4
January 2016 1 ከአሉባልታ የጸዳ መረጃን መሠረት ያደረገ በቤተክርስቲያን ዙሪያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለእርስዎ ማቅረብ ዓላማዋ ነው። የታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል መታሰቢያ በዓል በመላው ዓለም በድምቀት ተከብሮ ዋለ። አሜሪካ ተወልደው ላደጉ ወጣቶች ቅዳሴ በእንግሊዝኛ ተካሄደ የታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል መታሰቢያ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙት ዓብያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከብሮ ዋለ። በየዓመቱ ታህሳስ 19 እለት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓል በአትላንታ ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጂያ የቴነሲ እና የኖርዝ ካሮላይና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብጹእ አቡነ ሰላማ የኦሀዮ እና የፍሎሪዳ ሊቀ ጳጳስ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣አበው ካህናት፣ዲያቆናት፣ መዘምራን እና በአትላንታ እና አካባቢው የሚኖሩ ምእመናን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተክብሮ ውሏል። በመጋቤ ሀዲስ መምህር ልዑለ ቃል አማካይነት ከእለተ አርብ ጀምሮ የተካሄደው ህይወትን የሚያለመልም የወንጌል ጉባኤ እና ቅዳሜ ጧት በዶከተር አባ / ስላሴ መሪነት በሰሜን አሜሪካ ተወልደው ላደጉት ወጣቶች በእንግሊዝኛ የተካሄደው ቅዳሴ ለከብረ በዓሉ ሞገስ ሆኖቷል። በመጋቤ ሀዲስ መምህር ልዑለ ቃል አማካይነት የተካሄደው ጉባኤ በቤተክርስቲያናችን ተሹለክለው የገቡ ሐሰተኛ ወንድሞች (ቤጽ ሃሳውያን) ወደ እውነቱና ቀጥተኛይቱ የቤተከርስቲያናችን አስተምህሮ የሚመልስ ነው። በተለይም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በኦርቶዶክሳውያን መሃል ጥርጥርና የሀሰት ክስ የሚዘሩ ወገኖቻችን በእግዚአብሔር ቃል የሚያርም ትምህርት ሲሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመንጋው ላይ ለእረኝነት ለሾማቸው ሊቀ ጳጳሳት ቤተክርስቲያናን ከፈሪሳዊ እርሾ እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል። ይኸው ትምህርት በዲቪዲና በማህበራዊ የመገናኛ አውታሮች እንደተለቀቀ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ይህን ሊንክ ይከተሉ። hps://youtu.be/h-7vGAoi7A4 በመላው ዓለም የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል እንዴት እንደተከበረ የሚያሳይ ስዕላዊ ዜና ብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ እና ብጹእ አቡነ ፊልፓስ የሜሪላንድና የፊልአደልፊያ ሊቀ ጳጳስ በሳንሆዜ ቅዱስ ገብርኤል የተገኙበት ክብረ በዓል ይህን ይመስላል። ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የአውሮፓና የአፍሪካ ሊቀ ጳጳስ የተገኙበት የዲስ ቅዱስ ገብርኤል ክበረ በዓል

January 2016 - eneweyaye.com · ሀዲስ ሐዋርያ አባ ወልደ ትንሣኤ የተገኙበት በአውስትራልያ የሜልቦርን ቅዱስ ገብርኤል ክብረ

  • Upload
    lamdien

  • View
    222

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

January 2016 1

ከአሉባልታ የጸዳ መረጃን

መሠረት ያደረገ በቤተክርስቲያን

ዙሪያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን

ለእርስዎ ማቅረብ ዓላማዋ ነው።

የታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል መታሰቢያ

በዓል በመላው ዓለም በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

አሜሪካ ተወልደው ላደጉ ወጣቶች ቅዳሴ በእንግሊዝኛ ተካሄደ

የታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል መታሰቢያ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙት ዓብያተ ክርስቲያናት

በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

በየዓመቱ ታህሳስ 19 እለት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓል በአትላንታ ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጂያ የቴነሲ እና

የኖርዝ ካሮላይና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብጹእ አቡነ ሰላማ የኦሀዮ እና የፍሎሪዳ ሊቀ ጳጳስ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣አበው

ካህናት፣ዲያቆናት፣ መዘምራን እና በአትላንታ እና አካባቢው የሚኖሩ ምእመናን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተክብሮ ውሏል። በመጋቤ ሀዲስ

መምህር ልዑለ ቃል አማካይነት ከእለተ አርብ ጀምሮ የተካሄደው ህይወትን የሚያለመልም የወንጌል ጉባኤ እና ቅዳሜ ጧት በዶከተር አባ ገ/

ስላሴ መሪነት በሰሜን አሜሪካ ተወልደው ላደጉት ወጣቶች በእንግሊዝኛ የተካሄደው ቅዳሴ ለከብረ በዓሉ ሞገስ ሆኖቷል። በመጋቤ ሀዲስ

መምህር ልዑለ ቃል አማካይነት የተካሄደው ጉባኤ በቤተክርስቲያናችን ተሹለክለው የገቡ ሐሰተኛ ወንድሞች (ቤጽ ሃሳውያን) ወደ እውነቱና

ቀጥተኛይቱ የቤተከርስቲያናችን አስተምህሮ የሚመልስ ነው። በተለይም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በኦርቶዶክሳውያን መሃል ጥርጥርና የሀሰት

ክስ የሚዘሩ ወገኖቻችን በእግዚአብሔር ቃል የሚያርም ትምህርት ሲሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመንጋው ላይ ለእረኝነት ለሾማቸው ሊቀ

ጳጳሳት ቤተክርስቲያናን ከፈሪሳዊ እርሾ እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል። ይኸው ትምህርት በዲቪዲና በማህበራዊ የመገናኛ አውታሮች እንደተለቀቀ

የደረሰን መረጃ ያሳያል። ይህን ሊንክ ይከተሉ። https://youtu.be/h-7vGAoi7A4

በመላው ዓለም የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል እንዴት እንደተከበረ የሚያሳይ ስዕላዊ ዜና

ብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ እና ብጹእ አቡነ ፊልፓስ የሜሪላንድና የፊልአደልፊያ ሊቀ ጳጳስ በሳንሆዜ ቅዱስ ገብርኤል

የተገኙበት ክብረ በዓል ይህን ይመስላል።

ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የአውሮፓና የአፍሪካ ሊቀ ጳጳስ የተገኙበት የዲስ

ቅዱስ ገብርኤል ክበረ በዓል

January 2016 2

ሀዲስ ሐዋርያ አባ ወልደ ትንሣኤ የተገኙበት በአውስትራልያ

የሜልቦርን ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የቴክሳስ ሊቀ ጳጳስና ብጹእ አቡነ ዮሴፍ የተገኙበት የላስ ቬጋስ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳ፣ዩታ እና የአሪዞና ሊቀ ጳጳስ እና አባ ጽጌ ድንግል

የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ የተገኙበት የሳንዲያጎ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል በካናዳ የካልጋሪ ሊቀ ጳጳስ የተገኙበት የካልጋሪ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጂያ የኖርዝ ካሮላይና እና የቴኔሲ ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ሰላማ የኦሃዮ እና የፍሎሪዳ ሊቀ ጳጳስ የተገኙበት በአትላንታ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል

ብጹዕ አቡነ ሉቃስ

የዋሽንግተን ሊቀ ጳጳስ

የተገኙበት የሲአትል ቅዱስ

ገብርኤል ክብረ በዓል

"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።" መዝ 34:17

January 2016 3

አሜሪካ ተወልደው ላደጉ ወጣቶች ቅዳሴ በእንግሊዝኛ ተካሄደ (ከሰላመ ብርሃን - አትላንታ)

