37
1 ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

Embed Size (px)

DESCRIPTION

ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4/

Citation preview

Page 1: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

1ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

Page 2: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

2ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ይ ዘ ት / Content

• ዳግማዊ ምኒልክ (ርዕስ አንቀጽ)

• ም ኒ ል ክ ና የአድዋው ድል

• ምኒልክ- በጎታ

• አፍሪቃ! እንዴት ሰነበተች ?

ከኔልሰን ማንዴላ፣ ከዴሞክራቱ ጋ ር !

• ከኪነ ጥበብ ዓለም ፥

„ጣይቱ „

Page 3: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

3ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

እምዬ እንደገና

ምኒልክ

„በብረት ቅርጫት ቀፎ የሮም ጎዳና ላይ ያንን የኢትዮጵያ ንጉሥ ነኝ የሚለውን ሰው ይዤ እየጎተትኩ -ጥንታዊት ሮም በዚህ የታወቀች ናት- አመጥቼ አሳይችሁዋላሁ...“ ብሎ የፎከረው ጄኔራል አደዋ ላይ ተቀጥቶ ወታደሩን በትኖ ሸሽቶ ነፍሱን ለማዳን አሥመራ ይህ ሰው ገብቶአል። የአደዋን ጦርነት ለሚያውቁ ሰዎች ይህ አዲስ ታሪክ አይደለም።አዲሱ ታሪክ አዲስ መሆን ያለበት እንዴት አድረገው ኢትዮጵያኖች ተስማምተው በጋራ አንድላይ መላ-መተው የጣሊያንን ጦር አታለው ከምሽጉ አስወጥተው አውላላ ሜዳ ላይ ደበደቡት የሚለው ብልሃት ነው። ለዚህም ነው የአደዋ ጦርነት በትክክል መቼ እና በስንት ሰዓት ተጀመረ፣ ንጉሠ-ነገሥቱስ በዚያን ሰዓት የት ነበሩ የሚለውን ነገር በደንብ ለማስፈር አስቸጋሪ የሆነው። ሰሚንም ነገሩ ግራ የሚያጋባው በዚህ ምክንያት ነው ።

እሱንም ሁኔታ ወረድ ብላችሁ ትመለከቱታላችሁ።

ጣሊያኖች ሳይሆኑ በሁዋላ የተወለዱትና በታሪክ አጋጣሚ ሥልጣን ላይ የወጡ ወጣት „ኢትዮጵያኖች“ የምኒልክን ሓውልት ከራስ መኮንን ጋር እናፍርስ ብለው ተነስተው እንደ

Page 4: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

4ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ነበር አይረሳም።ይህም ነገር ሳይሳካላቸው፣ እንደምናውቀው ቀርቶአል። ይህንንም በምኒልክ ላይ የተጀመረውን ዘመቻ(መቼ አቆመ) ከብዙ በጥቂቱ ትንሽ ቆይታችሁ ዘለቅ ስትሉ ትደርሱበታላችሁ።ምኒልክ እንግሊዝ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ በ1900 ዓመተ-ምህረት መጀመሪያ ላይ የተካሄደውን „ የፓን አፍሪካ ጉባዔን በበላይ ጠባቂና በሊቀመንበርነት እንዲመሩ „ መጠየቃቸውን ዘግየት ብላችሁ እሱንም ዜና ታገኙታላችሁ።የምኒልክን መቶኛውን የሙት አመት ስናስታው ስለዚህ ንጉሥ ታሪካዊ ቦታውን ለመስጠትና ሙታንን የማስታወስ ባህል በአገራችንም እንደገና ተገቢውን ቦታ እንዲያገኝ-በማሰብነው።

በእርግጥ „የሰማዕታት ቀን“ የሚባል በዓል ነበረን። ግን ስንቶቻችን ነን የሞቱትን ዘመዶቻችንን አፈር ከለበሱ ወዲህ ዞር ብለን የምናስታውሰው?ስለምኒልክ ዛሬ ስናነሳ „…ቅባቅ ዱሱን የተቀባ አንድ ንጉሥ ብድግ ብሎ አሁን ከገባንበት ጣጣ መጣጣ እሱ መጥቶ ያወጣናል „ለማለት አይደለም።እሱማ! እንኳን እሱና በአንድ በዞረበት ያልታወቀ ስም የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችም ለብቻቸው በ21ኛው ክፍለ ዘመን „ዕድሜ ልካቸውን የሚገዙበት“ የብልጣ ብልጥነት የአታላዮች የአምባገነን ሥርዓት የማይሆን የማይደረግ ነገር እንደሆነ ሁላችንም ገብቶናል። የጠፋው ዕወቀትና ብልሃት -እንዴት? የሚለው ላይ ነው።ምኒልክ „አገሬንና ሕዝቤን ለነጮች አሳልፌ ለባርነት አልሰጥም“ ያለ የዘመኑ ጀግና ሰው ነበር። ከአሁኑ ዘመን ከእኛ ትውልድ ደግሞ የሚጠበቀው ሌላ ነገር ሳይሆን እንደዚህ ዓይነቱን አመለካከትና የዲሞክራሲ መብቶችን ከዚሁ ጋር አብሮ የማስጠበቅ ቆራጥነት ነው።በአጭሩ እሱም ከአገር ነጻነት ጋር እኩል አብሮ የሚሄድ የግለስብ ነጻነትና የግለሰብ መብቶች መከበር ከሁሉም ነገር በፊት ይህን ጉዳይ በሥራ ላይ ማዋል ነው።እሱ ደግሞ ምን እንደሆነ በትክክል ያሳየው „...ዲሞክራሲ እኮ ! በአፍሪካ አይሰራም... „ የሚሉትን ሰዎች አፋቸውን አንዴ ያስያዘው የአፍሪካው ልጅ የማንዴላ ሥራና ገድል ነው።እንግዲህ ስለማንዴላም አለፍ ስትሉ እዚሁ ቅጠሉ ላይ ታገኛላችሁ።

ለጊዜው መልካም ቀን

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

Page 5: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

5ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

Page 6: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

6ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ዳግማዊ ምኒልክ (ርዕስ አንቀጽ)

እኛ ኢትዮጵያኖች ሙታንን በማስታወስ „ዘለዓለማዊ“ ማድረግ ቀርቶ የሰባት አመቱ -ጥቂቱ ይህን ቀን ይጠብቃል- ተዝካር

ሳይወጣ እንኳን አብዛኛዎቻችን እንዳልነበሩ እንረሳቸዋለን።

አፈር ሰውዬው አንዴ ከለበሰ ማን አስታውሶት የእሱን መቃብር መልሶ መላልሶ ይጎበኛል? ማን አታክልት መቃብሩ ላይ ተክሎ አልፎ አልፎ እየወረደ እሱን ይኮተኩታል? አበባውንስ ጥዋት ማታ ወሃ እየቀዳ ማን ያጠጣል? ሜዳውንና አካባቢውንስ ማን ዞር ብሎ ይጠርጋል?

ይህን የሙታን ቀን የሚባለውን ነገር ቤተ- ክርስቲያናችንም አታውቅም። የሞስሊሙም ማህበረ ሰቡም እንደዚሁ አያውቀውም። አይንከባከበውም።

ለአገራቸው ዳር ድንበር ወይም ለነጻነታቸውና ለባንዲራቸው የሞቱትንና የወደቁትን ልጆቹዋን የመከላከያ የጦር ሠራዊቱም የጦር ኃይሉም ይህን ቀን በአመት አንዴ የሚያስታውስበት ቀን እንኳን - ሐውልት መሥራቱን እንተወው - የለውም።

ያለውንና የኖረውን ማጥፋት የነበረውን ማቃጠል ከዚያም አልፎ በእሱ ቦታ ደግሞ ለአዲሱ ትውልድ „…እኔም እኮ አዲስ ታሪክ መጻፍ እችላለሁ እንችላለን“ በሚለው ከንቱ ውዳሴ ብቻ ብዙ ትርዕይቶች ማቅረቡን የፖለቲካ መደቡ በተቃራኒው ያውቅበታል። በአለፉት አመታት እነደዚህ ዓይነቱን ቲያትሮች - የተመዘገቡ ናቸው- በተደጋጋሚ አይተናል።

Page 7: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

7ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

…ምን ለመሆን? ብሎ እነሱን የሚኮረኩር፣ የት ለመድረስ ?...ብሎ እነሱን በጥያቄ የሚያጣድፋቸው፣እሩጫው ወዴት ብሎ እነሱን የሚወቅሳቸው፣ የራሳቸው ሒሊናም ሆነ ሌላ ሰው የለም። በእርሱ ፋንታ በርቱ የሚል ድምጽ ግን እንደገደል ማሚቶ ከሁሉም ቦታ ይሰማል።

ስንቱ ነው የእናቱንና የአባቱን መቃብር የሚጎበኘው? አልፎ አልፎስ ብቅ ብሎ የሚጠርገው? የሚንከባከበው?

ምኒልክ ከሞተ አንድ መቶ አመቱ ነው። ይህን ምክንያት በማድረግ በስሙ የተዘከረበት ስሙ የተነሳበት ፣ጉባዔ በሥነስርዓቱ የተካሄደበት ጊዜ የለም። ቢኖርም ብዙበቦታ አልተሰማም።

ለቴዎድሮስም፣…ለዮሐንስም፣…ለዘውዲቱም ፣ለኃይለ ሥላሴም …ለንጉሥ ….እገሌና እገሊት ….ጥቂቱን ብቻ ለመቁጠር እነቁጠር ለእነሱም -ይህ ነው የአብዛኛው አስተሳሰብ- ምንም ስለ አልተደረገ „ለምን ለምኒልክ ብቻ ይህን ይህል ቦታ ከአልጠፋ ነገር ትሰጣላችሁ ?“ የሚለን ሰው አይጠፋም።

ምኒልክ የሚለው ስም በኢትዮጵያ የነገሥታትና የአገሪቱ ታሪክ -የሌሎቹ ስም ይደጋገማል - በአለፉት ሦስት ሺህ ዓመታት ምክንያቱ ምን እነደሆን በግልጽ አይታወቅም እንጂ- ሁለት ጊዜ ብቻ ነው በታሪክ ላይ ብቅ ያለው።

አንደኛው በኢትዮጵያ መንግሥትና ግዛት የምሥረታ ሚቶሎጂ [1]፣ የቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ ሲሆን፣

ሁለተኛው ደግሞ ከስንት ሺህ አመት በሁዋላ ብቅ ያለው የዳግማዊ ምኒልክ ሥራና ገድል ነው።

እኛ፣ የዚህን ትልቅ ጥቁር ሰው፣ የምኒልክን ታሪክ ዛሬ የምናነሳው መቶኛውን የሙት አመት ለማስታወስ ነው።

የእሳቸውን ታሪክ በጥቂቱ አስቀምጠን እንዳለፍን ምኒልክ ከሞቱ ከአምስት አመት በሁዋላ በደቡብ አፍሪካ የተወለዱት የሚስተር ኔልሰን ማንዴላ ዕረፍት - እኛም በዝግጅት ላይ እንዳለን ደርሶን- ይህ ዜና እኛንም እነደ ሌሎቹ አስደነግጦአል።

በሁለቱም የአፍሪካ መሪዎች መካከል የአንድ መቶ አመት ልዩነት አለ።

Page 8: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

8ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

አንደኛው ንጉሥ „…አገሬን ሕዝቤን ነጻነቴን ለባዕድ ለቅኝ ገዢ ወራሪ ኃይል አልሰጥም“ ብሎ በዲፕሎማሲውም መንገድ በሁዋላም ወረድ ብለን እንደምናየው፣እሱም አልሆን ሲል በጦር ሜዳም አደዋ ላይ ተዋግቶ የኢትዮጵያን ስም ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሕዝብን መብት- አሁን የእሱ ሐውልት ይፍረስ የሚሉትንም ሰዎች መብት ጭምር ተከራክሮ- ይህ ጀግና ሁሉንም ኢትዮጵያዊ አንድ ላይ አስተባብሮ ከእነሱም ጋር አብሮ አንድ ላይ ቆሞ ነጸነታቸውን፣ነጻነታችንን እሱ አስከብሮአል።

አለ ምክንያት አይደልም ኔልሰን ማንዴላ በሁዋላ የመሩት „የደቡብ አፍሪካ ናሺናል ኮንግሬስ ድርጅት „…ሃይማኖቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት፣…የነጻነት ጥማቱን እንደ ኢትዮጵያ፣… የማንነታቸውን ኩራታቸውንና አርበኝነታቸውን፣ ….ከነጮች ጋር የእኩልነትና መብታቸውን ትግል እንደ ኢትዮጵያ አድርገው…“ (-ለዚህ ደግሞ የማንዴላን ባዮግራፊ ተመልከት-) „ ለመታገል እነሱ አውጥተው አ ው ር ደ ው የተነሱት።

ኔልሰን ማንዴላ በብዙ ትላልቅ የሽንጎ አዳራሽ፣ የፓርላማ ሕንጻ ውስጥ በበርካታ የዓለም ከተማዎች ተጋብዘው ግሩም ንግግር ስለ የሰው ልጆች እኩልነት፣ስለ ነጻነትና ስለ ሰባአዊ መብቶች ስለ ዲሞክራሲና ስለ ዘረኛነት መጥፎ ጠንቅነት ንግግር እንዳደረጉ ሁላችንም እናስታውሳለን።

በኢትዮጵያ እንኚህ ሰውንና ድርጅታቸውን በረዳው በዋና ከተማው በአዲስ አበባው የሸንጎ መድረክ ላይ ግን ብቅ ብለው አንድ ጊዜም ንግግር እኚህ ሰው አላደረጉም። ለምን አዲስ አበባ የሽንጎ አዳራሽ ውስጥ ንግግር ለማድረግ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ምክንያቱ - እኚህ ሰው ኪዩባ ሳይቀር እዚያ ድረስ ወርደዋል- ለእኛ ግልጽ አይደለም። ለምን አሥመራ ሄደው እዚያም የሽንጎው አዳራሽ ውስጥ ሌላ ቦታዎች እንደአደረጉት እንደአልተናገሩ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።

