62
ለህትመት የተዘጋጀ ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና 2698BE የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

  • Upload
    menasse

  • View
    1.151

  • Download
    27

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ለህትመት የተዘጋጀ

ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና

2698BE

የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

Page 2: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

2 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ማውጫ

የስልጠናው አጭር መግለጫ

የስልጠናው መረጃ

ሞዱል 1፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ

ኮምፒውተርን መጠበቅ

ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ

ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት

የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት

የሞዱሉ ማጠቃላያ

መፍትሔ ቃላት

የሞዱሉ መረጃ

ይህ ስልጠና ስለ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና አጭር መግለጫ ይሰጣሃል። ለኮምፒውተርህ ስለሚጎዱ የስጋት ዓይነቶች እና ከእነዚህን ስጋቶች እንዴት ኮምፒውተርህን መጠበቅ እንደምትችል ትማራለህ። የመረጃ ልውውጥ ህጋዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ኮምፒውተር እና በይነመረብ ለተጠቃሚዎች ስለሚያቀርቧቸው ዋና ዋና ፈታኝ ሁኔታዎችም ትማራለህ።

የስልጠናው ማብራሪያ መግለጫ የተሳታፊዎች መግለጫ ይህ ስልጠና ኮምፒውተር የመጠቀም ችሎታን ለማዳበር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው የታለመ ነው።

ቀዳሚ አስፈላጊ ነገሮች ተማሪዎች ቢያንስ አንድ የሀገር ውስጥ ጋዜጣን ለማንበብ የሚያስችል መሰረታዊ የማንበብ እና የመረዳት ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል።

ተማሪዎች የመጀመሪያውን መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና መውሰድ ይኖርባቸዋል ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የኮምፒውተር ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል።

የስልጠናው ዓላማዎች

ይህን ስልጠና ከጨረስክ በኋላ፦

• ለሃርድዌር እና መረጃ ስጋት ስለሆኑት ድንገተኛ አደጋዎች ፣ የመሳሪያ ብልሽት ፣ አካባቢ ፣ የሰዎች ስህተት እና ጎጂ ተግባሮች ማብራራት እና

• እነዚህን ስጋቶች ለመቀነስ ርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ።

Page 3: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

3 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የሞዱሉ ይዘቶች

የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ

ኮምፒውተርን መጠበቅ

ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ

ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት

የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት

የሞዱሉ ማጠቃላያ

የሞዱሉ መግቢያ

እንደማንኛውም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ በአጋጣሚዎች ወይም ሆን ተብለው ለሚደረጉ አደጋዎች ሰለባ ነው። ከነዚህ አደጋዎች አንዳንዶቹ የማይመለሱ ሊሆኑ ይችላሉ። የኮምፒውተርህን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌር እና በውስጡ ያለን ውሂብ አንዳንድ የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ብዛት ካላቸው ጉዳቶች መታደግ ይቻላል።

ይህ ሞዱል ለኮምፒውተርህ እና በውስጡ ለተቀመጠው ውሂብ ስጋት የሆኑ አደጋዎችን ለይተህ እንድታውቅ ይረዳሃል። አንዳንድ የመከላከያ ርምጃዎችን በመውሰድ ኮምፒውተርህን ከነዚህ ስጋቶች እንዴት መጠበቅ እንደምትችል ይዳስሳል። በመጨረሻም ይህ ሞዱል ከበይነመረብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የስነ-ምግባር እና ህጋዊ ጉዳዮችን ያብራራል።

የሞዱሉ ዓላማዎች

ይህን ሞዱል ከጨረስክ በኋላ፦

• የኮምፒውተርን ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ማብራራት እና ለኮምፒውተር ስጋት የሆኑ አደጋዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ ፤ • ኮምፒውተርን ከተለያዩ አደጋዎች የመጠበቂያ ዘዴዎችን ለይተህ ማወቅ ፤ • የኮምፒውተርን ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ለማሳደግ የሚጠቅሙ ጥሩ ተሞክሮዎችን ማብራራት ፤ • ኮምፒውተርህ ደህንነቱ እንደተጠበቀ ለማቆየት የሚረዱ ቅንጅቶችን እና አማራጮችን ማብራራት እና • ኮምፒውተር እና በይነመረብ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቧቸውን ዋና ዋና ፈታኝ ሁኔታዎች ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።

በሁሉም የህይወት ተሞክሮዎችህ ውስጥ ኮምፒውተሮችን ትጠቀማለህ። መረጃ ለማስቀመጥ ፣ የሒሳብ ስራዎችን ለማከናወን ፣ ጌሞችን ለመጫወት ፣ ሙዚቃ ለማዳመጥ ፣ በይነመረብን ለመዳሰስ እና በኢ-ሜይል እና በውይይቶች ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ለመሰሉ የተለያዩ ዓላማዎች ኮምፒውተሮችን ልትጠቀም ትችላለህ።

ነገር ግን ኮምፒውተርህ እና በውስጡ የተከማቹ መረጃዎችህ ለጉዳት እና ለብልሽት የተጋለጡ ናቸው። ስለዚህ በተፍጥሮ አደጋዎች ፣ በሰዎች ስህተት ወይም በድንገተኛ ክስተት ወይም የሰርጎ ገቦች ወይም ቫይረስ ጥቃቶችን በመሰለ የጥቃት እንቅስቃሴ ከሚፈጠሩ አደጋዎች ኮምፒውተርህን መጠበቅ ይኖርብሃል።

ኮምፒውተርህን ከነዚህ አደጋዎች ለመጠበቅ የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ርምጃዎችን ልትወስድ ትችላለህ። ለምሳሌ ተገቢ የሆነ የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች እና የዘመነ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር በኮምፒውተርህ ውስጥ እንዲኖርህ በማድረግ። ኮምፒውተርህ በይበልጥ የተጠበቀ መሆኑን ርግጠኛ ለመሆን የቤተሰብህ አባሎችም ስለ ደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ማወቅ ይኖርባቸዋል።

በበይነመረብ አማካይነት ከሚገኝ መረጃ ጋር በተያያዘ ያሉ መብቶችን ማወቅም አስፈላጊ ነው። በብዙዎቹ የድር ጣቢያዎች የሚገኙ ይዘቶች የቅጂ መብት ያላቸው ንብረቶች ስለሆኑ ያለፈቃድ እነዚህን መጠቀም በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል።

ይህ ሞዱል ለኮምፒውተርህ ስጋት የሆኑ የተለያዩ አደጋዎችን ፣ እነዚህ አደጋዎች ስለሚያሳድሩት ተጽዕኖ እንዲሁም መፍትሔዎቻቸው ይዘረዝራል። ይህ ሞዱል የኮምፒውተርህን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለማዘመን ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎችም ያብራራል። ከዚህ በተጨማሪም ይህ ሞዱል በይነመረብን በምትጠቀምበት ጊዜ ልብ ልትላቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር እና ህጋዊ ጉዳዮች ያብራራል።

ሞዱል 1

የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

Page 4: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

4 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች

የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ምንድነው?

የተፈጥሮ አደጋዎች

ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎች

በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎችን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

የኮምፒውተር አደጋዎች እና የመከላከያ ርምጃዎች

ግለ ሙከራ

የትምህርት ክፍሉ መግቢያ

የግብር ወረቀቶችን የመሰሉ አስፈላጊ ሰነዶችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ታስቀምጣቸዋለህ። ስለዚህም ሰነዶችህ ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጠፉም። ካለፍቃድህም ማንም ሊያገኛቸው/ሊደርስባቸው እንደማይችል እርግጠኛ ነህ።

ኮምፒውተሮችን ብዙ ጊዜ የምትጠቀም ከሆነ በኮምፒውተር ላይ ሊቀመጥ የሚችል በርካታ መረጃ ሊኖርህ ይችላል። ይህ መረጃ የግብር ዝርዝር ፣ የግል ደብዳቤዎች ወይም የንግድ ስራ ደብዳቤዎች ሊሆን ይችላል። ይህ መረጃ ካላንተ ፈቃድ በሌሎች ሰዎች የማይታይ መሆኑን እርግጠኛ ልትሆን ይገባል። ይህ መረጃ ጉዳት እንዳይደርስበትም መጠበቅ ይኖርብሃል።

በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ የኮምፒውተርህን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌር እና ኤሌክትሮኒክ መረጃ ከጉዳት ፣ ከመጥፋት እንዲሁም ከስርቆት የመጠበቅ አስፈላጊነትን ትዳስሳለህ። በተጨማሪም በኮምፒውተርህ ያለን ውሂብ ለመጠበቅ ልትጠቀምባቸው ስለምትችላቸው የተለያዩ መፍትሔዎች እና መሳሪያዎች ትማራለህ።

የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች

ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦

• የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመናን ማብራራት ፤

• ተፈጥሮአዊ የኮምፒውተር አደጋዎችን ለይተህ ማወቅ ፤

• ኮምፒውተርህን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ ማወቅ ፤

• ለኮምፒውተርህ ስጋት የሆኑ የሰዎች ተግባሮችን ለይቶ ማወቅ እና

• ስጋት ከሆኑ የሰዎች ተግባሮች ኮምፒውተርህን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።

ክፍለ ትምህርት 1

የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

Page 5: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

5 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና ምንድነው?

ኮምፒውተርን ወይም በውስጡ የሚገኝን ውሂብ ሊያበላሽ የሚችል መንስኤ የኮምፒውተር ስጋት ነው። እንደ ርዕደ መሬት ወይም ከፍተኛ አውሎንፋስ ያሉ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች መጠነ ሰፊ አካላዊ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። አንተ ወይም ሌላ ሰው ኮምፒውተሩ በትክክል እንዳይሰራ ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ አስፈላጊ ፋይሎችን በአጋጣሚ ወይም ባለማወቅ ልታጠፉ ትችላላችሁ። ኮምፒውተርህ ከአውታረመረብ ጋር ሲገናኝ ኮምፒውተርህ የበለጠ ለኮምፒውተር ስጋቶች የተጋለጠ ይሆናል። ለምሳሌ ሌላ ተጠቃሚ ኮምፒውተርህን ያለፈቃድ ለመዳረስ አውታረመረቡን ሊጠቀም ይችላል።

እነዚህን ስጋቶች ለመቀነስ እና በጉዳት ምክንያት ሊደርሱ የሚችለውን የመጥፋት ዕድል ለመቀነስ ልትጠቀምባቸው የምትችላቸው የተለያዩ ርምጃዎች አሉ። መሰረታዊ የሆኑ መመሪያዎችን በመከተል በኮምፒውተርህ ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጉዳት መጠን መቀነስ እና ስለደህንነቱ እና ክብረ ገመናው እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።

የኮምፒውተር ደህንነት

የኮምፒውተር ሃርድዌር በሰዎች ቸልተኝነት አልያም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ሊበላሽ ይችላል። በተጨማሪም በኮምፒውተር ውስጥ ያለ ውሂብ እና ሶፍትዌር በአጋጣሚ ወይም ሆን ተብሎ ከሚደረግ ጥፋት እና ብልሽት መጠበቅ አለባቸው። የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ በኮምፒውተር ላይ እና በውስጡ በሚገኘው ውሂብ ላይ የሚደርስን እንደዚህ ያለ ጉዳት ለማስወገድ ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ያወሳል።

የኮምፒውተር ክብረ ገመና

በኮምፒውተርህ ላይ የግል ፋይሎችህንና ወይም ሰነዶችህን ታስቀምጣለህ እናም ማንም ሰው እንዲያነብብህ አትፈልግም። የኮምፒውተር ክብረ ገመና ማለት የግል ፋይሎች እና የኢ-ሜይል መልዕክቶች የመሳሰሉ መረጃዎችን ካለአንተ ፈቃድ ማንም እንዳይደርስባቸው ማድረግ ማለት ነው። የኮምፒውተር ክብረ ገመና ውሂብህን የመዳረስ ፈቃድን ለመገደብ ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው ርምጃዎች ያወሳል። የኮምፒውተር ክብረ ገመና በተጨማሪም ማንኛውም የግል የሆነ መረጃን በበይነመረብ ላይ ለማውጣት የሚደረግ ጥንቃቄን ያካትታል። እንደዚህ ያለ መረጃ እንደ ኢ-ሜይል እና የባንክ መለያዎች ያሉ የግል መለያዎችህን ለመዳረስ ሲባል ያልአግባብ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

Page 6: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

6 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ የተፈጥሮ አደጋዎች

ርዕደ መሬት ፣ ጎርፍ ፣ አውሎንፋስ እና የመሳሰሉት ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ኮምፒውተርህን በማንኛውም ጊዜ ሊያበላሹብህ ይችላሉ። የተፈጥሮ አደጋዎች ኮምፒውተሮች ላይ አካላዊ ጉዳት ሊያደርሱ እና ውሂብ እንዲጠፋ የሚያደርጉ እንደ እሳት ፣ ከመጠን ያለፈ ሙቀት አንዲሁም ፍንዳታዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ይህ ስዕላዊ ማስረጃ ለኮምፒውተር ደህንነት እና ክብረ ገመና ስጋት የሆኑ ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን ይገልፃል።

1. አብዛኞቹ የኮምፒውተር ክፍሎች በተወሰነ የሙቀት ክልል ብቻ መስራት እንዲችሉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። ከመጠን ያለፈ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ በሚኖርበት ጊዜ አንዳንድ የኮምፒውተር አካሎች በትክክል ያለመስራት ሊጀምሩ ይችላሉ እንዲሁም እነዚህን ክፍሎች በሌላ መተካት ሊያስፈልግህ ይችላል። ኮምፒውተርህ ከመጠን ላለፈ ሙቀት የተጋለጠ ከሆነ ከማስጀመርህ በፊት መደበኛ ሙቀት ወዳለበት ክፍል ውሰደው።

2. እሳት ኮምፒውተርህን ሊጠገን በማይችልበት ሁኔታ ሊጎዳው ይችላል። ኮምፒውተሩ በቀጥታ እሳት ሊይዘው ባይችልም ሊፈጠር የሚችለው ሙቀት በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ የኮምፒውተር ክፍሎችን ለማቅለጥ በቂ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ጭስ የሲፒዩ ፋንን ሊያበላሽ ይችላል ይህም ሲፒዩ እንዲግልና እንዲበላሽ ያደርገዋል።

3. ከፍተኛ በሆነ የኤሌክትሪክ ፍሰት የሚከሰት ፍንዳታ/ብልጭታ የኃይል መጨመርን ያስከትላል። የኃይል መጨመር ወይም መቆራረጥ የኮምፒውተርህን አንዳንድ ክፍሎች ዳግም እንዳይሰሩ አድርጎ ሊጎዳ የሚችል ድንገተኛ የኃይል አቅርቦት መጨመር ነው። ለምሳሌ ድንገተኛ የኃይል አቅርቦት መጨመር የኮምፒውተርህን ማዘርቦርድ ሊያቃጥል ይችላል።

Page 7: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

7 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

የተፈጥሮ አደጋዎች ኮምፒውተርህ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ ውሂብህን እና ኮምፒውተርህን ከተፈጥሮአዊ አደጋዎች ለመጠበቅ ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ርምጃዎች ያብራራል።

ርምጃ መግለጫ የውሂብ ምትክ መያዝ

የውሂብ ምትክ መያዝ የውሂብህን ቅጂዎች በዛ አድርጎ መያዝን ያካትታል። አንደ ጎርፍ እና ርዕደ መሬት ያሉ አደጋዎች በድንገት ሊከሰቱ ይችላሉ። ምትክ መያዝ በማንኛውም ሁኔታ የሚከሰትን የውሂብ መጥፋት መልሰህ እንድታገኘው ይረዳሃል። ውሂብህን በጥሩ ሁኔታ እንደገና ለማግኘት ምትክ አድርገህ የያዝከውን አስፈላጊ የሆነ መረጃህን ቅጂ ሌላ ህንፃ ወይም ከተማ ላይ ለይተህ በጥንቃቄ አስቀምጥ።

ኮምፒውተሮችን ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ማስቀመጥ

ኮምፒውተርህን ለተፈጥሮ ተጽዕኖዎች ሊጋለጥ እና ሊበላሽ በማይችልበት ስፍራ ላይ አስቀምጥ። ለምሳሌ ኮምፒውተሮችን አቧራ የሚበዘበት ወይም እርጥበት ያለበት ክፍል ውስጥ ከማስቀመጥ ተቆጠብ።

ጠባቂ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን መትከል

የማይቋረጥ ኃይል አቅራቢ (Uninterruptible Power Supply) (UPS) የመሰሉ መሳሪያዎችን መትከል ጊዜያዊ የኃይል መቋረጥ በሚከሰትበት ጊዜ በምትኩ የባትሪ ኃይልን ማቅረብ እንዲችሉ ያደርጋል። UPS በድንገተኛ የኮምፒውተር መዘጋት ምክንያት የሚከሰትን የሶፍትዌር ብልሽት ይከላከላል። UPS የኃይል መብዛት እና የኃይል አስተላላፊ መስመሮችንም ይቆጣጠራል። ይህም በኃይል መተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚከሰት የኃይል መብዛት እና መቆራረጥ ኮምፒውተርህን እንዳይጎዳ ይረዳል። የኃይል መብዛት ጠባቂዎችን እና የመስመር ተቆጣጣሪዎችን ለየብቻ መትከልም ትችላለህ። ነገር ግን እንደ መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ያሉ ክስተቶች ምክንያት በሚፈጠር ከፍተኛ የሆነ የኃይል መብዛት ሁኔታ ጊዜ አደጋን ለማስወገድ ኮምፒውተርህን ማጥፋ እና ከኃይል ምንጩ መንቀል ይኖርብሃል ።

ኮምፒውተሮችን ከእሳት መጠበቅ

የእሳት ሂደትን በሚቀንስ ነገር ዙሪያውን በማጠር ኮምፒውተርን ከእሳት መጠበቅ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በቂ የሆነ የእሳት መከላከያ መሳሪያዎችን እና ፈጣን የአደጋ መቆጣጠሪያ ርምጃ መውሰጃዎችን መትከል ትችላለህ።

ተገቢ የሆነን ሙቀት እና የአየር ሁኔታ መጠበቅ

የኮምፒውተርህ አገልግሎት አስተማማኝ እንዲሆን ለማድረግ ተስማሚ የሆነውን ሙቀት እና የአየር ሁኔታ መጠበቅ ይኖርብሃል። ይህንንም የአየር ማቀዝቀዣዎችን እና የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያዎችን የመሰሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ማድረግ ትችላለህ።

ርዕስ፦ በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎች

አንዱ የኮምፒውተር ስጋት ዓይነት በሰዎች የሚፈጠር ጉዳት ነው። በቢሮህ ውስጥ የሚሰራ አንድ የተከፋ ሰራተኛ ሆን ብሎ በኮምፒውተርህ ውስጥ ያለን መረጃ ለማበላሸት ሊነሳሳ ወይም ለማጥፋት ሊሞክር ይችላል። ሰርጎ ገብ ከበይነመረብ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ህገወጥ በሆነ መንገድ ኮምፒውተርህን ለመድርስ የሚሞክር ሰው ነው። ኮምፒውተርህን ከደረሰ በኋላ ሰርጎ ገብ በኮምፒውተርህ የሚገኝ መረጃን ሊሰርቅ ወይም ሊያበላሽ ይችላል። በሰዎች ከሚፈጠር ጉዳት በተጨማሪ እንደ ድንገተኛ የውሂብ ማጥፋት እና አካላዊ ጉዳት ያሉ የሰዎች ስህተት ለኮምፒውተርህ ስጋት ናቸው። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ በሰዎች የሚፈጠር ጉዳት እና በሰዎች ስህተት የሚመጡ የተለያዩ የኮምፒውተር ስጋቶችን ይገልፃል።

አደጋ መግለጫ ስርቆት

ማንኛውም ሰው ኮምፒውተህን መዳረስ የሚችል ከሆነ ኮምፒውተርህን ወይም የኮምፒውተሩን ክፍሎች ሊሰርቅህ ይችላል። እንደ ላፕቶፕ ያሉ ተንቀሳቃሽ ኮምፒውተሮችን የሚጠቀሙ ሰዎች ከመብዛታቸው አንፃር አካላዊ የኮምፒውተሮች ስርቆት የተለመደ ሆኗል።

ኮምፒውተርህ ከበይነመረብ ጋር በሚገናኝበት ጊዜም የምናባዊ ስርቆት ሰለባ ልትሆን ትችላለህ። አንዱ የምናባዊ ስርቆት ምሳሌ የሚሆነው የማንነት መለያ ስርቆት ነው ፤ በዚህም ሰርጎ ገቦች መለያህን በመጠቀም እና አንተን በመምሰል የግል መረጃዎችህን ሊሰርቁህ ይችላሉ። ይህን የሐሰት የማንነት መለያ በመጠቀም ሰርጎ ገቦች ፋይናንስህን መዳረስ ሊችሉ ወይም ህገ ወጥ ስራዎችን ሊያከናውኑበት ይችላሉ። ሌላው የምናባዊ ስርቆት ምሳሌ የሚሆነው የሶፍትዌር ህገ-ወጥ ቅጂ ነው ፤ ይህም የኮምፒውተር ንድፍ ወይም ፕሮግራም ስርቆት ነው። በተጨማሪም ይህ የኮምፒውተር ፕሮግራምን እና ምስጢራዊ ሰነዶችን ያለፍቃድ ማሰራጨት እና መጠቀም ማለት ሊሆን ይችላል።

Page 8: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

8 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ቫይረሶች ፣ ተውሳኮች እና ትሮጃን ሆርሶች

