41
~ 1 ~

ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

Embed Size (px)

DESCRIPTION

ኧረ ወዴት ? (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial ፍትህ ና ፍርድ ጃንሆይና ነጻ-ዜጋ፣ ፓርቲና ዲስፕሊን ሰብዓዊ መብት/ HUMAN RIGHTS WATCH ተስፋና ዕልቂት ዓለም እንዴት ሰነበተች አፍሪካ እንዴት ሰነበተች ኪነ ጥበብና ስፖርት ዋልያዎች ሲመጡ

Citation preview

Page 1: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 1 ~

Page 2: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 2 ~

ለአእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 3

ኧረ ወዴት ? (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial

ፍትህ ና ፍርድ

o ጃንሆይና ነጻ-ዜጋ፣ ፓርቲና ዲስፕሊን

o

ሰብዓዊ መብት/ HUMAN RIGHTS WATCH

ተስፋና ዕልቂት

ዓለም እንዴት ሰነበተች

አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

ኪነ ጥበብና ስፖርት

ዋልያዎች ሲመጡ

Page 3: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 3 ~

ኧረ ወዴት ? (ርዕስ አንቀጽ/ Editorial)

Published October 30, 2013 at 225 × 225 in ኧ ረ ወዴት ? (ርዕስ አንቀጽ/Editorial)

ወዴት ወዴት ?

ወዴት ወዴት ?

በጭለማ ጉዞ እውር መሪ ሲበዛ፣ ትንሽ የምትመስል ፋኖስ ከትልቁ ብርሃን ጋር አጋናኝታ እ ፍ ፎ ይ ማለታችን እንደማይቀር እርግጠኛ ነን። ኢትዮጵያ እንደዛሬ እጆቿን ወደ ስማይ ዘርግታ የምትጮህበት ጊዜ አልነበረም። „ሀ“ ብለን „ፐ“ ማለታችን አይቀርም[i]።

ውድ አንባቢ ሆይ!

ፋኖሱን ይዘን እንደተከታተላችሁት ቀስ እያልን እየዳበስንና ተጠንቅቀን እየረገጥን „ከጨለማው ዋሻ“ ወደ ብርሃኑ ዓለም ለመውጣት ጥረት እያደረግን ነው።

እንደምናውቀው ውጅንብርና ግርግር ቀውስና መከራ ትርምስና ዝብርቅርቅ ያሉ ነገሮች በአንድ ጊዜ መጥተው በአገራችን ነግሰዋል። እንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ደግሞ አንድን ሰው ግራ ያጋቡታል። ግራ እሱን የሚያጋቡት ሰው ደግሞ የሚያዘውና የሚጨበጠውን ባለ ባላው ቅርንጫፉም ዛፍ ይጠፋና ለሁሉም ነገር፣ ለሣሩም ለቅጠሉም ለቅራቅንቦውም፣ ሜዳው አመች ሁኖ ያገኘዋል። አውቆም ሆነ ሳይታወቅ፣ ትልቅ ቦታና አተኩሮ ለእነሱም ይሰጣል።

አያድርስ እንጅ ባህር ውስጥ ገብቶ ነፍሱን ለማዳን የሚፍጨረጨር አንድ ሰው እባብ ከአየ መነደፉን ረስቶ እሱን ከመያዝ አይመለስም። …ዘንዶም ወይም አዞም በአጠገቡ ሲላወስ ከአገኘም -አያድርስ ነው- ሕይወቱን ለማደን እነሱንም ለቀም

Page 4: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 4 ~

አድርጎ ባህሩ ላይ ቢጋልባቸው ደስ ይለዋል። ቢያንስ ይመኛል። ቢያንስ ይፈልጋል። እንደዚህ የሚለውን አነጋገርና ምሳሌ አንድ ቦታ ላይ አንስተን ነበር።

አሁን በየአለበት የምንሰማቸውና የምናያቸውም ነገሮች ሁሉ ይህንኑ አነጋገር ያስታውሰናል። ግን ደግሞ እንደ አንዲት ጥርት ያለች „የፓለቲካ ፍልስፍና„ በዚህ የቀውጢ ዘመን ዓይንን የሚትከፍት ጥበብ የለችም።

ወዴት እንደምንሄድ? ምን እነደምንፈልግ? ምን ማድረግ እንዳለብን? ከምን መጠንቀቅና መቆጠብ እንደሚገባን? …በአጭሩ ረጋ ማለትን የምታስተምር ጥሩ ትምህርት ከእሱዋ ሌላ የለም።

ቀደም ሲል ስለሸንጎ አንስተናል።

ከዚያ በፊት ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ጽፈናል። ትችት እነደ ሙያ ብለን ስለ ጋዜጣ ሚና በትንሹ ጠቃቅሰን አልፈናል። …. አሁን ደግሞ ስለ ሕግና ስለ የሕግ በላይነት፣ ስለ የሰው ልጆች ሁሉ፣ አንዱ አንዱን ሳይበልጥ እኩል ስለሚጋሩት መብት አንድ አጠር መጠን ያለች “…ስለ ሦስተኛው ምሶሶ“፣ አንዲት ጽሁፍ አዘጋጅተን እንድትመለከቱት አድርገናል። አውቀን አንድ ቦታ ላይ „ጃንሆይና ነጻ ዜጋ„ የሚለውን አረፍተ ነገር አስገብተናል።

መልሱንም ትችቱንም እዚያው ውስጥ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ጽሑፍ ውስጥ ታገኛላችሁ።

ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአንድ የዞረበት አስተሳሰብ ወደ ሌላው የቀና አመለካከት፣ ከአንድ የተሳሳተ መንገድ ወደ ቀጥተኛው ቀይሮ ይህቺን ዓለም በሌላ ዓይን መመልከት አስቸጋሪና ከባድ እንደሆነ እናውቃለን።

አውጥተን አውርደን ስናየው ከኢንላይትመንት ፋኖስ፣ ከሚቀጣጠለው ጧፍ ከእሱ ሌላ ምንም መፍትሔ የለም።

በኢንላይትመኔት፣ በጸጋ ልጆች፣ ከእግዚአብሔር በአገኘነው የተፈጥሮ መብታችን (ሌሎቹ ተፈጥሮ ብቻ ይሉታል) ማንም ሰው በዚህች ዓለም ላይ እኩል ሁኖ ስለተፈጠረ፣ ማንም ሰው በሌላው ላይ ተነስቶ የበላይነቱን አሳይቶ „…እኔ ብቻ አውቅልሃለሁ ስለዚህ አንተ አርፈህ ተቀመጥ„ ብሎ መወሰን እንደማይችል እናውቃለን።

Page 5: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 5 ~

ኃይልም፣ ጠበንጃም፣ ጉልበትም፣ እኔ ብቻ የሚባለው ዕብሪትም፣ ሐብትም፣ገንዘብም የሕዝብ ድጋፍ ከሌለው ውስንና ከንቱ ነው። ሕዝብ ደግሞ የሚፈልገውን ያውቃል።

ምንድነው የሚፈልገው?

ሰው ሥራና ዳቦ፣ ቤትና የግል ሐብት፣ ... መሬትና ገንዘብ፣ ፍትህና ፍርድ፣ ያለቁጥጥርና ክትትል ነጻ-አየር ተንፍሶ መኖርን፣ ደስታና ፈንጠዚያን፣ ጡረታና እንክብካቤን … አምላኩን አመስግኖ በሰላም ተኝቶ በሰላም መነሳት ነው።

መጻፍና መመራመር የሚፈልጉ አሉ። መምረጥና መመረጥ የሚመኙም አሉ። መተቸት፣ መቃወም …. የሚሹም አሉ። …. ይህን የመሰለ ጸጋ፣ የፈለጉትን መናገር፣ የፈለጉትን ማድረግ፣ … ለገዢው መደብ ብቻ የተሰጠ ልዩ የአምላክ መብት አይደለም ።

እንደምናውቀው የሰው ልጆች ሁሉ እኩል የሚጋሩት እኩል ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው የተፈጥሮ መብታቸው ነው። ይህን መብት ደግሞ አንዱ ከአንዱ አብልጦ ለእራሱና ለዘመዶቹ ብቻ እንዳያደርገው፣ ሁሉም እኩል የሚጋሩት „ሕግ ደንግገው“ የሰለጠኑ ሰዎች አውጥተዋል። እሱም ኢትዮጵያ እራሱዋ የፈረመቺው የዓለም አቀፉ የሰበአዊ መብት አዋጅ ነው።

አሁንም የምናነሳው አርዕስት ተቀድቶ የማያልቀው የነጻ-ዜጋ ጉዳይ ነው። አንድ የሚያደርገን ነገር ቢኖር (እሱ ብቻ አይደለም) የግለሰብ ነጻነት የተፈጥሮ መብታችን ነው።

መልካም ንባብ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ዋና አዘጋጅ።

[i] ሀ – እንደ alpha – ሰ – እንደ ሰው ይሆንና – ፐ – እንደ መጨረሻው ፊደላችን ተግልብጦ ና አእምሮ ው ተዘርግቶ ይበስላል፤ ምራቁን ይውጣል!

“The order of the Ge’ez system has remained the same for roughly 3000 years. It is also of note that the determinative sign for the first syllograph Hä, which is “a person standing with both his arms raised towards the heavens” and the corresponding first syllograph, “hoi,” of Ancient Egypt, which is a pictograph of the front end of a lion, are both correlated to “the Ethiopic philosophic evocation of 68 Psalms, Verse 31of the Bible, ‘Ethiopia stretches her hands unto God.”14” (cf. Gabriella F. Scelta)

Page 6: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 6 ~

ፍትህ ና ፍርድ

Published October 20, 2013 at 944 × 709 in ፍትህ ና ፍርድ

← Previous Next →

ፍትህ ና ፍርድ

ፍትህ ና ፍርድ

አረመኔ ሲገራ

ሕግና ሥርዓት፣ ደንብና መብት

የግለሰብ መብትና መብቶቹ

እንደ ሥልጣን ደስ የሚል፣ እንደ ሥልጣን የሚያጓጓ፣ እንደ ሥልጣን የሚያባልግና እንደ እሱም የሚያሳብድ፣ አሳብዶም አንድን ሰው „አውሬ“ የሚያደርግ ነገር የለም።

Page 7: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 7 ~

ያን ለመሆን ይህን ለማድረግ ደግሞ የዚያ ሰው ሁኖ በባህሪ መፈጠርንም ይጠይቃል።

አንድ ሰው እንደምንም ብሎ ሥልጣኑን እጁ ከአስገባ ደግሞ ያ ሰው „አረመኔ“ ለመሆን ለእሱ – ምንም የሚከለክለው ነገር ስለሌለ- በሩ ክፍት ነው።

የሥልጣን ኮርቻ ላይ አንዴ ከተወጣ ደግሞ ቦታው እራሱ… አትልቀቅም፣ አትውረድም ብሎ ይገፋፋል።

ሥልጣን ያለው ሰው እንደምናውቀው በሰው ሕይወት ሞትና ሽረት ላይ ይወስናል። ይህ ሰው የፈለገውን ሴትና ከረዳ አስገድዶም ቢሆን ይጠቀልላል። ከሰለቸውም ፈቶም ያባራል። በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ቁባቶቹን ቤተ-መንግሥቱ ውስጥ ይሰበስባል።

ያገኘውን ሐብት ይወርሳል። መሬት ያግበሰብሳል። ማዕድኑን ይቆጣጠራል። ንብረት ለእራሱና ለቤተሰቡ ያፈራል። ይህ አልበቃ ከአለው ደግሞ ይቀማል። ጎረቤቱንም ወሮ የጦር ችሎታ ከአለው ያስገብራል።

እዚያ ለመድረስ እንደዚያ ለመሆን ሦስት መንገዶች አሉ።

አንደኛው ከንጉሥ ዘር መወለድን ይጠይቃል። ሁለተኛው መንገድ በጦር ኃይል፣በኩዴታም በአመጽም ሥልጣንን ነጥቆ ወስዶ እጅ ማስገባት ነው። ሦስተኛው በምርጫ ነው።

ይህኛው ሦስተኛው በምርጫ ስልጣን ላይ የወጣው ገደቡንና የሥልጣን ዘመኑን ውስን መሆኑን በደንብ ያውቃል።

ግን ደግሞ ደስ ካለው ሒትለር

እንዳደረገው ሕጉን ሽሮ ሊሽረውም ይችላል እዚያው መሰንበት ነው።

Page 8: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 8 ~

ሁለቱ እላይ የተጠቀሱት አንዴ ሥልጣን ላይ ከወጡ ዕድሜ ልካቸውን ገዝተው ለልጆቻቸው ወይም ለጓደኞቻቸው ሥልጣኑን- ሁሌ ጊዜ ግን እነሱ እንደተመኙት አይሆንም እንጂ- „አውርሰው“ ያልፋሉ።

