24
Ze-Habesha Newspaper / October 2015 No. 79 612-226-8326 / [email protected] Voice of Ethio-Americans ጥቅምት 2008 ቅጽ VI ቁጥር. 79 [email protected] ዕውነት ያሸንፋል የ1966ቱ/የ77ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት መንግሥትም ሆነ ሰብአዊ ርኅራኄ የሚሰማን ዜጎች ሁሉ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል .... (6) የቀድሞው የሕወሓት ጀነራል ፓርላማው ይፍረስ አሉ የጨጓራ ባክቴሪያ ማርሻል የማን.ዩናይትድ አለኝታ ገጽ 16 ላይ ገጽ 6 ላይ ገጽ 21 ላይ በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ሸጋ እንጀራ፣ ግሮሰሪና መጋገሪያ Shega Foods የፍስክ እና የጾም ምግቦችን ቱጎ አድርገው ለመውሰድ ወደ ሸጋ ይደውሉ ሸጋ 100% የጤፍ እንጀራን ከየሱቁ ይጠይቁ በሸጋ ግሮሰሪ፡ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ ባህላዊ እቃዎች፣ ጤፍ፣ የስልክ ካርድ፣ መጽሐፍት፣ ሲዲዎች ሁሉም ይገኛሉ 2111 E Franklin Ave, Mpls, MN 55406 (612) 341-4373 የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ቤት መግዛት ከፈለጉ አክሎግን በቅድሚያ ያማክሩ 900 American Blvd E Ste 206, Bloomington, MN 55420 አርበኞች ግንቦት 7 ሚኒሶታ ደረሰ ነአምን ዘለቀ ከአስመራ መልስ የአርበኞች ግንቦት 7ን ወቅታዊ የትጥቅ ትግል ለማስተዋወቅና ለገቢ ማሰባሰብ የክብር እንግዳ ሆነው ሚኒሶታ ይመጣሉ ቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስቱ መሻሻል አለበት አሉ (ዘ-ሐበሻ) መሪዎቹን ትግሉ ያለበት ሜዳ ያገኘው አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ውጭ ሃገራት የሚያደርጋቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን ቀጥሎ አሁን ተራው ሚኒሶታ ሆኗል:: በሚኒሶታ በአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በክብር እንግድነት የሚገኙት የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትና በቅርቡ ከአስመራ የተለመሱት አቶ ነአምን ዘለቀ ናቸው:: የቀድሞው የጥምረት አመራር የአሁኑ የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ነአምን ከአስመራ መልስ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ በተለይ የትህዴን መሪ የነበረው አቶ ሞላ አስገዶም ከድቶ ኢትዮጵያ መግባቱ በተለይ በቅርቡ በተመሰረተው ሃገር አድን ንቅናቄ ላይ የፈጠረው ነገር የለም ማለታቸው ይታወሳል:: “ሞላ ካጎደለው ያሞላው” እንዲሉ አቶ ነአምን በዚህ ቃለምልልሳቸው አርበኞች ግንቦት 7 - ከአፋር ድርጅቶች እና ከትህዴን ጋር በመሰረተው የሃገር አድን ንቅናቄ የተመሰረተው ..... ሙሉውን ዝርዝር በገጽ 3 ላይ ያንብቡት:: ከ10 ዓመት በላይ በሚኒሶታ ቤት በማጋዛት የከበረ ሥም ያለው የቀድሞው የአገዛዙ ፕሬዝዳንት እና ተቃዋሚው የቀድሞው አንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኢትዮጵያ ስራ ላይ ያለዋለውንና በሕዝቡ ጭምር ሕገ መንግስቱ ከተጻፈበት ወረቀት በላይ ዋጋ የለውም የተባለውን የወቅቱን ሕገ መንግስት የተወሰኑ አንቀጾች እንዲሻሻሉ ጠይቀዋል። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገ መንግስቱ ላይ ከመግቢያው ስለ ብሄር ብሄረሰቦች የሚሰጠውን ትንታኔ፣የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ፣ የውክልና ጉዳይና የሕገ መንግስቱ በፌዴሬሽን ም/ቤት መተርጎሞ እንዲቀር፣ በህገ መንግስቱ የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ያገኛል የሚለው እና ጉዳዩ ወደፊት በሕግ ይወጣል ተብሎ ዛሬም ድረስ አለመውጣቱን በመትቀስ ሕገ መንግስቱ መሻሻል አለበት ወቅት ላይ ነው ቢሉም ስልጣን የሌለው ሕዝብ እንዴት ሕገ መንግስት ሊአሻሽል ይችላል ለሚለው ግልጽ ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል። በተለያዩ አፍሪካ አገሮች የታየውን የአገዛዝ ስርዓቶች ከሕዝብ የሚመጣውን የለውጥ ጫና (ነጋሶ... ወደ ገጽ 12 የዞረ)

የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ [email protected] ዕውነት ያሸንፋል … · Ze-Habesha Newspaper / October 2015 No. 79 612-226-8326 / [email protected] Voice

  • Upload
    others

  • View
    36

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Ze-Habesha Newspaper / October 2015 No. 79 612-226-8326 / [email protected] Voice of Ethio-Americansጥቅምት 2008 ᴥ ቅጽ VI ᴥ ቁጥር. 79 [email protected] ዕውነት ያሸንፋል

የ1966ቱ/የ77ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት መንግሥትም ሆነ ሰብአዊ ርኅራኄ የሚሰማን ዜጎች ሁሉ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል.... (6)

የቀድሞው የሕወሓት ጀነራል ፓርላማው

ይፍረስ አሉ

የጨጓራ ባክቴሪያ

ማርሻል የማን.ዩናይትድ

አለኝታገጽ 16 ላይገጽ 6 ላይ ገጽ 21 ላይ

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት

ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ሸጋ እንጀራ፣ ግሮሰሪና መጋገሪያ

Shega Foods

የፍስክ እና የጾም ምግቦችን ቱጎ አድርገው ለመውሰድ

ወደ ሸጋ ይደውሉ

ሸጋ 100% የጤፍ እንጀራን ከየሱቁ

ይጠይቁ

በሸጋ ግሮሰሪ፡ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ ባህላዊ እቃዎች፣ ጤፍ፣ የስልክ ካርድ፣ መጽሐፍት፣ ሲዲዎች ሁሉም ይገኛሉ

2111 E Franklin Ave, Mpls, MN 55406(612) 341-4373

የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ

ቤት መግዛት ከፈለጉ አክሎግን በቅድሚያ ያማክሩ

900 American Blvd E Ste 206, Bloomington,

MN 55420

አርበኞች ግንቦት 7 ሚኒሶታ ደረሰ

ነአምን ዘለቀ ከአስመራ መልስ የአርበኞች ግንቦት 7ን ወቅታዊ የትጥቅ ትግል ለማስተዋወቅና ለገቢ ማሰባሰብ የክብር እንግዳ ሆነው ሚኒሶታ ይመጣሉ

ቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስቱ መሻሻል አለበት አሉ

(ዘ-ሐበሻ) መሪዎቹን ትግሉ ያለበት ሜዳ ያገኘው አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ውጭ ሃገራት የሚያደርጋቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን ቀጥሎ አሁን ተራው ሚኒሶታ

ሆኗል:: በሚኒሶታ በአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በክብር እንግድነት የሚገኙት የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትና በቅርቡ ከአስመራ የተለመሱት አቶ

ነአምን ዘለቀ ናቸው::የቀድሞው የጥምረት አመራር የአሁኑ የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ

የሆኑት አቶ ነአምን ከአስመራ መልስ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ በተለይ የትህዴን መሪ የነበረው አቶ ሞላ አስገዶም ከድቶ ኢትዮጵያ መግባቱ በተለይ በቅርቡ በተመሰረተው ሃገር አድን ንቅናቄ ላይ የፈጠረው ነገር የለም ማለታቸው ይታወሳል::

“ሞላ ካጎደለው ያሞላው” እንዲሉ አቶ ነአምን በዚህ ቃለምልልሳቸው አርበኞች ግንቦት 7 - ከአፋር ድርጅቶች እና ከትህዴን ጋር በመሰረተው የሃገር አድን ንቅናቄ የተመሰረተው ..... ሙሉውን ዝርዝር በገጽ 3 ላይ ያንብቡት::

ከ10 ዓመት በላይ በሚኒሶታ ቤት

በማጋዛት የከበረ ሥም ያለው

የቀድሞው የአገዛዙ ፕሬዝዳንት እና ተቃዋሚው የቀድሞው አንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኢትዮጵያ ስራ ላይ ያለዋለውንና በሕዝቡ ጭምር ሕገ መንግስቱ ከተጻፈበት ወረቀት በላይ ዋጋ የለውም የተባለውን የወቅቱን ሕገ መንግስት የተወሰኑ አንቀጾች እንዲሻሻሉ ጠይቀዋል።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገ መንግስቱ ላይ ከመግቢያው ስለ ብሄር ብሄረሰቦች የሚሰጠውን ትንታኔ፣የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ፣ የውክልና ጉዳይና የሕገ መንግስቱ በፌዴሬሽን ም/ቤት መተርጎሞ እንዲቀር፣ በህገ መንግስቱ የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ያገኛል የሚለው እና ጉዳዩ ወደፊት በሕግ ይወጣል ተብሎ ዛሬም ድረስ አለመውጣቱን በመትቀስ ሕገ መንግስቱ መሻሻል አለበት ወቅት ላይ ነው ቢሉም ስልጣን የሌለው ሕዝብ እንዴት ሕገ መንግስት ሊአሻሽል ይችላል ለሚለው ግልጽ ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በተለያዩ አፍሪካ አገሮች የታየውን የአገዛዝ ስርዓቶች ከሕዝብ የሚመጣውን የለውጥ ጫና (ነጋሶ... ወደ ገጽ 12 የዞረ)

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 2

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 3

ከ10 ዓመት በላይ በሚኒሶታ ቤት በማጋዛት የከበረ ስም ያለው

ነአምን ዘለቀ ከአስመራ መልስ የአርበኞች ግንቦት 7ን ወቅታዊ የትጥቅ ትግል

ለማስተዋወቅና ለገቢ ማሰባሰብ የክብር እንግዳ ሆነው ሚኒሶታ ይመጣሉ(ዘ-ሐበሻ) መሪዎቹን ትግሉ ያለበት ሜዳ ያገኘው

አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ውጭ ሃገራት የሚያደርጋቸው

የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን ቀጥሎ አሁን ተራው ሚኒሶታ ሆኗል:: በሚኒሶታ በአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በክብር እንግድነት የሚገኙት የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትና በቅርቡ ከአስመራ የተለመሱት አቶ ነአምን ዘለቀ ናቸው::

የቀድሞው የጥምረት አመራር የአሁኑ የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ነአምን ከአስመራ መልስ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ በተለይ የትህዴን መሪ የነበረው አቶ ሞላ አስገዶም ከድቶ ኢትዮጵያ መግባቱ በተለይ በቅርቡ በተመሰረተው ሃገር አድን ንቅናቄ ላይ የፈጠረው ነገር የለም ማለታቸው ይታወሳል::

“ሞላ ካጎደለው ያሞላው” እንዲሉ አቶ ነአምን በዚህ ቃለምልልሳቸው አርበኞች ግንቦት 7 - ከአፋር ድርጅቶች እና ከትህዴን ጋር በመሰረተው የሃገር አድን ንቅናቄ

የተመሰረተው ከአራቱ ድርጅቶች በተውጣጡ 300 ወታደሮች መሆኑን ጠቁመዋል::

ወደ ሚኒሶታ ቅዳሜ ኦክቶበር 17/2015 የሚመጡት አቶ ነአምን ለሚኒሶታ ሕዝብ አሁን አስመራ ያለውን ትግል ሁኔታ እንደሚያስቃኙ ይጠበቃል:: በዚህ ዝግጅት ላይም ለአርበኞች ግንቦት 7 ማጠናከሪያ የሚሆን ጨረታ ይደረጋል ሲሉ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል:: እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ በሚኒሶታ; በደቡብ ዳኮታ; በአይዋ እና በሰሜን ዳኮታ ስቴቶች ሳይቀር የዚህ ገቢ ማሰባሰብ ትኬቶች እየተሸጡ ነው:: በተለይም በርካታ ሕዝብ ባለ $100, ባለ $250 እና ባለ $500 ዶላር ትኬቶችን እየገዛ መሆኑንም አዘጋጆቹ ጠቁመዋል:: ይህን ትኬት መግዛት የሚፈልጉም በስልክ ቁጥር 651-621-4416 መደወል እንደሚቻል አዘጋጆቹ ገልጸው በሚኒሶታ ያሉበት ቦታ ድረስ ትኬቶቹን አምጥተው

እንደሚሸጡ አስታውቀዋል::አቶ ነአምን ዘለቀ በክብር እንግድነት የሚገኙበት ይህ

የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ቅዳሜ ኦክቶበር 17,2015 ከቀኑ 2:00 ሰዓት ጀምሮ የሚደረግበት አድራሻ

BEST WESTERN PLUS CAPITOL RIDGE

161 Saint Anthony Avenue St Paul MN 55103 ነው:: ዘ-ሐበሻ ይህን ዝግጅት በድረገጿ ላይ የምትዘግብ መሆኗን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ትወዳለች::

ሚኒሶታ የደረሰው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰብ በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች እንደሚቀጥል ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል::

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 4

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 5

እጅ የሚያስቆረጥም የጾም እና

የፍስክ ምግቦች

ከረምቡላን እና ፑልንየያዘ ብቸኛው

የወገን ባር በመሆኑ

በየወሩ ምርጥ ዘፋኞችን እና ታዋቂ ዲጄዎችን

ይዞ መገኘቱ

ከደንበኞች ጋር የቤተሰብ ያህል የሚቀራረቡት

ሠራተኞቻችን

ራስ ቁርጥዘወትር ሐሙስ፣ አርብ

ቅዳሜና እሁድራስ ወዲያው የታረደ

ቁርጥ ሥጋ

ከጠንክርአዋዜ ጋር ይዞ ቀርቧል

ስፖርትየእንግሊዝ፣ የስፔን እና የአሜሪካ ሶከር

ና ፉትቦል ጨዋታዎችን 17 በላይ ቲቪዎች

እናሳያለን

ድግስ አስበዋል?

ሠርግ፣ ልደት፣ ምርቃት፣

የግል ፓርቲ አለብዎት? ቦታ

አጣሁ ብለው ተቸግረዋል?

ራስ የተንጣለለ የታችኛው

ላውንጁን ያከራያል። ይም

ጡና ካለምንም

ጭንቅንቅ ይዝናኑበት

በምግቦቻችን ጥራትና በዋጋችን ተመጣጣኝነት የሚወዳደረን ሬስቶራንት የለም

የእረፍት ቀንዎን በሙዚቃና ስፖርት ጨዋታዎች እየተዝናኑ ተወዳጁን ቁርጥ ይመገቡ

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 6

Ze-Habesha Newspaper is Legally Registered in state of

Minnesota - USAFounded in December 2008

Publisher :- ZeHabesha LLC

ዋና አዘጋጅ:-

ሔኖክ ዓለማየሁ ደገፉ

Editor in Chief:-

Henok A. Degfu e-mail:- [email protected]

[email protected]

አዘጋጆች:- ሊሊ ሞገስ፣ [email protected]

ቅድስት አባተ አማካሪ፡- ዶር ዓብይ ዓይናለም

Zehabesha LLC

6938 Portland Ave, Richfield MN 55423

) 612-226-8326 www.zehabesha.com

www.facebook.com/zehabeshawww.twitter.com/zehabesha

“Journalism can never be silent: that is its greatest virtue and its greatest fault. It

must speak, and speak immediately, while the echoes of wonder, the claims

of triumph and the signs of horror are still in the air.”

Henry Anatole Grunwald

በሚኔሶታ - አሜሪካ የተቋቋመ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው ዓላማው የማህበረሰባችን የወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ መገኛ መሆን ነው።

ዘ-ሐበሻ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ድርጅት፣ ጎሳ፣ ያልወገነ፣ ነጻ ጋዜጣ ነው፡፡

ዓብይ መልዕክት

በዲ/ን ኒቆዲሞስ እኛ ኢትዮጵያውያን ለረሃብ ክሥተት በፍጹም እንግዶች

አይደለንም፡፡ ጠኔ-ችጋር ደግሞ ደጋግሞ የጎበኘን፣ ረሃብ ስማችንን ያጎደፈብን፣ በሃፍረት አንገታችንን ያስደፋን፣ ቅስማችንን የሰበረን፣ ታሪካችንን ያጠለሸብን፣ የእልቂት፣ የሰቆቃ፣ የደም ምድር- ‹‹አኬል ዳማ›› በሚል የሚያሰቅቅ ስያሜ የተጠራን፣ መላው ዓለም በኀዘን ከንፈሩን የመጠጠልንና እንባ የተራጨልን ምስኪን ሕዝቦች ነን፡፡ ከዚህ አገራችን ለዘመናት ከተጎናጸፈችው እጅጉን ከምናፍርበትና ከምንሳቀቅበት ዓለም አቀፋዊ ገጽታ ጋር በተያያዘ በዛሬው መጣጥፌ ይዋል ይደር ሳንል ጊዜ ሰጥተን እንመካከር ዘንድ ዘንድሮ በዝናም እጥረት በአገራችን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለረሃብ ስለተጋለጡት ሚሊዮኖች ወገኖቻችን እስቲ አብረን ትንሽ እንቆዝም፡፡ በዚህች ቅጽበት ምናልባት አውቀነውም ይሁን ሳናውቅ በብዙ ትርፍና ባላስፈላጊ ወጪ በመዝናናት በጥሩ ምቾትና ድሎት ላይ ያለነውንና በማንኛውም ልኬት ሰዎች ለተባልን ሁሉ ፊታችንን መለስ አርገን ሚሊዮኖች ወገኖቻችን ለረሃብ ስለተጋለጡበትና በየአሥር ዓመቱ ብቅ እያለ ቤተኛው ስላደረገን የረሃብ ጉዳይ ላይ በጋራ እንወያይ ዘንድ ወደድኹ፡፡

እንደ መግቢያም ዛሬም ድረስ ሳስታውስው እጅጉን ከሚያሳዝነኝ ከአንድ ገጠመኜ ጽሐፌን ልጀምር፡፡ በደቡብ አፍሪካ የአርትና የባህል ሚ/ር፣ ማንዴላና የትግል ጓዶቻቸው ለ፳፯ ዓመታት በተጋዙበትና በዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት በተመዘገበው በሮቢን ደሴት የነጻነት ሙዚየምና እና በኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን ትብብርና የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጠውን ‹‹የአፍሪካ ቅርስና ቱሪዝም ጥናት የድኅረ ምረቃ/የፖስት ግራጁየት የትምህርት ፕሮግራም›› የስኮላር ሺፕ ዕድል አግኝቼ ትምህርቴን በተከታተልኩባት በኬፕታውን ከተማ በሮቢን ደሴት ሙዚየም የሆነ ገጠመኜ ነው፡፡

የዩኒቨርሲቲ ትምህርታችንን ከመጀመራችን በፊት የትምህርት ክፍላችን አስተባባሪ የሆነው ናይጄሪያዊው ጎልማሳ ከተለያዩ አገራት የመጣን ተማሪዎችን እርስ በርሳችን እንድንተዋወቅና እንዲሁም ይህን የነጻ የስኮላር ሺፕ ትምህርት ዕድል ለሰጠን ማንዴላና የትግል አጋሮቻቸው ለጥቁር ሕዝብ ነጻነት፣ ለሰው ልጆች መብትና እኩልነት ሲሉ ለበርካታ ዓመታት ቃላት ሊገልጸው የማይችለውን መከራና ግፍ በተቀበሉባት ለሮቢን ደሴት ወኅኒ/ግዞት ቤት ከነጻነት በኋላ ደግሞ ሺህዎች በየዕለቱ የሚጎርፉበት የነጻነት መታሰቢያ ሙዚየም ለመጎብኘትና ምስጋናችንን ለመግለጽ በሚል ነበር በደሴቲቱ የተገኘነው፡፡

የትምህርት ክፍላችን አስተባባሪ ከጉብኝታችንና ከቀኑ ውሎአችን በኋላ በሮቢን ደሴት በሚገኘው መኖሪያው የእራት

የ1966ቱ/የ77ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት መንግሥትም ሆነ ሰብአዊ ርኅራኄ የሚሰማን ዜጎች

ሁሉ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናልግብዣ አድርጎልን ነበር፡፡ ከኬፕታውን ሲ ፓይንት- ከኔልሰን ማንዴላ ጌት በመርከብ ለ፵፭ ደቂቃ ያህል ቀዝቃዛውንና ማዕበል የሚንጠውን የአትላንቲክ ውቅያኖስን በማቋረጥ፣ ውብ በሆነችው የደቡብ አፍሪካ እናት ከተማ በኬፕታውን ድንቅ ተፈጥሮ እየተደመምን፣ ከአድማሱ ጋራ የተጋጠመ የሚመስለውን ባለ ልዩ ግርማ ተራሮቿን በርቀት እየቃኘን፣ እንዲሁም በዓለማችን የመርከብ ቴክኖሎጂ ታሪክ ተወዳዳሪና አቻ የሌላት የተባለችውን የእንግሊዟን

ታይታኒክ መርከብ ከ1800 ተጓዦቿ ጋር ያሰጠመውን በባለ ግርማ ሞገሱን የአትላንቲክ ውቅያኖስ የመርከብ ላይ ጉዞና የዶልፊኖችን የውኃ ላይ አስገራሚ ትእይንትና በሮቢን ደሴት ጉብኝታችን የፈጠረብንን ልዩ ደስታ ስሜታችንን ከፍ እንዳደረገው ነበር የትምህርት ክፍላችን አስተባ ባሪ በሆነው በሮቢን ደሴት መኖሪያ ቤቱ ለእራት የታደምነው፡፡

ታዲያ እራት ተበልቶ አልቆ የደቡብ አፍሪካውያኑን ወይን እየተጎነጨን ስንጨዋወት በጨዋታችን መካካል በትምህርት ክፍላችን አስተባባሪ ቤት ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠውን የኔልሰን ማንዴላን የትግል ሕይወት የሚተርከውን መጽሐፍ አንስቼ ሳገላብጥ፣ ማንዴላ ለወታደራዊ ሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በነበሩበት ጊዜ በወቅቱ ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጣቸውን

ፓስፖርት በመጽሐፉ ላይ በአባሪነት መካተቱና የኢትዮጵያ ቆይታቸውን የሚያትተውን አስደናቂ ትረካ በማየቴ እጅጉን ደስ አለኝ፡፡ በአጠገቤ ለነበረችው ከዩኔስኮ ተወክላ ከሀገረ ናምቢያ ለመጣች የክፍል ጓደኛዬ መጽሐፉን እያሳየኋት ማንዴላ ስለ አገሬ ኢትዮጵያ የሰጡትን ድንቅ ምስክርነት በኩራት ካነብበኩላት በኋላ አገራችን ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የነጻነት ታጋይ ለኔልሰን ማንዴላና በአጠቃላይ ለጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ትግልና ተጋድሎ ያደረገችውን

አስተዋጽኦ ከአንጸባራቂው ከዓድዋው ድል ጋራ በአጭሩ ተረኩላት፡፡ ‹‹Oh really! እኔ ይሄን አላውቅም፤ ብዙዎች አፍሪካውያንም ይሄን የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ ስለ ኢትዮጵያ አብዛኛው የአገሬ ናምቢያ ሕዝብም ሆነ እኔ የምናውቀው ኹለት ነገሮችን ነው፡፡

አንደኛው በርካታ ተከታይ ያላቸውን ንጉሣችሁን ኃይለ ሥላሴን/ራስ ተፈሪውያንን ሲሆን ኹለተኛው ግን Sorry to say this …! ይሄን ስልህ እያዘንኩ ነው፤ በአገራ ችሁ ተከስቶ በነበረው አስከፊው ድርቅ/ራብ ስላለቁት ወገኖቻችሁን ነው የሰማሁትም፣ የማውቀውም፡፡ እውነቴን ነው የምልህ እንዲህ ዓይነት ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ኩራት የሆነውን ታሪካችሁን፣ ሥልጣኔያችሁንና የአፍሪካ ጫፍ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ (ረሃብ... ወደ ገጽ 11 የዞረ)

ፖለቲካ ኢኮኖሚ አሜሪካ ማኅበረሰብ

ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ-----የኢሬቻን በዓል በማስመልከት አንድ ጽሑፍ

እናበረክታለን ባልነው መሰረት ይህንን ኢትኖግራፊ ቀመስ ወግ ጀባ ልንላችሁ ነው፡፡ ታዲያ እኛ ባደግንበት አካባቢ በሚነገረው ትውፊት በዓሉ “ኢሬሳ” እየተባለ ስለሚጠራ በዚህ ጽሑፍ ውስጥም “ኢሬሳ” የሚለውን ስም መጠቀሙን መርጠናል፡፡ ወደ ነገራችን ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ የሚወሱት ጉዳዮች Carcar and the Ittu Oromo በተሰኘው የኢትኖግራፊ ጥናት ውስጥ በሰፊው የሚዳሰሱ በመሆናቸው ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች የጥናቱን የመጨረሻ ውጤት እንድትጠባበቁ እጠይቃለሁ፡፡ ምክንያቱም በጽሑፉ ውስጥ ከቀረበው ትረካ በላይ ሄጄ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች እንዳልገባ ጥናቱን የማከናውንበት ደንብ ስለሚያግደኝ ነው፡፡

----ጽሑፋችንን የተሳሳቱ ምልከታዎችን በማስተካከል

እንጀምራለን፡፡የዋቄፈንና እምነት ተከታይ የሆኑት ኦሮሞዎች

በሙሉ የኢሬሳን በዓል ያከብሩታል፡፡ ይሁንና በዚህ ዘመን በዓሉ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረው የቱለማ ኦሮሞ ይዞታ በሆነው የቢሾፍቱ ወረዳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ታዲያ የበዓሉ ማክበሪያ በሆነው ስፍራ ቆሪጥን የመሳሰሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስምና ዝና ያላቸው ጠንቋዮች የከተሙ በመሆናቸው ብዙ ሰዎች ኢሬቻን ጠንቋዮቹ የዛር መንፈሳቸውን በህዝቡ ላይ የሚያሰፍኑበት ዓመታዊ የንግሥ በዓል አድርገው ይመለከቱታል፡፡ አልተገናኝቶም!!

ጠንቋዮቹ በቅርብ ዘመን የበቀሉ ሀገር አጥፊ አራሙቻዎች ናቸው፡፡ ከበዓሉ ጋር አንድም ግንኙነት የላቸውም፡፡ ኖሮአቸውም አያውቅም፡፡ የኢሬቻ በዓል ግን ከጥንቱ የኦሮሞ ህዝብ የዋቄፈና እምነት የፈለቀ እና ለብዙ ክፍለ ዘመናት ሲተገበር የኖረ ነው፡፡ ጠንቋዮቹ በዚያ አካባቢ የሰፈሩት ከጣሊያን ወረራ ወዲህ ባለው ጊዜ ነው፡፡ እነዚህ ጠንቋዮች እዚያ የሰፈሩበት ምክንያት አለ፡፡ የገላን፤ የቢሾፍቱ እና የዱከም ወረዳዎች በጥንታዊው የቱለማ ኦሮሞ ደንብ መሰረት የነገዱ ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ማዕከላት ናቸው፡፡ እነዚህ መሬቶች በቱለማ ኦሮሞ ዘንድ “ቅዱስ” ተብለው ነው የሚታወቁት፡፡ “ቃሉ” የሚባለው የህዝቡ መንፈሳዊ መሪም የሚኖረው በዚህ አካባቢ ነው፡፡ የቱለማ ኦሮሞ ኢሬቻን የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት የሚያከብረውም በዚሁ ስፍራ ነው፡፡

በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ የኦሮሞ ህዝብ በነዚህ መሬቶች የሚያካሄደውን በዓላትን የማክበርና “ዋቃ”ን የማምለክ ተግባራት እንዳያከናውን ታገደ (ዝርዝሩን ለማወቅ የጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሤን “ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ”፣ ወይንም የኤንሪኮ ቼሩሊን The Folk Literature of The Oromo ያንብቡ)፡፡ ይሁንና ልዩ ልዩ የኦሮሞ ጎሳዎች እየተደበቁም ቢሆን ወደ ስፍራው መሄዳቸውን አላቋረጡም፡፡ በጣሊያን ዘመን ደግሞ እንደ ጥንቱ ዘመን ሰብሰብ ብለው በዓሉን ማክበር ጀመሩ፡

፡ ጣሊያን ሲወጣ እንደገና በጅምላ ወደስፍራው እየሄዱ በዓሉን ማክበሩ ቀረ፡፡ ነገር ግን ኦሮሞዎች ከጣሊያን በኋላም በተናጠልና በትንንሽ ቡድኖች እየሆኑ መንፈሳዊ በዓላቸውን በስፍራው ማክበራቸውን አላቋረጡም (እዚህ ላይ ጣሊያንን ማድነቃችን አይደለም፤ ታሪኩን መጻፋችን ነው እንጂ)፡፡

እንግዲህ በዚያ ዘመን ነው ጠንቋዮቹ በአካባቢው መስፈር የጀመሩት፡፡ እነዚህ ጠንቋዮች ይህንን ስፍራ ምርጫቸው ያደረጉበት ዋነኛ ምክንያት አለ፡፡ ጠንቋዮቹ ህዝቡ መሬቱን እንደ ቅዱስ ምድር የሚመለከት መሆኑን

ያውቃሉ፡፡ “ቃሉ” የሚባለው የጥንቱ የኦሮሞ ሀገር በቀል እምነት መሪ በስፍራው እየኖረ የህዝቡን መንፈሳዊ ተግባራት ይመራ እንደነበረም ያውቃሉ፡፡ የኦሮሞ ቃሉ በህዝቡ ከፍተኛ ክብር እንደሚሰጠው እና ንግግሩ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዳለውም ይገነዘባሉ፡፡ “ቃሉ” አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ጊዜ ከ“ዋቃ” የተሰጠውን ገደብ ሳይጥስ “ራጋ” የማከናወን ስልጣን እንዳለውም ይረዳሉ፡፡

እንግዲህ ጠንቋዮቹ የዘረፋ ስትራቴጂያቸውን ሲወጥኑ በጥንታዊው የኦሮሞ የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ዘንድ እንደ ቅዱስ የሚወሰደው ያ ማዕከላዊ ስፍራ ብዙ ገቢ ሊዛቅበት እንደሚችል ታያቸው፡፡ በመሆኑም በዚያ ቅዱስ ስፍራ ከትመው ከጥንቱ የኦሮሞ ቃሉ ስልጣንና ትምህርት የተሰጣቸው እየመሰሉ ህዝቡን ማጭበርበርና ማወናበድ ጀመሩ፡፡ ለረጅም ዘመን ማንም ሃይ ባይ ስላልነበራቸው የውንብድና ስራቸውን በሰፊው ሄደውበታል፡፡ አሁን ግን ሁሉም እየነቃባቸው ነው፡፡

ታዲያ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሚኖሩት ጠንቋዮች ተመሳሳይ ስትራቴጂ የሚጠቀሙ መሆናቸውን

ልብ በሉ፡፡ ለምሳሌ በወሎ፣ በሀረርጌ፣ በባሌና በጂማ የሚኖሩት ጠንቋዮች እነ ሼኽ ሑሴን ባሌ፣ እነ ሼኽ አባዲር፣ እነ አው ሰዒድ፣ እነ ሼኽ አኒይ ወዘተ… የመሳሰሉት ቀደምት ሙስሊም ዑለማ በመንፈስ እየመሯቸው መጪውን ነገር እንደሚተነብዩና ድብቁን ሁሉ እንደሚፈትሹ ይናገራሉ፡፡ በሰሜን ሸዋ፣ ጎንደር፣ ጎጃም ወዘተ… አካባቢዎች ያሉ ጠንቋዮች ደግሞ ቅዱስ ገብርኤልና ሚካኤል ራዕይ እያስተላለፉላቸው መጻኢውን ነገር ለመተንበይ እንዳበቋቸው ያወራሉ፡፡ ነገር ግን ሁላቸውም አጭበርባሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ጠንቋዮች ከክርስትናም

ሆነ ከእስልምና ጋር የሚያገናኛቸው ነገር እንደሌለ ሁሉ ከዋቄፈንና እምነትም ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ ሶስቱም እምነቶች ጥንቆላን ያወግዛሉ፡፡ እናም የቢሾፍቱ ቆሪጦች እና ኢሬቻ በምንም መልኩ አይገናኙም፡፡ ስለዚህ ኢሬቻን ከጥንቆላም ሆነ ከባዕድ አምልኮ ጋር ማያያዝ ስህተት ነው፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ መወሳት ያለበት ጉዳይ ለጠንቋዮች መጠሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን “ቃልቻ” የተሰኘውን ስም ይመለከታል፡፡ ይህ ስም በአንድ ጎኑ “ቃሉ” የሚለውን የኦሮሞ መንፈሳዊ አባት ያመለክታል፡፡ በሌላኛው ጎኑ ይህ መንፈሳዊ አባት የተወለደበትን ጎሳም ያመለክታል፡፡

የቃሉ ሹመት እንደ አባገዳ በምርጫ የሚከናወን ሳይሆን ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ አባት አባል የሆነበት ጎሳም በዚሁ ስም “ቃሉ” እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ የጎሳው አባላት የሆኑ ሰዎች ሃላፊነት ህዝቡን በመንፈሳዊ ተግባራት ማገልገል ነው፡፡ የዚህ ጎሳ ተወላጆች በከፍተኛ ደረጃ ይከበራሉ፡፡ ቃላቸው በሁሉም ዘንድ ተሰሚ ነው፡፡ ይሁንና የፖለቲካ መሪ

እና የጦር መሪ ለመሆን አይችሉም፡፡ የአባገዳ ምርጫ ሲከናወንም ለእጩነት አይቀርቡም፡፡ እንግዲህ “ቃሊቻ” የሚባሉት ከዚህ የተከበረ ጎሳ የተወለዱ ወንዶች ናቸው፡፡ ሴቶቹ ደግሞ “ቃሊቲ” በሚለው የማዕረግ ስም ይጠራሉ፡፡ የሁለቱም ትርጉም “የቃሉ ሰው” እንደማለት ነው፡፡ ጠንቋዮቹ “ቃሊቻ” ነን ማለት የጀመሩት ቃሉዎች በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ያላቸውን ክብር ስለሚያውቁ ነው፡፡ ነገር ግን “ቃሊቻ” እና ጠንቋይ የሰማይና የመሬትን ያህል የተራራቁ ናቸው፡፡