ቫይረሶች በኮምፒውተርህ ላይ ያለን ውሂብ ወይም ሶፍትዌር ሊያበላሹ እንዲሁም በኮምፒውተረህ ውስጥ የተቀመጠ መረጃን ሊሰርቁ የሚችሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች ናቸው። እነዚህ ቫይረሶች ካላንተ ዕውቅና ፣ በበይነመረብ ወይም እንደ ፍሎፒ ዲስኮች እና ሲዲዎች ባሉ የማከማቻ መሳሪያዎች አማካይነት ወደ ኮምፒውተርህ ሊገቡ ይችላሉ። ተውሳኮች አንዴ ኮምፒውተር ውስጥ ከገቡ በኋላ ራሳቸውን የሚያባዙ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ይህም እነርሱን ለማስወገድ ከባድ እንዲሆን ያደርገዋል። ትሮጃን ሆርሶች ራሳቸውን እንደጠቃሚ ሶፍትዌር የሚያስመስሉ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ለምሳሌ እንደ ጌም ወይም መገልገያ ሶፍትዌር ሊመስሉ ይችላሉ። ትሮጃን ሆርስ አንዴ ኮምፒውተር ውስጥ ከገባ በኋላ የኮምፒውተር ውሂብን ማበላሸት ይጀምራል።

ስፓይዌር

ስፓይዌር የሚባሉት ካላንተ ዕውቅና በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫኑ ፕሮግራሞች ናቸው። ስለ ድር አሰሳ ልምዶችህ ወይም ሌላ የግል መረጃ ዝርዝሮችህ ወደ ሌላ በአውታረመረቡ ላይ ያለ ኮምፒውተር በድብቅ/በሚስጥር መረጃ ሊልኩ ይችላሉ።

የበይነመረብ አጭበርባሪዎች

በይነመረብ በምትጠቀምበት ጊዜ በኢሜይል መልዕክቶች ወይም በውይይት መድረኮች አንዳንድ ሳቢ የሆኑ ነገሮች ሊላኩልህ/ሊቀርቡልህ ይችላሉ። እንደዚህ አይነት አቅርቦቶችን ከመቀበልህ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል ፤ ምክንያቱም እነዚህ አቅርቦቶች የገንዘብ ጥፋት የሚያስከትሉ በሚገባ የታቀዱ የአጭበርባሪዎች አካል ሊሆኑ ይችላሉና።

የመስመር ላይ አዳኞች የመስመር ላይ አዳኞች በመስመር ላይ ያለ ማንኛውንም ሰው አግባብ ባልሆነ መንገድ ወይም ስነምግባር በጎደለው ሁኔታ ወዳጅነት በመፍጠር የሚያማልሉ ግለሰቦች ናቸው። አንተ ወይም ቤተሰቦችህ የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ልትሆኑ ትችላላችሁ። የመስመር ላይ አዳኞች ኢሜይል ወይም የውይይት መድረኮችን በመጠቀም በፈለጉት አላማ ዙሪያ ከሰዎች ጋር ግንኙነታቸውን ያዳብራሉ።

ድንገተኛ የውሂብ መጥፋት

ብዙ ጊዜ ድንገተኛ በሆነ የሰዎች ስህተት ምክንያት የኮምፒውተር ብልሽት ሊደርስ ይችላል። ድንገተኛ የሆነ የአስፈላጊ ፋይል መጥፋት የውሂብን አንድነት ሊያዛባ ወይም ሌሎች ፋይሎች ወይም ፕሮግራሞች እንዳይሰሩ ሊያግድ ይችላል። ለምሳሌ ኮምፒውተሩ በትክክል እንዳይሰራ የሚያደርግን ፋይል በድንገት/ሳታውቅ ልታጠፋ ትችላለህ።

ድንገተኛ የሃርድዌር ብልሽት

በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ የኮምፒውተር ክፍሎች በቸልተኝነት ለሚከሰቱ ብልሽቶች የተጋለጡ ናቸው። ለምሳሌ በድንገት ላፕቶፕ ኮምፒውተርህ ቢወድቅብህ እንደ ማዘርቦርድ ወይም ሲዲ-ሮም ያሉ የኮምፒውተሩ ክፍሎችን ሊጎዳብህ/ ሊያበላሽብህ ይችላል። ይህም በኮምፒውተርህ ውስጥ ያለን መረጃ ያሳጣሃል። ከዚህ በተጨማሪም በማከማቻ መሳሪያዎች ወይም ተገጣሚዎች ላይ በምግብ ወይም መጠጥ መፍሰስ ምክንያት የሚደርስ አካላዊ ጉዳት ኮምፒውተርህ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

ርዕስ፦ በሰዎች ተግባራት የሚመጡ አደጋዎችን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

በሰዎች ከሚፈጠሩ ጉዳቶች እና የሰዎች ስህተቶች ጋር በተያያዘ የሚመጡ ስጋቶችን ለመቀነስ አንዳንድ ቀላል ርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ። ቀጥሎ ያለው ሰንጠረዥ ኮምፒውተርህን በሰዎች ከሚፈጠሩ ጉዳቶች እና የሰዎች ስህተቶች ለመጠበቅ መወሰድ ያለባቸውን ርምጃዎች ይገልፃል።

መፍትሔ መግለጫ መረጃን አስተማማኝ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ

መረጃህን አስተማማኝ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ማለትም ሌሎች በማይደርሱበት ሁኔታ አስቀምጥ። ይህም መረጃው የሚሰረቅበትን እና የሚበላሸበትን እድል ይቀንሰዋል።

ውሂብን መመስጠር

የWindows 7 ቢትሎከር (BitLocker) ባህሪ ውሂብን በአንፃፊ-ደረጃ ለለመስጠር ይረዳሃል። ይህን ባህሪ በመጠቀም ውሂብን በምትመሰጥርበት ጊዜ ያልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ደረቅ አንፃፊውን (ሃርድ ድራይቩን) በመንቀል እና ከሌላ ኮምፒውተር ጋር በማገናኘት ውሂቡን ማግኘት አይችሉም።

ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ፕሮግራሞችን መጫን

ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር በኮምፒውተር ማህደረ ትውስታ ውስጥ ቫይረስ እና ስፓይዌር እንዳለ የመፈተሽ እንዲሁም አዲስ ወደ ኮምፒውተሩ እንዳይገባ የመከላከል አቅም አለው። ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌርን በየጊዜው ማዘመን አለብህ ፤ ይህም አዳዲስ ቫይረሶችን እና ስፓይዌሮችን መለየት እንዲችሉ ያስችላቸዋል። አብዛኛው ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር የዘመነውን የሶፍትዌር ስሪት በራሱ ወደ ኮምፒውተር የሚጭን የራስ ማዘመኛ ባህሪ ያቀርባል።

እንደ Windows Mail ባለ የኢ-ሜይል ሶፍትዌር ውስጥ አብረው የተሰሩ ባህሪያት አይፈለጌ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለማገድ ያስችሉሃል ፤ እንዲሁም ቫይረሶችን እና ተውሳኮችን የሚፈትሹ ባህሪያትን ያቀርባሉ። Windows 7 Windows መከታ የሚባል በወቅቱ የመከላከል አቅም ያለው አብሮ የተሰራ ፀረ ስፓይዌር ፕሮግራም አካቷል።

ኬላ (firewall) መጫን

ኬላ መጫን የኮምፒውተር ጎጂ ስጋቶችን ለመከላከል ልትወስደው የምትችለው ውጤታማ መፍትሔ ነው። ኬላ (firewall) የበይነመረብ ፍሰትን ኮምፒውተርህን ወይም የግል አውታረመረብህን ከመድረሱ በፊት ለማጣራት ያስችልሃል። እንደ ሰርጎ ገቦች እና ቫይረሶች ያሉ ስጋቶችን የመከላከያ ተጨማሪ አገልግሎቶችንም ይሰጣል። ኬላ ባልተፈቀደ ተጠቃሚ ማንኛውም ከውጪ የሚደረግን መዳረስ በማገድ የኮምፒውተርህን ደህንነት እንድታረጋግጥ ይረዳሃል። በWindows 7 የሚገኘው Windows ኬላ የማይፈለግ የኮምፒውተር መዳረስን ያግዳል።

Page 9: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

9 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ምትክ ውሂብ መያዝ

አስፈላጊ የሆነን የኮምፒውተር ውሂብ በየጊዜው ምትክ ያዝ። የውሂብን ምትክ ቅጂዎችን በዛ አድርጎ መያዝ በድንገት መጥፋት ወይም መበላሸት ምክንያት የሚከሰትን የውሂብ ማጣት ይከላከላል።

ኮምፒውተርን አስተማማኝ በሆነ ስፍራ ማስቀመጥ

ኮምፒውተርህን ከአቧራ ነፃ በሆነ ፣ ንቅናቄ በሌለበት እና ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች የጸዳ ስፍራ ላይ አስቀምጥ። የኮምፒውተሩ ማስቀመጫ ጠረጴዛ ወይም መደርደሪያ የማይነቃነቅ እና ቋሚ መሆን ይኖርበታል። ይህም ኮምፒውተሩ በድንገት ቢገፋ እንኳ እንዳይወድቅ ይረዳዋል።

ኮምፒውተርህን ከመግኔጢሳዊ ዕቃ እና ፈሳሽ ነገር አርቅ። ለምሳሌ ኮምፒውተርህን መሬት ላይ ወይም ምንጣፍ ላይ አታስቀምጥ። በቁልፍ ሰሌዳ አቅራቢያ ሆነህ አትመገብ ወይም አትጠጣ እንዲሁም የቁልፍ ሰሌዳህን በድንገት ከሚፈስ ነገር ለመከላከል መሸፈኛ ተጠቀም።

ርዕስ፦ የኮምፒውተር አደጋዎች እና የመከላከያ ርምጃዎች

የሚከተሉትን የተለያዩ አይነት አደጋዎችን ለመከላከል የሚወሰዱ ርምጃዎች በተዛማጅ ምድባቸው በትክክለኛው የአማራጭ ሳጥን ምድብ ውስጥ የዓረፍተ ነገሩን ቁጥር በመፃፍ ደርድሯቸው።

ዓረፍተ ነገር

1 የኃይል መብዛትን መከላከያ እና የኤሌክተሪክ መስመር መቆጣጠሪያ

2 የውሂብ ምስጠራ

3 የእሳት ሂደትን የሚቀንስ ነገር

4 የማይነቃነቅ ጠረጴዛ

5 ከመግኔጢሳዊ ዕቃዎች ማራቅ

6 ፀረ ቫይረስ

7 የአየር ማቀዝቀዣዎች እና የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያዎች

8 የስፓይዌር መከላከያ

9 የቁልፍ ሰሌዳ መሸፈኛ

10 ኬላ

ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3

የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች የሚፈጠሩ ጉዳቶች የሰዎች ስህተቶች

ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።

Page 10: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

10 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3

የተፈጥሮ አደጋዎች በሰዎች የሚፈጠሩ ጉዳቶች የሰዎች ስህተቶች

7, 3, 1

10, 8, 6, 2

9, 5, 4

ርዕስ፦ ግለ ሙከራ ለትምህርት ክፍል፦ የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ

ጥያቄ 1 ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ኮምፒውተር ክብረ ገመና በይበልጥ የሚገልጸው የቱ ነው?

ትክክለኛውን መልስ የሆነውን ምረጥ።

ኮምፒውተርን ከእሳት እና ርዕደ መሬት መጠበቅ።

ኮምፒውተርን ከበዛ የኤሌክትሪክ ኃይል መከላከል።

ጓደኛህ ያላንተ ፈቃድ የኮምፒውተር መረጃህን እንዳያይ መጠበቅ።

ጠቃሚ የሆኑ የኮምፒውተር ፋይሎችን በድንገት እንዳይሰረዙ መጠበቅ።

ጥያቄ 2 ከሚከተሉት የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ውስጥ ኮምፒውተርህን እና በውስጡ የሚገኝ ውሂብን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል የምትመርጠው የቱ ነው?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

የበዛ የኤሌክትሪክ ኃይልን መከላከያ።

ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር።

ኬላ።

የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ።

ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።

Page 11: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

11 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

መልስ 1 ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ኮምፒውተር ክብረ ገመና በይበልጥ የሚገልጸው የቱ ነው?

ትክክለኛውን መልስ የሆነውን ምረጥ።

ኮምፒውተርን ከእሳት እና ርዕደ መሬት መጠበቅ።

ኮምፒውተርን ከበዛ የኤሌክትሪክ ኃይል መከላከል።

ጓደኛህ ያላንተ ፈቃድ የኮምፒውተር መረጃህን እንዳያይ መጠበቅ።

ጠቃሚ የሆኑ የኮምፒውተር ፋይሎችን በድንገት እንዳይሰረዙ መጠበቅ።

መልስ 2 ከሚከተሉት የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ውስጥ ኮምፒውተርህን እና በውስጡ የሚገኝ ውሂብን ከተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል የምትመርጠው የቱ ነው?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

የበዛ የኤሌክትሪክ ኃይልን መከላከያ።

ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር።

ኬላ።

የአየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ።

Page 12: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

12 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች

ኮምፒውተርን የመጠበቂያ መመሪያዎች

የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግብይቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎች

የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

ግለ ሙከራ

የትምህርት ክፍሉ መግቢያ

የባንክ ወይም የአስተማማኝ ገንዘብ ማጠራቀሚያ ሳጥንህን ለመድረስ የማንነት መለያህን መስጠት ይኖርብሃል። ይህ የማንነት መለያ ያንተን ንብረት ሌላ ሰው መድረስ እንደማይችል ርግጠኛ እንድትሆን ያደርገሃል።

በተመሳሳይ ለኮምፒውተርህ እና በውስጡ ለሚገኘው መረጃህ አስጊ የሆኑ አደጋዎችን ለመቀነስ የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ። ይህ የትምህርት ክፍል የኮምፒውተርህን ስርዓት ክወና ፣ ሶፍትዌር እና በውስጡ የሚገኝን ውሂብ ለመጠበቅ የሚያግዙህን አንዳንድ መሰረታዊ ምርጥ ተሞክሮዎች ያስተዋውቅሃል።

የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች

ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦

• ኮምፒውተርህን የመጠበቂያ መመሪያዎችን ለይተህ ማወቅ፤

• የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግንኙነቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለይተህ ማወቅ እና

• የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክት ልውውጥ ደህንነትን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።

ክፍለ ትምህርት 2

ኮምፒውተርን መጠበቅ

Page 13: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

13 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ ኮምፒውተርን የመጠበቂያ መመሪያዎች

አንድ ሚስጥራዊ ፕሮጅክት ኮምፒውተርህ ላይ አስቀምጠሃል ብለህ አስብ። ይህን ሪፖርት ለማዘጋጀት ለሳምንታት ስሰራ ቆይተሃል እናም አሁን የፕሮጅክትህን ሪፖርት ለሱፐርቫይዘርህ ማሳየት ፈልገሃል። የዚህ ሪፖርት አንድ ቅጂ ብቻ በኮምፒውተርህ ላይ ይገኛል። ይህ ሪፖርት እንዳይበላሽ ወይም እንዳይሰረዝ ደህንነቱን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ሌላ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ የሆነ ሰው አንተ በማትኖርበት ጊዜ ኮምፒውተርህን ይጠቀም ነበርና የፕሮጀክቱን ሪፖርት ከኮምፒውተርህ ላይ አጠፋው። እንደዚህ ያሉ አጋጣሚዎችን ለማስቀረት በኮምፒውተርህ ላይ የሚገኝን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ርምጃዎችን መውሰድ ይኖርብሃል። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ በኮምፒውተርህ የሚገኘውን ስርዓተ ክወና እና መረጃ ለመጠበቅ ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው ርምጃዎች ያብራራል።

መመሪያ መግለጫ የተጠቃሚ መለያ ተግብር

የስርዓተ ክወናህን እና የመረጃህን አደጋ ለመቀነስ ውጤታማ የሆነው መንገድ ያልተፈቀደላቸው ግለሰቦች ኮምፒውተርህን እንዳይደርሱ መጠበቅ ነው። ይህን ለማሳካት አንደኛው ዘዴ ኮምፒውተርህን ለመድረስ ለተፈቀደላቸው ሰዎች መለያዎችን ማቀናበር ነው። በዚህ መሰረትም እያንዳንዱ ተጠቃሚ በየደረጃው ተገቢ የሆነ የመዳረስ ፍቃድ ያገኛል።

ለምሳሌ በWindows 7 ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ወይም ሌላ ተጠቃሚ መለያዎችን ማቀናበር ትችላለህ። ለራስህ አብላጫውን መብት መወሰን እንዲሁም ልጆች ካሉህ የልጆች መለያን አቅም መገደብ ትችላለህ።

የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል አዋቅር

የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል በማቀናበር የደህንነት ጥበቃህን ከፍ ማድረግ እና ያልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎችን ኮምፒውተርህን እንዳይደርሱ ማገድ ትችላለህ። በብዙዎቹ መስሪያቤቶች ውስጥ እያንዳንዱ ሰራተኛ የተለየ የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል አለው። ሰራተኞቹ ኮምፒውተሮቻቸውን ለመድረስ ትክክል የሆነ የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ማስገባት ይኖርባቸዋል። በWindows 7 የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ማቀናበር ትችላለህ።

የይለፍ ቃልን በሚስጥር መጠበቅ

የይለፍ ቃልህ ለኮምፒውተርህ እንደ ቁልፍ ያገለግላል። የይለፍ ቃልህን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ኮምፒውተርህን ሊደረስ እና መረጃህን ሊያበላሽብህ ስለሚችል የይለፍ ቃልህን በሚስጥር መያዝ ይኖርብሃል።

የይለፍ ቃልህን በምታስገባበት ጊዜ ማንም እንዳያይ ጥንቃቄ አድርግ። የይለፍ ቃልህን ለሌሎች አታጋራ። የይለፍ ቃልህን ጽፈህ በኮምፒውተርህ ወይም በጠረጴዛህ ላይ አትተው። የይለፍ ቃልህ ተጋልጧል ብለህ ካሰብህ ሌሎች ያላግባብ ሳይጠቀሙበት በፊት በፍጥነት ቀይር።

ኮምፒውተርህን ቆልፍ

ማንም ሰው በሌለበት ሁኔታ ኮምፒውተርህን እንደበራ ትተህ በምትሄድበት ጊዜ ሌላ ሰው የኮምፒውተርህን ሶፍትዌር ወይም መረጃ ሊያበላሽብህ ይችላል። ይህንን በማትኖርበት ወቅት ኮምፒውተርህን ለጊዜው በመቆለፍ መከላከል ትችላለህ። ኮምፒውተር በሚቆለፍበት ጊዜ ወዲያውኑ የገጽ ማሳያውን ይዘቶች ይደብቅና በትክክለኛው የተጠቃሚ ስም እና የይልፍ ቃል እስኪከፈት ድረስ ምንም ስራ እንዲከናወን አይፈቅድም።

ኮምፒውተርን የመቆለፍ አካሄዶች እንደምትጠቀመው ስርዓተ ክወና ይወሰናል። ለምሳሌ በWindows 7 CTRL+ALT+DEL በመጫን እና ይህን ኮምፒውተር ቆልፍ የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ በማድረግ ኮምፒውተሩን መቆለፍ ትችላለህ። ይህ ኮምፒውተርን የሚቆልፍ ባህሪ በሁሉም ስርዓተ ክወናዎች ላይ እንደሌላ አስታውስ።

Page 14: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

14 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የመጠበቂያ ሶፍትዌር ጫን እንዲሁም አዘምን

ኮምፒውተርህን እንደ ቫይረሶች እና ስፓይዌር ባሉ ስጋቶች እንዳይጠቃ ክትትል ማድረግ ይኖርብሃል። በአሁኑ ጊዜ በቫይረስ የሚመጣ ጉዳት ትኩርት የሚያስፈልገው ነው። በጣም አስፈላጊ የሆነ መረጃ ልታጣ ትችላለህ እንዲሁም የስርዓተ ክወናህን እና ሌላ ሶፍትዌርን እንደገና መጫን ሊያስፈልግህ ይችላል። ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር በመጫን ኮምፒውተርህን ከቫይረሶች እና ስፓይዌር መከላከል ትችላለህ። እነዚህ ጠባቂ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች በኮምፒውተርህ የሚገኝን ቫይረስ እና ስፓይዌር ለማግኘት እና ለማስወገድ ያግዙሃል። አዲስ ቫይረስ እና ስፓይዌር ኮምፒውተርህን እንዳያጠቃውም ይከላከላሉ።

ኬላ መጫንም ሌላው ጥሩ ተሞክሮ ነው። ይህም ወደ ኮምፒውተርህ የሚደርሱትን አጣርቶ ያወጣል። ኬላ መጫን በመስመር ላይ ተጠቃሚዎች የሚደረግን የመድረስ ሙከራን በመገደብም ከሰርጎ ገቦች ይከላከላል።

በየጊዜው አዳዲስ ስጋቶች እየተፈጠሩ ስለሆነም የሶፍትዌር ኩባንያዎች በኮምፒውተርህ ልትጭናቸው የምትቻላቸው ዝምኖችን በየጊዜው ይፈጥራሉ። እነዚህ ዝምኖች በኮምፒውተርህ በተጫነው ሶፍትዌር ወይም ስርዓተ ክወና ላይ ጭማሪዎችን በማድረግ የኮምፒውተርህን በደህንነት ስጋቶች የመጋለጥ አቅም ይቀንሳል። የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌርህ አዳዲስ ቫይረሶችን እንዲያገኝልህ በየጊዜው ማዘመንህን አረጋግጥ።

Windows 7 ኮምፒውተርህን ፍቃድ ከሌለው መዳረስ ለመከላከል Windows ኬላን አካቷል። ከዚህ በተጨማሪም ኮምፒውተርህን ከብቅ-ባዮች እና ሌሎች የደህንነት ስጋቶች የሚከላከል Windows መከታ የሚባል የፀረ ስፓይዌር ፕሮግራም አካቷል።