ስለ ሥልጣን ለመረዳት፣ ስለሥልጣን ለማወቅ፣ ሥልጣን ለማን? ሥልጣን ለምን? ሥልጣን እሰከ መቼ? የሥልጣን አስፈላጊነት? ሥልጣንና ፖለቲካ? ሥልጣንና ሕዝብ? የሚባሉትን ጥያቄዎች ለማንሳትና ለመመለስ ወደ ቀድሞው ታሪክ ወደ ሕግ አመጣጥና ወደ ሕግ ትርጓሜ ወደ ፍርድ አሰጣጥና የሥልጣን ክፍፍል በአንድ አገር ውስጥ መሄድ ያስፈልጋል።

የሰው ልጆች በመጀመሪያ የተሰባሰቡትና በአንድነት የቆሙት እራሳቸውን ከአውሬና ከሌላ ቦታ መጥቶ ወግቶ ማርኮ መሬታቸውንና ንብረታቸውን ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ቀምቶ እነሱን ባሪያ አድረጎ ሊገዛቸው ከሚፈልጋቸው ኃይል ለመከላከል ነው።

አብሮ ለመኖር፣ አብረው ሲኖሩ ደግሞ አንድ ሥርዓት አንድ ሕግ እንደሚያስፈልጋቸው የሰው ልጆች ሁሉ ይህን ሰለሚረዱና ስለሚያስቡ አስፈላጊነቱን በደንብ (አንዱ ጋ ጠንከር ይላል ሌላው ጋ ለቀቅ ወይም ጠበቅ) እነሱ ያውቁታል።

ይህ ለነጮች ብቻ የተሰጠ ተሰጥኦ አይደለም።

ሰዎች ከዚያም ተነስተው እንደ ጊዜውና ዘመኑም የራሳቸውን ሥርዓት መስርተዋል። ያ ሥርዓት ደግሞ ቆሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ – ይህ የትም ቦታ የሚታይ ነው – አንድ ( የረቀቀ ይሁን አይሁን ሌላ ነገር ነው) „የመተዳደሪያ ሕግ“ ሃይማኖትም ሊሆን ይችላል፣በመጀመሪያም እሱ ነበር የሰው ልጆች የሃይማኖት አባቶች ደንግገው አውጥተዋል።

Page 9: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 9 ~

ያን ሕግ ወይም ያን ደንብ ወይ የሃይማኖት አባቱ ወይ ጠንቋዩ ወይ ጅግናው ወታደር ወይም መሪው ንጉሥ መከበሩን፣ በሥራ መተርጎሙን በጋራ ወይም በየፊና ይቆጣጠራሉ።

ሕግ ወይም ደንብ የመጣው ሕግም የተነደፈው ሕግ የተዘረጋው ሕግ በሥራ ላይ እኩል እንዲተረጎም የተደረገው ሕግንም ሁሉም እኩል እንዲያከብር የተደነገገው አንዱ ጉልበተኛ ከመካከላቸው ተነስቶ ሌላውን ባሪያው እንዳያደርገው ነው። ከዚያም አልፎ አንዱም ከእነሱ መካከል ተነስቶ „አውሬ ሁኖ“ ሌላውን „አርዶምእንዳይበላውም“ ነው።

በአጭሩ ሕግ የወጣው የጠንካራውን የአረመኔዎች ድርግት ለማጠናከር ሳይሆን የሕይወት ነገር ስለሆነ እነሱን ለመቆጣጠር ነው። ከዚህም ተገላግሎ በሰላም ከመኖር ፍላጎትም የመነጨ ነው።

ስለ ሕግና ስለ መብት ስለ ዳኝነትና ስለ ፍርድ ሲነሳ ብዙ ነገሮችን ለአየና ለቀመሰ ለአንድ ኢትዮጵያዊ እንግዲህ ብዙ ነገሮች ከተፍ ብለው ዓይኑን መተውት ትዝ ይሉታል።

አንደኛው ከዚህ ሁሉ መካከል የታወቀው የሰለሞን ፍርድ ነው።ከእሱም ጋር በአገራችን የሚታወቀው የንጉሥ ችሎት ነው።

በሁዋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍርድ ቤቶች ተቋቁመዋል። ጠበቃዎች ተምረው ወጥተዋል። የወንጀለኛ እና የፍትሓ ብሔር ሕጎች ረቀው ወጥተዋል።

ሁለተኛው ደርግ የሚባለው ፍጡር ከመሬት ተነስቶ አለፍርድ የወሰደው„አብዮታዊ እርምጃ“ የሚባለው ነገር ነው።

Page 10: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 10 ~

ሦስተኛው „ዲሲፕሊን አጎደላችሁ“ በሚለው ሳቢያ፣ በየድርጅቱና ነጻ አውጪ ነኝ እያለ በየተነሱት ኃይሎች፣ እንደዚሁ ጫካ ውስጥ በጥይት የተደበደቡ ወጣቶች ሕይወት ጉዳይ ነው።

አራተኛው አለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደዚሁ በአዋጅ የተወረሱ ቤቶች፣ መሬቶች፣ መኪናዎች፣ የባንክ ገንዘብና የግል ንብረቶች ቅሚያ ጉዳይ ነው።

አምስተኛው ከአለማዘዣ በማንም „የቀበሌ በአለሥልጣን“ የሚፈተሹ ቤቶች ሁኔታ ነው። ስድሰተኛው ጥፋታቸው ሳይመረመር አለፍርድና አለአንዳች ችሎት፣ አለጠበቃና አለ ማስረጃ እሥር ቤት ገብተው የሚማቅቁ ሰዎች ሕይወት ነው። ሰባተኛው…ለምን ጻፍክ፣ ለምን ተናገርክ፣ ለምን ተሰበሰብክ ተቸህ… ተብሎ አንድ ሰው በአገሩ እንደ አውሬ የሚታደንበት ሁኔታ ነው። ስምተኛው… ዘጠነኛው፣አሥረኛው ወዘተ እያለ ይሄዳል። አሁን ፍርድና ፍትሕ በኢትዮጵያ በአፍሪካ አለ?

ከአለስ ምን ይመስላል?

በሰለሞን ፍርድ እንጀምር።

የንጉሥ ሰለሞን ፍርድ ከእዚያ በፊት ከነበረው „…ዓይን ለዓይን ጥርስ ለጥርስ „ ከሚለው ከሓሙራቢ የፍርድ አሰጣጥ የፍርድ ፍጻሜና እርምጃ ይለያል።

በአጠቃላይ „… አትስረቅ፣ አትግደል፣ አታመንዝር፣ በሐሰት አትመስክር፣ የሰው ሐብት አትመኝ…“ከሚለውም ከሙሴ አሥርቱ ቃላት፣ ከታቦቱም ሕግጋት ይህኛው ተጨማሪ „አሥራ አንደኛ“ ስለሆነ ከእነሱም ለየት ይላል።

ያኛው የላይኛው የሙሴ ጽላት „የአኗኗር ዘይቤን“ በሰው ልጆች ዘንድ የሚደነግገው የሞራል ደንብ ነው። የኦሪት ህጎች በጥቅሉ፣ ይህን አታደርግ ያን ከአደርክ በሚሉ „በመከልከልና በቅጣት“ ላይ የተመሰረቱ ደንቦች ናቸው።

በጥበብ ላይ የተመሰረተው የሰለሞን ፍርድ ለአንድ ወገን ሳያዳላ ወይም በጭፍኑ እንደ „ሓሙራቢ ሕግም“ ነገር ሳያመዛዝን፣ ጊዜ ወስዶ ጉዳዩንና ችግሩን ጠለቅ ብሎ ሳይመረምርና ሳይመለከት „በጠፋው ጥፋት ልክ…ዓይን ከሆነ ዓይን እንዲጠፋ…“ በጥድፊያ ውሳኔ ላይ የሚደርስ ዳኝነት አይደለም።

የሰለሞን ፍርድ „ዕውነትን“ ፈልጎ፣ ዕውነትን አሽትቶ ለተነሳው ችግር፣ ዕውነትን ተመርኩዞ በጥበባዊ ዘዴ መፍትሔ የሚሰጥ ብየና ነው።

Page 11: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 11 ~

ዕውነትን ፈልጎ ማግኘት ደግሞ እንደዚሁ ቀላል አይደለም።

„ዕውነት“ ፍለጋ አስቸጋሪ ስለሆነ፣ እሱን ለመረዳት „ወንጄልን“ ለጊዜው ትተን ሃይማኖትን እንውሰድ።

በተለይ ሃይማኖትን አስታኮ ለሚወረወር ችግር „እርግጠኛና ዕውነተኛ“ መልስ ለመስጠት መሞከር በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ እናውቃለን። የጠለቀም ዕውቀት ቢኖረን (ሃይማኖት የለሽ ሃይማኖት ናቂ አቴኢስት ካልሆን በስተቀር እሱም ያጠራጥራል) ችግር ውስጥ እንገባለን።

ለመሆኑ የትኛው ሃይማኖት ነው በዓለም ላይ ከአሉት አምስቱ (ከዚያም ሊበልጡ ይችላሉ) ትላልቅ ሃይማኖቶች ውስጥ ዕውነተኛውና ትክክለኛው መንገድ የያዘው? ብለን እራሳችንን ብንጠየቅ መልሱ ከባድ እንደሆነ ለማንኛችንም ግልጽ እና አስቸጋሪ ፈተናም ነው። እላይ እንደተባለው አቴኢስቱ መልሱን አውቃለሁ ብሎ ሊነሳ ይችላል።

ግን ትክክለኛው – ቡዲዚም ነው ወይስ ሒንዱ? እስላም ነው ወይስ ክርስቲያን? ወይስ ደግሞ የአይሁድ ሃይማኖት?… ሃይማኖት የለሹ አቴኢስት እሱስ ትክክለኛ መንገድ የያዘ ሰው ነው? ወይስ አግኖስቲከሩ? ምናልባት ጴንጤው? ወይስ…ሺኢቱ? ወይስ ሱኒቱ?

ለመሆኑ ከእነዚህ ሁሉ መካከል ትክክለኛው ማነው ቢባል መገመት እንደሚቻለው „መልሱን“ አግኝቶ ለአንድ ሰው ማስረዳቱ በጣም አስቸጋሪ ነው። እንደ እምነታቸውና እንደ አስተዳደጋቸው ከተለያዩ ሰዎች የተለያዩ መልሶችን በእርግጥ እንሰማ ይሆናል።

እነዚህ የተለያዩ መልሶች ደግሞ በሥነ-ሥርዓቱ ከአልተያዙ „ፍቅርን ሳይሆን ጠብን በሰው ልጆች መካከል እንደሚጭሩ“ መገመቱ ከባድ አይደለም።

ኢራክን ና ሶሪያን፣ አፍጋኒስታን ና ናይጄሪያን፣ …ኬንያን፣ …ማየቱ በቂ ነው።

እኔ ነኝ ትክክለኛ ተባብለው በየቀኑ እንደምንሰማው እነሱ ይገዳደላሉ።

እንግዲህ ለዚህ ነው እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ውስጥ ገብቶ „ፍርድ“ መስጠቱ አስቸጋሪ ነው የሚባለውም። በዚያው መጠን „የማይከባበሩና የሚናናቁ“

Page 12: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 12 ~

ሃይማኖቶችም ተከታይ አማኝ ለማፍራት „ የእኔ አምላክ ከአንተ አምላክ ይበጣል አትድከም…“ ብለው በያለበት እንደሚቀሰቅሱ ሁላችንም እናውቃለን።

ትልቁ ችግሩ የሚነሳው ደግሞ – እላይ የአንዳንድ አገሮችን ስም ጠቅሰናል- „ በእኔ ሃይማኖት ሥር እሱ በሚፈቅድልህ ሕግና ሥርዓት በዚያ ደንብ ብቻ መኖር አለብህ…“ የሚለው አዋጅ ሲታወጅ ነው። ያ አዋጅ የታወጀ ዕለት ደግሞ በአንድ አገር ውስጥ ሰክኖ የኖረ ሰላም „ደፈረሰ…ያኔ ተበላሸ“ ማለት ይቻላል።

በሻሪያን ሕግ ወይስ በኦሪት

ሕግ?በክርስቲያን ሕግ ወይስ በቡዲዚም? በሂስና በግለሒስ ወይስ በአብዮታዊ እርምጃ? በቡርዡዋ ሕግ (እንደዚህ የሚባል ሕግ የለም) ወይስ በሶሻሊስት ሕግ?…የትኛው ሥርዓት ነው ለሰው ልጆች ትክክለኛው? በየትኛው ሥርዓትና ሕግ ሥር መኖር ትፈልጋለህ? ቢባል ይህ የሚያጣላ፣ ይህ የሚያከራክር ነጥብ መሆኑ ከአለፉት ዘመናት ከአገኘነው ተመክሮ በደንብ እናውቃለን።

ታዲያ ለመሆኑ ሕግ ምንድነው?