በውጭ አገር የሚወለዱ ልጆቻችን ባህላችንን፤ ሃይማኖታችንንና ትውፊታችንን በተለይም ደግሞ ቋንቋችንን ይዘው

እንዲያድጉ የማንፈልግ ኢትዮጵያዊያን አለን ብለን አናምንም። ዛሬ በአሜሪካ የሚኖሩ ሩቅ ምስራቃውያን፤ ሕንዶች፤

ሜክሲካኖች ወዘተ... ባህላቸውንና እሴታቸውን ለወለዱዋቸው ልጆቻቸው ለማስተላለፍ የሚያደርጉትን ጥረትና ትግል ስናይ

በእውነት ልንቀና እና ከእነርሱ ልንማር ይገባል። አሜሪካንን ታላቅ ከሚያደርጋት ነገር አንዱ ከተለያዩ አገራት የመጡ

ዜጋዎች ባህላቸውንና ቋንቋቸውን እንዲያሳድጉ አመቺ ሁኔታ ስለምትፈጥርላቸው ነው።

ልጆቻችንን በቋንቋችን በልጽገው ለማየት ጉጉት ቢኖረንም በተለያዩ ምክንያቶች እንደፈልግነው ሊሳካልን አልቻለም።

በየቤተክርስትያናቱ ቋንቋችንን ለማስተማር የሚደረገውን ጥረት ቀላል ባይሆንም ይህ እንዲቀጥልና

እንዲያድግ መደገፍ ብቻ ሳይሆን የየበኩላችንን አስተዋጽዖ ማድረግ ይኖርብናል። ይህን ዘገባ እንድጽፍ ያነሳሳኝ

ባለፈው ዲሴምበር 26 2015 ቅዳሴ በእንግሊዝኛ ለወጣቶች ይቀርባል የሚል ማስታወቂያ አይቼ ከቦታው ማለትም

አትላንታ ከሚገኘው ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤትክርስቲያን ሄጄ ያየሁትን የስማሁትንና የተገነዘብኩትን

ላካፍላችሁ በመሻቴ ነው። የ17ና 18 ዓመት ልጆቼ ናቸው ገፋፍተውኝ ይዣቸው የሄድኩት። ሄጄም ባየሁት በጣም ነው

የተደነቅሁት። ቤተክርስቲያኑ በወጣቶች ሙሉ በሙሉ ተሞልቶ ማየቴ በጣም ነው የገረመኝ። የሃይማኖቱን ሥርዓት

በመከተል አለባበሳችውን አሳምረው፤ በሥርዓት ሆነው ሲፀልዩ፣ ሲያዜሙ ሲያዳምጡ ማየቴ በጣም ነበር ያስደሰተኝ።

ጸሎቱ፤ ንባቡና ስብከቱ በእንግሊዝኛ በመሆኑ ፍጹም ጸጥ ባለ መንፈስ ነበር የሚከታተሉት፤ መሐል ላይ በሰባኪው

የሚጠየቁትን ጥያቄዎች ተሻምተው ይመልሳሉ። የቋንቋ ገደብ አላገዳቸውም።

መጀመሪያ ላይ ለምን በእንግሊዝኛ ብዬ ራሴን ጠይቄ ነበር። የአማርኛም ሆነ የግዕዝ ቋንቋ ካላወቁስ እንዴት ሊከታተሉ ይችላሉ? ቢያንስ ቢያንስ

ንባቡና ስብከቱ በሚያውቁት ቋንቋ መሆኑ ቅዳሴው እንደተለመድው በግዕዝ መሆኑ በጸጥታ ለመከታተል እንዲችሉ እንዳደረገ ለመረዳት ችያለሁ።

የእንግሊዘኛ ቅዳሴ ለልጆች ለምን አሰፈለገ?

ይህን በተመለከተ ፕሮግራሙን ካስጀመሩት በብዙዎቻችን ዘንድ ታዋቂ የሆኑት አባት ዶ/ር አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ የሚከተሉትን ምክንያቶች

ያቀርባሉ።

“በማያውቁት ቋንቋ በሚደረግ አገልግሎት ምን ያህል እንሚቸገሩ ሰለ ተመለከትንና

ይህ ችግራቸውም ለወደፊት ባህልና አምነት አልባ ያድረጋቸዋል አልፎም ለልጆቹ

መጥፋት ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለን ስለአመንን ነው። ዘመኑ በዘመናዊ

ቲክኒሎጅ የተራቀቀውን ያህል በግብረ ግብነት እየጠፋ ስለ ሆነ በዚህ ዘመን ላይ

መንፈሳዊና አዋቂ ሰው ማግኝት መልካምን ዘር ለማትረፍ የቤተክርስያን ተልዕኮዋ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዳሴ ደግሞ

ለዚህ መንፈሳዊ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ሰለሚያደርግ ለልጆቹ በሚያቁት ቋንቋ ማገለግል ትልቅ ኃላፈነት ብለን ሰለ