በተባለው ግል የታሪካቸው በባዮግራፊአቸው፣ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የኢትዮጵያን የአይሮፕላን አስተናጋጆች ተመልክተው እንደተገረሙ ጽፈዋል።ቆየት ብለው አይሮፕላን አብራሪውን ሲመለከቱና ጥቁር ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያኔ በዓይናቸው ሲያዩ መደነቃቸውን እኝህ ሰው ጠቅሰዋል።

„ፖሊሱን፣የክብር ዘበኛውን፣ንጉሡን….ሲቃኙ ደግሞ „ለካስ ይህም አለ ወይ…“

Page 9: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

9ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ብለው ሳይደብቁ በመጸሓፋቸው ላይ አሥፍረዋል። በሁዋላም „በጦር ትግል ሥልት“ በኢትዮጵያኖች እንዲሰለጥኑ በንጉሡ ትዕዛዝ ተደርጎአል።

ማንዴላ ከንጉሡ የተሸለሙት ሽጉጥ በሁዋላ ጋርዲያን እንደ ጻፈው (ለኃይሌ ቦታ የሰጠው አንድም ትውልድ የለም) ሁለት ሚሊዮን ፓውንድ እሰከ ማውጣት ድረስ እነደሄደ ጋዜጣው ተገርሞ ጽፎአል።

ምኒልክ በነጻነት ትግል፣ማንዴላም በነጻነት ትግል ሕያው ሁነው ሁለቱም ይኖራሉ። አንደኛው የተረሳውን ለመድገም የቅኝ ግዛት ወራሪዎችን በመከላከል ነው። ሌላው የቅኝ ገዢዎችን የበላይነት በመቃወም ነው።

ምኒልክ ነጻነታችንንአስክብሮ መንግሥቱን አመቻችቶ ለአጼ ኃይለሥላሴ እና ለእኛ ለአለነው ትውልድ አገሪቱን አስተላልፎ ሄዶአል። ማንዴላም ኢትዮጵያን አረአያ አድርጎ ሁሉም የደቡብ አፍሪካ ኑዋሪዎችና ተወላጆች ነጩም ጥቁሩም፣ክልሱም ሕንዱም …ቻይናው አረቡም… የአገሪቱ ዜጎቹ ሁሉ እኩል በነጻ የሚኖሩበት ዲሞክራቲክ ሕብረተሰብ መሥርቶ አልፎአል።

በሁለቱ ሰዎች መካከል የአንድ መቶ አመት ልዩነት አለ። ለምን ምኒልክ የዲሞክራቲክ ሥርዓት ለኢትዮጵያ አላመጣም ብለን ልንከሰው አንችልም።

የምኒልክን የነጻነት ትግልና የፖለቲካ ጥበብ ከእሱም ጋር የኔልሰን ማንዴላን „ለዲሞክራሲና ለሰበአዊ መብቶች መከበር- ጥቁር ይሁን ነጭ፣ክልስ ይሁን ሕንድ- የእነሱን የዜጎች መብት መጠበቅና ማወቅ ማክበርም“... እነዚህን ሁለቱን አስተሳሰቦች አጣምሮ፣አዳቅሎ ለአገሬ እሰራለሁ፣ እንደዚህ ዓይነቱን ፖለቲካም በኢትዮጵያ አራምዳለሁ ለሚል ሰው፣ ሁለቱ የሰሩት ሥራ ሕያው ሁኖ የሚቆም ግሩምና መልካም፣እጅግም ደስ የሚያሰኝ ጥሩ ትምህርት ነው። ከዚህ ውጭ መጀመሪያ ልማት በሁዋላ ዲምክራሲና ሰበአዊ መበት የሚለው ራዕይ „ …ዕብደትና ምኞት“ ነው።

„ዕብደት“ ደግሞ የሚመጣውና የሚሆነው ነገር ስለ ማይታወቅ ይህም ነገር አደገኛ ስለሆነ ከዚህ ነገር ራቁ ይባላል። “…ምኞት“ ግን ምኞትደግሞ የሌላውን መብት እስከአልተጋፈ ድረስ „ይፈቀዳል።“

መድሓኒት ቀማሚ ነጋዴዎች እንደሚሉት“...ከዚህ ለየት ያለ ሓሳብ ያላችሁ ሰዎች ….ብዙ ቦታ ሳትደርሱ ሐኪማችሁን ለማንኛውም ነገር ጥርጣሬ ከአላችሁ እነሱን እባካችሁ አነጋግሩ…።“

Page 10: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

10ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

እኛም ይህን ማለቱን ለዛሬ - ይቅርታ አድርጉልን-እንመርጣለን።

መልካም ንባብ! መልካም ትካዜ! መልካም ግንዛቤና ምናልባት ደግሞ መልካም ጥያቄና አስተያየት !

እንደ ምኒልክ በዓለም ላይ የተከበረ፣ እንደ እሱም በአንዳንድ በገዛ ልጆቹ አልአግባብ የተጠላ - ሰው የለም!

ዋናው አዘጋጅ ይልማ ኃይለ ሚካኤል

[1](ይህን ደግሞ በሌሎች ትላልቅ የዓለም ሕዝብ ታሪክ የምናየው ነው- ሌላው ቀርቶ በተኩላ ሞግዚትነትና ከእሱዋም „የእናት ወተት“( እርቦአት ልትበላቸው፣አውሬ ስለሆነች ትችላለች፣ ግን ታሪካቸው ላይ ይህን አላደረገችም) የእሱዋን ወተት ጠብተው ያደጉት- ይህን አልነበረም ብሎ መከራከር የአንባቢው ፋንታ ነው- ሁለቱ የሮም መንግሥት መሥራች ወንድማማቾች ሮሚውሲና ሮሙሎስ፣ እዚህ ላይ ይህን ማስታወሱ በቂ ነው፣…. ግሪኮችም፣ጀርመኖችም፣…ሩሲያና ቻይናዎችም ጃፓኖችም በየፊናቸው እረ ስንቱ ሥልጣኔ… ተመሣሣይ ታሪክ አሉአቸው)

Page 11: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

11ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ም ኒ ል ክጀግንነትና የአዋቂ ሰው ሥራ ታሪክ

የዘመናዊ ፖለቲካ አሠራር አጀማማር በኢትዮጵያ

ዜናው ተናፍሶ ወሬው ዓለምን አዳርሶ ጥቁሩንም ነጩንም ቀዩንም ፍጡር ከዚያም ራቅ ብለው የሚኖሩትንም ቢጫውንም ሕዝብ ያኔ ከነበሩት ከእነጌቶቻቸው ያስደነገጠው አንድ ነገር ቢኖር አደዋ ነው።

ትንሽ ቆይቶም ዜናው በቅኝ ግዛት መዳፍ ሥር ነጻነታቸውን ተገፈው የሚኖሩትን ያኔ „ባሪያዎች“ ተብለው የተናቁትን ሕዝቦች የልብ ልብ ሰጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስደሰተው በሁዋላም እንደምናነበው የታሪክ ጸሓፊዎችንም በብዙ ቦታ በጣም ያስገረመው የአደዋ ጦርነት፣ የተጀመረው በየካቲት 23 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 1888 ዓ.ም. ከጠዋቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአሥራ አንድ ሰዓት ላይ ነው። በዚህ በትክክል በስንት ሰዓት በሚለው ጥያቄ ላይ የተለያዩ ግምቶችና ማስረጃዎች -ከተለያዩ ሰዎች ይቀርባሉ።

Page 12: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

12ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

በአንድ በኩል …ጦርና ጋሻ አንካሴና ጎራዴ፣ውጅግራ ጠበንጃና ምንሽር የያዙ ብሎኮና ነጠላ በርኖስና ካባ የደረቡ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች ተሰልፈዋል። በሌላ በኩል …ይህን ያህል ሺህ ወታደሮች መድፍና መትረየስ ቦንብና ዘመናዊ ጠበንጃ ሽጉጥና ሴንጢ ይዘው ታጥቀው በጥይት ሊቆሉአቸው መለዮ ኮፊያቸውን አድርገው ተደርድረው መሽገው ቆመዋል ።

አውላላ ሜዳ ላይ ሁለቱ ጦሮች ቢጋጠሙ አሸናፊው ማን እንደሚሆን ለማንም ሰው ግልጽ ነው።ይህንኑ ተማምነው ነው ጣሊያኖች አገር አቋርጠው ባህር ተሻግረው ድንበር ጥሰው አድዋ ድረስ ዘልቀው ገብተው እዚያ አንደኛው ኮረብታ ላይ ለቀናት ለወራት የመሸጉት።

ገና በጥዋቱ ጦርነቱ ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃ በፊት አንድ መሥፍን የጦር ልብሱን እንደለበሰ አረፋ ከሚያድቅፈው ከነጩ ፈረሱ ላይ ዘሎ ወርዶ በጥድፊያና በኩራት እርምጃ የቤተክርስቲያኑን በር በርግዶ ሁለት እና ሦስት ጊዜ ዝቅ ብሎ ከተሳለመና ከአከተበ በሁዋላ በአራት ቢበዛ በአምስት ጋሻ ጃግሬዎቹ ታጅቦ ቀጥ ብሎ በቀጥታ ንጉሱ ወደ ተቀመጡበት ወንበር ዘልቆ ይራመዳል።

በዚያች ደቂቃ አጼ ምኒልክ ከሌሎቹ የተወሰኑ መኳንንቶቻቸውና መሣፍንቶቻቸው ጋር አንድ ላይ ሁነው አስቀድሰው ሥጋ ወደሙ ተቀብለው በሕልና ጸሎት አምላካቸውን ለመጨረሻ ጊዜ የሚማጸኑበት ደቂቃ ላይ ነበሩ።

ያ ነብር መስሎ ዘሎ ከእነ ክብር ልብሱ መቅደሱ ድረስ -ጫማውን ያውልቅ

አያውልቅ ምንም ይምናውቀው ነገር የለም- ግንባሩን ቋጥሮ መሬቱን እየረገጠ እያንቀጠቀጠ የገባው መሥፍን ጠጋ ብሎ ቀስ ብሎ በጆሮቸው ጦርነት መከፈቱን ያበስርላቸዋል።

„መ… ምን ዓይነት ጥሩ ወሬ ይዘህ መጣህ!“ ብለው ንጉሡ ፈገግ ይሉና ግድግዳው ላይ የተሳለውን በዓይናቸው የማሪያምን ሥዕል ፈልገው (ማሪያምን ከሁሉም አብልጠው ይወዳሉ ይባላል) ለሰከንድን ያህል ትክ ብለው ተመልክተው „እንግዲያውስ አሁኑኑ እንነሳ…“ ብለው ለእልፍኝ አስከልካያቸው ትዕዛዝ ይሰጣሉ። ያ መሥፍን ይህን ዜና ይዞ የመጣው ዲፕሎማቱም ጦረኛውም ራስ

መኮንን ነበሩ።

“…በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የኢጥዮጵያ መኳንንት ከመንጋቱ በፊት ተሰብስበው ቅዳሴ ይሰማሉ።የቤተክርስቲያኑ በር ክፍት ነው።ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ቅዳሴውን በሚመሩበት ጊዜ ሁለት ጥየት ተተኮሰ።ይህም ምልክት ነበር። በዚህ ጊዜ የሐረርጌው ራስ መኮንን የንጉሡ ታማኝ አጎት ከቤተክርስቲያኑ ወጡ ።ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ ተመልሰው ገብተው የጣሊያኖንችን መምጣት ተናገሩ። ንጉሡም ወሬውን በጸጥታ አዳመጡ። ከዚያም ራስ መኮንን ወደ አቡኒ ዘንድ ቀርበው በሹክሹክታ ነገሩዋቸውና ተመልሰው ከመቀመጫቸው ተቀመጡ።አኡኑም መሰወቀላቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው በደከመ አነጋገር ̀ ልጆቼ ዛሬ የእግዚአብሔር ፍረeድ የሚገለጽበት ቀን ነው።ሂዱ።ለሃይማኖታችሁና ለንጉሣችሁ ተከላከሉ።ሁላችሁንም ከኃጢአታችሁ እግዚአብሔር ይፍታህ´አሉ።መኳንንቱም አeየቀረበ መስቀል እየተሳለመ ወደ የሠፈሩ

Page 13: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

13ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ሄደ….” ብሎ አንቶኒ ሞክለር ሁኔታውን ዘግቦአል።

ሁለት እርምጃ ከመኳንንቶች ጋር እንደ ተራመዱ አንዱ መሥፍን ከቦታው ሳይንቀሳቀስ ወደ ሁዋላ ቀርቶባቸው ኑሮ፣ ዞር ብለው ንጉሡ ተጽፎ እንደተነበበው „…ጸሎታችንን ለአምላክችን በበቂ አድርሰናል የሚቀረን አሁን የድርጊት ሥራ ነው። ይህ ደግሞ እዚያው የጦር ሜዳ ይለይልናል፣በል ተነስ…“ ብለው የቄሱን መስቀል ተሳልመው ወደፊት በችኮላ ተራምደው የሚቁነጠነጠው ፈረሳቸው ላይ ወጥተው ወደ ጦር ሰፈራቸው አፈሩንና አቧራውን ከአጃቦዎቻቸው ጋር ወደ ላይ እየመቱ የሚሆነው አይታወቅም ሁሉም ይከንፋሉ ።

ጎህ ሲቀደ በጥዋቱ እራስ መኮንን ከድንኳናቸው ወጥተው የጦር ልብሳቸውን ዕጣ ዕድሉ ለጠላት ከአመዘነ የመጨረሻ ቀናቸው ነውና፣ ገና ሳይለብሱ (እሳቸው ብቻ አይደሉም) ሌሎቹም በመነጽራቸው ተቻኩለው የእራሳቸውንም የጠላት መንደርን እሳቸው እንደቃኙት ሁሉ የጣሊያን ጄኔራሎች ራቅ ከአለው በትይዩ ከሚታየው ጋራ ጫፍ ላይ ሁነው ምኒልክ ከእነ

