መሳሳም፣ መተቃቀፍና መደባበስ ነው፡፡ ይህን መፍትሄ መተግበሩ ምንም አይነት ተጨማሪ ጊዜ፣ ጉልበት ወይም ገንዘብ አይጠይቅም፡፡ ከዚህም በላይ በትዳሬ

‘ፍቅር እና ወንጀል” በሚለው አምዳችን በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ እዚህ አሜሪካ ውስጥ የሚፈጸሙ እውነተኛ የፍቅርና የወንጀል ታሪኮችን እንዲሁም ሌሎችን ዘገባዎችን እናቀርብበታለን።

ኬክ ጀምረናል

651-214-2584 ወይም 651-489-9220 ደውሉ

የጤፍ እንጀራችን ለምን ተወዳጅ

እንደሆነ ለማረጋገጥ ዛሬውኑ

በተለያዩ ስታይሎች ተኩስና ሹሩባ እንሰራለን የስፓ አገልግሎታችን ልዩ ነው ሙሽራ እንሞሽራለን የፀጉር ቀለም፣ ቁርጥ፣ ጸጉር መቀጠልና ሌሎችም አገልግሎቶች አሉን

Global Braids Salon፡ 1821 University Ave, Suit 130

St. Paul, MN 551004 651-646-5854

911 ሥራ የማይፈታው

የአሜሪካ የመረጃ ማዕከል

ከጥላሁን ብርሃኑ 9.1.1 በአሜሪካ

የሚገኝ ነፃ የስልክ ጥሪ ሲሆን ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥሪዎች፣ ለድንገተኛ አደጋ ጥሪዎች በከተማው ውስጥ እያገለገለ ይገኛል፡፡ የእሣት አደጋ ጥሪዎች እና የህክምና እርዳታ ጥሪዎች እንዳመጣጣቸው ግዜ ሣይወስዱ ወደየሥራ ክፍሎቹ እንዲሠራጩ ያደርጋሉ፡፡ ይህ የ911 አገልግሎት በሠባቱም ቀናት ያለማቋረጥ ለ24 ሰዓታት ይሰራል፡፡ በዚህም በአንድ ቀን አሁን ባለው መረጃ ከ800ሺህ እስከ 870ሺህ ጥሪዎችን ይቀበላል፡፡

የዚህን አገልግሎት ውጤታማነት ለማሻሻል አሜሪካዊያኑ ሁለት የስልክ መቀበያ ሂደቶች ተጠቅመዋል፤ ቀዳሚው ኦፕሬተር እስከ 160 ሴኮንድ እና ከዚያ በታች የሆኑትን ጥሪዎች ያስተናግዳል፡፡ ነገር ግን ከ60 ሴኮንድ በላይ ከሆነ ለሁለተኛው የስልክ ኦፕሬተር እንዲዛወር ያደርገዋል፡፡ ይህ ሁለተኛ ኦፕሬተር የተቀበለውን መረጃ በመያዝ ለሚመለከተው ክፍል መረጃውን በመስጠት በተፋጠነ ሂደት የግለሠቦቹን ችግር ይፈታል፡፡

ሁለተኛውም ይሁን አንደኛው የስልክ ጥሪ ተቀባይ ስለ አንድ ደዋይ የሚፈልገውን መረጃ መጠየቅ ወይም በሀሰት የተለያዩ አደጋዎች ደርሰዋል የሚሉ ወይም ቀላል የሆኑ የእርስ በርስ ግጭቶችን የያዙ ሊሆን ይችላሉ፡፡

ሁሉም የድንገተኛ ጥሪዎች ወደ አውቶማቲክ ማከፋፈያ (CAD) በፓዚትሮን ፓወር 9.1.1ውስጥ ያልፋሉ፡፡ በዚህም የስራ ጫናዎችን በማየት ለሁሉም ኦፕሬተሮች ጥሪዎቹን ያከፋፍላል፡፡

እነዚህም ስራዎች በcompoter Aidld dispatch system (CAD) በመጠቀም የሚመጡ ጥሪዎች ከየት አካባቢ የተደወለበትም ቁጥርንም ጭምር ለማየት እና መረጃን በፍጥነት ለመቀያየር ይጠቀሙበታል፡፡ የፖሊስ ፓትሮል መኪኖቹም ይህንኑ ስራ ለማገዝ MDC (mobile data computer) የሚባል ሲስተም ተገጥሞላቸዋል በመሆኑም ከ9.1.1 ጋር ተያይዘው የሚመጡ መረጃዎች በየቦታው ላሉ የፓትሮል ፖሊሶች በፍጥነት ይነገራል፡፡ የመረጃ ተቀባዩም ችግሩን በተነገረው አካባቢ ተገኝቶ ችግሩን ይፈታል፡፡