ምንድነው ሰለሞን ያደረገው?

ሁለት አንድ ላይ ያደጉ አንድ ላይ የሚኖሩ እንደአጋጠሚም አንድ ላይ አርግዘው በአንድ ጊዜ የወለዱ ወጣት ልጃገረዶች – ታሪኩን ታውቃላችሁ- ነበሩ።

የአንደኛዋ ልጅ – አብዛኛዎቻችን የምናውቀው ታሪክ ነው በእሱ እንጀምር – በድንገት ታሞ ጡት እያጠባችው ደረቱዋ ላይ ይሞትባታል።

በዚያን ሰዓት ጓደኛዋ የእራሱዋን ልጅ አስተኝታ ወሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ወርዳለች። ተመልሳ ስትመጣ ትርምስና ጩኸት፣ ሁካታና ግርግር በእዚያ አካባቢ ያሉ ጎረቤቶች ይሰማሉ። ሲደርሱ ለቅሶ ነው። አንዱ ልጅ ሞቶ አልጋው

Page 13: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 13 ~

ውስጥ ተጋድሞአል። ሁለቱ ሴቶች „የእኔ ልጅ ሞተ የለም የአንቺ“ እየተባባሉ ይጣላሉ።

ሁለተኛው ልጅ እቤት በቀረቺው ሴትዮ ክንድ ተጋድሞ „የእናቱን ጡት“ ይፈልጋል። አሁን የሞተው ልጅ የማን ነው የሚለው ጥያቄ ይነሳል።

ችግሩን ለመፍታት ጥበበኛው ንጉሥ ሰለሞን ፊት ይቀርባሉ።

የሚታወቀውን ታሪክ እናሳጥረው። ዳኛው አዝኖና ተክዞ ሁለቱም „የእኔ ነው የለም የእኔ ነው“ ብለው ስለ አስቸገሩና ስለ አስጨነቁት በመጨረሻው „በሰለሞናዊ ፍርዱ“ ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ በል „ ልጁን በሰይፍህ ለሁለት እኩል ሰንጥቀህ ለሁለቱም አከፋፍላቸው…“ ሲል ያቺ ልጅዋ የሞተባት ሴትዮ እጅ ነስታ፣ የንጉሱን ፍርዱን አመስግና ስትቀበል፣ የእናት ሆድ አላስችል ብሎአት ልጅዋ በሰይፍ ለሁለት ተሰንጥቆ ከሚሞትባት „… አትግደሉት! የሞተው ልጅ የእኔ ነው ይህኛው ልጅ ግን የእሱዋ ነው። ስጥዋት ጥፋተኛውም፣ ውሸታሙም እኔ ነኝ“ ብላ ትማጸናለች።

እንደምናውቀው በዚህ ሰለሞናዊ ፍርዱ ንጉሡ ልጁን ለወላጅ እናቱ መልሶ ሰጥቶ ያቺኛዋን ቀጥቶአታል።

ከሦስት ሺህ አመት በሁዋላ ዛሬ እንደዚህ ዓይነቱ ችግር ቢከሰት እዚያ ላይ ሁለቱን ሴቶች የሚያዳርስ ሙግት አይኖርም። በ ዲ ኔ ኤ ምርምራ በቀላሉ በትንሽ ደቂቃ እናትና ልጅን መለየትና ጥፋተኛዋ ማን እንደሆነች አጣርቶ አውቆ „መቅጣት“ ወይም „መገሰጽ“ ይቻላል። ያኔ ግን ይህ እንደዚህ ዓይነት ብልሃት አይታወቅም ነበር።

ከሰው ልጆች የፍርድ አሰጣጥ ታሪክ እንደምናውቀው በሁለቱ ዘመን መካከል – እላይ ከተጠቀሱት በዲ ኔ ኤ ምርመራና በሰለሞን ፍርድ – ብዙ ዓይነት አስፈሪ የሆነ የፍርድ አሰጣጥና አካሄዶች አይተናል። ሰምተናል። እንዴት እንደነበሩም አንብበናል።

በሰለሞን ፋንታ ፍርድ ሰጪው ሒትለር ቢሆን ኑሮ አለጥርጥር „ገና አሥር አሥር ልጆች ሁለታችሁም ትወልዱልኛላችሁ“ ብሎ እሱ ለዚሁ ሲል አስቀምጦ ወደ ሚቀልባቸው ጎረምሶች/መኮንኖች መንደር ( እንደዚህ ዓይነት የማረፊያና የመዝናኛ የልጆችም መፈልፈያ መንደር ያኔ ነበር) አታልቅሱብኝ ጥፉ ከፊቴ ብሎ ወደዚያ በየአመቱ ሕጻናት እንዲቀፈቅፉለት ይሸኛቸው ነበር። ወይም በመርዝ ጋዝ አይሁዶች ከሆኑ ደግሞ ፈጅቶ እንዲቃጠሉም ያደርግ ነበር።

Page 14: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 14 ~

ለስታሊን ሆነ ለፖልፖት መልሱ ለእነሱም ቀላል ነው።

„… እኛ ሶሻሊዝምን ለመገንባት ስንጣጣር እናንተ ከማንም ጋር ትዳራላችሁ“ ብለው ከእነ ባሎቻቸው ወይም ከእነ ወዳጆቻቸው ወደ ሳይቤሪያ ወይም ወደ አንድ ገደል ለድንጋይ ፈለጣ ያሳናብቱአቸው ነበር።

„አለፈቃድ አረገዛችሁ“ ተብለው „አብዮታዊ እርምጃ“ የሚወስዱባቸው ኃይሎችም እንዳሉ፣ ከመውሰድ የማይመለሱ እንዳሉ እናውቃለን።

ሕግ ያለበትና ሕግ የሌለበትን ቦታዎች ለማሳየት ነው የሞተውን ልጅ ታሪክ ያነሳነው።

የተለያዩ ሃይማኖቶች ባሉበት በአንድ አገር፣ በሃምሳና በሰማንያ ሚሊዮን ከዚያም የሚበልጡ ሰዎች በአንድ ግዛት ውስጥ በሚኖሩበት አገር፣ የተለያዩ የሚፎካከሩና የሚቃረኑ አመለካከቶችና አስተሳሰቦች በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉንም እኩል የሚያስተናግድ አንድ ሕግ የግድ ያስፈልጋል።

ለምን ያስፈልጋል?

ሕግ አንድን ሕዝብ ያስተሳስራል። ሕግ አገርን አንድ ያደርጋል። ሕግ ሰላምንና ጸጥታን ፍቅርንና ወንድማማችነትን መተማመንንና መከባበርን፣ መረዳዳትና በሰው ልጆች መካከል ያመጣል። እራስን ችሎም መኖርን ለግለሰቦች

Page 15: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 15 ~

ያስተምራል። ከዚያም ጋር ሕግ አንዱን ከአንዱ ሳይለይ ለግለሰቦች እኩል መብትና ነጻነታቸውን እኩል ደንግጎ የበላይና የበታች ሳይል ያስቀምጣል።

ለመሆኑ ሥልጣን ላይ የተቀመጠው አንድ በአለሥልጣን ሚኒስትርና አንድ ተራ ሰው በሕግ ፊት ሁለቱ እኩል ናቸው? የጦር መኮንኑ እና አንድ ጋዜጠኛ፣ አንድ ደራሲና አንድ የአገር መሪ ፕሬዚዳንት እነዚህ ሁለቱ እኩል ናቸው?

መለዮ የለበሰው ወታደርና ተማሪ፣ አንድ ለማኝና አንድ የባንክ ገዢ፣ አንድ አስተማሪና እንዲት ተማሪ በሕግ ፊት እኩል ናቸው? ጄነራሉና ተራ ወታደሩ፣ የቢሮ ጸሓፊና ሥራ አስከያጁ፣ አሰሪና ሰራተኛው፣ አባትና ልጅ በሕግ ፊት እኩል ናቸው?

ጠቅላይ ሚኒስተሩና ሚኒስትሮቹ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ታክሲ ነጂው፣ ኩሊውና እህል አስፈጪው፣ ንግሥቲቱና አትክልት ኮትኳቹ፣ ጳጳሱና ሹፌራቸው፣ እነዚህ ሁሉም በሕግ ፊት እኩል ናቸው?

ሁሉም በሕግ ፊት አዎን አንዱ አንዱን የማይበልጠው እኩል ሰዎች ናቸው።

በሰለሞን የጀመረው ጥበብ በሔለኒስቲክ ዘመን የተስፋፋው ዕውቀትና ፍልስፍና በሮም የግዛት ዘመን መልክ የያዘው ሕግና ሥርዓት በሁዋላ “በጨለማ ዘመን” በዳርክ ኤጅ ያ ሁሉ በጥቂት የሰው ልጆች ድካም የተደረሰበት የዕውቀት ደረጃ እንዳልነበር ሁኖ ይዳፈናል። ለምን ተዳፈነ?

ምክንያቱ ምንድነው? ይህ እራሱን የቻለ የምርምር ክፍል ነው። ብቻ ችግሩ የመጣው “ከሃይማኖት ጠንክሮ መውጣት ነው” የሚሉ አሉ። ወይም የትላልቅ መንግሥታት መውደቅና የሽፍቶች በአውሮፓና በሌለው ዓለም እንደ አሸን መፍላትና ብቅ ማለት ነው የሚሉም አሉ።

ቀስ በቀስ ተራ በተራ ጠፍተው የነበሩ ጽሑፎች በመካከለኛው ክፍለ-ዘመን ብቅ ይሉና በአውሮፓ ገዳማት ይተረጎማሉ። ሳይንስና ምርምር ዳዴ እያሉ ከወደቁበት ቦታ እየፈሩና እየቸሩ አንገታቸውን ያውም በጥንቃቄ ያነሳሉ። ሲመራመሩም ነበልባል እሳትም የበላቸውም ጭንቅላቶች አሉ።

ትምህርት ተስፋፍቶ፣ አንጎልም ክፍት ሁኖ….ጥያቄዎችም በዝቶ “ነገሥታትንና መሣፍንትን፣ የሃይማኖት አባቶችንና የቤተ-ክርስቲያን አለቆችን፣ ወግና ልማድን፣

Page 16: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 16 ~

ሥርዓትና ደንብን፣ አስተዳደግን፣ አስተሳሰብን የሚተቹ፣ የሚቃወሙ፣ እንዲታረሙ የሚጠይቁ፣ ይቀየር” የሚሉ ምሁሮች በያለበት ይነሳሉ።

ምሁሮች የነጻነትንና የሰው ልጅ የእኩልነትን ጥያቄ፣ የዲሞክራሲና የግለሰብ ሰበአዊ መብቶችን ጉዳይ አንስተው መከራከር ይጀምራሉ።

ይህን የግለሰቦችን ነጻነት ጥያቄ ለማንሳት ሆነ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት አንዳንዶቹ አሁን እንደሚሉት „ከልማትና ከዕድገት፣ ከእንዱስትሪ ፋብሪካ ቤቶች መስፋፋትና እሱም ከፈጠረው የሠራተኛው መደብ ጋር „ ምንም የሚያያይዘው ነገር የለም።

ለመናገር ለመተቸት፣ ለመቃወምና ለመደገፍ ለመምረጥና ለመመረጥ፣ የእኩልነት መብትን ጥያቄ ለማንሳት፣ ተቻችሎና ተከባብሮ አብሮ ለመኖር „በመጀመሪያ የፋብሪካ የኢንዱስትሪና የሠራተኛ መደብ ዕድገት “ የሚባል ቲዎሪም ያኔ አልነበረም። እንደዚህ የሚባል ነገር የለም።

እነቶማስ ጄፈርሰን ናቸው ከእንግሊዝ ንጉሥ የዘውድ ቅኝ ግዛት እነሱ እነደአሉት “ነጻ ለመውጣት” የፈላስፋውን የጆን ሎክን የሰበአዊ መብት ትምህርት (1632-1704) ለቀም አድርገው አሜሪካን አገር ትግላቸውን የጀመሩት።በሁዋላ ሕገ-መንግሥታቸውን ነድፈው ቋሚ አድርገው ያስፋፉት።

ሎክን ተከትለው እነቮልቴር፣እነ ዴኒስ ዲደሮ እነ ጃን ጃክሩሶ…(እንመጣባቸዋልን) ይቀጥሉበታል።

የፈረንሣይ አብዮት ነው „አንድ ንጉሥ፣ አንድ ሕግ፣ አንድ ሃይማኖት“ ብለው አገሪቱን ይገዙ የነበሩ ነገሥታትን ሽሮ ሰበአዊ መብትን ያወጀው።

ሌሎች አብዮቶችም አለምን ይወራሉ።

ሌሎቹ አብዮቶች የሩሲያ ሆነ የቻይና የኪዩባ ሆነ የኢትዮጵያ፣ የቬትናም የካምቦጂያ፣ የሰሜን ኮሪያ ወይም የሊቢያ፣ የግብጽ፤የሱዳን፣ …ብቅ ይላሉ።

እነሱ ግን በተቃራኒ ያመጡት የተገላቢጦሹን ነው። በዲሞክራሲ ፋንታ አምባገነንነት ነው።

“በአንድ ንጉሥ ቦታ” ይህ ነው ሓቁ የአንድ ሰው፣ የአንድ ቡድን፣ የአንድ ፓርቲና የአንድ ድርጅት አምባገነን ሥርዓትን ነው።

ይህ ደግሞ የማርክስና የኤንግልስ፣የሌኒ እና የስታሊን ሥራ ነው።

Page 17: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 17 ~

ለምንድነው በምዕራቡ ዓለም ሰበአዊ መብቶች የተከበሩት፣ እላይ በቆጠርናቸው በምሥራቁና በአፍሪካ አገሮች የማይከበሩት?