ውሂብ መስጥር

ውሂብን ፍቃድ ከሌለው መዳረስ ለመከላከል ሲባል ውሂብን ወደማይነበብ ቅርጸት መቀየር ምስጠራ ተብሎ ይጠራል። የተፈቀደለት ተጠቃሚ የተመሰጠረውን ውሂብ ወደሚነበብ እና የሚጠቅም ቅርጸት ዳግም መመልስ ይችላል። ይህም ሚስጠር መፍታት ይባላል። ዛሬ የተለያዩ የሶፍትዌር ምርቶች ውሂብን የመመስጠሪያ ዘዴዎችን አካተዋል።

በWindows 7 ምስጠራ ፋይልን ለሚመሰጥረው ተጠቃሚ በግልጽ የሚታይ ሲሆን ፣ ይህም ፋይሉን ከመጠቀም በፊት ምስጠራውን መፍታት አይኖርብህም ማለት ነው። ሁሌ እንደምታደርገው ፋይሉን መክፈት እና መለወጥ ትችላለህ።

ምትክ ውሂብ ያዝ

አስፈላጊ የሆኑ ፋይሎችን ቅጂ በሲዲ ፣ ዲቪዲ ወይም ፍሎፒ ዲስክ የመሳሰሉ የማከማቻ መሳሪያዎች ላይ በማስቀመጥ ፋይሎችህን ከመጥፋት ወይም ከመበላሸት ልትታደጋቸው ትችላለህ። ይህ ሂደት ምትክ ውሂብ መያዝ ይባላል። የተያዙትን ምትኮችም አስተማማኝ በሆነ ቦታ በማስቀመጥ ዋናው ፋይል በሚበላሽበት ወይም በሚጠፋት ጊዜ ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።

Page 15: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

15 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግብይቶችን ደህንነት የመጠቢቂያ ምርጥ ተሞክሮዎች

ኮምፒውተርህን ከበይነመረብ ጋር ማገናኘት ከአለም መረጃ እና መዝናኛ ጋር ያስተዋውቀዋል። ነገር ግን ኮምፒውተርህን ለመስመር ላይ አደጋዎች የተጋለጠ እንዲሆንም ያደርገዋል። ለምሳሌ ቫይረሶች ከተጠቃ ኮምፒውተር ወደ አንተ ኮምፒውተር በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ። ኮምፒውተርህ በእነዚህ የመስመር ላይ አደጋዎች የሚደርስበትን ጉዳት ለመቀነስ እንደ ጠንካራ የይለፍ ቃሎችን መፍጠር ፣ ውሂብ መመስጠር እና የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጠቀም ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን አጣምረህ መጠቀም ትችላለህ። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ የመስመር ላይ እና የአውታረመረብ ግንኙነቶችን ደህንነት ለመጠበቅ ልትወስዳቸው ስለምትችላቸው የተለያዩ ርምጃዎች ያብራራል።

ርምጃ መግለጫ ጠንካራ የይለፍ ቃል ተጠቀም

ጠንካራ የይለፍ ቃል ማለት በቀላሉ ሊገመት የማይችል ውስብስብ የይለፍ ቃል ነው። የይለፍ ቃል የዓብይ እና ንዑስ ሆሄያትን ፣ ቁጥሮችን እና እንደ ስርዓተ ነጥቦች እና የቁጥር ምልክት ያሉ ልዩ ቁንፊዎችን አጣምሮ የያዘ እንዲሁም ሙሉ ቃላትን ወይም ስሞችን ያላካተት ሊሆን ይገባል።

ጠንካራ የይለፍ ቃል የደህንነት እና ክብረ ገመና ጥቃቶች ዋንኛ መከላከያህ ነው። ቀጥሎ ለተዘረዘሩት ጠንካራ የይለፍ ቃላት ሊፈጠርላቸው ይገባል።

• ያልተገናኙ ኮምፒውተሮችን ለመዳረስ

• አውታረመረቦችን ለመዳረስ

• የግል እና የገንዘብ ሁኔታ ዝርዝር የመሰለ አንገብጋቢ መረጃ ያላቸውን ድረ ጣቢያዎች ለመዳረስ

• ማንኛውም አስፋለጊ የሆነን መረጃ ለመዳረስ

• ኮምፒውተር ላይ ለተቀመጠ የግል መረጃ

ከሰርጎ ገቦች እና ስፓይዌር መከላከል

በይንመረብን በምትዳስስበት ወቅት በኮምፒውተርህ ላይ የተጫነ ፕሮግራም በሌላ አገር ላይ ለሚገኝ ሰርጎ ገብ የግል መረጃህን አሳልፎ ሊሰጥብህ ይችላል። እንደዚህ ያሉ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች የስፓይዌር ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ያለንታ ዕውቅና በኮምፒውተርህ ላይ ይጫኑና ምስጢራው የሆነ መረጃን ከኮምፒውተርህ ወደ ሰርጎ ገቦች በድብቅ ያስተላልፋሉ። አንዳንድ ጊዜ ቀጣሪዎች ሰራተኞች የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች ላይ ሆን ብለው ስፓይዌር በመጫን የሰራተኞቻቸውን የኮምፒውተር ስራ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይጠቀሙበታል።

Windows 7 በኮምፒውተርህ ላይ ስፓይዌር በድብቅ እንዳይጫን የሚከለክል Windows መከታ የሚባል አብሮ የተሰራ ፀረስፓይዌር ፕሮግራም አካቶ ይዟል።

ለመስመር ላይ ደህንነት ጥበቃ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ (ISP) ደጋፊን ተጠቀም። ይህ ድጋፍ ፀረቫይረስ እና ፀረስፓይዌር ሶፍትዌር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ISPs የኬላ መከላከያ ፣ የኢ-ሜይል ቫይረስ መለያ እና የአይፈለጌ መልዕክት መከላከያን ያቀርባሉ።

የአሰሳ ታሪክን በየጊዜው አጽዳ

በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ የምትጎበኛቸው የድር ጣቢያዎች እና ድረ-ገፆች በአሳሽህ ታሪክ ላይ ይቀመጣሉ። እንዲሁም በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ በርካታ ፋይሎች በኮምፒውተርህ ጊዜያዊ ማህደረ ትውስታ ላይ ይቀመጣሉ። ይህ ጊዜያዊ ማህደረ ትውስታ መሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ይባላል። በመሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ላይ የሚከማቹት ፋይሎች ስለ ጎበኛሃቸው ድረ-ገፆች መረጃ ይመዘግባሉ።

ነገር ግን የተወሰኑት የእነዚህ ጊዜያዊ የበይነመረብ ፋይሎች በሰርጎ ገቦች ሊገኙ የሚችሉ እንደ የተጠቃሚ ስምህ እና የይለፍ ቃልህ ያለ የአንተ የግል መረጃን ሊይዙ ይችላሉ። ሰርጎ ገቦች የግል መረጃህን እንዳያገኙ ለመከላከል በአሳሽ ታሪክ እና በመሸጎጫ ማህደረ ትውስታ ውስጥ የሚገኙ ይዘቶችን በየጊዜው አጥፋ።

የድር ጣቢያዎችን በምትጎበኝበት ጊዜ ስምህን የሚያሳይ ማስታወቂያ

Page 16: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

16 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ልትመለከት ትችላለህ። ይህ የሚሆነውም ኩኪዎችን በመጠቀም ነው። ኩኪዎች ቀድሞ የጎበኘሃቸው የድር ጣቢያዎች አማራጮችህን ለመለየት እና ለመከታተል ሲሉ በኮምፒውተርህ ላይ የሚፈጥሯቸው ትናንሽ ፋይሎች ናቸው። ዋና ዓላማቸው የድር ጣቢያውን በምትጎበኝበት ጊዜ የበለጠ ላንተ የሚሆን መረጃ ለማቅረብ ነው። ነገር ግን ኩኪዎች የግል መረጃህን ስለሚይዙ ለኮምፒውተርህ ደህንነት ስጋት ሊሆኑም ይችላሉ። ለምሳሌ የመስመር ላይ ግዢ በምታካሂድበት ጊዜ ኩኪዎች የክሬዲት ካርድህን ዝርዝር መረጃ ሊይዙብህ ይችላሉ። በእነዚህ ምክንያቶች የግል መረጃህ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል ለመከላከል በየጊዜው ኩኪዎችን ማጥፋት ጥሩ ልምድ ነው።

የግል መረጃን ከማጋራት ተቆጠብ

አንዳንድ የድር ጣቢያዎች እንደ ስም ፣ ፆታ እና እድሜ ያለ የግል መረጃን በቅፆች ላይ እንድትሞላ ይጠይቃሉ። በኢ-ኮሜርስ ጣቢያዎች ደግሞ የባንክ መለያ ዝርዝሮችን ወይም የክሬዲት ካርድ ቁጥርህን ልትጠየቅ ትችላለህ። ነገር ግን ሰርጎ ገቦች ይህን መረጃ ሊያገኙት እና ላልተገባ ዓላማ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አስታውስ። አንዳንድ ኩባንያዎች ያልተፈለጉ የንግድ ኢ-ሜይል መልዕክቶችን ወደ አንተ ለመላክም ይህን መረጃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ስለዚህ በድር ጣቢያ ላይ ማንኛውንም የግል መረጃ ከማጋራትህ በፊት የድር ጣቢያው ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና መረጃውን መስጠት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አረጋግጥ።

የመስመር ላይ ግብይቶችን ደህንነታቸው በተጠበቀ ጣቢያዎች ላይ ብቻ አድርግ

የመስመር ላይ ግዢ በምታካሂድበት ጊዜ እንደ ባንከ መለያ ቁጥር እና ክሪዲት ካርድ ዝርዝሮች ያለ ወሳኝ መረጃን መስጠት ያስፈልግሃል። ስለዚህ የመስመር ላይ ግብይቶችን የምታካሂደው አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። አንድ የድር ጣቢያ አስተማማኝ ነው የሚባለው የስሙ ቅድመ ቅጥያ https ከሆነ ነው። ቅድመ ቅጥያው የድር ጣቢያው Secure Sockets Layer (SSL) ፕሮቶኮልን እንደሚተገብር ያመለክታል። SSL የሚተላለፈውን መረጃ በመመስጠር አስተማማኝ የመረጃ ግንኙነትን የሚያረጋግጥ የበይነመረብ ደህንነት ጥበቃ ፕሮቶኮል ነው። SSL ፕሮቶኮል የድር ጣቢያው እውነተኛ መሆኑን እና ለጣቢያው የምትሰጠው መረጃ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንደማይውል ያረጋግጣል።

አስተማማኝ የሆነ የድር ጣቢያ ስታስገባ አብዛኞቹ የድር አሳሾች የስገባሃው የድር ጣቢያ አስተማማኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ መልዕክት ያሳዩሃል። በአድራሻ አሞሌ ውስጥ የሚታይ የተቆለፈ ትንሽ የቁልፍ አዶ አስተማማኝ የሆነ የድር ጣቢያን ለመለየት ያግዝሃል። በተጨማሪም ማንኛውንም የመስመር ላይ ግብይት ከማካሄድህ በፊት የድር ጣቢያውን የደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መመልከት ትችላለህ።

Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በመጠቀም የደህንነት ጥበቃ ክፍሎችን አዋቅር

Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በWindows 7 የሚገኝ ባህሪ ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን ሁኔታ ለመመርመር እና በኮምፒውተርህ የተጫነውን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ለመከታተል የሚረዳ ምቹ የሆነ መገልገያ ይሰጣል። የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን ከመቆጣጠሪያ ፓኔል መክፈት ትችላለህ። የደህንነት ጥበቃ ማዕከል አራት ክፍሎች አሉት እነርሱም፦

• ኬላ፦ በWindows 7 ውስጥ Windows ኬላ በራሱ የሚሰራ ነው። ኬላ እንደ ቨይረሶች እና ተውሳኮች ያሉ ጎጂ ይዘቶች ወደ ኮምፒውተርህ እንዳይገቡ ለመከላከል ይረዳል።

• ራስ-ሰር ማዘመኛ፦ ይህ ባህሪ ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ዝምኖችን በMicrosoft ማዘመኛ የድር ጣቢያ ላይ መኖራቸውን ይፈትሻል። ይህን ባህሪ ማንቃት ኮምፒውተርህ የዘመነ እና በበይነመረብ ላይ ከሚገኙ አዳዲስ የደህንነት ስጋቶች የተጠበቀ ሆኖ እንደሚቆይ ያረጋግጣል።

• የማልዌር መከላከያ፦ ስፓይዌር እና ሌላ የማይፈለግ ሶፍትዌር ያንተን ፈቃድ በአግባቡ ሳይጠይቅ በኮምፒውተርህ ላይ ራሱን ሊጭን ይችላል። Windows መከታ ከበይነመረብ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ወቅታዊ የመከላከል ስራ ይሰራል።

• ሌሎች የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች፦ ሌሎች የደህንነት ጥበቃ

Page 17: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

17 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ቅንጅቶች የበይነመረብ ቅንጅቶችን እና የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ ቅንጅቶችን ያጠቃልላል። የበይነመረብ አማራጮችን በመጠቀም የደህንነት ጥበቃ ደረጃውን መካከለኛ ፣ መካከለኛ-ከፍተኛ ወይም ከፍተኛ ማድረግ ትችላለህ። Internet Explorer 8 ከቀድሞዎቹ ስሪቶች የበለጠ ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ጥበቃ ደረጃዎች አሉት። የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ በኮምፒውተርህ ላይ ለውጥ ከመደረጉ በፊት የይለፍ ቃል በመጠየቅ ያልተፈቀዱ ለውጦችን ይከላከላል።

ተዋናይ ይዘትን አሰናክል ተዋናይ ይዘት በይነመረብ በምታስስበት ጊዜ በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫኑ ትናንሽ ፕሮግራሞችን ያመለክታል። የእነዚህ ፕሮግራሞች ዋና አገልግሎት በቪዲዮች እና በሰሪ አሞሌዎች የታገዘ የበይነመረብ ተሞክሮ ግንኙነት ለአንተ ማቅረብ ነው። ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች እነዚህን ፕሮግራሞች በኮምፒውተርህ የሚገኝ መረጃን ለማበላሸት ወይም ያለአንተ ፈቃድ ጎጂ የሆነ ሶፍትዌርን ለመጫን ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች እንዳይጫኑ ለመከላከል ተዋናይ ይዘትን ማሰናክል ትችላለህ።

ርዕስ፦ የኢሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

ኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክት ለንግድ ስራ እና ለግል ግንኙነት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። ነገር ግን ሰርጎ ገቦች ፣ የመስመር ላይ አዳኞች እንዲሁም ተውሳኮችን እና ቫይረሶችን የሚፈጥሩ ሰዎች ኢ-ሜይልን እና ፈጣን መልዕክትን ለጥቃት ዓለማ ይጠቀሙባቸዋል። ለምሳሌ እነዚህ ሰዎች ጎጂ ሶፍትዌር አያይዘው ኢ-ሜይል ሊልኩ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች አስፈላጊ መረጃን ለመጠየቅ ወይም በተሳሳቱ አቅርቦቶች አንተን ለማማለል ኢ-ሜይልን ሊጠቀሙም ይችላሉ። ለዚህም ነው የኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክት ደህንነትን ለማረጋገጥ አንዳንድ ርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ የሆነው።

የኢ-ሜይል ደህንነትን ለማረጋገጥ አባሪ ያለውን ኢ-ሜይል ከመክፈት ተቆጠብ ፣ ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ አትስጥ ፣ ሳይፈለግ ለሚመጣ የንግድ መልዕክት ምላሽ አትስጥ እንዲሁም ራስህን ከአስጋሪዎች ጠብቅ። የፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለማረጋገጥ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ ውይይት አድርግ እንዲሁም በፈጣን መልዕክት የሚደርሱ አባሪዎችን አትክፈት። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ የኢ-ሜይል እና ፈጣን መልዕክትን ደህንነት ለማረጋገጥ ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ያብራራል።

ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።

አብሪዎች የያዙ ኢ-ሜይል መልዕክቶችን በምትከፍትበት ጊዜ ጥንቃቄ አድርግ

ፋይሎችን ለጓደኞችህ ለማጋራት የኢሜይል አባሪዎችን ልትልክ ትችላለህ። በኢ-ሜይል መልዕክትህ ውስጥ እንደአባሪ ሆኖ የፎቶ ወይም የሙዚቃ ፋይል ሊደርስህ ይችላል። ነገር ግን አባሪ የያዘ መልዕክትን በምትከፍትበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፍልጋሃል ምክንያቱም ይህ በብዛት የተለመደው ቫይረሶችን የማሰራጫ መንገድ ነውና።

Page 18: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

18 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።

ሳይፈለግ ለሚመጣ የንግድ መልዕክት ምላሽ አትስጥ

ምርቶቻቸውን ወይም አገልግሎቶቻቸውን የሚያስተዋውቁ ግለሰቦችን እና ኩባንያዎችን ጨምሮ ካልታወቁ ላኪዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ያልተፈለጉ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ልትቀበል ትችላለህ። እነዚህ መልዕክቶች ያንተን የግል መረጃ እንድትሞላ የሚፈልጉ የመስመር ላይ መጠይቆች ሊሆኑም ይችላሉ። እነዚህ ሳይፈለጉ የሚመጡ መልዕክቶች አይፈለጌ መልዕክት በመባልም ይታወቃሉ።

ብዙ ጊዜ አይፈለጌ መልዕክት ለኮምፒውተርህ ጎጂ የሆነ ይዘትን ሊያካትት ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም አይፈለጌ መልዕክትን ብዙ ጊዜ የማንነት መለያዎችን ለመስረቅ ስለሚጠቀሙበት ለእንደዚህ አይነት መልዕክቶች ምላሽ በምትሰጥበት ወቅት ወሳኝ የሆነ መረጃን ሳታውቀው ልታጋራ ትችላለህ። ስለዚህ ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ ከመስጠት መቆጠብ ይኖርብሃል። አይፈለጌ መልዕክት በደረሰህ ጊዜም ወዲያው ማጥፋት ይኖርብሃል። እንደ Windows መልዕክት ያለ የኢ-ሜይል ፕሮግራም የአይፈለጌ መልዕክትን ለማዛወር እና በቀጣይ ለማጥፋት ይረዳ ዘንድ የአይፈለጌ መልዕክት አቃፊ አካቷል።

ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።

ራስህን ከአስጋሪ ጠብቅ

ማስገር ከኮምፒውተር ተጠቃሚዎች የግል መረጃን በማውጣት ጎጂ ለሆኑ ዓላማዎች ለመጠቀም የሚደረግ የተለመደ ተግባር ነው። ለምሳሌ የሆነ ሰው ከባንክ ወይም ከሌላ የሚታመን ድርጅት የመጣ መልዕክት በማስመሰል የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለአንተ ላከልህ ከዚያም እንደ ክሬዲት ካርድ ወይም የይለፍ ቃል ያለ ወሳኝ መረጃን ጠየቅህ። በቀጣይ ይህ መረጃ ስለሚሸጥ ወይም ጥቅም ላይ ስለሚውል ለገንዘብ ኪሳራ ይዳርግሃል። ስለዚህ ለእንደነዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶች የግል መረጃህን የያዘ ምላሽ ከመስጠትህ በፊት ህጋዊ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ይገባሃል።

የተለያዩ የአስጋሪ ድር ጣቢያዎች እንደነዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ይጠቀማሉ። Internet Explorer 8 በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ ከጀርባ ሆኖ የሚሰራ እና አስጋር ድር ጣቢያዎችን ለይቶ የሚያገኝ Microsoft አስጋሪ ማጣሪያ የሚባል ባህሪን አካቷል።

Page 19: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

19 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።

ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ ውይይት አድርግ

የውይይት ተግባርህ ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ የተወሰነ መሆን አለበት። ከአዳዲስ እና ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር ግንኑነትን ማዳበር እንደ የመስመር ላይ አዳኞች እና አጭበርባሪዎች ላሉ ስጋቶች እንድትጋለጥ ያደርግል።

ከታች ያለው ሰንጠረዥ ከበይነመረብ ላይ የተወሰደ ስዕላዊ እንቅስቃሴን ያሳያል።

የፈጣን መልዕክት አባሪዎችን ከመክፈት ተቆጠብ

የፈጣን መልዕክት ዋንኛ ጎጂ የሆኑ አባሪዎችን ማስተላለፊያ መንገድ ነው። ላኪውን በሚገባ ካላወቅህ በስተቀር በፈጣን መልዕክት የደረሰህን ማንኛውም አባሪ ከመክፈት መቆጠብ አለብህ። የፈጣን መልዕክት አባሪ ኮምፒውተርህን ሊጎዳ የሚችል ቫይረስ ወይም ስፓይዌር ሊይዝ ይችላል።

ርዕስ፦ ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

የሚከተሉትን ኮምፒውተርን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች በተዛማጅ ምድባቸው በትክክለኛው የአማራጭ ሳጥን ምድብ ውስጥ የዓረፍተ ነገሩን ቁጥር በመፃፍ ደርድሯቸው።

ዓረፍተ ነገር

1 የአሰሳ ታሪክን በየጊዜው ማጽዳት

2 ምትክ ውሂብ መያዝ

3 የግል መረጃን ከማጋራት መቆጠብ

Page 20: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

20 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

4 ጠባቂ ሶፍትዌር መጫን እና ማዘመን

5 የተጠቃሚ ማንነት መለያ መተግበር

6 ከሰርጎ ገብ እና ስፓይዌር መከላከል

7 የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ

8 ተዋናይ ይዘትን ማሰናከል

ምርጫ 1 ምርጫ 2

የመስመር ላይ ስጋቶችን ማስወገድ የኮምፒውተር መረጃን መጠበቅ

ርዕስ፦ ግለ ሙከራ ለትምህርት ክፍል፦ ኮምፒውተርን መጠበቅ

ጥያቄ 1 በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ አንዱ ውጤታማ ዘዴ ኮምፒውተርህን ለሚጠቀም እያንዳንዱ ግለሰብ የአጠቃቀም ገድብ መወሰን ነው። ለዚህ ዓለማ ከሚከተሉት ዘዴዎች ውስጥ የትኛውን ትጠቀማለህ?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

ስርዓተ ክወናህን ማዘመን።

የተጠቃሚ መለያ ማቀናብር።

ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጫን።

የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ።

ጥያቄ 2 በይነመረብን በምትጠቀምበት ወቅት የተለያዩ የፋይል ዓይነቶች በኮምፒውተርህ ይፈጠራሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ለደህንነት ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለተጠቃሚው ጥቅም ሲባሉ ነው የሚፈጠሩት። ከሚከተሉት ውስጥ ለእነዚህ ፋይሎች ምሳሌ የሚሆኑት የትኞቹ ናቸው?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

ኩኪ

ቫይረስ

የተዋናይ ይዘት ፋይሎች

ተውሳክ

ጥያቄ 3 ከሚከተሉት ውስጥ የኢ-ሜይል እና የፈጣን መልዕክት ልውውጥህን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የትኞቹን ዘዴዎች ትጠቀማለህ?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

ከማይታወቁ ላኪዎች የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ሳትከፍት ማጥፋት።

ሳይፈለጉ የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለጓደኛህ ለማማከር መላክ።

ላኪው የባንክ ሰራተኛ ለሆነ የኢ-ሜይል መልዕክት የግል መረጃን የያዘ ምላሽ መስጠት።

በፈጣን መልዕክቶች የደረሱ አባሪዎችን ከመክፈት መቆጠብ።

ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።

Page 21: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

21 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

መልሶች

ምርጫ 1 ምርጫ 2

የመስመር ላይ ስጋቶችን ማስወገድ የኮምፒውተር መረጃን መጠበቅ

8, 6, 3, 1

7, 5, 4, 2

መልስ 1 በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ አንዱ ውጤታማ ዘዴ ኮምፒውተርህን ለሚጠቀም እያንዳንዱ ግለሰብ የአጠቃቀም ገድብ መወሰን ነው። ለዚህ ዓለማ ከሚከተሉት ዘዴዎች ውስጥ የትኛውን ትጠቀማለህ?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

ስርዓተ ክወናህን ማዘመን።

የተጠቃሚ መለያ ማቀናብር።

ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጫን።

የይለፍ ቃልን ጠብቆ መያዝ።

መልስ 2 በይነመረብን በምትጠቀምበት ወቅት የተለያዩ የፋይል ዓይነቶች በኮምፒውተርህ ይፈጠራሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ለደህንነት ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ነገር ግን ለተጠቃሚው ጥቅም ሲባሉ ነው የሚፈጠሩት። ከሚከተሉት ውስጥ ለእነዚህ ፋይሎች ምሳሌ የሚሆኑት የትኞቹ ናቸው?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

ኩኪ

ቫይረስ

የተዋናይ ይዘት ፋይሎች

ተውሳክ

መልስ 3 ከሚከተሉት ውስጥ የኢ-ሜይል እና የፈጣን መልዕክት ልውውጥህን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የትኞቹን ዘዴዎች ትጠቀማለህ?