*******እነሆ አሁን ወደ ኢሬሳ ገብተናል!!በጥንቱ የኦሮሞ የዋቄፈንና እምነት መሰረት

ብዙዎቹ በዓላት ወርሃዊ ናቸው፡፡ እነዚህ ወርሃዊ በዓላት የሚከበሩት በየአጥቢያው ባሉት መልካዎች፣ በኦዳ (ዋርካ) ዛፍ ስር እና “ገልመ ቃሉ” በሚባለው ቤተ እምነት ነው፡፡ ኢሬሳን የመሳሰሉት ታላላቅ በዓላት የሚከበሩት ግን በነገድ (ቆሞ) ደረጃ ሲሆን በዓላቱን የማክበሩ ስርዓቶች የሚፈጸሙትም በዞን ደረጃ ባሉ የበዓል ማክበሪያ ስፍራዎች ነው፡፡ እነዚህ የክብረ በዓል ስፍራዎች የሚገኙትም የእያንዳንዱ የኦሮሞ ነገድ የፖለቲካና የመንፈሳዊ ማዕከላት ባሉበት አቅራቢያ ነው፡፡ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር ስትመጡ “አዴሌ” እና “ሀረማያ” የተሰኙትን ሐይቆች ታገኛላችሁ አይደል?… አዎን! የአዴሌን ሐይቅ አልፋችሁ ወደ ሀረማያ ከመድረሳችሁ በፊት ወደ ጋራሙለታ አውራጃ የሚገነጠለው የኮረኮንች መንገድ ይገጥማችኋል፡፡ መንገዳቸው ወደ ጋራ ሙለታ የሆነ ተጓዦች እዚያ ከመድረሳቸው በፊት የአውቶቡሱ ረዳት በዚያ ስፍራ እንዲያወርዳቸው ይነግሩታል፡፡ ታዲያ ስፍራውን ምን ብለው እንደሚጠሩት ታውቃላችሁ?….. Mud-hii Irreessaa ነው የሚሉት፡፡ ቃል በቃል ሲተረጎም “የኢሬሳ ወገብ” እንደማለት ነው፡፡ አውዳዊ ፍቺው ግን “የኢሬሳ በዓል ማክበሪያ ስፍራ” እንደማለት ነው፡

፡በዚህ ስፍራ በአሁኑ ወቅት የኢሬሳ በዓል አይከበርም፡

፡ በጥንት ዘመናት ግን የምስራቅ ሀረርጌው የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የኢሬሳን በዓል የሚያከብረው በዚህ አካባቢ ነው፡፡ በዓሉ ይከበርበት የነበረውን ትክክለኛ ስፍራ ለማወቅ ካሻችሁ በዋናው የአስፋልት መንገድ ላይ ለጥቂት ሜትሮች እንደተጓዛችሁ ከመንገዱ በስተቀኝ በኩል ፈልጉት፡፡ በዚያ ስፍራ ላይ ከትንሽዬ ኮረብታ ስር የተጠጋ ሰፊ መስክ ራቅ ብሎ ብሎ ይታያል፡፡ ይህ ረግረጋማ ስፍራ በጥንቱ ዘመን አነስተኛ ሐይቅ እንደነበረበት ልብ በሉ፡፡ ሐይቁ ከጊዜ ብዛት ስለደረቀ ነው በረግረግ የተዋጠው መስክ እንዲህ አግጥጦ የሚታየው፡፡ እናም የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የዋቄፈንና እምነት ተከታይ በነበረበት የጥንት ዘመናት የኢሬሳን በዓል የሚያከብርበት ቅዱስ ስፍራ በዚህ የደረቀ ሐይቅ ዳርቻ የነበረው መሬት ነው፡፡

Mudhii Irreessa የሚባለው ስፍራ ከደረቀው ሐይቅ አቅራቢያ መሆኑና ይኸው ስፍራ አሁን ካሉት የሐረማያ እና የአዴሌ ሐይቆች (እሬሳ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

የኢሬሳ/ኢሬቻ በዓል ትውፊትና አከባበር

ታክስዎን የረዥም ዓመት ልምድ ባለው አክሎግ አስፋው ያሰሩ

900 American Blvd E Ste 206, Bloomington, MN 55420

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 8

እንመካከር

ውድ የጋዜጣችን ተከታታይ ሰብለ ጥያቄሽን በአክብሮት ተቀብለናል፡፡ በአጭሩም ጥያቄሽን እንዴት በወንዶች ተወዳጅ ለመሆን ለረጅም ጊዜ ተፈቃሪ መሆን እችላለሁ የሚል ይመስላል፡፡ በአጭሩ፡፡ ሆኖም ከጥያቄሽ እንደተረዳነው ለፍቅር ትስስርሽ ዘላቂነት አለመኖር ምክንያቱን በወንዶች ላይ በመጠምጠም አንዱ ከሌላው ይሻል ይሆናል በሚል እሳቤ መፍትሄውን ወንድ በመቀየር ላይ ያነጣጠርሽው ይመስላል፡፡ ይሁን እንጂ የማንኛውም ችግር መነሻ መሰረቱ ራሱ ባለቤቱ ነውና የወንዶችን ልብ ለመቀየር የራስን ልብ ከመቀየር ይጀምራልና ችግሩ የወንዶቹ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ያንቺ ነውና ወደ ራስሽ ተመልከች እላለሁ፡፡ የራስሽን ባህሪ ገምግሚ፡፡ ምን አይነት ባህሪሽ ደካማ እንደሆነና ወንዶችም በተደጋጋሚ የሚነግሩሽ የቱ እንደሆነ በማወቅ ለማረም ሞክሪ፡፡

ውድ ሰብለ፡- የማማለል ጥበብ ራሱን የቻለ ልዩ ክህሎት እንደመሆኑ መጠን ጥበቡን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር መታወቅ ያለባቸው መሰረታዊ እውቀቶች አሉ፡፡ ‹‹ማማለል›› የሚለውን ቃል ‹‹ማጥመድ›› በሚለው ቃል ብንተካው አንድ ነገር ለማጥመድ ከመዘጋጀትሽ በፊት ስለወንዱ ባህሪና የአጠማመድ ጥበቡ በቅድሚያ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ስለወንዱ ደካማ ጎንም

እንዲሁ ግንዛቤ መጨበጥ ያስፈልጋል፡፡ ይህን እንግዲህ ዓሳንና የዱር እንስሳትን እንደማጥመድ ልንመስለው እንችላለን፡፡ አንቺ የምትፈልጊውን ወንድም በእጅሽ ለማስገባት መሰረታዊ ሃሳቡ ተመሳሳይ እንደመሆኑ መጠን የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥበቦች መረዳት ያስፈልጋል፡፡

- ሕግ ማማለል በቀጥታ ሳይሆን በስሜት በኩል የሚደረግ መዘውራዊ ጥቃት፡- እንዲታወቀው የሰው ልጅ ሁለት የአዕምሮ ክፍሎች አሉት፡፡ እነሱም የላይኛውና ውስጠኛው በመባል የሚታወቁ ናቸው፡፡ የላይኛው የአዕምሯችን ክፍል የሚጠራው በግልፅ መረጃዎች ላይ በመንተራስ ቀጥተኛና ምክንያታዊ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚፈልግ፣ የሚያቅድና፣ የሚወስን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ፍቅር በቀጥታ በዚህ መሰል በምክንያታዊና ሎጅክ የሚወሰን ነገር አይደለም፡፡

በመሆኑም የማማለል ጥበቦችን ልዩ የሚያደርጋቸው ይህን የአዕምሮ ክፍል በማለፍና በመዝለል በቀጥታ ወደ ውስጠኛው የአዕምሮ ክፍል ዘልቆ መግባት የሚያስችሉ መሆናቸው ነው፡፡ እንደሚታወቀው ፍቅር ስሜት ነው፡፡ ስሜታችን ደግሞ ያለው በውስጠኛው የአእምሯችን ክፍል ውስጥ ነው፡፡ ይህን ክፍል ለመነካካትም አቋራጭ መላ ወንዶችን በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መቅረቡ ላይ ነው፡፡

የቀጥታ ቀረቤታ ብዙ ጊዜ አዋጭ አይደለም፡፡

ሕግ 2 ፍቅር ሃሳብ መሆኑን እወቂ፡- ስለ አንድ ነገር የበለጠ በታሰበ ቁጥር ለዚያ ነገር

የሚኖረን ፍላጎት ይጨምራል፡፡ ለአንድ ነገር የሚኖረንን ፍላጎት፣ የውሳኔና ድርጊት የበለጠ ለመጨመር ከተፈለገ ለዚያ ነገር የበለጠ ማሰብን ግድ ይለናል፡፡ ይህ በስነ ልቦና አጠራር ‹‹Obssesion›› የሚባለውንና አስተሳሰቡን የሚወክለውን ድርጊት ነው፡፡ የበለጠ የምናስበውን ነገር ለማድረግ እንገፋፋለን፡፡ በመሆኑም የማማለል ጥበቦች የመረጥሽውን ወንድ ፍቅረኛ የበለጠ ስለአንቺ አብዝቶ እንዲያስብ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

ያደረግሻቸውን ትዝ እያለው፣ በምታደርጊያቸው ግራ እየተጋባ፣ ራሱን እየጠየቀ፣ እየተደነቀና እየተብከነከነ በሄደ ቁጥር በአንቺ ፍቅር ተይዞ ያርፈዋል፡፡ የማማለያ ቴክኒኮች እንዴት ወንድ ልጅን በፍቅር ሊያሲዙ እንደሚችሉ ስትመለከቺ ሊገርምሽ ይችላል፣ ዋናው ዘዴያቸው በዚህ ሕግ ላይ የሚሽከረከሩ መሆናቸው ነው፡፡ በመሆኑም በተቻለ መጠን በህይወቱ ጊዜ የሌለውን ወንድ ለማማለል አትሞክሪ፡፡ ምክንያቱም ብዙ የሚያሳስባቸውና የሚጨነቅባቸው ጉዳዮች ያሉት በመሆኑ ነው፡፡ በአንፃራዊነት ጊዜ ያላቸው ወንዶች ስለ አንቺ አብዝተው

ለማሰብ ግን የተመቹ ናቸው፡፡

ሕግ 3 ወንዶችን በሚገባ ለማማለል የተለያዩ ብቃቶችሽ ላይ አነጣጥሪ፡-

በእርግጥ አንድ ልዩ ብቃት በራሱ የወንዱን ልዩ ትኩረት ለማግኘትና ለመሳብ ያስችል ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ አስተማማኙና የብዙዎችን ቀልብ እንድትስቢ የሚያደርግሽ ግን ከአንድ በላይ የተለያዩ የአማላይ ሴት ባህሪያትን መካን ስትችል ነው፡፡ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ያነገበ ወታደር እንዳስፈላጊነቱ መሳሪያዎችን የመጠቀም አቅምና አማራጭ ስለሚኖረው ጠላቱን በቀላሉ የማሸነፍ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሴቶች ወንዶች ‹‹ጠላቶቻቸውን›› በፍቅር ለማንበርከክ ሊጠቀሙትና ሊያነግቡት የሚገባው የተለያዩ የማማለያ ባህሪያትን ሊታጠቁ ይገባል፡፡ በመሆኑም አንድን ልዩ ብቃት ከሌለው ጋር በማጣመር መጠቀም ስትችዪ ነው አንቺን በተለየ ሁኔታ ተመራጭ የሚያደርግሽ፡፡ ስለሆነም ተወዳጅ ባህሪዎችሽ አብዣቸው፣ የሚነቀፉትንም ቀንሻቸው፡፡

ሕግ 4 ማማለል ስሜት የመበተን ኃይል ነውየምትፈልጊው ወንድ አንቺን እንዲያፈቅርሽ በማድረግ

እንቅስቃሴ ውስጥ (ወንዶች... ከገጽ 12 የዞረ)

ወንዶች ለእኔ ሣሙና የሆኑበት ምስጢር የ40 ቀን ዕድሌ በመሆኑ ይሆን?

ዕድሌ ሆኖ ወንድ አይበረክትልኝም፡፡ ወንዶች ለእኔ በአጭሩ ሳሙናዎች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ ይቀርባሉ፣ ነገር ግን እኔም ምስኪን ነኝ አምኜ እቀርባቸዋለሁ፡፡ እነሱም የልባቸውን ካገኙ በኋላ ‹‹ጌታ ያጣፍልሽ›› በማለት ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዴ የወንድ ልጅን ልብ ማግኘት አይቻልም እላለሁ፡፡ ስለሆነም ጥያቄዬ የወንድን ልጅ ልብ ማንበርከክና ልቡንም አግኝቶ ለማቆየት መስተፋቅር ይሻል ይሆን? በማለት ያሰብኩበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ውበት ሳያንሰኝ ወንዶች እንደ ዘንድሮ መብራት ብልጭ እያሉ የሚጠፉበት ምክንያቱ ግራ አጋብቶኛል፡፡ ወይስ የ40 ቀን ዕድሌ ሆኖ ነው? ሰብለ ነኝ

አለርጂን በተመለከተ ብዙዎቻችሁ ላቀረባችሁልን ጥያቄዎች የዶክተሩ ምላሽእንዲህ አይነት ምግብ ስመገብ ሰውነቴ ይቆጣል፣

እንዲህ አይነት ልብስ ወይም ደግ እንዲህ አይነት ቁሳቁ ስጠቀም አልያም አሞኝ የወሰድሁት መድሃኒት ሰውነቴ ያሳብጠዋል፣ ያሳክከኛል ወዘተ... የሚሉ ጥያቄዎች የብዙዎች አንባቢዎቻችን ናቸው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣውጤና መረጃ እንደሚያመለክተው ከሶስት እስከ አራት ሚሊየን የሚደርስ ሕዝብ ለተለያዩ ጉዳዮች አለርጂክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በየዓመቱ ድንገት ራሳቸውን የሚስቱና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ ነው የሚገልፀው፡፡

በአለርጂ የጤና ችግር ምንነት፤ መንስኤና መፍትሄ ዙሪያ እንደተለመደው ዶ/ሩ ሙያዊ ማብራሪያ እንደሚከተለው ሰጥተዋል፡፡

ጥያቄ፡- አለርጂ ራሱን የቻለ በሽታ ነው ወይስ የሌሎች በሽታዎች ምልክት ነው?

ዶ/ር፡- አለርጂ ራሱን የቻለ መንስኤ ያለው የጤና ችግር ነው፡፡

ጥያቄ፡- ምን አይነት በሽታ ነው?ዶ/ር፡- በህዋስም ሆነ በንጥረ ነገር መልክ ወደ

ሰውነታችን በሚገቡ ነገሮች የሰውነታችን የመከላከያ ኃይል ከመደበኛው (ከሚጠበቀው) በላይ ምላሽ ሲሰጥ የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡ በየትኛውም መንገድ ይሁን ወደ ሰውነታችን የሚገቡ ባዕድ ነገሮችን ለመከላከል ወይም ለማጥፋት የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮች (anti body) ማንጨት የሰውነታችን በሽታን የመከላከል ስርዓት ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ይህ ስርዓት ብዙውን ጊዜ የሚጠበቅበትን ተግባር የሚያከናውን ቢሆንም፣ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊና

ውጫዊ ምክንያቶች በሚፈጥሩት ተፅኖ ሳቢ፣ ጎጂዎችንና ጠቃሚ ሴሎችን በጅምላ በማጥፋት ከመጠን በላይ የሆነ እርምጃ ይወስዳል፡፡ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት አንዳንድ ጊዜ የራሳችንን አካል ክፍሎች ለምሳሌ ኩላሊትን፣ ልብን፣ መገጣሚያንና የአካል ንቅለ ተከላ ሲደረግ እንደ ባዕድ በመቁተር ያጠቃል፡፡ በዚህ ጊዜ ከሚፈጠሩ ችግሮች አንዱና ዋነኛው አለርጂ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ለአለርጂ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?ዶ/ር፡- ማንኛውም ሰው በየትኛውም ጊዜና ሰዓት

በአለርጂ በሚፈጠሩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድል አለው፡፡ ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለዚህ ውይይት ዋና ዋና የሚባሉትን ለማየት እንሞክራለን፡፡ የተለያዩ የምግብ አይነቶች ለአለርጂ መከሰት ምክንያት ይሆናሉ፡፡ በዓለም ላይ አለርጂን በማምጣት የሚታወቁ ወደ 8 የሚሆኑ የምግብ አይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም ወተትና የወተት ተዋፅኦዎች፣ ዓሳና ዓሳ ነክ ምግቦች፣ እንቁላል፣ ከተለያዩ የኦቾሎጂ አይነቶች የሚዘጋጁ ምግቦች፣ አኩሪ አተርና ምግብን ለማጣፈጥ ወይም ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ተብለው የሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች እንዲሁም በመድሃኒት ውስጥ የሚጨመሩ ኬሚካሎችና በፋብሪካ የታሸጉ ምግቦች ለአለርጂ የማጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት መድሃኒት አላርጂ ነው ማለት ባይቻልም፣ ለተለያዩ የህመም አይነቶች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለአለርጂ መከሰት ምክንያት ይሆናሉ፡፡

በኬሚካል ማምረቻዎች የሚሰሩ፣ ለአረም ማጥፊያ ኬሚካሎች ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አቧራ፣ የዕፅዋት ብናኝ፣ ቀዝቃዛ የአየር ፀባይና ከቤት ውስጥ እንስሳት ጋር የዕለት ተዕለት ግንኙነት የሚያደርጉ ሰዎች

ለአለርጂ ተጋላጭ የመሆን ዕድል አላቸው፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት ጉዳይ በተመሳሳይ

ጊዜና ቦታ አለርጂ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለአንዱ አለርጂ የሆነ ጉዳይ ለሌላው ላይሆን የሚችልበት ሁኔታ ሰፊ በመሆኑ ነው፡፡

ጥያቄ፡- አለርጂክ በብዛት የሚከሰትባቸው የአካል ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- አለርጂ በአብዛኛው የሚከሰተው ቆዳ ጋር በአለ ንክኪ ቆዳ ላይ ይከሰታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓይን፣ በአፍንጫ፣ በአፍ፣ በመተንፈሻ አካላትና በአንጀት አካባቢ ይከሰታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓይን፣ በአፍንጫ፣ በአፍ፣ በመተንፈሻ አካላትና በአንጀት አካባቢ ይከሰታል፡፡ ከሌሎች ሰዎች በተለያየ ምክንያት በሚወሰድ ደም አለርጂ ሊከሰት ይችላል፡፡

ጥያቄ፡- አለርጂ ሲከሰት ከሚታዩ ምልክቶች ዋና ዋና የሚሉትን ቢገልፁልኝ?

ዶ/ር፡- አለርጂ ሲከት የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን፣ አለርጂው እንደሚከሰቱበት ቦታ የሚታዩ ምልክቶችም የተለያዩ ናቸው፡፡

ዓይን አካባቢ ሲከሰትማሳከክ፣ መቅላት፣ ማበጥ፣ ህመም፣ ማበጥ፣ ቶሎ ቶሎ

እንባ መፍሰስና ብርሃን ማየት መፍራት ይከሰታል፡፡አፍንጫ እና የመተንፈሻ አካላት አካባቢ ሲከሰት፡-

ቀጭን ውሃ መሳይ ንፍጥ፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ መደፈን፣ ማሳከክ፣ ማሳል፣ የመተንፈሻ አካላት እብጠትና ውሃ መቋጠር፣ ፈሳሽ መብዛት፣ የአየር መታፈን፣ ማሳል፣ ስር ስር የሚል ድምፅ ሊከሰት ይችላል፡፡

ከምንመገበውና ከምንጠጣው ምግብ ጋር አለርጂ

ሲከሰት፡- አፍና ከንፈር ማበጥ፣ ምግብ ለመዋጥ መቸገር፣ ጉረሮ አካባቢ ህመምን ጨምሮ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥና የሆድ አካባቢ ህመም ይከሰታል፡፡

ከንክኪ ጋር በተያያዘ ቆዳ ላይ ሲከሰት፣ ማሳከክ፣ መቅላት፣ ሽፍታ እና ማበጥ ናቸው፡፡ አለርጂ ሲከሰት የሚያሳያቸው ምልክቶች ቀለል ያሉ ቢመስሉም ራስን ከመሳት እስከ ሞት ድረስ ሊያደርስ የሚችል በሽታ እንደሆነ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ በአንድ ይሁን በሌላ ምክንያት የሚፈጠር አላርጅ፣ ተገቢውን ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚድን ቢሆንም ተመልሶ የመምጣት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ለምንድን ነው አለርጂ እየተመላለሰ የሚመጣው?

ዶ/ር፡- ቀደም ሲል ለአለርጂ መከሰት ምክንያቶችን ገልፀናል፡፡ ስለሆነም ከአለርጂ አማጭ ምክንያቶች ራስን በተገቢ ሁኔታ ጥንቃቄ ማድረግ ካልተቻለ የቱንም አይነት ህክምና ቢደረግ ተመልሶ መከሰቱ አይቀርም፡፡

ጥያቄ፡- የዚህ በሽታ ስርጭት በዓለምም ሆነ በሀገራችን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

ዶ/ር፡- የአለርጂ ጤና ችግር በሀገራችንም ሆነ በዓለም ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ነው ጥናቶች የሚያሳዩት፡፡ በዓለም ከ25 ሰዎች 1 ሰው ለተለያዩ ጉዳዮች አለርጂ ነው፡፡ ችግሩ ከፆታ አንፃር ሲታይ ሁለቱንም የሚያጠቃ ነው፡፡ ይሄ ነው ተብሎ የሚገለፅ ልዩነት የለም፡፡ ነገር ግን ከዕድሜ አንፃር ግን በህፃናት ላይ በስፋት ይታያል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ከህፃናት የታሸጉ ምግቦችን፣ ከዳይፐሮች፣ ከሚለብሷቸው ልብሶች፣ ከሚጠቀሙባቸው ሳሙናዎችና ቅባቶች ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ጥያቄ፡- አለርጂ (አለርጂ... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

BISRAT ALEMAYEHU & ASSOCIATES

Meet your Friendly and Experienced professionals@

The Center for Multi-ServicesTax, Insurance, Real Estate, Notary, Application Forms,Translation and

Moreታክስ፣ ኢንሹራንስ፣ ሪል እስቴት፣ ኖታሪ፣ ውክልና፣

ትርጉምና በርካታ ተዛማጅ አገልግሎቶች

WISER INSURANCE AGENCY, St. PaulMore Insurance Companies, More Price Choices!

[Auto. Home. Life. Health. Business]

Address: 1821 University Ave. W. Suite S-301 Saint Paul, MN 55104Tel: 651 649 0644 / 651 209 6077 Fax: 651 649 0620

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 9

“ቤተክርስቲያኒቱ አጠቃላይ ተቋማዊ ለውጥ ያስፈልጋታል”

- ዲያቆን ዳንኤል ክብረትውድ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ዛሬ እንደተለመደው

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዕይታ ሳይሆን የቃለምልልስ ዕይታውን ነው የምናስነብባችሁ:: ሃገር ቤት ከሚታተመው የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ካደረገው ሰፋ ያለ ጉዳይ ለወቅታዊ ጉዳዮች ለአንባቢዎች ምላሽ ይሆናል ያልነውን አስተናግደናል::

እንደቤተ ክርስቲያን ተመራማሪና እንደ አገልጋይ ይመለከተወታል ብለን ስለምናስበው ርእሰ-ጉዳይ አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ፤ እንደሚያውቁት በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ያለው ሙስና በብዙ መገናኛ ብዙኃን ሲዘገብ ቆይቷል። ጉዳዩ ካመት ዓመት ከመሻሻል ይልቅ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው። ለመሆኑ ምዕመናንን ያስተምራሉ፣ ምሳሌ ይሆናሉ የሚባሉት አባቶች ራሳቸው በዚህ አሳፋሪ ተግባር ላይ መዘፈቃቸው እንዴት ይታያል? በዚህ ይዞታው የሚያስተምሩት ሕዝብስ እንዴት ሊሰማቸውና ሊቀበላቸው ይችላል? ለቤተ ክርስቲያኒቱስ አደጋ አይደለምን?

እንደኔ መረዳትና ጥናት ቤተ ክርስቲያን አሁን የተጋረጠባት አደጋ ከሁለት ነገሮች የመጣ ነው። አንደኛው ቤተ ክርስቲያኒቱ ዘመናዊውን ዓለም የተቀላቀለችበት መንገድ የፈጠረው ችግር ነው። የጥንቷ ቤተ ክህነት በተለይም ከ1950ዎቹ በፊት የነበረችው ቤተ ክህነት ከቤተ መንግሥቱ ጥግ ነበረች። አብዛኛው ሥራዋ መሬት ተኮር ነበር፤ ወደ ዘመናዊው የንግድ ዓለም አልገባችም ነበር። ለምታስተዳድረው መሬትም ከገበሬው የወጡት ቀሳውስት በቂ ነበሩ። እንዴት መሬት ማስተዳደር እንዳለባቸው በደንብ ያውቁ ነበር። በተጨማሪም በወቅቱ ለነበሩት ሥራዎች የሚበቃ የሰው ኃይልም ነበራት። ዘመናዊ ቤተ ክህነት ሲቋቋም ግን ለዘመናዊ ሥራ የሚሆን የሰው ኃይል አላደራጀችም። ለምሳሌ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ አያያዝ (Church Ac- counting) ትምህርት በየትኛው የቤተ ክርስቲያን ተቋም አይሰጥም። ዘመናዊ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ትምህርት ቤተ ክርስቲያኒቱ አትሰጥም። የቀድሞው ፍትሐ ነገሥት ቢኖርም በቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ሕግን የሚመለከት ትምህርት አሁን አይሰጥም። የንግድ ተቋማቷን ያለምንም ሙያ ነው የምታስተዳድረው። ስለዚህ ‹‹ለምን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ችግር ተፈጠረ?›› ብለን ስንነጋገር ችግሩ ያለው ከዚሁ ውስጥ ነው። ድጓው ውስጥ፣ ቅኔው ውስጥ፣ ቅዳሴው ውስጥ፣ ማህሌቱ ውስጥ፣ ሰዓታቱ ውስጥ ምንም ችግር የለም። ለዚህ የሚሆን በቂ የሰው ኃይልና በቂ ልምድ አላት። ዘመናዊ ተቋም የሚያስፈልጋት ዘመኑ ላመጣቸው አዳዲስ ዕውቀቶች ነው። ያልተማሩ ወይም ለነዚህ ዘመናዊ አሠራሮች ሙያ የሌላው ሰዎች ሲሰማሩ ክፍተት ተፈጠረ። በቢሊዮን የሚቆጠር የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት የሚመሩ ሰዎችን ብትመለከት ለቦታው የሚመጥን ዕውቀት የላቸውም። ድጓ፣ ቅኔ፣ አቋቋም ወዘተ. ተምረህ ቢሊዮን ገንዘብ ልታንቀሳቅስ አትችልም። የሙያ ክፍተት ይፈጥራል።

ሁለተኛው ችግር ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ የፖሊሲ ችግር ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ ‹‹ምን

ተግባር ላይ ነው የምሰማራው? ምን ላይ ነው የማልሰማራው? የትኛውን ነው የምሠራው? የትኛውን ነው የማልሠራው? የትኛው ይገባኛል? የትኛው አይገባኝም?›› የሚል ፖሊሲ ማውጣት አልቻለችም። ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከምናያቸው የንግድ ተቋማት ውስጥ አብዛኞቹ ሱቆች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን ‹‹በእንዲህ ዓይነት ንግድ ውስጥ መግባት አለባት? የለባትም?›› ያከራክራል፤ ፖሊሲ የላትም። ብዙ ትምህርት ቤቶች ከፍታለች፤ የትምህርት ፖሊሲ ግን የላትም። የጤና ተቋማት ከፍታለች፤ የጤና ፖሊሲ ግን የላትም። ሌሎችንም ተቋማት ከፍታለች፤ ነገር ግን ምንም ፖሊሲ የላትም። የቀድሞ ትምህርት ቤቷችን የምታስተዳድርበት እኮ ያልተጻፈም ቢሆን የተለመደ አሠራር አላት። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን የምትወቀስበት እነዚህን ዘመኑ አምጥቶ

የጨመረባትን ነገሮች በአግባቡ ማስተናገድ ባለመቻሏ ነው እንጅ ነባርና ልምድ ያካበተችባቸወን ዘርፎች በሚገባ ነው የምትከውናቸው። ይህ ምን አስከተለ? በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚንጠላጠሉ ሰዎችን ፈጠረ።

አሁን ያለው ችግር ግን የዕውቀት ችግር ብቻ ነው ማለት ይቻላል?

የዕውቀት ችግር ብቻ አይደለም። ወደዚህ ቦታ የምታሰማራቸዉን ሰዎች መርጠህ አዘጋጅተህ የማሰማራት ችግር አለ። ይህ ተቋማዊ ችግር ነው፤ የቤተ ክህነት ተቋማዊ ኪሳራ ነው። ዛሬ አንድ መርጌታ ልቅጠር ብትል ችግር የለም። አንድ አገልጋይ ካህን ለመቅጠር ብትል በቂ የሰው ኃይል አለ። ነገር ግን

በሥነ ምግባሩ የተመሰገነ፣ በቂ ዕውቀት ያለው እያልክ በመስፈርት የቤተ ክርስቲኒቱን ሀብት የሚያስተዳድር ሰው ለመቅጠር ችግር ነው። አይገኝም። አንድ ሰው ቅኔ ማህሌት ቁሞ ቢያበላሸዉ በሁሉም አቅጣጫ ‹‹እንደሱ አይደለም!›› የሚለው ሰውብዙነው።ነገርግንየቤተ ክርስቲያኒቱ ዘመናዊ አስተዳደር ሲበላሽ ‹‹እንደሱ አይደለም፤ አይሆንም!›› የሚል ሰው ጠፍቷል። ለዚህ የሚሆን በቂ ዕውቀትና በቂ ሥርዓት አልተዘረጋም። ያለ ፋይናንስ ፖሊሲ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያስተዳድር ተቋም ከቤተ ክህነት ውጭ የለም። አሁንም እኮ እንደ ድሮው ሞዴል 16፣ ሞዴል 30 እየተባለ ነው የሚሠራው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን በኮምፒዩተር ዘመን የዚህ ዓይነት አሠራር እንዴት ያስኬዳል? ሥርዓቱ በራሱ ለቁጥጥር ሳይሆን ለመብላት የተመቸ ነው። እንዲበላ ተብሎ የተዘጋጀ

አሠራር እኮ ሆኖ አይደለም። ግን ይህ በዘመኑ ዘመናዊ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ዘመኑ ተሻግሮታል። ምንም ያህል ጥሩ ሰው ብትሆን በዚህ መዋቅር ውስጥ ከሠራህ ሥርዓቱ በራሱ ያበላሽሃል::

መንግሥት የግዥ ሥርዓቱን በብር መጠን በቀጥታና በጨረታ ማስታወቂያ የሚፈጽምበት መመሪያ አለው። ይህም ሆኖ ስላልተቻለ እንደገና ማዕከላዊ የግዥ አሠራር አምጥቷል። ቤተ ክህነት ውስጥ ግን ዝርዝር የጨረታ አሠራር፣ ዝርዝር የግዥ ሂደት አሠራር አታገኝም። ይህ ሁሉ ግንባታ እየተከናወነ ግንባታ የሚመራ መምሪያ እንኳ የላትም። የግንባታውን ጥራት የሚቆጣጠር፣ ግንባታው የሚሠራው በትክክለኛ ጨረታ ነው ወይ? የሚሠሩ ሥራዎች ከቤተ ክርስቲያኒቱ ፖሊሲዎች ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው ወይ? ወዘተ. ብሎ የሚያይ አካል እኮ የለም። ያም ተነስቶ ‹‹ሱቅ እከፍታለሁ›› ቢል ከልካይ የለውም፤ ‹‹ሱቅ ሳይሆን ጉልት ገበያ›› እከፍታለሁ የሚለውም ከልካይ የለውም።

ቤተ ክርስቲያኒቱ በአንዳንድ ዘርፎች ለምሳሌ በሕንጻ ግንባታ፣ በቤተሰብ ጉዳይ ወዘተ. የበርካታ ዓመታት ልምድ ባለቤት ናት። ነገር ግን ያሳየችዉ ለውጥ የለም። እነዚህ ችግሮች ሲከሰቱ የሚመለከት ሰው እንዴት ጠፋ?