ቻምፕዮንስ... ወደ ገጽ 18 የዞረ

የመሳሰሉ ተጨዋቾችን ለመግዛት ማለት ነው፡፡ ለፒሬዝ የስኬት ቁልፉ ገንዘብ ማውጣት ነው፡፡ ሆኖም አልተሳካላቸውም፡፡ ባርሴሎና ማሸነፉን ቀጠለ፡፡ በዚህም ሪያልን ወደ ክለቦች ቁንጮነት ይመልሱት ዘንድ ጆዜ ሞውሪንሆን አመጡ፡፡ ተሳካላቸው? ባለፈው የውድድር ዘመን ላ ሊጋውን አሸንፈዋል፡፡ እጅግ ተፈላጊውን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ወደ ነጩ ቤት ለማምጣት ቢቃረቡም በሁለት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል፡፡ ይህ የውድድር ዘመን ደግሞ ያለጥርጥር የፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ መጨረሻ ነው፡፡ የሮናልዶና ማድሪድ ፍቺም እውን የሚሆንበት ዓመት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ በአውሮፓ ለመንገስ የመጨረሻ ሙከራቸውን ያደርጋሉ፡፡ ለክለቡ፣ ለፕሬዝዳንቱ፣ ለአሰልጣኙ፣ ለኮከብ ተጫዋቹ ለሁሉም ትኩረታቸው 10ኛው የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ማድሪድ ማምጣት ነው፡፡ በላ ሊጋው የካታላኑ ክለብ ለብቻው እየሮጠ በመሆኑ ብቸኛው የሪያል አማራጭ ቻምፒየንስ ሊግ ነው፡፡

ቁልፍ ፍጥጫዎች

ሮናልዶ ከራፋኤል ዳ ሲልቫ ሮናልዶ ባለፉት ስድስት ዓመታት ምርጥነቱን ያሳየ ልዩ

ተጨዋች ነው፡፡ ከባለተሰጥኦ ታዳጊነት ተነስቶ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ያደረሱት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና የተጫዋቹ ከሁሉም በላይ ምርጥ የመሆን ጥማት ናቸው፡፡ ዩናይትድ ተጫዋቹ ምን መስራት እንደሚችል ያውቃል፡፡ ለክለቡ የቅርብ ዓመታት ስኬት የሮናልዶን ሚናም አይዘነጋም፡፡ አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቀድሞ ቤቱ ተመልሷል፡፡ ለራፋኤል ይህ ትልቅ ስጋት ነው፡፡ ዩናይትድ ወደ ሩብ ፍፃሜው መግባት ከፈለገ ሮናልዶን የሚያቆምበትን ዘዴ መቀየስ አለበት፡፡ በማድሪድ እና ሲቲ ግጥሚያ ሮቤርቶ ማንቺኒ የታክቲክ ስህተት በመፈፀማቸው የማንቸስተሩ ክለብ እጅግ ባሳፋሪ ሁኔታ ተሸንፎ ይመለስ ነበር፡፡ ሮናልዶ አራት ወይም አምስት ማስቆጠር ሲችል እድሎችን አመከነ እንጂ፡፡

የፖርቹጋላዊው እና ራፋኤል አንድ ለአንድ መገናኘት የዩናይትድ ጋፊዎችን ማስጨነቁ አይቀርም፡፡ ከብራዚላዊው ይልቅም ፊል ጆንስ ቢሰለፍ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ጆንስ እጅግ የተረጋጋ እና በአየር ላይ ኳሶች ከራፋኤል የተሻለ በመሆኑ ሮናልዶን ሊያቆመው ይችላል፡፡ ነገር ግን ቁልፍ

የሚሆነው ፉል ባኩን መደገፍ እና ክርስቲያኖን ለሁለት መያዝ ነው፡፡ አንቶኒዮ ቫሌንሲያ ወሳኝ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው፡፡ ኢኳዶራዊው ለቡድኑ ሲል ራሱን እንደሚሰዋ በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ እርሱ በግጥሚያው የሚኖረው አቅም ሮናልዶ በአንድ ለአንድ ግንኙነቶች እንዳይጠቀም ያደርገዋል፡፡ ከዓለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱን ማቆም ከባድ ቢሆንም ዩናይትድ ከሌሎች ቡድኖች የተሻለ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ በውድድር ዘመኑ ማድሪድ ችግር ውስጥ ቢገኝም የቀድሞው የዩናይትድ ልጅ በቻምፒየንስ ሊግ ስድስት ጎሎችን በማስቆጠር በደርሶ መልስ ግጥሚያዎቹ ለእነ ራፋኤል ፈተና መሆኑ አይቀርም፡፡