ሊሆኑ የሚችሉትን መልሶች ሁሉ ምረጥ።

ከማይታወቁ ላኪዎች የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ሳትከፍት ማጥፋት።

ሳይፈለጉ የመጡ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለጓደኛህ ለማማከር መላክ።

ላኪው የባንክ ሰራተኛ ለሆነ የኢ-ሜይል መልዕክት የግል መረጃን የያዘ ምላሽ መስጠት።

በፈጣን መልዕክቶች የደረሱ አባሪዎችን ከመክፈት መቆጠብ።

Page 22: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

22 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች

ክብረ ገመናን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

የመስመር ላይ አዳኞች

ከመስመር ላይ አዳኞች የመጠበቂያ መመሪያዎች

ግለ ሙከራ

የትምህርት ክፍሉ መግቢያ

ኮምፒውተሮች በትምህርት ቤቶች ፣ ኮሌጆች እና መስሪያ ቤቶች ብቻ ሳይሆን በቤቶች ውስጥም በብዛት ያገለግላሉ። ኮምፒውተሮችን ለተለያዩ ዓላማዎች ልትጠቀምባቸው ትችላለህ። ለምሳሌ የቤት ውስጥ ወጪዎችን ለመያዝ ፣ ከቤተሰቦችህና ጓደኞችህ ጋር የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ለመመለዋወጥ ፣ በይነመረብን ለመዳሰስ እንዲሁም ጌሞችን ለመጫወት እና ሙዚቃ ለማደመጥ ልትጠቀምባቸው ትችላለህ። እያንዳንዱ የቤተሰብህ አባልም የኮምፒውተሩን የተወሰነ ጥቅም ሊያገኝ ይችላል።

ኮምፒውተሮችን በቤት እና በስራ ቦታ የመጠቀም ሁኔታ ከመጨመሩ አንፃር አንተ እና የአንተ ቤተሰቦች ኮምፒውተሮችን እና በይነመረብን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ስለሚያጋጥሙ የተለያዩ ስጋቶች መረዳት አስፈላጊ ነው። በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ ኮምፒውተርህን ከእነዚህ ስጋቶች ለመጠበቅ ስለሚረዱ የተለያዩ ርምጃዎች ትማራለህ።

የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች

ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦

• ክብረ ገመናህን ለመጠበቅ ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ርምጃዎች ለይተህ ማወቅ

• የመስመር ላይ አዳኞች እንዴት እንደሚሰሩ ማብራራት እና

• ቤተሰቦችህን ከመስመር ላይ አዳኞች ለመጠበቅ የሚረዱ መመሪያዎችን ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።

ክፍለ ትምህርት 3

ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ

Page 23: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

23 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ ክብረ ገመናን ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎች

እያደገ በመጣው የኮምፒውተሮች እና የበይነመረብ ተፈላጊነት የክብረ ገመና ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባበት በርካታ ሁኔታዎች አሉ። አንተ እና የአንተ ቤተሰቦች እነዚህን የክብረ ገመና ስጋቶች መከላከል ይጠበቅባችኋል። ራስህን እና ቤተሰቦችህን ከክብረ ገመና ጥቃት ለመከላከል የሚከተሉትን ቀላል ርምጃዎች መውሰድ ትችላለህ።

ማንነትህን ደብቅ

የግል መረጃህን ከምታውቃቸው ሰዎች ውጪ ለማንም ከማጋራት ተቆጠብ። ይህ ክበረ ገመናን ለመጠበቅ ምርጥ ህግ ነው። የኢ-ሜይል መልዕክቶችን በምትለዋወጥበት ወይም የፈጣን መልዕክትን በመጠቀም በምትወያይበት ጊዜ የአንተን ወይም የምታውቃቸውን ሰዎች የግል መረጃ ዝርዝሮች አለማሳወቅህን አረጋግጥ። እንዲሁም ኮምፒውተርህን እና የኢ-ሜይል ግንኙነቶችን ለመዳረስ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን ተጠቀም።

የኮምፒውተርህን እና የአስፈላጊ መረጃህን ምትክ በየጊዜው ያዝ

በኮምፒውተርህ የሚገኝን ሁሉንም አስፈላጊ እና ወሳኝ መረጃ ምትክ ቅጂ መያዝ ጥሩ ልምድ ነው። አስፈላጊ መረጃ የሚባለው ሰነዶች ፣ የውሂ ጎታዎች ወይም የዕውቂያ መረጃ ሊሆን ይችላል። የመረጃህን ምትክ ለመያዝ እንደ ሰዲ እና ሃርድ ዲስክ ያሉ የተለያዩ የማከማቻ መሳሪያዎች መጠቀም ትችላለህ። በኮምፒውተርህ ላይ ያለን መረጃ ምትክ በየጊዜው የምትይዝ ከሆነ የመጀመሪያው መረጃ በአጋጣሚ በሚበላሽበት ወይም በሚጠፋበት ጊዜ መረጃውን እንደገና ልታገኘው ትችላለህ። እንዲሁም የተያዘውን ምትክ መረጃ አስተማማኝ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ እና የይለፍ ቃላትን እና መስጠራን በመጠቀም ተገኝነቱን መገደብ ይመከራል።

የስርዓትህን ወቅታዊ ደህንነት በየጊዜው ፈትሽ

የኮምፒውተርህን ወቅታዊ የደህንነት ደረጃ በየጊዜው ፈትሽ። የዘመኑ ስርዓተ ክወናዎች የተለያዩ የደህንነት እና ክብረ ገመና ስጋቶችን ለመከላከል የኮምፒውተርህን አቅም ለመከታተል የሚረዱ አብረዋቸው የተሰሩ ባህሪያት አሏቸው።ለምሳሌ Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል የኬላ ቅንጅቶችን ለማዋቀር ፣ የሶፍትዌር ማዘመኛ መረሃግብሮችን ለማቀናበር እና በኮምፒውተርህ የተጫነን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ውጤታማነት ለመፈተሽ የሚረዳህ በWindows 7 ውስጥ የሚገኝ ክፍል ነው።

የቫይረስ ቅኝቶችን በየዕለቱ አካሂድ

በይነመረብ በምትጠቀምበት እያንዳንዱ ቀን ሁሉ ኮምፒውተርህ በቫይረሶች ሊጠቃ የሚችልበት ዕድል አለ። ስለዚህ በኮምፒውተርህ ላይ የቫይረስ ቅኝት በየቀኑ ማካሄድ አስፈላጊ ነው። ኮምፒውተርህን ከአዳዲስ ቫይረሶች ለመከላከልም በኮምፒውተርህ ያለን የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር እንደዘመነ ማቆየት ይኖርብሃል።

ፀረ ስፓይዌር

ስፓይዌር ፕሮግራሞች ወደ ኮምፒውተርህ በድብቅ በመግባት የአንተን እና የቤተሰቦችህን ግላዊ መረጃ ሊያስተላልፉ ይችላሉ። እነዚህን ጎጂ ፕሮግራሞች ለመከላከል ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ተጠቀም ፤ እንዲሁም ሶፍትዌሩን በየጊዜው አዘምን።

የመስመር ላይ ግብይቶችን አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ከሚታመኑ ሻጮች ጋር አድርግ

የመስመር ላይ ግብይትን በምታደርግበት ጊዜ እንደ ክሬዲት ካርድ ወይም የባንክ ሒሳብ መለያህን ዝርዝሮች ያለ የግል መረጃን ለድር ጣቢያው መስጠት ያስፈልግሃል። ይህ መረጃ ለሌሎች የተጋለጠ ከሆነ ለገንዘብ መጭበርበር ሊዳረግ ይችላል። ስለዚህ የመስመር ላይ ግብይቶችህን አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ብቻ ማድረግ ጠቃሚ ነው።

ጥቃትን ለበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው አሳውቅ

ብዙዎቹ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢዎች ስነ-ምግባር የጎደለው ወይም ህገወጥ ተግባራት በደንበኞቻቸው ላይ እንዲደርሱ የማይፈቅዱ የተዘጋጁ ውሎች እና ደንቦች አሏቸው። አንድ ሰው አይፈለጌ መልዕክትን በመላክ የመስመር ላይ ክብረ ገመናህን ለማጥቃት በሚሞክርበት ጊዜ ወይም ኮምፒውተርህን ያለፈቃድ ለመጠቀም ሙከራ በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ለበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው ማሳወቅ ይኖርብሃል። ይህ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ርምጃ እንዲወስድ ያስችልዋል።

የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ካልታወቁ/ስም የለሽ ላኪዎች አጣራ

ከማታውቃቸው ግለሰቦች በርካታ ቁጥር ያላቸው የኢ-ሜይል መልዕክቶች ሊደርስህ ይችላል። እነደዚህ ያሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶች አይፈለጌ መልዕክት በመባል የሚታወቁ ሲሆን ብዙ ጊዜ ቫይረሶችን ወይም ስፓይዌር የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ። የግል መረጃህን ለማግኘት የሚሞክሩ ሰርጎ ገቦችም አይፈለጌ መልዕክት ሊልኩልህ ይችላሉ። ስለዚህ ከእነርሱ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በኢ-ሜይል ሶፍትዌር ፕሮግራሞች አይፈለጌ መልዕክትን ለማገድ የሚረዱ ማጣሪያዎችን መፍጠር ትችላለህ። ለአይፈለጌ መልዕክት በጭራሽ ምላሽ መስጠት የለብህም። ምክንያቱም የማይፈለጉ መልዕክቶች ቁጥር እንዲጨምር እና የግል መረጃን በድንገት እንድታጋራ ሊያደርግህ ይችላል።

ከተቻለ ወሳኝ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን መስጥር

ምስጠራን መጠቀም የኢ-ሜይል ግንኙነትን ምስጢራዊነት የሚያረጋግጥ ቀላል እና ውጤታማ መንገድ ነው። ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ የመክተት ሂደት ሲሆን በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የተላከ ኢ-ሜይል እንዲያነብ ከታሰበው ሰው በስተቀር ለማንም የማይነበብ ሆኖ ይታያል። ብዙዎቹ የኢ-ሜይል ሶፍትዌር ፕሮግራሞች ለምሳሌ Windows መልዕክት ይህን የኢ-ሜይል ምስጠራ ባህሪ ያቀርባሉ።

Page 24: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

24 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ የመስመር ላይ አዳኞች

በይነመረብ በሁሉም የአለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች ታዋቂ የሆነ የመገናኛ ዘዴ ነው። ስለ ማንነቱ ወይም ስለ ዓለማዎቹ በቅጡ ከማታወቀው ግለሰብ ጋር ልትግባባ እና ወዳጅነት ልትመሰርት ትችላለህ። በዚህ መሰሉ የበይነመረብ ግንኙነት ሰዎች ወጣቶችን በማለል አግባብ ላልሆነ ወይም አደገኛ ግንኙነት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። በዚህ ዓይነት ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች የመስመር ላይ አዳኞች ይባላሉ።

የመስመር ላይ አዳኞች በጥቅሉ ልጆችን በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ዒላማቸው ያደርጋሉ። ልጆች የወጣትነት ዕድሜያቸው ሲደርስ ቀስ በቀስ ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጪ እየሆኑ እና አዳዲስ ግንኙነቶችን እየፈለጉ ይመጣሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ከእነዚህ ልጆች ጋር የታማኝነት እና የወዳጅነት ግንኙነቶችን ይመሰርታሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ከገንዘብ ጋር ለተያያዘ ጥቅም አዋቂዎችንም ኢላማ ሊያደርጉ ይችላሉ።

የመስመር ላይ አዳኞች በውይይት ክፍሎች ፣ በፈጣን መልዕክት ፣ በኢ-ሜይል ወይም በውይይት መድረኮች በመጠቀም ሰለባዎቻቸውን ያጠምዳሉ። ከእነዚህ መገልገያዎች ውስጥ የውይይት ክፍሎችን አዳኞች በብዛት ይጠቀሙባቸዋል። የመስመር ላይ አዳኞች ብዙ ጊዜ የአንድ የውይይት ክፍል አባል እንደሆኑ በማስመሰል የሐሰት ማንነት ያቀርባሉ። ለምሳሌ የውይይት ክፍሉ ለልጆች ብቻ የተዘጋጀ ከሆነ የመስመር ላይ አዳኙ በውይይት ክፍሉ ውስጥ ለመሳተፍ ማንነቱን ልጅ አስመስሎ በቀላሉ ሊቀርብ ይችላል።

ርዕስ፦ ከመስመር ላይ አዳኞች የመጠበቂያ መመሪያዎች

አንተ እና የቤተሰብህ አባሎች የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ልትሆኑ ትችላላችሁ። እነዚህ አዳኞች ለገንዘብ ጥቅም ሲሉ ከአንተ ወይም ከቤተሰብህ አባሎች ጋር ግንኑነት ለመፍጠር ሊሞክሩ ይችላሉ። አዳኞች አንተ እና የቤተሰብህ አባሎችን አግባብ የሌለው ግንኙነት ውስጥ ለማስገባትም ሊሞክሩ ይችላሉ። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ ራስህን እና የቤተሰብህን አባሎች ከመስመር ላይ አዳኞች ለመጠበቅ ልትከተላቸው የምትችላቸውን የተወሰኑ መመሪያዎች ይዘረዝራል።

መመሪያ መግለጫ የአዳኝን ባህሪ የሚገልጹ ምልክቶችን እወቅ

የመስመር ላይ አዳኞች አንዳንድ የሚጠበቁ ባህሪያት አሏቸው ፤ እነዚህም እነርሱን በቀላሉ ለመለየት ሊረዱህ ይችላሉ። የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወደጅነትን መፍጠር ይወዳሉ። እንዲሁም ሁልጊዜ ወደ አላማቸው ያዘነበለ ፍላጎታቸውን እና ስሜታቸውን ይገልፃሉ። አንተ እና የቤተሰብህ አባሎች ከአስመሳይ የመስመር ላይ አዳኞች ጋር የሚደረግ ግንኙነትን ለማቆም እንደዚህ ያለ ባህሪን ለይታችሁ ስለማወቃችሁ ማረጋገጥ ይጠበቅብሃል።

በመስመር ላይ ባሉ እንግዳ ሰዎች ለሚመጡ አቅርቦቶች ጥንቃቄ አድርግ

የመስመር ላይ አዳኞች በስጦታዎች ወይም በአጓጊ አቅርቦቶች ኢላማዎቻቸውን ያማልላሉ። ለእንደዚህ ዓይነት ስጦታዎች ወይም አቅርቦቶች ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል። እንዲሁም በበይነመረብ የሚቀርቡ ስጦታዎችን እንዲጠራጠሩ የቤተሰብህን አባላት አስተምር።

ስለ መስመር ላይ ደህንነት ርምጃዎች ቤተሰብህን አስተምር

የቤተሰብህ አባላት የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማ ከመሆን እንዲርቁ ስለ ትክክለኛው የውይይት ክፍል ባህሪ አስተምራቸው። ገላጭ ባልሆኑ እና ነፃ በሆኑ የገጽ ስሞች እንዲጠቀሙ ንገራቸው። የገጽ ስሞች ትክክለኛ ስምን ፣ ዕድሜን ፣ ፆታን ወይም የመገኛ መረጃን የሚሰጡ መሆን የለባቸውም ምክንያቱም ይህ መረጃ አግባብ ለሌለው ጥቅም ሊውል ይችላል።

አንዳንድ የድር ጣቢያዎች በሀሰተኛ አስተያየቶች መረጃን ለማውጣት ይሞክራሉ። ለእንዚህ የድር ጣቢያዎች ምንም ዓይነት የግል መረጃ ካላንተ ፈቃድ እንዳያሳውቁ ለቤተሰብህ አባላት ንገራቸው። እንዲሁም እንደ ስም ፣ የአያት ስም ፣ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር ያሉ የግል መረጃ ዝርዝሮችን በውይይት ክፍሎች እና የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ውስጥ አሳልፈው እንደማይሰጡ አረጋግጥ። የቤተሰብህ አባላት የተጠቀሚ ስማቸውን እና የይልፍ ቃላቸውን ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ለማንም ማጋራት የለባቸውም።

ልጆች የድር ጣቢያዎችን ሲጎበኙ መመሪያዎችን ስጣቸው

እንደ ወላጅነት ወጣት ልጆች አግባብ ያልሆኑ ወይም ከአስመሳይ የመስመር ላይ አዳኞች ጋር የሚያገናኙ የድር ጣቢያዎችን እንዳይጎበኙ ከልክላቸው። ወላጆች ልጆች ማንኛውንም የድር ጣቢያ በሚጎበኙበት ወቅት መመሪያዎችን ለልጆቻቸው እንዲሰጡ ይመከራል።

እንደ ወላጅ ልጆች የማይመች ዓይነት ወይም ደስ የማይል ይዘት ያለው የድር ጣቢያን እየጎበኙ ከሆነ እንዲተዉ ወይም ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠጥ ያስፈልጋል። እንዲሁም ከመጠን ያለፈ የግል መረጃን የሚጠይቁ የድር ጣቢያዎችን እንዳይጠቀሙ ልጆችህን አስተምራቸው።

Page 25: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

25 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ልጆች የሚጎበኟቸውን የድር ጣቢያዎችን እወቅ

ወላጆች ልጆቻቸው የሚጎበኟቸውን የድር ጣቢያ ዓይነቶች በየጊዜው መፈተሸ ይኖርባቸዋል። ቀድሞ ተጎብኝተው የነበሩ የድር ጣቢያዎችን የአሳሹን ታሪክ በማየት መከታተል ትችላለህ። ወይም የኮምፒውተርን የመስመር ላይ እንቅስቃሴ ለመከታተል የሚያግዙ የሶፍትዌር ፕሮግራችሞችን መጠቀም ትችላለህ።

አግባብነት የሌላቸውን የድር ጣቢያዎች ከመዳረስ አግድ

የአሳሽህን የይዘት አማካሪ ባህሪ እንዲሰራ በማድረግ የቤተሰብህ አባላት ሊጎበኟቸው የሚችሉትን የድር ጣቢያዎች መቆጣጠር ትችላለህ። ይህን ባህሪ በመጠቀም ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን የድር ጣቢያዎች ልጆች እንዳይጎበኙ ማገድ ትችላለህ። የድር ጣቢያዎችን ለይቶ ለማገድ የሚያግዙ የሶፍትዌር ፕሮግራሞችን መጫንም ትችላለህ።

የውይይት እንቅስቃሴዎችን ተቆጣጠር

በልዩ ሁኔታ የተሰራ ሶፍትዌር የውይይት እንቅስቃሴዎችን ሊቆጣጠር እና በኮምፒውተርህ ላይ አግባብነት የሌለውን የመረጃ ልውውጥ ሊያመለክት ይችላል። ይህን ሶፍትዌር በመጫን የልጆችህን የውይይት እንቅስቃሴዎች መከታተል ትችላለህ።