በነገራችን ላይ በ1950ቹ አቡነ ቴዎፍሎስ ጀምረውት ነበር። ግን ሕንጻዎቹ ተሠርተው አልቀው ገና ቤተ ክርስቲያኒቱ

ማስተዳደር ሳትጀምር ደርግ ወረሳቸው። በዚህ ምክንያት ልምዱ ሊካብት አልቻለም። አብዛኛዎቹ ሕንጻዎች ደግሞ በበጎ አድራጎት ተሠርተው የተበረከቱ ነበሩ። የተወረሱት ሕንጻዎች ሲመለሱ እነርሱን የሚያስተዳድር መምሪያ ብትከፍትም በየአጥቢያው ያሉ ሕንጻዎችን የሚያስተዳድር አካል ግን አልመደበችም። ዘመናዊውን ቤተ ክህነት ስታቋቁም የዕውቀትና የልድም ክፍተት ነበረባት። እስከአሁን ድረስ ያልተሞላው ችግር እርሱ ነዉ። ለምሳሌ አንድ በሠራተኛ አስተዳደር በቤተ ክህነት የተመደበና አንድ ደግሞ በመንግሥት በሠራተኛ አስተዳደር የተመደበ ሰው እኩል ዕውቀት የላቸውም። በመንግሥት መሥሪ ያ ቤቶች በሙያው (ዲ/ን ዳንኤል... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

High Risk Diverse Media Messages –

October 2015እንደ አስም፣ ሲ.ኦ.ፒ.ዲ (COPD)፣ የስኳር ወይም

የልብ በሽታ የመሳሰለ የረጅም ጊዜ የጤና እክል ካለብዎት፤ በየዕለቱ መድሃኒት በመውሰድ፣ ኢንሄለር (አፍ ውስጥ የሚነፋ የአስም መድሃኒት) በመያዝ፣ ትክክለኛ አመጋገብ በመመገብ፣ ወይም የደም ውስጥ ስኳርዎን እና ኮሎስትሮልዎን በመቆጣጠር ጤነኛ ሆነው ለመቆየት ይሞክሩ። ነገር ግን ራስዎን ጤነኛ አድርጎ ለመጠበቅ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሊያደርጉት የሚችሉት ሌላ ነገርም እንዳለ ያውቃሉን? የእንፍሉዌንዛ ክትባት መከተብ ይችላሉ።

እንደ አስም፣ ሲ.ኦ.ፒ.ዲ (COPD)፣ የስኳር ወይም የልብ በሽታ የመሳሰለ የረጅም ጊዜ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ከእንፍሉዌንዛ የተነሳ ለከፍተኛ የተወሳሰበ ችግር ይጋለጣሉ። ባለፉት የእንፍሉዌንዛ ወቅቶች ወደ ሆስፒታል ከገቡት 80 ከመቶ ያህሉ አዋቂ ሰዎች፣ የረጅም ጊዜ የጤና እክል የነበረባቸው ሲሆኑ፣ 50 ከመቶ ያህል የሚሆኑት ልጆችም ተመሳሳይ ችግር የነበረባቸው ናቸው። ምንም እንኳን በቁጥጥር ስር ቢሆኑም፤ እንፍሉዌንዛ እነኚህን የጤና እክሎች የከፋ ሊያደርጋቸው ይችላል። እነኚህ የጤና እክሎች ያለባቸው ሰዎች በሽታ የመከላከል አቅማቸውም ስለሚደክም ሰውነታቸው እንፍሉዌንዛን ለመዋጋት ያቅተዋል። ለዚህም ነው የረጅም ጊዜ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች በየዓመቱ የእንፍሉዌንዛ ክትባት መከተብ ያለባቸው።

በእንፍሉዌንዛ ምክንያት ሆስፒታል በሚገቡ ልጆች ዘንድ አስም በጣም የተለመደ የጤና እክል ነው። እንደ አስም፣ ሲ.ኦ.ፒ.ዲ (COPD) የመሳሰሉ የሳንባ በሽታዎች የአየር ቧንቧዎችን ስለሚያሳብጡ እና በአክታ ስለሚዘጉ ለመተንፈስ አስቸጋሪ ይሆናል። እንፍሉዌንዛም የአየር ቧንቧዎችዎን እና ሳንባዎችዎን የማበጥ ዕድል ስለሚያሰፋ ወደ ሆስፒታል የሚያደርስ ከፍተኛ የአስም ጥቃት እና ሕመም ሊያስከትል ይችላል። በ2012-13 የእንፉሉዌንዛ ወቅት በእንፉሉዌንዛ ተይዘው ሆስፒታል በገቡ የሚኔሶታ አዋቂ ሰዎች ዘንድ የልብ በሽታ በጣም የተለመደ የጤና እክል ነበር። የልብ በሽታ ካለብዎት፣ እንፍሉዌንዛ ሌላ የልብ ጥቃት እንዲደርስብዎት የማድረግ አጋጣሚዎን ያሰፋል። እንፍሉዌንዛ፣ 1ኛ ዓይነት ወይም 2ኛ ዓይነት የስኳር በሽታ ያለባቸውን ሰዎች የደም ጉሉኮስ መጠን አደገኛ ወደ ሆነ ከፍተኛ ደረጃ ከፍ ሊያደርገው ይችላል። እንዲሁም የስኳር በሽተኛ መሆን በራሱ በኒሞኒያ የመያዝ አጋጣሚን ከፍተኛ ያደርጋል፤ ወይም በእንፍሉዌንዛ ከተያዙም በኋላ የኒሞኒያ ክትባት መውሰድ ያስፈልግ ይሆናል።

የሚኖሩት የረጅም ጊዜ የጤና እክል ካለው የቤተሰብ አባል ጋር ነውን? ከሁሉም በላይ፣ የእንፍሉዌንዛን ክትባት ጨምሮ እንዲወሰዱ የሚታዘዙልዎትን ክትባቶች አጠናቀው መውሰድ አስፈላጊ ነው። የእንፍሉዌንዛን ክትባት መከተብ፣ እንፍሉዌንዛን ከፍተኛ የጤና እክል ላይ ወዳሉ ሰዎች ከማስተላለፍ ለመከላከል ይረዳል። የቤተሰብዎን አባላት ከበሽታ ለመጠበቅ ይከተቡ።

በሒኪም የታዘዘ መድሃኒት እየወሰዱም ቢሆን እንኳን የእንፍሉዌንዝ ክትባት መከተብ ጉዳት አያመጣም። አዋቂ ሰዎች የእንፍሉዌንዛን ክትባት ከዶክተሮች ቢሮዎች፣ ከፋርማሲዎች፣ ከስራ ቦታዎች፣ ከጤና ክሊኒኮች እና የጤና መምሪያዎች ማግኘት ይችላሉ። ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ ሌሎች ክትባቶችም ሊያስፈልግዎት ስለሚችሉ ሐኪምዎን ያነጋግሩ። አብዛኞቹ የጤና ኢንሹራንስ ፕላኖች የታዘዙ ክትባቶችን ሂሳብ ይሸፍናሉ—ለኢንሹራንስዎ ቢደውሉ ዝርዝር መረጃውን ሊሰጥዎት ይችላሉ። የጤና ኢንሹራንስ ከሌልዎት ወይም የክትባት ወጪን ለመሸፈን አቅም ከሌልዎት፣ በአካባቢዎ ኢንሹራንስ ለሌላቸው እና በቂ የኢንሹራንስ ሽፋን ለሌላቸው አዋቂ ሰዎች ክትባት የሚሰጥ ክሊኒክ (Uninsured and Underinsured Adult Vaccine) (UUAV) በሚከተለው ድረ ገጽ ይፈልጉ፦ http://www.health.state.mn.us/divs/idepc/immunize/adultvax/clinicsearch.html።

Nuru Dedefo, ESQ.Attorney at Law & Counselor

- Car Accidents- Work place Injuries- Immigrations- Family Law- Criminal Law

If you have legal issues, you need a lawyer who fights for your rights. Nuru Dedefo

fights for your rights.

If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:

3989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 55421(763)-781-5254 (office), (612-559-0489) Cell

(763)-781-5279 Fax

ሸጋ እንጀራ፣ ግሮሰሪና መጋገሪያ

Shega Foods

የፍስክ እና የጾም ምግቦችን ቱጎ አድርገው ለመውሰድ

ወደ ሸጋ ይደውሉ

ሸጋ 100% የጤፍ እንጀራን ከየሱቁ ይጠይቁ

በሸጋ ግሮሰሪ፡ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ ከየትኛውም ሱቅ የማያገኟቸው የሃገር ቤት ባህላዊ እቃዎች፣ ጤፍ፣ የስልክ ካርድ፣ መጽሐፍት፣ ሲዲዎች፣ ሁሉም ይገኛሉ

2111 E Franklin Ave, Mpls, MN 55406(612) 341-4373

የባህል አልባሳት በብዛትም

በጥራትም ይዘናል

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 10

እጅግ በመናደድና ድምጿን ከፍ አድርጋ ‹‹ይሄ ሁሉ ገንዘብ እያለህ ለልደት ቀኔ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው የምትሰጠኝ?›› ካለችው በኋላ፣ በፍጥነት ቤቱንና ባሏን በቆመበት ትታቸው ወጣች፡፡ ትዳሩም በዚህ መሰል ሁኔታ ውስጥ ወደመለያየት አመራ፡፡

በርካታ ዓመታት አለፉ፡፡ ሴቲቱ የተሳካለት የቢዝነስ ሰው ሆነች፡፡ የቀድሞ ባሏ ምን ያህል ሊያረጅ እንደሚችል በማሰብ ልትጎበኘው አሰበች፤ ለበርካታ ዓመታት አልተያዩም፡፡ ነገር ግን ለጉብኝቷ ፕሮራሞቿን ከማስተካከሏ በፊት የቀድሞ ባሏ መሞቱን ሰማች፡፡ ሁሉንም ንብረቱን ለእርሷ ነበር ተናዞ ያለፈው፡፡

በቀድሞ ባሏ መኖሪያ ቤት ስትደርስ፣ ልቧን ድንገተኛ ሐዘንና ፀፀት ተሰማው፡፡ የቀድሞ ባሏን ጠቃሚ የሚባሉ ወረቀቶች ማገላበጥ ጀመረች፡፡ ከዛም በሚገባ የተያዘውንና ከዓመታት በፊት ትታው የሄደችውን መጽሐፍ ቅዱስ ተመለከተች፡፡

በእንባ ታጅባ መጽሐፍ ቅዱሱን ከፈተችው፡፡ ገፆችን መግለጥ ስትጀምር ባሏ ያሰመረበትን መልዕክት አስተዋለች፡፡ መልዕክቶቹን እንዳነበበች፣ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ውስጥ አንድ ነገር ሲወድቅ ተመለከተች፡

፡ በመደብር ማሳያ ውስጥ የተመለከተችው ስሟ የሰፈረበት የዳይመንድ ቀለበት ነበር፡፡ የልደት ቀኗ እና ‹‹ሁልጊዜም እወድሻለሁ›› የሚል መልዕክትም ተጽፎበታል፡፡

የሌለን የምንመኘውን ነገር በማስታወስ የተሰጡንንና ያሉንን ነገሮች እናበላሻቸው፡፡ የሚሰጠን ስጦታ በፈለግነው መጠቅለያ ባይታሸግ ምክንያቱ ስጦታው የተሻለ ስለሆነ ነው፡፡ ምንጊዜም ትንንሽ ነገሮችን አንግፋ፣ ምክንያቱም ወደ ትልቅ ነገር የሚያንደረድሩን እነሱ ናቸውና፡፡ የጠበቅነውን ነገር ባናገኝ እንኳን ወደ አላስፈላጊ ውሳኔ ውስጥ ለመሄድ መቸኮል የለብንም፡፡ በኋላ ላለመፀፀት፡፡ በተቻለ መጠንም ብዙ ላለመጠበቅ ጥረት እናድርግ፡፡ ብዙ ጠብቀን የጠበቅነውን ያህል ብናገኝ ብዙም አንደሰትም፡፡ ከጠበቅነው በታች ብናገኝ ደግሞ በጣም እናዝናለን፡፡ ከሰዎች በሚደረግልን ችሮታና ስጦታ በጣም ለመደሰት ከፈለግን ጥሩው ዘዴ ቀድሞውኑ ትንሽ መጠበቅ ነው፡፡ ስጦታው ወይም ችሮታው ከጠበቅነው በላይ መሆን ሲጀምር በአድናቆ እንደሰታለንና፡፡

ትዝብት ከአሜሪካ

ፒያሣ ገበያ ሲመጡ ምንም እንደማያጡ ይተማመኑ

በጣም የሚያማምሩ ነገሮች የሚታዩም

የሚጨበጡም አይደሉም!!

ሚስት ለልደቷ ከባሏ ስጦታ ትጠብቃለች፡፡ ለብዙ ወራት መደብር ማሳያ ውስጥ ያየችውን የዳይመንድ ቀለበት ስትመኘው ነው የቆየችው፣ ባለቤቷ ወጪውን የመሸፈን አቅም እንዳለው ስለምታውቅ ሲሆን፣ የምትፈልገውንም ስጦታ በግልፅ ነግራዋለች፡፡

የልደት ቀኗ በተቃረበ ቁጥር፣ ይህቺ ሴት ባሏ የዳይመንድ ቀለበቱን የመግዛት ምልክት እንዲያሳያት እየጠበቀች ነው፡፡ በመጨረሻ በልደት ቀኗ ማለዳ ላይ፣ ባል ሚስቱን ወደ ጥናት ክፍሉ ጠራት፡፡ ከዚያም እንደሷ ያለ ሚስት በማግኘቱ ምን ያህል እንደሚኮራ ነገራት፡፡ ፍቅሩን ከገለፀላት በኋላም የሚያምር የስጦታ ሳጥን አቀበላት፡፡

እጅግ በመጣደፍ የስጦታ ዕቃውን ከፈተችው፡፡ ከዛም ስሟ በወረቀት የተፃፈበትን መጽሐፍ ቅዱስ ነበር ያገኘችው፡፡

የአገዛዙ የቀድሞው የአየር ሀይል አዛዥ የይስሙላው ፓርላማ የአገሪቱን ሀብት ከሚያባክን ይፍረስ ሲሉ ጠየቁ

* የመቶ በመቶ ምርጫ ውጤት አያስጨፍርም የችግር ማሳያ ነው * ሙስናና የመልካም አስተዳደር ዕጦት አገሪቱን አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊጥል

ይችላል አሉጥንቅር በሃብታሙ አሰፋየአገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን የተሰጠው ፓርላማ ህገ-መንግስታዊ

ስልጣኑን ተጠቅሞ የዜጎችን ጥቅም ማስጠበቅ ካልቻለ አሁን እንዳለበት የገዥው ፓርቲ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ብቻ ለይስሙላ ከተቀመጠ የህዝቡን አደራ መሸከም ካልቻሉ የአገሪቱዋን ሀብት ያለ አግባብ ከሚባክን ህዝበ ውሳኔ አዘጋጅቶ የማይረባ መሆኑ ህጋዊ ድጋፍ አግኝቶ ተቋሙን ማፍረስ ነው ሲሉ የአገዛዙ የቀድሞ የአየር ሀይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሀይማኖት በቅፅል ስማቸው ጆቤ ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ጥናት ላይ ገለፁ።

በ1993 ህውሐት ለሁለት ሲከፈል አንጃ ተብለው ከተባረሩት መካከል አንዱ የሆኑት ጆቤ (ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት) ከእነ አቶ ስየ ገብሩ አስራት በተለየ የስርዓቱ ደጋፊ ሆነው የቆዩ ሲሆን ሰሞኑን በኢንተርኔት በተሰራጨው ብልሹ አስተዳደርና የዴሞክራሲ ምህዳር በማስፋትና በተቋማት ግንባታ በሚለው ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባቀረቡት ጥናት ስርዓቱ እየተባለሸ የሔዱ የፍትህ መጓደልና ሙስናና በሀብታምና በደሃ መካከል ያለው የተጋነነ ልዩነት ድህነት አደገኛ ሁኔታ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ዘርዝረዋል።

አገዛዙ የሚፎክርበትን የመቶ በመቶ የምርጫ ውጤት ማሸነፉን በተመለከተ ሜ/ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) በዚሁ ጥናት እንደገለፁት “ብዙ ማንነቶች፣ በርካታ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች መልስ እንሻለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ባሉበት አገር አንድ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አገሮቹ መቶ በመቶ መቀመጫውን መቆጣጠር እሚያሳየን ነገር አንድም ፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ችግር መኖሩን አልያም የምርጫ ስርዓቱ ችግር እንደነበረበት ነው። መቶ በመቶ እሚባል ውጤት አስቁኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ይሔ ውጤት አስቂኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ይሔ ውጤት አርቆ ለሚያስብ ሰው አደጋ እንጅ የድል ምልክት ተደርጎ መቆጣጠር አይቻልም ሲሉ አጣጥለውታል የዴሞክራሲ ምህዳሩ እየጠበበ መሔድ አገሪቱዋን ወደ አላስፈላጊ መንገድ ይመራል የሚለው ይሄው ጥናት አያይዘውም ተራ ፍርድ የማግኘት ጉዳይ አይደለም ሙስናና የመልካም ያልሆነ አስተዳደር አገርን ሊበትን የሚችል ነው ይላል::

የቀድሞው የአገዛዙ ጄኔራል በጥናታቸው ለስርዓቱ አደገኛ ያሉዋቸውን ዋና ዋና ችግሮች ያመላከቱ ሲሆን አንድ ገዥ ፓርቲ በእኔ አውቅልሃለሁ ብቻ መራመድ አደገኛ ሁኔታን ይጋብዛል የመንግስትና የፓርቲም ሆነ ጥቂት በግል ስም የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃን ተራ አድርባይነት መስተካከል አለበት በዚሁ ከቀጠሉ አደገኛ ነው ካሉ በኋላ ህግ ከሚፈቅደው ውጭ ገለልተኛ ሊሆን የሚገባው መከላከያ ሳይቀር ለህውሓት ልሳን የሆነውን ወይን ጋዜጣን በገንዘብ በተዘዋዋሪ መደጎሙ አስገራሚ ዕብሪት ነው ካሉ በኋላ በምርጫ ሰሞን በአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሙሉ የህውሓት 40ኛ ዓመት ልደት ከፍተኛ ሽፋን መስጠቱ በተቃራኒው ለተቀዋሚዎች የሚተነፍሱበት ሁኔታ መጥበቡን አመላክተዋል።

በሕውሓት ጉባኤ ሰሞን የተወሱ ጄኔራሎች መቀሌ ላይ መታየታቸውን ሰው ነገረኝ ነገር ግን የሔዱት ልግል ጉዳይ ሊሆን ይችላል እንጂ በህግ የሚያስቆጣ ተግባር ስለሆነ የፖለቲካ ተፅዕኖ ለመፍጠር መቀሌ ገብተዋል ለማለት ማስረጃ የለም እያሉ የደረሳቸውን መረጃ በዚሁ ጥናት ያጣጣሉት የቀድሞው የአገዛዙ የአየር ሀይል አዛዥ በጥናቱ እንዳስቀመጡት “በተለይ የመከላከያ

ጉዳይ አሳሳቢ ነው በታዳጊ አገር ስለምንገኝ እና ዴሚክራቲክ ተቋሞቻችን ደካማ በሆኑበት ግዜ የታጠቀው ሃይል ወይ ራሳዩ ንጉስ ወይም አንጋሽና አፍራሽ ለመሆን ይዳዳዋል አሁን የታየው ምልክት እንዳይሰፋ ከወዲሁ መጠናት አለበት የሲቪሉ ቁጥጥር መጠናከር አለበት ሲሉ ስጋታቸውን ጠቅሰዋል ። የመከላከያን ከፍተኛ ስልጣን ሙሉ በሚያሰኝ ደረጃ የተቆጣጠሩት ከአንድ የትግራይ ብሔር የተውጣጡ መሆናቸውን ተከትሎ የሚቀርበውን ቅሬታ በዚህ ጥናት ሳያነሱ አልዋል።

የቀድሞው የአገዛዙ የአየር ሀይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አበበ (ጆቤ) አቶ ገብሩ አስራት የህውሓትን ገበና ያጋለጡበትን<< ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ>> የተሰኘውን መፅሐፍ ተችተው አቶ መለስና ሜጄር ጄኔራል ሳሞራ የነሱትን ለመደገፍ መሞከራቸውን በዚህ ጥናት ግርጌ የግል መልእክት በሚል ለማስተካከል የሞከረቱ ሲሆን አንዳንዶች ለስልጣን እጅ መንሻ አድርገው እንደቆጠሩባቸው ያም ስህተት ነው ሲሉ ለማስተባበል ሞክረዋል። የጆቤ ዋናው የጥናት ትኩረት ዛሬም እደግፈዋለሁ ያሉትን ስርዓት ወደፊት ለማስቀጠል ይረዳል ያሉትን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ስርዓቱ አይታደስም ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል የሚለውን የብዙሃኑን ድምጽ ሳያካትቱ አልፈዋል።

በምርጫ 97 ቅንጅት በከፍተኛ ድምፅ አሸንፎ ህዝባዊ ድጋፍ ሲያገኝ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተሰጠው የህዝብ ድምጽ ሲሰረቅ እና ህዝቡ በየአቅጣጫቀው ተቃቀውሞ ሲያቀርብ ከህውሓት የተባረሩ ጥቂት ጓደኞቻቸውንና በድርጅቱ የተቀየሙትን ለማስተባበርና ህውሃትን እናድን የሚል እንቅስቃሴ የጀመሩ ቢሆንም በህወሃት የበላይነት የሚመራው አገዛዝ ከ193 በላይ

ንፁሃን ገድሎ ሁኔታውን በመቆጣጠሩ ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ሳያደርጉ መቅረታቸውን ነገር ግን በምርጫ የተሸነውን የሕወሃት-ኢህአዴግ አገዛዝ ለማዳን ከጓደኞቻቸው ጋር መምከራቸውን ያለ አንዳች ሀፍረት ለአንድ መጽሔት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ መግለጻቸው አይዘነጋም።

በተቃውሞ ጎራው በኩል የስርዓቱ አደገኛ አዝማሚያ አገሪቱን ወደ አልተፈለገ ያለመረጋጋት ሊመራት ይችላል የሚለውን ስጋት የስርዓቱ ደጋፊዎች ጭምር እያሳሰባቸው መምጣቱን የቀድሞው የአገዛዙ አየር ሀይል አዛዥ ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት ጥናት የተቃውሞው ጎራ ስጋት አግባብ እንደነበር ተጨማሪ ማስረጃ ሆኖ ይጠቀሳል::

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 11

ረሐብ... ከገጽ 6 የዞረድረስ የዘለቀ አኩሪ የነጻነት ተጋድሎ ታሪክ ያላችሁ ታላቅ

ሕዝቦች መሆናችሁን አላውቅም፡፡›› ‹‹እንደ ቢ.ቢ.ሲ ባሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ያስተላለፉልንና ስለ አገራችሁ የምናውቀው የራብ፣ የጦርነትና የሰቆቃ ምድር መሆናችሁን ነው፡፡›› እንደውም አለችኝ ይህቺ ናምቢያዊት የክፍል ጓደኛዬ፤ ‹‹እንደውም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአገራችሁ ደርሶ የነበረው ረሃብ ባደረሰባችሁ አሰቃቂ እልቂት ልባቸው ክፉኛ ያዘነባቸው የአገሬ የናምቢያ አዛውንቶች አንዳንድ ሰዎች ምግብ ያለ አግባብ ሲጥሉ ሲያዩ ‹Hey please Think the Starved People in Ethiopia››› እንደሚሉ ስትነግረኝ ያ የነበረው የቀኑ ውሎ ደስታዬና በአገሬ የነጻነት ታሪክ ተጋድሎ ኩራቴ በአፍታ ወደ ኀዘን ተቀየረ፡፡ ምነው ይሄን መጽሐፍ ባላነሳሁት-በቀረብኝ በሚል ጥፍሬ ውስጥ የመግባት ያህል ሃፍርትና ውርደት ተሰማኝ፡፡ ከዛች ቅጽበት በኋላ ከዚህች ሴት ጋራ ብዙም ማውራት አልቻልኩም፡፡ ሺህ ዘመናትን ካስቆጠረው ረጅሙ ታሪካችን፣ ቅርሳችንና ሥልጣኔያችን፣ በእጅጉ ከምንኮራበት የነጻነት ተጋድሎ ታሪካችን፣ ከአምላክ ከተቸረን የተፈጥሮ ጸጋችንና ውበታችን ይልቅ ክፉ ክፉው ታሪካችን እንዲህ ከጫፍ እጫፍ መሰማቱና መናኘቱ፣ መተረቻና መጠቋቆሚያ፣ የረሃብ መዝገበ ቃላት ፍቺ

ማድመቂያ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና የእልቂት፣ የደም ምድር ‹‹አኬል ዳማ›› መገለጫ ሕዝቦች መሆናችን ግራ እያጋባኝ ይሄው ዛሬም ድረስ ይሄ ክፉ ትዝታዬ ከእኔ ጋራ ይኖራል፡፡ በእርግጥ ይህ ዓይነቱ ገጠመኝ የእኔ ብቻ ገጠመኝ ነው ብዬ አላስብም፡፡

በርካታ ኢትዮጵያውያን በሔዳችሁበት አገርና ምድር ሁሉ ተመሳሳይም ብቻም ሳይሆን እንዳውም ከኔም ገጠመኝ ካልኩትም የከፋ ብዙ አንገታችሁን ያስደፋና ያሳቀቀን ገጠመኝ እንዳለን አውቃለሁ፡፡ በዛው በደቡብ አፍሪካ የነጻ ትምህርት ዕድል አግኝቶ ከሔደ ጓደኛችን መካከል ከሌሎቻችን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወፈር ያለና የሌሎች አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ዓይነት በስፖርትና በምግብ የዳበረ ሰውነት ያለውን ወገናችንን አንዲት ደቡብ አፍሪካዊት የክፍሉ ተማሪ፣ ‹‹አንተ ረሃብ ከሌለበት የኢትዮጵያ ክፍል የመጣህ መሆን አለብህ …!?›› እንዳለችው በቁጭትና በኀዘን ሆኖ አጫውቶናል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊትም አንጋፋው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አንድ ለትምህርት ወደ ደቡብ ኮሪያ ሄዶ የነበረ ኢትዮጵያዊ ወጣት በዩኒቨርስቲው መምህራንና የክፍል ጓደኞቹ ከረሃብ እልቂትና ጦርነት ተርፎ ለዚህ ዕድል መብቃቱ ኩራት ሊሰማው እንደሚገባው በነጋ ጠባ ሲነግሩትና ሲያስረዱት እርሱም ይሄን ይረዱኝ ይሆን

በሚል ስለ አገሩ ያለውን እውነታ ቢነግራቸውም ሊያምኑት ባለመቻላቸው ባጋጠመው የሥነ-ልቦና ቀውስ፣ ብቸኝነትና ባይተዋርነት እጅጉን ተማሮ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ትምህርቱን ጥሎ ወደ አገሩ እንደተመለሰ የሚተርክ ጽሑፍ እንዳስነበበን ትዝ ይለኛል፡: በሄዱበትና በተሰደዱበት አገር በነጋ ጠባ ስለ ኢትዮጵያ የሚወራው የረሃብ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና የእልቂት ታሪክ ቅስማቸውን ሰብሮት በባእድ ምድር ቀና ብለው መራመድ እያቃታቸው በኀዘን፣ ሰቀቀንና በቁጭት አንጀታቸው እያረረ፣ እግዚኦ የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ መቼ ነው ስማችንና ታሪካችንን የምትለውጠው!? በሚል ተማኅጽኖ እንባቸውን እያፈሰሱ ከአምላካቸው ጋራ የሚሟገቱ በርካታ ወገኖች ዛሬም ድረስ አሉን፡፡

ስለ አገራቸው፣ ስለ ወገኖቻቸው በቁጭት የሚንገበገቡ፡፡ ይህን ለዘመናት አንገታችንን ያስደፋንን የረሃብ፣ የእርስ በርስ ጦርነት የውርደት ታሪካችንን ለማደስ ጉልበቴ በርታ በርታ እያልንበት ባለንበት ዘመን ረሃብ በራችንን ዳግመኛ ማንኳኳቱና በተከታታይ ምልክቱ ቢታይም በተለየ ግን በዘንድሮው ወርኻ ክረምት በዝናም እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ለረሃብ ለተጋለጠው በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝባችንን ከረሃብ፣ ከችጋር እልቂት ይታደጉልን ዘንድ መንግሥታችን ለጋሽ አገራትንና ዓለም አቀፍ የዕርዳታ

ድርጅቶችን እየተማጸነ ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ የሚሠሩ ወርቅ እጆችን ይዘን ስንዴ ልመና እንዴት ይታሰባል፣ ሕልማችን ሕዝባችንን በቀን ሦስት ጊዜ ማብላት ነው፣ ረሃብን ታሪክ እናደርገዋለን፣ በምግብ እህል ራሳችንን እየቻልን ነው … ዕድገታችንን የኢኮኖሚ ግሥጋሤያችን ዓለም ሁሉ እጁን በአፉ ላይ እንዲጭን እያደረግነው ነው … ወዘተ እንዳልተባልን፣ እንዳላስባልን ዛሬ ግን ይኸው ዓይናችንን በጨው አጥበን በምዕራባውያኑ ደጃፍ ምግብ ልመና አኩፋዳችንን ይዘን መሰለፋችን እጅጉን ያሸማቅቃል፣ ያሳፍራልም፡፡

መንግሥት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ባለፈው ወርኻ ክረምት የዝናም ስርጭቱ ዝቅተኛና የተጠበቀውያን ያህል ባለመሆኑ የተነሣ ከ፬.፭ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለረሃብ እንደተጋለጠና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አሳውቆአል፡፡ ለረሃብ የተጋለጡትን ወገኖቻችንን ቁጥር በተመለከተ መንግሥት ይፋ ያደረገው ቁጥር የተዛባ መሆኑን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየገለጹ ነው፡፡ እነዚሁ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና የዕርዳታ ድርጅቶች ለረሃብ የተጋለጠው ሕዝባችን ቁጥር ወደ ፯ ሚሊዮን እንደሚጠጋና ይህ ቁጥርም ወደፊት ሊያሻቅብ እንደሚችል እየተናገሩና እያስጠነቀቁ መሆናቸው ሌላኛው በፊታችን የተጋረጠብን ክፉ ዜና/መርዶ መሆኑ ማወቅ ሁላችንንም ግድ ይለናል፡፡ ሰላም! -

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 12

ወንዶች... ከገጽ 8 የዞረ

እያንዳንዱ አቀራረብሽ የወንዱን ትኩረት የሚበትንና የአንቺን መስህብነት በአትኩሮ ውስጥ እንዲመሰጥ ማድረጉ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም አቀራረብሽ ይህን ሕግ ሊከተል ይገባል እንጂ እንደተለመደው አይነት ተራ አቀራረብ ሊሆን አይገባም፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ሁልጊዜም ቢሆን ይህን መሰል መስህባዊ ገፅታን መላበስ ይጠበቅብሻል፡፡ የተፈላጊነትን ስሜትን መፍጠር፣ ትኩረትን ወዳንቺ መሳብ፣ የሚፈለጉ ነጥቦች መሆናቸውን አትርሺ፡፡ በአነጋገርሽ፣ በአለባበስሽ፣ በሽቶሽ፣ በእክብካቤሽና፣ በፈቅር ጨዋታሽ፡፡

ሕግ 5 የአማላይነት ባህሪ የሚያሳድጉሽ ነው፡- እንደሚታወቀው በተፈጥሯቸው በአንድ ወይም በሁለት ምክንያቶች ከፍተኛ የማማለል ባህሪ የተካኑ ሴቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በታሪክ ውስጥ በአማላይነታቸው የሚታወቁት ሴቶች ስለማማለል ስነ ልቦና አልተማሩም ወይም አላበቡም፡፡ ይህን ክህሎት ግን በተፈጥሯቸው የታደሉት ባህሪ ነው፡፡ የስነ ልቦናም ጥናቶች እንዳስቀመጡት ከሆነ ደግሞ የትኛውንም ባህሪ በአዲስ መልክ መካን ይቻላል፡

፡ የግድ በተፈጥሮ ላንታደለው እንችላለን፡፡ ማዳበር የምንፈልገውን ባህሪ ግን ደጋግሞ በመተግበር የራሳችን እንዲሆን ልናደርገውና እንደውም ተፈጥሯዊ መለያችን እስኪመስል ድረስ ከእኛ ጋር እንዲኖርና እንዲንፀባረቅ ልናደርገው እንችላለን፡፡ በመሆኑም ዕድሜ ልክሽን በወንዱ ልብ ውስጥ በፍቅር ለመቀጠል ማድረግ ያለብሽ ነገር ቢኖር የማማለያ ጥበቦቹን ደጋግመሽ በመለማመድ በዘለቄታዊነት ባህሪሽ እንዲሆኑ ማድረግ ትችያለሽ፡፡ አንድ እውቀት ወደባህሪ ደረጃ የሚዳብረውና አብሮሽም ሊቆይ የሚችለው እውቀቱን በተግባር ደጋግመሽ ስትለማመጂው መሆኑን ማወቅ ይኖርብሻል፡፡ ልክ አሪፍ የውሃ ዋና ብቃት ይኖርሽ ዘንድ ደጋግመሽ መዋኘት እንደመኖርብሽ ሁሉ የማማለል ብቃትም ከዚሁ ጋር ይመሳሰላል፡፡

ሕግ 6 ሁሉም ወንዶች ሊያፈቅሩሽ አይችሉምና አትጨነቂ፡- በእርግጥ የተለያዩ የአማላይነት ብቃቶችን በተላበስሽ ቁጥር ትኩረትን የመሳብና ፍላጎትን ወዳንቺ የመግዛት አቅምሽና አድማስሽ መስፋቱ አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉንም ወንዶች ማማለል ትችያለሽ ማለት ግን አይደለም፡፡ የምትፈልጊውን አይነት ወንድ መርጠሽ ነገር ግን በአንቺ ፍላጎት ባያድርበት ልትጨነቂ አይገባም፡

፡ አማላይነትሽ በሁሉም ወንዶች ላይ ሁልጊዜ ላይሰራ ይችላል፡፡ አንቺም ራስሽ የሁሉንም አይነት ወንዶች አትኩሮትና ምርጫ ማሳካት አይጠበቅብሽምም፡፡ አንዳንድ ወንዶች እንደውም ጭራሽ ለሴት ልጅ ፍላጎት የሌላቸውም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ሕግ 7 ዋናው ነገር ልዩነት መፍጠርሽ ነው፡- በዓለማችን ላይ የተለያዩ ልዩ ተመራጭ ብቃት ያላቸውን እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሴቶች መኖራቸውን መርሳት የለብሽም፡፡ ፍቅር በምንልበት ጊዜ እንግዲህ ውድድር መሆኑንም መርሳት የለብሽ፡፡ ከብዙሃኑ ጎራ በወንዶች ዓይን ልብ ውስጥ በአንፃራዊነት የተሻለች ሴት መሆን ይጠበቅብሻል፡፡ ይህ ደግሞ ከሌሎች ተወዳዳሪ ሴቶች ወይም እሱ ከሚቀርባቸው ሴቶች ወይም ከአሁን ቀደም ከሚያውቃቸው ሴቶች የበለጠ ተመራጭ ለመሆንና ተመራጭነታችሽም ቀጣይነት ያለው ይሆን ዘንድ ከአንድ በላይ ልዩ የሚያደርጉሽ አማላይ ባህሪያትን መካን ይጠበቅብሻል፡፡

ከዚህ ህግ ውስጥ ማወቅ ያለብሽ ልዩነትሽ ላይ ማነጣጠሩ ላይ ነው፡፡ እናም አንቺ ማለት ከአንድ ወይም ሁለት ተመራጭነት በላይ ልዩ የሚያደርጉሽን ነገሮች ማብዛቱ ላይ ነው፡፡ ከተወዳዳሪዎችሽ ምንጊዜም ልቀሽ እንትታይና

ልትገኝ የሚያደርግሽ፡፡ በየጊዜው ልዩ የሚያደርጉሽን አዳዲስ ተጨማሪ ነገሮች ማሳደግ ይጠበቅብሻል፡፡ በዚህ ተለዋዋጭና እያደገ በሚሄድ አማላይ ዓለም ውስጥ አንቺም ልዩ ልዩ ባህሪያትሽን እያሳደግሽና መለወጥ ያለበትንም ሁሉ በተሻለ ነገር ለመለወጥ ዝግጁ መሆን ይጠበቅብሻል እላለሁ፡፡ ዋና ዋናዎቹ መስህባዊ ኃይሎች እነዚህ ናቸውና በራስሽ ላይ ስሪ እንጂ በወንዶቹ አትማረሪ እላለሁ፤ ሰላም፡፡

ነጋሶ... ከገጽ 1 የዞረለማምለጥና ዕድሜያቸውን ለማራዘም <<ሕገ መንግስት

እናሻሽላለን>> የሚል ማቅረባቸውን በማስታወስ የእርስዎን የሕገ መንግስት ይሻሻል ጥያቄ ሊጠቀሙበት አይችሉም ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር ነጋሶ በሩዋንዳን፣በብሩንዲና በሌሎች አፍሪካ አገሮች ስልጣንን ለማራዘም ሕገ መንግስት እናሻሽላለን መባሉን አስታውሰው ሊጠቀሙበት ይችሉ ይሆናል ነገር ግን በዚህ ፍራቻ ብቻ ሕገ መንግስት ይሻሻል ብሎ ከመጠየቅ እንደማያግድ ጠይቀዋል።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከህብር ሬዲዮ ጋር ያደረጉት ሙሉ ቃለ ምልልስ በዘሐበሻ እና ህብር ሬዲዮ ድህረ ገጾች በተጨማሪ በዩቱብ ላይ ይገኛል።

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 13

ሜሲ... ከገጽ 21 የዞረከ1992 በኋላ ታላቁን ዋንጫ ሲያነሳ የቡድኑ አባል

የነበረ ቢሆንም በግማሽ ፍፃሜው በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ሳይሰለፍ ቀርቷል፡፡