አጃቢዋቻቸው አቧራውን እየመቱ ሲመጡ በቀዩ ጃንጥላቸው በአንዴ ለይተው አይተዋቸው ነበር። ቀይ የለበሰ፣ የአንበሳ ጎፈር አናቱ ላይ የጫነ ፣የክብር ልብሱን ያወጣ-የመጨረሻ ሰዓት ሊሆን ይችላል- ብዙ ነው።

ያቺ ቀይ የንጉሥ ጃንጥላ ግን እንደ ደረጃው መሣፍንቱና መኳንንቱ አረንጓዴና ጥቁር መያዝ ይችላል- በሁዋላም አጼ ኃይለ ሥላሴን ማይጨው ላይ ጉድ ልታደርግ ምንም አልቀረም ነበር።

በእሳቸው ላይ ተነጣጥሮ የተተኮሰው ጥይት እሳቸውን ስቶ የጃንጥላ ያዣቸውን ሕይወት ይዞ ሄዶአል።

ድብልቅልቁ መንደራቸው ንጉሡ እንደደረሱ ወጥቶ ጠብቆአቸዋል። አንዱ ጠበንጃውን ይዞ ጋሻና ጦር የያዘውን አለቃውን ተከትሎ አብሮ ወደ ገላጣው ሜዳ ይሮጣል።ሴቶች ከውድ ባሎቻቸው ይሰናበታሉ።

የደረሱ ልጆች ወዲያና ወዲህ ከአባቶቻቸው ወይም ከተላላቅ ወንድሞቻቸው ትዕዛዝ ለመቀበል ወዲያና ወዲህ ይነሰነሳሉ።ገና ያልተጫኑት …በቅሎው አህያው ፈረሱ የቀንድ ከብቱ በጉና ፍየሉ ተደናግጠው በረቱ ውስጥ ይራወጣሉ።

Page 14: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

14ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ቀደም ሲል በጥዋቱ የመጀመሪያው ጥይት

ድምጽ ሳይሰማ ብዙዎቹ የንጉሠ ነገሥቱን አጀብና ግርግር አይተው -እሳቸው ያኔ ለማስቀደስ ወደቤተክርስቲያን መሄዳቸው ነበር -ገላጣውን ደማቁን የጸሓዩዋን ጮራ፣ጎሁን አይተው „…ዛሬ ድሉ“ ሁሌ እንደሚሉትና እንደሚመኙት „የእኛ ነው…“ ብለው ቀኑን መርቀው ተቀብለው ነበር።

እንደዚህ ብለው ለማሰብም ወታደሮቹ ምክንያት ነበራቸው። ሁለት ሦስት ጊዜ በኃይለኛ ዝናብ በእሱ ምክንያት ይከፈታል ተብሎ የታሰበውና ያለቀለት ጦርነት በጣሊዯኖቹ በኩል እንዲተላለፍ ተደርጎአል።

ፍረሃቻ በኢትዮጵያ ወታደሮች ዘንድ በሁዋላ አንዱ እንደጻፈው በፍጹም አይታይም ነበር። የአገር ነጻነት በሞትና በሽረት በደምና በመስዋዕተነት በጀግንነትና በቆራጥነት በሕብረትና በአንድነት ብቻ እንደሚመጣ ከታሪካቸው ከአገኙት የቆየና የነበረ ልምምድና እና

ተመክሮ በደንብ አድርገው ያውቃሉ። ይህን የመሰለ ቆራጥ ወኔ ከሌለ ደግሞ ትርፉ የሁዋላ ሁዋላ በሌላው ዓለም እንደታየው ውርደትና ባርነት እንደሆነም በደንብ ያውቁታል።

ለዚህ ነው ተሰባስበው ሁሉም አደዋ ድረስ የወጡት።

ቤተ-ክርስቲያን ለመሳለም ያልሄዱት – ሁሉም ወታደር መንደሩን አለ ትዕዛዝ ጥሎ መውጣት አይፈቀድለትም- ጥዋት ተነስቶ ዛፉን ተደግፎ

በየድንኳኑ የተቀመጡትን ከተሸነፉ በሁዋላ ምናልባት ስደተኛ የሚሆኑትን ታቦቶች ከቦ ዳዊቱን ይደግማል ። ድርሳኑን ያነባል። ከአምላኩም ጋር ይነጋገራል።

ሌሎቹ ስለሕልማቸው ከሕልም ፈቺዎች ጋር የዚያን ቀን ጥዋት ላይ ይወያያሉ።ብሩህ ዓለም ፣ትልቅ ዕድል፣ ሐብትና ልጆች አንተን ከዚህ በሁዋላ ይጠብቀኻል። አታስብ ታገኛለህ።ትሾማለህ ፣ትሸለማለህ።አንተ ደግሞ ተጠንቀቅ አለበለዚያ ….ይባባላሉ።

የሚመጣውን የማያውቁ ሴቶቹ ቡና

Page 15: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

15ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ለቅመው ቡና ቆልተው ቡና በዚያን ሰት ያፈላሉ። ቆሎ-የቡና ቁርስ- ይቆላሉ። በሶ ያበስላሉ። እንጀራ ይጋግራሉ። እንጨት ፈላጭ፣ በሬ አራጅ ድንኳን ተኳይና አፍራሽ ይንቆራጠጣሉ። ሕጻናት ልጆች ከብቶች ከበረት ያወጣሉ።በረትም ውስጥ ምን እንደሆን አይታወቅም መልስው ነድተው ይመልሳሉ።

በአጭር ጊዜ በጥቂት ሰዓታት እሰከ አፍንጫው ድረስ ታጥቆ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛቱ ሕዝቡዋንም ባሪያ አድርጎ ለመግዛት የመጣውን የጣሊያን ጦር በወታደሩ ድፍረትና በልጆቹዋ ጀግነኝነት በመሣፍንቱ ሕብረት፣በአንድ ንጉሥ ሥር በመላው ሕዝብ ተሣትፎ በአንዴ ለመደምሰስ ትእዛዝ ብቻ ሳምንቱን በሙሉ እነሱ የሚጠብቁት አሁን ተነስተዋል።

ተነስ የተባለ ሰዓት ያ ሕዝብ እንደ ጎርፍ ነው ያ ሰው ፣ቀፎው እንደ ተነካ ተርብ ሜዳውን ተነስቶ ከንፎ እንደሚያጥለቀልቀው የታወቀ ነው። ትንሽ ቆይተን እንደምናየው የሆነውም ይህ ነው። ሰው ይፎከራል።ቀረርቶ ይሰማል።ሲሮጥ ይወደቃል።ይነሳል።… ከበሮው፣እምብልታው፣ማሲንቆው፣ነጋሪቱ …ምኑ ቀረ ይጎሰማል።

ብድግ ብሎ ያ ጦር ያገኘውን ያገኙትን ወደ ሜዳው እየሮጠ ፊቱ ያገኘውን ሰው ሁሉ ፈጀው።

ያየውን የሰማውን አንዱ የጣሊያን ጸሓፊ እንደዚህ አድረጎ ያቺን የቀውጢ ሰዓት ለመጪው ትውልድ አስቀምጦታል።

„… የአበሾች ጦር ወራሪ እንጂ `ጦርነት` አልነበረም።ሕዝቡ ከሁሉም ብሔረሰብ ተወጣጥቶ ቀርቦአል።የሚዋጋው ደግሞ

ፈረሱ በቅሎው አህያው ሁሉ በአንድነት ከሰዎች ጋር ተደባልቆ በመሆኑ ግራ ገብቶን ነበር።ጦርነቱን ከወታደሮች ጋር ብቻ አልገጠምንም።

በጦርነቱ ውስጥ ሴቶች ሽማግሌዎች ሕጻናት ቄሶችና ቆማጣዎች ሳይቀሩ ወጉን…“ ብሎ የዚያን ጊዜ በዚያን ዘመን አጃቢ ጋዜጠኛ ሁኖ በጦርነቱ ላይ ጠሳተፈው ካፒቴን ምልቴዶ ከጄኔራሎቹ አፍ ያዳመጠውን ቃል እንደዚህ አድረጎ ጥሩ አድርጎ “በአደዋ ሪፖርቱ ” ላይ ለመጪው ትውልድ እንዲያውቁት ዘግቦአል።

ተእኛ ወገን ይህን የጦር ሜዳ ድልና ትርምስ በጥሩ ቃላት አሳምሮ ያቀረበው ያስቀመጠው/ጡት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረ የሱስ ጣሊያን አገር የተማሩ እዚያም ብዙ አመታት የኖሩ ያነበቡ የተመራመሩ ትልቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር ናቸው።

በተመሳሳይ ብዕር ከዚያ በማያንስ ለየት ባለ ዓይን ጸሓፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴም -አውሮፓ ያልሰነበቱ- በማህደራቸው ላይ አሥፍረውልን ሄደዋል።

አፈወርቅ „…ጦርነቱ ተጀመረ።…ከዚያማ ወዲህ ምን ይነገራል።ኢትዮጵያዊው …አደጋ እንደተጣለበት ባየ ጊዜ የቸኮለው በሌጣው

Page 16: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

16ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

(የቀረው ግን ገና እንቅልፉን አላስብ ተኝቶ ነበር)በሌጣው ፈረሱ ላይ ወጣ። የጣሊያ መድፍ ነው በማለዳ የቀሰቀሰው።…የሸዋ ፈረሰኛ፣የጎጃም እግረኛ የትግሬ ነፍጠኛ ያማራ ስልተኛ ከቦ ያናፋው ይቆላው ያንገደግደው ጀመር።

ከእንዝርት የቀለለ የጁዬ ተነብር የፈጠነ በገምድሬ ተቋንጣ የደረቀ ትግሬ …(ጠላትን) ፈጀው አሰጣው ዘለሰው።

ወደሁዋላ ቀርቶ የነበረው ሁሉ ነገሩን ሳያውቅ ወደ ዮርነቱ ይጓዝ ነበር።ነገር ግን የጄነራል ባራቲየርን መሸሸና የጦሩነረ መፈታት ባየ ጊዜ ያ ወደሁዋላ የነበረው የታሊያን መድፈኛ መጫኛውን በጎራዴ እየቆረጠ መድፉን እየጣለ በመድፉ ሥፍራ እሱ እየተተካ በአጋሰሱ እየጋለበ ደንግጦ

አሥመራ ገባ…“

ጥቂት ቆይቶ እንግዲህ ሜዳው ደም ለብሶ ሣሩ አፈሩ እንዳለ ቀይ ሁኖአል። ጥቁሩም ነጩም ወንድ ልጅ ተናንቆ አደኛው ለባሪያ ፍለጋ ሌላው ለመብቱ- ተያይዘው ወድቀዋል።

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ተጋድሞ

ያቃስታል።ትንሽ ወይም መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት አንደምንም ብሎ አጠገቡ በአገኘው ፈረስ ላይ ወጥቶ እንደገና ጠላቱን አባሮ ለመግጥም ኮርቻው ላይ ለመውጣት ይተናነቃል። ሌላው ጓደኛውን እንዲረዳው ወይም እንዲጨርሰው ከባድ ጥያቄ ያነሳበታል። ሚስቱን ልጆቹን ቤቱንና ሐብቱ እንዳይበተኑ ጧሪ አናትና አባቱ እንዳያጡ ዘመዶቹን ጭምር -ጣሊዩንም ኢትዮጵያዊም – አደራ እያለ ይህን ከአላደረክ ….ውሻ

ውለድ እያለ እየረገመ ያንቀላፋል።

በሁዋላ ይህን ጸሓፊ ሁሉ እየቆጠረ እንደጻፈውና እኛ አገላብጠን እንዳየነው ከሁለቱም ወገን በአንዴ እና በአጭር ጊዜ ከ ስንት….ሺህ ወታደሮች በላይ ተረፈረፉ ብለው ደብተራቸው ላይ ዘግበውታል።

በቢላና በሴንጢ በጎራዴና በሳንጃ በጥይተና በመድፍ የቆሰለ ክንድ፣ አንገትና ትከሻ፣ በጥይት የተበተነ ቅልጥም ፣አከርካሪ አጥንት ስንት

እንደሆን መገመት ያስቸግራል።

በጣሊያን በኩል አለጥርጥር የቆሰሉትን የሚንከባከቡ ሓኪሞች ነበሩ። በኢትዮጵያ በኩል ከወጌሻ አወቂዎች ሌላ የቆሰለውን ክንድ በጥይት የተመታውን ቅልጥም ማን ቆርጦት ቁስሉን እንደ ጠገነው፣ማን የውጋት ማስታገሻ እንደሰጠ ምንም የምናውቀው ነገር የለም። እኛ የማናውቀው የጦር

Page 17: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

17ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ሜዳ ቁስል መድረቂያ መድሓኒት፣ውጋት ማስታገሻ፣ጭንቀት ማስረሻ…ቅጠላ ቅጠሎች እና ሥራ ሥሮች ይዘው ይቅረቡ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።

ምናልባት የቄራ አራጆች፣የቤተ መንግሥት ወጥ ቤቶች ብልት አውጪ ጎሮምሶች ሐኪም ሁነው የአገራቸውን ልጆች ረድተው እንደሆን እንደዚሁ ምንም የምነውቀው ነገር የለም። ብዙው ጀግና ግን ከአከለ ስንኩልነት ሞትን እንደሚመርጥ አርበኞች – ብዙ ጊዜ አይናገሩም- ከተናገሩ ይህን ውሳኔ እንደሚመርጡ እነሱ ያነሳሉ።

ማታ ላይ ጅብ ወድቆ የሞተውን ወታደር ከሁለቱም ወገን እኩል ቀብሮል።አሞራ የተረፈውን ከእነአጥንቱ አንስቶ ከንፎአል።የተረፈውን በተነጋታው በዚያ በደም በተበከለው ምድር ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተሰብስበው ቄሶች ፍትሃት አውጥተው፣ጉድጓድ ተምሶ እኩል አንድ ላይ ጥቁሩና ነጩን አንድ ላይ አብረው ቀብረዋል። እነደ አነበብነው የሩሲያ ቀይ መስቀል ሐኪሞች አብረው ተሰልፈዋል። በቁጥር ስንት እንደነበሩ፣ነርሶቹና አስታማሚዎቹ ምን ይህል እውቀት እንዳላቸው፣የመድሓኒቱ ብዛት ስንት ሳጥን እንደሆነ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።

