Upload
zerihun-alemayehu
View
65
Download
0
Embed Size (px)
DESCRIPTION
Tesfaye G Nefse Hoy
Citation preview
ከጥፋት ጉድጉድ ውስጥ ከረግርግ ጭቃ ያወጣኝ
እግሬን በድጋይ ላይ አቁሞ ያጸናኝ
በፀጋው ደግፎ በህይወት ያኖረኝ
ከክፉ ፍላፃ በጁ የከለለኝ
ነፍሴ ሆይ አግዚአብሔ አምላክ ነውና ስገጂለት
መሃሪው ጌታዬ ምስጋና ይብዛለት
በሒወቴም ሁሉ እኔም ልገዛለት
ቸርነቱን ልንገር ምህረቱን ልዘምር
ቅኔም ልቀኝለት
ኦ ቅኔም ልቀኝለት
ድካምን ህመምን ቁስልን ስብራትን አይቶ
ዘመድ ርቆ ሲቆም የሱስ ተጠግቶ
በፍቅር አክሞ ሕይወትን ያድሳል
ለውለታው ምላሽ ከቶ ምን ይግኛል
ነፍሴ ሆይ አግዚአብሔ አምላክ ነውና ስገጂለት
መሃሪው ጌታዬ ምስጋና ይብዛለት
በሒወቴም ሁሉ እኔም ልገዛለት
ቸርነቱን ልንገር ምህረቱን ልዘምር
ቅኔም ልቀኝለት
ኦ ቅኔም ልቀኝለት
የጫንቃዬ ሸክም ጌታዬ ደርሶ ጣለልኝ
የእዳዬ ጽህፈት በሞቶ ሻረልኝ
ምህረቱ ድንቅ ነው በኔላይ ያሳየው
እግሩ ስር ወድቄ ጌታዬን ላክብረው
ነፍሴ ሆይ አግዚአብሔ አምላክ ነውና ስገጂለት
መሃሪው ጌታዬ ምስጋና ይብዛለት
በሒወቴም ሁሉ እኔም ልገዛለት
ቸርነቱን ልንገር ምህረቱን ልዘምር
ቅኔም ልቀኝለት
ኦ ቅኔም ልቀኝለት