የአራት ጊዜ የወርቅ ኳስ ተሸላሚው የሆነው ኮከብ በቻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰለፍ ዕድል ያገኘው ዲሴምበር7 2007 ባርሴሎና በዶኔስክ ከሻክታር ጋር ባደረገው ጨዋታ ነበር፣ አሰልጣኝ ፍራንክ ራይካርድ ቀድሞ ከምድብ ማጣሪያ ማለፉን ያረጋገጠውን ቡድን በቋሚ ተሰላፊዎች ከመጠቀም ይልቅ አዳዲስ ፊቶችን ለመመልከት በነበረው ፍላጎት ሜሲን ከተጠባባቂ ወንበር አንስቶ ለማጫወት እቅድ ነደፈ፣ የካታላኑ ክለብም በጨዋታው 2-0 ለመሸነፍ ተገደደ፡፡

ሊዮ በቻምፒዮንስ ሊጉ የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረው ኖቬምበር 2/2005 ነበር፣ በኑካምፕ ባርሴሎና የግሪኩን ፓናቲናይኮስን 5-0 በረታበት ጨዋታ ሶስተኛውን ጎል አግብቶ በታላቁ መድረክ የጎል አካንቱን ከፈተ፡፡

በቻምፒዮንስ ሊጉ 100ኛ ጨዋታውን የፈፀመው የግራ እግሩ አጥቂ በውድድሩ አምስት ጊዜ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ሲፈፅም 48 ጎሎችንም አስቆጥሯል፤ ይህ በሁለት ጨዋታ አምድ ጎል የማስቆጠር ያህል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

በአንድ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረባቸው ጨዋታዎች 16 ደርሰዋል፤ በሶስት አጋጣሚዎች ሃትሪክ ሰርቷል፡፡ ከምንም በላይ በ2010/11 የውድድር ዘመን ግማሽ

ፍፃሜ ሪያል ማድሪድ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ባየርን ሙኒክ ላይ በኑ ካምፕ ያስቆጠራቸውን ሁለት ጎሎች መቼም ቢሆን አይዘነጋም፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ተጨማሪ የማይረሳቸው አጋጣሚዎች ተከስተዋል፡፡ በ2011/12 የውድድር ዘመን ሁለተኛው ዙር ላይ ባርሳ ባየር ሌቨርኩሰን ላይ ሰባት ጎሎችን ሲያስቆጥር (ጨዋታው 7-1 ተጠናቅቋል) ሜሲ አምስት ጎሎችን አግብቶ ነበር፣ ባለፈው ዓመት የሻክታር ዶኔስኩ አጥቂ ሉዌስ አድሪያኖ በባቴ ቦርሶቭ ላይ ተመሳሳይ የጎል መጠን እስኪያስቆጥር ድረስ የባርሴሎናው ልጅ ሪከርዱን በብቸኝነት ይዞ ነበር፡፡

በ2009/10 የውድድር ዘመን በቻምፒዮንስ ሊጉ በአንድ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረበት ወቅት ነበር፡፡ በኢምሬትስ ከአርሰናል ጋር 2-2 የተለያየው ባርሳ በኑካምፕ የሰሜን ለንደኑን ክለብ 4-1 ሲያሸንፍ የላ ሜሲያው ግኝት የተጋጣሚ ቡድን ተከላካዮችን እጅግ በጣም አሰቃይቶ አራቱንም ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ ይህንን ሲፈፅም እግርኳስን ተንከባክቦ እና ውበትን ጨምሮ ተጫውቷል፡፡

‹‹ሊዮኔል በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ መሰለፍ ይፈልጋል›› ይላል ከ2008-2010 ድረስ በባርሴሎና አብሮት የተጫወተው አጥቂው ቲዮሪ ሆንሪ፣ ‹‹በኮፓ ዴል ሬይ ከመጀመሪያው ዙር ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ መጫወት ይሻል፡፡ በልምምድ ሜዳ ላይ እንኳን ማሸነፍ

እንጂ ሽንፈት አይፈልግም፡፡ በአንድ የጨዋታ እንቅስቃሴ ጥፋት ከተፈፀመበት ከራሱ ግብ ጠባቂ ኳስ እንዲሰጠው በትህትና ጠይቆ ከፊቱ የሚገኙትን ተጨዋቾች በሙሉ አልፎ ኳስ እና መረብን ማገናኘት ይፈልጋል፡፡ ተጋጣሚው ጎል በማስቆጠር በድጋሚ ጨዋታውን ሲጀምር ድንገት ኳስ ይነጥቅና ተጨማሪ ጎል ያገባል፣ የእርሱ ቡድን እስኪያሸንፍ ድረስ ይህንን ደጋግሞ ይፈፅማል፡፡ የዚህ አይነት ተጨዋች ከዚህ ቀደም ገጥሞኝ አያውቅም››

በእርግጥም ሜሲ የእግርኳስ ‹‹ሊቅ›› ነው፣ ኧረ እንዲያውም በህይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚገኝ ታላቅ ተጨዋች መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ብቃቱ ማቆሚያ ያለው አይመስልም፣ እርሱን የሚያውቁ ይህንን ይመሰክራሉ፣ ነገሩ የተጋነነ አይደለም፣ የተጋነኑ የሚመስሉ አስተያየቶችን መስጠትም ፍትህን ማዛባት አይሆንም፡፡

‹‹የፕላኔታችን ምርጡ ተጨዋች›› የሚል ማሞካሻን ያገኘው እንዲሁ አይደለም፣ እስካሁን በነበረው የእግርኳስ ህይወት የነበረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ እና ሪከርዶቹ ከግምት ውስጥ ገብተው ነው፣ የዚህ ሁሉ ምስጢር ምን ይሆን?

‹‹ሪከርዶቼን ወደ ኋላ መለስ ብዬ አልመለከትም፤ አሁንም ድረስ እግር ኳስን እየተጫወትኩኝ የምገኘው ለዚህ ነው፡፡ እርግጥ ነው በእኔ ቦታ ላይ የሚጫወት የትኛውም ተጨዋች ጎሎችን ማስቆጠር ይሻል፤ የእኔ ቀዳሚ ግብ ዋንጫዎችን ማንሳት ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን

የሚያነሳሳኝ ዋንጫ ነው፤ ዋንጫዎችን ማንሳት ተነሳሽነት ይፈጥርብኛል፤ እንደ ቡድን ከዚህ የተሻለ ነገር ማግኘት አይቻልም›› ይላል፡፡

በዚህ ደረጃ የሚገኝ ተጨዋች ከግል ሽልማት ይልቅ በቡድን ለሚገኝ ስኬት ቅድሚያ ሲሰጥ መመልከት ያስደስታል፡፡ ተጨዋቹ በ90ሺ ወይም 90 ተመልካቾች ፊት ቢጫወት ሁልጊዜም ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ዋንጫዎችን ለማንሳት ነው፡፡

‹‹ተነሳሽት ለማግኘት አልቸገርም፤ እግርኳስን መጫወት እወዳለሁኝ፤ በልምምድ ሜዳ ላይ መገኘት ያስደስተኛል፡፡ በዚህ አይነት መልኩ በየዕለቱ የማሳልፈው ነገር ደስታ ይሰጠኛል፤ አንድ ስኬት ስታገኝ ተጨማሪ ድሎችን ደጋግመህ ማሳካት ትፈልጋለህ›› የሚል አስተያየትን የሚሰጠው ኮከብ ‹‹ልምምድም ይሁን ጨዋታ አልያም ዋንጫዎችን ማንሳት ያስደስተኛል፡፡ ምርጡ ህይወቴ እነኚህ ናቸው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ከቡድኔ ጋር ዋንጫዎችን ማንሳት እፈልጋለሁኝ፤ በቃ ይኸው ነው›› ይላል፡፡

‹‹ወርልድ ክላስ›› ተጨዋቾችን ከሌሎች መደበኛ ተጨዋቾች የሚለያቸው የድል ረሃብ ስሜታቸው ነው፤ በየጊዜው ዋንጫዎችን ለማንሳት ያላቸው ፍላጎት በድል ላይ ድል እንዲደግሙ ያስችላቸዋል፡፡

እርግጥ ነው 2014 ለሜሲ አስደሳች አልነበረም፡፡ በላ ሊጋው የመጨረሻ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድን የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ የገባው (ሜሲ.. ወደ ገጽ 23 የዞረ)

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 14

ኪነጥበብ የጤና ሞግዚት ስፖርት ወንጀል/ፍቅር

አብዱ ኪያር ዘንድሮ አንበሳ ሆኖ መጣሄርሜላ አበበ ከልደታ

የራሳቸውን ግጥምና ዜማ ከሚሰሩት ጥቂት የሃገራችን ድምጻውያን ጋር በዋነኝነት ይሰለፋል:: ብዙዎች ደግሞ መድረክ ላይ ሲጫወት ልክ እንደ ሲዲው ኩልል አርጎ በመዝፈን ያደንቁታል:: ለጥቂት አመታት አዳዲስ ስራ ሰርቶ አልቀረበም ነበር :: ምክንያቱንም ሲገልጽ ትምህርት ቤት ገብቶ ሲማር በመቆየቱ እንደሆነ አስረድቷል:: በአሁኑ ሰአት ላይ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት እራሱን አሳድጎ ሶፍትዌር ዴቨሎፐር ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል:: በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ስለሱ ሲናገሩ ሰው አክባሪ ግልጽ እና ጥርስ የማያስከድን በጣም ተጫዋች ሰው ነው ይሉታል:: እኔና በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ያደረገውን ቆይታ በኢቢኤስ ክተመለከትን በኋላ ከለፉና ከጣሩ ምንም የማይደረስ ነገር እንደሌለ ስላሳየን ወደነዋል አክብረነዋል ልባችን ውስጥም ልዩ ቦታ ሰጥተነዋል:: ከጥበቡ ውጭ ለእውቀት እንዲህ ያለ ስፍራ በመስጠቱና ከዝና ጋር ትምህርት ቤት ሄዶ ስኬታማ በመሆኑ እጅግ በጣም አድንቀነዋል ብዙም አስተምሮናል::

ድምጻዊ አብዱ ኪያር አዲሱ ጥቁር አንበሳ የተሰኘ አልበሙን እንካችሁ ብሎናል ይህ ማለት አራተኛ ስራው መሆኑ ነው:: ያለፉት ሶስቱ አልበሞቹ መርካቶ ሰፈሬ ፍቅር በአማርኛ ና ምነው ሸዋ በህዝብ ዘንድ እጅግ ከፍ ያለ ፍቅር እና አድናቆት አስገኝተውለታል::

እንግዲህ ስለ አብዱ ኪያር ይሄን ካልኩ በኋላ ወደ አዲሱ ጥቁር አንበሳ የሙዚቃ አልበም ጽሁፌን ልቀጥል:: ሁሉንም ዘፈን ያቀናበረው አሸብር ማሞ ሲሆን ታላቁ የሙዚቃ መምህር ፈለቀ ሃይሉም ተሳትፎበታል:: ተክሉ ደምሴ ሳክስፎን ሰጠኝ አጣናው ማሲንቆ በመጫወት እዚህ ስራ ላይ ተሳትፈዋል::11 ዘፈኖች ሲኖሩት የተለያየ ሪትም አላቸው ሬጌ፣ ችክችካ፣ ዙክ… በየዘፈኖቹ ላይ የሚያነሳቸው ሃሳቦች ልዩ መሆናቸውን ዘንድሮም በብዙ ዘፈኖቹ አሳይቶናል:: በየቀኑ የምናየውን ነገር ልብ ካለማለታችን ወደ ሩቅ እንመለከታለን:: አይናችን ስር ያለ ግን ደሞ አግዝፈን የማናየውን ነገር በጥበብ ቀምሮ የሰጠንን ጥቁር አንበሳን እንመልከተው:: ስንቶቻችንን ነው በአንበሳ ነው ለካ የተከበብነው እንድንል ያደረገን? ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአየር መንገድ አርማ አንበሳ የአውራ ጎዳና አርማ አንበሳ የቴሌ አርማ አንበሳ ሳንቲሞቻችን አንበሳ አንበሳ አውቶቡስ አንበሳ ጫማ አንበሳ ሻይ ስንጎብዝ አንበሳ ስንበረታ አንበሳ ስናይል አንበሳ ስንቀድም አንበሳ ስንጎብዝ አንበሳ... ለባእድ እጅ አልልሰጥም በማለት ሃገራችንን ያቆዩልንን ጥቁር አንበሶችን በዚህ መልኩ በጥበብ ሲያመጣልን ተደስተናል ታላቅ ኩራትም ተሰምቶናል::

ሆ ብሎ ሆ ከተነሳ ያስፈራል ጥቁር አንበሳእናት አገራችን ኢትዮጵያ ሆ ብሎ ሲነሳ የሚያስፈራ ህዝብ እንዳላት እናቴን

እንዳትነኩ ብሎ ሁሉም እንደ አንበሳ የሚቆጣ ህዝብ እንደሆነ በጥበብ ሲነገረን ያውም በዘፈን ኩራታችን ጨምሯል:: ሌላው የድሮውንና የወደፊቱን የገለጸበት ጥበብ ነው:: የጥንቱን ታላቅነት አሁንም የሚደረገውን አድርገን መመለስ እንዳለብን በግልጽ የሚናገር ግጥም በመሆኑ ሊሰመርበት የሚገባ የዘላለም ጥቅስ ነው::

በራስ መተማመን በውርስ ያቀበለንለመስሪ ለፓሻ ለሶልዳቶ ያልጣለንጀግና አገር አክባሪ አንበሳ አያት አለንታላቅ እንደነበርን ታላቅ እንሆናለን!!!!!!!! መስሪ ማለት የግብጽ ሰው ማለት ሲሆን ፓሻ ማለት ደግሞ የቱርክ

የውትድርና ማዕረግ ስም ነው:: ሶልዳቶ ማለት በጣሊያንኛ ወታደር ማለት ሲሆን አብዱ ኪያር ይሄን ዘፈን ሲሰራ ምን ያህል እንደተመራመረና እንደተጨነቀበት ጽሁፍ የሚችል ያውቀዋል::

አሁን ደግሞ በታላቁ የኢትዮጵያ ቅኝት በአንች ሆዬ መልካም አመት በዓል ብሎ በሰራው ዘፈን ላይ ትንሽ ልበል:: በበአሉ ለሁሉም መልካም ምኞትን ሲገልጽ ቤተሰብ ወዳጅ ጓደኛን ብቻ አይደለም ያነሳው:: በኢትዮጵያ የዘፈን ግጥም ውስጥ ተብሎና ተነግሮ በማያውቅ መልኩ ለተሰደዱ በህመም ለተሰቃዩ እንዲሁም ወህኒ እና እስር ቤት የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልካም አመት በዓል ብሎበታል::

ከአገር ርቀው ለተሰደዱትበህመም በስቃይ ካልጋ ለዋሉትበህግ ተይዘው እስር ቤት ላሉትያድርግላቸው እንደሚመኙትሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስማማ እና ብሩህ የሆነ የመልካም ምኞት

ስለሆነ በጣም ኮርኩሮኛል:: እዛው ዘፈን ላይ ሌላ እጅግ የሚደንቀው ግጥም ደግሞ ያለፈው ታሪካችን እንዴት እንደሚያኮራና ከየትና የት ሰው እንደተቀበልን የሚያሳይ ነው::

ከእየሩሳሌም ደግሞም ከመካእኛን አክብሮ ከሩቅ ጃማይካኢትዮጵያን ብሎ በኛ ሲመካ ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካተቀብለናል ትመስክር አፍሪካአብዱ ኪያርን በዚህ ግጥሙ ኢትዮጵያውያን ምን ያህል በሃይማኖት የተለያዩ

ቢሆኑም ወንድማማች እና ደራሽ ወገን መሆናቸውን አሳይቷል:: በዚህ በአሁኑ ዘመን የሃይማኖት አክራሪዎች የሚያደርጉትን እያየን እና እየተመለከትን ባለንበት ዘመን አብዱ ኪያር ይሄን የመሰለ አገራዊ ቅኝት በፍቅርና በወገን ደራሽ ስሜት ሲያንቆረቁረው ልቤን ነክቶኛል ሰውነቴን ውርር እስኪያረገኝ ድረስ በአገር ፍቅር አጥምቆኛል::

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየንየወንጌሉ ሰው ላገሬ እስላሙ ወገኑ አይደል ወይ ደራሽ ወንድሙየቁርአኑ ሰው ለክርስቲያኑ

ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ ረመዳን ስፆም በርታ የሚል ጓዴ አይዞህ የምለው ሲሆን ኩዳዴ የኔና የሱን ታላቁን ፍቅር ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክርአብዱ ኪያር ኑርልን ከክፉ ይጠብቅህ ታላቅ አገራዊ ክብር ይገባሃል:: ይህ

ዘፈን ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ለማወቅ ቅኝቱን ማወቅ ያስፈልጋል አንቺ ሆየን:: ብዙዎቹ የአንቺ ሆየ ዘፈኖች የኢትዮጵያ የሰርግ ዘፈኖች ናቸው ብዙ ጊዜም አዳዲስ ዘፈኖች በዚህ ቅኝት አይሰሩም:: አብዱ ኪያር ሂፕ ሃፕ ሬጌ ዳንስ ሆል ስታይል ዘፈኖችን እየዘፈነ ያደገ የመርካቶ የአራዳ ልጅ ሲሆን በዚህ ቅኝት ዘፍኖ ግን ድፍን የኢትዮጵያን ህዝብ አስደስቷል:: አራዳ ማለት እንዲህ ወደ ውስጣዊ ማንነቱ በጥልቀት የሚያይ መሆኑንም አስመስክሯል አንዳንድ ቅላጼው ላይም ለማ ገብረህይወትን እጅግ በጣም አስታውሶኛል:: በሚቀጥለው ክፍል ስለ አልተነጣጠልንም ስለ ዳኛው እና ስለ ሌሎቹ ዘፈኖች በስፋት እሞነጭራለሁ:: ሰላም ቆዩልኝ::

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 16

የሰዎችን የደም አይነት መቀየር ተቻለ እንዴ?

የጨጓራ ካንሰር በመላው ዓለም ሰዎችን ለሞት በማብቃት ረገድ በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን ኤች ፓይሎሪ ከተባለው የጨጓራ ባክቴሪያ ከፍተኛ ትስስር አለው ተብሏል፡፡ በደቡብ አሜሪካና በቻይና በተደረጉ የረጅም ዓመታት ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ከሆነ የጨጓራ ካንሰር ያለባቸው ወይም በጨጓራ ካንሰር ከሞቱት ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ የጨጓራ ባክቴሪያ አለባቸው፡፡

የጨጓራ ባክቴሪያ በታዳጊ አገራት ህዝቦች ውስጥ በአማካይ በ67 በመቶ ሰዎች ላይ በጨጓራቸው ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ላይ ደግሞ እስከ 90 በመቶ እንደሚደርስ ይታወቃል፡፡ በበለፀጉ አገራት ውስጥ 58 በሚሆኑ ሰዎች ጨጓራ ውስጥ ባክቴሪያው አብሮ ይኖራል፡፡ የጨጓራ ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ባክቴሪያው ከሌለባቸው ጋር ሲነፃፀሩ በስድስት እጥፍ ይጨምራል፡፡

ባክቴሪያው በዓመት በዓለም ለ600 ሺ ሰዎች በጨጓራ ካንሰር እንዲታመሙ ያጋልጣል፡፡ የጨጓራ ባክቴሪያ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በጨጓራ ካንሰር እንዲታመሙ ያጋልጣል፡፡ የጨጓራ ባክቴሪያ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በጨጓራ ህመም ወቅት በሚደረገው የደምና የትንፋሽ ምርመራም ሊታወቅ የሚችልና ባክቴሪያውንም ሊፈውሱ የሚችሉ አንቲባዮቲክ መድሃኒቶች መታከም እንደሚችል ይታወቃል፡፡ ለመሆኑ ይህ ባክቴሪያ ምንድን ነው? እንዴትስ ነው ለህመም የሚዳርገን፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የባክቴሪያው ምንጭ?

ይህ የጨጓራ ህመም መንስኤ መሆኑ የታወቀው፣ ኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያ አስገራሚ ታሪኩ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በቅርብ ጊዜ የወጡ የምርምር ውጤቶች ከምስራቅ አፍሪካ በራቁ መጠን የባክቴሪያው የመከሰትና የበሽታ ምንጭ የመሆን ዕድሉ እየቀነሰ እንደመጣ አሳይተዋል፡፡

የሰው ዘር መገኛ የሆነው ምስራቅ አፍሪካም፣ የባክቴሪያው መነሻ ስፍራ እንደነበርና ከምስራቅ ተነስቶ ወደተቀረው የዓለም ክፍል መሰራጨቱን፣ ጥልቅ የዘረመል ምርመራና ትንተና አድርገው እንደደረሱበት ተመራማሪዎቹ ይገልፃሉ፡፡ በጥናቱ ውጤት መሰረትም ኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያ ከዛሬ

58 ሺ ዓመት በፊት በምስራቅ አፍሪካ ወደተቀረው ዓለም መሰራጨት ጀምሯል፤ አለምንም አዳርሷል፡፡

ጓደኛ ወይስ ጠላት?ሁሉም ባክቴሪያው ያለበት ሰው በጨጓራ ካንሰር

ይያዛል ማለት ግን አይደለም፡፡ ነገር ግን ምልክት የሚያሳዩና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥራቸው አነስ ያለ በመሆኑ በርካቶች ከስቃይ ድነዋል፡፡ በአንዳንዶች ላይ በሽታ የመከላከል አቅማቸው እስካልተዳከመና በሆዳቸው የሚመነጩ አሲዶች መዛባት እስከተፈጠረ ድረስ ዕድሜ

ልክ ባክቴሪያውን ተሸክመውት በሽታ ሳያስከትል ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ረጅም ጊዜ የሚዘልቅና መሻሻልን የሚያሳይ የጨጓራ ህመም ያለባቸው ሰዎች፣ የህመማቸው ምክንያት ኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያ ሊሆን የመቻሉ ዕድክ ከፍ ያለ

መሆኑን ባለሞያዎቹ ይገልፃሉ፡፡ ነገር ግን ባክቴሪያው የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉ የጨጓራ ታማሚ ይሆናሉ ማለት አለመሆኑን ያስታውሳል፡፡

ባክቴሪያው የሆድ ግድግዳን ሰርስሮ በመግባት፣ የጨጓራና አንጀት ቁስለትን የሚያመጣ ሲሆን በዝቅተኛ ደረጃም ቢሆን የሆድ ካንሰር የማስከተል አቅም አለው፡፡ ለዚህ መፍትሄው ሙሉ በሙሉ እስኪድን ተገቢውን ህክምና ተከታትሎ መውሰድና መጨረስ መሆኑን ባለሞያዎች ያስታውሳሉ፡፡ በሽታ ካላስከተለ ግን ጓደኛዎ ሆኖ ተስማምቶ መኖር እንዲችል ሰውነታችን ይፈቅድለታል፡፡

በበርካታ ሰዎች ዘንድ ምንም ምልክት ሳያሳይ ሊቀመጥ የሚችለው የኤች.ፓይሎሪ ኢንፌክሽን፣ ከ10-20 በሚሆኑት ሰዎች ላይ የጨጓራ ህመምን በማስከተሉ ይታወቃል፡፡ በኢኮኖሚ ያደጉት አገራት የተሻለ ንፅህና እና የፀረ ባክቴሪያ ህክምና ያላቸው በመሆኑ፣ ችግሩ የሚበረታው እንደ እኛ ባሉ አዳጊ ሀገራት ነው፡፡ ኢንፌክሽ በአብዛኛው በልጅነት ዕድሜ ይጀምራል ወደ አዋቂነት ዘመንም አብሮ ይሸጋገራል፡፡

የባክቴሪያው ከሰው መኖሪያ ስትራቴጂና ምልክቶችባክቴሪያው ወደ ሰውነት የሚገባው፣ በዓይነ ምድር

የተበከለ ምግብና ውሃን በመጠጣት ቢሆንም፣ በባክቴሪያ በታመሙ ሰዎች ምራቅ ውስጥም ባክቴሪያው ስለሚገኝ በሰዎች ምራቅ ሊተላለፍም ይችላል፡፡ ሆድ ውስጥ ከመኪና ባክቴሪያ የሚስተካከል አሲዶች የሚመነጩ በመሆናቸው፣ አብዛኞቹ ባክቴሪያዎች ይህን ተቋቁመው መኖር ባይችሉም ኤች.ፓይሎሪ ግን ይህንንም ተቋቁሞ ወደ ሆድ ከዚያም አንጀት ላይ ዘልቆ መኖር ይችላል፡፡ ይህን ማድረግ የሚያስችለውና የሆን አሲዶች መበረዝ የሚያስችለው የራሱን ኢንዛይም ያመነጫል፡፡ የአሲዱ መጠን ዝቅተኛ በሆነበት የሆ ግድግዳ ህዋሳትም ዘንድ ተደብቆ ሊኖር ይችላል፡፡ (ኤች.ፓይሎሪ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

በተለያየ የአደጋ እና ህመም ምክንያት ከሚጠየቁ የህክምና ሥራዎች አንዱ የደም ዝውውር ነው፡፡ ለዚህ ተግባር ደግሞ ከተጎጂው ጋር ተመሳሳይ የሆነ በቂ የደም አይነትና መጠን ማግኘት ለብዙ የህክምና ተቋማት ፈታኝ ተግባር ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከሰሞኑ በካናዳው የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፣ ተመራማሪዎች የተገኘው ውጤት ግን ይህን መሰል ችግሮችን ለማቃለል መንገድ የሚጠርግ ነው እየተባለ ነው፡፡ አንዳንድ ባለሙያዎች ግን የደም አይነትን መቀየር የሰዎችን ጂን መቀየርን ይፈልጋል፤ ይህ የመተግበር ዕድሉ በጣም አናሳ ነው ሲሉ ውጤቱን ሞግተዋል፡፡ ለመሆኑ የደም አይነት ቅየራው እንዴት ባለ መልክ ነው የሚካሄደው? በጉዳት የደም ልገሳን ለሚፈልጉ ሰዎችስ ምን አይነት ፋይዳ ይኖረዋል ለሚሉትና መሰል ጥያቄዎች ተከታዩ ፅሁፍ ይሰጣል፡፡

መነሻው፡- ቆየት ባለ ትራንስፊዩዥን በተሰኘ የምርምር ጆርናል

ላይ በአንዲት የ4 ወር ዕድሜ ያላት ህጻን ላይ ተከስቶ የነበረ የደም አይነት ለውጥ በህክምናው ዘርፍ በርካቶችን አነጋግሮ ነበር፡፡ ህፃኗ ሩቤላ በሚባል በቫይረስ የሚመጣ በሽታ በታመመችበት ወቅት፣ የደም አይነቷ ከ‹ኤ› ወደ ‹ኦ› በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተቀይሮ ተገኝቶ ነበር፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ በወቅቱ ከምርመራ ስህተት ጉዳዩ ተከስቶ እንዳይሆን በሚል ተደጋጋሚ ክትትል ቢያደርጉም ውጤቱ ላይ የመጣ ለውጥ አልነበረም፡፡ በኋላ ላይ የተሰጠው ድምዳሜም ቫይረሱ በህፃኗ ደም ላይ የሚገኘውን የደም አይነት ወሳኝ ቅመም (አንቲጂን) ድምጥማጡን አጥፍቶ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም ምንም አይነት አንቲጅን የሌላቸው ሰዎች የሚይዙትን ኦ የተሰኘውን የደም አይነት ልትይዝ ችላ ይሆናል የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን ይህንን ክስተት በበለጠ ጥልቀት ለማጥናት ጥረት እየተደረገ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ ይህ ነው የሚባል በሽታ አምጪ ተዋህስያን

የሰዎችን የደም አይነት በጉዳት የመቀየር አቅም የሚያሳይ ደምዳሚ ጥናት እስካሁን አልቀረበም፡፡

የደም ልገሳን ምቹና ተደራሽ ለማድረግና፣ የደም አይነት

ለውጥን ጥረቶች የነበሩ ቢሆንም ከሰሞኑ ካናዳውያኑ ተመራማሪዎች ያገኙት ውጤት፣ በዘርፉ የተሰማ ውጤት ያለው አዲስ ወሬ ሆኗል፡፡

ጥቂት ስለደም አይነቶችየህክምና ሳይንስ ባለሞያዎች፣ አሁን በደረሱበት

እውቀት በዋናነት አራት የደም አይነቶች ቢኖሩም

በውስጣቸው ግን በርካታ ንዑስ ዘርፎችን ያካትታሉ፡፡ መሰረታዊ የሚባሉት አራት የደም አይነቶች ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ፣

እና ኦ ናቸው፡፡ እነዚህን አይነቶች በዋናነት የሚወስኑትን በቀይ የደም ህዋሳት ላይ ተጣብቀው የሚገኙት ቅመሞች (አንቲጅኖች) ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት በቀይ የደም ህዋሳቱ ላይ ‹‹ኤ›› አንቲጅን ያለው ሰው የደም አይነቱ ‹‹ኤ›› ሲባል፣ ቢ አንቲጅን ያለው ደግሞ የደም አይነቱ ‹‹ቢ›› ይባላል፡፡ ሁለቱም አንቲጅኖች የያዙ ሰዎች ደግሞ ‹‹ኤቢ›› የደም አይነት ይኖራቸዋል፡፡ ምንም አይነት አንቲጅን የሌላቸው ደግሞ ‹‹ኦ›› የደም አይነት ባለቤት ናቸው፡፡

‹‹ኦ›› የደም ባለቤቶች፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ዘንድ ደርሶ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል አንቲጅን የሌላቸው በመሆኑ ለሁሉም ሰው ደማቸውን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ‹‹ኤቢ›› የደም አይነት ያላቸው ደግሞ የትኛውም አይነት አንቲጅን ያለው ደም ቢመጣ፣ አጥቂ ነገሩን ለማርከስ የሚያስችል ፀረ አንቲጅን ስላላቸው ከሁሉም የደም አይነት ደም መቀበል ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለይ ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚነሳው አር.ኤች የተባለው የደም አይነትም፣ ከነፍሰ ጡር ሴቶችና የሚወልዷቸው ጨቅላዎች ጋር በሚነሱ የደም ዝውውር ጉዳዮች ወቅት ትኩረት ይሰጠዋል፡፡

እስካሁን ባለው የህክምና ዕውቀትና ትግበራ መሰረት፣ የደም ዝውውር ስራዎች ይህን መሰረታዊ ጭብጥ ይዘው ደም ለሚፈልጉ ሰዎች የዝምድና ምርመራን በማድረግ ያስተላልፋሉ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአብዛኛው የዓለም አገራት ያለው የደም ፍላጎትና አቅርቦት ከፍተኛ ልዩነት ያለበት በመሆኑ፣ ሰዎች በደም እጦት ዕድል የሚያስቀሩ ኢንዛይም መስራት ችለዋል፡፡ ይህ ኢንዛይም ኤ ወይም ቢ በሚባሉት የደም አይነቶች ላይ የሚገኙትን መለያ ቅመሞች (አንቲጅኖችን) ቆራርጦ በማስወገድ፣ መለያ የለሽ የደም ህዋሳት ‹‹ኦ›› የደም አይነት እንዲይዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ደሙም ለየትኛውም ሰው ሊሰጥ የሚችል የደም አይነት ይሆናል ማለት ነው፡፡

የጥናት ቡድኑ መሪ ዴቪድ ኩዋን ስለቀሪ ተግባራት ሲናገሩ፣ ‹‹ይህ በርካታ (ደም... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

ኤች.ፓይሎሪ (የጨጓራ) ባክቴሪያ ጓደኛ ወይስ ጠላት?