ርዕስ፦ ግለ ሙከራ

እያንዳንዱን ጥንድ ዓረፍተ ነገር እውነት እና ሐሰት የሆኑ ዓረፍተ ነገሮችን ይዟል። እውነት የሆነውን ዓረፍተ ነገር በቀኝ በኩል በሚገኘውና እውነት በሚለው አምድ ስር ምልክት በማድረግ አመልክት።

ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት

1 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ ይችላል።

2 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ አይችልም።

3 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን ይፈጥራሉ።

4 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን አይፈጥሩም።

5 ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።

6 ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።

7 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር ይቻላል።

8 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር አይቻልም።

9 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በማመቅ መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።

10 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ በመክተት መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።

11 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው አያደርጉም።

12 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው ያደርጋሉ።

13 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው ይገባል።

14 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው አይገባም።

15 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች አያማልሉም።

16 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች ያማልላሉ።

17 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን አይገባም።

18 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን ይገባል።

ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።

Page 26: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

26 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት

1 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ ይችላል።

2 ለአይፈለጌ መልዕክት ምላሽ መስጠት የግል መረጃህን አሳልፈህ እንድሰጥ ሊያደርግህ አይችልም።

3 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን ይፈጥራሉ።

4 የመስመር ላይ አዳኞች ቶሎ ወዳጅነትን አይፈጥሩም።

5 ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።

6 ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ጎጂ ፕሮግራሞችን ለመፈተሽ ያግዝሃል።

7 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር ይቻላል።

8 የውይይት እንቅስቃሴን መቆጣጠር አይቻልም።

9 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በማመቅ መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።

10 ምስጠራ የኢ-ሜይል መልዕክትን በኮድ በመክተት መነበብ እንዳይችል ያደርጋል።

11 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው አያደርጉም።

12 የመስመር ላይ አዳኞች ልጆችን ኢላማቸው ያደርጋሉ።

13 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው ይገባል።

14 ልጆች የድር ጣቢያዎችን ለብቻቸው እንዲጎበኙ ሊፈቀድላቸው አይገባም።

15 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች አያማልሉም።

16 የመስመር ላይ አዳኞች ኢላማዎቻቸውን በስጦታዎች ያማልላሉ።

17 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን አይገባም።

18 ለውይይት የምትጠቀምበት የገጽ ስም እውነተኛ ስምህ ሊሆን ይገባል።

Page 27: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

27 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች

የኮምፒውተር ደህንነት ቅንጅቶችን ማወቀር

ኮምፒውተርን እንደዘመነ ማቆየት

ግለ ሙከራ

የትምህርት ክፍሉ መግቢያ

ኮምፒውተርህን ከበይነመረብ ጋር ስታገናኝ የኮምፒውተርህ ሶፍትዌር እና መረጃ በቀሪው አለም መገኘት የሚችሉ ይሆናሉ። ከበይነመረብ መገናኘት የኮምፒውተርህን በቫይረሶች ፣ ስፓይዌር እና ሰርጎ ገቦች የመጠቃት አቅም ከፍ ያደርገዋል። ነገር ግን በኮምፒውተርህ ላይ ያሉትን የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች በማዋቀር እና ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ሶፍትዌርን እንደዘመነ በማቆየት እንዚህን የደህንነት ስጋቶች መቀነስ ትችላለህ።

በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ በስርዓተ ክወናህ ያሉትን የደህንነት ቅንጅቶች በማዋቀር የኮምፒውተርህን ደህንነት እንዴት ከፍ እንደምታደርግ ትማራለህ። ይህ የትምህርት ክፍል የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌርን በራስ ሰር ለማዘመን ኮምፒውተርህን እንዴት እንደምታዋቅርም ያብራራል።

የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች

ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦

• በኮምፒውተርህ ያሉ የተለያዩ የደህንነት ጥበቃ ቅንጀቶችን ማብራራት እና

• ኮምፒውተርህ እንደዘመነ ለማቆየት ያሉትን አማራጮች ለይተህ ማወቅ ትችላለህ።

ክፍለ ትምህርት 4

ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት

Page 28: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

28 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ የኮምፒውተር ደህንነት ቅንጅቶችን ማወቀር

በበይነመረብ ላይ ትልቁ የኮምፒውተርህ ስጋቶች ቫይረሶች እና ሰርጎ ገቦች ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ስጋቶች የሚከሰቱት የኮምፒውተርህ የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች በትክክል ሳይዋቀሩ ሲቀሩ ወይም የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር ሲጠፋ ወይም ጊዜው ያለፈበት ሲሆን ነው። የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች በኮምፒውተርህ ላይ የሚዋቀሩት የስርዓተ ክወና ስትጭን ነው። ነገር ግን እነዚህን የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች አንተ በፈለከው መንገድ ልታሻሽላቸው ትችላለህ።

ለምሳሌ በWindows 7 የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በመጠቀም ማየት እና ማሻሻል ትችላለህ። Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በመጠቀም የሚከተሉትን ርምጃዎች መተግበር ትችላለህ።

• ለምትጎበኛቸው የድር ጣቢያዎች የክብረ ገመና እና የደህንነት ጥበቃ ደረጃዎችን ለመወሰን የበይነመረብ የድኅንነት ጥበቃ አማራጮችን ተጠቀም።

• በበይነመረብ የሚደረግን ያልተፈቀደለት የኮምፒውተር መዳረስን ለመከላከል የኬላ ቅንጅቶችን አሻሽል።

• አዳዲስ ቫይረሶችን የመከላከል አቅሙን የተሻለ ለማድረግ የዘመነ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር በራስ ሰር እንዲያወርድ እና እንዲጭን አድርገህ ኮምፒውተርህን አዋቅር።

• ያልተፈለገ ጎጂ ሶፍትዌርን ከኮምፒውተርህ ውስጥ ፈልጎ ለማግኘት እና ለማስወገድ የማልዌር መከላከያ ቅንጅቶችን አዋቅር።

በዚህ ትዕይንት ውስጥ በWindows 7 የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን በመጠቀም እንዴት እንደምታዋቅር ትመለከታለህ።

የሚከተለው ሰንጠረዥ የመስመር ላይ ትዕይንት ደረጃዎችን እና ማስረጃዎችን ይዟል።

የደረጃ ዝርዝር

1 የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን ማቀናበር

2 የመቆጣጠሪያ ፓነልን ለመክፈት ፣ ጀምር (Start) አዝራርን ጠቅ አድርግና በመቀጠል የመቆጣጠሪያ ፓነል (Control Panel) ላይ ጠቅ አድርግ።

3 Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን ለመክፈት ፣ በመቆጣጠሪያ ፓነል ውስጥ ፣ የደህንነት ጥበቃ (Security) ላይ ጠቅ አድርግና በመቀጠል የደህንነት ጥበቃ ማዕከል (Security Center) ላይ ጠቅ አድርግ።

4 የኮምፒውተርህን የኬላ ቅንጅቶች ለመመልከት ፣ በWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል መስኮት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ Windows ኬላ (Windows Firewall) ላይ ጠቅ አድርግ።

5 ለኬላ የተዘጋጁትን አማራጮች ለመመልከት ፣ በቀኝ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ ቅንጅቶችን ለውጥ (Change settings) ላይ ጠቅ አድርግ።

6 ቅንጅቶቹን ለመለወጥ መፈለግህን ለማረጋገጥ ፣ በተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ የመልዕክት ሳጥን ላይ ቀጥል (Continue) ላይ ጠቅ አድርግ።

7 በWindows ኬላ ቅንጅቶች (Windows Firewall Settings) ሳጹነ ተዋስኦ ውስጥ ፣ ጠቅላላ (General) ትር ላይ ያሉትን አማራጮች ተመልከት።

8 ለኬላ ያሉትን የተለዩ ለመመልከት ፣ የተለዩ (Exceptions) ትርን ጠቅ አድርግና በመቀጠል ፣ የተለየን ለማንቃት አመልካች ሳጥኑን ምረጥ (To enable an exception, select its check box ) መለያ ስር ባሉት ዝርዝሮች ወደታች ሸብልል።

Page 29: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

29 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

9 በWindows ኬላ የተከለከሉ የአውታረመረብ ተያያዦችን ለመመልከት ፣ የላቁ (Advanced )ትርን ጠቅ አድርግ።

10 በWindows ኬላ ቅንጅቶች (Windows Firewall Settings) ሳጹነ ተዋስኦ ውስጥ ፣ ሰርዝ (Cancel) ላይ ጠቅ አድርግና በመቀጠል በWindows ኬላ መስኮት ውስጥ ፣ ዝጋ (Close) አዝራርን ጠቅ አድርግ።

11 የራስ ሰር ማዘመኛዎችን ቅንጅቶች ለመመልከት ፣ በWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል መስኮት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ Windows ማዘመኛ (Windows Update) ላይ ጠቅ አድርግ።

12 በWindows ማዘመኛ መስኮት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ ቅንጅቶችን ለውጥ (Change settings) ላይ ጠቅ አድረግ።

13 በቅንጅቶችን ለውጥ መስኮት ውስጥ ፣ ሰርዝ (Cancel) ላይ ጠቅ አድርግና በመቀጠል በWindows ማዘመኛ መስኮት ውስጥ ዝጋ (Close) አዝራርን ጠቅ አድርግ።

14 Windows መከታን ለመመልከት ፣ በWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል መስኮት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ Windows መከታ ላይ ጠቅ አድርግ።

15 በWindows መከታ ያሉትን አማረጮች ለመመልከት ፣ በWindows መከታ መስኮት ውስጥ መሳሪያዎች (Tools) ላይ ጠቅ አድርግ።

16 በመሳሪያዎች እና ቅንጅቶች (Tools and Settings) ገጽ ላይ ፣ በቅንጅቶች (Settings) ስር ፣ አማራጮች (Options) ላይ ጠቅ አድርግ።

17 ያሉትን አማራጮች ለመመልከት በአማራጮች (Options) ገጽ ወደታች ሸብልል።

18 በWindows መከታ መስኮት ውስጥ ሰርዝ (Cancel) ላይ ጠቅ አድርግ።

19 የWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን ወደነበረበት ለመመለስ ፣ በተግባር አሞሌ ላይ ፣ በመቆጣጠሪያ ፓነል የግራ ክፍለ መቃን ውስጥ\የደህንነት ጥበቃ አዝራር ፣ Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል (Windows Security Center) አዝራር ላይ ጠቅ አድርግ።

20 የበይነመረብ አማራጮችን ለመመልከት ፣ በWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል መስኮት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ የበይነመረብ አማራጮች (Internet Options) ላይ ጠቅ አድርግ።

21 ጠቅላላ ቅንጅቶችን ለመመልከት ፣ የበይነመረብ ባህሪያት (Internet Properties) ሳጹነ ተዋስኦ ውስጥ ፣ ጠቅላላ (General) ትርን ጠቅ አድርግ።

22 የድር አሳሹን የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች ለመመልከት የደህንነት ጥበቃ (Security) ትርን ጠቅ አድርግ።

23 የበይነመረብ የክብረ ገመና ቅንጅቶችን ለመመልከት ክብረ ገመና (Privacy) ትርን ጠቅ አድርግ።

24 የይዘት ቅንጅቶችን ለመመልከት ይዘት (Content) ትርን ጠቅ አድርግ።

25 የበይነመረብ መያያዞችን ቅንጅቶች ለመመልከት መያያዞች (Connections) ትርን ጠቅ አድርግ።

26 የበይነመረብ የፕሮግራም ቅንጅቶች ለመመልከት ፕሮግራሞች (Programs ) ላይ ጠቅ አድርግ።

27 የድር አሳሹን የላቁ ቅንጅቶች ለመመልከት የላቁ (Advanced) ትርን ጠቅ አድርግ።

28 የበይነመረብ ባህሪያትን ሳጹነ ተዋስኦ ለመዝጋት እሺ (OK) ላይ ጠቅ አድርግ።

Page 30: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

30 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አስረጂ

የWindows 7 ቅንጅቶችን ለመለወጥ የመቆጣጠሪያ ፓነልን መጠቀም ትችላለህ።

የመቆጣጠሪያ ፓነል Windows የደህንነት ጥበቃ ማዕከልን ይዟል ፤ ይህም የኮምፒውተርህን ደህንነት ለመቆጣጠር እና ለማሳደግ የሚያግዙ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠሃል። አማራጮቹን በመጠቀም እንደ ኬላ ቅንጅቶች ፣ ራስሰር ማዘመኛዎች ፣ የማልዌር መከላከያ እና የበይነመረብ ደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች ያሉ የተለያዩ የደህንነት ጥበቃ መገልገያዎችን ሁኔታ መፈተሸ ትችላለህ።

Page 31: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

31 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

Windows ኬላ ኮምፒውተርህን በበይነመረብ ወይም በኮምፒውተር አውታረብ ከሚመጣ ያለፈቃድ መዳረስ ይከላከላል።

የWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል መስኮት የቀኝ ክፍለ መቃን Windows ኬላ እንደ በራ ወይም እንደ ጠፋ ያሳያል። ቅንጅቶቹን ለውጠህ ካልሆነ በስተቀር Windows ኬላ ሁልጊዜ እንደ በራ ነው።

Windows ኬላ መስኮት የቀኝ ክፍለ መቃን እንደ የአውታረመረብ አካባቢ እና የማስታወቂያ ዝርዝሮችን የመሰሉ የአሁን ጊዜ ቅንጅቶችን ያሳያል።

ቅንጅቶቹን እንዳንተ ፍላጎት ልታሻሽላቸው ትችላለህ። ቅንጅቶቹን ለመለወጥ አስተዳዳሪ ሆነህ ወደ ኮምፒውተሩ መግባት ይኖርብሃል። በWindows 7 ውስጥ ያሉ ቅንጅቶችን ለመለወጥ ከሞከርክ የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ በኮምፒውተርህ ያለፈቃድ የሚደረግን ቅንጅቶችን የማሻሻል ሙከራ ይከላከልልሃል።

Page 32: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

32 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ የአስተዳዳሪን የይለፍ ቃልን እንድትወስን ያሰናዳሃል ወይም የኮምፒውተርህ አፈፃጸም ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ተግባሮችን ከማከናወኑ ወይም ሌሎች ተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ቅንጅቶችን ከመለወጡ በፊት ያንተን ፈቃድ እንዲጠይቅህ ያደርግልሃል።

የWindows ኬላ ቅንጅቶች ሳጹነ ተዋስኦ ጠቅላላ የሚለው ትር ለWindows ኬላ ሶስት ቅንጅቶችን ያቀርባል።

Windows ኬላ ሁሌ የበራ ስለሆነ የመጀመሪያው አማራጭ ተምርጧል።

ከኮምፒውተርህ ጋር የመገናኘት ሙከራዎችን በሙሉ ለመከልከል ከፈለግህ ፣ ሁሉንም ገቢ መያያዞች አግድ የሚለውን አመልካች ሳጥን መምረጥ ትችላለህ።

አጥፋ (አይመከርም) አማራጭ Windows ኬላን ለማሰናከል ይረዳሃል። Windows ኬላን ለማሰናከል ከፈለግህ ፣ የኮምፒውተርህን ደህንነት ጠብቆ የሚያቆይ ሌላ ኬላ መጠቀምህን ማረጋገጥ አለብህ።

Page 33: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

33 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የኮምፒውተርህን ሁሉንም ገቢ መያያዞች አግደሃል እንበል። የተወሰኑ ፕሮግራሞች በWindows ኬላ መረጃ እንዲልኩ እና እንዲቀበሉ መፍቀድ ከፈለግህ ፣ እነዚህን ፕሮግራሞች የተለዩ ብለህ መዘርዘር ትችላለህ። አንድን ፕሮግራም ሁልጊዜ የተለየ ሆኖ በWindows ኬላ እንዲገናኝ ከፈቀድህ ኮምፒውተርህን የበለጠ ለጥቃቶች የተጋለጠ እንዲሆን ታደርገዋለህ። ለማታውቃቸው መተግበሪያዎች የተለዩ አታድርግ።

ኮምፒውተርህ ከተለያዩ አውታረመረቦች ጋር ሊያያዝ ወይም በእነዚህ አውታረመረቦች ሊገኝ የሚችል ሊሆን ይችላል። የላቀ የሚለው ትር ላይ በWindows ኬላ በመጠቀም ልትከለክለው የምትፈልጋቸውን የአውታረመረብ ግንኙነቶች መወሰን ትችላለህ።

Page 34: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

34 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ማዘመኛዎች የኮምፒውርህን ደህንነት እና አፈፃጸም የሚያሳድጉ የሶፍትዌር ጭማሮዎች ናቸው። Windows ራስሰር ማዘመኛ የደህንነት ጥበቃ እና ሌሎች አስፈላጊ ዝምኖችን ማዘመኛዎቹ በተገኙበት ጊዜ ሁሉ ይጭናል።

ራስሰር ማዘመኛን ለአዳዲስ ዝምኖች Windows ማዘመኛ ድረ ጣቢያን እንዲፈትሽ ፣ ዝምኖቹን እንዲያወርድ ወይም ያንተን ፈቃድ መጠየቅ

Page 35: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

35 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ሳያስፈልገው በተወሰነ ጊዜ ላይ በቀጥታ እንዲጭን አድርገህ ማዋቀር ትችላለህ።

ስፓይዌር ማስታወቂያዎችን ሊያሳይ ፣ ስለ አንተ መረጃ ሊሰበስብ ወይም ያንተን ፈቃድ በአግባቡ ሳይጠይቅ የኮምፒውተርህን ቅንጅቶች ሊለውጥ የሚችል ሶፍትዌር ነው።

Windows መከታ ኮምፒውተርን ከብቅ-ባዮች ፣ አፈፃጸም ከሚያዘገይ እና በስፓይዌር እና ሌላ ያልተፈለገ ሶፍትዌር ምክንያት የሚከሰቱ የደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል የሚረዳ የፀረ ስፓይዌር ፕሮግራም ነው።

Windows ኬላን ከተጠቀምክ የቫይረስ ብየናዎቹ የዘመኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብህ። እነዚህ ብየናዎች ስለ አስመሳይ የሶፍትዌር ስጋቶች መረጃን የያዙ ናቸው።

በWindows መከታ መስኮት ውስጥ የሁኔታ ስፍራው የመጨረሻውን ቅኝት ሰዓት እና ቀን ፣ የቅኝት መረሃግብሩን እና Windows መከታ በወቅቱ የሚጠቀመውን የቫይረስ ብየናውን ስሪት ማሳየቱን አስተውል።

Windows መከታ አደገኛ ፕሮግራሞች በብዛት የሚጠቀሙባቸው ቦታዎች ላይ በተወሰነ የጊዜ ክፍተት ፈጣን ቅኝት ያካሂዳል። Windows መከታ አደገኛ ፕሮግራሞች በኮምፒውተርህ ላይ ለማሄድ ወይም ራሳቸውን ለመጫን በሚሞክሩበት ጊዜም ማስጠንቀቂያ ያሳየሃል።

Page 36: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

36 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የWindows መከታን አገልግሎቶች ለመቆጣጠር የተለያዩ ቅንጅቶችን ማሻሻል ትችላለህ።

በአማራጭ ገጽ ላይ ድግግሞሹን እና የራስ ሰር ቅኝት አይነቱን መምረጥ ትችላለህ።

Windows መከታ ስፓይዌር እና አስመሳይ ጎጂ ሶፍትዌርን ከኮምፒውተርህ ላይ ያገኛል። የተገኘው ስፓይዌር እና ጎጂ ሶፍትዌር የተለያዩ የማስጠንቀቂያ ደረጃዎች ተዘጋጅቶላቸዋል።

የማስጠንቀቂያ ደረጃዎቹ Windows መከታ ለተገኙት ስጋቶች ምን ዓይነት ርምጃ እንደወሰደ ይበይናሉ። ራስ ሰር ቅኝት ለሚያገኘው ለእያንዳንዱ ደረጃ ጎጂ ሶፍትዌር የተለያየ ርምጃ ወይም ምላሽ ማዋቀር ትችላለህ።

Windows መከታ ለኮምፒውተርህ ወቅታዊ መከላከያም ይሰጣል።

የላቁ አማራጮች የሚለው Windows መከታ ምን ዓይነት ፋይሎችን መቃኘት እንዳለበት ለመምረጥ ያግዝሃል። እንዲሁም ፋይሎችን ከራስ ሰር ቅኝት ማስወጣት ትችላለህ።

Page 37: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

37 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የበይነመረብ ደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን በበይነመረብ ባህሪያት ሳጹነ ተዋስኦ ውስጥ የበይነመረብ አማራጮች አገናኝን በመጠቀም ማሻሻል ትችላለህ።

በጠቅላላ ትር ላይ የአሳሽህን መነሻ ገጽ መወሰን ትችላለህ።

Internet Explorer 8 የጎበኛሃቸውን የድር ጣቢያዎች ቅደም ተከተል ዝርዝር ወይም ታሪክ ይይዛል። የተወሰኑ ቀናትን ታሪክ እንዲያስቀምጥ አድርገህ የታሪክ ቅንጅቶችን ማሻሻል ትችላለህ። አንድ ድረ ገጽ በምትጎበኝበት ጊዜ የድረ ገጹ ቅጂ እና ተያያዥ ምስሎችና ሌሎች ፋይሎች በኮምፒውተርህ ላይ ይከማቻሉ። እነዚህን ፋይሎች አጥፋ አዝራርን ጠቅ በመድረግ ማጥፋት ትችላለህ።