ጦርነቱ ግን በዚሁ ቀን አላለቀም። ሌሎች ተጨማሪ ቀናቶችን ጠይቆአል።

ጸሓፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ አጤ ምኒልክ ለጦርነት የተነሱት እላይ እንደ ተባለው ከገብርኤል ቤተክርስቲያን ሳይሆን ከጦር ሠፈራቸው ነው ይላሉ።

“…በዚያን ቀን የዘቡ ተራ የትግሬው ገዢ የራስ መንገሻ ነበር።500 ነፍጥ የሚሆን

የያዙ የሱ ሰዎች ዘብ ሲጠብቁ በየካቲት በ23 ቀን የቅዱስ ጊዮርጊስ ለት ለሊቱን በ11 ሰዓት የኢጣሊያ ወታደር ተሰልጎ መጥቶ ከበሩ ላይ አደጋ ጥሎ ከዘበኛው ጋራ ተታኮሰ። እነዚያም ተታኩሰው ከኢጣሊያኖች 2 ባሻባዙቆችን ማረኳቸው። ምርኮኞቹንም ቢጠይቋቸው እንዲህ አሉ። የአጤ ምኒልክ ሠራዊት ቀለብ ሊመጣ ርቆ ሄድዋል፣ሠፈሩም ባዶ-ነው አደጋ እንጣልበት ብለው ኢጣሊያኖች 4 ጄኔራል ባባ ገሪማ በኩል፣ አንድ ጄኔራል በማሪያም ሽዋቴ በኩል ተሰልፎ መጥቷል ብለው አወሩ።

ይህን ወሬ በሰማ ጊዜ ከዘበኞቹ አንዱ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ሠፈር መሮጥ ጀመረ። ቀኛዝማች ታፈስንም ከመንገድ አገነው።ሌሊቱም አልነጋም፣ገና ጨልሞ ነበርና ማነህ ተባባሉ።ይህነንም ወሬ ነገረው። ቀኛዘዝማች ታፈሰም ይህንን በሰማ ጊዜ ከበቅሎ የነበረውበፈረስ ተዛውሮ ወደ ንጉሡ ድንኳኘ በፈረስ ደረሰ ።የንጉሠ ነገሥቱን የእልፍኝ ዘበኞች ተጣርቶ መምጣቴን ወደ ጃንሆይ አሰሙለeኝ አለ። አጤምነኒልክም ይህን በሰሙ ጊዜ አለጊዜው ስለምንመጣ ብለው ከእልፍኝ ድንኻን ወጥተው ጠየቁት። እሱም ኢጣሊያ አደጋ ሊጥል ተሰልፎ ጠቅሎ መምጣቱን ተናገረ።…” (ከጳውሎስ ኞኞ የተገኘ)

ለሚቀጥሉት ቀናት የኢትዮጵያ ሠራዊት ጣሊያን እያባረረ ከትግራይ አስወጥቶ

Page 18: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

18ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

አሥመራ ድረስ ሸኝቶአቸዋል።

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ “የበሰለ የፖለቲካ አካሄድንና እርምጃን የማያውቁ ጥራዝ ነጠቅ ወጣቶች” አንድ የጀርመን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ጎታ ከተማ በጀርመን አገር ዘንድሮ በተደረገው የመጀመሪያው የምኒልክ ታሪካዊ

ጉባዔ ላይ እንዳሉት “ብቅ ብለው …ከመሬት ተነስተው ነገሮችን ሳይመረምሩና ሳያመዛዝኑ አጼ ምኒልክን ኤርትራን ለጣሊያን አሳልፈው ሰጡ የሚባለው ብለው ክስ እሳቸውንም የሚከሱ ሰዎች የያራምዱትና የሚያራምዱት አቋም ተገቢ አመለካከት አይደለም” ብለው የተቹአቻው።

መቼ ይህ ብቻ ።

አንድ አዛውንት አርበኛ ተናደው የዛሬ ሃያ አመት ገደማ እንዳሉት- መለስ ብሎ ለማስታወስ የምኒልክ ሐውልት በይፋ በአደባባይ ጩኸትና በጋዜጣ፣ በራዲዮም ጭምር ተለፍፎአል – „ገና”ሰ ውዬው እንዳሉት”… አፍንጫቸውን በደንብ ያልጠረጉ መቀመጫቸውንም ያላበሱ የአገራቸወን ታሪክ የማያውቁ ልጆች የምኒልክ ታላቅነት ረስተው ሐውልታቸው ከአራዳ ጊዮርጊስ ይነሳ፣ ይፍረስ፣የመኮንንም

መታሰቢያ ይውደቅ ብለው እሰከመሟገት ድረስ ዘልቀዋል።…ይህን መስማቱ“ ሰውዬው ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ ያኔ እንዳሉት ” ማየቱም መስማቱም …ያሳዝናል ያሳፍራል…“ አርበኛው ብለዋል።

እንደ ምኒልክ በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ ገኖ የወጣ የሃያኛው ክፍለ-ዘመን መሪ በአፍሪካ (ማንዴላንና አጼ ኃይለ ሥላሴን አብረው የሚጠቅሱ አሉ) የለም።

እንደእሳቸውም እንደ ምኒልክ በሌላ በኩል „…ተማርን እናውቃለን ከእኛ በላይ ማንም ሰው የለም ብለው በሚመጻደቁ „ሰዎች፣በተለይ ነጻ- አውጭዎች ነን ብለው በሚኩራሩ ሰዎች ዘንድም የተጠላ ንጉሥ“ ( የታወቀውን ክሳቸውን መልሶ ለማስቀመጥ) በአፍሪካ የትም ቦታ የለም።

ምኒልክ በአውሮፓ ነጮች ጣሊያንን መክቶ በማዋረዱ እንደ ተጠላ፣ በዚያውም መጠን ይህን ንጉሥ እንዳከበሩት መጥቀሱ የተጸፈውን መድገም ነው።

ምኒልክ እንደምናውቀው የአገሩን የኢትዮጵያን ነጻነት ብቻ ሳይሆን የጥቁርን ሕዝብ መብት ያስከበረ ጀግና ነው።

ያ ልጅ ሲወለድ ኢትዮጵያ ያኔ በመሣፍንቶች ተከፋፍላ ደክማ ሆና የወደቀች የተረሳች አገር ነበረች። እሱ ብቻ አይደለም።አብዛኛው የዓለም ሕዝብም በጠንካራዎቹ ያኔ ኃያላን መንግሥታት ተብለው በሚጠሩ የአውሮፓ መንግሥታት ሥር፣ በእነሱ በቅኝ ገዢዎች መዳፍ ሥር ወድቃ ፍዳውን ታይ እንደ ዕቃም ትሸጥ ትለወጥም ነበር።

የዛሬዋ ሰሜን አሜሪካ በእንግሊዚና

Page 19: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

19ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

በፈረንሣይ በስፔን ጭምር ተይዛ ትገዛ ነበር። ወረድ ሲባል ደቡብ አሜሪካ በስፔንና በፖርቱጋል መዳፍ ሥር ነበሩ።….እሲያና አውስትራሊያ ደግሞ እንደዚሁ፣በእንግሊዝና በስፔን በሆላንዶች ጭምር ተይዘው ይማቅቁ ነበር።…. ግርክና ቡልጋሪያ መካከለኛው ምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ ደግሞ በተራዋ በቱርክ ሥር ተጠቃለው እነሱ ይተዳደሩም ነበር።

እንደ ምኒልክ በአንዳንድ „ቀባጣሪዎች ዘንድ „ አንዱ እንደ አለው “የተጠላው“ አጼ ቴዎድሮስ ነው። እሱም ንጉሥ ይህን አይቶ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ „ከአውሬዎች አፍ ለማዳን“ የፖለቲካ አካሄዱን በደንብ አላወቀበትም እንጅ ተነስቶ የተቻለውን አበርክቶአል ።

አጼ ቴዎደሮስ ኢትዮጵያን አንድለማድረግ ሲነሱና አባታቸውን ንጉሥ ኃይለመለኮትን አሳደው ድል አድርገው ወጣቱን ምንሊክ እና የሸዋ መኳንንትን ማርከው ይዘው ወደ ጎንደር ሲመለሱ ገና የእናቱንና የአባቱን ፍቅር ያልጨረሰ የአሥር አመት ልጅ -ምኒልክ እንደነበረ ይነገርላቸዋል።

የጣሪክ አጋጣሚ ነው እንጅ- ዕድሜ ለንግሥት ቪክቶሪያ ማለት እንችላልን- ቴዎድርስ ሲሞት እጃቸው የገባችውን ኢትዮጵያን እንግሊዞችም ይዘዋት እሰከ መጨረሻው ሰዓት እስከ 1960 ዓ.ም. (እ.አ.አ) ድረስ – አብዛኛው የጥቁር ሕዝብ አፍሪካ ነጻ የወጣበት ቀን ድረስ እስከዚያ ድረስ እኛንም አባቶቻችንና እናቶቻችን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ጭምር እኩል ቀጥቅጠው እነሱ በገዙን ነበር።

አንዳንድ ሰዎች አሁን በደርግ ጊዜና ከደርግ ወዲህ በተፈጠረው ሁኔታ ግራ ተጋብተው „የእንግሊዝ ወይም የጣሊያን ወይም

የቱርክና የአረቦች…ቅኝ ተገዢ ብንሆን እንሰለጥን ነበር…“ እሰከማለትና እሰከ መመኘት ድረስ ሄደው ይህን ነገር ከአንዴም ሁለቴ እንደ „ጥሩ ነገር“ አንስተው ሲጫወቱ ከሰዎች አንደበት እኔ ብቻ ሳልሆን እናንተም ሳትሰሙት አልቀራችሁም።

ባርነትና የነጮች ተገዢ መሆን ምኑም ላይ ጥሩ ነገር የለውም።እሩቅ ቦታ መሄድ አያስፈልግም። ለአርባ አመታት በተከታታይ የጣሊያን ቅን ግዛት የነበረችው ኤርትራ፣ወይም ጅቡቲ ወይም ሱማሌ ፣ወይም ደግሞ ኮንጎ፣ሊቢያ ግብጽ፣ናይጄሪያ፣ ለሦሰት መቶ አመታት በነጮች ሥር የማቀቀቺው ደቡብ አፍሪካ…እነሱ ዛሬ የት ደረሱ ብሎ መጠየቅና መመራመር ተገቢ ነው። በነጮቹ እንደሚባለው ገዢነት የትም አልደረሱም።

ደቡብ አፍሪካና ናይጄሪያ ኬንያና ጋና ለምን የዲሞክራቲክ መንገድን ሲከተሉ ለምን ሱማሌና ኤርትራ እነዚህ እንደላይኞቹ ኮለኒ የነበሩ አገሮች የአምባገነን ሥርዓትን መረጡ? ለሚለው ጥያቄ መልሱን ማግኘት ከባድ አይደለም።

እሱን ግን የተነሳነው ስለምኒልክ ገድልና ሥራ

መተረክ ስለሆነ እዚህ ላይ እንተው።

ኢትዮጵያም ነጻነቱዋን ጠብቃ የነጻ- ጥቁሮች

Page 20: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

20ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

መንግሥት ባትሆን ኑሮ፣ አጼ ኃይለ ሥላሴም አይኖሩም ። እሳቸውም በኢትዮጵያ ላይ

አይነግሱም። እሳቸው ባይኖሩ ደግሞ ያ የአውሮፓ የቅኝ ገዢዎች መጨፈሪያ አህጉር ሆና የከረመቺው አፍሪካ ፣ በስድሳው አመተ ምህርት በምንም ዓይነት ነጻ መሆኑዋ- በደንብ ከአሰብን- የሚያጠራጥር ነው።

ኢትዮጵያ ባትኖር ኑሮ-ይህ ነው ሓቁ- እንኳን ጥቁር አፍሪካ ጥቁር አሜሪካኖቹም ከነጮች የበላይነት መዳፍ ወጥተው የእኩልነት መብታቸውን ዛሬም -ግልጽ እንሁን- አይቀዳጁም ነበር። ይህን ሓቅ ሌሎቹም አንስተው ተናግረውታል። ደጋግመው ብለውታል።

መቼም ኢትዮጵያን ለመውረር እንደ ቀላል ነገር እንደ መናፈሻ ውስጥ ሽርሽር፣ እንደ ሜዳ ላይ የፈረስ ግልቢያ፣እንደ የወንዝ ወሃ፣ግራና ቀኝ እየመቱ ሲያሸኝም እያንቦጫረቁ እንደመሻገር አድርገው የተመለከቱት ጣሊያኖች ብቻ ነበሩ። ሌሎቹማ ሞክረው አልሆነላቸውም። ምኒልክ ሲታመም እንግሊዞቹም፣ ከእነሱ ጋር ፈረንሣዮቹም፣ጀርመንኖቹም

ስንት ተንኮል እንደሰሩ ተጽፎአል።

ምን ያድርጉ አሰብን የመሰለ ወደብ በትንሽ ብር በስምንት ሺህ ማርትሬዛ ቀደም ሰል ከአንዱ የዋህ ነጋዴ ገዝተዋል።ይህ የአሁኑን የመሬት ቅሚያ ወረራ -ሊዚንግን ያስታውሳል።

ምጽዋን አታለው ይዘው በጥቂት ጊዜያት የራስ አሉላን ግዛት ባህረ-ነጋሽን ጨምረው በሁዋላ ያንን አካባቢ ኤርትራ ብላው ሰይመው ፃሊያኖች ባንዲራቸውን ሰቅለው ቁጭ ብለዋል።