ታላቅ መንፈሳዊ ጥሪ - ከደብረሰላም መድሃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

ዓመታዊው የመድሃኔዓለም ክብረ በዓል

እሁድ ኖቬምበር 8, 2015

እንዲሁም ለዋዜማው ቅዳሜ ኖቬምበር 7 ቀን ታላቅ መንፈሳዊ መርሃግብሮች ብጹአን አባቶች እና ተጋባዥ እንግዶች

በሚገኙበት ይደረጋል

4401 Minnehaha Ave S Minneapolis MN 55406

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 17

የጤና ሞግዚት አዘጋጅ፦ ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

የስጋ ደዌ ነገር…የሥጋ ደዌ በሽታ ምንድነው?የሥጋ ደዌ በሽታ ማይኮባክቴሪየም ሌፕሬ /Mycobacterium leprae/ በተባለ የባክቴሪያ አይነት የሚከሰት በሽታ ሲሆን ባክቴሪያው በዋነኛነት ቆዳንና ከማዕከላዊው ስርዓት ነርቭ

ውጭ ያሉትን ነርቮችን /peripheral nerves/ የሚያወድም በሽታ ነው፡፡ ባክቴሪያውን ደግሞ ከላይ እንዳነበባችሁት እስከነአባት ስሙ ጠቅሰነዋል፡፡ ዘመዱን ማወቅ ከፈለጋችሁ የቲቢ በሽታ ነው፡፡ ከቲቢ በሽታ ጋር ብዙ የሚያመስላቸው ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ከተዋቀረበት ዘረ መል አንፃር ብናየው የሥጋ ደዌን በሽታ የሚያመጣው ባክቴሪያ ለሥራ ከሚንቀሳቀስባቸው ፕሮቲን ከተጫነባቸው 1605 ዘረ መሎች ውስጥ አንድ ሺ አራት መቶ ሰላሳ ዘጠኙ የቲቢን በሽታ በሚያመጣው ባክቴሪያ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ይገኛል፡፡

ሁለተኛው መመሳሰል ደግሞ የቲቢን በሽታ ለማከም ከምንጠቀምባቸው ‹‹5›› መድሃኒቶች ውስጥ አንዱን ለሥጋ ደዌ በሽታ እንጠቀምበታለን፡፡ ስለዚህ የሥጋ ደዌ በሽታ የእርግማን ውጤት ነው ካልን የቲቢ በሽተኞችን ተመሳሳይ ፍረጃ ልንሰጣቸው ይገባናል፡፡ ነገር ግን አላደረግንም፡፡ ምክንያቱም የእርግማን በሽታ ስላልሆነ ነው፡፡ ስለዚህ የሥጋ ደዌ በሽታን በእንጀራ እናት ዓይን ልናየው የሚገባበት ሁኔታ መኖር የለበትም፡፡

በዓለማችን ላይ ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በሥጋ ደዌ በሽታ የተጠቁ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ከ4000-5000 የሚደርሱ ሰዎች በየዓመቱ እንደሚጠቁም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በህንድ ወደ 1400 ዓ.ዓ እንደተገኘ ሲጠቁሙ በአሁኑ ሰዓት በዓለም የሥጋ ደዌ በሽተኞች ከተጠቁት ሰዎች ውስጥ 70% የህንድ ድርሻ ነው፡፡

ማሳሰቢያበዘ-ሐበሻ የጤና አምዶች ላይ የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ ለማስተማሪያነት እና ግንዛቤ ለመስጠት እንጂ እንድትታከሙበት አይደለም። ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ህመም ሲሰማ ወደ ዶ/ር ጋር በመሄድ

በዶ/ር ትዕዛዝ እንድትታከሙ አደራ እንላለን።

የግጥም ጉባዔ

ኣንችን ብቻ ከበዕውቀቱ ስዩም

ከተለየሁሽ ወድያ ስንት ቅጽሮች ፈረሱ ስንት

ሕዝቦች ፈለሱ ስንት ኮከቦች ተተኮሱ ስንት ጸሀዮች ተለኮሱ ስንት ዝነኞች ተረሱ

ስንቶችስ ካመድ ተነሱስንት ባሕሮች ደረቁ

ስንት ኣለቶች ውኃ ኣፈለቁ ስንቶች ኣማልክት ሞቱ ስንት ደናግል ገለሞቱ

ባ’ለት ኣጥር የከለሉት፤ የማይጣስ ጥሶ፤

ሾልኮ በብረት ጣት የጨበጡት፤ ከመዳፍ ሥር፤ ኣፈትልኮ ምንም ነጻ መስሎ

ቢታይ፤ ሁሉም የጊዜ ግዳይ ሁሉም የጊዜ ምርኮ

ኣንቺ ከየት ኣመጣሽው፤ የለውጥን ሞገድ መግቻ ባስቀመጥኩሽ ያገኘሁሽ፤

ኣንችን ብቻ ኣንችን ብቻ፡፡ -

ከህንድ ወደ አውሮፓ ሊመጣ የቻለበት ምክንያት ደግሞ ታላቁ እስክንድር ህንድን ድል ነስቶ ሲመለስ ባጀቡት ወታደሮች አማካኝነት እንደሆነ ምሁራን አትተዋል፡፡ ታዲያ የሥጋ ደዌ በሽታ ምክንያቱ እርግማንና ቁጣ ነው እየተባለ በሚሰበክበት ዘመን በ1873 ዓ.ም የኖርዌይ ተወላጅ የሆነው ዶ/ር አርመር ሃንሰን የተባለው ሊቅ ማይኮባክቴሪየም ሊፕሬ የተባለ ባክቴሪያ ለበሽታው ምክንያት መሆኑን ገለፀ፡፡

በዚህ ምክንያት በእንግሊዝኛው ሌፕረሲ እየተባለ የሚጠራው የሃንሰን በሽታ እየተባለ ተጠራ፡፡ ውድቀቱንና ህመሙን በእርግጣምና በቁጣ የሚያብራራ ሳይሆን በምክንያትና በማስረጃ የሚተነትን ማህበረሰብ ለመፍጠር ዶ/ር ሃንሰን በተሰጠው ዕድሜ ተጋ፡፡ አሁን የሥጋ ደዌ በሽታ የእርግማንና የዘር በሽታነቱን ትቶ መንስኤነቱ ባክቴሪያ የሆነ በሽታ መሆኑን ያለጥርጥር ታመነ፡፡ እንደውም በሐኪሞቹ ዘንድ ሌፕረሲ እየተባለ የሚጠራውን በሽታ ሀንሰን ዲዚዝ /Hansen’s Disease/ ማለት ይቀናቸዋል፡፡

ይኸውም በህዝቡ ዘንድ የተጠሉትንና የተገለሉትን በሽተኞች በተወሰነ መልኩ ለማለዘብ ታስቦ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ዶ/ር ሃንሰን ለስሙ መጠሪያ የሚሆን ቁና ሰፋ፡፡ እኛም ደግሞ ‹‹የቁምጥና በሽታ›› /ቃሉን ስለተጠቀምኩት ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ ለማስረዳት እንደሆነ ተረዱልኝ/ እያልን እንጠራው የነበረውን ፀያፍ ሆኖ ስለተገኘ ዛሬ ላይ ‹‹የሥጋ ደዌ›› በሽታ እንዳልነው ማለት ነው፡፡

የሥጋ ደዌ በሽታ እንዴት ይተላለፋል?የሥጋ ደዌ በሽታ በዘር የሚተላለፍ አይደለም፡፡ ይህ ማለት

እናት ወይም አባት በሥጋ ደዌ በሽታ ከተጠቁ ልጅ ግዴታ የሥጋ ደዌ በሽተኛ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ዘር ተጽዕኖ ያላቸው በሽታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የደም ግፊት መጨመር፣ የስኳር ህመም፣ ደም ያለመርጋት ችግር ወዘተ.. የመሳሰሉት በሽታዎች ከዘር ጋር ቁርኝት አላቸው፡፡ የሥጋ ደዌ ህመም ግን ከዚህ መስመር የወጣ ነው፡፡

የሥጋ ደዌ በሽታ የሚተላለፈው በህመሙ የተጠቃ ሰው ከአፍንጫ የሚወጣው ፈሳሽ ወደ ጤነኛው የመተንፈሻ አካል ወይም ቧንቧ በኖ የመግባት ዕድል ካገኘ ነው፡፡ በተጨማሪ ባክቴሪያው በቆዳ ላይ ስለሚገኝ ከሥጋ ደዌ በሽተኞች ጋር ለብዙ ጊዜ የሚደረግ የቆዳ ለቆዳ ንክኪ በሽታውን ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡

በተረፈ ግን ህዝባችን እንደሚያስበው የሥጋ ደዌ በሽታ በጣም ተላላፊ የሆነ በሽታ አይደለም፡፡ ይህንን እውነት

ለማቆም የሚከተሉትን የሃሳብ ክራንቾች እናምጣ፡፡1. ከ95% በላይ የሚሆነው ህዝብ የሥጋ ደዌን በሽታ

ሊያመጣ የሚችለውን ባክቴሪያ ሊመክት የሚችለውን መድህን ከሰውነቱ ታጥቋል፡፡

2. ከ85% በላይ የሆኑት የሥጋ ደዌ በሽተኞች በሽታውን አስተላላፊ አይደሉም፡፡

3. በሽታውን አስተላላፊ ከሆኑት ውስጥ ደግሞ መድሃኒቱን

በጀመሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሽታ የሚያስተላልፉበትን ችሎታ ያጣሉ፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት በ1990ዎቹ ባወጣው የጤና ግብ መሰረት የሥጋ ደዌን ህመም ቁጥርን ከ10,000 ሰዎች ውስጥ ቢበዛ አንድ ሰው ላይ ብቻ እንዲገኝ አወጀ፡፡ ይህንንም ሃሳብ እውን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አደረገ፡፡ ደግሞም ተሳክቶለታል፡፡

የሥጋ ደዌ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው

ከላይ እንደተገለፀው የሥጋ ደዌ በሽታ የሚያመጣው ባክቴሪያ ከቆዳና ነርቭ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን የምልክቶቹም መገለጫ ከእነዚህ አካላት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉት ምልክቶች የታዩበት ሰው የሥጋ ደዌን በሽታ ሊጠረጥር ይገባል፡፡

- የቆዳ ቀለም መልቀቅ ወይም ቀላ ያለ የቆዳ ጉብታ- በእነዚህ የቆዳ ለውጥ በተስተናገደባቸው ቦታዎች

ላይ ስሜት መቀነስ ወይም ሙሉ ለሙሉ መደንዘዝ ወይም መቆንጠጥ ስሜት ካለ

- ምንም ህመም የሌለው ቁል እጅ ወይም እግር ላይ ከወጣ- ጉጥ ወይም ጉብ ጉብ ያሉ የቆዳ እብጠት ፊት ላይ ከወጣ- ህመም ያለውና እብጠት ያሳየ ነርቭ

የሥጋ ደዌ በሽታ በጊዜ ካልታከመ የሚመጡ ችግሮች

1. እጅና እግር ላይ ያለው ተጽዕኖ እጅና እግር እስከመቆመጥ ድረስ የሥጋ ደቄ በሽታ

ሊያመጣ የቻለበት መንገድ ነርቭን ስለሚያጠቃ ነው፡፡ ለምሳሌ በእጃችን ላይ የተዘረጋውን አልናር ነርቭን /Uinar nerve/ ሲያጠቃ የእጃችን 4ኛ 5ኛ ጣቶች /የቀለበት ጣትንና ትንሽዬ ጣትን/ አጣሞ ያስጎነብሳቸዋል፡፡ ራዲያል የተሰኘውን ነርቭ ካበላሸ ደግሞ የመዳፍ መውደቅን ወይም መጎንበስን /Wrist drop/ ያስከትላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የነርቭ መገለሽለጥን ተከትሎ ቆዳችን ስሜት ማጣጣም ሲያቅተው ለቁስለት ይጋለጣል፡፡ ሲቆስል ወይም እግራችን ላይ አደጋ ሲገጥመን ምንም ስለማይሰማን ለተወሳሰበ ኢንፌክሽን አጋልጦ እጅ እግር ሊያሳጣ ይችላል፡፡

2. አፍንጫየአፍንጫ ልም አፅምን /Cartillage/ ስለሚበላ የአፍንጫን

ቅርጽ ሊያሳጣ ይችላል፡፡ በህክምናው አገላለፅ አፍንጫ የኮርቻ ቅርጽ ሊያሲዘው ይችላል፡፡ /Saddle-nose deformity/፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአፍንጫን የማሽተት ፀጋ ሙሉ ለሙሉ ሊያሳጣ ይችላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አፍንጫ ላይ የሚከሰተውን የቅርጽ መወላገድ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች መላ አለን ብለዋል፡፡

3. ዓይንባክቴሪያው ዓይን ላይም የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው፡፡

ይኸውም የዓይን ቆብ ውድቀት /Ptosis/ ወይም ለመግለጥ መቸገር ሲመጣ ከበተጨማሪ የኮርኒያ ቁስለት ያመጣል፡፡

4. የዘር ፍሬየሥጋ ደዌ በሽታ የዘር ፍሬ ብግነት ስለሚያመጣ

ለመካንነትና፣ ለስንፈተ (የሥጋ ደዌ... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

እሬሳ... ከገጽ 24 የዞረYaa Waaqa (አንተ አምላክ ሆይ)Jabaa hundaa olii (ከሁሉም በላይ ጥንካሬ

ያለህ)Tolchaa bobbaa fi galii (ወጥቶ መግባቱንም

የሚያሳምረው)Guraacha garaa garbaa (ጥቁሩ እና ሆደ

ሰፊው)Tokicha maqaa dhibbaa (በመቶ ስም

የሚጠራው አንድዬ)ይህ የጥቁር ነገር ከተነሳ ዘንዳ በኦሮሞ ባህል

መሰረት ጥቁር በሬ ከፍተኛ ዋጋ ያለው መሆኑን ልብ በሉ፡፡ የቢሾፍቱና የገላን አካባቢ የኦሮሞ አርሶ አደር ሁለት ነጭ በሬዎች የሚገዙበትን ዋጋ ለአንዱ ጥቁር በሬ ብቻ ሊያወጣ ይችላል፡፡

*******የኢሬሳ እና የደራራ በዓላት በጥንቱ ዘመን

ከኦሮሞ ህዝብ በተጨማሪ የምስራቅ ኩሻዊያን (Eastern Cushitic People) በሚባሉት የቤጃ፣ የሳሆ እና የሶማሊ ህዝቦችም ይከበሩ እንደነበረ ተረጋግጧል፡፡ እነዚህ ህዝቦች ቀደም ብለው የእስልምናን እምነት በመቀበላቸው በዓላቱን ማክበሩን ትተውታል፡፡ ይሁንና እንደነርሱ የኩሻዊ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው የአፋር ህዝብ እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ የኢሬሳን በዓል ያከብር እንደነበረ ልዩ ልዩ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

ሁለቱ በዓላት የሚከበሩባቸውን ወቅቶች፣ የየበዓላቱን ዓላማ እና በዓላቱ የሚከሩባቸውን አውዶች ያጠኑ ምሁራን በዓላቱ በጥንት ግብጻዊያንም ይከበሩ እንደነበረ አረጋግጠዋል፡፡ ይሁንና ተመራማሪዎቹ “የበዓላቱ ምንጭ ጥንታዊት ግብጽ ነች ወይንስ ከግብጽ በታች የሚኖሩት የኩሽ (ኑቢያ) ህዝቦች?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ተቸግረዋል፡፡ ጥያቄውን አስቸጋሪ ያደረገው የግብጻዊያኑ እምነት ብዝሃ አማልክት (Polythe-ism) የተቀላቀለበት መሆኑ ነው፡፡ ኩሻዊያኑ ግን “ዋቃ”፣ “ዋቅ፣ “ዋቆ” እያሉ በተቀራራቢ ቃላት ከሚጠሩት አንድ አምላክ በስተቀር ሌሎች አማልክት የሏቸውም፡፡ በዚህ ረገድ የሚደረገው ጥናት ሲጠናቀቅ ውጤቱ የሚታወቅ ይሆናል፡፡

ይህንን ጽሑፍ ከማጠናቀቄ በፊት አንድ ነገር ልናገር፡፡ ይህም “ኢሬቻ ባህል ነው” እየተባለ የሚነገረውን ይመለከታል፡፡ ሁሉም የምርምር ውጤቶች እንደሚያሳዩት ኢሬሳ በመሰረቱም ሆነ በይዘቱ ሃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡ አከባበሩም የዋቄፈንና እምነትን ደንብ የተከተለ ነው፡፡ ስለዚህ ሚዲያዎች በዓሉን ሲያስተዋውቁ “ኢሬቻ ሁሉን አቀፍ ባህል ነው” ማለታቸውን መተው አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ከራሱ እምነት አንጻር በዓሉን ማክበሩ የማይሆንለት በርካታ ኦሮሞ ስላለ ነው፡፡ ወደ ክብረ በዓሉ ስፍራ መሄድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መሄድ ይችላል፡፡ የማይፈልገውም እንደዚያው!

አንዳንዶች እንደሚያደርጉት “ኢሬቻ የኦሮሞነት መለያ ነው” ማለቱ ግን አግባብ አይደለም፡፡ ለምሳሌ እኔ ስለበዓሉ እዚህ የጻፍኩት ሙስሊም ነኝ፡፡ ጽሑፉን የጻፍኩትም በምርምር ሂደት ያገኘሁትን መረጃ በማቀናበር ነው እንጂ በዓሉን ስለማከብር አይደለም፡፡ ለሁሉም ግን ኢሬሳን ለሚያከብሩት የዋቄፈንና እምነት ተከታይ የኦሮሞ ወገኖቻችንን መልካም በዓል እንዲሆንላቸው እመኛለሁ!!

-----አፈንዲ ሙተቂመስከረም 22/2008ሀረር -ምስራቅ ኢትዮጵያ------ምንጮች1. Afendi Muteki: The Ittu Oromo of

Carcar, Origin, Institutions and Disper-sions (A Project on Progress)

2. Gada Melba: Oromia, An Introduc-tion to History of the Oromo People: Khar-tum፡ 1988

3. Enrico Cerulli: A Falk Literature of the Oromo People: Harvard: 1922

4. Johann L. Krapf, :Travels, Researches and Missionary Labors during an Eighteen Year’s Residence in Eastern Africa, London, 1860

5. Mohammed Hasasan: The City of Harar and the Islamization of the Oromo in Hararge, Atlanta, 1999

6. የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ “በገዳ ስርዓት የቱለማ ኦሮሞ ፖለቲካ”፤ ፊንፊኔ፣ 2000

7. ልዩ ልዩ ቃለ ምልልሶች

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 18

የወሩ ታላቅ ዜና

ኖቤል ሽልማቱ ሐዲስ እንግዳእአአ የ2011 የዓረብ ለውጥ ንቅናቄ (ዓረብ ስፕሪንግ) መነሻ በመሆን

ዕውቅና ባገኘችው ቱኒዚያ ላይ ሰሞኑንም በዚሁ ታሪኳ ላይ አዲስ ምዕራፍ ተጨምሯል። ይኸውም በንቅናቄው ወይም በአብዮቱ ሂደት አገሪቱን በሌሎች በርካታ የዓረብ አገሮች እንደታየው ካሉ የሁከት፣ የግጭትና የሽብር ድርጊት የታደጉ አራት አካላት ታላቁን ዓለም አቀፍ ሽልማት የኖቤል የሰላም ሽልማት- አሸናፊ መሆናቸው መረጋገጡ ነው።

የዘንድሮው (እአአ የ2015) የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑት «ናሽናል ዲያሎግ ኳርቴት» በሚል ስም የሚታወቁት አራት አካላት ናቸው። አራቱ አካላትም የቱኒዚያ የሠራተኛ ማህበር (ቱኒዚያን ጀኔራል ሌበር ዩኒየን) የቱኒዚያ ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ቱኒዚያን ኮንፌዴሬሽን ኦፍ ኢንዱስትሪ)

የንግድና ዕደ- ጥበብ ማህበር፣ (ትሬድ ኤንድ ሐንዲክራፍትስ) እና የቱኒዚያ ሰብዓዊ መብቶች ኅብረት እንዲሁም (ቱኒዚያ ሂውማንራይትስ ሊግ) እና የቱኒዚያ የጠበቆች ማህበር (ቱኒዚያን ኦርደር ኦፍ ሎየርስ) ናቸው። እነዚህ አካላት ወይም ሕዝባዊ ድርጅቶች የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዚን አልአቢዲን ቤን አሊ አምባገነናዊ መንግሥት በተወገደ ማግስት የተመሰረተውን መንግሥት የገጠመውንና አገሪቱን ወደ ጠቅላላ ሁከትና ግጭት አቃርቦ የነበረውን አስቸጋሪ ሁኔታ በሁሉን - አቀፍ ውይይትና ድርድር እንዲቃለልና እንዲወገድ በማድረግ ወደ ዴሞክራሲ ለሚደረገው ሽግግር አመቺ ሁኔታ መፍጠራቸው ተረጋግጧል። አገሪቱን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር ያደረገው የተጠቀሱት ሕዝባዊ ድርጅት ተግባር «የኖቤልን የሰላም ኮሚቴ» ዕውቅና በማግኘት ለሽልማት አብቅቷቸዋል። ሽልማቱን 1.2 ሚሊዮን ዶላር የወርቅ ሜዳሊያና ዲፕሎማ ወይም የምስክር ወረቀት ያስገኛል።

በቱኒዚያ የለውጥ እንቅስቃሴው የተጀመረ አአአ በ2010 ውስጥ በጐዳና ላይ ንግድ ኑሮውን ለመግፋት የሞከረ ወጣት ዕድሉ ሲነፈገው ራሱን አቃጥሎ ሕይወቱን ያጠፋበትን ሁኔታ ተከትሎ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ የተነሳው የተቃውሞ እንቅስቃሴ እያደገ መጥቶ እአአ ጥር 2011 የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዚን አልአቢዲን ቤን አሊ ከሥልጣን ተወግደዋል። የእርሳቸው መንግሥት በወደቀ ማግስት የተመሰረተው መንግሥት የአገሪቱን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች በቅፅበት ማስወገድ አልተቻለም። ፅንፈኛና አክራሪ ቡድኖች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሁከት ከመፍጠር አልተኙም። ይህ እንቅስቃሴ ሁለት

ለዘብተኛ አቋም እንደነበራ ቸው ከተነገረላቸው ሞሐመድ አብዱራሂምና ቾክሪ ቤላይድ ከተባሉት ታዋቂ ፖለቲከኞች መገደል ጋር ተዳምሮ በወቅቱ በሥልጣን የነበረውንና «ኢናህዳ» በተባለው የፖለቲካ ፓርቲ የሚመራው መንግሥት አገሪቱን በጥንካሬ ለመምራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ።

ሁኔታው አገሪቱን ወደ ጠቅላላ ሁከትና ግጭት በማቃረቡ የተጠቀሱት ሕዝባዊ ድርጅቶች ብሔራዊ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ያደረጉት ጥረት በመጀመሪያ ጊዜያዊ የአንድነት መንግሥት እንዲመሠረት ቀጥሎም በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አዲስ መንግሥት የሚመሰረትበትን ሁኔታ አመቻችተዋል። በዚህም መሠረት ከእአአ 2011 አንስቶ ገዢ የፖለቲካ ፓርቲና በነበረው «ኢናህዳ» እና «ኒዳ ቱኒስ» የተባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋነኞች ተፎካካሪዎች የሆኑበት ጠቅላላ ምርጫ ተካሔዶ በተገኘው ውጤት መሠረት

ቱኒዚያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተሸጋግራለች። ይኸው ምርጫ ቱኒዚያ እአአ በ1956 ነፃነቷን ከፈረንሳይ ካገኘችበት ጊዜ ወዲህ በነፃነትና በግልፅነት የተካሔደ ምርጫ እንደሆነ ተነግሮለታል። በምርጫው «የኒዳ ቱኒስ» መሪ የሆኑት አንጋፋ ፖለቲከኛ ቤጂ ካይድ ኢሴብሲ አሸንፈው ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መሥርተዋል።

የዓረብ ለውጥ ንቅናቄ ወይም አብዮት ከተካሔደባቸው የዓረብ አገሮች መካከል ሶሪያና የመን ወደ እርስበርስ ጦርነት ገብተው ሕዝቦች ለእልቂትና ለስድት ተዳርገዋል። በቱኒዚያ ግን ተመሳሳይ ሁኔታ አሳይቶ የነበረው ሁኔታ በተጠቀሱት ሕዝባዊ ድርጅቶች መሪዎች አርቆ አስተዋይነትና የፖለቲካ ኃይሎችም ለውይይትና ድርድር ያሳዩት በጐ ፈቃደኝነት ከተጠቀሰው ስምምነት ላይ በማድረስ በዚህ ረገድ አገሪቱ በአርአያነት እንድትታይ አድርጓል። የተጠቀሱት አካላት ያደረጉት የሰላም ጥረትም እንደተጠቀ ሰው በኖቤል የሰላም ኮሜቲ ተቀባይነትን አግኝቶ ለሽልማት አብቅቷል።

ሐውሲን አባሲ የተባሉት የቱኒዚያ ሠራተኛ ማህበር መሪ አካላቱ ለኖቤለ የሰላም ሽልማት መርጃ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት «ናሽናል ዲያሎግ ኳርቴት የሽልማቱ አሸናፊ መሆኑ ለዴሞክራሲያዊት ቱኒዚያ ሰማዕታት የተሰጠ ዕውቅና እንደሆነ ገልፀዋል።

ቱኒዚያ አሁንም ከሽብርተኞች እንቅስቃሴ ነፃ እንደሆነች ታውቋል። በቅርቡ ቱኒስ ውስጥ በሚገኘው ቦርዶ ሙዚየም ውስጥ 22 ሰዎች የተገደሉበት እንዲሁም በሱሲ የጠረፍ (ኖቤል... ወደ ገጽ 22 የዞረ)

ያልተነገሩ ሙዚቃ

4 ጥቅሞችስለ ሙዚቃ እና አንጎል ዝምድና የሚያወሩ በርካታ የጥናት ሥራ ውጤቶች አሉ፡

፡ ሙዚቃ አንጎል ላይ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአካል ክፍሎች ላይም አይነተኛ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ይታወቃል፡፡

ከቅርብ ጊዜዲህ ይፋ እየሆኑ ከሚገኙ የጥናት ሥራ ውጤቶች መካከል አንዱ ሙዚቃ የፈጠራ ችሎታን ያሻሽላል የሚል ይገኝበታል፡፡ ከዚህ መረጃ ጋር በተያያዘ ይሁን አይሁን በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም በተለያየ የፈጠራ መስክ ሥራ ላይ የሚገኙ የፈጠራ ሰዎች በአመዛኙ ከሙዚቃ ጋር ጥብቅ ትስስር አላቸው፡፡ የስዕል ሥራቸውን እያከናወኑ ሙዚቃ የሚያዳምጡ ሰዓሊዎች ማየት ለአብነት ያህል የተለመደ ነው፡፡ በትምህርት ቤቶች አካባቢም ጥናት እያጠኑ ሙዚቃ የመስማት ልምድ ያላቸው ተማሪዎች አሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ግጥምን በጃዝ አጅቦ የማቅረብ ልምድም አብነት ሊሆን ይችላል፡፡ የግጥም ሥራቸውን ከጃዝ ሙዚቃው ጋር አጣምረው እና አዋህደው ለተመልካች ማቅረብ የቻሉት ገጣሚዎች ሲጀመር ግጥሙንም ሲፅፉም ሆነ ከመፃፋቸው በፊት ተነሳሽነት እና ስሜት ውስጣቸው ለመቀስቀስ ሙዚቃ ሊያዳምጡ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡

1. ሙዚቃ ለማለም አቋራጭ መንገድ ነውዳንኤል ሌቪቲን የሚባል ግለሰብ ማክጊል ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሰራው ጥናት መሰረት

ሙዚቃ አንጎልን በጥልቀት ማለም የሚችልበት ሁኔታ ውስጥ አዋዝቶ ይከተዋል ይላል፡፡ ብዙ በተለይ ደግሞ ከኪነ ጥበብ ሥራ ጋር የተያያዙ ፈጠራዎች የሳይንስ የፈጠራ ሥራዎችንም ሊጨምር ይችላል፡፡ ከአንጎል ማለም ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ዝነኛው ፊዚሲስት አንስታይን ምናብ ከእውቀት ይበልጣል ያለውም ለዚህ ይሆናል፡፡ ሰፊ ምናብ ያለው የፈጠራ አቅሙም ላቅ ያለ ነው፡፡ በመሆኑም ሙዚቃ የማለም አቅማችንን እና ምናባችንን በማስፋት የፈጠራ ችሎታን ከፍ ያደርጋል፡፡

2. ሙዚቃ ውስብስብ ስሜቶችን ለመረዳት ይረዳልውስብስብ የሆኑ ስሜቶችን በሥራችሁ ውስጥ መግለፅ የምትፈልጉ ከሆነ ሙዚቃ

በእጅጉ ሊረዳችሁ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፣ በህይወት ስለተለያችሁ አንድ ሰው ማስታወሻ ታሪክ ለመፃፍ ስትነሱ የሀዘን ስሜትን የሚያጭሩ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ጠቃሚ ነው፡፡ በርሊን ፍሪ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ አጥኚዎች የሀዘን ስሜትን የሚገልፁ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ እርጋታን፣ ሰላምን እና ናፍቆት የመሳሰሉትን ስሜቶች በጥልቀት ለመረዳት እና ለመግለፅ ይረዳል ይላሉ፡፡ በሚገርም መልኩ የሀዘን ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ከሀዘን ይልቅ ናፍቆትን በመቀስቀስ የመውደድ ስሜት ውስጥ የመክተት ጉልበት አለው፡፡

እያዘኑ እስክስታ የሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ስለ ባዕድ ሀገር ኑሮ አንጀትን በሚበላ መልኩ የሚያቀነቅነው ይኸው ዘፈን አድማጩን ላቡ እስኪንጠባጠብ ድረስ እስክስታ የሚያስመታም ነው፡፡ ስለ አዛኝ ሁኔታ ቢሆንም ዘፈኑ የሚያወራው አንድ ሰው በሀዘን ስሜት ተኮራምቶ እንዲቀመጥ አያደርግም፡፡ በመሆኑም ሙዚቃ ውስብስብ እንዲሁም ጥልቅ የሆኑ የሰው ልጅ ስሜትን የመግለፅ አቅም ስላለው አድማጩም እነዚህን ስሜቶች እንዲረዳና በሥራው ውስጥም እንዲገልፃቸው ያግዛል፡፡ ስሜትን መረዳት እና መግለፅ መቻል በሌላ በኩል የፈጠራ ችሎታን ያሻሽላል፡፡

3. የሞዛርትን ሙዚቃ ማዳመጥ አይጠበቅባችሁምቀደም ሲል የተሰሩ ጥናቶች የሞዛርት የሙዚቃ ሥራዎች አንጎልን በእጅጉ

የማነቃቃት ኃይል እንዳላቸው ያሳያሉ፡፡ አሁን ላይ እየተካሄዱ የሚገኙ ተጨማሪ ጥናቶች ግን ከሞዛርት ውጭ ማንኛውም ዓይነት ሙዚቃ አንጎልን የማነቃቃት ኃይል እንዳለው የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ዋናው መመዘኛ የአድማጩ ስሜት ብቻ ነው፡፡ የምትወዷቸው እና ስሜታችሁን ኮርኩረው ነፍስ የሚዘሩባችሁ ሙዚቃዎች እስካሁን ድረስ እነዚህ ሙዚቃዎች አንጎላችሁን የማነቃቃት እና የፈጠራ ችሎታህን በዛው ልክ ከፍ የማድረግ ጉልበት አላቸው፡፡ ፍራንሴስ ሮሸር የተባሉ ሳይኮሎጂስት ‹‹ምስጢሩ የምታዳምጡትን ሙዚቃ ከመውደዳችሁ ወይም ካለመውደዳችሁ ጋር ብቻ የተያያዘ ነው›› ይላሉ፡፡ ይህ ለፈጣሪ የሚሆኑት ለስላሳ ሙዚቃዎች ብቻ ናቸው የሚለውን የተለመደ አስተሳሰብ የሚጋፋ ነው፡፡ የትኛውም ሙዚቃ እስከወደድነው ድረስ ንቃት ሊያላብሰን እና የፈጠራ አቅማችንን በዛው ልክ ሊያሳድግ ይችላል፡፡

4. በሥራ ጊዜ በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን አዳምጡ

የምትሰሩበት ሥራ በዋናነት ከፅሑፍ ጋር የተያያዘ ከሆነ ግጥም እና ድምፃዊ ያላቸውን ሙዚቃዎች ወደ ጎን በማድረግ በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ይመከራል፡፡ አብረው እያቀነቀኑ ሥራ ከመስራት ይልቅ በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን እያዳመጡ ሥራን መስራት ትኩረት ለማድረግ እና አንጎልን ለማነቃቃት እንዲሁም የፈጠራ ችሎታን በዛውም ልክ ለማሻሻል ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡

SUB-SAHARAN AFRICAN YOUTH and FAMILY SERVICES (SAYFSM)

Lakkoofsa bilbilaa፡ (651)644-3983, (651)644-1470, (612)554-5676የስልክ ቁጥር፤ (651)644-3983, (651)644-1470, (612)554-5676

SAYFSM Dhaaba Hawaasummaa namoota dhalootan Afrikaanota ta’aniifi tajaajila garaagaraa kan laatudha.-Daddarbaa Vayirasii HIV/AIDS to’achuudhaafi dhaabni kun (SAYFSM) barnoota fayyummaa barsiisa, Kondomii raabsa, akkasumas qorannaa dhiigaa tola hojjeata-Qorannaan dhiigaa kun namoota leenjii ga’aa fi ragaa ogummaa qa-baniin raawwatama-Namnni fedha qoratamuu qabu waajjira SAYFSM keessatti yookiin bakka abbaan dhiimmaa itti amanetti qoratamuu danda’a-Namni nubiratti (SAYFSM) qoratamu icitiin odeeffannoosaa sadarkaa cimaatti eegama.**************************************************************************** SAYFSM Dhaabbata MNsure wajjin walii galuudhan namoota In-shuuraansii fayyaa hinqabneefi gargaarsa iyyannoo barreessuu laataHanga ammaatti jiraattota Minnesota tiifi gargaarsa heddu kennee jiraOdeeffannoon abbaan dhimmaa himatu hundi icitiidhaan eegamaMNsure tti iyyannoo galfachuu yoo barbaaddan beellama otuu hin qa-batin yeroo gabaabaa keessatti dhimma keessan xumurattu

* SAYFSM በትዉልድ አፍሪካዊያን ለሆኑ ግለሰቦች የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሰብአዊ ድርጅት ነዉ፤* የ HIV/AIDSን ስርጭት ለመግታት ድርጅቱ (SAYFSM) ኮንዶም ያድላል፣ የጤና ትምህርትና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ ነጻ የደም ምርመራ ያከናዉናል፤* የደም ምርመራዉ በቂ ስልጥና ባላቸዉና ችሎታቸዉ በተመሰከረላቸዉ ባለሙያዎች ይከናወናል፤* HIV ለመመርመር ፍላጎት ያለዉ ማንኛዉም ግለሰብ በድርጅቱ በጽህፈት ቤት ወይንም ባለጉዳዪ ባመነበት ቦታ ምርመራዉ ሊከናወን ይችላል* በ SAYFSM ምርመራ የሚደረግለት ግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃዉ በከፍተኛ ደረጃ ይጠበቃል። ***************************************************** SAYFSM ከMNsure ጋር በመተባበር የህክምና እንሹራንስ ለሌላቸዉ ግለሰቦች የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ሁኔታዉ በፈቀደ መሰረት እንሹራንስ እንዲያገኙ እርዳታ ያደርጋል* እስከ አሁን ድረስ ለብዙሃኑ የሚኒሶታ ነዋሪዎች በርካታ አገልግሎት ሰጥቷል* ባለጉዳይ የሚሰጠን መረጃ በሚስጥር ይጠበቃል* በ MNsure ድረግጽ (web site)የማመልከቻ ቅጽ ለመሙላት ከፈለጉ ያለቀጠሮ ጉዳይዎን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ይፈጽማሉ

1885 University Ave. W #297 St. Paul, MN 55104 Phone: 651-644-3983

ሳይኮሎጂ

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 19

በሊሊ ሞገስ

ፊት (Aloe)ፊት ለቆዳ በጣም አስፈላጊ ጥቅም ይሰጣል፡፡ የፊት ጄልን ሁልጊዜ ከንፈር ላይ በማድረግ የከንፈርን

ጤንነት መጠበቅ ይቻላል፡፡

የኮከናት ዘይት (Coconut Oil)የኮኮናት ዘይት የተሰነጣጠቀ እና የደረቀ ከንፈር እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ትንሽ የኮከናት ዘይት

በተደጋጋሚ በተለይ በቅዝቃዜና በደረቅ ወቅት መጠቀም የከንፈርን ጤንነት፣ ውበት እና ልስላሴን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

የፈረንጅ ዱባ (Cucumber)የተቆረጠ የፈረንጅ ዱባ መውሰድ እና ከንፈርን በዚያ ማሸት (ማሳጅ ማድረግ) የከንፈርን ጤንነት እና

ልስላሴን ይጠብቃል፡፡

ማርና ቫዝሊን (Honey and Petroleum Jelly)ከፍተኛ የምግብነት ኃይል ያለው ማር ባክቴሪያ እንዳይኖርም ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ቆዳን

ከድርቀት ይከላከላል፡፡ ማርና ቫዝሊን በመቀላቀል ምርጥ የሆነ ቅባት አዘጋጅቶ መጠቀምም ይቻላል፡፡

አዘገጃጀት እና አጠቃቀምትንሽ ማር በመውሰድ መቀባትና እንዲደርቅ ለትንሽ ደቂቃ መጠበቅ፡፡ በመቀጠልም ከንፈር ምንም

ሳይንቀሳቀስ ከላይ ትንሽ ቫዝሊን በመቀባት ከ10-15 ደቂቃ እንዲቆይ ማድረግ፡፡ በመጨረሻም ለብ ባለ ውሃ መታጠብ፡፡ ይህንንም በቀን አንድ ጊዜ ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ያህል ማድረግ ደረቅ ከንፈር እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

ፓፓያ (Papaya)ፓፓያን በመጠቀም የተሰነጣጠቀ ከንፈርን መከላከል ይቻላል፡፡ የውስጡን ፓፓያ መውሰድና ከ10-15

ደቂቃ ከንፈር ላይ መቀባትና በመጨረሻም መታጠብ፡፡ ከንፈር ለስላሳ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ውሃበቂ ውሃን በደንብ አለመጠጣት ደረቅ እና የተሰነጣጠቀ ከንፈር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ በቀን ከ2-3

ሊትር ውሃ መጠጣት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የከንፈርን መሰነጣጠቅ የሚከላከል ሲሆን ሰውነት ውስጥ የሚገኝንም ቆሻሻ ለማስወገድ ይረዳል፡፡

ቫይታሚን ኤየቫይታሚን ኤ እጥረት ለከንፈር መሰነጣጠቅ እና መድረቅ ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ በቫይታሚን ኤ

የበለፀጉ ምግቦችን እንደ ካሮት እና መሰል አትክልቶችን እንዲሁም ቲማቲም የመሳሰሉትን መመገብ ከንፈርን ጤናማ እና ለስላሳ ያደርጋል፡:

የሴቶች ጤና/Womens Health

ለሚሰነጣጠቅና ለሚደርቅ ከንፈርቀላል የአጠባበቅ ዘዴ

በሊሊ ሞገስ‹‹የዛሬ ዓመት፤ የዛሬ ዓመት የማሙሽ/የሚሚዬ እናት›› ብለን

እንደዳርናቸው የፈጣሪ እገዛ ተጨምሮበት ይኸው ዛሬ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ዱብ አደረጉ፡፡ ታዲያ የጓደኞቻችንን ደስታ ለመካፈል (አራስ ለመጠየቅ) ጎራ ብለናል፡፡ ደስ የሚል ቀናትን ሳይሆን ወራትን ያስቆጠረ የሚመስል ድንቡሽቡሽ ልጅ ነው፡፡ ሁላችንም ልናቅፈው ብንፈልግም አልደፈርንም፡፡ ህፃን አይደል ፈራነው፡፡ ከመካከላችን አንዷ ‹‹አራስ እንቅልፍ የለውም ይባላል እውነት ነው?›› ጠየቀች፡፡

አራሷ ጓደኛችን በፍጥነት እና የተሰላቸ በሚመስል ‹‹ድሮ የሚባለው እና ተረት የሚመስለው ሲደርስ እውነት ነው፡፡ አዎ! እንቅልፍ የሚባል ነገር የለም፡፡ ቤቢዬ ሃይለኛ ቁርጠት አለበት፤ እኔም በልጅነቴ እንዲህ ነበርኩ አሉ፡፡ ይኸውላችሁ እንደ ደህና ነገር የሆድ ህመም ወርሶ ተወሰደ፡፡ ህመሙ ሲነሳበት ቁጭ አድርጎ ያሳድረኛል›› የቻልነውን ያህል የማፅናኛ ቃል ወርውረን ወደየቤታችን ተመለስን፡፡ እኔ ግን አንድ ነገር ጥያቄ ሆኖብኛል፡፡ ሆድ ህመም በዘር ይተላለፋል?