አመንን ነው።”

“ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤

መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ ።” ማቴ 19:14

January 2016 4

ዘግይተው የደረሱን ዜናዎች

መጋቤ ብሉይ አባ ኃ/ሚካኤል በአሌክሳንደሪያ ቨርጂንያ መካነ ራማ ቅዱስ ገብርኤል በአትላንታ የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ አባ ኃ/ሚካኤል ከ6 ወራት በፊት ባልተለመደ መልኩ በአውደ ምህረት ላይ

የስራ መልቀቂያ አቅርበው ሄደው በአሌክሳንደሪያ ቨርጂንያ መካነ ራማ ቅዱስ ገብርኤል የሚባል በወያኔው ሲኖዶስ

ስር የሚመራ ቤ/ክ መክፈታቸው ይታወሳል። ለአንድ ወር ያህል ከቆዩ በኃላ “በአትላንታ ምእመናን ይመለሱ

ተብዩ ስለተለመንኩኝ ተመልሻለሁ” ብለው ነበር። በወቅቱ በህጋዊው ሲኖዶስ ከተወገዙት ከአባ መላኩ ጋር

የከፈቱትን ቤተክርስቲያን ሲያመስርቁ የሚያሳይ ምስል በመታየቱ በፊት ሱባኤ ገባሁ ብለው እርሳቸው ቺካጎ

ከወያኔው ሲኖዶስ አባል ከአቡነ ዘካርያስ ጋር በማህበረ ቅዱሳን ጉባኤ ላይ በመታየታቸው ተቆጥቶ የነበረውን

ምእመናን እንደገና ቤተክርስያን ምእመናን ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ መፍጠሩ የሚታወስ ነው። በማስከተልም

ህጋዊው ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ ወጥ የሆነ መመሪያ እንዲያስተላልፍ በተጠየቀው መሰረት ህጋዊው ሲኖዶስ

ኦሀዮ ባካሄደው 43 ጉባኤ ላይ በስሩ የሚገኙ ካህናት በተወገዝው ሲኖዶስ ስር ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ጋር

ሄደው ማግልገል እንደማይችሉ በምልዓተ ጉባኤ ካጸደቁ በኃላ መመሪያውን አስራጭተዋል። http://

ecadforum.com/Amharic/archives/15806/

ከዚህ ሁሉ ሂደት በኃላ በቅርቡ ሲአትል ገብሬል አክበረው ተመልሰው የማርያም እለት ቅዳሴውን አቋርጠው

ሲወጡም ታይተዋል። የእመቤታችንን ቅዳሴ ያቋረጡበት ምክንያትም ተዘግቶ እንደገና ወደተከፈተው ወደ

ቨርጂንያው ገብርኤል ለመብረር ነበር። እንደገና የተከፈተው ቤተ ክ/ርስቲያን ጃንዋሪ 2/ታህሳስ 23 ቀን

የገብርኤል ክብረ በዓልን የአባ መላኩ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ በተገኙበት አባ ኃ/ሚካኤል በዓሉን ሲያከብሩ

የሚያሳይ ፎቶ እና ቪድዮ ደርሶናል። ማየት ማመን ስለሆነ እንደ አንድ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሚመስል

ንግግር ሲያደርጉ እንዲሰሙ እና ፍርዱን ለአንባቢዎችና ለተመልካቾት ትተናል። ይህን ሊንክ ይከተሉ።

https://youtu.be/ng1uxmfvoJU

የበዓሉን ሙሉ ሥነሥርዓት ለመከታተል ይህን የሚከተለውን የFacebook ሊንክ ይከተሉ።

https://www.facebook.com/mekaneselamst.uraeleotcwdc/videos/666553450113857/

ጸባቴ የማነ ብርሃን በአትላንታ በሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ቤተ መቅደስ

በአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ካቴድራል የረጅም ዘመን የአግልግሎት እድሜ ያላቸውና ለቤተክርስቲያና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ አባል በደረሰባቸው የቤተሰብ ሃዘን

ምክንያት ስርዓተ ፍታቱ የተካሄደው በሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ነበር። በዚሁ የስርዓተ ጸሎት ላይ በስነ ምግባር ጉድለት ምክንያት ከመሰረቱት ቤ/ክ ተከሰሰው