ኢትዮጵያን ከያዙ፣ ቀይ ባህርን ከጠቀለሉ፣ሱማሌን ከአካተቱ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የጦር መርከባቸውን ከላይ እስከ ታች ተዘዋውሮና ተንሸራሽሮ አላፊ አግዳሚውን የደም ሥር መንገድ የሚቆጣጠሩበትና የሚያዙበት ቀን እሩቅ እንደማይሆን ለእነሱ ታይቶአቸዋል።

አካባቢው ዱሮም ሆነ አሁንም መንደሩንም ጠረፉንም ባሕሩንም ለመቆጣጠር አመች እንደሆነ ለሮማውያኖች ገና ዱሮ ግልጽ ነበር። ጥንታው ግሪኮችም ከቱርክና ከአረቦችም ጋር ሁነው ይህን ያውቃሉ።ቀይ ባህርን የያዘ የእሲያና የአውሮፓን መገናኛ በር ያዘ ማለት ነው።

ከዚያም በላይ-ብዙዎቹ እንደሚገምቱት፣ በከርሰ መሬቱ ውስጥ ነዳጅ ዘይትና

Page 21: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

21ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ጋዝ አለው።እዚያ ባህር ውስጥ ግሩም ጣት የሚያስቆረጥሙ የባህር ፍራ ፍሬዎችና የማይጠገቡ የዓሣ ዓይነቶችና ዘሮች ብዙም ሳይደከምበት የሚጠመድበት፣የሚሰበሰብበት ቦታ ነው።

ከባህሩ ወጣ ሲሉ ግሩም አየር ያለው የኢትዮጵያ ደጋው አካባቢ ያ ምድር በተፈጥሮው የሚማርክ ነው። አለፍ ሲሉና ወረድ ሲሉ ደግሞ መሬቱ ለስንዴና ለገብስ ለቦቆሎና ለጥራጥሬ ለሥጋ ከብትና ለዶሮ እርባታም መሓል አገሩም በሕዝብ ብዛት ለተጣበበቸው የጣሊያን ዘር ጥሩ መሰፈሪያና መኖሪያም ያመቸ ነው። ርቀቱም ከሮም እሩቅ አይደለም። በመርከብ በቀላሉ ይደረስበታል።

እንደሌላው የአፍሪካ ግዛቶች ደጋውና ወይነ ደጋው የኢትዮጵያ መሬት አውሬና ወባ ወይም ተላላፊና አስፈሪ በሽታዎች የሉትም። ቀዝቀዝ ያለው አየሩ ይህ ደግሞ የትም በትሮፒካል አፍሪካ የማይገኝ ቦታና ምድር ነው።

እንግዲህ በጥጋብና በንቀት -ነጭ በመሆናቸው ብቻ -በማንቋሸሽና በመጥላላት -ትንሽ በመቅላታቸው ብቻ – በጭንቅላት ጨዋታ እኛ እንበልጣቸዋለን በሚለው የዘረኝነት አመለካከት- የእኛን የቆየ ጥበብና ብልሃት ባለማወቅ- ኢትዮጵያን በዚያውም በቀላሉ የምሥራቅ አፍሪካን አካባቢ ከሌሎቹ ቀድመን እኛ እያዛለን በሚለው ከንቱ ምኞታቸው በኢትዮጵያ ላይ ጣሊያኖቹ የድብቅ ጦርነት አውጀው አምባላጌ ላይ ቀደም ሲል ገብተው እዚያ መሽገዋል።

በትክክል ለመናገር ጦሩ በኢትዮጵያ ላይ የታወጀው አድዋ ላይ አይደለም። ጦሩ የታወጀው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር

ተስማምተው ምጽዋን የያዙ ዕለት ነው።

ኢትዮጵያን ለመያዝ ደግሞ ሥነ-ልቦናችንን እና ባህሪአችንን አስተሳሰባችንና አካሄዳችንን በደንብ ጊዜ ወስደው እነሱ አጥንተዋል።

ትንሽ እነሱ ያስቸገራቸው፣ያስቸግሩ ይሆናል ብለው ያሰቡት እነሱ እራሳቸው„ሸዋ“ ብለው ነጥለው የሚጠሩት „የአማራው“ ሕዝብ ክፍል ነበር።

እንደ አንድ ሰው ሆኖ የተነሳባቸው ግን ወደሁዋላ ላይ ቆየት ብለን እንደምናየው „አማረው“ ብቻ ሳይሆን ሁሉም -መቁጠር አያስፈልግም- ድፍን የኢትዮጰያ ሕዝብ ነው። ይህን ማስተባበር ደግሞ አንድ ምሁር እንደአለው የምንልክ ችሎታ ነው።

ትግሬና አማራ፣ጎንደሬና ጎጃሜ ወሎና ሐማሴን፣ኦሮሞና ከፋ፣ እስላምና ክርስቲያን፣ካቶሊክና ኦርተዶክስ፣ሱማሌና አፋር፣ደቡብና ሰሜን….አንዳንዶቹ ችግሮች ብቻ ለመጥቀስ፣ በዘር በቋንቋ፣ በዘውዱ ይገባኛል ጥያቄ ፣በእበልጥ ፉክክር፣በንቀት በቅናት… ነጮቹ ተዘዋውረው በአካሄዱት ጥናቶች እንደደረሱበት „አለመግባባት“ (በሕዝቡ መካከል አይደለም) በገዢው መደብ ተወካዮች መካከል እንዳለ ተገንዝበዋል።

ዘውዱ ምኒልክ እጅ ያኔ በመግባቱ ሌላው የገዢ ክፍል አኩርፎአል። ሌላው ቀርቶ የዮሓንስ ዘውድ በኑዛዜው መሰረት ለራስ መንገሻ በመሰጠቱ የትግራይና የሐማሴን መሣፍንት ራስ መንገሻን ከድተው እጃቸውንም ግዛታቸውንም ይዘው ለጣሊያን ማስረከቡን መርጠዋል።

ደጃች ባህታ ሐጎስ አካለጉዛዬን፣ደጃች ደብብ አሥመራንና አካባቢዋን ፣ባላምበራስ

Page 22: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

22ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ክፍለ ኢየሱስ ደግሞ ከረንና ቦጎስን እንደ ገጸ-በረከት ጋዜጠኛው ጳውሎስ ኞኞ እንደ ጻፈው እንደ ገጸ-በረከት ለጣሊያን መንግሥት ማበረከቱን እነሱ መርጠዋል።

ጄኔራል ባራቲየሪ የጣሊያን ጦር ዋና አዛዥ ይህን ተመልክቶ ሌሎችንም ግንዝቤዎች ከግምቱ ውስጥ አስገብቶ ፣ ኢትዮጵያን ወሮ ነጻነቱዋን ገፎ ያንን እሱ እንደአለው „ንጉሠ ነገሥት ነኝ የሚለውን ምኒልክ የሚባለውን ሰው ከብረት በተሠራ ቅርጫት እንደ ዱር አውሬ እጅና እግሩን አሥሮ በሮም መንገድ ላይ ለተሰበሰበው ሕዝብ የምሥራቹን እየጎተተኩ አቀርባለሁ…“ብሎ እሰከ መፎከር ድረስ ይህ ሰው እንደሄደም መገንዘብ ይቻላል።

ምኒልክን በብረት ቅርጫት በቀፎ ውስጥ የተመኘ ሰው -ያውም ደግሞ በሮም መንገድ ላይ በሰንሰለት ለመጎተት እቅድ ያወጣ ሰው- ለሌቹ ተራው ሕዝብና ለመሣፍንቶቹ ምን እንደተመኘ መገመት አያስቸግርም።እንግዲህ ምኒልክ ይህን አይቶ ነው ይህንንም ሰምቶ ነው ግሩም የሆነውን ፖለቲካውን የቀየሰው።

የዱሮውን የሮም ኢምፓየር ግርማ ሞገስ ለማስመለስ አርፍዳ የተነሳችው ጣሊያን እንደ ኢትዮጵያ ያለች „ትንሽ“ ጭዳ አገር እንደምንም ብላ ፈልጋ አግኝታለች። ይህንን የይገባኛል ፍላጎት ቀደም ሲል በርሊን ላይ በተካሄደው አፍሪካን የመቀራመጥ ጉባዔ ላይም አንስታለች።

ሮም -ጥንታዊት ሮም- ያኔ በአውሮፓና በሌላው ዓለም በምትፈራበትና በምትከበርበት ዘመንና ጊዜ ድል የመታቻቸውን አገር መሪዎች በብረት

ሰንሰለት አሥራ በሮም መንገድ ላይ እንደ ጥሎሽ ትጎትታቸው እንደነበር መጽሓፍም ላይ በላይብረሪ በፊልም ቤት ጊዜ ያለው ሰው ይህን ነገር ሊመለከት ሊከታተል ይችላል።

በዘመናቸው ሮማውያን ፈረንሣይንና እንግሊዝን ጀርመንና ግሪክን …ስላቭንና

ባልካንን ባሪያ እድርገው መንገድ ላይ ነድተው አዋርደው እነሹ ገዝተዋል።

ያንን ነበር እንደገና እነሱ ከአንድ ሺህ ስንት መቶ አመት በሁዋላ ተመልሰው ተቋቁመው -በገዛ ድካማቸው ተከፋፍለው ተበታትነው የወደቁት- ለዓለም ሕዝብ እንደገና ለማሳየት የፈለጉት።

ሮም ሁሉን አዋርዳ የእርሻ መሬቱን ቀምታ ወርሳ፣ ከብቶቹን እየናዳች ህዝቦቹዋን ስትቀልብ ያኔ እላይ የተጠቀሱት አገሮች የዛሬን አያድርገው ዝም ብለው ያዩዋት ነበር።

ከሁለት ሺህ አመት በሁዋላ „ሥልጣኔና ትምህርትን፣ ባርነትንና ድህነትን ከኢትዮጵያ አጠፋለሁ „ (በዚህ መፈክር ነው ሌሎቹ የአፍሪካ ግዛቶች የተያዙት በእንደዚህ ዓይነቱ ጥሪ ነው አሁንም አንድ አገር የሚወረረው …) ይህን ለኢትዮጵያ አመጣለሁ ብላ

Page 23: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

23ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

በአለፈው ክፍለ-ዘመን ጣሊያን ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው። ይህንንም “የሮም ሥልጣኔ አዋጅ” ሕዝቡ አጨብጭቦ እንዳይቀበል እንቅፋት የሆነውን ንጉሥ „በብረት ቅርጫት አሥሬ ማን እንደሆንኩ አሳያለሁ „ የሚለውም ዛቻ – የዶሮውን የሮም በላይነትን በተዘዋዋሪ ለአውሮፓያኖች ዞር ብለው እንዲያስታውሱት- በተዘዋዋሪ መልዕክቱን እንዲያዳምጡት የተደረገው።

ምኒልክንና ጣይቱን መኮንንና ጎበናን፣ገበየሁንና መንገሻን፣ዳርጌንና ወሌን አሉላንና ባልቻ አባ ነፍሶን እና…(ጀግኖቹ

ቆጥሮ መጨረስ አይቻልም) በብረት ቀፎ ወደ ሮማ አሥሮ ለመውሰድ የተመኙት የጣሊያን ጂኔራሎች በአንድ ቀን በተካሄደው ጦርነት አድዋ ላይ እነሱም ከነሕልማቸው ጭምር ተንኮታኩተው እንዲወድቁ የተደረገው።

ያ ምኒልክን በብረት ሰንሰለት ያለው ጂኔራልም ወታደሮቹን ሜዳ ላይ በትኖ የራሱን ነፍስ ለማዳን ሸሽቶ አሥመራ ገብቶአል።ይህ ሰው ሸሸ ተብሎም የሁዋላ ሁዋላ የጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርዱን የተቀበለው።

የምኒልክ ጉዞ በተለያዩ እቅጣጫዎች

እነዚህ ሁሉ ፈጠራ ሳይሆኑ – የታሪክ ጸ ሓ ፊ ዎ ች ተስማምተው እንደሚሉት- በ ደ ን ብ የ ተ መ ዘ ገ በ ታሪክ ነው። እነዴት እነደነበር ብሎ መለስ ብሎ መመልከቱም ለማንም ሰው ጠቃሚ ነው።

አንደኛው እሰከ አሁን ድረሰ በብዙ ጻሓፊዎች ዘንድ ትልቅ አተኩሮ ያልተሰጠው የምኒልክ እና የምኒልክ አማካሪዎች በዚያን ዘመን -ይህን በደንብ አላምጦ መዋጥ ያስፈልጋል- ለፕሬስ የሰጡትን ትልቅ ሚና እንደገና መመልከት ጠቃሚ ስለሆነ ጥሩ ነው።

ስለመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጋዜጣ ስለ አእምሮ ምስረታ እይደለም አሁን ወደ መጨረሻው ላይ የምናነሳው። ከዚያም በፊት ስለነበሩት በብራናና እና በበሬ ግንባር ላይ ስለ ሚጻፉት፣እነሱንም ስለሚመዘግቡት ጸሓፊ ትዕዛዞችና ካህናት ጉዳይ እነሱም ስለ ነበራቸው „የአመለካከት ነጻነትና አቀራረባቸው ስልት“ አይደለም አሁን ወደመጨረሻው ላይ ለማንሳት የተፈለገው።

የንጉሠ-ነገሥቱን የጦር ሠፈር ስንመለከተው (ስለ ጣሊያኖቹ መንደር ሌላ ጊዜ እናነሳለን) ምኒልክ „እኔ ብቻ አውቃለሁ እናንተ ግን ዝም ብላችሁ አርፋችሁ ትዕዛዜን ተቀበሉ“ የሚሉ መሪ እንዳልነበሩ አንረዳለን።