ሐኪም ለማነጋገር እና ለማረጋገጥ ወስኛለሁ፡፡ እግረ መንገዴም የሆድ ህመም ምንነትን፣ መንስኤና መፍትሄውን እንዲነግሩኝ አንድ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም አነጋገርኩ፡፡ የዚህ ፅሑፍ ዋቢ እሳቸው ናቸው፡፡

ብዙዎቹ ይቆርጠናል፣ ያቃጥለናል ችክክ አድርጎ ይይዘናል በሌላም መንገድ የሆድ ህመማቸውን ይገልፃሉ፡፡ በጥቅሉ ግን በሆድ አካባቢ የተለየ ስሜት መኖሩ የሆድ ህመም ልንለው እንችላለን፡፡ የገበዩ ትን ዕቃ ጠቅለል አድርጎ የሚይዘው ዘንቢል አልያም ፌስታ ሉን ያስተውሉ፡፡ ከሸመቱት አንዱ የተበላሸ እንደሆነ የዘንቢሉን እ ጣ ፈንታ ልብ ይበሉ የተበላሸው ሸቀጥ ካልወጣ ሌሎችንም በክሎ ፌ ስታሉንም ማወኩ አይቀሬ ነው፡፡ ሆዳችንም ልክ እንደዚያው ነው፡፡

የላይኛው የሆዳችን ክፍል ለመታመሙ በርካታ ምክንያቶችን መጠቃቀስ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ጨጓራ፡- ጨጓራ ላይ ችግር ካለ ሆችንን ሊያቃጥለን፣ ሊቆርጠን እና ሌሎች ስሜቶችም ሊስተዋሉብን ይችላሉ፡፡

የጉበት እና ሀሞት መታወክም እንዲሁ ለሆዳችን ህመም መንስኤዎች ናቸው፡፡ የተበከለ ምግብ እና ውሃ አንጀታችንን ያስቆጣል፡፡ የሱ ሰላም ማጣት እንብርታችን አካባቢ ያለውን የሆዳችንን ክፍል ለህመም ይዳርጋል፡፡

ከእንብርታችን በታች የሽንት መተላለፊያ ቱቦዎች፣ ፊኛ በሴቶች

ደግሞ የማህፀን ችግር ሲኖር ሆድ ህመም ይኖራል፡፡ የቆዳ እና የጡንቻ ጤናማ አለመሆን ለሆድ ህመም መንስኤ

ሊሆን እንደሚችል ዶ/ር ረዘነ በርሄ አጫውተውኛል፡፡ በጥቅሉ ይላሉ እሳቸው ለሆድ ህመም መንስኤው እጅግ ብዙ ነው፡፡ በትክክል ይሄ ነው ለማለት መመርመር ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡

በተለይ የሆድ ህመም ጠንከር ያለ ከወትሮ በተለየ መልኩ የሚያጣድፍ ከሆነ ጊዜ ሳይወስዱ ሐኪም ዘንድ መሄድ ይመከራል፡፡

‹‹የሆድ ህመም ታግሰውት ከሚያለፉት ጊዜያዊ የሆድ ቁርጠት ጀምሮ በአፋጣኝ ቀዶ ህክምና ሊያስከትል የሚችል የህመም ምልክት ነው››

መነሻችን ላይ የተጨዋወትነው የአራሷ ጓደኛችን ልጅ የሆድ ህመሙን በዘር መውሰዱን የነገረችኝን ለዶ/ሩ አነሳሁላቸው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አንድ አንድ ቤተሰቦች የማይስሟሟቸው ምግቦች አሉ፡፡ ያኔ ወላጅ ሲታመም ልጆችም ምግቡን በልተው ሲታመሙ ይስተዋላል፡፡ እናም ይህ ቤተሰብ የሆድ ህመሙን ላመጣው ምግብ

አለርጂክ መሆናቸውን እንጂ በዘር መተላለፉን አያረጋግጥም፡፡ ታዲያ በምግብ ምክንያት የሆድ ህመሙ ቤተሰባቸውን ሁሉ

የሚያሰቃይ ሰዎች የዘር ነው ቢሉ አይፈረድባቸውም ሳይንሱ ግን ይህንን አላረጋገጠም፡፡

‹‹እጅግ ብዙ መንስኤዎች ያሉት የሆድ ህመም በዘር ከቤተሰብ ወደ ልጅ አይተላለፍም››

የሆድ ህመም መንስኤ ቀላል ነው በሚል ይህን ህመም በቤቴ ልንከባከበው ብለው ባህላዊ መድሃኒት መጠቀምም አይመከርም፡፡ በተለይ ደግሞ የሆድ ህመሙ ከትኩሳት፣ ከማቅለሽለሽ፣ ከማስመለስ፣ ከተቅማጥ ወይም ከድርቀት ጋር ከሆነ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም፡፡ የሐኪም ደጆችን በአፋጣኝ ማንኳኳት ተመራጭ ነው፡፡

ብዙውን ጊዜ የቤቱን እማወራ እምናደንቃቸው በሚያቀርቡት ምግብ ጣዕም ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው ቀርቶ መንገድ ላይ የሸተተን ድብን ያለ ቁሌት በሽታው አጣጥመን የቀመስነው ያህል አድንቀን የምናልፍ ብዙዎች ነን፡፡ በተለይ የእኛ ሀገር የምግብ አሰራርና አመጋገብ ባህሉን ተከትሎ ሲወርድ ሲዋረድ የተቀበልነውና እያስኬድነው ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ‹‹በዘር የሚተላለፍ ከተባለስ

የምግብ አሰራር እና አመጋገባችን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም!››በሰጠናቸው ሙቀት የምግብ ንጥረ ይዘታቸውን አጥተው ሆዳ

ችንን ለመሙላት ብቻ የምንመገባቸው ምግቦች የፈለግነውን ጥጋብና እርካታ ሰጥተውን አያልፉም፡፡ ሆዳችንን በመንፋት፣ በማቃጠል፣ በተቅማጥ እና በድርቀት ምቾት በማሳጣት ጭምር አበሳሰላችን የምግቡን ጤናማነት እንዳሳጣው ይገልፁልናል፡፡ እናም ምግብ ለሆድ መታወክም ሆነ ለጤናማ መሆን ባለ ትልቅ ድርሻ ነው፡፡

የምግብ ባለሙያዎች እንደሚሉት ምግባችን በጣም እሳት ሳይገባው በጣምም ጥሬ ሳይሆን በማብሰል መመገብ ተመራጭ ነው፡፡

በተከሰተው የሆድ ህመም ሳቢያ ደጋግመው የሆስፒታል ደጆችን ረግጠው ይሆናል፡፡ በምላሹም ካልረኩ እንዲህ ቢያደርጉ፡-

- አልኮል ባያዘወትሩ ወይም ባይጠጡ- ጥሬ ምግቦችን ቢተውስ- ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ቢያስወግዱ- ውሃ በበዛበት ቢጠጡ- ለአመጋገብዎ አትኩሮት በመስጠት ጤናማነታቸውን

አረጋግጠው ቢመገቡ፡፡የሰው ልጅ ከመታመሙ በፊት የሚወስደው ጥንቃቄ ከታመመ

በኋላ ቶሎ ለመዳኑ ዋስትና ነው፡፡

የሆድ ቁርጠት በዘር ይተላለፋል?

በወንጌል አማኞች የምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን

ሜኔሶታ ይሙጡ- እግዚአብሔር ያየሎትን የክብር ፍፃሜ ይገናኙ!!!!

Come On & Meet Your Glorious Destiny! መጋቢ አበባየሁ አበበ Family Life Educator and Councilor

መደበኛ ፕሮግራሞቻችን ፡-

ዘወትር እሁድ ከ4፡00pm-7፡00pm አምልኳና በእረኝነት ፀጋ የትምህርት ግዜ (መዝ 23) ዘወትር ረብዕ ከ5፡00pm-7፡00pm አምልኳና የእግዚአብሔር ቃል ጥልቅ ሚስጢር ልዩ የትምህርት ግዜ (ሮሜ 16፣25) ዘወትር ቅዳሜ ከ4፡00pm-7፡00pm የፀሎት ፣ ልመናና የምልጃ ልዩ ግዜ በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮች ላይ፣ በተለይም በትዳርና በቤተሰብ ህይወት ላይ መፀሐፍቅደሳዊና ሞያዊ ምክሮችን (Counseling) እንሰጣለን።

አድራሻችን ፡- የአምልኮ ስፍራችን 1697 Lafond Ave, Saint Paul, MN,55104 ቢሮአችን 1821 University Ave. S-229, Saint Paul, MN,55 104 (የቀድሞ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቢሮ የነበረው)

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 20

ዲ/ን ዳንኤል... ከገጽ 9 የዞረልምድና ችሎታ ያለው ሰው ይቀጠራል። ቤተ ክህነት

ግን እንደዚህ ያለ አሠራር የለም።ግን እኮ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች መምህራን

ለመቅጠር በመስፈርት ማስታወቂያ ሲያወጡ እናያለን!ዕውቅና ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር

ስለሚያስገድዳቸው ነዋ። ግን ‹‹አንድ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት ምን መምሰል አለበት?›› ያልን እንደሆነ ‹‹ይህን የሚመልስ›› ብሎ የሚያስቀምጥ ፖሊሲ የለም። አሜሪካ ብትሄድ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች በደንብ ይታወቃሉ። ግልጽ የሆነ መመሪያና ፖሊሲ አላቸው። የእኛ ግን ምንም የለም። ምኑ ነው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት ያስመሰለው? ምንም የለም። ትምህርት ሚንስቴር ይቆጣጠራቸዋል እንጅ እኮ የቤተ ክህነት ትምህርት ዘርፍ የሚባል ተቆጣጣሪ ድርጅት የላትም።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሙስና ጉዳይ ትልቅ መነጋገሪያ እየሆነ መጥቷል። መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች በዚህ ዓይነት ምግባር ተዘፍቀዉ እንዴት ነው ምዕመኑን መምራት የሚችሉት? በዚህ ይዞታቸዉ የሚያስተምሩት ሕዝብስ እንዴት ሊሰማቸዉና ሊቀበላቸዉ ይችላል?

እሱ ከባድ ነው። ምዕመኑን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የመነጠል አደጋም አለው። ምዕመኑ አባቶቹን ማመን ያቅተዋል። ነገ አሥራት በኩራቱን ለመክፈል፣ ኑዛዜውን ለንስሀ አባቱ ለመናገር ወዘተ. ይቸግረዋል። ለዚህ ነው ቤተክርስቲያኒቱ መንቃት ያለባት። አጠቃላይ ተቋማዊ ለውጥ ያስፈልጋታል። ቤተ ክህነታዊ ለውጥ ያስፈልጋታል። መምሪያዎቿን እንደገና የማየት፣ ፖሊሲ ማርቀቅ ያስፈልጋታል። መዋቅራዊ አሠራሩ በደንብ እንደገና መፈተሽ አለበት። ጥብቅ፣ ግልጽና አሳታፊ የሆነ አሠራር መዘርጋት አለበት። ለምሳሌ አጥቢያዎች ኦዲት መደረግን መልመድ አለባቸው። በውጭ ኦዲተር ኦዲት ተደርገው መቅረብ አለባቸው። ሕዝቡ ለሰጠው ገንዘብ ጠያቂ ስለሚሆን ለሕዝቡ በግልጽ መቅረብ አለበት። ይህ አለመሆኑ ደካማ አሠራርን ተጠቅመው መቦጥቦጥ የሚፈልጉ ሰዎችን ይስባቸዋል። ጠንካራ ሥርዓት ሲኖር በዚህ መጠቀም የሚፈልጉ ሰዎች አይቀርቡም፤ ይፈሩታል።

አሁን ባለው ሁኔታ ለውጥ የሚመጣ ይመስልዎታል?እኔ በሂደት ለውጡ በሁለት መንገድ ይመጣል ባይ ነኝ።

ወይ ውስጥ ያሉት አባቶች ችግሩን በደንብ ተረድተውት ዘላቂ መፍትሔ ለመፈለግ ይነሳሉ። ካልሆነ ደግሞ ወቅቱ ያስገድዳል። እንዲህ ሆኖ መቀጠል አይቻልም። የሆነ ጊዜና ቦታ ላይ ግጭት ይፈጠራል። ግጭቱን ቀድመህ ከደረስክበትና ከፈታኸው ጥሩ ነው። ካልሆነ ግን ለውጡም ግጭቱም ይመጣል። ግን ኪሳራ ያስከትላል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ትውልዱም መሸከም የማይችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። ግን የዚህ ዓይነቱ ለውጥ አስጊ ነው፤ ጥሩ ለውጥ አይደለም። ለውጡ ከተቋሙ ከራሱ ቢመጣ ነው ጥሩ የሚሆነው።

ቤተ ክርስቲያኒቱ በገንዘብ እጅግ ሀብታም እንደሆነች ይታወቃል። ነገር ግን ‹‹ይህን ያህል ሀብት አላት›› ተብሎ ሪፖርት አይቀርብም። የግልጽነት አለመኖሩ ደግሞ ነገሮችን ይበልጥ እያወሳሰባቸው ነው። በእርስዎ አስተያየት ሪፖርት የማይቀርብበት ምክንያት ምንድን ነው?

እውነት ነው፤ አጠቃላይ ሀብቷን የሚመለከት ሪፖርት ቀርቦ አያውቅም። አጠቃላይ ሀብቷን ሪፖርት ለማቅረብ የሚያስችል ሥርዓትም የላትም። ይህን የሚመራ ትልቅ የፋይናንስ ተቋም ያስፈልጋል። መንግሥት እኮ ይህን ያክል ገንዘብ የሚያስተዳድረው ገንዘብ ሚንስቴር የሚባል ተቋም ይዞ ነው። ቤተ ክህነት እኮ ገንዘብ ሚኒስቴርን የሚስተካከል ትልቅ የፋይናንስ ተቋም ያስፈልጋታል። ከ35,000 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ያሏት፣ ከ40,000 በላይ ካህናት ያሏት፣ ከ1,100 በላይ ገዳማት ያሏት ቤተ ክርስቲያን ሀብትየሚያስተዳድር ያስፈልጋታል።

የገንዘብ ተቋም ጎሰኝነቱም ሌላው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ነው ይባላል። ይህስ እንዴት ይታያል?

እኔ ‹‹ጎሰኝነቱን የበለጠ እንዲያብብ ያደረገው የተንሰራፋው ሙስና ነው›› ነው የምለው። አካባቢያዊነት በአገራችን የኖረ ነው። ሆኖም ሙስናው ላይ ስትቆም አካባቢያዊነት ወደ ጎሳኝነትና ጠባብነት ያድጋል። ሙስና ላይ ስትቆም የምታምናቸው ሰዎችን ትፈልጋለህ። ስለዚህ ጎሰኝነቱ የቆመው ሙስናው ላይ ባይ ነኝ።

በመርህ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ገንብታ የንግድ ተቋማትን ከማስፋፋትና ትምህርት ቤት ከማቋቋም የትኛውን ብትሠራ ተመራጭ ይሆናል?

መሆንማ የነበረበት ቤተክርስቲያን አስተማሪ ናት፤ መካሪ ናት፤ ለሕዝብ ደህንነት የቆመች ናትና የመጀመሪያ ሥራዋ አብያተ ክርስቲያናትን ማስፋፋት ነው። ቀጥሎ ትምህርት ቤቶችን መሥራት፣ የአረጋውያንን መጦሪያ መሥራት፣ የድሆችን መመገቢያ መሥራትና ሌሎችንም ማከናወን ነው የነበረባት። ‹‹እነዚህን ነገሮች ለመሥራት ገንዘብ ያስፈልገኛል›› ካለች ቀጥሎ የሚመጡ ነገሮች ናቸው። እንደምታዩት በአገራችን አብያተ ክርስቲያናቱን የንግድ ድርጅቶች ውጠዋቸዋል። ስለዚህ ድሮ ከሩቅ የምትሳለመውን አሁን ከሩቅ መሳለም አትችልም። የትኛው ነው የገዘፈ? ግዝፈት ትኩረትን ያሳያል። ቤተክርስቲያኒቱ ትንሽ ሆና የንግድ ሕንጻው ግን ግዙፍ ሆኖ ትኩረታችን የትኛው ላይ ነው? ይህ ሁሉ ቀጣዩ ትውልድ ለሚጠይቀው ጥያቄ ከባድ መልስ ነው።

ደም.... ከገጽ 16 የዞረጊዜያትን የወሰደብን ምርመራ አዲስ ብስራት ነው፡፡

ነገር ግን አሁንም ጣጣውን የጨረሰ አይደለም፡፡ ተጨማሪ ሙከራዎችን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ደረጃ ያገኘነውም ውጤት ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የሰው ልጆች የበሽታና እንግዳ ነገሮችን መከላከያ ስርዓት በጣም ንቁ በመሆኑ፣ አንቲጅኑን ቆራርጠን ስናስወገድ ሊቀሩ የሚችሉ በጣም ጥቃቅን ቅሪቶች እንኳ ሰውነትን በማስቆጣት ያልተፈለገ ውጤት ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ ምርምሮችን የፈለግነውም ለዚህ ነው›› ብለዋል፡፡ የምርምሩ ውጤት ሲጠቃለል፣ የትኛውም ሰው ከራሱ የደም አይነት ጋር መዛመዱ ሳያስጨንቀው፣ ከማንም ሰው ደም ካገኘ ለአደጋና የደም ልገሳ በሚፈልጉ የጤና ችግሮች ወቅት ደም ሊያገኝ ይችላል ማለት ነው፡፡ የዚህን ምርምር ውጤት በተግባር ላይ መዋል የሚጠራጠሩ ባለሞያዎች እንደሚሉት፣ የሰው ልጅን የደም አይነት ለመቀየር ይህን የሚቆጣጠሩትን ጂኖች መቀየር አለዚያም የደም ህዋሳት የሚሰሩበትን አጥንትን በንቅለ ተከላ መቀየር ያስፈልጋል ባይ ናቸው፡፡ ይሁንና የአዲሱን ምርምር ውጤትም ውድቅ አላደረጉም፡፡ የደም አይነት አሳዋቂ አንቲጅኖችን ማስወገድና፣ የማዘዋወር ሂደት ውስብስብ የሰውነት ፊዚዮሎጂ አልፎ ስኬት ማስመዝገቡ፣ ጊዜ ሊወስድ ይችላል የሚል ጥንቃቄ የተሞላውን አስተያየት ግን ሰንዝረዋል፡፡

የደም ልገሳ ጉዳይስ?ይህ ከፍተኛ የደም ፍላጎትን ለመሙላት፣ አንድ ሁነኛ

መፍትሄ ይሆናል ተብሎ የቀረበው የምርምር ውጤት ወደ ትግበራ ለመግባት ጊዜ የሚፈልግ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እስከዚያው ግን ለወገኖቻችን ምርጡ ተግባር ደም

ልገሳን ማበረታታት ይሆናል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ከለጋሾች የሚገኘው ደም፣ ከአጠቃላዩ ፍላጎት 30 በመቶውን ብቻ ይሸፍን የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ይህ ምጣኔ ከፍተኛ መሻሻልን እያሳየ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደም ባንክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባደረጋቸው ጠንካራ እንቅስቃሴዎች፣ በየጤና ተቋማቱ የሚፈለገውን የደም መጠን ከበጎ ፈቃደኞች በመሰብሰብ በአብዛኛው እያሟላ መሆኑንም ሰምተናል፡፡ አሁንም ግን የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ ልምድ በጥሩ ደረጃ ላይ ደርሷል ለማለት አያስደፍርም፡፡

በተለይ በርካታ እናቶች በወሊድ ወቅት በሚፈጠር ከፍተኛ የደም መፍሰስ በሚሞቱባቸው የገጠር አካባቢዎች ምትክ ደም እንደልብ ማግኘት አይቻልም፡፡ አዳዲሶቹ የምርምር ውጤቶች ሰዎች አስተማማኝ የደም አቅርቦት ያለገደብ የሚያገኙበትን አማራጭ ለማቅረብ መጣራቸውን በብስራትነት ቢሰማም፣ ጊዜው ደርሶ ምሉዕ መፍትሄ እስኪሆኑ ድረስ ግን ደም በመለገስ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ የብዙዎችን ህይወት ማዳንን ቸል አይበሉት እንላለን፡፡

ኤች.ፓይሎሪ... ከገጽ 16 የዞረከግድግዳው የሚያጣብቅን ፕሮቲን ራሱ በማምረት

ራሱን ያኖራል፡፡ባክቴሪያው ገብቶ በሽታውን የሚያስከትል ከሆነ

አንዳንድ ምልክቶች መታየታቸው አይቀርም፡፡ ከእነዚህ ምልክቶች መካከል በላይኛው የሆድ አካባቢ ህመምና ምቾት ማጣት፣ የሆድ መነፋት፣ ሳይበሉ መጥገብ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ጥቂቶቹ እንደተለመዱት ናቸው፡፡ አንጀት የሚቆስልና የሚደማ ከሆነ የሂሞግሎቢን መጠንን ያሳንሳል፡፡

ስለ ባክቴሪያው በኢትዮጵያ ምን ተባለ?በተጣበበና የንፅህና ሁኔታው ዝቅተኛ በሆነ አካባቢ

የሚኖሩ ሰዎች፣ ንፁህ የውሃ አቅርቦት የሌላቸው እንዲሁም አብረው የሚኖሩት ሰው፣ በዚህ የጨጓራ ባክቴሪያ የታመመባቸው ሰዎች በባክቴሪያው ኢንፌክሽ የመያዝ ዕድላቸው ከፍ ያለ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህን የተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ እነ ፍቅሬ ዕንቁስላሴ ‹‹He-licobacter pylori infection in Ethiopian Children›› በሚል ርዕስ፣ ዕድሜያቸው ከ2-6 ባሉ ልጆች ላይ ጥናት አካሂደው ነበር፡፡ ለሁለት ዓመታት የተከታተሏቸውና በጥናቱ ጅማሬ ወቅት ባክቴሪያው ያልነበረባቸው ልጆች መካከል 58 ከመቶ የሚሆኑት በባክቴሪያው ተይዘው ተገኝተዋል፡፡ ለልጆቹ በባክቴሪያው መለከፍ ምክንያት ሆኖ የተገኘው ደግሞ ልጆቹ የጠጡት ውሃ ከጉድጓድ አልያም ከወንዝ የሚቀዳ መሆኑ እንደሆነ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ጤናማ የውሃ አቅርቦትን መጠቀም በበሽታው ላለመያዝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብሏል ጥናቱ፡፡ ኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያ የጨጓራ ህመም መንስኤ ሊሆን ይችል እንደሆነ ለማየት፣ በ300 አዋቂ ኢትዮጵያውያን የጨጓራ ህመምተኞች ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሜዲካል ፋኩልቲ በተደረገ ጥናትም 91 ከመቶዎቹ ላይ ባክቴሪያው ተገኝቷል፡፡ ሌሎች በተለያዩ ባለሞያዎች የተደረጉ ጥናቶችም በእርግጥም ኤች.ፓይሎሪ ከጨጓራ ህመም ጋር ያለውን ተዛምዶ አሳይተዋል፡፡

የምርመራና የህክምና ነገርየጨጓራ ባክቴሪያ የህመምዎ መንስኤ መሆኑን

የሚናገሩ፣ ቀደም ብለን ያነሳናቸው ምልክቶችን ካዩ ለምርመራ ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ ባለሞያዎቹ ይመክራሉ፡፡ ባክቴሪያውን በሰገራ፣ የደም፣ የትንፋሽ ናሙና በመውሰድ አለዚያ በኢንዶስኮፒ ቀጭን ቱቦን ወደ ሆድዎ በመላክ የጨጓራዎን ጉዳት እና የባክቴሪያዎን መኖር ማጣራት ይቻላል፡፡ ጥቂት የጨጓራዎትን ብጫቂ ሥጋ በናሙናነት በመውሰድም ለውጠን በማይክሮስኮፕ በመመርመር ችግሩን ለማወቅ ይሞክራል፡፡ ነገር ግን ለባክቴሪያው ፖዘቲቭ ሆነዋል ማለት ታመዋል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ ይህን ለማለት የበሽታው ምልክቶች መታየት ይኖርባቸዋል፡፡

ባክቴሪያው ከተገኘ ሶስት አይነት መድሃኒቶችን ባቀናጀ ዘዴ ባክቴሪያውን ለማጥፋት የሚሰጥ ህክምና ይደረግልዎታል፡፡ የመጀመሪያው በሆድ ውስጥ የሚመነጩትን አሲዶች ለጊዜው በመቀነስ የቆሰለ ጨጓራዎት እንዲድን ሲረዳ፣ ሁለቱ ፀረ ባክቴሪያዎች ደግሞ ባክቴሪያውን ለመግደል ይውላሉ፡፡ መድሃኒቱ ለ7

ቀናት ተሰጥቶት ለውጥ ያላመጡ ከሆነ ለተጨማሪ 7 ቀናት ሌሎች ፀረ ባክቴሪያዎን በመጨመር ህክምናው በአጠቃላይ ለ14 ቀናት ይዳረግልዎታል፡፡

ባክቴሪያው በጊዜ ካልታከመ የጨጓራ እና አንጀት መቁሰል ካስከተለ፣ በተጨማሪ ለጨጓራ ካንሰር ደረጃም ሊዘልቅ ስለሚችል ሙሉ በሙሉ መታከም እንደሚኖርበት ስፔሻሊስቶቹ አጠንክረው ይናገራሉ፡፡ ባክቴሪያው በጤናማ ሰዎ ዘንድ ሊገኝ የሚችል በመሆኑ፣ የበሽታ ምልክት እስካልታየ ድረስ ህክምናው ላያስፈልግዎ ይችላል፡፡ ጤና ይስጥልን!

የሥጋ ደዌ... ከገጽ 17 የዞረ

የሥጋ ደዌ በሽታ መድሃኒት አለው ወይ?የሥጋ ደዌ በሽታ እንደዘመዱ ቲቢ ሁሉ መድሃኒት

ያለው በሽታ ነው፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት ለህክምና እንዲመች ብሎ የሥጋ ደዌ በሽታን በሁለት አበይት ክፍል ከፍሎታል፡፡

- የመጀመሪያው ባለጥቂት ባክቴሪያ /Paucibacillary Leprosy/ የሚባለው ሲሆን በቁጥር ከ1-5 የሚደርሱ የቆዳ ለውጦች ያስተናገደ አልያም ደግሞ አንድ ያበጠ ነርቭ ብቻ ያለው በሽተኛ በዚህ ምድ-ብ ስር ውስጥ ያካትታል፡፡

- ሁለተኛው ደግሞ ባለብዙ ባክቴሪያ /Multi bacil-lary leprosy/ የሚባለው ሲሆን ስድስትና ከዚያ በላይ ቆዳ ለውጦችን ያስተናገደ ወይም ከአንድ በላይ ያበጠ ነርቭ የያዘ ህሙም የሚካተትበት ምድብ ነው፡፡

የሥጋ ደዌ በሽታ የሚድን እንደመሆኑ መጠን የሚሰጠው መድሃኒት ባክቴሪያውን በመገላገል ህመሙን ማዳን፣ ለተለመደው መድሃኒት ምላሽ የማይሰጡ የባክቴሪያ ትውልዶች እንዳይነሱ ማድረግ፣ በሽታው ድጋሚ እንዳያገረሽ ማድረግና ያልታከመ የሥጋ ደዌ በሽታ ሊያመጣ የሚችለውን የእጅና የእግር መጣመም ወይም መቆረጥን ለመከላከል መድሃኒቱ እጅጉን ይጠቅማል፡፡

ስለዚህ ለባለጥቂቱ ባክቴሪያ የሥጋ ደዌ በሽታ መድሃኒቱ ለስድስት ወር ሲሰጥ ለባለብዙ ባክቴሪያ የሥጋ ደዌ በሽታ ደግሞ ለአንድ ዓመት ይሰጣል፡፡ መንግሥት ይሄንን መድሃኒት በነፃ ለታካሚዎቹ ያደርሳል፡፡ በጽሑፌ መግቢያ የነበረው የ57 ዓመቱ ሰውዬ ባለብዙ ባክቴሪያ የሥጋ ደዌ በሽተኛ ሲሆን ህመሙም በላብራቶሪ ተረጋግጦ ህክምናውን ጀምሯል፡፡

በሥጋ ደዌ የተጠቁ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

ዓይናቸው በሥጋ ደዌ ህመም ምክንያት ሥራው ለተስተጓጎለባቸው የሚከተሉትን እንክብካቤዎች ሊያደርጉ ይገባቸዋል፡፡

1. ዓይናቸውን ሙሉ ለሙሉ መጨፈን ለማይችሉና ኮርኒያቸው ለደረቀባቸው ሰዎች

- የዓይኖት ቆብ ደካማ ሆኖ ካገኙት ለመጨፈን አጥብቀው ይሞክሩ፡፡

- በራሱት ጊዜ ለመጥቀስ ይሞክሩ- በሚተኙበት ጊዜ ዓይኖን በልብስ ይሸፍኑ- ቀን በሚሆንበት ጊዜ ለዓይኖት መነጽር መጠቀም

አልያም ደግሞ ኮፍያ ወይም ስካርፍ ይልበሱ፡፡ - ዓይኖትን በየጊዜው መስታወት ላይ ሆነው ይመልከቱ፡

፡ ባዕድ አካል መኖሩን ወይም ዓይኖት ቀልቶ እንደሆነ ያስተውሉ፡፡ ቀልቶ ከሆነ የጤና ባለሙያ ያማክሩ፡፡

- በየጊዜው ዓይኖትን በንፁህ ውሃ ይጠቡት፡፡ - ዓይኖትን ሊያለሰልሱ የሚችሉ ፈሳሾችን ይጠቀሙ፡

፡ ለምሳሌ የጉሎ ዘይት ጠብታ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በየትኛውም የመድሃኒት ቤት መደብሮች የጉሎ ዘይትን ሊያገኙት ይችላሉ፡፡

2. ለእጆት ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች- ሁልጊዜ እጆትን የተጎዳ፣ የተሰነጠቀ ወይም የተቧጨረ

ቁስል እንዳለው ይመልከቱ፡፡ ምክንያቱም እንደሌሎች ሰዎች ቁል በሚኖርበት ጊዜ ስለሚታወቆት ነው፡፡

- ሁልጊዜ የደነዘዘው የእጆትን ክፍል በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል በውሃ ውስጥ ይዘፍዝፉት፡፡ ይህም የቆዳዎትን እርጥበት ይጠብቅሎታል፡፡

- እጆት ላይ ቁስል ከወጣ በንፁህ ጨርቅ ይሸፍኑት፡፡ 3. ለእግሮት ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች- ዘወትር የእግሮትን ውስጠኛ ክፍል (ሶል) የደረሰበት

መጫጫር ወይም ጉዳት እንዳለ ይቃኙ- እግሮትን በውሃ ከዘፈዘፉ በኋላ ቫዝሊን ወይም ዘይት

ይቀቡት፡፡ - ረጋ ብለው ቢራመዱና በተቻለ መጠን የእግር ጉዞ

ቢቀንሱ ይመረጣል፡፡ - እግሮት ላይ ቁስል ካለ እረፍት ያድርጉበት፡፡ ከዚህ

በተጨማሪ ቁስሉን በንፁህ ጨርቅ ይሸፍኑት፡፡

የሥጋ ደዌ በሽታን መከላከል ይቻላል ወይ?