ለምንድነው በሕግ ፊት በምዕራቡ ዓለም የሰው ልጆች እኩል የሆኑት፣ ለምንድነው በአፍሪካና በቻይና በሩሲያና በኮሪያ…በኪዩባ የሰው ልጆች በሕግ ፊት እኩል ያልሆኑት?

ለምንድነው መተቸት መቃወም መምረጥና መመረጥ፣ መደራጀትና መወዳደር በአንዳንድ አገሮች የተፈቀደው በሌሎቹ የተከለከለው? ወይም ለምድነው አንደኛው ወገን ሳይመረጥ ተመረጥኩ ብሎ የሚያጭበረብረው?

ለምንድነው በአንዳንድ አካባቢ ስለ የግለሰቦች ሰበአዊ መብት ሳይነሳ፣ እሱ ሳይከበር ስለ ብሔር /ብሔረሰቦች መብትና እኩልነት ብቻ የሚወራው? በሌላው አካባቢ ለግለሰብ መብቶች ቅድሚያ የሚሰጠው?

መልሱ ቀላል ነው። ሥልጣን ለመውጣት፣ ሥልጣን ላይ ለብዙ አመታት እስከ ዕድሜ ልክ ለመቆየት፣ ሥልጣንን ለማውረስ፣ ሥልጣንን ይዞ ሰውን ለመቆጣጠር፣ የዲሞክራሲና የግለሰቦችን ሰበአዊ መብቶች ማወቅ፣ በሥራም ተርጉሞ ማክበር፣ ለገዢው መደብ አደገኛ እንደሆነ እንደሚሆን ያውቃሉ።

አስተዋይ አንባቢ እንደሚረዳው ፣ ኢንላይትመንት ከጨለማ ወደ ብርሃን የሰው ልጆች እንደገና በአደረጉት ጉዞ ሁለት መንገዶችን ነው የተከተሉት። አንደኛው የእነሎክ፣የእነ ቮልቴር፣የእነ ቶማስ ጄፈርሰን…የአሜረካንና የፈረንሣይን የእንግሊዝን መንገድ ነው። ሁለተኛው የማርክስና የሌኒን የስታሊንና የማኦ …የእነፓልፖትን መንገድ ነው። ሦስተኛው በሃያኛው ክፍለ-ዘመን ብቅ ያለው የሒትለርና የሞሶሊን የፋሽሽቶች አምባገነን ሞዴል ነው።

Page 18: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 18 ~

ለምንድነው ምዕራቦቹ የመጀመሪያውን መንገድ መርጠው የተከተሉት? ለምንድነው የዲሞክራሲመብቶችን ለእራሰቸውም፣ ለሕዝቡም፣ ለሁሉም እኩል የሰጡት መብቱን የሰጡት? መብቱን እኩል የተጋሩት አለ ሕግ አይደለም። መብት ገደብ አለው። ምን ዓይነት ገደብ?

የሰው ልጆች አንድ ወጥ ሳይሆኑ የተለያዩ መሆናቸውን ስለሚያውቁ ነው። የሰው ልጅ ቁጥጥር ከአልተደረገበት አውሬ መሆኑን ስለተገነዘቡም ነው።

እላይ እንደተጠቀሰው ዲሞክራሲና የዲሞክራሲ ሥርዓት፣ የግለሰቦች ሰበአዊ መብቶች መከበር ሕግ የመጣውና የወጣው ፈላጭ ቆራጩን ንጉሣዊ አገዛዝን ከመቃወም ነው። ይህ አንደኛው ምክንያት ነው።

ሁለተኛው፣ ዓለም አቀፋዊው የሰበአዊ መብት አዋጅ የታወጀው አረመኔውን የሒትለርንና የሞሰለኒን ሥርዓት ተመልሶ እንዳይመጣ ለማገድ ነው።

ሌላው ምክንይት ያኔ በሥነ-ሥርዓቱ የአዋጁን መልዕክት ያዳመጠው ሰው የለም እንጂ የሚፈራውን „የኮሚኒስቶቹን አምባገነን ሥርዓት“ በዓለም ላይ እንዳይስፋፋም ለማገድ ነው።

ቁጥጥር የሌለው፣ ቁጥጥር የማይደረግበት ሥርዓትና ገዢ የፈለገውን ስም ይያዝ አደገኛ ነው። ስለዚህ አንዱ ክፍል ሌላውን ክፍል እንዲቆጣጠረው ተደርጎአል። የሥልጣን ክፍፍል፣ የሥልጣን ሽንሸና፣ የሥልጣን ተዋረድ፣ የሥልጣን ገደብ፣ የሥልጣን ተቆጣጣሪ፣ ክፍሎች ወደላይና ወደታች፣ ወደጎንና በዙሪያ ጥምጥም ተዘርግተዋል።

ብዙ ቦታ እንደምናየው ሁሉም መንግሥታት “ሸንጎ-ፓርላማ” የሚባል ሕንጻ አላቸው። ግን ሁሉም ሸንጎ አንድ አይደለም።

በምዕራቡ ዓለም ሽንጎውን የሚቆጣጠረው ክፍል አለ። ሕግ አውጪ እና የሕግ መምሪያ የሕግ አስፈጻሚም ክፍሎች አሉ። እዚሁ ላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሽንጎ ውስጥ ወንበር አላቸው። ከመንግሥት ቁጥጥር ነጻ የሆኑ የሙያ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋሞች፣ የሲቢል ድርጅቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ደራሲና ጸሓፊዎች፣ ሠልፍና አቤቱታዎች፣ የሴቶችና የወጣቶች፣ የአሰሪና የባለጸጋዎች፣ የአዛውንትና የስፖርት…እነዚህ ሁሉ ዓይናቸውን በባለሥልጣኖች ላይ ጥለው በቁራኛ የሚከታተሉ ክፍሎች ናቸው።

ይህን ማድረግ ሁሉም ቦታ ይቻላል? አዎን ይቻላል። ሥልጣን ላይ የተቀመጠው መንግሥት አሻፈረኝ ከአለስ?

Page 19: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 19 ~

በአደባባይ ጩኸት፣ በተቃውሞ አመጽ ሕገ-መንግሥቱን እንዲያከብር አለበለዚያም ቦታውን በሕዝብ በተመረጠ ለሌላ ችሎታ ላለው ለሚሰራ ኃይል እንዲለቅ ይደረጋል። ሥልጣን በየአራት አመቱ በምርጫ እንዲወሰን ይደረጋል። ለዕድሜ ልክ የሚሰጥ የሚታደል ሥልጣን በ21ኛው ክፍለ-ዘመን የለም።

ለዚህ ደግሞ በቂ ምሳሌዎች አሉ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

———

[1] ሔሊኒስቶች ከሰለሞን በሁዋላ ብቅ ይላሉ። የእነሱ ትምህርትም ብርሃንን ይገልጣል።

Page 20: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 20 ~

ጃንሆይና ነጻ-ዜጋ፣ ፓርቲና ዲስፕሊን

Published October 28, 2013 at 535 × 280 in ጃንሆይና ነጻ-ዜጋ፣ ፓርቲና ዲስፕሊን

Next →

ጃንሆይና ነጻ-ዜጋ

ጃንሆይና ነጻ-ዜጋ

ፓርቲና ዲስፕሊን

ለምንድነው የታወቀውን ነገር እንደገና ለማብራራት የምንሞክረው? አሁን ምን ይጠቅማል? ምን ያደርጋል በንጉሥና በተራ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት ደግመን የምናነሳው?

መልሱን የምንረዳው አሁን ሳይሆን ከጥቂት አረፍተ ነገር በሁዋላ ነው። በትክክል የምንገዘበው ደግሞ ወደ መጨረሻው ላይ ነው።

ከንጉሠ-ነገሥቱ የተላለፈልን (አብዛኛዎቹ ዕድሜአቸው ቢያንስ ከሃምሣ አመት በላይ የሆኑት አዛውንቶች የማይረሱት) አንድ የቆየ አነጋገር አለ።

እሱም „…የምንወደው ሕዝባችንና የሚወደን ሕዝባችን…!“ የሚለው የ ቀ ኃ ሥ ግሩም አነጋገር ነው። እሳቸው „ሕዝባቸውን እንደሚወዱ“ ጥርጥር የለም። ሕዝቡ ደግሞ „እንደሚወዳቸው…“ መገመት ይቻላል።

ግን አንድ ችግር አለ።

Page 21: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 21 ~

በዚያውም መጠን የማይታወቀው ምን ያህል ሕዝብ እሳቸውን ጸሓዩን ንጉሥ„እንደሚወዳቸው“? ምን ያህልስ ሰው እንደ „ሚጠላቸው“ አንዳችም ጥናት እንደ አውሮፓ ወይም አሜሪካ ይህን ነገር የሚከታተል የምርመራ ጣቢያ በአገራችን ስለሌለ፣ ስለአልነበረም፣ በትክክል ለመናገርና ይህን ያህል ነው ብሎ ማስቀመጥ አይቻልም።

የአገራችን የኢትዮጵያ ነገር የሚያስገርም ነውና አሁንም ቢሆን„…የምንወደው ሕዝባችንና የሚወደን ሕዝባችን…“ የሚሉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እንዳሉ እንዲያው ከነገረ ሥራቸው ተነስተን ስንመለከተው፣ መገመት ይቻላል።

ግን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሁለቱም ፖሊተከኞች ሆኑ ሌሎቹ „የኢትዮጵያ ንጉሥና የነጉሠ-ነገሥቱ ዙፋን ላይ አልተቀመጡም። “ ንጉሥም አይደሉም።

በሌላ ቋንቋ አቶ ኃይለ ማሪያም እንደ ሳውዲው ንጉሥ ፣ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂም እንደ ሞሮኮ ንጉሥ ኢትዮጵያንና ኤርትራን ሊገዙ „ቅባ ቅዱሱን“ የተቀቡ የዕድሜ ልክ „ንጉሦች“ የሚታወቀውን ለመድገም፣ እነሱ “የተነሱ አይደሉም።”

እነሱም -እኛ እሰከ ምናውቀው ድረስ- አንድም ቦታ ንጉሥ ነን አላሉም። እነሱም ይህን አይክዱም። ከአፋቸውም አንድ ቀን አልወጣም።

አመጣጣቸውንም ክደው „የሰለሞን ዘርን ነን“ ስለዚህ ሥልጣኑም ቤተ-ምንግሥቱም „ዕድሜ ልካችን ድረስ ይገባናል“ እሰከ አሁን አላሉም።

ሁለቱም እንደ እኔና እንደ አንተ፣ እንደ እሷና እንደ እሱ፣ አንደ እከሌና እከሊት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ዜጎች ተራ ሰዎች ናቸው።

ንጉሡ ደግሞ እንደምናውቀው „ልዩ – ፍጡር“ ናቸው። እነሱ እንደሚሉት፣ የሃይማኖት አባቶች እንደሚያስተምሩት „…እግዚአብሔር ከሰው ሁሉ የመረጠው“ እሰከ ዕድሜ ልኩ የሚገዛ „…ልዩ ሰው“ ነው። ንጉሥ እንደምናውቀው አይከሰስም። ንጉሥ አይወቀስም፣ አይተችም። ከሥልጣንህም በቃህ ውረድ አይባልም። በዘልማድ የኢትዮጵያ ሕዝብ „…ሰማይ አይታረስም ንጉሥ አይከሰስም …“ ብሎ ጨርሶታል።

ታዲያ ለምንድነው ንጉሡ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌላውም ዓለምም አንድ በአንድ ተራ በተራ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ የተደረገው?