በዚህ ትር ላይ የድር ጣቢያዎች እንዴት መታየት እንዳለባቸው ቅርጸ ቁምፊን ፣ ቀለም እና የቋንቋ ቅንጅቶችን በመምረጥ ማወቀር ትችላለህ። የድር ጣቢያው ሲፈጠር በተተገበሩት ቅንጅቶች ፋንታ እነዚህን ቅንጅቶች ለመተግበር የተደራሽነት አዝራርን ጠቅ ማድረግ እና ተገቢ የሆኑትን አማራጮች መምረጥ ይገባሃል። ለምሳሌ የቅርጽ ቁምፊ አዝራርን በመጠቀም የቅርጸ ቁምፊ ቅጡን ከወሰንክ በድር ጣቢያዎች ላይ የቅርጸ ቁምፊ መጠንን ተው የሚለውን አማራጭ መምረጥ አለብህ ፤ በዚህም የድር ጣቢያዎቹ አንተ እንደፈለከው ሆነው ይታያሉ።

Page 38: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

38 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

Internet Explorer በአለም አቀፍ ድር ላይ ያሉትን የድር ጣቢያዎች በሙሉ በአራት ዞኖች ይመድበቸዋል፦ በይነመረብ ፣ የአካባቢ ውስጠመረብ ፣ የታመኑ ጣቢያዎች እና የተገደቡ ጣቢያዎች። እያንዳንዱ ዞን የተወሰነ በዞኑ ያሉ ጣቢያዎች ጋር የተያያዙ የተለያዩ የደህንነት ስጋቶችን ለማመልከት የሚረዳ የደህንነት ጥበቃ ደረጃ አለው። በደህንነት ጥበቃ ትር ላይ ፣ አንድ የተወሰነ ዞን መምረጥና በመቀጠል ለተመረጠው ዞን የደህንነት ጥበቃ ደረጃውን መምረጥ ትችላለህ።

እንደ የመስመር ላይ መገበያያ ጣቢያዎች ፣ የመስመር ላይ ትምህርት ጣቢያዎች እና ሌሎች የግል መረጃህን እንድታስገባ የሚፈልጉ ጣቢያዎች የመሳሰሉ የተለያዩ የድር ጣቢያ ዓይነቶችን በምትዳስስበት ጊዜ ለማንነት ስርቆት እና መጭበርበር ልትጋለጥ ትችላለህ።

የተለያዩ የድር ጣቢያዎች ኩኪዎች ተብለው የሚጠሩ ስላንተ መረጃን የሚያከማቹ ፋይሎችን በኮምፒውተርህ ላይ ይፈጥራሉ። የክብረ ገመና ትር ምን ዓይነት ኩኪዎች በኮምፒውተርህ ላይ መቀመጥ እንዳለባቸው የምትወስንበትን የክብረ ገመና ቅንጅቶች እንድትመርጥ ይረዳሃል።

ከዚህ በተጨማሪ በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ የብቅ-ባዮች መስኮቶች እንዳይከፈቱ መምረጥ ትችላለህ።

Page 39: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

39 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

በይዘት ትር ላይ ፣ ልጆችህ ወይም ሌላ ወጣት ተመልካቾች በይነመረብን በሚዳስሱበት ጊዜ የሚያዩትን ይዘት ለመቆጣጠር የወላጆች ቁጥጥር ባህሪን ማንቃት ትችላለህ። ለምሳሌ ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን የድር ጣቢያዎች ልጆች እንዳይጎበኙ መገደብ ትችላለህ።

የይዘት አማካሪ ባህሪ የተወሰኑ የድር ጣቢያዎችን በተሰጣቸው የይዘት ደረጃ መሰረት ያግዳል ወይም ይፈቅዳል።

ሰርቲፊኬቶች እንደ ግዢ ያለ የመስመር ላይ መገበያየት ውስጥ የሚጠቀሙትን የሰው ወይም መሳሪያ ማንነት መለያ ለማረጋገጥ ይጠቅማሉ።

ሌላው ዳሰሳን የሚያፋጥን የInternet Explorer 8 ባህሪ ራስ-ጨርስ ነው። ራስ-ጨርስ በአድራሻ አሞሌ ፣ በቅፆች ወይም የይለፍ ቃሎች ላይ የፃፍከውን መረጃ ያስቀምጥና የድር ጣቢያዎቹን ዳግም ስትጎበኝ አንድ አይነት መረጃ መፃፍ ስትጀምር መረጃውን ወዲያው ይሰጠሃል።

የዜና እና መጽሔት ጣቢያዎችን የመሰሉ አንዳንድ የድር ጣቢያዎችን በምትጎበኝበት ጊዜ ወደ ምግቦች ባህሪ ልትመጣ ትችላለህ። ምግቦች በድር ጣቢያ ላይ የታተመ በተደጋጋሚ የዘመነ ይዘትን ይይዛሉ። ለምግብ ከተመዘገብህ Internet Explorer ጣቢያውን ለመጨረሻ ጊዜ ከጎበኘኸው ጀምሮ አዲስ የሆነ ይዘትን በራሱ በመፈተሽ ያወርዳል።

በተያያዦች ትር ላይ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቀናበር ትችላለህ። እንደ አካባቢ አውታረመረብ ቅንጅቶች ፣ የደውል ቅንጅቶች እና ምናባዊ የግል አውታረመረብ ቅንጅቶች ያሉ የተለያዩ ቅንጅቶችን ለኮምፒውተርህ መወሰን ትችላለህ።

Page 40: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

40 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

Windows 7 እንደ ኢ-ሜይል ፣ የዜና ቡድኖች ፣ የቀን መቁጠሪያ እና የበይነመረብ ጥሪዎች ላሉ የበይነመረብ አገልግሎቶች የሚጠቀማቸውን ፕሮግራሞች ለመወሰን የፕሮግራሞችን ትርን መጠቀም ትችላለህ።

ነባሪ የድር አሳሽን መወሰን ትችላለህ።

የድር አሳሾች የተለያዩ ላይ-ተጨማሪዎችን ይጠቀማሉ። ከእነዚህም ውስጥ የበይነተገኝ እና መልቲሚዲያ ይዘትን እንድታይ በማስቻል በድር ጣቢያ ላይ ያለህን ተሞክሮ የሚያሳድጉ ሰሪ አሞሌዎች እና ቅጥያዎች ይጠቀሳሉ።

ላይ-ተጨማሪዎችን አቀናብር የሚለውን አዝራር ጠቅ በማድረግ በኮምፒውተርህ ላይ ተጭነው ያሉ የተለያዩ ላይ-ተጨማሪዎችን ማግበር እና ማሰናክል ትችላለህ።

የላቁ የሚለው ትር ረቂቅ የድር አሳሽህ መስተካከያ ባህሪ ይዟል።

ለምሳሌ የበይነመረብ ይዘትን ተነባቢነት ለማሻሻል እና አካለ ስንኩላን ለሆኑ ሰዎች የመጠቀም ተሞክሯቸውን ለማሳደግ የድር አሳሹን የተደራሽነት አማራጮችን መለወጥ ትችላለህ።

የአሰሳ አማራጮችን ግላዊነት በማላበስ ድረ-ገፆችን ፈጥነው እንዲጭኑ ማድረግ ትችላለህ።

Page 41: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

41 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ ኮምፒውተርን እንደዘመነ አቆይ

አዳዲስ በሽታዎችን ለመከላከል አዳዲስ መድሀኒቶች በየጊዜው ይፈጠራሉ። በተመሳሳይ የኮምፒውተር ኢነዱስትሪ አዳዲስ ቫይረሶችን ፣ ተውሳኮችን እና ስፓይዌርን ለመከላከል የፀረ ቫይረስ ሶፍትዌርን እና ተመሳሳይ ምርቶችን ስሪት በየጊዜው ያዘምናል። ኮምፒውተርህን በተሻለ ሁኔታ ለመከላከል በዘመኑ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር ስሪቶች ኮምፒውተርህን እንደዘመነ ማቆየት ይኖርብሃል።

የMicrosoft ማዘመኛ የድር ጣቢያ የኮምፒውተርህን ስርዓተ ክወና ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑትን የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎች ያቀርብልሃል። እነዚህን የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎች ከዚህ የድር ጣቢያ ማውረድና እና በኮምፒውተርህ ላይ መጫን ትችላለህ። ማዘመን የፈለከውን የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌርን ተከታትሎ ማካሄድ ከባድ መስሎ ከታየህ ይህን የማዘመን ሂደት በራሱ እንዲሰራ ኮምፒውተርህን ማዋቀር ትችላለህ።

በዚህ ትዕይንት ውስጥ ኮምፒውተርህን እንደዘመነ ለማቆየት ልትጠቀምባቸው የምትችላቸውን በWindows ማዘመኛ ውስጥ ያሉ የተለያዩ አማራጮች ትመለከታለህ።

የሚከተለው ሠንጠረዥ የመስመር ላይ ትእይንት ደረጃዎችን እና ማስረጃዎችን ይዟል።

የደረጃ ዝርዝር

1 ኮምፒውተርን እንደዘመነ ማቆየት

2 Windows ማዘመኛን ለመክፈት ፣ ጀምር (Start) አዝራር ላይ ጠቅ አድርግ ፣ ሁሉም ፕሮግራሞች (All Programs) ላይ ጠቅ አድርግና በመቀጠል Windows ማዘመኛን (Windows Update) ላይ ጠቅ አድርግ።

3 በWindows መስኮት የግራ አሞሌ ውስጥ የሚታዩትን አገናኞች ተመልከት።

4 የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎችን በራስ ሰር ለማውረድ እና በኮምፒውተርህ ላይ ለመጫን፣ በWindows ማዘመኛ መስኮት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ ማዘመኛዎችን ፈልግ (Check for updates) ላይ ጠቅ አድርግ።

5 ያሉትን ማዘመኛዎች ዝርዝር ለመመልከት ፣ በቀኝ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ ለኮምፕዩተርህ ማዘመኛዎችን አውርድና ጫን (Download and install updates for your computer) ስፍራ ውስጥ ፣ ያሉ ማዘመኛዎችን እይ (View available updates) ላይ ጠቅ አድርግ።

6 ለWindows ማዘመኛ ያሉትን አማራጮች ለማየት ፣ በWindows ማዘመኛ መስኮት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ ፣ ቅንጅቶችን ለውጥ (Change settings) ላይ ጠቅ አድርግ።

7 የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎችን በተወሰነ ጊዜ እና ድግግሞች በራስ ሰር ለማውረድና ለመጫን ፣ ማዘመኛዎችን በራስሰር ጫን (ይመከራል) (Install updates automatically (recommended)) አማራጭ መመረጡን አረጋግጥ።

8 የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎች በራስ ሰር ከወረዱ በኋላ ማስጠንቀቂያ ለመቀበል ፣ ማዘመኛዎችን ፈልግ፤ ይሁን እንጂ የመጫን አማራጩን እኔ ልውሰድ (Download updates but let me choose whether to install them) ላይ ጠቅ አድርግ።

9 የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎች በሚኖሩበት ጊዜ ማስጠንቀቂያ ለመቀበል ፣ ማዘመኛዎችን ፈልግ፤ ይሁን እንጂ ለማውረድና ለመጫን አማራጩን እኔ ልውሰድ (Check for updates but let me choose whether to download and install them) ላይ ጠቅ አድርግ።

10 ራስ ሰር ማዘመኛን ለማሰናክል ማዘመኛዎችን መቼም አትፈልግ (አይመከርም) (Never check for updates (not recommended)) ላይ ጠቅ አድርግ።

11 የሚመከሩ ማዘመኛዎችን ለማካተት ፣ ማዘመኛዎችን በማውረድ፣ በመጫን ወይም በማስታወቅ ተገቢ ማዘመኛዎችን አካት (Include recommended updates when downloading, installing, or notifying me about updates ) አመልካች ሳጥን መመረጡን አረጋግጥ።

12 ቅንጅቶችን ለውጥ መስኮትን ለመዝጋት ፣ ይሁን (OK) ላይ ጠቅ አድርግ።

13 በተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያ የመልዕክት ሳጥን ውስጥ ፣ ቀጥል (Continue) ላይ ጠቅ አድርግ።

Page 42: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

42 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አስረጂ

Windows ማዘመኛ ኮምፒውተርህን እንደዘመነ ለማቆየት የሚያግዝህ የWindows 7 ቅጥያ ነው።

Microsoft እንደ የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎች ያሉ ኮምፒውተርህን ከቫይረሶች እና የደህንነት ስጋቶች ለመከላከል የሚረዱ ጠቃሚ ማዘመኛዎችን በWindows ማዘመኛ የድር ጣቢያ ላይ ይለቃል።

ከዚህ በተጨማሪ Microsoft የመተግበሪያዎች ማሻሻያዎችን ጨምሮ የኮምፒውተርህን አፈፃጸም የሚያሻሽሉ መገልገያዎችን የመሰሉ ወሳኝ ማዘመኛዎችን ይለቃል።

Windows ማዘመኛ ኮምፒውተርህን በመመርመር ለኮምፒውተርህ መተግበሪያዎች እና ሃርድዌር የሚሆኑ ዝርዝር ማዘመኛዎችን ያቀርብልሃል።

Page 43: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

43 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

Windows ማዘመኛን ከጀምር ምናሌ በምታስጀምርበት ጊዜ ፣ የራስ ሰር ማዘመኛን ሁኔታ የሚያሳይ መስኮት ይከፈታል።

ይህ መስኮት የኮምፒውተርህን ዝርዝር የማዘመን ታሪክ ይሰጣል።

የWindows ማዘመኛ መስኮት ለWindows ማዘመኛ ወቅታዊ የWindows 7 ቅንጅቶችን እንደሚያሳይም ተመልከት።

ማዘመኛዎችን በራስ ሰር ለመጫን ራስሰር ማዘመኛን ከዋቀርክ ፣ Windows ማዘመኛ የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎችን ከMicrosoft ማዘመኛ የድር ጣቢያ በራስ ሰር በማውረድ ይጭናል።

ይህ የማውረድ ሂደት ከጀርባ ስለሚከናወን ስራህን አያደናቅፍህም።

ነገር ግን የአንዳንድ ማዘመኛዎችን ጭነት በተሳካ ሁኔታ ለመጨረስ ኮምፒውተርህን እንደገና ማስጀመር ሊያስፈልግህ ይችላል። ለእንደዚህ ያሉ ማዘመኛዎች Windows 7 የእንደገና የማስጀመሪያ መልዕክት ያሳያል።

ለአዳዲስ ማዘመኛዎች የWindows ማዘመኛ ድር ጣቢያን በራስህ ለመፈለግ ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ የሚገኘውን ማዘመኛዎችን ፈልግ የሚለውን አገናኝ ጠቅ ማድረግ አለብህ።

Page 44: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

44 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

Windows ማዘመኛ በድር ጣቢያው ላይ ያሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ማዘመኛዎች እንደሚያሳይ ተመልከት። ማዘመኛዎችን ጫን የሚለውን አዝራር ጠቅ በማድረግ ሁሉንም ማዘመኛዎች ጫን።

ዝርዝሩን በመገምገምም ለኮምፒውተርህ መጫን የምትፈልጋቸውን ማዘመኛዎች መምረጥ ትችላለህ።

Windows ማዘመኛ የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎችን እንዴት እንደሚያወርድ እና እንደሚጭን የተለያዩ አማራጮችን ያቀርብልሃል። ያሉትን ዝርዝር አማራጮች ለማየት ፣ በግራ ክፍለ መቃን ውስጥ ቅንጅቶችን ለውጥ አገናኝ ላይ ጠቅ አድርግ።

Page 45: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

45 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የመጀመሪያውን አማራጭ ስትመርጥ ፣ Windows ማዘመኛ ማዘመኛዎቹን በራስ ሰር በማውረድ ይጭናል። Windows ማዘመኛ ማዘመኛዎቹን የሚያወርድበትን እና የሚጭንበትን የተወሰነ ቀን እና ሰዓት መምረጥ ትችላለህ።

Windows ማዘመኛ ማዘመኛዎቹን እንዲያወርድ ኮምፒውተርህ በተገለጸው ሰዓት ላይ ከበይነመረብ ጋር መገናኘት ይኖርበታል።

ሁለተኛውን አማራጭ ከመረጥክ ፣ Windows ማዘመኛ ማዘመኛዎችን ከድር ጣቢያው ላይ በራስ ሰር ያወርዳል ነገር ግን በኮምፒውተርህ ላይ አይጭናቸውም።

ማዘመኛዎቹን ካወረደ በኋላ ፣ Windows ማዘመኛ ማዘመኛዎቹ ለመጫን በኮምፒውተርህ ላይ እንደሚገኙ የሚያሳውቅ ማንቂያ ያዘጋጃል። የፈለካቸውን ማዘመኛዎች እንደፍላጎትህ መጫን ትችላለህ።

Page 46: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

46 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ሦስተኛውን አማራጭ ከመረጥክ ፣ ኮምፒውተርህ የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎችን በራስ ሰር አውርዶ አይጭንም።

Windows ማዘመኛ በድር ጣቢያው ላይ አዳዲስ ማዘመኛዎች እንዳሉ ብቻ ይፈልጋል። ማዘመኛ ካለ Windows ማዘመኛ ስላሉት ማዘመኛዎች የሚያሳውቅ ማንቂያ ያሳያል። ይህ ማንቂያ የማዘመኛዎቹን አላማ እና ጥቅም ይገልፃል። ማዘመኛዎቹን በመገምገምና በማጽደቅ ማዘመኛዎቹን እንደፍላጎትህ ማውረድ እና መጫን ትችላለህ።

አራተኛውን አማራጭ በመጠቀም በራስሰር ማዘመኛን ማሰናክል ትችላለህ። ራስሰር ማዘመኛን ካሰናከልክ Windows ማዘመኛ ማንኛውንም ማዘመኛ ለማውረድም ሆነ ለመጫን ፍለጋ አያደርግም።

ስለዚህ ማዘመኛዎች ቢኖሩም ምንም አይነት ማንቂያ አይደርስህም።

ይህን አማራጭ ከመረጥክ ኮምፒውተርህ በቅርብ ጊዜ የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎች ስለማይዘምን ለደህንነት ስጋቶች ሊጋለጥ ይችላል።

Page 47: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

47 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ከአስፈላጊ ማዘመኛዎች በተጨማሪ ፣ የኮምፒውተርህን አስተማማኝነት እና ደህንነት ለማሻሻል Windows ማዘመኛን የሚመከሩ ማዘመኛዎችን በራስ ሰር እንዲጭን ማቀናበር ትችላለህ።

እነዚህ የሚመከሩ ማዘመኛዎች ያን ያህልም ወሳኝ ያልሆኑ ችግሮችን ሊፈቱ እና የኮምፒውተር ተሞክሮህን ሊያሳድጉ ይችላሉ።

በቅንጅቶችን ለውጥ መስኮት ውስጥ ቅንጅቶችን ካዋቀርክ በኋላ የተሻሻሉትን ቅንጅቶች ማስቀመጥ አለብህ።

Page 48: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

48 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ኮምፒውተርህ ተጨማሪ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር ካለው ፣ ለምሳሌ የተጫነ ፀረ ቫይረስ እና ፀረ ስፓይዌር ካለም ሶፍትዌሩን በየጊዜው ማዘመን ይገባሃል።

Page 49: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

49 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ ግለ ሙከራ ለትምህርት ክፍል፦ ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት

የሚከተሉትን የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች በተዛማጅ ምድባቸው በትክክለኛው የአማራጭ ሳጥን ምድብ ውስጥ የዓረፍተ ነገሩን ቁጥር በመፃፍ ደርድሯቸው።

ዓረፍተ ነገር

1 የሚቃኙትን የፋይል ዓይነቶች መምረጥ

2 ለኮምፒውተርህ ገቢ መያያዞችን ማገድ

3 የሚመከሩ ማዘመኛዎችን ማውረድ

4 ራስሰር ማውረድን ማግበር

5 ለሚወርድ ማስጠንቀቂያ መቀበል

6 ስጋቶችን ለመከላከል የሚወሰዱ ነባሪ ርምጃዎችን ማዘጋጀት

7 ከቅኝቱ የሚወጡ ፋይሎችን መምረጥ

8 ለፕሮግራም የተለየ ማዘጋጀት

ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3

የማልዌር መከላከያ Windows ኬላ ራስ ሰር ማዘመኛዎች

ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።

Page 50: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

50 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ምርጫ 1 ምርጫ 2 ምርጫ 3

የማልዌር መከላከያ Windows ኬላ ራስ ሰር ማዘመኛዎች

7, 6, 1

8, 2

5, 4, 3

Page 51: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

51 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የትምህርት ክፍሉ ይዘቶች

አእምሮአዊ ንብረት ምንድነው?