ሰውዬው „ምክርን“ የሚመርጡ ለምክር ትልቅ ቦታ የሚሰጡ ብዙ ከመናገር የሰውን ሓሳብ የሚያደምጡ፣አዳዲስ ሓሳቦችን

Page 24: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

24ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

የሚያስተናግዱ የሚያመዛዝኑና ከዚያም በተገኘው አዲስ አመላካከትና አስተሳሰብ ከዚያ ተነስተው „ፍርድ“ መስጠትን የሚያስቀድሙ ናቸው። የሚያስቸኩል የሚያንቀዠቅዥ ነገር ስለሌም እንደገና አሰላስሎ ለመመልከት ነገርን ማሳደር የሚመርጡም መሪ ናቸው።

በአንድ በኩል ይህ ነው ችሎታቸው የአገሪቱን መሣፍንትና መኳንንቶች፣የጦር አለቆችንና ካህናትን ሰፊ ዕውቀት ያላቸውን የአገሪቱን ሊቃውንቶችንና ሊቀ-ሊቃውንቶችን፣ወይዛዝራትና የቤት እመቤቶች ሳይቀሩ ፣ወይ በቡድን ወይም ደግሞ ተራ በተራ በነፍስ ወከፍ እየጠሩ የሚሰነዘሩትን ሓሳቦች እያዳመጡ መላ የሚመቱት ጥሩ ንጉሥ አድርጎአቸዋል።

በሌላ በኩል ከፈረንሣይና ከሩሲያ ከአርመንና ከግሪክ ከጀርመንና ከኦስተሪያ -ከሲዊስ የመጡ መልእክተኞች ይሁኑ፣ ነጋዴ መንገደኞች ወይም ተቀጥረው የሚሰሩ አማካሪዎችን እየጋበዙ የእነሱንም አመለካከት የሚያዳምጡ ሰው ወጥቶአቸዋል።ሌላው ቀርቶ ከእራሳቸው ከጣሊያኖቹ ጋርም እሰከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ይነጋገሩ ነበር።

አዚያው ላይ እያወቁ መሣፍንቱንና መኳንንቱን በእሳቸው ላይ ለማሸፈት በድብቅ ከራሶችና ደጃዝማቾቻቸው ጋር

የሚገናኙትን ባለ-ሙያዎቻቸውን „…እስቲ ጣሊያኖቹ ምን እንደሚሉ አዳምጡአቸው“ ይሉም ነበር።

“ለመኮንን ምኒልክን ከከዱ ሐረርን በንጉሥነት፣ለሚካኤል ወሎን ለዳርጌ ሸዋን ለተክለ ሃይማኖት ሰሜንና በጌምደርን ለመንገሻ ደግሞ የንጉሠ-ነገሥት ዘውዱን እንሰጣችሁዋለን…” ብለው እንደሸነገሉአቸው እንደሚሸነግሉአቸው ምኒልክ እያውቁ

“በርቱ አዳምጡ ይሉአቸው” ነበር።

ቢጨንቃቸው ጣሊያኖቹ አንድ ቀን ወጣቱን የአውሮፓ ተማሪ የራስ ዳርጌን ልጅ ፣ልጅ ጉግሣን ከትምህርት ቤት ጠልፈው እሱን ለማንገሥ ወደ አደዋ አምጥተው ጦሩን ለመበተን የማይሆን ሙከራ አድርገዋል። ይህንንም የምኒልክ የጦር ሠፈር በደንብ ያውቀዋል።

የምኒልክ ችሎት አስቦበት (ነገር እናሳጥር) ጣሊያን ከምሽጉ አውጥቶ አውላላ ሜዳ ላይ ለመምታትና ለመቅጣት ሁለት ምሥጢር የያዙ “መሰረተ ቢስ ወሬዎችን” በጥንቃቄ የጣሊያን ጆሮዎች እንዲገቡ አድርገዋል።

አንደኛው ንጉሥ ምኒልክ ከአገራቸው ከወጡ በሁዋላ በረጅሙ አድካሚ ጉዞ በየዱሩና በየገደሉ መንከራተታቸው “በጠና ክፉኛ ታመዋል። ራስ ወሌም ሳይታሰብ በድንገት ሞተው ከዚህች ዓለም ሕይወታቸው አልፎአል” የሚል ሲሆን “ወታደሩም የኢትዮጵያ ዘማች ጦር” -ያኔ በያለበት ስንቅና ቀለብ በጎተራ የትም አልተቀመጠም- “የሚበላው አጥቶ ረሃብ ገርፎት ለዝርፊያ በሁሉም አቅጣጫ ወጥቶ ተበትናአል። ስለዚህ ጊዜው አሁን ነው..” የሚለው አጓጊ ዜና ይጨመርበታል።

በአናቱ „ክረምቱ ሳይገባ ወንዙ ሳይሞላ

Page 25: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

25ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ወደቤታቸውና ወደግዛታቸው መመለስ የሚፈልጉ መሣፍንቶች ምኒልክን ጥለው ከድል አድራጊው ከሮማ መንግሥት ጋር አብረው ለመቆምና አብረው የበላይነቱን ተቀብለው ለመሥራት ስለአሰቡ ጦርነቱን እባካችሁ ቶሎ ክፈቱና ገላግሉን እኛም ዞር ብለን ከእናንተ ጋር ተደባልቀን የምንልክን ጦር ብዙ ደም ሳይፈስ ከውስጥ ሆነን እናንተ እየገፋችሁ ስትመጡ እንበትነዋለን….“ የሚል “ዕውነተኛ ” መልዕክት የያዙ ሁለት መልእክተኞች በስውር ወደ ጣሊያን ምሽግ (በመሣፍንቱ ስም) በመላክ ” አዲሱን ሤራ ፍላጎታቸውን ” ይገልጹላቸዋል።

ሦስት ቀን በመሉ በረሃብ ተጠብሶ አንዲት ጠባቂ የሌላት ትንሽ ጠቦት በግ እንዳገኘ ጅብ የጦሩ አዣዥ ጂኔራል ባራቲየር ዘሎ የዚህን ወሬ ቀንድ ይነክስና ለወራት የመሸገበትን ካምፕ ጥሎ ወደ አደዋ ሜዳ ይወርዳል።

“ሤራው ” ይሰራል። እዚያም አንዱ እንዳለው „…አፈር ድሜውን” እሱ ለጥቂት እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲያመልጥ „እሱ የሚመራው ጦር ይበላል።“

ይህ ዜናም ዓለምን በአንዴ ያዳርሳል።

በጣሊያኖች ጥበብና በእነሱ በንቀት ላይ በተመሰረተው ብልሃትና ዘዴ ይህ -በድል አድራጊው በጥቁር አፍሪካ ጦር የመመታታቸው ዜና- ዓለምን በምንም ዓይነት አያዳርስም ብለው እነሱ ገምተው ነበር።

ግን ለዚህ-ይህ ነው የመዝጊያችን ነጥብ- ኢትዮጵያኖች አውጥተው አውርደው እነሱም እንደ አቅማቸው ደግሰው የሚከተለውን መልስ አዘጋጅተው ጠብቀው ነበር።

እሱም በዘመናዊ አነጋገር የሓሳብና የሥነ ልቦና ጦር የሚባለውን ስም ያተረፈው መንገድ ነበር።

ስለዚህ ነገር በሰፊው ተጠቅሶ ባለመጻፉ አሁን ይህን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያከታተሉ ሰዎች አዲስ ይመስላቸዋል እንጂ ጋዜጠኛው ጳውሎስ ኞኞ እግዚአብሔር ነፍሱን ይማረውና በዘመኑ ተናዶ አንስቶታል።

ለማስታወስ።

የአደዋን ዘመቻ ለማክሽፍ አጤ ምኒልክ ሦስት አብይ እርምጃዎችን የሁዋላ ሁዋላ የማይቀር ነገር ነው ብለው – ይህም ለአገሪቱም ለኢትዮጵያ፣ ለእሳቸውም በታሪክ ፊት የሚጠየቁበት ስለሆነ መጪውን ሁኔታም ተረድተው፣(ወጣ ወረደ ለማንም ሰው ቢሆን የመኖርና የአለመኖር ጥያቄም ስለሆነ -ምናልባትም ነገሥታቱ ሲነግሱና ቅባ ቅዱሱን ተቀብተው ዘውዱን ሲደፉ በጆሮአቸው ካህናቶቹ አንድ ነገር ተናግረዋቸው ሊሆን ይችላል…ምን ይታወቃል ?- ወይም የፖለቲካ ችሎታ ?… ሌላ ጊዜ ግን በእርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ እንመለስበታለን ) እሳቸው „ አጤ ምኒልክ እምዬ ምኒልክ“ ወስደዋል።

አንደኛው -ይህ ነው ምኒልክን ከቴዎድሮስም ሆነ ከዮሐንስም የሚለያቸው አንድ ነጥብ- „በይገባኝል ጥያቄ በየአለበት የሚበጣበጡትን መሣፍንቶች አንድ ሳላደርግና እነሱን ሳላሰባስብ ጦርነት ማንም ይምጣ ማን ከፍቼ ላሸንፍ አልችልም „ ብለው በማሰባቸውና ለዚያም መፍትሔ በመፈለጋቸው ነው።

ለዚህም ነው ፣በእርግጥም በምኒልክ የግዛት ዘመን በእሳቸው ሥር „….ጦር አንስቶ የተዋጋቸውንም አንከባክበው ቁስሉንም አክመው አብረው በልተውና ጠጥተው ሾመው ሸልመው…ግዛቱን ወይ ለእሱ ወይም

Page 26: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

26ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ለልጁ ሰጥተው…እንደ ልማዱና ባህሉ እንደ ወጉና ሥርዓቱ እንዲያስተዳድር ግን ደግሞ መልሶ ከድቶ ከሌላው ጋር ቆሞ እንፈነግጦ እንዳይወጋቸው አስጠንቅቀው“ ከሁሉም ጋር ተከባብረውና ተቻችለው ኑረዋል።

በዚህም ብልሃት የውጭ ጠላትን ተንኮል አክሽፈው መያዣና መጨበጫ አሳጥተዋል።

ሁለተኛው የምኒልክ ብልሃት እንደ ሚቀጥለው እንደዚህ ነው። ሌላው የአውሮፓ ኃያላን መንግሥታት ከጣሊያን ተሻርኮ በቡድን ወይም በነጠላ እንዳይወጋቸው ከጦርነቱ በፈት ሳይሆን ከጦርነቱ በሁዋላም „የጣሊያን ምርኮኞችን ሲከባከቡ፣የሞቱትን ሲቀብሩ፣ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር በደብዳቤ ለመገናኘት የሚፈልጉትን….እኔ ይህንና ያንን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ….“እያሉ ለተለያዩ የአውሮፓ መንግሥታትን ለቫቲካን ጳጳሳት ጭምር የሚጽፉትን ደብዳቤ ዛሬ ስንመለከተው በዲፕሎማቲክ የአሰራር ዘዴ ንጉሡ የሚጫወቱትን ጨዋታ -ይህ ደግሞ ብልጣብልጥነት ሳይሆን ከልብ የመነጨ የፖለቲካ እርምጃ (መቶ አመት ይበልጠዋል)ይህን መመልከቱ በጣም እጅግ በጣም የሚደነቅ ነው።

ሦስተኛው እኛን አሁን በነጻ የኢንፎርሜሽን ልውውጥ ዘመን ያደግነውና ያሳለፍነውን ትውልድ የሚገርምና የሚያስደንቅ የአባቶቻችን ሥራ ነው።

ምንድነው ያደረጉት?

ጦር ሜዳ የሆነውን ነገር፣…የተገኘውን ድል፣…ከጣሊያን ጄናራሎች ጋር በፍጥጫው ጊዜና ሰዓት የተደረገውን ንግግር ሳይቀር፣…. ድክመታቸውንና ጥንካሬአቸውን፣…ሽሽታቸውንና ውድቀታቸውን፣ስለተማረኩት ወታደሮች፣ስለ መሣሪያ ክምችታቸውና ስንቱ በእጃቸው ላይ እንደወደቁ ሳይቀር አንድ በአንድና፣ተራ በተራ እራሳቸው አጼ ምኒልክ እና ግራዝማች ዮሴፍ በሌላ ሰው ስም በዚያ መልክ እየጻፉ ወደ አዲስ አበባ እየላኩ (ይህ ነው ችሎታቸው) እዚያ የሚገኙትን የውጭ አገር

ዲፕሎማቶችንና ተወካዮችን በጦር ሜዳ ከዚያ በተገኘ ዜና በየጊዜው እነሱን ይመግቡአቸው ነበር። „…ፊውዳል ፊውዳል ምንም የማያውቁ መሓይም ፊውዳል … የሚለው ቀባጣሪ ዛሬ ይህን ሲሰማ „ አንዱ ወዳጄ እንዳለው „ እንደተለመደው የአማራ ፈጠራ ነው ሊል ይችላል።“ ግን አይደለም። ዕውነቱ እንደሚቀጥለው ነው።

እነሱም ይህን የመሰለ ዜና የሚደርሳቸው የዓለም መንግሥታት አምባሳደሮች በተለይ የፈረንሣዩና የሩሲያው ተጠሪዎችና ዲፕሎማቶች፣ የደብዳቤውን ይዘት እየገለበጡ፣እያጣፈጡና እያሳመሩ፣ወደ ፓሪስና ወደ ሞስኮ ወደ ለንደንና ወደ ጣሊያን ጭምር ለጋዜጣ አሳታሚዎች ይልኩ ነበር።

Page 27: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

27ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

በዚህ ነው ጣሊያኖች እዚያ „….እየተለበለቡና እየተቀጡ፣ጦር ሜዳ ላይ ድል እየተመቱና እየሸሹ….አሽነፍን፣እያሽነፍን ነው…ድሉ ዞሮ ዞሮ የእኛ ነው „ የሚለውን የሐሰት ወሬ በአገራቸውና በአውሮፓ ሲያናፍሱት ፣ኢትዮጵያኖች -ይህን ማን ያላሰበውን ጨዋታ እነሱ በየጊዜው በሚልኩት ዜና እየተከታተሉ ያኔ ያጋልጡት፣ያጋልጡትም የነበረው።