Page 22: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 22 ~

በምንስ ብልሃት ነው እነሱ ከዙፋናቸው የወርዱትስ?

A

አንድ ዜጋ አንድ ተራ ሰው አንድ ከእኔና ከአንተ ምን ዓይነት ልዩነት የሌለው ሰው ሲያተፋ ከታየ እሱ ይተቻል፣ ይወቀሳል፣ እንዲታረም ይጠየቃል። ከሥልጣንም ከዚህ ሁሉ አመት በሁዋላ በቃህ እስቲ ደግሞ ውረድ ተብሎ ምርጫ ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል።

በአሜሪካን አገር የምናየው ይህን ነው። በፈረንሣይና በጀርመን፣ በጃፓንና በኬንያ በደቡብ አፍሪካ፣ እንዲሁም በናይጄሪያና በጋና የምናየውም ተመሳሳይ አሰራርን ነው። …ምርጫ የሸንጎ ምርጫ እዚያ ይካሄዳል።

በሌላ በኩል እነ ንግሥት ኤልሳቤጥን፣ የጃፓኑን ንጉሠ ነገሥት አይህቶ፣ የስፔኑ ሁዋን ካርሎ፣ የስዉዲኑን፣ የዴንማርኩን፣ የቤልጅጉን፣ የኖረዌውን…ወደው በገዛ ፈቃዳቸው እስከ አለቀቁ ድረስ „በቃችሁ ውረዱ“ ተብለው እነሱ ሕዝቡ አይጠየቁም። ለምን?

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ግን እንደ ሌሎቹ ከሁለት ተከታታይ ምርጫ በሁዋላ-ይህ የአሜሪካን ሕግ ነው- ጓዛቸውን ጠቅልለው ከዋይት ሓውስ በሚቀጥሉት አመታት መጨረሻ ላይ እንደሚወጡ ግልጽ ነው። ሌሎቹ የአውሮፓና የላቲን አሜሪካ መሪዎች በየአራት አመቱ አደባባይ ወጥተው ሕዝብ ፊት ቀርበው ወይ እንደገና ይመረጣሉ ወይ ተሸንፈው ከፖለቲካ ዓለሙ ይሰናበታሉ። ይህን ማለት የታወቀውን መድገም ነው።

አቶ ኢሳያስና አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ሚስተር ሮበርት ሙጋቤና የአንጎላው ዶሳንተስ…ቁጥራቸው ረዥም ነው- ዕድሜ ልካቸውን የሚገዙበት ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም። ለምን? ምክንያቱ ምንድነው?

ማን ጠየቃቸው እነሱን ይህን ያህል አመት በሥልጣን ላይ እንዲቆዩ?ማን ለመናቸው? ማን መረጣቸው? ማን ፈቀደላቸው? ለመሆኑ ምን የሚያሳምን ነገር ጨብጠዋል? ለምን እነሱ ብቻ ሥልጣኑ ላይ እንዲሰነብቱ ይደረጋል?….ለምን አንተ ወይም አንቺ በሕዝብ ተመርጣችሁ አገሪቱን አትመሩም? አታስተዳድሩም?…እግዚአብሔር ሥልጣኑን መርቆ ነው የሰጣቸው? ወይስ ሕዝቡ ?

ይህን ለመረዳት ችግሩ ያለው አንድ ቦታ ላይ ነው። ይህም ዕውነቱን እንናገር ከተባለ የተቃዋሚውንም ጎራ ያጠቃልላል።

Page 23: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 23 ~

ምን አጠፉ እነሱ ደግሞ? የሚል ድምጽ ሊሰማም ይችላል።

የተቃዋሚ ቡድኖችን ጎራ ተመልከትን፣ እነሱስ እንዴት ነው የተመሰረቱት? አባሎቻቸውን እንዴት ነው የሰበሰቡት ብለን እራሳችንን እንጠይቅ?

ቀድሞ ድርጅቱን የመሰረተ–ይህ ነው ብልሃቱ–ቀድሞ የድርጅቱን ሕግ የነደፈ፣ ቀድሞ ሮጦ የድርጅቱን አመራር የጨበጠ፣ ተከታይ ደጋፊዎቹን ሰብስቦ ያዋቀረ…እሱ „ቅባ ቅዱሱን ሳይቀባ ንጉሥ“ የሆነ፣ እራሱን በራሱ የሾመ፣ እንደ ናፖሊዮን ዘውዱን ከሚንቀጠቀጠው ጳጳሱ እጅ ቀምቶ አናቱ ላይ የደፋ ሰው ማለት ነው።

ከዚያ በሁዋላ ይህን ሰው አስመልክቶ „ዕውነተኛ ምርጫ“ በድርጅቱም ውስጥ ሆነ ከድርጅቱም ውጭ ሥልጣን ይዞ ብቅ ያለ ቀን „ ሕዝቡ እሱን እንዲመርጠው „ አይደረግም ። ይህ እንዳይሆን ተሟጋቾቹም ብዙ ናቸው።

B

ከዚህ በሁዋላ በተነደፈው አይዶኦሎጂም ሥር ሁሉንም ሰው ሰካክቶ ሽንሽኖ አስቀምጦ፣ “በዲስፕሊን፣ በሥልጣን ተዋረጅ፣ በበላይና በታች፣ በቅጣትና በዱላ በጥይትና በባሩድ አስፈራርቶ….“ ድርጅትንና የድርጅቱን አባሎች ተብትቦ በመያዝ፣ ሁሉንም ልክ አስገብቶ ሥልጣንን አንድ ቀን በጠበንጃ ኃይል ይዞ ቤተ- መንግሥት መግባት ዋና የትግል ዓላማና ጉዞ ነው።

እንደዚህ ዓይነቱ ነገር በሃይማኖት ድርጅቶችም ውስጥም በደንብ ይታያል። ከዚህ ያለተለየ ጉዞ በአመጣጥ ታሪካቸውም አብዛኛዎቹ አላሳዩም።

እንደ ንብረታቸው ነው እነዚህ ሰዎች ሕዝቡንም እያንዳንዱንም ሰው ሁሉ የሚያዩት። እንደ ሓብታቸው ነው ሁሉንም ከቁጥጥራቸው እንዳይወጣ በዓይነ

Page 24: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 24 ~

ቁራኛ የሚጠብቁት። እንደ የግል „ባሪያቸው“ ነው መብቱን ቆይተው የሚገፉት። ከዚያ በሁዋላ መብቱን መርገጥ ቀላል ነው።

የሰው ልጅ ግን የትም ቦታ ይኑር የትም ይወለድ፣ ነጭ ይሁን ጥቁር፣ ቢጫ ይሁን ቀይ…. ቤቱን ዘግቶ ወጥቶ ንጹህ አየር መተንፈስ ይገልጋል። ቡና ቤት ገብቶ ሳይገላመጥ ከጓደኞቹ ጋር የልቡን ተነጋግሮ ወቅሶ ተችቶ ሐሳቡን ከሌላው ጋር ተከፋፍሎ ወደ ቤቱ ማንንም ሳይፈራ መመለስ ይፈልጋል።

የባቡር ወይም የአይሮፕላን ቲኬቱን ገዝቶ፣ መኪናውን ወይም ብስክሌቱን ይዞ፣ ፈረሱ ላይ ወይም አንድ አውቶብስ ላይ ተሳፍሮ፣ ቢፈልግ ዘመዱን፣ መጠየቅ ባይፈልግ ሜዳ ላይ ዱንኳኑን ተክሎ ማደር ይፈልጋል።

የፈለገውን ልብስ፣ የወደዳትን ሴት ልጅ፣ ደስ የሚለውን ሙያ፣ ቢፈልግ ጢሙን ማሳደግ፣ ባይፈልግ መላጨት፣ ማግባትንና መፍታት፣ አንገቱን ሳይደፋ ቀና ብሎ መሄድን የሰው ልጆች ሁሉ እኩል መብት ስለአላቸው፣ ማንንም ሳይፈራ ማድረግ ይፈልጋል።

ፊደል የቆጠረውማ አለ አንዳች ቁጥጥርና ፍረሃቻ በአገሩ መሬት አለ- ሳንሱር መጻፍ ይመኛል። ዕውቀቱን ማከፋልና ትውልዱን ማስተማር፣ ዛፍና አበባ ተክሎ መኮትኮት፣ ግቢውን ማሳመር የግል ቤቱንና የግል እርሻውን መጠበቅ ይፈልጋል።

ገበሬ የግል የእርሻ መሬቱን ይመኛል። ሠራተኛው ሥራውን፣ ተማሪው የትምህርት ዕድሉን፣ እናቶችና አባቶች ጡረታቸውን፣ በሽተኛው ሕክምና እና እንክብካቤን፣ ረሃብተኛው ምግብን፣ ሜዳ አዳሪው ፍራሽና አልጋን አዘጋጁልኝ ይላል። ይህ ለማለት ደግሞ መብቱ ነው።

ጥያቄው ሌሎቹ ነጮቹ በምን ብልሃትና ዘዴ እላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ፈቱ የተቀሩት ደግሞ እዚያው የችግር አዙሪት ውስጥ ገብተው፣ መንገዱ ጠፍቶአቸው ከዚያ ለመውጣት ያልቻሉት? የሚለው ጥያቄ ነው።

መልሱ አርባውንና ሃምሳውን አመታት እንደሚባለው „የብሔር -ብሔረሰብ ትግል፣ እሰከ መገንጠል“ የሚባለው ፍልስፍና በኢትዮጵያ ተገቢውን መልስ ባለ ማግኘቱም አይደለም።እሱማ ለጦር ትግል ሁሉንም ጋብዞ ሰውን አፋጅቶአል። ከዚያም ጦርነት የተገኘው ውጤት ምን እንደሆን ሰው ሁሉ ያውቀዋል።

Page 25: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 25 ~

እንደ ተባለው ኤርትራና ኢትዮጵያ (ያኔ እንደተባለው) „የአፍሪካ ታይዋንና ደቡብ ኮሪያ፣ ሲንጋፖርና …“በአሥርና በሃያ ሦስት አመታት ጊዜ ውስጥ ሆነው የአውሮፓን ገበያ በእንዱስትሪ ምርታቸው አላጥለቀለቁም ።

C

ብዙዎቹ የተመኙት “የመደብ ትግሉም ሶሻሊዚምም የላብ አደሩ አምባገነን መንግሥት በኢትዮጵያ”ያም ቢሆን መፍትሔ አልነበረም። አይደለምም።

አንድ ድርጅት ሓብትና ንብረት በአዋጅ ወረሶ እንድን አገር „ሌኒን እንዳለው፣ ማርክስ እንዳስተማረው፣ ስታሊን በተግባር እንዳሳየው…“ እያሉ ያንን ሕዝብና ያንን አገር እንደ የግል ሐብት እሱን „በሶሻሊዝም ስም“ እጅ አስገብቶ እሱን ቁጭ ብሎ መሸጥና መለወጥ ያ አገሪቱ ከገባችበት ችግር እንደማያወጣት አሁን ያለንበት ሁኔታ እራሱ ምስክር ነው።

የኢትዮጵያ ችግርና የኢትዮጵያ መፍትሔ ያለው ሌላ ቦታ ነው።

እንደሚባለውም የአገራችን ችግር፣ አሁን ያለንበትና የገባንበት መከራ ትላንትና ብቅ ያለው ግሎባላይዜሽን የሚባለው ነገር ይዞልን የመጣ ችግርም አይደለም። ወይም ሌሎች እንደሚሉት የቅኝ ገዢዎች ተንኮል የለቀቁብን በሽታ አይደለም።

ችግሩ ያለው በእኛው መካከል ነው።

እንደ ሰንሰለት ተብትቦ ከያዘን የድርጅት „የዲስፕሊን እሥር ቤት“ መውጣት አለብን። እንደ ባሪያ ፣ እንደ ሎሌ አሽከር ወዲያና ወዲህ ከሚያዋክብን „ፍልስፍናና ትምህርት እምነትና… „ እንዲያውም ወደ ሃይማኖት ከተቀየረው „የፖለቲካ አስተሳሰብ“ ከእሱ ነጻ- መውጣት አለብን።

እንደዚህ ከአልን ደግሞ ከጨለማ ወደ ብረሃን፣ እንወጣለን። ከገባንበት ዋሻ ወጥተን ዓለምን በሌላ ዓይን እናያለን። ፍረሃትን አስወግደን በጠራ አንደበታችንን ግሩም ውይይትን በመካከላችን እንከፍታለን። የተለጎመውን አፋችንን ከፍተን „ለመሆኑ አንተ ማን ነህ? ምን ትፈልጋለህ? ምን ለአገርህ ሰራህ? ምን መስራት ትፈልጋለህ? ችሎታህ ምንድነው? አሁን ደግሞ ይበቃሃል ቦታውን ለሌላው ልቀቅ…“ማለት እንጀምራለን።

እንደዚህ ዓይነቱ አካሄድ ደግሞ ወደ ጦር ሜዳ አይወስደንም። ጦር ክፈቱ ብሎም አይጋብዘንም። እንዲያውም ጦርነት ምን ይህል የሰው ነፍስና ሐብት

Page 26: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 26 ~

ያወጣል? ስንት መስዋዕትነትን ይጠይቃል? ስንት አመት ይፈጃል? ወደሚለው ጥራት ወደ አለው ጥያቄና መልስ ይወስደናል?