የቅጂ መብት ጥሰት እና መከላከያው

መረጃ በመለዋወጥ ዙሪያ ያሉ የህግ ጉዳዮች

ግለ ሙከራ

የትምህርት ክፍሉ መግቢያ

በበይነመረብ ላይ ዜናን ፣ ጽሁፎችን ፣ ስዕሎችን ፣ ዘፈኖችን ፣ ፊልሞችን እና ሶፍትዌርን ያካተቱ መጠነ ሰፊ የመረጃ ዓይነቶችን ታገኛለህ። በማንኛውም ጊዜ መረጃን ለመሰብሰብ ፈጣን እና ቀላል የሆነው በይነመረብን መፈለግ ነው። ለምሳሌ ለትምህርት ቤት መልመጃዎችህ መረጃ ለመፈለግ ወይም ለመስሪያቤትህ የሚሆን አቀራረብ ሃሳቦችን ለማግኘት በይነመረብን ልትጠቀም ትችላለህ። ከተለያዩ የድር ጣቢያዎችም ዘፈኖችን እና ፊልሞችን ማውረድ ትችላለህ።

በብዙዎቹ የድር ጣቢያዎች ላይ መረጃ ለማውረድ ገንዘብ እንደትከፍል አትጠየቅም። ነገር ግን እነዚህ የነፃ ማውረዶች በርግጥም ነፃ አይደሉም። በድር ጣቢያ ላይ ያለ መረጃ በፈጠረው ጸኃፊ ወይም መረጃውን ባተመው የድር ጣቢያ ህጋዊ ባለቤትነት የተያዘ ነው። ስለዚህ ይዘቶቹን ለመጠቀም የጸኃፊውን ወይም የድር ጣቢያውን ባለቤት ፍቃድ ማግኘት ሊያስፈልግህ ይችላል። በድር ጣቢያ ላይ ያሉ ይዘቶችን ከማውረድህ በፊት የተሰጡህን መብቶች እና ፍቃዶች ማወቅ ይኖርብሃል።

ይህ የትምህርት ክፍል አእምሮአዊ ንብረት በኮምፒውተር መስክ ምን ዓይነት ፍቺ እንዳለው እና አእምሮአዊ ንብረትን ያለፈቃድ መጠቀም በቅጂ መብት ጥሰት እንዴት ሊያስጠይቅ እንደሚችል ያብራራል። በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ ከመረጃ ልውውጥ ጋር ስለ ተያያዙ የተለያዩ የህግ ጉዳዮችም ትማራለህ።

የትምህርት ክፍሉ ዓላማዎች

ይህን የትምህርት ክፍል ከጨረስክ በኋላ፦

• አእምሮአዊ ንብረት እና የቅጂ መብት በኮምፒውተር መስክ ሲተገበሩ ምን እንደሚመስሉ ማብራራት ፤

• የተለያዩ የቅጂ መብት ጥሰት ተግባሮችን መለየት እንዲሁም እነዚህን ተግባሮች ለመከላከል የሚወሰዱ ርምጃዎችን መለየት እና

• ከመረጃ ልውውጥ ጋር የተያያዙ የህግ ችግሮችን መለየት ትችላለህ።

ክፍለ ትምህርት 5

የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት

Page 52: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

52 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ አእምሮአዊ ንብረት ምንድነው?

መኮንን አሰፋ ለአንድ የጋዜጣ አታሚ ድርጅት ይሰራል። ስለ ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ጽሁፍ ማዘጋጀት አለበት። መኮንን የተወሰነ መረጃ ከድር ጣቢያ ላይ ስላገኘ ጽሁፉ ላይ አስገብቶታል። ነገር ግን መረጃውን ያገኘበትን ምንጭ በጽሁፉ ላይ አልጠቀሰም። ጽሁፉ ከታተመ በኋላ መኮንን የቅጂ መብት ህግ ጥሰት የህግ ውንጀላ ተጋለጠ። ይህም የሆነበት ምክንያት አእምሮአዊ ንብረትን ያለባለቤቱ ፍቃድ በመጠቀሙ ነው።

በበይነመረብ ላይ የሚገኝ ማንኛውም መረጃ በፈጠረው ሰው ህጋዊ ባለቤትነት የተያዘ አእምሮአዊ ንብረት ነው። ለምሳሌ አንድ ጽሁፍ በድር ጣቢያ ላይ ስታትም ጽሁፉ ያንተ አእምሮአዊ ንብረት ነው። እንደ አእምሮአዊ ንብረት ባለቤትነትህ የንብረቱን አጠቃቀም የመቆጣጠር ሙሉ መብት አለህ። ከእነዚህም ውስጥ፦

• ንብረቱን የመቅዳት ፣ የማባዛት ወይም የማሰራጨት ፣

• የንብረቱን መብቶች የማጋራት ወይም የመሸጥ እንዲሁም

• የንብረቱን መብቶች በነፃ የመስጠት ሙሉ መብት አለህ።

ማስታወሻ፦

የአእምሮአዊ ንብረት ትክክለኛ መብቶች ባለቤቱ በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ሊያዩ ይችላሉ።

አእምሮአዊ ንብረትን ያለባለቤቱ ፍቃድ የመጠቀም መብት የለህም። የአእምሮአዊ ንብረት ባለቤትን መብቶች ለመጠበቅ የወጡ ህጎች አሉ። እነዚህ ህጎች የቅጂ መብት ህጎች በመባል ይጠራሉ። እነዚህን ህጎች መጣስ ለህግ ተጠያቂነት ሊያጋልጥ ይችላል።

ርዕስ፦ የቅጂ መብት ጥሰት እና መከላከያው

የቅጂ መብት ያለውን አእምሮአዊ ንብረት ያለባለቤቱ ፈቃድ ስትጠቀም ለቅጂ መብት ጥሰት ሊያጋልጥህ ይችላል። የሆነ ሰውን ስራ መቅዳትና ምንጭ ሳትጠቅስ እንደራስህ ስራ አድርገህ መጠቀም ፕላጃሪዝም በመባል ይታወቃል። አንድ በድር ጣቢያ ላይ ያለን ስዕል ቀጥተኛ ቅጂ ወሰድክ እንበል። ከዚያም ይህን ስዕል እንደራስህ ፈጠራ በሌላ የድር ጣቢያ ላይ አስቀመጥከው ነገር ግን ምስሉን ያመጣብህበትን የድር ጣቢያ አልጠቀስክም። ይህ የፕላጃሪዝም ውጤት ነው።

በብዙ አገሮች ውስጥ አንድን ስራ በሌላ ቃል መጥቀስ እና ልክ እንደራስ የመጀመሪያ ስራ አድርጎ ማስተላለፍ እንደ ፕላጃሪዝም ይወሰዳል። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ ልታውቃቸው እና ልታስወግዳቸው የሚገቡ የቅጂ መብት ያለውን ንብረት ያላግባብ መጠቀሞችን ያብራራል።

የቅጂ መብትን ያላግባብ መጠቀም መግለጫ

ሙዚቃ መቅዳት ዘፈኖችን እንድታወርድ እና እንድታጋራ የሚፈቅዱ ብዙ የድር ጣቢያዎች አሉ። ነገር ግን ከእነዚህ የድር ጣቢያዎች አንዳንዶቹ ዘፈኖቹን በነፃ ለማውረድ የማቅረብ ህጋዊ ስልጣን የላቸውም። ከእነዚህ የድር ጣቢያዎች ላይ ዘፈኖችን ማውረድ የቅጂ መብት ያላቸውን ሙዚቃዎች ያላግባብ መጠቀም ነው።

ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ስትፈጽም የቅጂ መብት ያለውን ሙዚቃ ያላግባብ ተጠቀምክ ይባላል።

• የቅጂ መብት ያለውን ሙዚቃ ያለባለቤቱ ፍቃድ ወይም የቅጂ መብት ክፍያውን ሳትከፍል ከድር ጣቢያ ላይ ካወረድክ።

• የቅጂ መብት ያለውን ሙዚቃ ከድር ጣቢያ ላይ ካወረድክ እና የወረደውን ሙዚቃ በሲዲ ወይም በዲቪዲ ከቀዳህ።

• የቅጂ መብት ያለውን ሲዲ ወይም ዲቪዲ ካባዛህ እና ቅጂዎቹን ለሌሎች ካጋራህ።

• የቅጂ መብት ያላቸውን ዘፈኖች በበይነመረብ የዘፈኖችን መጋራት በሚፈቅዱ የድር ጣቢያዎች ላይ ካጋራህ።

Page 53: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

53 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ሶፍትዌርን ያለፈቃድ መጠቀም

ሶፍትዌርን ያለፍቃድ ከመጠቀም እንድትቆጠብ ስለሚከተሉት ሁኔታዎች ዕወቅ፦

• የቅጂ መብት ያለውን ሶፍትዌር ያለባለቤቱ ፍቃድ ወይም የቅጂ መብት ክፍያውን ሳትከፍል ከድር ጣቢያ ላይ ካወረድክ ሶፍትዌርን ያለፈቃድ መጠቀም ነው።

• ህጋዊ የሆነ ሶፍትዌርን ገዝተህ ካባዛህና ለሌሎች ቅጂዎችን ካሰራጨህ ይህም ሶፍትዌርን ያለፈቃድ መጠቀም ነው።

• አንዳንድ የኮምፒውተር ሻጮች ፍቃድ የሌለውን የሶፍትዌር ቅጂ በሚሸጧቸው ኮምፒውተሮች ላይ ይጭናሉ። ይህን የሚያደርጉትም ከፍቃድ ክፍያ ለመዳን ነው። ነገር ግን ፍቃድ የሌለው ሶፍትዌር የተጫነባቸውን ኮምፒውተሮች መግዛት ሶፍትዌርን ያለፈቃድ መጠቀም ነው። ስለዚህ ኮምፒውተር በምትገዛበት ጊዜ በኮምፒውተሩ ላይ ቀድሞ የተጫነውን ሶፍትዌር ወይም ከኮሚውተሩ ጋር የሚሸጠውን ሶፍትዌር የፍቃድ ሰነዶች እንደያዝክ አረጋግጥ።

የንግድ ምልክትን መቅዳት

የንግድ ምልክት የቅጂ መብት ባለቤቱን ለመለያነት የሚያገለግል የቅጂ መብት ያለው ንብረት ነው። የንግድ ምልክትን ያለባለቤቱ ፍቃድ መቅዳት ወይም መጠቀም ህገ ወጥ ተግባር ነው። ለምሳሌ የMicrosoft የንግድ ምልክትን የMicrosoftን ፍቃድ ሳታገኝ በቢዝነስ ካርድህ ላይ መጠቀም የቅጂ መብት ጥሰት ነው።

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የንግድ ምልክትን የመጠቀም ፍቃድ ሊኖራቸው ይችላል ነገር ግን የአጠቃቀም ገደቦች ይኖሩታል። ለምሳሌ አንድ ሰው የMicrosoft የንግድ ምልክትን Microsoftን በመወከል የንግድ ስምምነቶችን በሚያደርግበት ጊዜ ብቻ እንዲጠቀም ፍቃድ ሊኖረው ይችላል። አሁን ይህ ሰው የMicrosoft የንግድ ምልክትን በመጠቀም ለግል ጥቅሙ የንግድ ስምምነቶችን ቢያደርግ ይህ የቅጂ መብት ያለውን የንግድ ምልክት ያላግባብ መጠቀም ይሆናል።

ተጨማሪ መረጃ

የድር ጣቢያ የቅጂ መብት ያለውን መረጃ እንድታወርድ ሊፈቅድልህ ይችላል። ነገር ግን እንደዚህ ያለን መረጃ ስታወርድ በህግ ልትጠየቅ የምትችልበት ሁኔታ ያጋጥምሃል። ብዙ ጊዜ በድር ጣቢያ ላይ የተቀመጠ መረጃ ህጋዊ የቅጂ መብት አለው እንዲሁም የቅጂ መብት ጽሁፍ ወይም ምልክት ይይዛል። ነገር ግን ማንኛውም መረጃ የቅጂ መብት ጽሁፍ ወይም ምልክት ባይኖረው መረጃው የቅጂ መብት የለውም ማለት አይደለም። በእንግሊዝ የቅጂ መብት ህግ መሰረት አንድ ሰው አንድን ሃሳብ ወይም ጽንሰ ሃሳብ በአካል ባስተላለፈበት ቅጽበት ስራው የሰውዬው የቅጂ መብት ንብረት ይሆናል። በተመሳሳይ በአሜሪካ የቅጂ መብት ህግ መሰረት የቅጂ መብት ባለቤቱ የቅጂ መብቱ ህጋዊ ሆኖ ባይመዘገብ እንኳ በቅጂ መብት ንብረቱ ላይ ሙሉ ባለመብት ይሆናል።

ማንኛውም የቅጂ መብት ጥሰት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። የቅጂ መብት ባለቤቱ የቅጂ መብቱን ህጎች በጣሰው ሰው ላይ ህጋዊ ርምጃ ሊወስድ ወይም ለተፈጸመበት ተግባር ትልቅ የገንዘብ ካሳ ሊጠይቅ ይችላል። ስለዚህ ማንኛውንም መረጃ ከድር ጣቢያ ላይ ከማውረድህ በፊት የአለም ዓቀፍ እና የሃገር ውስጥ የቅጂ መብት ህጎችን ጠንቅቀህ ዕወቅ።

የቅጂ መብት ያለው ንብረት ህጋዊ አጠቃቀሞች

ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ የቅጂ መብት ያለው ንብረትን የተወሰኑ ህጋዊ አጠቃቀሞች ያብራራል። ህጋዊ አጠቃቀም መግለጫ የቅጂ መብት ያለውን ንብረት ለትምህርታዊ ዓላማዎች መጠቀም

የቅጂ መብት ያለውን ንብረት የተወሰነ ክፍል ለትምህርታዊ ዓላማዎች ከተጠቀምክና ምንጩን ከጠቀስክ ፣ ይህ አግባብ የሆነ የቅጂ መብት ያለውን ንብረት አጠቃቀም ነው። ለምሳሌ የአንድን መጽሐፍ የተወሰነ ክፍል ይዘቶችን ለትምህርት ቤት ወይም ኮሌጅ ጽሁፎችህ የመጽሐፉን ምንጭ ጠቅሰህ መጠቀም ትችላለህ። በተመሳሳይ የአንድ መጽሐፍ ግምገማ እየፃፍክ ከሆነ ከመጽሐፉ የወጡ ጽሁፎችን መጥቀስ ትችላለህ።

ንብረቱን በማውረድ ፋንታ አገናኞች ማጋራት

ይዘቶችን ከድር ጣቢያዎች ላይ በመቅዳት በራስህ ስራ ውስጥ ከማካተት ይልቅ የይዘቶቹን ማጣቀሻዎች ወይም አገናኞች ማቅረብ ትችላለህ። ለምሳሌ ስለ አንድ የድር ጣቢያ ይዘቶች በጽሁፍ ውስጥ መጥቀስ ልትፈልግ ትችላለህ። ከድር ጣቢያው ላይ ይዘቶቹን በመቅዳት ፋንታ የዚህን የድር ጣቢያ አገናኝ በጽሁፍ ውስጥ ማቅረብ ብቻ ይበቃል። በዚህ ዓይነት ዘዴ የቅጂ መብት ያለውን ይዘት በመጠቀም ሙሉ ለሙሉ ፕላጃሪዝምን ማስወገድ ትችላለህ።

Page 54: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

54 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የቅጂ መብት ያለውን ይዘት የቅጂ መብት ባለቤቱን በማስፈቀድ መጠቀም

የቅጂ መብት ያለውን ይዘት የቅጂ መብት ባለቤቱን ፍቃድ በመጠየቅ በስራህ ውስጥ መጠቀም ትችላለህ። በእንዲህ አይነት ሁኔታዎች ብዙ ጊዜ የቅጂ መብት ያለውን ይዘት ለመጠቀም በጽሁፍ የተሰጠ ፍቃድ ያስፈልግሃል።

የቅጂ መብት ባለቤቱ የሚከተሉትን የመወሰን ነፃነት እንዳለው አስታውስ፦

• የቅጂ መብት ያለውን ይዘት ለመጠቀም ፍቀድ መስጠት ወይም አለመስጠት ይችላል።

• የቅጂ መብት ያለውን ይዘት በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ለመጠቀም መብት መስጠት ይችላል።

• የቅጂ መብት ያለውን ይዘት ለመጠቀም ፍቃድ ለመስጠት ክፍያ መጠየቅ ይችላል።

• የቅጂ መብት ያለውን ንብረት ለመጠቀም ውሎችን ማዘጋጀት ይችላል። ለምሳሌ የቅጂ መብት ያለውን ሶፍትዌር የማውረድ እና የማጋራት ፍቃድ ሊኖርህ ይችላል። ነገር ግን ሶፍትዌሩን ለግል ትርፍ ማስገኛነት የመጠቀም ፍቃድ ላይኖርህ ይችላል።

የአንድ ንብረት የቅጂ መብት ጊዜው ካለፈበት ወይም የቅጂ መብት ባለው ንብረት ውስጥ ያለው ሃሳብ ወይም ሂደት በብዙኃኑ የታወቀ ከሆነ ያንን ንብረት ወይም ሃሳብ ፍቃድ መጠየቅ ሳያስፈልግህ መጠቀም ትችላለህ።

ርዕስ፦ መረጃ በመለዋወጥ ዙሪያ ያሉ የህግ ችግሮች

በይነመረብን በስፋት ከመጠቀም ጋር ተያይዞ እንደ ቁማር እና ስም ማጥፋት ያሉ ህገ ወጥ እና ስነ-ምግባር የጎደለው ተግባር ውስጥ የመሳተፍ ዕድል ይኖርሃል። ህገ ወጥ እና ስነ-ምግባር ስለጎደላቸው ጉዳዮች ማወቅ እና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲሁም እነዚህ ጉዳዮች ከአገር አገር ብሎም በአንድ አገር ባሉ ክፍሎች ውስጥም ከቦታ ቦታ ሊለያዩ እንደሚችሉ አስታውስ። ቀጥሎ የሚገኘው ሰንጠረዥ ህገ ወጥ እና ስነ-ምግባር የጎደለው የመረጃ ልውውጥ አጠቃቀምን ያብራራል።

ህገ ወጥ ተግባር መግለጫ የሰውን ስም ማጥፋት

በኢ-ሜይል ፣ በውይይት (ቻት) ወይም በመስመር ላይ የማህበረሰብ የውይይት መድረኮች ላይ ግንኙነቶችን ስታደርግ የሰውን ስም ሊያጠፋ የሚችሉ ሃሳቦችን እንዳትጽፍ ተጠንቀቅ። ስም ማጥፋት ማለት ስለ አንድ ሰው ውሸት የሆነና የሰውዬው ማንነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር መረጃ ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ ጎረቤትህ የሆነ ዝነኛ ሰው ህገ ወጥ የሆነ ንብረት እንዳለው የሚገልጽ የሐሰት መልዕክት በመስመር ላይ የውይይት መድረክ ላይ አሰፈርክ እንበል። የጎረቤትህን ታማኝነት ወይም ተቀባይነት የሚጎዳ የሐሰት መረጃ በማሰራጨትህ ይህ ተግባር እንደ ስም ማጥፋት ሊወሰድ ይችላል።

ማስታወሻ፦

የሐሰት መረጃ የሚያጣጥል መረጃ ባይሆንም እንኳ እንደ ስም ማጥፋት ተግባር ሊወሰድ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ መረጃው የሰውን ስም የሚያጎድፍ ከሆነ የእውነት መረጃ ቢሆንም እንኳ እንደ ስም ማጥፋት ተግባር ሊወሰድ ይችላል።

ህትመታዊ ስም ማጥፋት እና ቃላዊ ስም ማጥፋት ሁለቱ የስም ማጥፋት አይነቶች ናቸው። ህትመታዊ ስም ማጥፋት (Libel) በህትመት ላይ የሚወጣ የስም አጥፊነት ሲሆን ቃላዊ ስም ማጥፋት (slander) በቃል/በአፍ የሚደረግ ስም አጥፊነት ነው።

በአብዛኞቹ አገሮች የህግ ስርዓት ውስጥ ህትመታዊውም ሆነ ቃላዊ ስም ማጥፋት በወንጀል የሚያስቀጡ ናቸው። ቅጣቱ ከገንዘብ መቀጮ እስከ እስር ቅጣት የሚያደርስ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ የእስር የወንጀል ቅጣቱ ጊዜ እንደሁኔታው ሊወሰን ይችላል። ለምሳሌ በአንዳንድ አገሮች ውስጥ ፕሬዝዳንቱን መስደብ በወንጀል የሚያስቀጣ ነው። ነገር ግን በአንዳንድ አገሮች ውስጥ ከመገናኛ ብዙሃኑ አማካዩ ዜጋ የአነሰ የህግ ከለላ አላቸው። ስለዚህ ማንኛውንም የስም ማጥፋት መረጃን ከማውጣትህ በፊት የሀገር ውስጥ ህጎችን ጠንቅቀህ ዕወቅ።

ተገቢ ያልሆነን የድር ጣቢያ መጎብኘት

አንዳንድ የድር ጣቢያዎች ባለህበት ግዛት ወይም አገር የተከለከሉ ተግባሮችን የሚያከናውኑ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ። በበይነመረብ ላይ ምንም ዓይነት ገደብ እና የመቆጣጠሪያ መንገድ ስለሌ እነዚህን ጣቢያዎች በበይነመረብ ላይ መዳረስ ይቻላል። ለምሳሌ ያለህበት አገር ህግ ቁማርን የሚከለክል ቢሆንም የቁማር ጣቢያን ልትዳረስ ትችላለህ። ነገር ግን ይህ በአንተ ላይ የህግ ተጠያቂነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

የህግ ስርዓት እንደየአገሩ እና ግዛቱ ሊላይ እንደሚችልም ማወቅ ይኖርብሃል። ለምሳሌ በአንድ አገር ውስጥ ህጋዊ በሆነ መንገድ መግዛት እና መሸጥ የምትችላቸው ምርቶች በሌላ አገር ውስጥ ህገ ወጥ ግዢ ወይም ሽያጭ ሊሆን ያችላል። ስለዚህ ምንም እንኳ አንድ የድር ጣቢያ አንተ ባለህበት አገር ውስጥ ህገ ወጥ የሆነን ምርት እንዳትገዛ ላይከለክልህ ቢችልም ምርቱን ለመግዛትህ በህግ ልትጠየቅበት ትችላለህ።

Page 55: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

55 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ርዕስ፦ ግለ ሙከራ

እያንዳንዱን ጥንድ ዓረፍተ ነገር እውነት እና ሐሰት የሆኑ ዓረፍተ ነገሮችን ይዟል። እውነት የሆነውን ዓረፍተ ነገር በቀኝ በኩል በሚገኘውና እውነት በሚለው አምድ ስር ምልክት በማድረግ አመልክት።

ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት

1 አእምሮአዊ ንብረትን ያለፍቃድ መጠቀም ህጋዊ ተግባር ነው።

2 አእምሮአዊ ንብረትን ያለፍቃድ መጠቀም ህገ ወጥ ተግባር ነው።

3 የስዕል ስራ ህጋዊ ባለቤት ሰዓሊው ነው።

4 የስዕል ስራ ህጋዊ ባለቤት ሰዓሊው አይደለም።

5 የአንድ መጽሐፍ ፀኃፊ የመጽሐፉን አጠቃቀም መቆጣጠር አይችልም።

6 የአንድ መጽሐፍ ፀኃፊ የመጽሐፉን አጠቃቀም መቆጣጠር ይችላል።

7 አንድ የቅጂ መብት ባለቤት የቅጂ መብቶቹን መሸጥ ይችላል።

8 አንድ የቅጂ መብት ባለቤት የቅጂ መብቶቹን መሸጥ አይችልም።

9 የቅጂ መብት ጥሰት ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ አይችልም።

10 የቅጂ መብት ጥሰት ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል።

11 የቅጂ መብት ያለውን ዘፈን ማጋራት የቅጂ መብት ጥሰት አይደለም።

12 የቅጂ መብት ያለውን ዘፈን ማጋራት የቅጂ መብት ጥሰት ነው።

13 ህትመታዊ የስም ማጥፋት በአፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

14 ህትመታዊ የስም ማጥፋት በጽሁፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

15 ቃላዊ የስም ማጥፋት በጽሁፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

16 ቃላዊ የስም ማጥፋት በአፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

17 የመስመር ላይ ቁማር ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል።

18 የመስመር ላይ ቁማር ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ አይችልም።

ማስታወሻ፦ ትክክለኛዎቹ መልሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይገኛሉ።

Page 56: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

56 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ዓረፍተ ነገር እውነት ሐሰት

1 አእምሮአዊ ንብረትን ያለፍቃድ መጠቀም ህጋዊ ተግባር ነው።

2 አእምሮአዊ ንብረትን ያለፍቃድ መጠቀም ህገ ወጥ ተግባር ነው።

3 የስዕል ስራ ህጋዊ ባለቤት ሰዓሊው ነው።

4 የስዕል ስራ ህጋዊ ባለቤት ሰዓሊው አይደለም።

5 የአንድ መጽሐፍ ፀኃፊ የመጽሐፉን አጠቃቀም መቆጣጠር አይችልም።

6 የአንድ መጽሐፍ ፀኃፊ የመጽሐፉን አጠቃቀም መቆጣጠር ይችላል።

7 አንድ የቅጂ መብት ባለቤት የቅጂ መብቶቹን መሸጥ ይችላል።

8 አንድ የቅጂ መብት ባለቤት የቅጂ መብቶቹን መሸጥ አይችልም።

9 የቅጂ መብት ጥሰት ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ አይችልም።

10 የቅጂ መብት ጥሰት ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል።

11 የቅጂ መብት ያለውን ዘፈን ማጋራት የቅጂ መብት ጥሰት አይደለም።

12 የቅጂ መብት ያለውን ዘፈን ማጋራት የቅጂ መብት ጥሰት ነው።

13 ህትመታዊ የስም ማጥፋት በአፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

14 ህትመታዊ የስም ማጥፋት በጽሁፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

15 ቃላዊ የስም ማጥፋት በጽሁፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

16 ቃላዊ የስም ማጥፋት በአፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ነው።

17 የመስመር ላይ ቁማር ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል።

18 የመስመር ላይ ቁማር ለህግ ችግሮች ሊያጋልጥ አይችልም።

Page 57: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

57 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የሞዱሉ ማጠቃለያ

ክፍለ ትምህርቶች የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና መግቢያ

ኮምፒውተርህ ከተለያዩ የደህንነት እና ክብረ ገመና ስጋቶች የተጠበቀ መሆን ያስፈልገዋል። ስጋቶቹ በሚከተሉት መልክ ሊሆኑ ይችላሉ፦

• ተፈጥሮአዊ አደጋዎች

• የሰዎች ስህተቶች ወይም አጋጣሚዎች

• በስርቆት ፣ በሰርጎ ገቦች የሚደረግ ያለፈቃድ መዳረስ ወይም የቫይረስ ጥቃቶች የመሰሉ ጎጂ ተግባሮች

ያልተያያዙ ኮምፒውተሮችም ሆኑ በአውታረመረብ ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች የእነዚህ ስጋቶች ሰለባ ሊሆን ይችላል። የኮምፒውተርህን ሃርድዌር ፣ ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ አንዳንድ የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎችን መውሰድ ይኖርብሃል።

ኮምፒውተርን መጠበቅ ኮምፒውተርህን እና በውስጡ የተቀመጠን መረጃ ከተለያዩ የደህንነት እና የክብረ ገመና ስጋቶች መጠበቅ ይኖርብሃል። በኮምፒውተርህ ውስጥ የሚገኘውን ስርዓተ ክወና ፣ ሶፍትዌር እና መረጃ ለመጠበቅ የሚከተሉትን ርምጃዎች ውሰድ፦

• የተጠቃሚ መለያ ተግብር

• የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል አዋቅር

• የይለፍ ቃልን በሚስጥር ጠብቅ

• ኮምፒውተርህን ቆልፍ

• ውሂብን ፍቃድ ከሌለው መዳረስ ለመከላከል ውሂብ መስጥር

• በሌላ የማከማቻ መሳሪያ ላይ ምትክ ውሂብ ያዝ

• የኮምፒውተር ስርዓትህን እና ተጋላጭ ሶፍትዌርን አዘምን

ከአውታረመረብ ወይም ከበይነመረብ ጋር የተገናኙ ኮምፒውተሮች ከምንም ጋር ካልተያያዙ ኮምፒውተሮች በበለጠ ሁኔታ የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች ያስፈለጓቸዋል። ከአውታረመረብ ጋር ለተያያዙ ኮምፒውተሮች አንዳንድ ጥሩ ተሞክሮዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

• የዘመነ የደህንነት ጥበቃ መጠቀም

• ኮምፒውተርህን ከሰርጎ ገቦች እና ስፓይዌር መከላከል

• የአሰሳ ታሪክን እና የተሸጎጡ ፋይሎችን በየጊዜው ማጽዳት

• በየጊዜው ኩኪዎችን ማጥፋት

• የመስመር ላይ ግብይቶችን ደህንነታቸው በተጠበቀ ጣቢያዎች ላይ ብቻ ማድረግ

• የግል ታሪክህን ለድር ጣቢያ በጭራሽ አሳልፎ አለመስጠት

• በWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል ውስጥ ያሉ የደህንነት ጥበቃ ክፍሎችን ማንቃት እና ማዋቀር

• ተዋናይ ይዘትን ማሰናከል

• ከበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢዎች የደህንነት ጥበቃ እገዛን መጠቀም

Page 58: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

58 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የኢ-ሜይል አባሪዎች ቫይረሶችን ወይም ተውሳኮችን ሊይዙ ይችላሉ። ኢ-ሜይል እና ውይይትን በምትጠቀምበት ልትከተላቸው የሚገቡ የደህንነት ጥበቃ ርምጃዎች፦

• የዘመነ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር ተጠቀም

• አባሪዎችን የያዙ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ከመክፈት ተቆጠብ

• አይፈለጌ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን አጥፋ

• ሳይፈለጉ የሚመጡ የንግድ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን አጥፋ

• ራስህን ከአስጋሪ ጠብቅ

• ከምታውቃቸው ሰዎች ጋር ብቻ ውይይት አድርግ

ቤተሰቦችህን ከደህንነት ስጋቶች መጠበቅ

የኮምፒውተርህን ክብረ ገመና ለመጠበቅ የሚከተሉትን አስተማማኝ ርምጃዎች መውሰድ ትችላለህ፦

• ማንነትህን ደብቅ

• የኮምፒውተርህን ደህንነት ሁኔታ በየጊዜው ፈትሽ

• የቫይረስ ቅኝቶችን በየዕለቱ አካሂድ

• ፀረ ስፓይዌር ሶፍትዌር ተጠቀም

• የመስመር ላይ ግብይቶችን አስተማማኝ በሆኑ የድር ጣቢያዎች ላይ ከሚታመኑ ሻጮች ጋር አድርግ

• ጥቃትን ለበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢው አሳውቅ

• አይፈለጌ መልዕክትን አስወግድ ወይም ቀንስ ያለፈቃድ የሚደረግን መዳረስ ለመከላከል ወሳኝ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን መስጥር

ኮምፒውተርን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደዘመነ ማቆየት

ትክክለኛ የሆነ የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን በኮምፒውተርህ ላይ ማቀናበር በበይነመረብ የሚደረግን ኮምፒውተርህን የመዳረስ ሙከራ ይከላከላል እንዲሁም ያገኛል። የWindows የደህንነት ጥበቃ ማዕከል የሚከተሉትን የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶች ይሰጠሃል፦

• የበይነመረብ አማራጮች

• Windows ኬላ

• ራስሰር ማዘመኛዎች

• የማልዌር መከላከያ

ለተሻለ የኮምፒውተርህ ደህንነት የደህንነት ጥበቃ ቅንጅቶችን መርምር እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ አሻሽል።

ኮምፒውተርህን እንደዘመነ ለማቆየት የሚከተሉትን ርምጃዎች መውሰድ ትችላለህ፦

• ከMicrosoft ማዘመኛ የድር ጣቢያ ላይ አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎችን በማውረድ ኮምፒውተርህን እንደዘመነ አቆይ።

• ኮምፒውተርህ የደህንነት ጥበቃ ማዘመኛዎችን በራስ ሰር እንዲያወርድና እንዲጭን የራስሰር ማዘመኛዎችን አዋቅር።

Page 59: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

59 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

የኮምፒውተር ስነ-ምግባራት

የአእምሮአዊ ንብረት ባለቤት የንብረቱን አጠቃቀም የመቆጣጠር ሙሉ መብት አለው። የቅጂ መብት ህጎች አእምሮአዊ ንብረቶችን ይጠብቃሉ። የቅጂ መብት ጥሰት በሚከተሉት መልኮች ሊሆን ይችላል፦

• ፕላጃሪዝም

• ሶፍትዌርን ያለፈቃድ መጠቀም

• የቅጂ መብት ያለውን ንብረት ከድር ጣቢያዎች ላይ ያለፈቃድ ማውረድ

የቅጂ መብት ያላቸውን ንብረቶች ለመጠቀም ህጋዊ መንገዶች አሉ። የቅጂ መብት ያለውን ንብረት በህጋዊ መንገድ ለመጠቀም፦

• የቅጂ መብት ያለውን ንብረት በከፊል በመውሰድ ለትምህርታዊ ዓላማዎች መጠቀም እና ምንጩን መጥቀስ

• የቅጂ መብት ያለውን ንብረት በመቅዳት ፋንታ የንብረቱን ማጣቀሻዎች ወይም አገናኞች ማቅረብ

• ንብረቱን ለመጠቀም የቅጂ መብት ባለቤቱን ፈልግና ፍቃድ ተቀበል

በይነመረብ እንደ ቁማር ፣ ስም ማጥፋት እና ባለህበት አገር ውስጥ መግዛትም ሆነ መሸጥ ህገ ወጥ የሆነ ምርትን መግዛት ያሉ ህገ ወጥ እና ስነ-ምግባር የጎደለው ተግባር ውስጥ እንድትሳተፍ ሊያደርጉ የሚችሉ እድሎችን ሊያቀርብልህ ይችላል። ስለዚህ በእንደዚህ ዓይነት ተግባር ውስጥ ከመሳተፍህ በፊት የሀገር ውስጥ እና ዓለም ዓቀፍ ህጎችን ጠንቅቀህ ዕወቅ።

Page 60: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

60 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

መፍትሔ ቃላት

ተዋናይ ይዘት

ተዋናይ ይዘት በይነመረብን በምታስስበት ጊዜ በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫን ትንሽ ፕሮግራም ነው። የተዋናይ ይዘት ዋና አገልግሎት በቪዲዮች እና በሰሪ አሞሌዎች የታገዘ የበይነመረብ ተሞክሮ ግንኙነት ለአንተ ማቅረብ ነው። አንዳንድ ጊዜ ተዋናይ ይዘት ያለፍቃድ ኮምፒውተርህን ለመዳረስ እና በኮምፒውተርህ የሚገኝ መረጃን ለማበላሸት ወይም ያለአንተ ፈቃድ ጎጂ የሆነ ሶፍትዌርን ለመጫን ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ።

ምትክ መያዝ

የአንድን ፕሮግራም ፣ ዲስክ ወይም መረጃ ቅጂ አባዝቶ መያዝ ምትክ መያዝ ይባላል።

መሸጎጫ ማህደረ ትውስታ

በይነመረብን በምትዳስስበት ጊዜ የተከፈቱ ፋይሎችን ቅጂ በኮምፒውተርህ ላይ ለማከማቸት የሚያገለግል ጊዜያዊ ማህደረ ትውስታ ነው።

የኮምፒውተር ክብረ ገመና

የጠቃሚ መረጃ ፣ የግል ፋይሎች እና የኢ-ሜይል መልዕክቶች ትክክለኛ ፈቃድ እስካለገኙ ድረስ በማንም ሊገኙ እንዳይችሉ አድርጎ መጠበቅ ነው።

የኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ

የኮምፒውተር ስርዓትን እና በውስጡ ያለ መረጃን ከድንገተኛ ወይም ሆን ተብሎ የሚደረግ ማጥፋት እና ማበላሸት መጠበቅ ነው።

ኩኪ

አንድ ተጠቃሚ የድር ጣቢያን በሚጎበኝበት ጊዜ በኮምፒውተር ላይ የሚፈጠር ትንሽ ፋይል ነው። ቀድሞ የጎበኘሃቸው የድር ጣቢያዎች ጣቢያውን የጎበኙ ተጠቃሚዎችን ለመለየት እና የተጠቃሚዎችን አማራጮች ለመከታተል ኩኪዎችን ይጠቀማሉ።

የቅጂ መብት

እንደ ጽሁፍ ፣ ሙዚቃ ፣ ስዕል ወይም የኮምፒውተር ፕሮግራም ያለ የፈጠራ ስራን ባለቤት መብቶች በህግ የመጠበቂያ ዘዴ ነው።

ምሰጠራን መፍታት

የተመሰጠረን ውሂብ መነበብ እና መጠቀም ወደሚችል ቅርጸት መልሶ የመቀየር ሂደት ነው።

ምስጠራ

ውሂብን ወደማይነበብ እና መጠቀም ወደማይቻልበት ቅርጸት መቀየር ምስጠራ ተብሎ ይጠራል። ምስጠራ በተለይ ውሂብን በበይነመረብ በማስተላለፍ ጊዜ ያለተፈቀደለት የውሂብ መዳረስን ለመከላከል የሚደረግ ነው።

ኬላ

ከበይነመረብ የሚመጣ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ኮምፒውተርህን ወይም የግል አውታረመረብህን ከመድረሱ በፊት የሚያግድ ማጣሪያ ነው። እንደ ሰርጎ ገቦች እና ቫይረሶች ያሉ ስጋቶችን የመከላከያ ተጨማሪ አገልግሎቶችንም ይሰጣል። ኬላ ባልተፈቀደ ተጠቃሚ ማንኛውም ከውጪ የሚደረግን መዳረስ በማገድ የኮምፒውተርህን ደህንነት እንድታረጋግጥ ይረዳሃል።

ሰርጎ ገብ

ያለፈቃድ ኮምፒውተርህን ለመድርስ የላቀ የኮምፒውተር ዕውቀትን የሚጠቀም ሰው ነው። ኮምፒውተርን ከደረሰ በኋላ ሰርጎ ገብ በኮምፒውተር ውስጥ የሚገኙ ፕሮግራሞችን እና መረጃን ላልተገባ ዓላማ ሊጠቀምበት ወይም ሊያበላሽ ይችላል።

Page 61: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

61 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አእምሮአዊ ንብረት

በበይነመረብ ላይ የሚገኝ ማንኛውም መረጃ በፈጠረው ሰው ህጋዊ ባለቤትነት የተያዘ አእምሮአዊ ንብረት ነው። የአእምሮአዊ ንብረት ባለቤት የሆነው ሰው የመረጃውን አጠቃቀም የመቆጣጠር ሙሉ መብት አለው።

የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ (ISP)

የበይነመረብ ግንኙነትን ለግለሰቦች ፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለሌሎች ትላልቅ ድርጅቶች የሚያቀርብ ኩባንያ ነው።

ህትመታዊ የስም ማጥፋት

የታተመ የጽሁፍ ስም ማጥፋት ሲሆን በህግ የሚያስቀጣ ነው።

የመስመር ላይ አዳኝ

በውይይት ክፍሎች ፣ በፈጣን መልዕክት ፣ በኢ-ሜይል ወይም በውይይት መድረኮች በመጠቀም የበይነመረብ ተጠቃሚዎች ጋር ግንኙነትን በማዳበር ከገንዘብ ጋር ለተያያዘ ጥቅም ወይም አደገኛ ግንኙነት ውስጥ ለማስገባት የሚሞክር ግለሰብ ነው።

የይለፍ ቃል

የኮምፒውተር ተጠቃሚው እንደማንነት መለያ ኮድ የሚጽፈው ልዩ ህብረቁምፊ ነው። የይለፍ ቃል የኮምፒውተርን ስርዓት እና ወሳኝ ፋይሎችን ከመዳረስ ለመከልከል የሚያገለግል የደህንነት ጥበቃ ርምጃ ነው።

ማስገር

ማስገር ከኮምፒውተር ተጠቃሚዎች እንደ የይለፍ ቃል እና የክሬዲት ካርድ ዝርዝር ያለን የግል መረጃ በማውጣት ጎጂ ለሆኑ ዓላማዎች የመጠቀም ተግባር ነው።

ፕላጃሪዝም

የሆነ ሰውን ስራ መቅዳትና ምንጭ ሳይጠቅሱ እንደራስ ስራ አድርጎ መጠቀም ፕላጃሪዝም ይባላል።

ከመጠን ያለፈ ኃይል

እንደ ኮምፒውተር ያሉ የኤሌክተሮኒክ መሳሪያዎችን ዳግም እንዳይሰሩ አድርጎ ሊጎዳ የሚችል ድንገተኛ የኃይል አቅርቦት መጨመር ነው።

ጥብቅ ሶኬት ንብርብር (SSL)

የሚተላለፈውን መረጃ በመመስጠር አስተማማኝ የመረጃ ግንኙነትን የሚያረጋግጥ የበይነመረብ ደህንነት ጥበቃ ፕሮቶኮል ነው። SSL ፕሮቶኮል የድር ጣቢያው እውነተኛ መሆኑን እና ለጣቢያው የምትሰጠው መረጃ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንደማይውል ያረጋግጣል።

ቃላዊ የስም ማጥፋት

በአፍ የሚደረግ የስም ማጥፋት ሲሆን በህግ የሚያስቀጣ ነው።

ሶፍትዌርን ያለፈቃድ መጠቀም

የቅጂ መብት ያለውን ሶፍትዌር የባለቤቱን ፍቃድ ሳያገኙ መጠቀም ወይም መቅዳት ሶፍትዌርን ያለፈቃድ መጠቀም ነው።

አይፈለጌ መልዕክት

ካልታወቀ ላኪ የሚላክ የማይጠቅም እና የማይፈለግ የኢ-ሜይል መልዕክት ነው። አይፈለጌ መልዕክት አንድን መልዕክት ለማሰራጨት በአንድ ጊዜ ለብዙ ተቀባዮች የሚላክ ነው።

Page 62: ዕውቅና ያለው የMicrosoft የኤሌክትሮኒክ መማሪያ (E-Learning) ስልጠና - Computer Security

ስልጠና፦ ኮምፒውተር ደህንነት ጥበቃ እና ክብረ ገመና

62 © 2007 Microsoft ኮርፖሬሽን ፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ስፓይዌር

ካላንተ ዕውቅና በኮምፒውተርህ ላይ የሚጫን የኮምፒውተር ፕሮግራም ነው። ስፓይዌር ስለ ድር አሰሳ ልምዶችህ ወይም ሌላ የግል መረጃ ዝርዝሮችህ ወደ ሌላ በአውታረመረቡ ላይ ያለ ኮምፒውተር በድብቅ/በሚስጥር መረጃ ሊልክ ይችላል።

ትሮጃን ሆርስ

ራሱን ጌም ፣ መገልገያ ወይም ሶፍትዌር የሚያሰመስል ጎጂ የኮምፒውተር ፕሮግራም ነው። ትሮጃን ሆርስ ሲታይ ጠቃሚ ሶፍትዌር ቢመስልም በምታሄደው ጊዜ የኮምፒውተር ስርዓቱን የሚጎዳ ነገር ይሰራል።

የተጠቃሚ ስም

በኮምፒውተር ስርዓት ወይም አውታረመረብ ላይ ተጠቃሚን ለመለየት የሚጠቅም ስም ነው። በተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል የሚጠበቅ ኮምፒውተርን ለመዳረስ ተጠቃሚው ትክክለኛውን የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ስብጥር ማስገባት ይኖርበታል።

ቫይረስ

ኮምፒውተር በትክክል እንዳይሰራ ለማድረግ ወይም በኮምፒውተር ውስጥ ያለን መረጃ ለማበላሸት የተሰራ የኮምፒውተር ፕሮግራም ነው።

ተውሳክ

አብዛኛውን ጊዜ በእያንዳንዱ የኮምፒውተር ማህደረ ትውስታ ላይ የራሱን ቅጂዎች በመፍጠር በኮምፒውተሮች ላይ ራሱን የሚያሰራጭ የኮምፒውተር ፕሮግራም ነው። ተውሳክ በአንድ ኮምፒውተር ላይ ራሱን በማባዛት ኮምፒውተሩ እንዲበላሽ ሊያደርግ ይችላል።