አማካይ ክፍል ይህ ክፍል የጨዋታውን ውጤት ሊወስን ይችላል፡፡

ባርሴሎናን የመሳሰሉ ቡድኖች አማካይ ክፍሉን በማጨናነቅ ዩናይትድን ከውድድር ውጭ አድርገውታል፡፡ ለደጋፊዎች ራስ ምታት የሚሆነው ደግሞ ፈርጉሰን ችግሩን በትክክል አለመቅረፋቸው ነው፡፡ ማድሪድ ሶስት የአማካይ ክፍል ተጨዋቾችን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ዣቢ አሎንሶ፣ ሳሚ ኬዲራ እና ሞድሪችን፡፡ ክሮኤሺያዊው ከቶተንሃም የመጣው ከሜሱት ኦዚል የበለጠ በአማካይ ክፍሉ ለቡድኑ ስለሚጠቅም ነው፡፡

ይህን ችግር ባለፈው የውድድር ዘመን ባየርን በሚገባ ተጠቅሞበታል፡፡ ቶኒ ክሩስ ወደ ኋላ በማፈግፈግ የሙኒክን የአማካይ ክፍል በሶስት ተጨዋቾች የተያዘ በማድረግ ከሪያል ሁለት አማካይ ተጫዋቾ የቁጥር ብልጫ እንዲኖረው አስችሏል፡፡ ስለዚህ ሞድሪች የመጣው ማድሪድን በአማካይ ክፍሉ ጠንካራ ለማድረግ እና ኳስን የበለጠ እንዲቆጣጠር ለማስቻል መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

በዚህ የተነሳ ዩናይትድ ዌይኒ ሩኒ የሞድሪችን ሚና እንዲወጣ ማድረግ እና ኳስ ሲቆጣጠር አሎንሶን ሰው ለሰው መያዝ አለበት፡፡ ታክቲኩ በአርሰናል ግጥሚያ በሚገባ ተተግብሯል (ሚኬል አርቴታን ኳስ እንዳይደርሰው ማድረግ)፡፡ ይህ የማድሪድን ማጥቃት ከምንጩ ማድረቅ ማለት ነው፡፡

የማድሪድ 4-2-3-1 ከዩናይትድ 4-4-1-1 ጋር የሚገናኝ ቢሆንም ወሳኙ ፍልሚያ የሚኖረው መሀል ሜዳው ላይ ነው፡፡ ሩኒ እና ሞድሪች ለየቡድኖቻቸው የሚኖራቸው ውጤታማነትም የግጥሚያውን አሸናፊ ሊወስን ይችላል፡፡

(ውድ አንባቢያን፡ ይህ ሰፊ ዘገባ የአርሰናልንም ምድብ ይዳስሳል። ሙሉውን ለማንበብ zehabesha.com ላይ ይግቡ)

ፀጉር የውበት አክሊል ነውና ወደ ግሎባል ሳሎን በመምጣት ተውበው ይሂዱ

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

January 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 47 ጥር 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 47 ገጽ page

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

At Furniture CFW we understand your goal of having a warm and inviting home – not just a house. We offer the highest quality furniture, a vast array of styles, and excellent value so that your goal can easily become a reality.

2941 Chicago Ave Minneapolis, MN 55407 612-998-5300

We offer Fairytale We offer Fairytale

Wedding Settings Wedding Settings

and fantasy event and fantasy event

decor by a Profes-decor by a Profes-

sional sional

Florist. Elegant back-Florist. Elegant back-

drops and fabulous drops and fabulous

floral arrangements. floral arrangements.

We are conveniently located at 2508 Riverside Ave.,

in Minneapolis. Call us at (612) 338- 2275 or

(763) 498-2554 or visit us at www.riversidekellofloral.net

SERVICES: Church decorations Reception hall decorations, including

aisle treatment Bouquet, boutonnières & corsage- silk or Natural

Chair covers table close Cake table décor

We can create a custom wedding floral arrangement, floral centerpiece, flower girl

basket, or any floral design for that special occasion. We listen to your ideas and

use our artistic abilities to create floral works of art for your wedding.

ALL MANNER OF HIGH END DECORATIONSALL MANNER OF HIGH END DECORATIONS tailored to suit your dream and funds! We are available for all of your

wedding decoration needs