ከጦርነት ሌላ ሌላ ብልሃቶችና ዘዴዎች አሉ ወይ ወደሚለው የፖለቲካ አመለካት ይወስደናል።

የነጻ-ዜጋ ኮንሰፕት፣ የነጻ ሰው ሕብረተሰብ ምሥረታ ያም አስተሳሰብ -እናሳጥረው- ኢትዮጵያንና ልጆቹዋን አንድ ያደርጋል። እንዴት? መልሱን እዚሁ እኛ አብዛኛዎቻችን የምንኖርበት የአውሮፓና የአሜሪካን ሕብረተሰብ ሰጥቶናል። አብዛኛው የእሲያና የላቲን አሜሪካ አገሮችም እንደኛው ብዙ አመታት ተንከራተው እነሱም በመጨረሻው መልሱን አግኝተው ደርሰውበታል።

ጃፓንና ደቡብ ኮሪያም አውቀውበታል። እሱም የነጻ -ዜጋ የግለሰብ መብት፣ የሚለው ፍልስፍና ነው።

ለመሆኑ ይህ ምን ይመስላል? እላይ እኮ የአገሮች ስም ጠቅሰናል።

ከሣቴ ብርሃን

Page 27: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 27 ~

ሰብዓዊ መብት/HUMAN RIGHTS WATCH (Document)

Published October 28, 2013 at 151 × 150 in ሰብዓዊ መብት/HUMAN RIGHTS WATCH (Document)

ሰብዓዊ መብት/HUMAN RIGHTS WATCH (Document)

Ethiopia audio page

Ethiopia: Political Detainees Tortured

Embargoed for Release Not for Publication Until: 03:01 in Nairobi, Friday, October 18, 2013 00:01 GMT, October 18, 2013

(Nairobi, October 18, 2013) – Ethiopian authorities have subjected political detainees to torture and other ill-treatment at the main detention center in Addis Ababa, Human Rights Watch said in a report released today. The Ethiopian government should take urgent steps to curb illegal practices in the Federal Police Crime Investigation Sector, known as Maekelawi, impartially investigate allegations of abuse, and hold those responsible to account.

The 74-page report, “

READ MORE

HRW English Report (PDF)

_____________

Page 28: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 28 ~

በግዳጅ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ ፖሊስ በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ በደሎችን ይፈጽማል።

October 18, 2013

“መረጃ ለማግኘት ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዋናከተማዋ እምብርት በየጊዜው ጥቃት ይፈፅማሉ” ብለዋል፡፡ ሌፍኮ እንዳሉት “ድብደባ፣ ማሰቃየት እና በማስገደድ ቃል መቀበል ለጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የተገባ አይደለም።”

በሂዩማንራይት ስዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ

(ናይሮቢ፣ጥቅምት 7 ቀን 2006 ዓ.ም)

“They Want a Confession”

Torture and Ill-Treatment in Ethiopia’s Maekelawi Police Station

October 17, 2013

Get the report:

Download the full report

Download the summary and recommendations in Amharic

Go to report home »

Page 29: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 29 ~

ተስፋና ዕልቂት

Published October 28, 2013 at 572 × 322 in ተስፋና ዕልቂት

Next →

ሞት ለላምፔዱዛ ሞት በላምፔዱዛ፣ ሞት ለነጻ ሕይወት! ለነጻ-ኑሮ!

ተስፋና ዕልቂት

ሞት ለላምፔዱዛ

ሞት በላ ምፔዱዛ፣ ሞት ለነጻ ሕይወት! ለነጻ-ኑሮ!

ሰው ሲሞት፣ ማንም ሰው በከንቱ ሲሞት ያሳዝናል። እንዴት ነው የሞተው? ሲባል ደግሞ የሚሰማው መልስ አንዳንዴ አንጀት ይበላል።

የባህር ወሃ ሞገድ ሚዲትሬንያን ላይ መንገደኛን ሲበላ አዲስ አይደለም። የሰሃራ በረሃ ነጋዴንና መንገደኛን ከርሱ ውሰጥ ሲያስቀር እንደዚሁ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም።

ሰዎች ያን በረሃና ባህር ለመቋረጥ ሲጓዙ ይዘረፋሉ። ይገደላሉ። ሴቶች ብቻቸውን ከሆኑም ይደፈራሉ። ይህ አዲስ አይደለም።

ሰው እንደ በግ ታርዶ ሆድ ዕቃው ተከፍቶ ለታመሙ ሐብታሞች መለዋወጫ ሲሆን መስማቱ ግን ለእኛ አዲስ ነገር ነው። እዚያው ላይ ወንዶች ልጆች በወንዶች ሲደፈሩ ደግሞ መስማቱ ይህ ለእኛ አዲስ ነገር ነው።

ባህሩን አቋርጠው ጣሊያኖች አፍሪካን ይዘዋል። አልፈውም ኢትዮጵያን ከአንዴም ሁለቴ አገሪቱን ለመግዛት ወግተዋል። አፍሪካውያኖችም-ሓኒባልም ዝሆን ይዘው ባህሩን

Page 30: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 30 ~

አቋርጠው ጣሊያንን ወሮአል። ተመልሰው መጥተው ግን ሮማውያኖች እነሱን ፈጅተው ሰው እንዳይኖርበት ጨው ነስንሰው ድራሻቸውን አጥፍተዋል።

ዘንድሮ ግን የሚሰማው ሌላ ነው።

ንጉሠ-ነገሥቱን አሸንፈን፤ ደርግን ቀጥተን፣ አማራውን አሳይተን፣ ነጻ-ጋዜጣ አምጥተን፣ ነጻ-የሠራተኛ ማህበር፣ ነጻ-ፓርቲ ነጻ -ሽንጎ ነጻና -ዲሞክራቲክ ኤርትራን በአጭር ጊዜ አቋቁመን፣ እንደ ሲንጋፖርና እንደ ደቡብ ኮሪያ እንሆናለን፣በዚያም አገር እንመሰርታልን ብለው የተነሱት „ነጻ-አውጪዎች“ ከደርግ የባሰ፣ ብዙዎቹ እንደሚሉት ከሰሜን ኮሪያ ያለነሰ „አምባገነን በመፈጠራቸው“ ወጣቱ ትውልድ አገሪቱን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።

እነሱ ብቻ አይደሉም።

እንደተነበበው፣ ከኢትዮጵያና ከሶሪያ ከኢራክና ከአፍጋኒሳታን፣ ከሱማሊያና ከሱዳን፣ ከሊቢያና ከቱኒዚያ፣ ከግብጽና …በቃን ብለው የሸሹ ሰዎችም ይገኙበታል።

ለምን? ምንነክቶአቸው ነው ሰዎች አገራቸውን ለቀው የሚሰደዱት?

አንድ ከሱማሌ ነፍሱን ለማዳንና ሕይወቱን ለማስተካከል የፈለገው ሰው እንዳለው- የተፈጠርነው መከራ ለማየት አይደለም- „እዚህ ብቀር እርግጠኛ ነኝ እሞታለሁ። ወደ አውሮፓ ጉዞዬን ባደርግ የመሞት ዕድሌ ቢያንስ ሃማሳ ለሃምሳ ነው። ከአልሆነልኝ መንገድ ላይ እሞታለሁ። ከተሳካ ደግሞ አውሮፓ እገባለሁ። እኔ ሞትን አልፈራም። ከፈለገ ደግሞ የማይቀረው ሞት ይምጣ!“ ብሎአል።

ሰዎች ተጨንቀው ይህን የመሰለ ደረጃ ላይ ደርሰዋል:- ሞትን የመጣው ይምጣ አልፈራውም እስከ ማለትም ሄደዋል።

ለምን አንድ ሰው በሕይወቱ ላይ ይፈርዳል?

ይህን ስንመለከት ጥፋተኛው ማን ነው ሊባል ነው?

እንደሚባለው የጣሊያን መንግሥት? ወይስ የአውሮፓ አንድነት ድርጅትና የአውሮፓ መንግሥታት? …ወይስ ደግሞ ምንም ነገር ወሃው ላይ ብታዩ አትርዱ የተባሉ ዓሣ አጥማጆች? ለመሆኑ ቀይ መስቀልም ጥፋተኛ ነው?

ዋና ተጠያቂ እላይ የተጠቀሱ አገሮች መሪዎች ናቸው። እነሱ ያቋቋሙት አስተዳደር።

ለምንድነው የጀርመን ኑዋሪዎች ተሰደው በመርከብ ሲጓዙ ሰመጡ የሚለውን ዜና ጥዋት ማታ በራዲዮ የማንሰማው? ለምንድነው አንድ አሜሪካዊ ወደ አፍሪካ በጀልባ ሲሸሽ ተገልብጦ ሞተ የሚባለው ወሬ በቴለቪዥን የማይነገረው? ለምንድነው አንድ እንግሊዛዊ ወይም የራሻ ስደተኛ ተወላጅ የሚድትሬኒያን ባህር ሲያቋርጥ ወይም ሰሃራ በረሃ ላይ ሲጓዝ የአፍሪካ አውሬ አንበሳ በላው በላቸው የማይባለው?

Page 31: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 31 ~

አሁን አይደለም ዱሮ ብልሃቱ ገና በአልገባቸው ክፍለ-ዘመን…. እንግሊዞች፣ ጀርመኖች፣ ጣሊያኖች፣ አይሪሾች፣ ግሪክና ፈረንሳዮች፣ ፖሊሺና …ድፍን አውሮፓ ረሃብ ገብቶ ሲጠብሳቸው፣ ችግር ሲያጠቃቸው፣ አረመኔ መንግሥት ሲገፋቸው፣ … መንደራቸውን ለቀው ተሰደው አሜሪካን ገብተዋል።

ስንቱን ያኔ ወሃ እንደበላው አናውቅም። ስንቱ በበሽታ እንደተቀሰፈ አናውቅም። ስንት ሴቶቹ እንደተደፈሩ የተጻፈ ታሪክ በእጃችን የለም። ወንዶች ሲደፈሩ ስንሰማ ግን የመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በኢትዮጵያ ፓስፖርት የዛሬ አርባና ሃምሳ አመታት ማንም እንደሚንቀሳቀስ ተንቀሳቅሶም አውሮፓ እንደሚጋባ በደንብ እናውቃለን። ይህን ዕድል ከአገኙት ውሰጥም የአሁኑ የአሥመራ ገዢዎች እንዳሉበት የታወቀ ነው።

በዚህ ፓስፖርት የኢትዮጵያ ተወላጅ ግሪኩም አርመኑም ሕንዱም ፓኪስታኑም የአፍሪካ ታጋዮችም ጭምር ማንም ሳይጠይቃቸው በይፋ በመርከብና በአይሮፕላን ይንቀሳቀሱ፣ ከዚያም አልፎ የዓለም አቀፍ ድርጅትም ውሰጥ ገብተው ይሰሩ እንደነበር ይታወቃል።

በኢትዮጵያ ፓስፖርት -የዛሬውን አያድርገው ያኔ ጀርመን አገርና ሌላ የአውሮፓ ከተማዎች አለ ቪዛ ይገባም ይወጣም ነበር።

ያ ዘመን ምን ይደረጋል:- አልፎአል።

አሁን „ሰው ሁሉ“ አገሩን ለቆ ሲወጣ ተጠያቂው ማን ነው? ለምንድነው አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱበት ምክንያት?

ቁም ነገሩ ያለው እዚያ ላይ ነው። መልሱን ደግሞ ፈልጎ ለማግኘት ቀላል ስለሆነ ሁላችሁም ታውቁታላችሁ። ይህ ሁኔታ በጊዜው ካአልታረመ ነገ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እድላቸውን ሲሞክሩ መሞታቸው አይቀርም።

ሞት ለላምፔዱዛ

ሞት በላምፔዱዛ፣ ሞት ለነጻ ሕይወት! ለነጻ-ኑሮ!