ይህ ነው እንግዲህ እኛን ዛሬ ቁጭ ብለን ያለፈውን ታሪክ የምንከታተለውና የምናየውን ሰዎች በመጨረሻው „…እነዚያ ምንም የማያውቁት -በነጮቹ ፕሮፓጋንዳ የተባሉት ገና መገራትና ሥልጣኔ የሚባለውን ነገር ከክርስትና ሃይማኖት ጋር ከእሱም ጭምር መማር አለባቸው የተባሉት አሕዛብና አውሬ ኢትዮጵያኖች – …“ በዘመናቸው የሰሩት ሥራ።

ምኒልክና አባቶቻችንና እናቶቻችን ጭምር አንድ ላይ ሁነው ኢትዮጵያን አመቻችተው ለሚቀጥለው ትውልድ አስተላፈዋል። ሌላው ቀርቶ የምኒልክ ሞት ኢትዮጵያን ለመያዝ ለአሰፈሰፉት ኃያላን መንግሥታት በር ይክፈታል ብለው አባቶቻችን ያንን ሰዓትና ጊዜ ለእኛ እና ለአገሪቱ ደህንነት ሲሉ ደብቀዋል።

ምኒልክ አዲስ አስተዳደርን፣ ዘመናዊ ትምህርትን፣ጥበብና ዕውቀትን፣ሕክምናና ቴክኒክን፣በተለይ ከቅኝ ግዛት እኛን አድነው ወደ ሃያኛው ክፍለ ዘመን አስገብተዋል።

እርግጥ ኤርትራን በነበረው የሚሊተርና የጊዜው ችግር -ረሃብ ነበር፣ክረምት ገብቶ ነበር፣ሁሉንም ማጣት ነበር- ንጉሡ ምኒልክ ያን አካባቢ ለማስመለስ አልቻሉም ነበር።

ኤርትራ ግን አቶ ዘውዴ ረታ እንደ ጻፉት በአጼ ኃይለ ሥላሴ ብርታት በኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጥረት፣በዓለም አቀፉ ውሳኔ ተመልሳ ከእናት አገሩዋ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና

“ተዋህዳለች።” ተመልሳም ይህች አገር የዛሬ …አመት ተገንጥላለች።ተገንጥላም የአንድ ሰው አምባገነን መዳፍ ውስጥ- በዚህ ላይ ስምምነት አለ – ይህቺ አገር ገብታለች። „….ነጻነት ወይስ ባርነት“-ጥያቄው ያኔም አሁንም እንዳለ ነው።

ዳግማዊ ምኒልክ „ባርንትን አጥፍቶ እኛን ከነጮች ባርነት አድኖናል።“

ጊዜው አሁን ከዚያ „ከየሃያኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ ዕብደት“ በሁዋላ „የሣልሳዊ ምኒልክ ጊዜ ነው።“

እሱ ደግሞ „ዘውድ የደፋ ቅባ ቅዱሱን የተቀባ የአንድ ንጉሥ ኢትዮጵያ ወይም የአንድ ድርጅት ኢትዮጵያ …“ ሳይሆን ለተወሰነ ጊዜ ብቻ እንዲያስተዳድር በሕዝብ የተመረጠ፣ ተቀባይነት ያለው አስተዳደር ማለት ነው። „ሣልሳዊ ምንልክ“ ደግሞ ፣እንሰብሰብውና ሓሳባችንን ሸብ አድርገን እንዝጋው፣ …አንተም እሱም፣እሱዋም፤ያቺም- ሕዝብ ከመረጣችሁ ያውላችሁ መንገዱ- ማንም የኢትዮጵያ ዜጋ ለአጭር ጊዜ ኃላፊነቱን የሚቀበልበት ጊዜና ዘመን ማለት ነው ።

አቶ አሰፋ ጨቦ አንድ ጊዜ ተገርመው የዛሬ ሃያ ወይም ሃያ ሁለት አመት ገደማ አገራቸውን ጥለው ወደ አሜሪካን አገር ሳይገቡ ቦን ከተማ ላይ አንድ ነገር እኚህ ሰው ….አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣አፋር፣ጉራጌ፣ሱማሌ፣ኤርትራ፣ኩናማ…ነፍጠኛ የሚባለው ፈሊጥ ያኔ በዚያ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዚህ መከፋፈል ጌጥ በነበረበት ዘመን…ሰውዬው እነደዚህ ብለው ነበር።

„…. ምኒልክ በገጽተው“ አቶ አሰፋ ጨቦ “… እኔን ይመስላል! ነፍጠኛ! ነፍጠኛ አማራ …አገር ለቆ ይውጣ… የሚለውን ቃል አልቀበለውም ” ብለው ሓሳባቸውን ሰንዝረው ነበር።

ዕውነትም ምኒልክ ሁላችንንም ኢትዮጵያኖችን – ትርጉሙም ጥቁር ማለት ነው- ጥቁር ሕዝቦችን በሙሉ ይመስላል።ይወክላል።ለእነሱም

Page 28: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

28ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

መብት መከበር በተግባር ተዋግቶአል።

በ ዘሥራ ዘጠነኛውና በሃያኛው ክፍለ-ዘመን በሰላም አልጋው ላይ የአረፈ የኢትዮጵያ ንጉሥ ማን ነው ቢባል ምኒልክ ብቻ ነው።

ምን ይታወቃል በሰላማዊ ምርጫ ዘመን ፣ እኛም አንድ ቀን አራትና አምስት ጠቅላይ ሚኒስትሮቻችንን ከእነ ፕሬዚዳንቶቻችን (የክልል አይደለም) አብረን አቁመን አሰልፍን አንድ ቀን -እንደ አሜሪካና እንደ ጀርመን እንደ እንግሊዝና ፈረንሣይ እኛም እነጋብዛቸው ይሆናአል። እዚያ ላይ ለመድረስ ግን የብርሃን ፍልስፍናን ኢንላይትሜንትን አኝኮ መዋጥ ያስፈልጋል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

Page 29: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

29ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ምኒልክ- በጎታ/Gotha

እንደ ዳግማዊ ምኒልክ በዓለም የተደነቀ እንደ እሳቸው ደግሞ በአንዳንድ የአገሪቱ ልጆች ዘንድ የተናቀ የአፍሪካ ንጉሥ የለም።ደፍረው -ይህ ይገርማል- ሐውልታቸው እንዲፈርስ አዲስ አበባ ላይ አንዳንዶቹ ጠይቀዋል። ብዙዎቹም ይህ የመታሰቢያ ሐውልቱ እንዳይነካ ታግለዋል። ለምልክትም ቀለም ጥቂቶቹ ቀብተዋል።በጀርመን አገር ጎታ በሚባለው ከተማ የመቶኛ የሙት አመታቸውን ምክንያት በማድረግና እሱንም በማስታወስ አሥራ ስድስተኛ „የውርሰ ኢትዮጵያ የሳይንስና የምርምር ጥናት ማህበር“ አመታዊ ጉባዔውን እዚያ አካሂዶ በንጉሠ ነገሥቱ በአጼ ምኒልክ ሥራና ገድላቸው ላይ ሦስት ቀን የፈጀ አተኩሮ ለእሳቸው ሰብሰባው ሰጥቶአል። ጎታ ታሪካዊ ከተማ ናት።እዚህ ነው የጀርመኑ የሲሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ የመጀመሪያውን የድርጅቱን ፕሮግራም ነድፎ ለጀርመን ሕዝብ ያስተዋወቀው።እዚህ ነው ከአምስት መቶ አመት በፊት እነ ዶክትር ማርቲን ሉተር የፕሮቴስታንትን ሃይማኖት እንቅስቃሴ በዘመናቸው ለኩሰው ይህን እምነት ሊያስፋፉ፣ሊያራምዱት የቻሉት።እዚሁ ነው ከሦስት መቶ ሃምሣ አመት በፊት ኢትዮጵያዊው አባ ጎርጎርዮስ እና የጀርመኑ ተወላጅ ሒዮብ ሉዶልፍ በቤተ መንግሥቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደገና የተገናኙት።

Page 30: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

30ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

እንግዲህ እዚሁ የቤተ-መንግሥቱ አንደኛውና ትልቁ አዳራሽ- የመስተዋትአዳራሽ ውስጥ- ነው ከጥቅምት 11 እሰከ ጥቅምት 13 2013 ዓ.ም (እአአ) „ውርሰ ኢትዮጵያ“ የተባለው ድርጅት አሥራ ስድስተኛውን አመታዊ ጉባዔውን ጠርቶ፣ንጉሠ ነገሥቱን አጼ ምኒልክን ከሞቱ ከአንድ መቶ አመት በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የእኝህን ትልቅ ሰው ሥራና ገድል ያስታወሰው።ጉባዔውን የከፈቱት የከተማው ከንቲባ ሚስተር ክኑት ክሮይች እና የውርሰ ኢትዮጵያ ድርጅት የቦርዱ ሊቀመንበር ልጅ ዶ/ር አስፋ ወሰን አሥራተ ሁለቱም አንድ ላይ ሁነው እየተፈራረቁ ተራ በተራ በአደረጉት ረጅም ንግግራቸው ነው።ወደፊት እንዲታሰብበትም ስለ የእህት ከተማዎች ጉዳይም እዚያው አብሮ ተያይዞ በልጅ ዶ/ር አስፋ ወሰን አሥራተ ይህ ሐሳብ ለከንቲባው ቀርቦ ቤቱ ውስጥ ጉዳዩ ተሰምቶአል። ጎንደርና ጎታ እህትማማቾች ቢሆኑ ከጊዜውና ከታሪኩም ጋር አብሮ ስለሚሄድ መልካም ነው ተብሎአል። ተራ በተራ ከዚያ በሁዋላ፣ አንድ በአንድ - ተናጋሪ ምሁራኖቹ አትራኖሱንና መድረኩን፣ዘመናዊ መግለጫ ቢመሩንም እየተቀባበሉ፣ለረጅም አመታት ብቻቸውን ተቀምጠው ከአካሄዱት ጥናቶችና ምርምሮች ለእኛ - መገመት እንደሚቻለው- ሁሉንም ሳይሆን „ቀንጥበው!“ በትንሹም ከዚያ ላይ „ቦጭቀው“ ማለት እንችላልን“…ስለ አጼ ምኒልክ ገድልና ሥራ፣ ትልቅነትም ሦስት ቀን በፈጀው ስብሰባ ላይ ምሁሮቹ ለተሳታፊ እንግዶቹ ፣ በጭብጭባ እየታጀቡ -ከደረሱበት ጥናቶቻቸው ጋር እኛን አስተዋዉቀዋል።ረፈድ ሲል በስብሰባው ላይ ለመገኘት ያልቻሉት የታሪክ ጸሓፊውና የምሁሩ የፕሮፌሰር ባይሩ ተፍላ አጭር ጥናት ቤቱ ውስጥ ተነቦአል።ጳውሎስ ኞኞን ጋዜጠኛውን እያመሰገኑ (ከላኩት ደብዳቤ ላይ እንደተሰማው) የአሜሪካኑን ጸሓፊ ሚስተር ቡርጋርድን እየጠቀሱ „…እንደ ምኒልክ በደጋፊዎቻቸው የሚደነቁ የዚያኑ ያህል ደግሞ በተቃዋሚዎቻቸው ዘንድ የሚናቁና -አሜሪካኑ እንደ አለው- እንደ እሳቸው የሚከሰሱ መሪ የለም „ ብሎ ያስቀመጠውን አመለካከት በላኩት ደብዳቤ ላይ ይህን ቃል አስቀምጠው ወደ ተነሱበት አርዕስት ፕሮፌሰር ባይሩ ዘልቀወል።ቀደም ሲል ሌላው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴም -በአቀረቡት ጥናት ላይ ተመሣሣይ ነገር በኢትዮጵያ እንደተመለከቱ እሳቸውም ወርወር አድረገው ለመናገር በተነሱበት አርዕስት ላይ ወደፊት በተራቸው ገፍተዋል። „አባቶቻችን በጋራ አንድ ላይ ተነስተው አደዋ ላይ ጣሊያንን ድል ያደረጉበትንና ያሸነፉበትን መቶኛ አመት አንድ ላይ በጋራ ለማክበር እንኳን፣ መግባባት ከአንዳንዶቹ ጋር እንደ አልተቻለም“ ምሁሩ አስታውሰው „…ምኒልክ ኮትኩተው እኚህ ንጉሥ አሳድገው ወደ ከፍተኛ የሥልጣን ደረጃ ላይ ስለአደረሱአቸው፣ የዝቅተኛው መደብ ልጆች „ ፕሮፌሰር ባህሩ በአቀረቡት ጥናት ስለእነሱ በተለይ ስለ ፊታውራሪ ሐብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ የጦር ሚኒስትሩ ማተቱን መርጠዋል። እግረ መንገዳቸውንም ከብዙ በጥቂቱ ስለ ራስ ጎበናም ምሁሩ ጠቅሰዋል። ሁለቱም በኢትዮጵያ ታሪክና በዘመናዊ ኢትዮጵያ አስተዳደር ምሥረታ ትልቅ ሚና እንደተጫወቱ ይህን ማን የሚያውቀው ነው።