የተባረሩት ጸባቴ አባ የማነ ብርሃን ተገኝተው ነበር። ጸባቴ በብጹዕ አቡነ ይስሃቅ ጸሎተ ፍተት ላይ ስልጣነ ክህነታቸውን የሚያስገፍፍ የቀኖና ጥሰት ፈጽመዋል።

የፈጸሙት የቀኖና ጥሰትም ህጋዊውን ቅዱስ ፓትርያርክን ፣ አቡነ ዜናማርቆስና አቡነ መልከጸዴቅ እንደዚሁም በወቅቱ ገለልተኛ የነበሩት አቡነ ገብርኤል እያሉ በማን አለብኝነት

በሥልጣነ ክህነት እና በአገልግሎት ዘመን የሚበልጧቸውን አባቶች ከህዝብ ጋር እንዲቀመጡ አስደርገው የሊቀ ጳጳሱ ጸሎተ ፍትሃት ራሳቸው መርተውታል። በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

ስርዓት መሰረት አንድ ተራ መነኩሴ በስልጣነ ክህነት ደረጃ ላቅ ያለው አባት አለዚያም ቅዱስ ፓትርያርኩ ያዘዘው አባት ቅዳሴውን ይመራል። ቤተክርስቲያናችን በስርዓት

የምትመራ መዋቅራዊ ቤ/ክ እንጂ የግብር ይውጣ ዓይነት አሰራር የምትመራ ወይም ትእቢተኞች እንዳሻቸው የሚፈነጩባት አይደለችም። በወቅቱ አቡነ ገብርኤል በቆኖናው

መሰረት ስርዓት ፍታቱ እንዲካሄድ ጸባቴን አበክረው ቢመክሯቸውም አሻፈረኝ ብለው በአደባባይ ቀኖና ደፍጥጠዋል።ስለሆነም ጸባቴ በቤተክርስቲያን ላይ ለፈጸሙት ስህተት

ይቅርታ ሳይጠይቁ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ መድረክ ላይ መቆም አይችሉም። በመሆኑም የሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል መድረክ ተደፍሯል። ያስደፈሩትም ጓደኛቸው

የቤተክርስቲያና አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ አባ ኃ/ሚካኤል ናቸው። በተደጋጋሚ “ቤተክርስቲያናችሁን ጠብቁ” የሚሉት አባ ኃ/ሚካኤል ራሳቸው ግን ኃላፊነታቸው

አልተወጡም። ብዙ ምእመናን ያስገረመው ሃዘንተኛ ሊያጽናኑ መጥተው በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በካቴድራሉ የአሰራር ሂደት ውስጥ ጣልቃ መግባታቸው ነው።

እንደ ግለሰብ ሃዘን መድረስ ይችላሉ ግን መድረክ ሊሰጣቸው አይገባም ነበር። ቢሰጣቸውም ሃዘንተኞች ከማጽጽናት ውጭ አስከሬን አስቀምጠው የራሳቸውና የጓደኛቸው አጀንዳ

ውስጥ መግባታቸው አብዛኛውን ምእመናን ማሳዘኑን የደረሰን ሪፖርት ያስረዳል።

ከመጋቢው ጋር የተቀመጡት አባ ጽጌ ገነት ይባላሉ።

የአባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

አባ ጽጌ ገነት በጠብመንጃ ኃይል መንፈቅለ ሲኖዶስ አካሂዶ

ህጋዊውን ቅዱስ ፓትርያርክ አሳዶ ቤተክህነቱን የተቆጣጠረውን

የአዲስ አበባውን ሲኖዶስ ህጋዊ ሲሉ በታየው ቪድዮ ላይ

ተደምጠዋል። መጋቤ ይህንኑ አዳምጠው ከኚህ አባት ጋር አብረው

ቀድሰው በማግስቱ ጃንዋሪ 3 እሁድ ለት በአትላንታ ሰዓሊተ

ምህረት አቡነ መርቆርዮስ ስም እየጠሩ ቀድሰዋል። ቅዳሜ አቡነ

ማትያስ እሁድ አቡነ መርቆርዮስ፤ ድንቅ ነው

“ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።“1ኛ ቆሮ 10:13