Source: http://www.stern.de/panorama/mittelmeer-vor-italien-kuestenwache-rettet-800-fluechtlinge-2066861.html

Page 32: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 32 ~

ዓለም እንዴት ሰነበተች

Published October 23, 2013 at 223 × 226 in ዓለም እንዴት ሰነበተች

ዓለም እንዴት ሰነበተች

ውድ አንባቢ

የሚያበረታቱና ተስፋ የሚሰጡ ዜናዎችን ከአፍሪካ እንሰማለን። በእዚያው

መጠን የሚያስደነግጡና የሚያሳዝኑ ወሬዎችንም እናዳምጣለን።

አሰዛኙን አቆይተን፣ በጥሩ ዜና እንጀምር።

አምባገነኑ የቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ቻርልስ ቴለር በሰራውና

በአደረገው ጥፋት የተፈረደበትን የሃምሳ አመት እሥራት ቅጣት “አለልክ

በዛብኝ” ብሎ “ጉዳዩ እንደገና እንዲታይለት ያቀረበው የይግባኝ ማመልከቻ

ውድቅ ሆነ“ የሚለውን ዜና እናስቀድማለን።

„ሞገደኛው ቻርልስ ቴለር“ እንደ ኬንያው ኡሁሩ ኬንያታና እንደ ምክትል

ፕሬዚዳንቱ የዴንሃጉ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ኢሰበአዊ ሥራ በአገራችሁ

ሰራችሁ ተብለው ከተከሰሱት የአፍሪካ መሪዎች አንደኛው ናቸው።

ሁለተኛው ዜና “ድርጅት መስረታችሁ በኮንጎ ውስጥ ጦርነት ከፍታችሁ ሴቶች

ትደፍራላችሁ፣ ንብረት ታወድማላችሁ፣ ሕዝብ ታፈጃላችሁ፣ ለአቅመ አዳም

ያልደረሱ ወጣት ሕጻናት አስገድዳችሁ ታዋጋላችሁ፣ ባንክ ትዘርፋላችሁ፣ … ”

ተብለው እዚህ ጀርመን አገር ስለተከሰሱት ቡድኖች እናነሳለን።

Page 33: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 33 ~

በሦስተኛ ደረጃ በቻይና እንደትልቅ የሕብረተሰቡ ማስተካከያ ሜካኒዝም እንደ

ትልቅ ቁም ነገር በአገሪቱ ከማኦ ጊዜ ጀምሮ ስለተስፋፋው „ የሒስና የግለሒስ

ዘመቻም“ አንስተን ይህ ነገር አንድን ሕዝብ አንድን አገር ወዴት እነደሚወስድ

እንመለከታልን።

„አሁን እኛን ምን አግብቶን የቻይና ፖለቲካ ውስጥ ገብተን እንፈተፍታለን?

…ምንስ አገባን ?“ ሊባል ይቻላል።

ቻይና እንደሚታወቀው የብዙዎቹ የአፍሪካ መሪዎች አረያና ሞዴል ናት።

በመሆኑዋም „ሙስናን ለመዋጋትና በሥልጣን መባለግን ለመቆጣጠር“

አብዛኛው የአፍሪካ መሪዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች “በነጻ-ፍርድ ቤትና በነጻ-

ጋዜጣ” ይህን ችግር ከመቆጣጠር ጊዜአቸውን እንደ ቻይና የኮሚኒስት ፓርቲ

“በሒስና በግለሒስ፣ በሴሚናርና በውይይት” እንደሚያጠፉ አብዛኛዎቻችን

እናውቃለን።

አራተኛው – ይህ ነው የሚያሳዝነው ዜና- ዱሮ „በደጉ ዘመን፣ በንጉሡ ጊዜ“

በኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮርተው የትም መንቀሳቀስ የሚችሉ ኢትዮጵያውያኖች

(ዛሬ ኤርትራውያኖች) ያ የተመኙትና ያ የአለሙት የዲሞክራሲ ሕልም

ሳይሳካላቸው ቀርቶ በስደት ጉዞ ላምፔዱሳ ላይ መሞታቸው አንድ ሐተታ

እንድንጽፍ ገፋፍቶናል።

ዓለም እንዴት ሰነበተች እንጀምር።

ዓለም እንዴት ሰነበተች

አዲስ ሰው ምንም የማያውቅ ባልሆነ አስተሳሰብ ያልተበከለ „ንጽህ ሰው

እንፈጥራለን“ የሚለው የአንዳንድ „አብዮተኞች በሽታ“ ረጅም ዕድሜ አለው።

ከአለባበስ በአንዳንዶቹ ይጀምራል።ከአነጋገር፣ ከአጠራር፣ ከሰላምታና እራሱ

የእጅ አነሳስንም ያካትታል።

ኮሊታ የለው የማኦና የስታሊን አለባበስ፣ የሌኒን ኮፊያ፣ የሒትለርና የሞሰሊን

ሰላምታን እነዚህን ሁሉ ያጠቃልላል።

Page 34: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 34 ~

የሰሜን ኮሪያ የጠጉር አቆራረጥ፣ የኡልብርሽትና የእነሆኔከር የድምጽ አጣጣልና

አነጋገር፣ የታሊባን ጢም፣ የአራፋትና የክሜር ሩጅ የአንገት ልብሶች እነዚህ

ሁሉ:- አንዳዶቹን ለመጥቀስ በዓይን የሚታዩ ነገሮች ናቸው። በእኛም ሀገር

አንዳዶቹ ትልቅ ዲስኩር ሲያደረጉ የእጅ አወራወሩ ወደዚያው ተጠግቶአል!

ይህም ነገር ኢትዮጵያና ኢራን፣ኒካራጉዋና ቦሊቪያ፣ ሌላም አካባቢና ቦታ

(ይኸው ሠላሣም አርባም አመት ይሆነዋል) ዘልቆ ገብቶአል። ከእሱም ጋር

„ሒስና ግለሒስ“ (ደግሞም፣ ግምገማ እራስን ማጋለጥ በሚባል ስምም እኛ

ዘንድ በአዲስ ስም ተጠምቋል) የሚባለው ነገር፣ እነማኦ ሴቱንግ በነጻ-ፍርድ

ቤትና በነጻ-ዳኛ ፋንታ ለቻይና (ለዓለምም) ያስተዋወቁት የችሎት ፍርድም

ከዚያም ተንደርድሮ፣ ዳኞችን ሥራ ፈት ለማድረግ አፍሪካ ገብቶአል።

ሃሳቡን ያፈለቀው „ ጸረ-ኮሚኒስቶቹን” እሱ እንደሚለው ” ከፓርቲው

ለማጽዳት“ በዚያም ሳቢያ ብቻውን ለመግዛት የተነሳው ዮሴፍ ስታሊን ነው።

ስታሊን በዚህ ሥራው በሚሊዮን የሚቆጠሩ „ጓደኞቹን“ በጅምላ በአደባባይና

በራዲዮ እያስለፈለፈ ፈጅቶአል።

የማኦ „ሒስና ግለ ሒስ“ ለማታለል ለየት ያለ ይመስላል። ግን እሱም ቢሆን

አብረው ከጎኑ ሁነው ጃፓንን የታገሉትን ጓደኞቹን ሳይቀር በግለ-ሒስ ስም

„አምናችሁ ጥፋታችሁን ከተቀበላችሁ ትፈታለችሁ፣ ድርጅቱም ይቅርታ

ያደርግላችሁዋል „ እየተባሉ፣ እንደተመዘገበው „በብዙበሚሊዮን የሚቆጠሩ

ቻይናዎች በፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሳይታይ፣ ጥፋታቸው ሳይመረመር በጥይት

ተደብድበው አልቀዋል።“

ሌሎቹ በአደባባይ ተወግረው እዚያው ወድቀው ቀርተዋል። ማኦ በዚህ በዚያ

በታሪክ „የካልቸራል አብዮት“ የሚባለውን ስም ባተረፈው ዘዴ ከሚስቱና

ከጓደኞቹ „ተገላግሎ“ ሥልጣኑን አጠናክሮ ወጥቶአል። አይረሳም ደረታቸው

ላይ “እኔ ጸረ-አብዮተኛ ነኝ ” የሚል ሰሌዳ አሸክሞ እንደ ከብት ሰውን መንገድ

ላይ ማኦና ተከታዮቹ ነድተው መሳቂያ መሳለቂያ አድርገው በሁዋላ

ረሽነዋቸዋል።

Page 35: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 35 ~

እሱ ማኦ ከሞተ በሁዋላ በሩሲያ ኩሩቾብ ስታሊንን እንደተቸው፣ በአደረገው

ድርጊቱ በኮምኒስት ፓርቲው ማኦም ተተችቶአል። ግን ሁሉም እንደተመኙት

በዚያ አላቆመም።

ለዘመናት ይህ „ሒስና ግለሒስ „ የሚባለው የአሰራር ዘዴ ተረስቶ ከከረመ

በሁዋላ አሁን ከፔኪንግ እንደምንሰማው፣ እዚህ የሚጻፉትም ጋዜጣዎች

እንደሚመሰክሩት „በዚህ ወራት በትልቁ በቻይና የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ

በሊቀመንበሩ በሺ ጂንፒንግ ሰብሳቢነት ሥር ትላልቅ መሪ የአገሪቱ ካድሬዎች

የተለመደውን የሒስና ግለሒስ ለቅሶ ማዥጎድጎድ „ ጀምረዋል።

የቻይና አመራር የተረሳውን እንደተለመደው „የጥፋት ሙሾ በቴሌቭዢን

ለማውረድ ተሰባስቦአል“ በሚለው አርዕሰቱ ሥር „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“

የተባለው የጀርመኑ ዕለታዊ ጋዜጣ የሚከተለውን ቁም ነገር ለአንባቢዎቹ አምዱ

ላይ እንዲመለከቱት አስፍሮአል።

„አንደኛው አገረ ገዢ የእራሱን ገደብ ባለማወቅ“ ይኸው ጋዜጣ እንደሚለው

እሱ በሰጠው ግለ-ሒስ ሙሾው „…ልቡን አሳብጦ፣ ሌላውን የሚንቅ ጥጋበኛ

ፖለቲከኛ እራሱን አድርጎ፣ ያይ እንደነበረ“ አትቶ፣ ወደ ሌለው ዞር ብሎ፣

የቅስቀሳና የፕሮፓጋንዳው ኃላፊ ደግሞ „በመንግሥትና በሕዝብ ሐብት ምን

የመሰለ ቅልጥ ያለ ድግስ እየደገሰ ገንዘብ እንደሚያባክን ተጸጽቶ፣ እራሱን

እሰከማጋለጥ ድረስ ሄድዋል…“ ይኸውጋዜጣ ይለናል።

በሦስተኛ ደረጃ የፓርቲውን ዋና ጸሓፊ ጠቅሶ የሚከተለውን አረፍተ ነገር

አስቀምጦአል።

„…ጥርሱን እየነከሰ ተጸጽቶ” በአደረገው ንግግር ” በዚያ ትልቁና ምቾት በአለው

ላንድክሩዘር አውራጎዳናውን እየሰነጠቀ ሲከንፍ ምንኛ ደስታ ይሰማው

እንደነበረ ካድሬው አስታውሶ አሁን ግን በሥራው አፍሮ…ተናዞአል…“ በሚለው

አመለካከቱ አዚያ ያየውንና እዚያም የሰማውን „ቲያትር“ ለአንባቢዎቹ

አቅርቦአል። ወደው ይሆን ተገደው?