Page 31: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

31ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ፊታውራር ሐብተ ጊዮርጊስ ግን በሥልጣን ሽግግሩ ዘመን ከምኒልክ ወደ ልጅ ኢያሱ፣ ከእያሱ ወደ ዘውዲቱና ወደ አጼ ኃይለሥላሴ በሰገሌም ጦርነት ጊዜ እኝህ ሰው የተጫወቱት ሚና በፕሮፌሰሩ ጥሩ ሁኖ ቀርቦአል። መለስ ብለውም „እንደዚህ ዓይነቱ አሠራር - ብልህንና አስተዋይን ሰው ማቅረብ፣ ነገር የገባውንና ነገርን የሚመለከት ሰው መርጦ ወስዶ ኮትኩቶ ለከፍተኛ ኃላፊነትና ማዕርግ ማድረስ …በድሮም የኢትዮጵያ ነገሥታቶች ዘንድ ያለ የቆየ ባህል ነው።“ ብለዋል።ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አደርገው ያቆዩትም እሴቶች እንደዚህ ዓይነት ተመክሮዎች ናቸው።ስለ ምኒልክ ትልቅነትና ስለ ምኒልክ ግሩም የረቀቀ የፖለቲካ ጥበብ ፣ ስለ አመራር ብልሃታቸውና ሚዛናዊ ፍርዳቸው፣ ስለ አመለካከት ስልታቸውና ስለ የፖለቲካ እርምጃቸው፣ የተጠነቀቀም፣ ረጋ ያለ አካሄዳቸው -መቼም ይህ ነው የማይባል ንግግር ያደረጉት የጀርመኑ የፖለቲካ ሳይንስ አስተማሪ ፕሮፌሰር ራይነር ቴትዝላፍ የሚባሉ ሰው ናቸው።„ከፓን አፍሪካኒዝም ማለት ከመላው የጥቁሮች ራዕያና ነጻ ዓለም ኑሮና ሕይወት ጋር አያይዘው“ ሁሉንም ተናጋሪ ቀድመው በጥወቱ ሰዓት ላይ ደህና አድርገው በአቀረቡት ጽሁፋቸው ላይ የምኒልክን ጉዞ መምህሩ አስቀምጠዋል።

„…ምኒልክ ለጥቁር አፍሪካ ምሁሮች ለነዚያ በቅኝ ገዢዎች የበላይነት መከራቸውን ያዩ፣ የተጨቆኑ ጥቁር ሕዝቦች፣ እነሱ ምሁሮቹ አንድ ቀን ተነስተን እናመጣለን ብለው የሚመኙትን ሓሳብ በድርጊትና በተግባር ንጉሡ በሥራ ላይ አውለው በማየታቸው እጅግ አድርገው ሁሉም በምኒልክ ሥራ ተደንቀዋል። እንዲያውም እንግሊዝ አገር በሺህ ዘጠኝ መቶ አመተ ምህረት መጀመሪያ ላይ በተካሄደው የመጀመሪያው የጥቁር ዘሮች የፓን አፍሪካ ኮንግሬስ ላይም የበላይ ጠባቂ መሪና የስብሰባው ሊቀመንበር አጤ ምኒልክን እንዲሆኑላቸው ጠይቀውም ነበር። ንጉሡ ግን“ ፕሮፌሰሩ እንዳሉት „ሌላ ጋላፊነትና ሌላም የመንግሥት ሥራ ስለነበራቸው በስብሰባው ላይ ተገኝተው የፓን አፍሪካን ጥቁሮች ጥያቄ ሊያሟሉ አልቻሉም።“ምኒልክና ጥንታዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለተበደሉትና በጭቆና ሥር ለሚማቅቁት የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ትልቅ አስተዋጾ እንደ አደረጉ ዘርዝረዋል። „ኢትዮጵያን ገንብተው፣አንድ አድርገው፣አመቻችተው ለቀጣዩ ትውልድ አሳልፈው እንደሄዱም …“ አትተዋል።„ምኒልክ ግን ብቻውን ሳይሆን ከሌሎቹ የአገሪቱ መሣፍንትና መኳንንቶች፣ ካህናትና የሃይማኖት አባቶች፣ ከዝቅተኛው ክፍል ከመጡ ከእነ ራስ ጎበናና ከእነ ፊታውራሪ ሐብተ ጊዮርጊስ፣ ከውጭ አማካሪዎቻቸውም ጋር ከእነ አልፍሬድ ኢልግ -አንዳዶቹን ለመጥቀስ እየተማካከሩ ኢትዮጵያን በጋራ ከሁሉም ጋር እንደገነቡና ወድቆ የነበረውን የኢትጵያዊነት መንፈስንም እንደገና እንዳደሱ፣ አድሰውም በዓለም ላይ ተገቢውን ቦታ እንዲይዝም እንዳደረጉ“…የተቀሩት ጠቁመዋል።

„ምኒልክን ምኒልክ እንዲሆን“ ባህሪውንም አመለካከቱንም ረጋ ያለ የፖለቲካ አካሄዱንም ጠርቦ ሞርዶ አስተካክሎ እዚያ ያደረሰውን ነገር „ከሞላ ጎደል „ ለማስረዳት መድረኩን የተረከቡት ዶ/ር አህመድ ሐሰን ናቸው።

Page 32: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

32ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

አራት ጣቢያዎችን ጠቅሰውልናል።

አንደኛው በልጅነት ዕድሜአቸው በጠምቄ ገዳም ያሳለፉት ጊዜና ከአስተማሪያቸው ከአባ ሸዋ ዘርፍ ያገኙት ተመክሮና ትምህርት ነው። ሁለተኛው ተማርከው በአጼ ቴዎድሮስ ችሎት እዚያ ላይ ያሳለፉት ጊዜና የቁም እሥር ዘመን ነው።ሦስተኛው አብሮአቸው ታሥረው የነበሩት የሸዋ መሣፍንቶችና መኳንንቶች „ምክር ነው።“ የመጨረሻው ትምህርት መቅደላ ላይ የተዋወቁአቸው የአውሮፓ „ምሁሮች“ ናቸው። ምኒልክ በእነዚህና በሌሎች ተመክሮች የኢትዮጵያ ነጻነት ጠብቆና አስከብሮ ለቀጣዩ ትውልድ አስተላልፎ ሄዶአል። „ተማረ፣አወቀ፣ነገር ገብቶታል“ የተባለው ትውልድ ደግሞ እንደምናውቀው „…በተለያዩ ፍልስፍናዎችና የአምባገነን ፖለቲካ አይዶኦሎጂዎች“ አብዶ፣ ቀላሉን …የሰበአዊና የዲሞክራሲዊ መብቶች መከበርን እንኳን፣ የነጻ-ሕብረተሰብን መመሥረትን፣ የግል ሐብትን፣ ነጻ ስብሰባና ነጻ ፕሬስን ሲቃወም ይህን በ21 ኛው ክፍለ ዘመን በአዲስ አበባና በአሥመራ ማየቱና መሰማቱ ምንድነው። በምኒልክ ላይ የትችት ናዳቸውን የሚወረውሩ ከአሉ፣ እራሳቸው በመጀመሪያ ኢትዮጵያን ከሚበትነው ከአምባገነን ከቴታሊቴሪያን አስተሳሰብ ማለቀቅ ይኖርባቸዋል። እንደዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ግን - ንጉሣዊ አገዛዝን ቀደም ሲል ፣ፈሺዝምን፣ ከእሱም ጋር ፍልስፍናው የተወለደውም እዚህ ነው- ኮምንዝምንም በደንብ በሚያውቀው በጀርመኑ አገር ስብሰባ ላይ እንደዚህ ዓይነቱ ትችት አልተሰማም።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

Page 33: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

33ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

አፍሪቃ! እንዴት ሰነበተች ?

ከኔልሰን ማንዴላ

ከዴሞክራቱ ጋር !መቼም ስለዚህ ሰው በአለፉት ሁለትና ሦስት፣…አራትና አምስት ቀናት፣ ሌላው ቀርቶ በአንድ ቀን ብቻ በዓለም ዙሪያ ታትመው የወጡትን ዕለታዊ ጋዜጣዎች እነሱን ብቻ አንድ ሰው ጠርዞ ቢያወጣው ረጅምና ብዙ ገጽ የያዘ ጥሩ መጽሓፍ ሊወጣው ይችላል።

ይህ ከሆነ ለምን አሁን እንደገና ስለ ኔልሰን ማንዴላ?

የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች አንዲት ጋዜጠኛ ተገርማ ከዚያ ሁና እንደዘገበቺው ስብሰባቸውን አቁመው - ይህ የትም አልታየም የትም አልተደረገም እሱዋም እንደዚህ ዓይነቱ ክብር የትም አልተሰማም ትላለች- የሕሊና ጸሎት መሞታቸው እንደተሰማ እነሱ ብድግ ብለው አድርገዋል።

Page 34: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

34ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ከቶኪዮ እስከ ኦስሎ፣ከብራዚል እስከ ቻይና ከሎንዶን እስከ ሞስኮ፣ ከዋሽንግተን እስከ ሓቫና …አፍሪካማ አንዲት ቅንጣት ታህል የማንዴላን ሓሳብና መንፈስ የማይከተሉ መሪዎች እነሱም ቢሆኑ - ብድግ ብለው አጠቃላይ የሆነውን መግለጫቸውን፣ ከእነ ባራክ ኦባማ ጋር ተጋርተው ሁሉም ሰጥተዋል።

የሚገርመው ትላልቅ የዓለም የዜና አውታሮችና የቴሌቪዢን ጣቢያዎች ሁሉም ለሰውዬው ዕረፍት ትልቅ ቦታ ስጥተው ቀኑን በመሉ መኔልሰን ማንዴላ ታሪክና ሥራ ላይ ተመላልሰውበታል።

ምንድነው ነገሩ? ማንዴላን ከሌሎቹ ከምናውቃቸው ከእነ ሮበርት ሙጋቤ እና ከእነ አልባሽር፣ ከእነ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እና ከእነ መለሰ ዜናዊ፣ ከእነእሳያስና ከእነሙባራክ፣ ከእነ ጋዳፊና ከእነ ቤን ዓሊ…ከካውንዳና ከነኡሁሩ ኬንያታ ከእነ ፖል ካጋሜና ከነካቢላ …ከፖልፖትና ከማኦ… መዘርዘሩ ይሰለቻል እሱን የሚለየው? ማንዴላን ፍጹም ልዩ የሚያደርገው? ልዩ አድርጎትስ „ዓለም“ ስለ እሱ እንደዚህ የሚያወራው?

ሰማይና ምድር ናቸው፣ ማንዴላ ሌላ ሰው፣ እነሱ ሌላ ለምንድነው ሁለት ፍጡሮችን የምታወዳድረው ? የምትሉ አላችሁ።

የለም „ማንዴላ እኮ የእነሱ ሰው ስለሆነ የእነሱ በመሆኑ ነው“ የምትሉም ሰዎች አትጠፉም።

የፈለገ ሰው ብዙ ነገር ሊጽፍ ይችላል። ብዙም በቃላት የተዋበ አስተያየቱን ስለ ማንዴላ - በሥልጣን ዘመኑ የእራሱን ሕዝብ የፈጀውም የበደለውም ሁሉ ሳይቀር ሊሰጥ ይችላል።

እኛ ደግሞ በሦስት የሰው ልጆች በዚህች ዓለም ላይ ለመኖርና ለአለመኖር በሚያስፈልጋቸው ነገሮች ላይ የተመሰረተ ሥራ በማካሄዱ ብቻ - አዚህ ሥራው ደግሞ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንደገኘ አስምረን ለማለፍ እንፈልጋልን።

እነሱም:- አንደኛ ማንዴላ በመሓላ ቃሉ ሥልጣኑን እንደተረከበ በቂም በቀል ፋንታ ይቅር ለእግዚአብሔርን፣ በጥላቻ ፋንታ ፍቅርን፣ የቀድሞ ጠላቶቹን፣ የእሥር ቤት ጠባቂ ፖሊሶቹን ሳይቀር አሳዶ በመግደል ፋንታ ጋብዞ ማነጋገርንና አብሮ መብላትን ይህ ሰው መርጦአል።

ሁለተኛው „አሸንፍኩ እኛ አሸንፈናል“ ብሎ አገሪቱን በጥቁርና በነጭ፣በክልስና በሕንድ፣በአረብና በተለያዩ ዘሮች፣ ጎሣዎች ከፋፍሎና ሰንጥቆ ደቡብ አፍሪካን እሱና ድርጅቱ ለመግዛት አልተነሳም። ይልቅስ ይህ ሰው ቀስተ ደመና በሚባለው አዲሱ

Page 35: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

35ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

ፍስፍናቸው ሁሉንም ድልድይ ሁኖ አቀራርቦ ሁሉንም ሰብስቦ እኩል የዜጋ መብት ሰጥቶ አንድ አድረጎአቸዋል።

ሦሰተኛው እንደዚሁ አፍሪካ አይታም ሰምታም የማታውቀውን ነገር አድረጎ ይህ ሰው ዓለምን አሰደንቆአል። ማንም አለጠበንጃ ወይም አለተቃውሞ፣ አለ አመጽ በገዛ ፈቃዱ ከሥልጣን በማይወርድበት ዘመን ኔልሰን ማንዴላ በገዛ ፈቃዱ- ዕድሜ ልኩን እሰከ የሞት ቀኑ ድረስ ደቡብ አፍሪካን ለገዛ ይችል ነበር- ከሥልጣኑ ወርዶአል።

እንግዲህ ይህ ሥራው ነው ሕያው አድረጎት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ለዘለዓለም የሚያቆየው።

ትንሽ ከእሱ ሥራዎች ውስጥ አንዱዋን ጫፍ ብቻ የአፍሪካ መሪዎች፣ፖለቲከኞች… ጎትተው አውጥተው እሱዋን በሥራ ቢተረጉሙ የትና የት በተደረሰ ነበር።

ይህን እንደማድረግ ማንዴላ እንደዚህ ማንዴላ የእኛ ነው ብለው ሲመጻደቁ እነሱን መስማቱ ይቀፋል።

ለመሆኑ ያኔ የት ነበርክ አንተም ሥልጣን ላይ የነበርክ ጊዜም የማንዴላን ዓይነት ሥራና አስተሳሰብ ለመከተል ምን አገደህ? ያሰኛል።

ዛሬስ አሁንስ አመለካከትህን ለመቀየር አሰራርህን ለመለወጥ ማን ከለከለህ ማንስ አገደህም ያሰኛል።

ማንዴላ ተሰናብቶአል። ትቶት የሄደው ሥራው ሕያው ነው። አስተሳሰቡም ድንቅ ነው። እንደዚህ ዓይነቱን የጥላቻ ሳይሆን የፍቅር አስተሳሰቡን ከየት አመጣው? ማን አስተማረው?

Page 37: ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4

37ለ አእምሮ፣ ህዳር 2006 ዓ ም፣ ቅጽ 2፣ ቁጥር 4