የሥጋ ደዌን በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል የተዘጋጀ መድሃኒት የለም፡፡ ለቲቢ በሽታ ተብሎ ህፃናት እንደተወለዱ የሚሰጣቸው የቢሲጂ ክትባት እስከ 50 ፐርሰንት የመከላከል አቅም አለው ተብሏል፡፡ ቤተሰባቸው ውስጥ የሥጋ ደዌ በሽታ ያለባቸው በየዓመቱ ቢታዩ ወይም ቼክ አፕ ቢደረጉ ተመራጭነት አለው፡፡ ይህንን ክትትልም ቢያንስ ለአምስት ዓመት ቢቀጥል ተመራጭነት አለው፡፡ የሥጋ ደዌን በሽታ መከላከልና የግንዛቤ ለውጥ ማምጣት የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡ እንደዚህ ከሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ያቀደው ከ10,000 ሰዎች ውስጥ ከአንድ በታች የሚለው ሃሳብ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡

እሬሳ... ከገጽ 7 የዞረአቅራቢያ መገኘቱ የአጋጣሚ ነገር እንዳይመስላችሁ፡

፡ በነገድ ደረጃ የኢሬሳ በዓል የሚከበርባቸው ማዕከላት በሙሉ በሐይቅ ዳርቻ የሚገኙ ናቸው፡፡ ይህም ምክንያት አለው፡፡ አንደኛው ምክንያት የጥንቱ የኦሮሞ የዋቄፈንና እምነት “ፍጥረት የተገኘው ከውሃ ነው” የሚል አስተምህሮ ያለው በመሆኑ “ዋቃ” ፍጥረተ ዓለሙን በጀመረበት የውሃ ዳርቻ በዓሉንና የአምልኮ ተግባሩን መፈጸም ተገቢ ነው ከሚል ርዕዮት የመነጨ ነው፡፡ ይሁንና ሁሉም የውሃ አካል ለዚህ ክብር አይመጥንም፡፡ ኦሮሞ ከሰው ልጅ ነፍስ ቀጥሎ ለከብቶቹ ነፍስ በእጅጉ ይጨነቃል፡፡ በመሆኑም ኢሬሳን የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት በዳርቻው የሚከበርበት የውሃ አካል ከሰዎች በተጨማሪ ለከብቶች ህይወት አስፈላጊ መሆኑም ይጠናል፡፡ ይህም ማለት ውሃው በኦሮሞ ስነ-ቃል “ሃያ” (ቦጂ) እየተባለ የሚጠራው ጨዋማ ንጥረ ነገር ያለው ሊሆን ይገባል ለማለት ነው፡፡ በዚህ ማዕድን በአንደኛ ደረጃ የሚታወቁት ደግሞ “ሆራ” የሚባሉት በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ያሉ ሐይቆች ናቸው፡፡

ታዲያ የእነዚህ “ሆራ” ሐይቆች ልዩ ባህሪ ነጠላ ሆነው አለመገኘታቸው ነው፡፡ በተለያዩ ክልሎች ያሉት ሆራዎች በቡድን ተሰባጥረው ነው የሚገኙት፡፡ በአንዳንድ ስፍራዎች እስከ ሶስት ያህል ሆራዎች አሉ፡፡ በአንዳንድ ስፍራዎች ደግሞ እስከ ስምንት የሚደርሱ ሆራዎች ይገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ የኦሮሞ ነገዶች እነዚህን በማዕድናት ክምችት የበለጸጉ ሐይቆች ወጥ በሆነ ሁኔታ “ሆረ” (Hora) እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡ የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ ግን “ሀረ” ነው የሚለው፡፡ “ሀረ ማያ” የሚለው የሐይቁ ስያሜም የሚያመለክተው ይህንኑ ነው፡፡ እንግዲህ ኢሬቻ የሚከበረው በእንዲህ ዓይነት ሐይቆች አቅራቢያ ነው፡፡

*******ከላይ ስጀምር “የኢሬሳ በዓል ማክበሪያ ስፍራ ለነገዱ

የፖለቲካና የሃይማኖት ማዕከል የቀረበ ነው” ብዬ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የ“ሀረ ማያ”ን ሐይቅ ያየ ሰው በአባባሌ መደናገሩ አይቀርም፡፡ ነገሩ ግን እውነት ነው፡፡ በዛሬው ዘመን “ሃረ ማያ” በትውፊት ውስጥ ያለው አስፈላጊነት እየተረሳ የመጣው የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የኢኮኖሚ ስርዓቱን ከከብት እርባታ ወደ ግብርና ማዞር በጀመረበት ዘመን እስልምናንም እየተቀበለ በመምጣቱና የፖለቲካ ማዕከሉም በዚሁ ሂደት ውስጥ በመረሳቱ ነው፡፡ ነገሩን ጠለቅ ብሎ ያየ ሰው ግን የጥንቱን የአፍረን ቀሎ የፖለቲካ ማዕከል ከሀረማያ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ያገኘዋል፡፡ ይህም “ቡሉሎ” የሚባለው ስፍራ ነው (ስፍራው ለወተር ከተማ ይቀርባል)፡፡ በዚህ መሰረት የዛሬዎቹ የሀረማያ እና የቀርሳ ወረዳዎች የጥንቱ የአፍረን ቀሎ ኦሮሞ የፖለቲካና የመንፈሳዊ ማዕከላት ነበሩ ማለት ነው፡፡

ከአፍረን ቀሎ ኦሮሞ ምድር ወደ ምዕራብ ተጉዘን “ጨርጨር” በሚባለው የኢቱ ኦሮሞ መሬት ውስጥ ስንገባ ደግሞ ነገሩ በግልጽ ይታየናል፡፡ የኢቱ ኦሮሞ የኢሬሳን በዓል የሚያከብርበት ስፍራ በአሁኑ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን የቁኒ ወረዳ፣ በደነባ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡ ስፍራው እስከ አሁን ድረስ Mudhii Irressa እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ ስፍራ ከዝነኛው “ኦዳ ቡልቱም” በሁለት ኪሎሜትር ያህል ብቻ ነው የሚርቀው፡፡ “ኦዳ ቡልቱም” የኢቱ ኦሮሞ ጥንታዊ የፖለቲካና የእምነት ማዕከል ሲሆን በኢቱ ኦሮሞ ትውፊት መሰረት ስድስት “ሆራዎች” አሉት፡፡ እነርሱም “ሆረ ባዱ”፣ “ሆረ ቃሉ”፣ “ሆራ ቁኒ”፣ “ሆረ ባቴ”፣ “ሆረ ጎሄ” እና “ሆረ ዲማ” ይባላሉ፡፡

እነዚህ ሃይቆች በበጋ ወቅት አነስ ብለው ቢታዩም ሙሉ በሙሉ የጠፉበት ሁኔታ አልተከሰተም፡፡ ከነርሱ መካከል ትልቁ “ሆራ ዲማ” ሲሆን በተለምዶ “ሀሮ ጨርጨር” እየተባለም ይጠራል፡፡ “ሆረ ዲማ” የምስራቅ ኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ነው (የአስፋልቱ መንገድ ወደዚያ ስለማይደርስ የመሃል ሀገር ሰዎች በአብዛኛው ሃረማያን ነው የሚያውቁት፤ ይሁንና “ሆረ ዲማ” በስፋቱ የሀረማያን ሶስት እጥፍ ይሆናል)፡፡ “ሆራ ባዱ” ደግሞ ለኦዳ ቡልቱም በጣም የቀረበው ሐይቅ ነው፡፡ የኢቱ ኦሮሞ የኢሬሳን በዓል የሚያከብረው ግን “ሆረ ቃሉ” ከተሰኘው ሐይቅ አጠገብ ነው፡፡ ይህም ሃይቅ ከሆረ ባዱ በስተምስራቅ ይገኛል፡፡

ስድስቱ ሐይቆች ካሉበት ስፍራ ጀምሮ እስከ ገለምሶ ከተማ ድረስ ያለው መሬት በኢቱ ኦሮሞ አጠራር “ፎዱ” ይባላል፡፡ “ማዕከል” ማለት ነው፡፡ ይህ ማዕከላዊ ወረዳ ለሶስት ጉዳዮች ብቻ የተከለለ ነው፡፡ አንደኛ “አባ ቦኩ” የሚባለው ርእሰ መስተዳድርና “ቃሉ” የተባለው መንፈሳዊ መሪ መኖሪያ ነው፡፡ ሁለተኛ የኦዳ ቡልቱም የገዳ ስርዓት ማዕከላዊ ተቋማት፣ የህዝቡ መንፈሳዊ ተቋማት እና የዞን አቀፍ በዓላት ማክበሪያ ስፍራዎች የሚገኙበት ክልል ነው፡፡ ሶስተኛ ለህዝብ ጠቀሜታ ብቻ የሚውሉት ስድስቱ ሆራዎች የሚገኙበት ክልል ነው፡፡ በመሆኑም የኢቱ ኦሮሞ ተወላጆች በሙሉ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ከብቶቻቸውን ወደነዚህ ሐይቆች እያመጡ ውሃ ያጠጧቸዋል፡፡ የኢቱ ሽማግሌዎች እንደሚናገሩት ከብቶች የሆራን ውሃ ካልጠጡ እንዳሻቸው ሳር አይመገቡም፡፡ ስለዚህ ከብቶቹን ወደ ሆራ መውሰዱ እጅግ አስፈላጊ ተግባር ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ይህ ስርዓት Nadha Baasuu ይባላል፡፡

የቱለማ ኦሮሞ የኢሬቻን በዓል የሚያከብርበትንም ስፍራ ካያችሁ ተመሳሳይ ነገር ታገኛላችሁ፡፡ በኦዳ ቡልቱም ዙሪያ ያሉት ስድስት ሐይቆች በቱለማ ምድርም አሉ፡፡ እነርሱም “ሆረ አርሰዲ”፣ “ሆረ ኪሎሌ”፣ “ሆረ ሀዶ”፤ “ሆረ ገንደብ”፣ “ሆራ ዋርጦ” እና “ሆረ ኤረር” ይባላሉ፡፡ የቱለማ ኦሮሞ ኢሬቻን የሚያከብረው “ሆረ አርሰዲ” በተሰኘው ሐይቅ ዳርቻ ነው፡፡

እነዚህ ስድስት ሐይቆች የቱለማ ኦሮሞ የፖለቲካ ማዕከል ከሆነው “ኦዳ ነቤ” በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኙት፡፡ ይህ ኦዳ ነቤ በዱከም ወረዳ ውስጥ ከሸገር በ37 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ የፖለቲካ ማዕከል ዙሪያም (እሬሳ... ወደ ገጽ 24 የዞረ)

በቋንቋ የተነሳ መንጃ ፈቃድማውጣት ተቸግረዋል?

Global Translation & Interpreterበቋንቋ የተነሳ የኮምፒውተር ፈተናውን ማለፍ ተስኖዎታል?

በዚህ የተነሳ መኪና መንዳት አልቻሉም? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር አለ፤

አስተምረን ወስደን እናስፈትንዎታለን።

Tajajila AfaanOromoos Nikennina !

ልብ ይበሉ የእርስዎን ቋንቋ እንናገራለን2400 Minnehaha Avenue Suite - 204

Minneapolis, MN 55404

(612) 275-0970በተጨማሪም የትርጉም ድርጅታችን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲኖርብዎ ወይም በማንኛውም ሰዓት

የትርጉም ሥራ ሲያስፈልግዎ ክፍት ነው።

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 21

ስፖርት

አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በ2013 ራሳቸውን ከአሰልጣኝነት ሲያገልሉ ማን ያልደነገጠ ነበር? በኦልድትራፎርድ ደግሞ ይሄ ስሜት ፍፁም የተለየ ነበር፡፡ በማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ሳይሆን በመላው እንግሊዝ እንደ ፈርጉሰን አይነት ውጤታማ አሰልጣኝ ፈልጎ ማግኘት አይቻልም፡፡

ሰር አሌክስ ጡረታ የመውጣት እቅድም ሆነ ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም የባለቤታቸው ካቲ መንትያ እህት -ብሪጌት ሮበርትሰን ህልፈተ ህይወት ይሄንን ውሳኔ እንዲያሳልፉ እንዳስገደዳቸው ጠቅሰዋል፡፡

‹‹ያለጥርጥር በሥራዬ እቀጥል ነበር›› ብለዋል- ታላቁ አሰልጣን ከቴሌግራፍ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ‹‹በአንድ ምሽት ባለቤቴ (ካቲ ፈርጉሰን) ቴሌቪዝን እየተመለከተች ፊቷ ላይ ጥሩ ነገር አላስተዋልኩም፣ ከቴሌቪዥኑ ይልቅ የቤቱን ጣሪያ ስትመለከት አስተዋልኩኝ፣ የብቸኝነት ስሜት እንደተሰማት አውቃለሁኝ፣ እርሷ እና ብሪጌት መንትያ ነበሩ›› ብለዋል፡፡

የፈርጊ ባለቤት ካቲ አሰልጣኙ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጥያቄ ያቀረቡላቸው በ2002 ነበር፡፡ በወቅቱ ታላቁ አሰልጣኝም ይሄንን ውሳኔ ለማሳለፍ ከውሳኔ ላይ ደርሰው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የኋላ ኋላ ውሳኔያቸውን ለውጠው በሚወዱት ሙያ ቀጠሉ እንጂ፡፡

‹‹ለሁለተኛ ጊዜ ይሄንን ጥያቄ ስታነሳልኝ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ አልቻልኩም፤ ከእውነተኛው ምክንያት ውጭ ሌላ ምክንያት ሊኖራት እንደማይችል አውቃለሁኝ›› የሚል አስተያት ሰጥተው በውሳኔያቸውን እንደማይፀፀቱ ገልፀዋል፡፡

የብሪጌት ህይወት ያለፈው በኦክቶበር 2012 ነበር፤ ፈርጊ የባለቤታቸው ስሜት ከመጥፎው አጋጣሚ በኋላ በጎ እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የአሁኑ ባለቤታቸውን ያገኙት በ1966 በግላስኮው ‹‹የአድማ ስብሰባ›› ላይ ነበር፡፡

ታላቁ አሰልጣኝ የግል ህይወታቸውን የሚተርከው

መጽሐፍ ላይ በሰጡት አስተያየት ‹‹ባለቤቴ ሁልጊዜም ቢሆን የቤቱን በር ክፍት አድርጋ ትጠብቀኝ ነበር፤ ሌሊት 8፡00 እና 9፡00 ሰዓት ቤት ስመጣ እንኳን በር ስር ሆና

ትጠብቀኝ እንደነበር መናገር አለብኝ፤ ስመጣ የሞቀ አቀባበል ታደርግልኝ ነበር›› ብለዋል፡፡

ፈርጊ ለመጨረሻ ጊዜ ለንባብ ያበቁትን መጽሐፍ ማስታወሻነቱን ለባለቤታቸው መንትያ እህት ብሪጌት

አበርክተዋል፡፡ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው ስኬታማ የሆኑት በባለቤታቸው ድጋፍ እንደሆነ ለመግለፅ ፍርሃት አልተሰማቸውም፤ ኧረ እንዲያውም ‹‹ቀዳሚዋ እርሷ ናት››

ለማለት አልሰነፉም፡፡ በ39 ዓመት የአሰልጣኝነት ቆይታቸው ላስመዘገቡት

ስኬት ባለቤታቸውን ቀዳሚ ሲያደርጉ ብዙዎች ውስጣቸው ተነክቷል፤ ጥሩ ትምህርት እንዳገኙም ጥርጥር

የለውም፤ አሰልጣኙ የስኬት እና በአንድ ክለብ ውስጥ ረጅም ዓመት የማሰልጠን ምልክት ናቸው፡፡

እርሳቸው በሜይ 2013 ለ13ኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ከሆኑ በኋላ የተሾሙት አሰልጣኞችም ቢሆኑ ከስኬት ጋር ተራርቀዋል፡፡ ከሳምንታት በፊት የኔቪል ወንድማማቾች ወላጅ አባት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ፈርጊ በስፍራው ደርሰው ከመኪናቸው ሲወርዱ እዚያ የነበሩ ደጋፊዎች በጣም በጩኸት ስሜት ውስጥ ሆነው ‹‹እናመሰግናለን፤ ሰር አሌክስ›› ብለዋቸዋል፡፡

በማንችስተር ዩናይትድ የነበራቸውን የ26 ዓመት ቆይታ አስመልክተው ‹‹ጡረታ እንደምወጣ እያወቅኩኝ እንኳን የክለቡን ደረጃ ለማስጠበቅ ጥረት ሳደርግ ነበር፤ ደካማ በሚባሉ ቦታዎች ላይ ተጨዋቾችን ማስፈረም ነበረብን፤ በምንም ነገር ዙሪያ ስለማንችስተር ዩናይትድ ስናገር የአውቶብሱ ጉዞ እንደሚቀጥል ገልጫለሁኝ፣ ማንም ወደ ኋላ አይቀርም፤ በቀጣይ መዳረሻችንን በተመለከተ ሁሉም አካል በእኛ ላይ ሙሉ እምነት ነበረው›› የሚል አስተያየትን ሰጥተዋል- ፈርጊ፡፡

ህይወት ከኦልድ ትራፎርድ በኋላ

ፈርጉሰን ውሳኔያቸውን ካሳለፉ በኋላ ወደ ኋላ አልተመለሱም፣ ውሳኔያቸውን ተከትሎ ቀጣይ ስራቸውን የወሰኑት ቀደም ብለው ነበር፡፡

‹‹ጡረታ ከወጣሁኝ በኋላ ዕድሜው እንደገፋ ሰው ያለ ሥራ መቀመጥን አልመረጥኩም›› ይላሉ- ቁጡው አሰልጣኝ፡፡

ጨምረውም ‹‹አባቴ ከመርከብ ሥራው ጡረታ የወጣው በ65 ዓመቱ ነበር፤ በግሌ እርሱ እንደሆነው መቀመጥን አልመረጠም፣ (ፈርጉሰን... ወደ ገጽ 22 የዞረ)

ሰር አሌክስ ጡረታ የወጡት ለሚስታቸው ሲሉ መሆኑን ይፋ አደረጉ

ባርሴሎና ባለፈው ወር በቻምፒዮንስ ሊጉ ሮም ኦሎምፒክ ላይ ከሮማ ጋር 1-1 በተለያየበት ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ በቀዩ እና ሰማያዊው ማልያ 100ኛ የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን ፈፅሟል፣ አርጀንቲናዊው በውድድሩ 80 ጎሎችን ካስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ በ77 ጎሎች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

አራት ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ያነሳው የ27 ዓመቱ ሜሲ የመጀመሪያ ድሉ በ2009 በሮም ኦሎምፒኮ ያሳካው ነበር፣ በጨዋታው ሊዮኔል ከዣቪ ኸርናንዴዝ የተሸጋገረለትን የአየር ላይ ኳስ ወደ ጎልነት ለውጦ ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል፤ ጨዋታውም 2-0 ተጠናቅቋል፡፡

በ2011 ባርሴሎና ማንችስተር ዩናይትድን 3-1 በረታበት ጨዋታ ሜሲ አንድ ጎል አስቆጥሯል፣

በዌምብሌይ ኳስ እና መረብን ያገናኘው አጭሩ አጥቂ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ቡድኑ በተመሳሳይ

ጁቬንቱስን 3-1 ሲያሸንፍ ጎል ማስቆጠር አልቻለም፡፡ ሊዮ ባርሴሎና በ2006 በፓርክ ደ ፕሪንስ

አርሰናልን 2-1 አሸንፎ (ሜሲ.. ወደ ገጽ 13 የዞረ)

ይህን አምድ ሊሊ ሞገስ ከአፕል ቫሊ ና እና ዳኒ ከሚኒያፖሊስ ያዘጋጁታል

ማንችስተር ዩናይትድ ለአንቶኒ ማርሻል ግዥ 38 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብን ለሞናኮ ሲከፍል ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል የእብደት ተግባርን የፈፀሙ ተደርገው በአንዳንዶች

ተቆጥሮባቸው ነበር፡፡ ለአንድ የ19 ዓመት ወጣት 36 ሚሊዮን ፓውንድ እጅግ ውድ የሚባል ዋጋ ነው የሚል አስተያየትን የሰጡ ወገኖችም በርካታዎች ሲሆኑ ታይተዋል፡፡ በግሩም የአጨራረስ ብቃት ሁለት ጎሎችን በሳውዝ ሀምፕተን መረብ ላይ ለማሳረፍ መቻሉ ቫንሃል ትክክለኛውን ውጤታማ የአጥቂ መስመር

ተጨዋችን ማግኘታቸውን ያረጋገጠላቸው ሆኗል፡፡ማንችስተር ዩናይትድ በሴንት ሜሪ ስቴዲየም

ሳውዝሀምፕተንን 3ለ2 በሆነ ውጤት ለማሸነፍ በቻለበት ግጥሚያ ከመረብ ያሳረፋቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግጥሚያዎች በስሙ ያስመዘገቧቸው ጎሎቹን ብዛት ሶት በማድረስ የኦልድ ትራፎርድ የፉትቦል ህይወቱን ባማረ ሁኔታ ለመጀመር ችሏል፡፡ ማርሻል ለማንችስተር ዩናይትድ ሶስቱን የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን ለማስቆጠር የፈጀበት ለ80 ደቂቃዎች ብቻ በሜዳ ላይ መቆየት ነው፡፡

በአንፃሩ ራዳሜል ፉልካኦ ባለፈው ሲዝን ሙሉ ሲዝንን ለማንችስተር ዩናይትድ በስሙ ያስመዘገባቸው ጎሎች ብዛት አራት ብቻ ናቸው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሉዊ ቫንሃል ማንም ባልገመተው መልኩ የቡድናቸው ጎሎችን የማስቆጠር ችግርን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ ኃይል ያለው አስገራሚ ወጣትን ማግኘት መቻላቸውን ነው፡፡ ከዝውውሩ ወዲህ ማንችስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3ለ1፣ እንዲሁም ሳውዝሀምፕተንን 3ለ2 በረታበት ሁለት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች

ከመረብ ያሳረፋቸው ሁሉም ሶስት ጎሎች በግሩም የአጨራረስ ብቃት ከመረብ የተገናኙ በመሆናቸው በ19 ዓመቱ ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል አጥቂ ብቃት የፉትቦሉ አለም አግራሞቱን በመግለፅ ላይ ነው፡፡

በሴንት ሜሪ በተደረገው (ማርሻል... ወደ ገጽ 23 የዞረ)

ሜሲ!!!የእግርኳሱ መሲህ

አንቶኒ ማርሻል አዲሱ የቀይ ሰይጣኖቹ አለኝታ

በ1901 Portland Ave South Minneapolis MN 55404 ከጠዋቱ 10፡00 እስከ 12፡00 ያለን የምልጃና የአምልኮ ጊዜ ቀጥሏል።

በዕለታዊ የፀሎት ጊዜ አብራችሁን ለመቆም ለምትፈልጉም ፓስተር ደስታዬን በ612-225-8269 ደውለው ያነጋገሩ።

የዓርብ ምሽት ፕሮግራማችን ከምሽቱ 6 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት እንደቀጠለ ነው።እሁድ ከሰዓት በኋላ 4:30 እስከ 6:30 የአምልኮ፣ የቃል፣ የፈውስና እና ትንቢታዊ

አገልግሎቶች ጀምረናል።እሁድ ማለዳ በ 11:30 ላይ በ4000 Linden Ave White Bear Lake MN

የምናደርገው ፕሮግራምም ቀጥሏል።ከእስራት ለመፈታትና ሌሎች ሲፈቱ ማየት ከፈለግን አጥብቀን እንጸልይ።

ሠይጣን ይዋጋል እንጂ አያሸንፍም!!በ እግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወገኖቼ ሁሉ ሕዝባችን እንዳይዋደድ; እንዳይቀባበል;

እንዳይከባበር ቋንቋን የሚደበላልቅ ክፉ መንፈስ እንደተመታ የ እግዚአብሔር መንፈስ ያረጋግጥልኛል:: ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር የልጆቹን ልመና;

ጸሎትና ምልጃ ሰምቶ በታላቅ መለኮታዊ ስልጣንና ክብር ከፊታችን ወጥቷልና ለእርስ በእርስ በመጸለይና ይቅር በመባባል ልባችንን እናዘጋጅ::

ሕዝባችንን እና የምንኖርባትን ሃገር ሕዝብ በመወከል ዕለታዊ ጸሎት ከጠዋቱ ከ10:00 - 12:00 ሰዓት - ከሰዓት በኋላ ከ1:00 - 3:00 በየቀኑ ቀጥለናል::

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 22

ፈርጉሰን... ከገጽ 21 የዞረ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (በትርፍ ጊዜያቸው በሃርቫርድ

ቢዝነስ ስኩል ያስተምራሉ) መስራት ነበረብኝ፡፡… …ከዚያ ውጭ በዩናይትድ እንደ ዳይሬክተር እና አምባሳደር

እንዲሁም ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና (ዩኒሴፍ) ጋር መስራትን መርጫለሁኝ፤ ከዩናይትድ ጋር በየዓለማቱ በመጓዝ ቡድኑ ሲጫወት መመልከት ያስደስተኛል›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፈርጉሰን ስኬት ምስጢርየዘመኑ እግርኳስ እንደ ሰር አሌክስ አይነት ስኬታማ

አሰልጣኝ ተመልክቶ አያውቅም፤ ፈርጊ ሁልጊዜም አንድን አሰልጣን ለስኬት የሚያበቃው ‹‹ስብዕናው፣ በውስጡ ያለው ኃይል፣ ውሳኔ ሰጪነቱ (የውሳኔ ሰው መሆን)፣ አስተውሎቱ እና ግንኙነቱ ነው›› የሚል መረጃን ሰጥተው ‹‹ይህ በኬብል ካምፓኒ አልያም ባርክሌይስ ባንክ ለሚሰራ ሰው ሳይቀር ይሰራል፣ ሁልጊዜም ቢሆን የምትገናኘው ከሰው ልጅ ጋር ነው፣ ከሰው ልጅ ጋር ስትገናኝ ደግሞ ቀጥተኛ መሆን እና ተነሳሽነት መፍጠር ግድ ይልሃል፣ በአለቃቸው ላይ ከፍተኛ እምነት ሊኖራቸው ይገባል›› በማለት ምስክርነታቸውን ገልፀዋል፡፡

ፈርጊ በመጽሐፋቸው ላይ የስኬታማነታቸውን ምስጢር በግልፅ ዘርዝረዋል፣ ወደ ኋላ መለስ ብለውም ‹‹ምንም ነገር ለማድረግ አልፈራም ነበር፤ ተጋጣሚዬን ለማሸነፍ ምንም አይነት ሪስክ ከመውሰድ ወደኋላ አልልም፤ ከዚህ በተጨማሪም በወጣት ተጨዋቾች መጠቀም ያስደስተኛል›› የሚል አስተያየትን ሰጥተው ‹‹በወጣበት ተጨዋቾች ላይ ከፍተኛ እምነት አለኝ፤ በአበርዲንም ሆነ ሴይንት ሜሪን ወጣት ተጨዋቾችን ለታላቅ ስኬት የማብቃት ችግር አልነበረብኝም፤ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ከመጣሁኝ በኋላ በ1950ዎቹ ሰር ማት በስፒ የሰራውን ነገር መድገም ነበረብኝ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ወጣት ተጨዋቾች የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው፡፡ ይሄ እውነታ ለግማሽ ምዕተ ዓመት በኦልድ ትራፎርድ ሲተገበር ነበር›› በማለት የክለቡን ባህል ለማስቀጠል ባደረጉት ጥረት እንደሚኮሩ ገልፀዋል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ ለሁለት አስርት ዓመታት በባለግርማ ሞገሱ አሰልጣን ተመርቷል፤ በጎቫን በአስቸጋሪ ውጣ ውረድ ያለፉት ፈርጊ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ከመምጣታቸው በፊት በስኮትላንድ በተጨዋችነት እና አሰልጣንነት አገልግለዋል፡፡ በተጨዋችነት ዘመናቸው ኃይል እና ጉልበትን ቀላቅለው የተጋጣሚ ቡድን ተከላካዮችን ስቃይ ውስጥ ይከትቱ ነበር፤ በአሰልጣንነት ዘመናቸው ደግሞ ቁጡነታቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

‹‹የመጣህበት መንገድ ለአለሰልጣኝነት ህይወቴ ጠቅሞኛል፤ ጥቂት እድለ ቢስ የሆኑ ሰዎችን ስናግዝ ቆይተናል፡፡ ለምሳሌ በጀማሪ ሰራተኞች አድማ ላይ መሳተፍ አያስፈልገኝም፣ አልያም እነኚህ ጀማሪ ሰራተኞች በአድማ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማበረታታት አይጠበቅብኝም፡፡ እኛ (የፋብሪካ ሠራተኞች) ጥሩ ክፍያ ይከፈለን ነበር፤ ችግር አልነበረብንም›› የሚል አስተያየትን ሰጥተው ‹‹የአሰልጣኝነት ፍቃድ ያገኘሁት በ24 ዓመቴ ነበር፡፡ ዕድሜዬ 32 ሲሞላ ለአሰልጣኝነት ዝግጁ ነበርኩኝ፤ እየተጫወትኩኝ አሰለጥን ስለነበር ለመወሰን አልቸገርኩም፡፡ በእግር ኳሱ ኢንዱስትሪ መማር አለብህ፣ አለበለዚያ በስራው መቆየት አትችልም›› በማለት አሰልጣኝነት ፈታኝ ሙያ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በቁጣ ተጨዋቾችን የሚያርዱት ታላቁ አሰልጣኝ በግላስኮው ቡና ቤት ከፍተው ይሰሩ ነበር፡፡ ወደኋላ ተመልሰው ‹‹ቡና ቤት አስቸጋሪ ስራ ነው፣ ይሰለቻል፣ ቅዳሜ ማታ ያለው ግርግር ይፈትናል፣ ሰዎች ይወጣሉ- ይገባሉ፡፡ የአሰልጣኝነት ዕድል ሳገኝ ስኬታማ መሆን እንደምችል ለራሴ ነገርኩት፣ እርግጥ ነው አሰልጣኝነት የውድቀት ስጋት አብሮ ያስከትላል፣ ነገር ግን ወደ ቡና ቤት ከመመለስ በአሰልጣኝነት ሙያ ስኬታማ መሆን እንዳለብኝ ቁርጠኛ ሆንኩኝ፣ በጭራሽ ወደኋላ ማሰብ እና መመለስ አላስፈለገኝም›› የሚል መረጃን ይሰጣሉ፡፡

በመጀመሪያ ክለባቸው ፈርጊ ተቸግረው ነበር፤ ያገኙት ባጀት እና የተጨዋቾች ቁጥር አነስተኛ መሆን አሰልጣኙን ፈትኗቸዋል፡፡ ‹‹በአበርዲን በጣም ብዙ ነገሮችን ተምሬያለሁኝ፤ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ጠንካራ ማንነት ይዞ መቅረብ እና በወጣት ተጨዋቾች ላይ መሥራት አስፈላጊ እንደሆነ ተገነዘብኩኝ›› የሚል አስተያየትን የሚሰጡት ፈርጉሰን በማንችስተር ዩናይትድ ተመሳሳይ የሆነ አካሄድን ተጉዘው እንደ ብሪያን ሮብሰን፣ ብሪያን ማክሌር፣ ማርክ ሂዩስ፣ ስቲቭ ብሩስ፣ ፖል ኢንስ እና ሮይ ኪንን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ከታች አንስተው ለታላቅነት ለማብቃት አልተቸገሩም፡፡

ግልፅ የሆነ የመሪነት መርህ ያላቸው ቁርጠኛው አሰልጣኝ ‹‹ተጨዋቾቹ የማይደሰቱበትን ነገር በጠንካራ ማንነት መለወጥ ይቻላል፤ የዚህ አይነት ሰብዕና የተጨዋቾችን

ማንነት ይለውጣል፤ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የአሸናፊነት መንፈስ ያሰርፃል፣ በቃ ነገሩ ይህን ያህል ቀላል ነው›› የሚል አስተያየትን ይሰጣሉ፡፡

እርግጥ ነው ከሰራተኛው መደብ መገኘታቸው በስልጠናው ውጤታማ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፤ ‹‹ከንጋቱ 11፡00 እና 12፡00 ላይ ከእንቅልፋቸው ተነስተው የማሽን ስራዎች ላይ የሚጠመዱ ሰዎችን መመልከት ለስራ ያነሳሳል፣ ሥራዎች የሚሰሩት በጋራ በመሆኑ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ይኖረዋል›› ይላሉ፡፡

የመጨረሻዎቹ ዓመታት ፈተናሰር አሌክስ ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት የነበሩት

የመጨረሻዎቹ ዓመታት ከተለያዩ ስመጥር ተጨዋቾች ጋር መጋፈጥ ነበረባቸው፤ ዴቪድ ቤካም በማንቸስተር ዩናይትድ የስኬት ዘመን ቁልፍ ከሚባሉ ተጨዋቾች መሀከል አንዱ ቢሆንም የኋላ ኋላ በሁለቱ ግለሰቦች መሀከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንግሊዛዊው ለስንብት ተዳርጓል፡፡ አሰልጣኙ በ2003 ወደ ሪያል ማድሪድ እንዲያመራ ቢያደርጉም አሁን ግን ሁሉም ነገር አልፎ በድጋሚ ወዳጅነት መስርተዋል፡፡

‹‹ነገሮችን መቆጣጠር ያስፈልጋል፤ ለራስ የሚራ ከፍ ያለ ዓት መቆጣጠር አያስቸግረኝም፤ (ክርስቲያኖ) ሮናልዶ ከመስታወት ፊት ቆሞ ሊቀነጃጅ ይችላል፡፡ ይህንን የምመለከተው በበጎ ስሜት ነው፡፡ የተጋጣሚ ቡድን ተጨዋቾች እርሱን ለማቆም የመሰላቸውን ጥፋት ሊፈፅሙ ይችላሉ›› ይላሉ፡፡

‹‹አንድ ተጨዋች ፌራሪ መኪና እየነዳ ለምን ይሄንን የመኪና ሞዴል እንደመረጠ ራሳችሁን ለትጠይቁ ትችላላችሁ፤ ሆኖም ይህ የእርሱ ምርጫ ነው፡፡ በሊጉ መጨረሻ ወይም በወረደ ክለብ ውስጥ የሚገኝ ተጨዋች ያንን መኪና ይዞ ከተማ ውስጥ ሊያሽከረክር አይችልም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህንን መተግበር ይከብዳቸዋል፣ እውነተኛ ተጨዋቾች በዚህ ረገድ አይቸገሩም››

ኤሪክ ካንቶናን ተቆጣጥሮ ለስኬት መብቃት የቻለ አሰልጣኝ ምንም ነገር የሚሳነው አይመስልም፣ ‹‹ከካንቶና ጋር በየዕለቱ አወራ ነበር፤ የሚገባውን ክብር ያላገኘ መሳጭ ሰው ነው፣ በትክክለኛ ክለብ ውስጥ ስለነበር የሚፈልገው የሚያበረታታው ሰው ነበር፤ በልምምድ ሜዳ ላይ ተዳክሞ እና ዓይኑ ጠብቦ ልትመለከቱት ትችላላችሁ፣ የድብርት ስሜት ተጫጭኖት ምንድነው የሆነው? እንድትሉ ያደርጋል፡፡ ሆኖም አንድ ጊዜ ልምምድ ከጀመረ በኋላ ሁሉም ነገር ያስተካክላል›› የሚል መረጃን ሰጥተው ‹‹ሮናልዶ ሌላው ታላቅ ተጨዋች ነበር፣ ግን ደግሞ ፍፁም ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋች ነው፣ ሁሉንም ነገር በአግባቡ ይፈፅማል›› በማለት ከትልልቅ ተጨዋቾች ጋር በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ አልፈው እንደሰሩ ይናገራሉ፡፡