ወረድ ብሎ ነገሩ በዚያ ተጀመረ እንጂ አላለቀም ይለናል።

Page 36: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 36 ~

በቴሌቭዢን የተጀመረው የኮሚኒስቶቹ ሙሾ ማውረድ ወደ ዕለታዊ ጋዜጣ

ተሸጋግሮ፣ “ ከሁናንና ከዩናን እንዲሁም ከቾንግቺንግ ከተማዎች“ የሚከተሉትን

አረፍተነገሮች ጸሃፊው አነበብኩ ይለናል።

„እንባ እየተናነቃቸው፣ በሰሩት ሥራዎቻቸው አፍረው ሁሉም ካድሬዎች

ድርጊታቸውን፣ የቻይና ሕዝብ ጋዜጣ እንደጻፈው፣ ዘክዝከው አውጥተዋል።“

ዓላማው በአንድ በኩል በሕዝብ ዘንድ እየተጠላ የመጣውን የኮሚኒስት ፓርቲና

አባሎቹን አንዴ ሊቀመንበር ማኦ እንደአደረጉት ሊቀመንበር xi Jinpingም

ደግመው ከተነጣጠረባቸው ኢላማ „በሥልጣን መባላግ፣ በሙስና መጨማለቅ፣

…ጦር አውጄአለሁ ብለው“ ለማምለጥ ነው።

ሌላው ማኦ እንደደረገው -ይኸው ጋዜጣ እንደጻፈው- እግረመንገዳቸውንም

ተቃዋሚዎቻቸውን በዚህ ዘመቻ ሳቢያ፣ አለፍርድ ቤት ክስ፣ አለ በቂ ምርመራና

አለ ማስረጃ፣አለ ጠበቃ “ጥፈተኛ ናችሁ” ተብለው ተጠራርገው እንዲወጡ

ለማድረግና ከእነሱም በዚህ ዘዴ በአጭሩ ለመገላገል ነው።

ሙስና ሆነ በሥልጣን መባለግን፣ ለመቆጣጠር፣ መልካም አስተዳደርና

ዲሞክራሲን ለማምጣት ይህ ነው የታሪኩ ሞራል „…ሂስና ግለ -ሂስ“ እንደ ሙሾ

በቴሌቪዥን ላይ እያለቀሱ ማውረድ ሳይሆን መድሐኒቱ „…ነጻ-ፍርድ ቤት፣ ነጻ-

ጋዜጣ ፣ ነጻ ሕዝብና ነጻ ውይይት፣ ነጻ- ምርጫና…ነጻ-ትችት…“ በአንድ አገር

ማካሄድ ሲቻል ብቻ ነው።

“ጥፋተኛ ተብሎ የተጠረጠረውም ሰው” ጥፋቱ በነጻ-ዳኛ በፍርድ ቤት ታይቶ

ፍርዱን እሰከሚቀበል ድረስ-የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ የሰበአዊ

መብት አዋጅ እንደሚለው-ይህ ሰው “ጥፋተኛ አይደለም።”

ሙስናንና በሥልጣን መባለግን ለመቆጣጠር (ሌላ ነገር ከጀርባው እስከሌለ

ድረስ) እንደሚባለው “በሒስና በግለ ሒስ” አገር የቀናበት ቦታ የለም። የነፍስ

አባት ጋ አለጠበቃ ተኪዶ “ንሰሃ መግባት”ይቻላል። እሱ ግን ሌላ ዓለም ነው።

እኛ የምንኖርበት ዓለም አለ ነጻ ጠበቃ አለ ነጻ-ዳኛና ፍርድ ቤት አለ ግልጽ የሆነ

የዲሞክራቲክ ጨዋታና ሕጎች፣አለ ነጻፕሬስ እና አለ ነጻ ዜጋ ትርፉ የጥቂት

አምባገነኖች “ራት” መሆን ነው።

የታሪኩም ሞራል የተባለውን ለመድገም ይህ ነው።

Page 37: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 37 ~

አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

Published October 28, 2013 at 495 × 544 in አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

በሰሜን አፍሪካ በግብጽ የሚካሄደውን የፖለቲካ ውዝግብ ጋዜጠኖቹ ሳይረሱ፣ በማሊ የሚታየውን ትርምሶች ችላ ሳይሉ፣ ኮንጎን አይተው ሳያልፉ፣ ጅቡቲን ሳይዘሉ፣ ትላልቅ እዚህ አውሮፓና እዚያ አሜሪካ በየቀኑ እየታተሙ የሚወጡ ዕለታዊ ጋዜጣዎች፣ ያለፈው ወር „ድፍን ኬንያን ስለአናጋው“ የሽብር ፈጣሪዎች ጠለፋና ግድያ፣ ፍጅትና የቦንብ ፍንዳታ፣ ልዩ አተኩሮ ስጥተው ሁሉም ቅጠሎች ስለዚህ ጉዳይ በሰፊው ጽፈዋል።

Page 38: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 38 ~

ከዚሁም ዜና ጋር የሞገደኛውን -እዚህ እንደጻፉት-የቀድሞውን የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት የቻርልስ ቴለርን ሃምሳ አመት የእሥራት ፍርድ፣ ቦታውን ተሻምቶም እንዲወስድ አድርገዋል።

ስለሱዳን አመጽ አንስተዋል።በጎረቤት አገር በሱዳን የዋጋ መወደድን፣ የቤንዚን መጨመርን፣ ከዚያም አልፎ „የወታደሩ መንግሥት የፕሬዚዳንት አልባሽር አገዛዝ በቃን „የሚለውን „ሕዝብ እንቅስቃሴ“ የእነሱንም ታሪክ እነዚሁ ጋዜጠኞች ተገቢውን ቦታ ሰጥተው እኛን አስደስተዋል።

በቻርልስ ቴለር ላይ የቀረበው ዘገባና ሐተታ አንጀት ያርሳል። እሱም ይህን ይመስላል።

„ሃምሣ አመት ለቻርልስ ቴለር“ በሚለው አርዕስቱ ሥር የጀርመኑ ጋዜጣ ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ የሚከተሉትን ሓሳቦች ለአንባቢዎቹ በሐተታ መልክ አምዱ ላይ አሥፍሮ አንባቢዎቹ እንዲመለከቱት እነሱን ጋብዞአል።

„…የሕዝብ ድምጽና የሕዝብ ጩኸት፣ በላይቤሪያ ሰውዬውን ቀደም ሲል በትክክል ወንጀለኛ ነው ብሎ መስክሮበታል።“ ከአለ በሁዋላ ጸሓፊው ቀጥሎ„…ቻርልስ ቴለር ጦረኛ እና ሥልጣን የጠማው ሰው ነው።ከዚያም በላይ ይህ ሰው ጠብ ጫሪና እሳት ለኳሽ አደገኛ ፍጡር ነው፣ የሚለውን የቅጽል ሽሞች በግዛት ዘመኑም እሱ ያተረፈ ሰው ነው። ስለዚህ „ ይላል ጋዜጣው „…ፍርድ ቤቱ የተከሣሹን የይግባኝ ማመልከቻውን ተመልክቶ ውድቅ ማድረጉ፣ የሃምሣ አመት የእሥራት ፍርዱን ሳይሽርና ሳይቀንስ እሱን መልሶ አረጋግጦ በይኖበት አሁን ይፋ ማውጣቱና ይህን ማሳወቁ ትክክል ነው።…ፍርድ ቤቱ ግን …እግረ-መንገዱን በመረጃ ስብሰባ ላይ በርካታ የሚያጠያይቁ ክፍት የሆኑ ነገሮችን ማስተካከል መቻል ነበረበት።ይህን ግን አላደረገም። …ያም ሆኖ …ይህ በቻርልስ ቴለር የተበየነው ፍርድ ማንም የአፍሪካ መሪ እራሱን ከሕግ በላይ አድርጎ፣ በገዛ ሕዝቡ ላይ ከእንግድህ መጨፈር አይችልም።ፍርዱ ይህንንም ያሰየናል።“ ብሎ ጸሓፊው ሐተታውን በዚህ ዓረፍተ-ነገር ዘግቶአል።

„ሳይሽሩ፣ ፍርዱንም ሳያሻሽሉ…“ ሌላው የጀርመን ጋዜጣ „ዲ ኖየ ኦስናብሩከር“ ቀጠል አድርጎ እንዳለው“… እዚያው ብያኔ ላይ ዳኞቹ በመርጋታቸው ከእንግዲህ በምንም ዓይነት ወለም ዘለም የማይለውን አቋማቸውን ለሁላችንም ግልጽ አድርገውልናል።…ከእንግዲህ አንድ ጦረኛ እና አንድ ዲክታተር፣ አንድ አምባገነን ሥርዓት ወደፊት አለ ፍርድና አለቅጣት በሰራው ሥራ ሳይጠየቅበትና ፍርድ ቤት ሳይቀርብ አርፎ መተኛት እንደማይችል፣ ዳኞቹ ተስማምተው በወሰዱት

Page 39: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 39 ~

እርምጃ በአሳዩትም ጥንካሬ ጥሩ አድርገው መጪውን ጊዜ ወዴት እንደሚያመራ ግልጽ አድርገዋል።…

በአለፉት አመታት በአፍሪካ ለረጅም ጊዜያት አምባገነኖችን ማንም ሰው ሳይከሳቸውና እነሱንም ማንም ሰው ፍርድ ቤት ሳያቀርባቸው የፈለጉትን ሥራ ሰርተው የልባቸውን አድርሰው ተቀምጠዋል። አሁን ግን በቻርልስ ቴለር ላይ በተወሰደው ቆራጥ ፍርድ፣ ይህ ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሰሪያውን አግኝቶአል።

ይህ እራሱን አንዴ ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ከእሱም ገድላና የተአምር ሥራዎች ጋር የእራሱን ሥራ ድርጊትና ያወዳድር የበበረ ሰው አሁን ፍርዱን ተቀብሎአል…“ ብሎ በዚህ ሐተታው ከአንባቢዎቹ ተሰናብቶአል።

„ደር ሽፒግል“ የተባለው ትልቁ የሰሜን ጀርመን ሳምንታዊ መጽሔት ደግሞ በተራው „በዲሞክራቲክ የሩዋንዳ ነጻ-አውጪ ስም“ እዚህ ጀርመን አገር በስደት ላይ የሚገኘውን እዚያ በአገሩ- ክሱ እንደሚለው – የጦር እንቅስቃሴ የሚያካሄደውን የሽምቅ ተዋጊዎች ጦር ከእነድርጅቱ ትመራለህ ተብሎ ለተከሰሰው ለአንድ የሩዋንዳ ተወላጅ ዶክተር ኢግናስ ሙሩዋናሽያካ መጽሔቱ አምዱን ለግሶ ታሪኩን እንደዚህ አድርጎ አቅርቦአል።

„..ለአቅመ-አዳም ያልደረሱ ለጋ ወጣቶችን በማሰለፍ፣ ሴቶችን በመድፈር፣ የጦር እሳት በአገሪና በጎረቤት አገር በኮንጎ በመለኮስ ግዲያና ዝርፊያ በማካሄድ አንድ ትልቅ ሚና ትጫወታለህ ተብሎ ይህ ሰው ጀርመን አገር መከሰሱን መጽሔቱ ለአንባቢዎቹ ጽፎአል።

ወረድ ብሎም „በዚህ ኢ-ሰበአዊ ሥራቸው፣ ድርጊታቸው ከፍርድ ያመለጡ የሚመስላቸው ሰዎች መዝናኛ ቦታ እዚህ አውሮፓ እንደሌላቸው“ ከሌሎቹ ጋዜጣዎች ጋር በዚህ ወራት ይህን የመሰለ ታሪክ አምዱ ላይ አስፍሮ እሱም እንደተለመደ ከአንባቢዎቹ ተሰናብቶ ዞር ብሎአል።

ኒዮርክ ታይምስና ዋሽንግተን ፖስት፣ ዘኢንዲፔንደንተና ሔራልድ ትሪቢውን“…ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አገራቸው የገባችበትን ችግርና ቀውስ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ተገንዝቦ በእሳቸው ላይ የተመሰረተውን የፍጅት ክስና የቀጠሮ ቀናቸውን ፍርድ ቤቱ እንዲያስተላልፍላቸው የጠየቁት ጥያቄ ሰሚ ጆሮ አጥቶ ውድቅ ፍርድ ቤቱ እንደ አደረገው“ ዘግበዋል።

ሌሎቹ እዚሁ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ዴንሓግ የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ተጋብዘው ይህንኑ ቃላቸውን በመስጠታቸው በአገራቸው በኬንያ

Page 40: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 40 ~

የማስፈራሪያ ዛቻ በእነሱና በዘመዶቻቸው ላይ ስለወረደባቸው ምስክሮች በሰፊው ጽፈዋል።

ፍርድ ቤቱም ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ እንደጻፈው „…የምስክሮችን ደህንነት ለመጠበቅና የፍርድ ቤቱንም የምርመራ ሥራ ሳይሰተጓጎል በሥነ-ሥርዓቱ ለማካሄድ አስፈራሪ ሽብር ፈጣሪዎችን ኬንያ ድረስ ወርዶ እነሱን አሳዶ ለቅሞ እዚሁ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት አቅርቦ እነሱን ለመቅጣት አንድ ውሳኔ ላይ እንደደረሰም“ አያይዞ ዜናውን አንስቶአል።

የአስፈራሪ አምባገነኖች ዘመን በዚህ እርምጃ ቢያንስ የታገደ ይመስላል።

ፍርድና ፍትህ „የሰበአዊ መብቶች መግለጫ“ ላይ እንደ ሰፈረው ዓለም አቀፋዊ እየሆነ የመጣም ይመስላል።

***

Page 41: ለ አእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 3

~ 41 ~

እምቢ በል!

Published October 17, 2013 at 1240 × 150 in እምቢ በል!

ማን ነው የሚለየው!

*ማን ነው የሚለየው፣

ይኸም ትውልድ

ፍም እሳት ነው!

እምቢ በል! እምቢ በል! እምቢ ይላል!

እምቢ እምቢ እምቢ!

ዝናዬ ዝናዬ ኧረ ዝና!

http://www.youtube.com/watch?v=c340a89C8uo

ለአእምሮ / የጥቅምት 2006/October 2013 /ፍትህ ና ፍርድ/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 3