በአሰልጣኝነት ዓለም የፈርጉሰን ቀዳሚ መርህ ሌሎችን ማመን ነው፡፡ ነገሩ በሁለቱም መንገድ ይገለፃል፤ ይህንን መርህ እንዲያብራሩ ጥያቄ ስታቀርቡላቸው ‹‹በአሰልጣኝነት ቁልፉ ነገር በተጨዋቾቹ ላይ ከፍ ያለ እምነት መጣል ነው፡፡ እምነት ስትጥል ምንም ነገር ፈልገህ ሊሆን አይገባም፤ ለአንተ በመጫወታቸው የምቾት ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ ግድ ነው፡፡ ራስህን ለእነርሱ አሳልፈህ መስጠት አለብህ፤ ሁልጊዜም ቢሆን ‹‹ይኸውላችሁ፤ እዚህ የተገኘሁት በአንድ ምክንያት ነው፡፡ ያላችሁን ምርጥ ብቃት አውጥታችሁ እንድትጠቀሙ እሻለሁኝ፣ ይህ ምርጥ ሰው እንድትሆኑ ያስችላችኋል፤ በዚህ ላይ ጥሩ ክፍያ ታገኛላችሁ እላቸዋለሁኝ፣ በማንቸስተር ዩናይትድ ይህንን ስፈፅም ነበር፡፡ ተጨዋቾቹ የራሴ ናቸው፣ ስኬታማ እንድሆን አግዘውኛል፣ ስለዚህ ለእነርሱ ታማኝ መሆን ነበረብኝ›› የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

‹‹ፀጉር አድርቅ›› ቁጣየፈርጉሰን ቁጣ አስፈሪ ነው፡፡ ኧረ እንዲያውም

የሚያስበረግግ በመሆኑ ‹‹ፀጉር አድርቅ›› ቁጣ እስከመባል ደርሷል፤ ‹‹ይሄ የማይረባ ስም ለረጅም ዓመታት አብሮኝ ኖሯል፣ ሆኖም ቡድኔ በጭራሽ በፍርሃት ስሜት ተሸብቦ አልተጫወተም፣ አንድ ተጨዋች እንኳን በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኖ አልተጫወተም፡፡ ተጨዋቾቼ በሙሉ ያላቸውን አቅም አውጥተው ሲጫወቱ ቆይተዋል፣ ሁልጊዜም ቢሆን ጀብደኛ ነበሩ፤ በቃ መልሱ ይኸው ነው›› ይላሉ፡፡

‹‹እርግጥ ነው በትክክለኛ ምክንያት ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል ወይም መበሳጨት ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ እንደሆነ መታወቅ አለበት፤ ይሄ ነገር ካልረዳነው ትርጉሙ አይገባንም፡፡ ‹‹አንድ አባባል አለን፤ ማንም በርህን አንኳኩቶ ገንዘብ አይሰጥህም፡፡ በሩን አንኳኩተህ አንድ የሆነ ነገር ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ወደ ሜዳ ውስጥ ገብተህ ጨዋታውን በማሸነፍ ገንዘብ ማግኘት አለብህ››

ሰር አሌክስ ተጨዋቾቻቸውን ለተደራራቢ ስኬት ያበቁበት የራሳቸው አካሄድ አላቸው፡፡ ‹‹ብዙዎቹን ምን ያህል ሜዳልያ አንገታቸው ላይ እንዲጠብቁ እጠይቃቸዋለሁኝ፤ (ራያን) ጊግስ ላይ ደርሳችኋል? የሚል ጥያቄ አነሳላቸዋለሁኝ፤

ስንቶቻችሁ ዘጠኝ ጊዜ አሳክታችኋል? ለ10ኛ ጊዜ ይህንን ክብር ማግኘት አትፈልጉም? እላቸዋለሁኝ›› ይላሉ፡፡

ከፈርጉሰን ስኬት በርካታ ነገሮች መማር ይቻላል፤ ጡረታ መውጣት ከክለብ ባለቤቶች፣ ሊቀመንበሮች እና ስራ አስኪያጆች ጋር በምን አይነት መልኩ ‹‹ንግግር ማድረግ›› እንዳለባቸው እንደተረዱ የገለፁት አሰልጣኝ ‹‹ዓለምን መቆጣጠር እችላለሁኝ›› የሚል አስተሳሰብ ጤናማ አይደለም፡፡ ከሜዳ ላይ ሰራተኞች እንዲሁም ከፅዳት እና ሻይ ቤት ሰራተኞች ጋር መነጋገር ተገቢ ነው›› የሚል አስተያየትን ይሰጣሉ፡፡

በስፒ፣ ጃክ ስቴይን እና ቢል ሻንክሌ ስኬታማ አሰልጣን ነበሩ፤ ‹‹ንግግርህ ግልፅ መሆን አለበት፤ ትክክለኛውን መረጃ ለተጨዋቾቹ በማስተላለፍ የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ይቻላል›› ይሄ የፈርጊ የመጨረሻ ቃል ነው፡፡

ሜሲ... ከገጽ 23 የዞረበጣም ይገርማል፡፡ በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ጥምረት

መፍጠር እንደምንችል አልጠራጠርም፡፡ ቅድሚያ የምንሰጠው ለቡድን ሥራ ነው፡፡ ኔይማር ባለው ኳሊቲ፣ የኳስ ንክኪ እና አካል ብቃት የዓለማችን ምርጡ ተጨዋች መሆን ይችላል፡፡ ሉዊስ (ሱዋሬዝም) ተመሳሳይ ነው፤ የኳስ ቁጥጥሩ፣ እይታው፣ እንቅስቃሴው፣ ደሙ ነፍሳዊ አጨዋወቱ በአጠቃላይ የማይታመን ነው፡፡ ሁላችንም የተለያዩ ግብአቶችን እናበረክታለን››

ምናልባት አሁን ባለው ሁኔታ ከሜሲ ቀድመው ሊቀመጡ የሚችሉት ፔሌ እና ዲዮጎ ማራዶና ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከ2003 ጀምሮ ለባርሴሎና መሰለፍ የጀመረው ይህ ኮከብ ዕድሜው ገና 27 መሆኑን አምኖ መቀበል ያስቸግራል፡፡

ስኬቱን ልዩ የሚያደርገው ዘመናዊው እግርኳስ በአካል ብቃቱ ረገድ ወደላቀ ምዕራፍ መሸጋገሩ፣ ታክቲካዊ ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጣቸው መሆኑ፣ ክፍተቶችን ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ እንዲሁም መከላከል ላይ ማተኮሩ ነው፡፡ ያም ቢሆን ሁሉም ነገር ለዚህ ተጨዋች ከባድ አልሆነም፡፡

በዚህ ዘመን ለፈጣሪ ተጨዋቾች ከፍተትን ማግኘት ፈታኝ ቢሆንም ሜሲ ግን ሳይቸገር የሚፈልገውን ነገር በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡ ኧረ እንዲያውም ከእያንዳንዱ ጨዋታ ስኬት አልፎ አራት ጊዜ የወርቅ ኳስ በማግኘት በግሉ ሪከርዱን በእጁ አስገብቷል፡፡

ባለፉት 11 ዓመታት ለባርሴሎና እና አርጀንቲና በጋራ 311 ጨዋታዎች ፈፅሟል፤ በስድስት ትልልቅ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ ሆኗል፡፡ በእነኚህ ጊዜያት 591 ሺ 626.4 ማይል ተጉዟል፤ በአራት የተለያዩ አህጉት 1061 ሰዓታት በርሯል፡፡ በአጠቃላይ 44 ቀናት በጉዞ አሳልፏል፡፡ በሌላ አነጋገር መሬትን 23.9 ጊዜ ዞሯል፡፡

‹‹የብራዚሉ ሮናልዶ የልጅነት አርአያዬ ነበር፣ ለባርሴሎና እና ብራዚል የማይታመን ነገር ሰርቷል፡፡ ከእርሱ የበለጠ ተሰጥኦ የታደለ አጥቂ አልተመለከትኩም፣ የሚገርም ተሰጥኦ ባለቤት ነው፤ ሁሉም ሰው ይህንን መመልከት ይችላል፣ ከምንም ነገር ተነስቶ ጎሎችን ያስቆጥራል፣ የሚያደርጋቸውን ሙከራዎች አስገራሚ ነበሩ፡፡ ከሜዳ ውጭም ቢሆን ድንቅ ሰው ነበር፤ ዚኔዲን ዚዳንንም መጥቀስ አለብኝ፤ እርሱ ሲጫወት መመልከት ያስደስተኝ ነበር፡፡ የፈረንሳውያን ጀግና ነው፤ ከሜዳ ውጭም ቢሆን በአስደናቂ ስብዕና አለው›› የሚለው ሜሲ ነው፡፡

በኤንሪኬ ዘመን ሜሲ የቦታ ለውጥ አድርጓል፡፡ ወደ ኋላ ተመልሶ በአማካይ ቦታ ላይ እስከመሰለፍ ደርሷል፤ ሜሲን ወደፊት በአማካይ ቦታ ላይ ለመጫወት እቅድ አለህ? የሚል ጥያቄን ስታነቡበት ‹‹አዎን፤ ይህ እንደሚቻል ይሰማኛል፤ በርካታ ተጨዋቾች ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ወደኋላ ተመልሰው ይጫወታሉ፤ በቀጣይ ወደ ኋላ ተመልሼ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች እንደምሆን ይሰማኛል፤ ከወዲሁ በአማካይ ቦታ በመጫወት በአማካይ ቦታ ላይ በመጫወት በርካታ ቦታዎችን አካልያለሁኝ፤ እንደ አጥቂ በፊት መስመር ላይ መጫወት ያስደስተኛል፤ በርካታ አጥቂዎች በጥልቀት ወደኋላ ተመልሰው በአማካይ ቦታ ላይ በመጫወት የእግር ኳስ ህይወታቸውን ያራዝማሉ፤ ሁልጊዜም በሩጫ ላይ የተመሰረተ አጨዋወት መከተል አይቻልም የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

ከላ ሊጋ ክለቦች ሊዮ የፔፕ ጋርዲዮላውን ባየርን ሙኒክ መመልከት ያስደስተዋል፤ ‹‹ፔፕ ሁልጊዜም አዳዲስ ነገሮችን ይሞክራል፤ ይህ ለእግርኳስ አስደሳች ነገር ነው፤ በአውሮፐ አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር በጣም ያስደስታል›› የሚል አተያየትን ሰጥቶ ‹‹እርሱን በተቃራኒ ወንበር ላይ ሲቀመጥ መመልከት የእንግዳ ስሜትን ይፈጥራል፤ በእግርኳስ ህይወቴ ስሜትን ይፈጥራል፤ በእግርኳስ ህይወቴ ላበረከተው አስተዋፅኦ በጣም ላመሰግነው እወዳለሁኝ፤ ሆኖም የእርሱን ቡድን በተቃራኒ ስገጠም የማስበው ማሸነፍን ብቻ ነው›› ይላል፡፡

የሜሲ ተሰጥኦ የዳበረው በልምምድ እንደሆነ ግልፅ ነው፤ ከባርሴሎና ተጨዋቾች መሀከል በልምምድ ሜዳ ላይ ታታሪው ማነው? የሚል ጥያቄ ስታስተከትሉበት ‹‹ይህንን

መናገር ይከብዳል፤ ሆኖም ዣቪ እና ኢንዬስታን ማስቀደም አለብኝ፤ ለረጅም ዓመታት የዚህክለብ ልብ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በልምምድ ሜዳ እንደ እነርሱ አይነት ታታሪ ተጨዋቾች አልተመለከትኩም›› በማለት ይመልሳል፡፡

ኖቤል... ከገጽ 22 የዞረ መዝናኛ 38 ቱሪስቶች የተገደሉበት የሽብር ጥቃት

ይህንኑ ያመለክታል። ይሁን እንጂ ቱኒዚያ የጀመረችው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመመሥረት ጥረቷ ከየአቅጣቸው አድናቆትን አትርፎላታል።

የኖቤል የሰላም ሽልማት የሚሰጠው እአአ ከ1833 እስከ 1896 በኖረው ስዊድናዊ ሳይንቲስትና ባለሀብት አልፍረድ ኖቤል ባደረገው ኑዛዜ መሠረት ነው። አልፍረድ ኖቤል ከሀብቱ ከፍተኛውን ድርሻ ለሽልማት እንዲውል የተናዘዘው። ከ355 የምርምር ግኝቶቹ መካከል አንዱና ዋነኛው ዳይናማይት /ድማሚት/ በጦርነት ወቅት ሕዝብን ለጅምላ እልቂት ለሚዳርግ ተግባር መዋሉ ስለአሳዘነው እንደሆነ ታውቋል። በአንድ ወቅት ሉድቪግ የተባለ ወንድሙ ሲሞት አንድ የፈረንሳይ ጋዜጣ ሟቹ አልፍረድ ኖቤል መስሎት “የሞት ነጋዴው ሞተ” (ዘመርቻንት-አፍ ዴዝ አዝዴድ) ብሎ ያወጣው ጽሑፍ ስሜቱን ስለነካው ለተጠቀሰው ኑዛዜ ሳያደፋፍረው አልቀረም፡፡

አልፍረድ ኖቤል ባደረገው ኑዛዜ መሠረት በስሙ በዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ካፒታል በተቋቋመ ፋውንዴሽን ከሚሰጣቸው ሽልማቶች መካከል የኖቤል ሰላም ሽልማት ብቻ በኖሮዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን የቀሩት የሚሰጡት በአገሩ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶኮልም ውስጥ ነው።

በኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ምርጫ የኖቤል የሰላም ሽልማት የሚሰጠው በዋነኛነት የሰውን ልጅ ጦርነት ከሚያስከትለው መከራ ወይም ችግር ከመጠበቅ ጀምሮ ጨቋኝ ሥርዓቶችንና ዘረኝነትን በመዋጋት ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር የላቀ ተግባር ለአከናወኑ ሰዎችና ድርጅቶች እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሠረት የጦርነትን አስከፊ ሁኔታ ተገንዝቦ የዓለም ቀይ መስቀል ማህበርን የመሠረተው ሄንሪ ዱና እ አ አ በ1910 የመጀመሪያው የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሲሆን፤ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ የዓለም ማህበር (ሊግ- ኦፍ ኔሽንስ) እንዲመሠረት ከፍተኛ ድርሻ ያበረከቱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ውድሮው ዊልሰንም ይህንኑ ሽልማት ለማግኘት ሁለተኛ ሆነዋል። በኋላም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ አካላቱና ኮፊ አናንን ጨምሮ ጥቂት የድርጅቱ ዋና ጸሐፊዎች የሽልማቱ አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል።

እንደአራቱ የቱኒዚያ ሕዝባዊ ድርጊቶች /ናሽናል ዲያሎግ ኳርቴት ሁሉ በርካታ አፍሪካውያን የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት የደቡብ አፍሪካውን አፓርታይድ የዘርና ቀለም ልዩነት ሥርዓት ለማስወገድ ከጅምሩ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉት የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ኤኤንሲ) የቀድሞ ፕሬዚዳንት አልበርት ሊቱሊ እ አ አ በ1960 የኖቤልን ሰላም ሽልማት አግኝተዋል። እ አ አ በ1978 ደግሞ ለመካከለ ኛው ምሥራቅ ችግር ሰላማዊ መፍትሔ ለመፈ ለግ ባደረጉት ጥረት ዕውቅና ያተረፉት የግብፅ ፕሬዚዳንት አንዋር ሳደት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜናሂም ቤጊን ጋር ሽልማቱን አግኝተዋል።

እ አ አ በ1984 በጠንካራ ፀረ- አፓር ታይድ አቋማቸው የታወቁት የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ አንግሊካን ቤተክርስቲያን ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ሽልማቱን ያገኙ ሲሆን እ አአ በ1993 ደግሞ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ሽልማቱን አግኝተዋል።

እአአ በ2001 ደግሞ ጋናዊው የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን ሽልማቱን ከድርጅቱ ጋር አሸንፈዋል። የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት እንቅስቃሴ /ግሪን ቤልት ሙቭመንት/ አራማጇ ኬንያዊት ዋንጋሪ ማታይ ሽልማቱን እአአ በ2004 ያገኙ ሲሆን እአአ በ2005 ደግሞ ግብፃዊው የኢንተርናሽናል አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሞሐመድ አልባራዳይ የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል።

በመጨረሻም እ አ አ በ2011 የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኢሌን ጆንልን ሰርሊፍና ሊማህ ግቦዊ ከተባለችው የአገራቸው የሰላም ንቅናቄ አራማጅና ተዋከል ካርማን ከተባለችው የየመን የሰላም ታጋይ ጋር የኖቤል የሰላም ሽልማቱን አግኝተዋል።

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 23

ተኩስ በ$25 ብቻ

በቅርቡ ከሃገር ቤት መጥታ በሳሎናችን ሥራ የጀመረችው ስታይሊስት በከተማው በአዳዲስ የሹሩባዋ ዲዛይኗ

ብዙ እየተወራላት ነው፤ መጥተው ይጎብኟት

ማርሻል... ከገጽ 21 የዞረግጥሚያ ሁን ማታ ያስቆጠራት ሌላኛዋ ጎል በሜዳ

ላይ የነበሩት ሁሉም የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾችን ባሳተፈ መልኩ በ45 ፓሶች በሜዳ ላይ የነበሩትን ሁሉንም የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾችን ባሳተፈ መልኩ ቢሆንም የሁሉም ታዋቂ የፉትቦል ተንታኞችን ልዩ ትኩረት የሳበው ግን አንቶኒ ማርሻል የወጣበት ውድ ዋጋ ምንም አይነት ተፅዕኖ ሳይፈጥርበትና በማንቸስተር ዩናይትድ የፊት አጥቂ መስመር መሰለፍ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ጫናን በመቋቋም ከወዲሁ ሶስት የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን ከመረብ ለማሳረፍ መቻሉ ነው፡፡

በማርሻል ዙሪያ አስተያየታቸውን ከሰነዘሩት የፉትቦል ተንታኞች ውስጥ የቀድሞው የሊቨርፑል ዝነኛ ግርሃም ሶውነስ ‹‹ሰፊ ልምድን ከማጣቱ በስተቀር ሁሉንም አይነት ብቃቶችን አሟልቶ የያዘ አስገራሚ ወጣት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በተለይም ከፍተኛ ፍጥነቱና እውነተኛ የሆነ የሰውነት ጥንካሬን መላበሱ አስገራሚ ሆኖብኛል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ለማንቸስተር ዩናይትድ በተሰለፈባቸው ሁለት ግጥሚያዎች ያደረጋቸው ሶስቱንም አላማቸውን የጠበቁ ጎል የማስቆጠር ሙከራዎችን ከመረብ ማሳረፉ ያማረ የጎል አጨራረስ ብቃትን መላበሱን የሚያሳይ ነው›› በማለት ፈረንሳዊው ወጣት አጥቂን አድንቆታል፡፡

የማንችስተር ዩናይትዱ የቀድሞ ዝነኛ አምበል ጋሪ ኔቭል በበኩሉ ‹‹ሉዊ ቫንሃል ለአንቶኒ ማርሻል ግዥ ውድ ዋጋ መክፈላቸው አስገራሚ ሆኖብኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም በአንድ ሲዝን ሌላው ቀርቶ እስከ 15 የሚደርስ ጎልን ማስቆጠሩ አጠራጣሪ ሆኖብኝ ነበር፡፡ በተግባር ያየነው

ግን ማርሻል ማንችስተር ዩናይትድን ብዛት ያላቸው ጎሎችን ለማሳፈስ የሚያስችለው ትክክለኛው የአጥቂ መስመር ተጨዋች መሆኑን ነው፡፡ ለዚህ አባባሌ አንዱ ምክንያት የሆነኝ ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን በተጋነነ መልኩ የመግለፅ ባህል የሌለው መሆኑ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ ባህል ያላቸው ተጨዋቾች ብዙውን ጊዜ የራስ የመተማመን መንፈሳቸው እጅግ ያማረ ሲሆን መታየቱ የተለመደ ነው›› የሚል አስተያየቱን በመሰንዘር ሉዊ ቫንሃል ማርሻልን በዝውውር መስኮቱ መጨረሻ ቀን የገዙበት ተግባራቸውን አድንቆላቸዋል፡፡

የአንቶኒዮ ማርሻል የእስካሁኑ የሲዝኑ የፕሪሚየር ሊግ የቁጥር መረጃዎች

80- በሜዳ ላይ የቆየባቸው የፕሪሚየር ሊግ ደቂቃዎች4- ያደረጋቸው አጠቃላይ ጎል የማስቆጠር ሙከራዎች3- አላማቸውን ያገኙለት የጎል ሙከራዎችና

ያስቆጠራቸው የሊጉ ጎሎችአንቶኒ ማርቫል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ

በተሰለፈባቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት የሊጉ ግጥሚያዎች በእያንዳንዱ ላይ ጎልን በማስቆጠር ታሪክ ሶስተኛው የማን ዩናይትድ ተጨዋች ሆኗል፡፡ ሌሎቹ ሉዊስ ሳህና ፍሬዲሪኮ ሜኬዳ ናቸው፡፡

ማርሻል በእስካኑ ሲዝን ያስቆጠራቸው 3 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎች የቼልሲዎቹ ኤደን ሃዛርድ፣ ዲያጎ ኮስታና ፔድሮ በድምሩ በስማቸው ካስመዘገቧቸው ጎሎች ብዛት ጋር እኩል ናቸው፡፡

ሜሲ... ከገጽ 13 የዞረባርሴሎና 1-1 ተለያይቶ በመጨረሻም ዋንጫውን

ተነጥቋል፤ በቻምፒዮንስ ሊጉ በዲያጎ ሲሞኒ ቡድን ሩብ ፍፃሜ ላይ ሽንፈትን አስተናግዶ ረጅም ርቀት መጓዝ አልቻለም፣ በዓለም ዋንጫው ደግሞ አርጀንቲና በፍፃሜው ጨዋታ በጀርመን 1-0 ተሸንፋ ከ1986 በኋላ ይህንን ዋንጫ ለማንሳት የነበራት ዕድል ሳይሳካ ሲቀር ሊዮ በግሉ ከፍ ያለ ትችት አስተናግዷል፡፡

2015 ዓመት ግን የእርሱ ነበር፡፡ በግልም ሆነ እንደ ቡድን ከፍ ያለ ስኬትን አስመዝግቧል፡፡ ‹‹በዓለም ዋንጫ ለፍጻሜ ቀርቦ ሽንፈትን ማስተናገድ ጥሩ የሆነ ስሜትን አይፈጥርም፣ ለአገሬ ታላቁን ዋንጫ ማስገኘት እፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋች ከመጥፎ አጋጣሚ በማገገም ወደፊት መጓዝ ተገቢ ነው›› የሚል አስተያየትን ሰጥቶ ‹‹እንደ እግርኳስ ተጨዋች ሽንፈትን ካስተናገድክ በኋላ በቀጣይ የሚገጥምህን ፈተና በብቃት በመወጣት መጥፎውን አጋጣሚ መርሳት ምርጥ አማራጭ ነው፤ የዓለም ዋንጫው መጥፎ አጋጣሚ ጥሩ ስሜት እንደማይፈጥር ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን ብስጭቱ ለድል ያነሳሳይል፡፡

ሊዮ የተናገረውን ነገር በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሚገባ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ የላ ሊጋውን ዋንጫ ለማንሳት ባልተቸገረው ባርሴሎና ሜሲ በርካታ ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ለማንሳት አልተቸገረም፡፡ ከምንም በላይ በበርሊን ጁቬንቱስን 3-1 አሸንፎ ሻምፒዮን ሆኗል፤ በእነኚህ ድሎች የአጭሩ ኮከብ አስተዋፅኦ ከፍ ያለ ነበር፡፡

ለባርሴሎና ያለፈው ዓመት አስደሳች ነበር፤ ለሁለተኛ ጊዜ የሶስትዮሽ ዋንጫ ባለቤት በመሆን በስፔን ብቸኛው

ክለብ ሆኗል፡፡ በ2009 በፔፕ ጋርዲዮላ እንዲሁም ባለፈው ዓመት በሉዊስ ኤንሪኪ ይህንን ስኬት ሊጎናፀፍ ሊዮ የሁለቱም ቡድን መሪ ተዋናይ ነበር፡፡

እርግጥ ነው በባርሴሎና ያለፈው ዓመት ታሪካዊ ስኬት አርጀንቲናዊውን ብቻ አጉልቶ መጥቀስ ሌሎቹን መናቅ ይሆናል፤ ሉዊስ ሱዋሬዝ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ታላቅነቱን አስመስክሯል፡፡ በቻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ ጭንቀት ላይ ለነበረው የካታላኑ ክለብ ኳስ እና መረብን አገናኝቶ ቡድኑን ከጭንቀት መገላገሉ እንዴት ይረሳል? ሶስተኛውን ጎል አግብቶ የቡድኑን አሸናፊነት ያረጋገጠው ኔይማርስ እንዴት ይዘነጋል?

ሶስቱ አጥቂዎች ባለፈው ዓመት በሁሉም ውድድሮች በጋራ 119 ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡ ይህ አስገራሚ ሪከርድ ነው፤ በላ ሊጋው 81 ጎሎችን አግብተዋል፡፡ ባየርን ሙኒክ በተመሳሳይ ወቅት በቡድን ደስ ሊጋው 80 ጎሎችን አግብቷል፤ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ቼልሲ 73 እንዲሁም የሴሪ አው አሸናፊ ጄቬንቱስ 70 ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

‹‹በጣም ዕድለኛ ነኝ›› ይላል- ሊዮ፣ ባለፈው ዓመትም ከታላቅ አጥቂዎች ጎን ተሰልፎ ተጫውቻለሁኝ- ከሮናልዲንሆ ጋር ድንቅ የሆነ መግባባት ነበረኝ፡፡ ከእርሱ በኋላ ደግሞ ከሳሙኤል ኤቶ፣ ቲዮሪ ሆንሪ፣ ፔድሮ፣ ዴቪድ ቪያ እና አሌክሲስ (ሳንቼዝ) ጎል ተሰልፌ በመጫወት አስደሳች ጊዜያትን አሳልፌያለሁኝ፡፡

‹‹ከምንም በላይ ከኔይማር እና ሱዋሬዝ ጋር የፈጠርኩት ጥምረት የተለየ ነው፤ ሁለቱ አጥቂዎች የብቃታቸው ጫፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጋራ የተጫወትነው ለአንድ ዓመት ብቻ ቢሆንም ጥምረታችን (ሜሲ.. ወደ ገጽ 22 የዞረ)

October 2015 I volume VII I No. 79 ጥቅምት 2008I ቅጽ VII I ቁጥር. 79 Page ገጽ 24

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት

ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር

ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

እርሶ የሺ እንጀራን ካልቀመሱ ደንበኞቻችንን ለምን እንደሚመገቡት ይጠይቋቸው፤

የኛ የጥራት ምስክሮቻችን ደንበኞቻችን ናቸው

እሬሳ... ከገጽ 20 የዞረ ህዝቡ ሃይማኖታዊ ጉዞ የሚያደርግባቸው Sadeettan

Tulluu Waaqaa (ስምንቱ የአምላክ ተራራዎች) የሚባሉት የሸዋ ከፍተኛ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም “ቱሉ ጩቃላ”፣ “ቱሉ ኤረር”፣ “ቱሉ ፉሪ”፣ “ቱሉ ገላን”፣ “ቱሉ ዋቶ ዳለቻ”፣ “ቱሉ ፎየታ”፣ “ቱሉ ወጨጫ” እና “ቱሉ ኤግዱ” የሚባሉት ናቸው፡፡ የህዝቡ አባ ገዳዎች መቀመጫ የሆኑት የአዋሽ መልካ በሎ እና የገላን ደንጎራ መስኮች የሚገኙትም በዚሁ ወረዳ ነው፡፡ እንግዲህ የቱለማ ኦሮሞ የኢሬቻን በዓል የሚያከብርበት “ሆራ አርሰዲ” ያለው እነዚህ የፖለቲካና የሃይማኖት ማዕከላት ባሉበት መሬት ላይ ነው፡፡

እላይ ከጠቀስናቸው ሶስት ነገዶች በተጨማሪ ሌሎች የኦሮሞ ነገዶችም በዓሉን ያከብሩታል፡፡ ይሁን እንጂ ከኦሮሞ ነገዶች መካከል ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላቸው የአርሲ እና የመጫ ነገዶች በዓሉን በአንድ ስፍራ የሚያከብሩት አይመስለኝም (መረጃው ያላችሁ አካፍሉን)፡፡ታዲያ ከቱለማ በስተቀር ሁሉም ኦሮሞዎች በዓሉን “ኢሬሳ” እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡ ቱለማ ግን “ኢሬቻ” ነው የሚለው፡፡ ይህ ልዩነት ግን ሌላ ሚስጢር የለውም፡፡ በሌሎች ዘዬዎች በምንናገርበት ጊዜ በ“ሳ” ድምጽ የምናሳርገውን ቃል በቱለማ ዘዬ “ቻ” እያሉ መናገር የተለመደ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ

“ለሜሳ”፣ “ከሌሳ”፣ “በሬሳ”፣ “ሙርቴሳ” የመሳሰሉት ቃላት በቱለማ ዘዬ “ለሜቻ”፣ “በሬቻ”፣ “ሙርቴቻ”፣ “ከሌቻ” በሚል ድምጸት ነው የሚነገሩት፡፡

*******ለመሆኑ የኢሬሳ በዓል የሚከበረው ለምንድነው?……የኦሮሞ ሽማግሌዎች ይህንን ጥያቄ ሲመልሱን

“የኢሬሳ በዓል የሚከበረው ለዋቃ ምስጋና ለማቅረብ ነው” ይላሉ፡፡ መነሻውንም ሲያስረዱ “ዋቃ ክረምቱን በሰላም ስላሳለፈልንና ከሰማይ ባዘነበው ውሃ መልካም ፍሬ ስለሰጠን ያለ ክፍያ በቸርነቱ ለሚንከባከበን አምላክ ምስጋና ማቅረብ የተገባ በመሆኑ ነው” ይሉናል፡፡ “ዋቃ” ፍጥረተ ዓለምን ያስገኘውና ሂደቱንም የሚያስተናብረው አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ኦሮሞ ችግር ሲገጥመው አቤቱታውን የሚያቀርበው “ለዋቃ” ነው፡፡ በደስታ ጊዜም ተሰብስቦ “ዋቃ”ን ያመሰግናል፡፡ ኢሬሳ የዚህ ዓይነቱ የምስጋና ማቅረቢያ በዓል ነው፡፡

ኢሬሳ በክረምቱ የወንዞች ሙላት ምክንያት ተቆራርጠው የነበሩ ቤተ ዘመዶችና ልዩ ልዩ ጎሳዎች የሚገናኙበት በዓል ነው፡፡ በመሆኑም በበዓሉ የተገኙት ሁሉ ይቅር ይባባሉ፡፡ ገንዘባቸውን ለሌሎች ያበደሩ ሰዎችም በሌሎች ላይ ያላቸውን እዳ ይሰርዙላቸዋል፡

፡ በዓሉ የሚከበርበት ቀን የዓመቱ መጀመሪያ ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ዓመቱ የደስታና የብልጽግና ይሆን ዘንድ የመልካም ምኞት መግለጫዎች ይጎርፋሉ፡፡ የህዝቡ መንፈሳዊ መሪ የሆነው “ቃሉ” ለህዝቡና ለሀገሩ “ኤባ” (ምርቃት) ያደርጋል፡፡ ታዲያ ማንኛውም ሰው ወደ በዓሉ ስፍራ ሲሄድ አለባበሱን ማሳመር ይጠበቅበታል፡፡ በእጁም የወይራ ቀንበጥ፣ እርጥብ ሳር አሊያም የአደይ አበባን ይይዛል፡፡

በነገራችን ላይ በጥንቱ ዘመን ከዚሁ የኢሬሳ በዓል ትይዩ ሌላ በዓል ይከበር እንደነበርም ልብ በሉ፡፡ ይህኛው በዓል የሚከበረው የክረምቱ ዝናብ ሊጀምር በሚያስገመግምበት የሰኔ ወር መግቢያ ላይ ነው፡፡ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራዎች ደግሞ ተራሮችና ኮረብታዎች ናቸው፡፡ ይህ በዓል “መጪው ክረምት መልካም የዝናብና የአዝመራ ወቅት እንዲሆንልን ለዋቃ ጸሎት ማድረስ” በሚል መንፈስ ነው የሚከበረው፡፡ በዓሉ በምዕራብ ሀረርጌው የኢቱ ኦሮሞ ዘንድ “ደራራ” እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ የቱለማ ኦሮሞ ደግሞ “ኢሬቻ ቱሉ” (የተራራ ላይ ኢሬሳ) ይለዋል፡፡ በዓሉ በሌሎች ኦሮሞዎች የሚጠራበትን ስም ግን አላውቅም፡፡ በደራራ ጊዜ የሚፈለገው ትልቁ ነገር “ጸሎት” (Kadhaa) ማብዛት ነው፡፡ መዝፈንና መጨፈር አይፈቀድም፡፡ በኢሬሳ

ጊዜ የሚፈለገው ግን “ምስጋና” (Galata) ማብዛት እና ደስታን ማብሰር ነው፡፡ በዚህኛው በዓል ዘፈንና ጭፈራ ይፈቀዳል፡፡

በሁለቱም በዓላት የዋቃ ስም ይለመናል፡፡ ለዋቃ መስዋእት ይቀርባል፡፡ ለመስዋእት የሚታረደው ጥቁር በሬ አሊያም ጥቁር ፍየል ነው፡፡ ይህም በጣም መሰረታዊ ነገር መሆኑን ልብ በሉ፡፡ በበሬው ቆዳ ላይ ቀይ ወይንም ነጭ ነጥብ በጭራሽ መኖር የለበትም፡፡ የበሬው ገላ ከጭረትና ከእከክ የነጻ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም በሬው በደንብ የበላና የደለበ ሊሆን ይገባል፡፡

አንዳንድ ሰዎች “የበሬው ቆዳ ጥቁር መሆን አለበት” የሚለውን አስተርዮ እንደ ባዕድ አምልኮ እንደሚያዩት ይታወቃል፡፡ ነገሩ ግን እንዲያ አይደለም፡፡ የበሬው ቆዳ ጥቁር መሆኑ የሚፈለገው በዋቄፈንና እምነት መሰረት “ሰዎችን የፈጠረውና በሰዎች የሚመለከው አምላክ ጥቁር ነው” ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ ይህም “አምላክ በመልኩ ጥቁር ነው” ማለት ሳይሆን “ዋቃ በስራው እንጂ በአካሉም ሆነ በሚስጢሩ ለሰው ልጅ በጭራሽ አይታወቅም” ለማለት ነው፡፡ በመሆኑም የጥንቱ ኦሮሞዎች ዋቃን ሲለማመኑት እንዲህ ነበር የሚሉት፡፡

(እሬሳ... ወደ ገጽ 17 የዞረ)